[{"id":1,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)::"},{"id":2,"translation":"2. ምስጋና ሁሉ ለዓለማቱ ጌታ ለአሏህ ይገባው።"},{"id":3,"translation":"3. እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ ለሆነው::"},{"id":4,"translation":"4. የፍርዱ ቀን ባለቤት ለሆነው (ለአላህ ብቻ ይገባው)::"},{"id":5,"translation":"5. (ሙስሊሞች ሆይ! ጌታችሁን) አንተን ብቻ እንገዛለን:: ካንተም ብቻ እርዳታን እንለምናለን (በሉ)።"},{"id":6,"translation":"6. ቀጥተኛውን መንገድ ምራን::"},{"id":7,"translation":"7. የእነዚያን ለእነርሱ በጎ የዋልክላቸውን፤ በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን በሉ)::"}]},{"id":2,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አሊፍ ፤ ላም፤ ሚም፤"},{"id":2,"translation":"2. ይህ መጽሐፍ (ቁርኣን) (ከአላህ የተወረደ ለመሆኑ) ምንም ጥርጥር የለበትም:: አላህን ለሚፈሩም ሁሉ መመሪያ ነው::"},{"id":3,"translation":"3. ለእነዚያ በሩቁ ነገር ለሚያምኑት፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው ለሚሰግዱት፤ ከሰጠናቸዉ ሲሳይም ለሚለግሱ።"},{"id":4,"translation":"4. ለእነዚያም ወደ አንተ በተወረደው መጽሐፍና ካንተ በፊትም በተወረዱት መጽሐፍት ሁሉ ለሚያምኑ፤ በመጨረሻው ቀን መኖርም ለሚያረጋግጡ ሰዎች ሁሉ (መመሪያ ነው)፡፡"},{"id":5,"translation":"5. እነዚያ (የተጠቀሱትን ባህሪያት የሚላበሱ ሰዎች ሁሉ) በጌታቸው መመሪያ ላይ በትክክል የሚጓዙ ናቸው:: ፍላጎታቸውን ያገኙትም እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡"},{"id":6,"translation":"6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ (በአላህ ፤ በአንተ መልዕክተኛነትና በአላህ አናቅጽ) የካዱት ሰዎች ብታስጠነቅቃቸዉም ባታስጠነቅቃቸዉም ለእነርሱ ሁሉም እኩል ነው:: (ምንም ለውጥ አያመጣም) አያምኑምና፡፡"},{"id":7,"translation":"7. አላህ እነዚያ እውነትን እያወቁ የካዱ ሰዎችን በልቦቻቸው እና በመስሚያቸው ላይ አትሞባቸዋል:: በዓይኖቻቸው ላይም መሸፈኛ አለ:: ለእነርሱም በጀሀነም ውስጥ ከባድ ቅጣት አለባቸው፡፡"},{"id":8,"translation":"8. ከሰዎች መካከል ለይስሙላ «በአላህና በመጨረሻው ቀን አምነናል» የሚሉ ክፍሎች አሉ:: እነርሱ ግን (የሚዋሹ እንጂ) ትክክለኛ አማኞች አይደሉም።"},{"id":9,"translation":"9. አላህንና እነዚያን በትክክል በአላህ ያመኑትን ሰዎች ያታልላሉ:: ነገር ግን በዚህ ተግባራቸው ነፍሶቻቸውን እንጂ ሌላን ማንንም አያታልሉም:: እነርሱ ግን ይህ መሆኑን በትክክል አያውቁም፡፡"},{"id":10,"translation":"10. በልቦቻቸው ውስጥ (የንፍቅና) በሽታ ሰርጿል:: አላህም ሌላን በሽታ ጨመረባቸው:: ለእነርሱም ይዋሹ በነበሩበት ምክንያት አሳማሚ ቅጣት አለባቸው፡፡"},{"id":11,"translation":"11. በምድር ላይ ሁከትን አትፍጠሩ በተባሉ ጊዜ እኛ እኮ አስተካካዮች ነን ይላሉ፡፡"},{"id":12,"translation":"12. (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ:: አጥፊዎች እነርሱ ብቻ ናቸው:: ግን እነርሱ ይህንን አይገነዘቡም፡፡"},{"id":13,"translation":"13, «ሰዎቹ እንዳመኑት ሁሉ እናንተም እመኑ» በተባሉ ጊዜ «ቂሎቹ እንዳመኑት እናምናለንን?» ይላሉ። (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተዉሉ። ቂሎቹ እነርሱ ብቻ ናቸው:: እነርሱ ግን ይህንን አያውቁም።"},{"id":14,"translation":"14. ከእነዚያ በአላህ በትክክል ካመኑት ሰዎች ጋር በተገናኙ ጊዜ «እኛም (ልክ እንደ እናንተው) አምነናል» ይላሉ። ወደ ሰይጣኖቻቸው ባገለሉ ጊዜ ደግሞ «እኛ እኮ ከእናንተ ጋር ነን፤ እኛ በእነርሱ ተሳላቂዎች ብቻ ነን» ይላሉ።"},{"id":15,"translation":"15. አላህ በእነርሱ ይሳለቅባቸዋል:: በአመጻቸዉም ውስጥ የሚዋልሉ ሲሆኑ ያቆያቸዋል፡፡"},{"id":16,"translation":"16. እነዚህ እነዚያ ስህተትን በቅንነት የገዙ (የለወጡ) ሰዎች ናቸው:: እናም ንግዳቸው ትርፋማ አይደለም:: ቅኑን መንገድም አልተከተሉም፡፡"},{"id":17,"translation":"17. የእነርሱ ንፍቅና ምሳሌ ልክ እንደዚያ እሳትን እንዳነደደና ከዚያ በዙሪያው ያለውን ሁሉ ባበራችለት ጊዜ አላህ ብርሃናቸውን እንደወሰደባቸው እና በጨለማዎች ውስጥ የማያዩ ሆነው እንደተዋቸው ብጤ ነው፡፡"},{"id":18,"translation":"18. እነርሱ (ሓቅን የማይሰሙ) ደንቆሮዎች፤ (ሓቅን የማይናገሩ) ዲዳዎች፤ (ሓቅን የማያዩ) እውሮች ናቸው:: ስለዚህ እነርሱ (ከስህተት) አይመለሱም።"},{"id":19,"translation":"19. ወይም (ምሳሌያቸው) ከሰማይ እንደወረደ ዝናብ (ባለቤቶች) ነው:: በእርሱ (በደመናው) ውስጥ ጨለማዎች፤ ነጎድጓድና ብልጭታ ያሉበት ሲሆን ከመብረቆቹ ሊመጣ ከሚችል ጥቃት ሞትን በመፍራት ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ እንደሚያደርጉ ሰዎች ቢጤ ነው:: አላህ ከሓዲያንን (በእውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡"},{"id":20,"translation":"20 ብልጭታው ዓይኖቻቸውን ሊነጥቅ ይቀርባል:: ለእነርሱ ባበራላቸው ቁጥር በውስጡ ይሄዳሉ:: በእነርሱም ላይ ባጨለመባቸው ጊዜ ደግሞ ይቆማሉ:: አላህ በፈለገ ኖሮ መስሚያዎቻቸውንና ማያዎቻቸውን ይወስድባቸው ነበር:: አላህ በነገሮች ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::"},{"id":21,"translation":"21. እናንተ ሰዎች ሆይ! ያን እናንተንና እነዚያን ከናንተ በፊት የነበሩትን የፈጠረውን ጌታችሁን (አላህን) በብቸኝነት ተገዙት:: ቅጣትን ልትጠነቀቁ ዘንድ፡፡"},{"id":22,"translation":"22. እርሱ (አላህ) ያ ለእናንተ ምድርን ምንጣፍ፤ ሰማይን ጣራ ያደረገ ጌታ ነው::ከሰማይ ዳመና ውሃን ያወረደና ከዚያ በውሃው ከፍሬዎች ሁሉ ለእናንተ ሲሳይን ያወጣላችሁ ነው:: እናም (ብቸኛ ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትሆኑ ለአላህ (በአምልኮ) አጋሮችን አታድርጉ፡፡"},{"id":23,"translation":"23. (እናንተ ሰዎች ሆይ!) በአገልጋያችን (በሙሐመድ) ላይ ባወረድነው (ቁርኣን) በመጠራጠር ላይ ከሆናችሁም ከእርሱ ጋር ሊወዳደር የሚችል አንድ ምዕራፍ እንኳን እስቲ አምጡ:: እውነተኞች እንደሆናችሁ ከአላህ ሌላ ረዳቶቻችሁንም ሁሉ ጥሩ፡፡"},{"id":24,"translation":"24. (ይህንን) ባትሰሩ ግን በርግጥም አትሰሩትምና (አትፈጽሙትምና) ከዚያች መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች ከሆነው ከገሀነም እሳት ራሳችሁን ጠብቁ:: ለከሓዲያን ሁሉ ተደግሳለችና፡፡"},{"id":25,"translation":"25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በትክክል በአላህ ያመኑትንና መልካም ተግባራትን የሰሩትን ሰዎች ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መሆኑን አብስራቸው:: በእርሷም ፍራፍሬ በተለገሱ ቁጥር (ፍሬዎቿ ስለሚመሳሰሉ) «ይህማ ያ ከአሁን በፊት የተመገብነው ነው።» ይላሉ:: (እርሱ ተመሳሳይ ሆኖ ይሰጣቸዋል) ለእነርሱም በውስጧ ንጹህ ሚስቶች አሏቸው:: እነርሱም በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው::"},{"id":26,"translation":"26. አላህ ማንኛውንም ነገር ትንኝም ትሁን ከሷም በላይ የሆነን ነገር ምሳሌ ከማድረግ አያፍርም። እነዚያማ ያመኑት ምሳሌው ከጌታቸው የተነገረ እውነት መሆኑን ያውቃሉ:: እነዚያ የካዱ ግን «አላህ በዚህ አባባል ምንን ምሳሌ ፈልጎበት ነው?» ይላሉ:: አላህ በምሳሌው ብዙዎችን ያሳስታል:: በእርሱም ብዙዎችን ያቀናል:: በእርሱም አመጸኞችን እንጂ ሌላን አያሳስትም::"},{"id":27,"translation":"27. እነዚያ የአላህን ቃል ኪዳን ከጠበቀ በኃላ የሚያፈርሱ፤ እንዲቀጠልም አላህ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ፤ በምድር ላይ ሁከት የሚፈጥሩ ከሳሪዎች እነርሱ ብቻ ናቸው::"},{"id":28,"translation":"28. (እናንተ ከሓዲያን ሆይ!) ሙታን የነበራችሁትን ሕያው ያደረጋችሁ፤ ከዚያም የሚገድላችሁ፤ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁና ከዚያም ወደ እርሱ የምትመለሱ ስትሆኑ እንዴት በአላህ ትክዳላችሁ!"},{"id":29,"translation":"29. አላህ ያ በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ለእናንተ ጥቅም ሲል የፈጠረ ጌታ ነው:: ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበና ሰባት ሰማያት አደረጋቸው:: እርሱ ሁሉን ነገር አዋቂ ነውና፡፡"},{"id":30,"translation":"30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ለመላዕክት «እኔ በምድር ላይ (ምትክ) ወኪል ላደርግ ነው።» ባለ ጊዜ (የሆነውን ለህዝቦችህ አስታውስ)። «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ፤ የምናሞግስህ ስንሆን በምድር ውስጥ የሚያጠፉትንና ደሞችንም የሚያፈሱትን ታደርጋለህን?» አሉ:: አላህም «እኔ እናንተ የማታውቁትን ነገር ሁሉ አውቃለሁ» አላቸው።"},{"id":31,"translation":"31. ለአደምም ስሞችን ሁሉ አስተማረው:: ከዚያም በመላዕክት ላይ (ተሰያሚዎቹን) አቀረባቸው። «እውነተኞች ከሆናችሁ የእነዚህን ተሰያሚዎች መጠሪያ ንገሩኝ?» አላቸው።"},{"id":32,"translation":"32. እነርሱም «ጥራት ይገባህ አንተ ካስተማርከን ነገር በስተቀር እኛ ምንም እውቀት የለንም:: አንተ ብቸኛው ጥበበኛና አዋቂው ነህና›› አሉ፡፡"},{"id":33,"translation":"33. አላህም «አደም ሆይ! ስሞቻቸውን ንገራቸው።» አለው። ከዚያም ስሞቻቸውን በነገራቸው ጊዜ «እኔ የሰማያትንና የምድርን ሩቅ ምስጢር አውቃለሁ። የምትገልጹትንና ያንንም ትደብቁት የነበራችሁትን ሁሉ አውቃለሁ አላልኳችሁምን?» አላቸው።"},{"id":34,"translation":"34. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላዕክትን «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ የሆነውን አስታውስ። ከዲያብሎስ በቀር መላዕክት ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ። እርሱማ እምቢ አለ። ኮራም። ከከሓዲያንም ሆነ።"},{"id":35,"translation":"35. «አደም ሆይ! አንተና ሚስትህ በገነት ውስጥ ተቀመጡ:: በእርሷም ዉስጥ በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ:: ግን ከበደለኞች ትሆናላችሁና ይህችን ዛፍ አትቅረቡ።» አልናቸው።"},{"id":36,"translation":"36. ሰይጣንም ከእርሷ አሳሳታቸው። ከነበሩበትም ገነት አወጣቸው። «ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲሆን ሁላችሁም (ወደ ምድር) ውረዱ። ለእናንተም በምድር ላይ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ።» አልናቸው።"},{"id":37,"translation":"37. ከዚያም አደም ከጌታው የመታረቂያ ቃል ተማረ:: ጌታዉም ተማጽኖውን ተቀበለው:: አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና፡፡"},{"id":38,"translation":"38. «ሁላችሁም (አደም፣ ሐዋና ሰይጣን) በአንድ ሆናችሁ ከገነት ወደ (ምድር) ውረዱ አልናቸውም። ከዚያም ከእኔ የሆነ መመሪያ ቢመጣላችሁ መመሪያዬን የተከተሉ በእነርሱ ላይ ስጋትም ትካዜም የለባቸውም።"},{"id":39,"translation":"39. «እነዚያም በመልዕክተኞቻችን የካዱና በራዕያችን ያስተባበሉ ሁሉ ግን እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ የእሳት (ገሀነም) ጓዶች ናቸው።» (አልናቸው።)"},{"id":40,"translation":"40. እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ያችን በእናንተ ላይ የለገስኳትን ጸጋዬን አስታውሱ:: ቃል ኪዳኔንም ሙሉ:: እኔም ቃልኪዳናችሁን እሞላላችኋለሁና። እኔንም ብቻ ፍሩኝ።"},{"id":41,"translation":"41. (እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ከናንተ ጋር ያለውን መጽሐፍ እውቅና የሚሰጥ ሆኖ ባወረድኩት (ቁርኣን) እመኑ:: በእርሱም የመጀመሪያ ከሓዲያን አትሁኑ:: በአንቃጾቼ ጥቂት ገንዘብ አትለውጡ:: እኔንም ብቻ ፍሩኝ፡፡"},{"id":42,"translation":"42. እውነቱን ከውሸት ጋር አትቀላቅሉ:: እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ፡፡"},{"id":43,"translation":"43. ሶላትን ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ:: ዘካንም ለተገቢው አካል ስጡ:: ለጌታችሁም ከአጎንባሾች ጋር አጎንብሱ:: (ከሰጋጆች ጋር ስገዱ)።"},{"id":44,"translation":"44. እናንተ መጽሐፍን የምታነቡ ሆናችሁና ሰዎችን በበጎ ስራ እያዘዛችሁ ራሳችሁን በመልካም ምግባር ከማነጽ ትዘነጋላችሁን? አታስተውሉምን?"},{"id":45,"translation":"45.በመታገስና በሶላትም ተረዱ፡፡ እርሷ (ሶላት) በፈሪዎች ላይ እንጂ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት።"},{"id":46,"translation":"46. እነዚያ ከጌታቸው ጋር እንደሚገናኙና ወደ እርሱ ተመላሾች መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ናቸው።"},{"id":47,"translation":"50. የእስራኤል ልጆች ሆይ! ያችን በናንተ ላይ የለገስኳትን ጸጋዬንና እኔም በዓለማት ላይ ያበለጥኳችሁ (አባቶቻችሁን በጊዜያቸው ከነበሩት ዓለማት ያበለጥኩዋቸው) መኾኔን አስታውሱ፡፡"},{"id":48,"translation":"48. ማንኛዋም ነፍስ ከሌላዋ ነፍስ ምንንም የማትመነዳበትን፤ ከእርሷም ምልጃን የማይቀበሉባትን፤ ከእርሷም ቤዛ የማይያዝባትንና እነርሱም በየትኛዉም አካል የማይረዱበትን ቀን ቅጣት ፍሩ (ተጠንቀቁ)፡፡"},{"id":49,"translation":"49. ከፈርዖን ቤተሰቦች (ከጎሳዎቹ) ብርቱን ቅጣት የሚያቀምሷችሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁን የሚያርዱና ሴቶቻችሁን የሚተዉ ሲሆኑ ከእነርሱ ባዳንናችሁ ጊዜ (የሆነውን ታሪክ አስታውሱ)። ያ ክስተት ከጌታችሁ ለእናንተ ታላቅ ፈተና ነበር።"},{"id":50,"translation":"50. (እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) በእናንተ ምክንያት ባህሩን በከፈልን ጊዜ የሆነውን ታሪክም አስታውሱ:: ወዲያውኑም አዳንናችሁ:: የፈርዖንንም ቤተሰቦች ዓይናችሁ እያየ አሰመጥናቸው::"},{"id":51,"translation":"51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳ የአርባ ሌሊትን ቀጠሮ ከእኛ በወሰደበት ጊዜ (የሆነውን ታሪክ ለህዝቦችህ አስታውስ):: ከዚያም ከእርሱ (መሄድ) በኋላ እናንተ ራሳችሁን በዳዩች ስትሆኑ ወይፈንን አምላክ አደረጋችሁ::"},{"id":52,"translation":"52. (ቢሆንም) ከዚያ በኋላ ታመሰግኑ ዘንድ ለእናንተ ምህረትን አደርግን::"},{"id":53,"translation":"53. (እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ወደ ትክክለኛው መንገድ) ትመሩ ዘንድ ለሙሳ እውነትንና ውሸትን የሚለይን መጽሐፍ በሰጠነው ጊዜ (የዋልንላችሁን ውለታ አስታውሱ)::"},{"id":54,"translation":"54. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ሙሳ ለሕዝቦቹ (እንዲህ) ባለም ጊዜ የዋልነውን ውለታ አስታውሱ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! እናንተ ወይፈንን አምላክ በማድረጋችሁ ነፍሶቻችሁን በደላችሁ:: በመሆኑም ወደ ፈጣሪያችሁ ተመለሱ:: ከመካከላችሁ ወንጀለኛ ወገኖቻችሁን ግደሉ:: ይሃችሁ ድርጊት በፈጣሪያችሁ ዘንድ ለእንናተ በላጭ ነው። በእናንተም ላይ ምህረቱን አወረደ:: እነሆ እርሱ (አላህ) ጸጸትን ተቀባይ ምህረተኛ አዛኝ ነውና።"},{"id":55,"translation":"55. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) «ሙሳ ሆይ! አላህን በይፋ እስከምናይ ድረስ ለአንተ በፍጹም አናምንልህም።» ባላችሁ ጊዜ (የሆነውን ታሪክ አስታውሱ)። እናንተም በዓይናችሁ እየተመለከታችሁ መብረቅ መታችሁ።"},{"id":56,"translation":"56. ከዚያም ታመሰግኑ ዘንድ ከሞታችሁ በኋላ አስነሳናችሁ፡፡"},{"id":57,"translation":"57. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) በናንተ ላይ ዳመናን አጠለልን:: እንደ ነጭ ማር ያለ «መንን» እና ድርጭትን ለምግብነት አወረድን:: «ከሰጠናችሁም ጣፋጮችን።» ብሉ አልን:: እኛን አልበደሉንም:: ነፍሶቻቸውን ግን ይበድሉ ነበር::"},{"id":58,"translation":"58. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) «ወደዚህች ከተማ ግቡ። ከእርሷም ከፈለጋችሁት ስፍራ የፈለጋችሁት መልኩ ተመገቡ:: በሩንም አጎንበሳችሁ ግቡ:: ‹ጥያቄያችንም የኃጢአቶቻችን መሰረዝ ነው።› በሉ:: ኃጢአቶቻችሁን እንምራለን ለበጎ ሰሪዎችም ምንዳ እንጨምርላቸዋለን።» ባልን ጊዜ የሆነውን አስታውሱ።"},{"id":59,"translation":"59. እነዚያም እራሳቸውን የበደሉት እነርሱ ከተባሉት ሌላን ቃል ለወጡ። በነዚያም በበደሉት ላይ ያመጹ በመሆናቸው ምክንያት መቅሰፍትን ከሰማይ አወረድንባቸው።"},{"id":60,"translation":"60. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ሙሳ ለሕዝቦቹ የመጠጥ ውሃን በፈለገ ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውሱ:: «ድንጋዩን በዘንግህ ምታው።» አልነው:: መታዉም ከእርሱም አስራ ሁለት ምንጮች ፈለቁ (ፈነዱ)፤ ሰዎቹ ሁሉ በትክክል መጠጫቸውን አወቁ:: «ከአላህ ሲሳይ ብሉ፤ ጠጡም፤ አመጸኞችም ሆናችሁ በምድር ላይ አታበላሹ።» (አልናቸው)።"},{"id":61,"translation":"61. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) «ሙሳ ሆይ! በአንድ ዓይነት ምግብ ላይ በፍጹም አንታገስም:: ስለዚህ ጌታህ ከእነዚያ ምድር ከምታበቅላቸው ከቅጠላ ቅጠሏ፤ ከዱባዋ፤ ከስንዴዋ፤ ከምስሯና ከሽንኩርቷ ያወጣልን ዘንድ ለምንልን።» (ባላችሁም ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውሱ):: ሙሳም «ያንን ዝቅተኛ የሆነውን በዚያ ከፍተኛና በላጭ በሆነው ነገር ልትተኩ ትፈልጋላችሁን? ወደ ከተማ ውረዱ:: የጠየቃችሁትን ነገር ታገኛላችሁና።» አላቸው። ውርደትና ድህነት ተጣለባቸው:: በአላህም ቁጣ ተመለሱ:: ይህ እነርሱ በአላህ ተዐምራት ይክዱና ነብያትንም ያለ አግባብ ይገድሉ ስለነበሩ፤ በኃጢአትም ላይ በመዘፈቃቸውና እንዲሁም ወሰንን የሚያልፉ በመሆናቸው ነው።"},{"id":62,"translation":"62. እነዚያ በአላህ ያመኑ፣ እነዚያ አይሁዳውያን፣ ክርስቲያኖችና ሳቢያኖችም ሁሉ ከእነርሱ መካከል በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመኑና መልካምን ስራ የሰሩ ሁሉ በእነርሱ ላይ (ምንም ይደርስብናል ብለው) ፍርሀት የለባቸዉም። (ምንም ነገር ያመልጠናል ብለው) አያዝኑምም።"},{"id":63,"translation":"63. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ከበላያችሁ የጡርን ተራራ ያነሳን ሆነን « (ከእሳት ቅጣት) ትጠበቁ ዘንድ የሰጠናችሁን በርትታችሁ ያዙ:: በውስጡ ያለውን ነገር አስታውሱ።» ብለን የጠበቀ ቃል ኪዳናችሁን በያዝንበት ጊዜ የሆነውን ታሪክ (ልብ በሉ)።"},{"id":64,"translation":"64. ከዚያም ከዚህ በኋላ ቃልኪዳኑን ተዋችሁ:: በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ በትክክል ከጠፊ ህዝቦች በሆናችሁ ነበር።"},{"id":65,"translation":"65. እነዚያም ከናንተ መካከል በቅዳሜ ቀን አሳን በማጥመድ ወሰን ያለፉትንና ለእነርሱም «ወራዳዎች ዝንጆሮዎች ሁኑ።» ያልናቸውን ሕዝቦች ታሪክ በእርግጥ አወቃችሁ።"},{"id":66,"translation":"66. የመንደሯን ሰዎች ቅጣትም ለእነዚያ በጊዜያቸው ለነበሩትና ለእነዚያም ከበኋላቸው ለሚመጡት ሕዝቦች መቀጣጫ ለፈራሂያንም (ትምህርት) አደረግናት።"},{"id":67,"translation":"67. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ሙሳ ለህዝቦቹ «አላህ ላም እንድታርዱ ያዛችኋል» ባለም ጊዜ (የሆነውን ታሪክ አስታውሱ)። እነርሱም ለሙሳ «መሳለቂያ ታደርገናለህን?» አሉት። እሱም «ከተሳላቂዎች ከመሆን በአላህ እጠበቃለሁ» አላቸው።"},{"id":68,"translation":"68. እነርሱም «እስቲ ጌታህን ጠይቅልን:: እርሷ ምን እንደሆነች (እድሜዋን) ያብራራልን ዘንድ» አሉ:: እርሱም «‹እርሷ በውልም ያላረጀች ጥጃም ያልሆነች በዚህ መካከል ልከኛ የሆነች ጊደር ናት።› ይላችኋል። የታዘዛችሁትንም ስሩ።» አላቸው።"},{"id":69,"translation":"69. እነርሱም “እስቲ ጌታህን እንደገና ጠይቅልን:: መልኳ ምን እንደሚመስል ይገልጽልን ዘንድ” አሉ:: እርሱም “መልኳ ደማቅ ተመልካቾችን የምታስደስት ዳልቻ ላም ናት ይላችኋል” አላቸው፡፡"},{"id":70,"translation":"70. ጌታህን ጠይቅልን :: እርሷ ምን እንደሆነች ይግለጽልን:: ምክንያቱም ላሞቹ በሙሉ በእኛ ላይ ተመሳሰሉብን:: እኛም አላህ የሻ እንደሆነ በእርግጥ (ትክክለኛውን አቅጣጫ የምንይዝ) ተመሪዎች ነን” አሉ፡፡"},{"id":71,"translation":"71. እርሱም: «‹እርሷ ያልተገራች ምድርን በማረስ የማታስነሳ፤ እርሻንም የማታጠጣ፤ ከነውር ሁሉ ነፃ የሆነች፤ ጸያፍ ምልክት የሌለባት ናት።› ይላችኋል አላቸው።» እነርሱም «አሁን ገና በትክክል መጣህ።» አሉ:: ከዚያ ትዕዛዙን ላለመፈጸም የቀረቡ ሆነው ላሟን አረዷት።"},{"id":72,"translation":"72. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ነፍስ በገደላችሁና በእርሷም ጉዳይ በተከራከራችሁ ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውሱ:: አላህ ያን በውስጣችሁ ትደብቁት የነበራችሁትን ሚስጢር ሁሉ ገላጭ ነው፡፡"},{"id":73,"translation":"73. (የሙቱን በድን) «በታረደችው ላም ከፊል አካል ምቱት አልን »:: (እናም መቱትና ተነሳ:: የገደለው ማን እንደሆነ ነገራቸውና እንደገና ሞተ::) ሰዎች ሆይ! ልክ እንደዚሁ ትገነዘቡና ታውቁ ዘንድ ሙታንን ህያው በማድረግ ተዓምራቶቹን ያሳያችኋል፡፡"},{"id":74,"translation":"74. ከዚያም ልቦቻቸው ከዚህ (ትዕይንት) በኋላ ደረቁ:: እርሷም በድርቅና እንደ አለት ድንጋዩች ወይም ከእርሱ ይበልጥ የበረቱ ናቸው:: ምክንያቱም ከድንጋዩች መካከል ጅረቶች (ወንዞች) የሚፈሱበት፤ ከእነርሱም የሚሰነጥቅና ከእርሱ ውሃ ምንጭ የሚወጣው፤ ከእነርሱም አላህን ከመፍራቱ የተነሳ ወደ ታች የሚወርድ አለና:: አላህ ከምትሰሩት ነገር ሁሉ ከአንዱም ዘንጊ አይደለም፡፡"},{"id":75,"translation":"75. ከ(አይሁድ) መካከል የአላህን ቃል የሚሰሙና ከዚያም እውነቱን ከተረዱ በኋላ ሆን ብለው እነርሱ እያወቁ የሚለውጡት ቡድኖች እያሉ ለእናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?"},{"id":76,"translation":"76. እነዚያም ያመኑትን ሙስሊሞችን ባገኙ ጊዜ “እኛም እንደናንተው አምነናል” ይላሉ:: እርስ በርሳቸው ብቻ በተገናኙ ጊዜ ግን “አላህ በእናንተ ላይ የገለጸላችሁን ነገር በጌታችሁ ዘንድ እርሱን መረጃ እንዲያቀርቡባችሁ ትነግሯቸዋላችሁን? አታስተውሉምን?” ይባባላሉ::"},{"id":77,"translation":"77. አላህ የሚደብቁትንም ሆነ የሚገልጹትን ነገር ሁሉ የሚያውቅ ጌታ መሆኑን አያውቁምን?"},{"id":78,"translation":"78. ከእነርሱም መካከል መጽሐፍን የማያውቁ መሃይማን አሉ:: ግን ከንቱ ምኞቶችን ይመኛሉ:: እነርሱም መጠራጠርን እንጂ ትክክለኛ እውቀት የላቸዉም::"},{"id":79,"translation":"79. እነዚያ መጽሐፍን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያ በእርሱ ጥቂት ዋጋን ሊገዙበት ብለው: «ይህ ከአላህ ዘንድ የወረደ ነው» ለሚሉ ሁሉ ወዮላቸው። እነርሱ ከዚያ እጆቻቸው ከፃፉት ወንጀል ወዮላቸው:: እነርሱ ከዚያ ከሚሰሩት ኃጢአት ወዮላቸው።"},{"id":80,"translation":"80. (አይሁዶች) “የገሀነም እሳት ለተቆጠሩ ውስን ቀናት ብቻ እንጂ ፈጽሞ አትነካንም” አሉ። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) “በዚህ ጉዳይ ከአላህ ዘንድ ቃል ኪዳን ይዛችኋልን? ይህ ከሆነ አላህም ኪዳኑን አያፈርስም:: ወይስ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን?” በላቸው።"},{"id":81,"translation":"81. እንዴታ እነዚያ መጥፎን ተግባር የሰሩና በኃጢአትም የተከበቡ ሁሉ በእርግጥ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱም በውስጧ ለዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው።"},{"id":82,"translation":"82. እነዚያም ያመኑና በጎ ስራዎችን የሰሩ ሁሉ የገነት ጓዶች ናቸው። እነርሱም በውስጧ ለዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው።"},{"id":83,"translation":"83. (የኢስራኢል-ልጆችን) “አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ:: ለወላጆችም በጎን ስራ ስሩ:: ለዝምድና ባለቤቶች፤ ለየቲሞችና ለሚስኪኖችም በጎን ዋሉ:: ለሰዎችም ሁሉ መልካምን ብቻ ተናገሩ :: ሶላትን ደንቡን ጠብቃች ስገዱ:: ዘካን ለተገቢው ስጡ” በማለት ጥብቅ ቃልኪዳን በያዝንባቸው ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ):: ከዚያም ከእናንተ ጥቂቶቹ ሲቀሩ ሸሻችሁ:: እናንተ (ቃልኪዳንንም) የምትተው ናችሁ፡፡"},{"id":84,"translation":"84. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) የሕዝቦቻችሁን ደም አታፍስሱ:: ወገኖቻችሁን ከመኖሪያ አገሮቻቸው አታስወጡ በማለት የጠበቀ ቃልኪዳናችሁን በያዝንባችሁ ጊዜ (የሆነውን) አስታውሱ:: ከዚያም በቃል ኪዳኑ ትክክለኛነት አጸናችሁ::እናንተም በዚሁም ትመሰክራላችሁ፡፡"},{"id":85,"translation":"85. ከዚያም ቃል ኪዳናችሁን በማፍረስ የምትገድሉ፤ ከናንተም መካከል የሆኑ ሕዝቦችን በኃጢአትና በመበደል ላይ በመተባበር ከአገሮቻቸው የምታስወጡ እናንተው ራሳችሁ ናችሁ:: ምርኮኞች ሆነው ወደ እናንተ ሲመጡም ቤዛ ትሆኗቸዋላችሁ:: እነርሱን ከመኖሪያ ክልላቸው ማባረሩ በእናንተ ላይ የተከለከለ ነው:: በመጽሐፉ በከፊሉ አምናችሁ በሌላው ትክዳላችሁን? ከእናንተ መካከል ይህንን ጸያፍ ተግባር የሚሰራ ሰው ሁሉ ቅጣቱ በቅርቢቱ ሕይወት ውርደት አንጂ ሌላ አይደለም:: በትንሳኤ ቀንም ወደ ብርቱ ቅጣት ይመለሳሉ። አላህ ከምትሰሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም።"},{"id":86,"translation":"86. እነዚያ ቅርቢቱን ሕይወት በመጨረሻይቱ ዓለም የለወጡ ናቸው። ከእነርሱ ላይም ቅጣቱ ምንጊዜም አይቀለልላቸዉም:: እርዳታም ከማንም አያገኙም።"},{"id":87,"translation":"87. ለሙሳ መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው:: ከርሱ በኋላም ሌሎች መልዕክተኞችን ልከናል:: የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ተዐምራትን ሰጠነው:: ቅዱስ መንፈስ (ጅብሪል) በሚባለው መላአክ አበረታነው:: ነፍሶቻችሁ በማትወደው ነገር መልዕክተኛው በመጣላችሁ ቁጥር እነርሱን ከመከተል ይልቅ በትዕቢት ከፊሉን አስተባበላችሁ:: ከፊሉን ደግሞ ትገድላላችሁን?"},{"id":88,"translation":"88. “ልቦቻችን ድፍኖች ናቸው” አሉ:: (እውነታው ግን ይህ አይደለም)። አላህ በክህደታቸው ምክንያት ረገማቸው። በመሆኑም ጥቂትን እንጂ አያምኑም።"},{"id":89,"translation":"89. ከእነርሱ ጋር ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭ የሆነ መጽሐፍ ከአላህ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ ከመምጣቱ በፊት በእነዚያ በካዱት ላይ ይረዱበት የነበሩ ሲሆኑ ያ ቀድሞውኑ ያውቁት የነበረ ነገር በመጣላቸው ጊዜ በእርሱ ካዱ:: እናም የአላህ እርግማን በካሐዲያን ላይ ይሁን፡፡"},{"id":90,"translation":"90. ነፍሶቻቸውን የሸጡበት (የለወጡበት) ነገር ከፋ! ይኸዉም አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ችሮታውን ማውረዱን በመመቅኘት አላህ ባወረደው ነገር መካዳቸው ነው:: እናም የአላህን ቁጣ በተደጋጋሚ አትርፈዋል:: ለካሐዲያንም አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":91,"translation":"91. «አላህ ባወረደው እመኑ» በተባሉ ጊዜ «በእኛ ላይ በተወረደው መጽሐፍ ብቻ እናምናለን» ይላሉ:: ከእርሱ ኋላ የመጣው ቁርኣን ምንም እንኳን ከእነርሱ ጋር ላለው መጽሐፍ አረጋጋጭና ትክክለኛ የሆነ ቢሆንም ይክዳሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ ከአሁን በፊት የአላህን ነብያትን ለምን ገደላችሁ?» በላቸው።"},{"id":92,"translation":"92. ሙሳ በግልጽ መረጃ ታጅቦ ወደ እናንተ መጥቶ ነበር:: ግን እርሱ በሌለበት ወይፈንን አምላክ አደረጋችሁ:: አጥፊዎች ነበራችሁ፡፡"},{"id":93,"translation":"93. የጡርን ጋራ ከበላያችሁ በማንሳት (በተውራት ሕግ እንደትሰሩ) ቃል ኪዳናችሁን በያዝን ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ):: «የሰጠናችሁን በጽናት ያዙ:: ያልነውንም ስሙ።» አልን:: «ሰማን ግን አመጽን» አሉ:: የወይፈኑም ውዴታ በክህደታቸው ምክንያት በልቦቻቸው ውስጥ ገብቷል:: «ትክክለኛ አማኞች እንደሆናችሁ እምነታችሁ የሚያዛችሁ ነገር የከፋ ነው።» በላቸው።"},{"id":94,"translation":"94. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ለአይሁድ) «የመጨረሻይቱ አገር ገነት በአላህ ዘንድ ከሌሎች በተለየ ለእናንተ ብቻ በመሆኗ እውነተኞች ከሆናችሁ እስቲ ሞትን ተመኙ።» በላቸው።"},{"id":95,"translation":"95. እጆቻቸው (ባሳለፉት) በሰሩት ወንጀል ምክንያት ሞትን ምንጊዜም ፈጽሞ አይመኙትም:: አላህ በዳዩችን አዋቂ ነው፡፡"},{"id":96,"translation":"96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አይሁድ ሁሉ እና ከእነዚያ ጣኦትን በአላህ ካጋሩት ይበልጥ በሕይወት ላይ የሚጓጉ ሆነው በእርግጥ ታገኛቸዋለህ:: ለአንዳቸውም አንድ ሺህ ዓመት ዕድሜ ቢሰጥ ይወዳል:: እርሱም (ዕድሜ መሰጠቱ) ከቅጣት የሚያድነው አይደለም:: አላህም የሚሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና።"},{"id":97,"translation":"97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመልዐኩ ጅብሪል ጠላት የሆነ (ግልጽ ከሃዲ ነው)። ከርሱ በፊት የወረዱ መጽሐፍትን የሚያረጋግጥ ለአማኞች መሪና ብስራት ነጋሪ ሲሆን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ ያወረደው መሆኑን ንገራቸው።"},{"id":98,"translation":"98. ለአላህና ለመላዕክቱ፤ እንዲሁም ለመልዕክተኞቹ፤ ለጅብሪልና ለሚካኢልም ጠላት የሆነ ሁሉ ግልጽ ከሐዲ ነው:: አላህ ደግሞ ለከሓዲያን ሁሉ ጠላት ነው::"},{"id":99,"translation":"99. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ አንተ ግልጽ የሆኑ (አናቅጽን) መመሪያዎችን በእርግጥ አውርደናል:: በእነርሱም አመጸኞች እንጂ ሌላ አይክድም::"},{"id":100,"translation":"100. ቃልኪዳን በገቡ ቁጥር ከእነርሱ መካከል ከፊሉ ቃል ኪዳኑን ይጥለዋልን? (ያፈርሰዋልን?):: ይልቁንም አብዛኞቻቸው አያምኑም፡፡"},{"id":101,"translation":"101. ከእነርሱ ጋር ያለን መጽሐፍ የሚያረጋግጥ መልዕክተኛ ከአላህ ዘንድ ተልኮ በመጣ ጊዜ ከእነዚያው መጽሐፍት ከተሰጣቸው ወገኖች ከፊሎቹ ምንም እንደማያውቁ ሆነው የአላህን መጽሐፍ ወደ ኋላቸው ወረወሩት (ጣሉት)።"},{"id":102,"translation":"102. (የአላህን መጽሐፍ አንቀበልም ያሉ አይሁዶች) ሰይጣናት በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ድግምት ተከተሉ:: ሱለይማን ጌታውን አልካደም::( ድግምተኛ አልነበረም::) ሰይጣናት ግን ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲሆኑ በጌታቸው ካዱ:: በባቢሎን (በባቢል) በሁለቱ መላዕክት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደውን ተከተሉ:: (ሀሩትና ማሩት) ግን «እኛ ለእናንተ መፍፈተኛዎች ነንና በጌታህ አትካድ» እስከሚሉ ድረስ አንድንም አያስተምሩም ነበር:: ከእነርሱም በባልና በሚስቱ መካከል የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ:: እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር አንድንም በርሱ አይጎዱም:: (ድግምት የሚማሩ ሁሉ) የሚጎዳቸውንና ቅንጣት የማይጠቅማቸውን ትምህርት ይማራሉ:: የገዛው በመጨረሻይቱ አገር ምንም ዕድል የሌለው መሆኑን በእርግጥ ተገንዝበዋል:: ነፍሶቻቸውን የሸጡበት ዋጋ ምንኛ ከፋ:: የሚያውቁ በሆኑ ኑሮ (ይህን ተግባር ባልተገበሩት ነበር::)"},{"id":103,"translation":"103. በአላህ ባመኑና የከለከለውን በተጠነቀቁ ኖሮ (መልካምን በተመነዱ ነበር):: የሚያውቁ ቢሆኑ ከአላህ ዘንድ የሚገኘው ምንዳ (ነፍሶቻቸውን ከሚሸጡበት) በላጭ ነው::"},{"id":104,"translation":"104. (እናንተያመናችሁ ሆይ!) ለነብዩ \"ራዒና\" አትበሉ:: “ኡንዙርና” (ተመልከተን) በሉ:: የምትባሉትንም ስሙ:: ለካሃዲያንም ሁሉ አሳማሚ ቅጣት ተዘጋጅቶላቸዋል::"},{"id":105,"translation":"105. እነዚያ ከመጽሐፍ ባለቤቶችም ሆነ ከአጋሪዎች በአላህ የካዱት በእናንተ ላይ ከጌታችሁ የሆነ መልካም ነገር መውረዱን አይወዱም:: አላህም በችሮታው (በነብይነት) የሚፈልገውን ሰው ይመርጣል:: አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው::"},{"id":106,"translation":"106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከቁርኣን አናቅጽ መካከል አንዱን እንኳን ብንሽር ወይም እርሱን ብናስረሳህ ከእርሱ የሚበልጥ ወይም ተመሳሳዩን እናመጣለን:: አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ መሆኑን አላወቅክምን?"},{"id":107,"translation":"107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ መሆኑን እና ለእናንተም ከአላህ ሌላ ወዳጅም ሆነ ረዳት እንደሌላችሁ አላወቅክምን?"},{"id":108,"translation":"108. (ሰዎች ሆይ!) ከአሁን በፊት (ነብዩ) ሙሳ እንደተጠየቀው ዓይነት መልዕክተኛችሁን (ሙሐመድን) ልትጠይቁ ትፈልጋላችሁን? በእምነት ክህደትን የሚለውጥ ሁሉ በእርግጥ ትክክለኛውን መንገድ ስቷል፡፡"},{"id":109,"translation":"109. ከመጽሐፍ ባለቤቶች መካከል ብዙዎቹ እውነቱ ከተገለጸላቸው በኋላ ከነፍሶቻቸው በሆነው ምቀኝነት በመገፋፋት ከእምነታችሁ በኋላ ከሓዲያን ሊያደርጓችሁ ተመኙ:: እናም አላህ ትዕዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ይቅርታ አድርጉ:: እለፏቸዉም:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና::"},{"id":110,"translation":"110. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ሶላትን አስተካክላችሁ ስገዱ:: ዘካንም ለተገቢዎች ስጡ:: ለነፍሶቻችሁም የምታስቀድሙትን በጎ ስራ በአላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::"},{"id":111,"translation":"111. «ገነትን አይሁድ ወይም ክርስቲያኖች የሆነ እንጂ ሌላ አይገባትም።» አሉ:: «ይህች ከንቱ ምኞታቸው ናት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውነተኞች እንደሆናችሁ እስቲ ማስረጃችሁን አምጡ።» በላቸው።"},{"id":112,"translation":"112. ጉዳዩ እንደመሰላቸው አይደለም:: ይልቁንም በጎ ሰሪ ሆኖ ፊቱን ለአላህ የሰጠ ሁሉ ለእርሱ በጌታው ዘንድ ምንዳ አለው:: በእነርሱ ላይ ስጋትም የለባቸዉም። አይተክዙምም።"},{"id":113,"translation":"113. እነርሱ መጽሐፉን የሚያነቡ ሲሆን አይሁድ «ክርስቲያኖች በምንም ላይ አይደሉም።» አሉ:: ክርስቲያኖችም «አይሁዶች በምንም ላይ አይደሉም።» አሉ። እንደዚሁ እነዚያ የማያውቁት አጋሪዎችም የነሱን ተመሳሳይ ንግግር ተናገሩ:: አላህ በዚያ ይለያዩበት በነበሩት ነገር ላይ ሁሉ በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡"},{"id":114,"translation":"114. የአላህን መስጊዶች በውስጣቸው ስሙ እንዳይወሳበት ከከለከለና መስጊዶችንም ለማበላሸት ከጣረ ይበልጥ ድንበር አላፊ (አጥፊ) ማን ነው? እነዚያ በፍርሃት ተውጠው እንጂ ወደ መስጊዶች ሊገቡ አይገባቸዉም። ለነርሱም በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አለባቸው:: በመጨረሻይቱ ሀገርም ታላቅ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":115,"translation":"115. ምስራቁም ምዕራቡም የአላህ ብቻ ነው:: በአላህ ትእዛዝ (ፊቶቻችሁን) ለሶላት ወደ የትም አቅጣጫ ብታዞሩ የአላህ ፊት እዚያ ዘንድ ነው:: አላህ በእርግጥ ችሮታው ሰፊና ሁሉን አዋቂ ነዉና፡፡"},{"id":116,"translation":"116. አላህ «ልጅ አለው።» አሉ:: ከሚሉት ጥራት ተገባው:: ይልቁንም በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው:: ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው::"},{"id":117,"translation":"117. ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው:: ማንንም ነገር ማስገኘት በፈለገ ጊዜ ለእርሱ የሚለው ‹‹ሁን›› ብቻ ነው:: ወዲያዉም እንዳለው ይሆናል፡፡"},{"id":118,"translation":"118. እነዚያ የማያውቁት «(አንተ መልዕክተኛ ስለመሆንህ) አላህ ለምን አያናግረንም? ወይም (ለእውነተኛነትህ) ተዓምር አይመጣልንም ኖሯልን? አሉ:: እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩትም ልክ እንደዚሁ ንግግራቸው ብጤ ብለዋል:: ልቦቻቸው በክህደት ተመሳሰሉ:: ለሚያረጋግጡ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን በእርግጥ አብራርተናል::"},{"id":119,"translation":"119. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርገን በእውነት ላክንህ:: ከእሳት ጓዶችም ሁኔታ አትጠየቅም፡፡"},{"id":120,"translation":"120. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አይሁድም ሆኑ ክርስቲያኖች የየራሳቸውን ሀይማኖትን እስከምትከተል ድረስ ፈጽሞ አይደሰቱብህም:: «ትክክለኛው መንገድ በእርግጥ የአላህ አመራር ነው።» በላቸው። ትክክለኛው እውቀት ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል አንተን ከአላህ የሚከላከልልህ ወዳጅም ሆነ ረዳት የለህም::"},{"id":121,"translation":"121. እነዚያ መጽሐፉን የሰጠናቸው ሰዎች ተገቢ ንባቡን ያነቡታል:: በእርሱም ያምናሉ:: እነዚያ በእርሱ የሚክዱ ግን ከሳሪዎች እነርሱ ብቻ ናቸው::"},{"id":122,"translation":"122. እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ! እኔ ያ በእናንተ ላይ የለገስኳችሁን ጸጋዎቼንና (በዘመናችሁ ከነበሩት) የዓለማት ሕዝቦች በላይ ያበለጥኳችሁ መሆኔን አስታውሱ።"},{"id":123,"translation":"123. አንዲት (አማኝ) ነፍስ ለሌላ (ከሓዲ) ነፍስ ምንንም የማትጠቅምበትን፤ ከእርሷም ቤዛ የማይወሰድበትን፤ ምልጃም ለእርሷ የማትፈይድበትን፤ እነርሱም ከየትም በኩል የማይረዱበትን ቀን ተጠንቀቁ፡፡"},{"id":124,"translation":"124. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂምን ጌታው በትዕዛዛት በፈተነውና በፈጸማቸውም ጊዜ (የነበረውን ታሪክ አስታውስ):: «እኔ የሰው ዘር መሪ አድርጌሀላሁ።» አለው:: ኢብራሂምም «ከዘሮቼም አድርግ?» ሲል ጠየቀ:: አላህም «ኢብራሂም ሆይ! ቃል ኪዳኔ ለግፈኛ አጥፊዎች ተፈፃሚ አይሆንም እንጂ።» አለው።"},{"id":125,"translation":"125. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቤቱንም (ከዕባን) ለሰዎች መሰባሰቢያና የሰላም ማዕከል ባደረግን ጊዜ የነበረውን ታሪክ አሰታውስ:: (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከኢብራሂም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ:: ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ {1}","footnotes":"(1) ቤቱን የምለው ከእባን ነው የምያመለክተው"},{"id":126,"translation":"126. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም «ጌታዬ ሆይ! ይህንን ሀገር (መካን) ሰላማዊ ሀገር አድርገው:: ከኗሪዉም መካከል በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነውን ክፍል ከፍራፍሬዎች ሲሳይ ስጠው።» ባለ ጊዜ (የነበረውን ታሪክ አስታውስ):: አላህም «የካደውንም በጥቂቱ እንዲጎናጸፍ አደርገዋለሁ:: ከዚያ ወደ እሳት ቅጣት እዳርገዋለሁ:: ይህም እጅግ አስከፊ መመለሻ ነው።» አለ"},{"id":127,"translation":"127. ኢብራሂምና ኢስማዒልም (እንደሚከተለው) በማለት እየለመኑ የካዕባን ህንፃ (መሰረቶች ግንባታ) ባሳደጉ ጊዜ (የነበረውን ታሪክ አስታውስ): «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበለን:: አንተ ሰሚና አዋቂ ነህና።"},{"id":128,"translation":"128. «ጌታችን ሆይ! ላንተው ፍጹም ታዛዦችም አድርገን:: ከዘሮቻችንም ላንተ ፍጹም ታዛዦች ሕዝቦችን አስነሳ:: አምልኳዊ ክንውኖቻችንንም አሳውቀን:: ንሰሀችንን ተቀበለን:: ጸጸትን ተቀባይና ሩህሩህ አንተ ብቻ ነህና::"},{"id":129,"translation":"129. «ጌታችን ሆይ! በውስጣቸው ከእነርሱ የሆነን መልዕክተኛ፤ በእነርሱ ላይ አናቅጽህን የሚያነብላቸው፤ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውንም ከክህደት የሚያጠራቸውንም ላክላቸው:: አሸናፊዉና ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና።» የሚሉም ሲሆኑ (ከዕባን ገነቡ)።"},{"id":130,"translation":"130. ከኢብራሂምም እምነት ሞኝ ካልሆነ በስተቀር የሚያፈገፍግ ማን ነው? በቅርቢቱም ዓለም በእርግጥ (ለተልዕኳችን) መረጥነው:: በመጨረሻይቱ ዓለምም እርሱ ከመልካሞቹ ነው።"},{"id":131,"translation":"131. ጌታው ለእርሱ «ፍጹም ታዛዥ ሁን።» ባለው ጊዜ «ለዓለማቱ ጌታ ታዛዥ ሆኛለሁ።» አለ።"},{"id":132,"translation":"132. ኢብራሂምም ልጆቹን በተመሳሳይ አዘዘ:: የዕቁብም እንደዚሁ በዚሁ ጉዳይ ልጆቹን አዘዘ:: (እንዲህም አለ) «ልጆቼ ሆይ! አላህ ለእናንተ ሀይማኖትን መረጠ:: ስለዚህ እናንተ ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጂ እንዳትሞቱ።» አላቸው።"},{"id":133,"translation":"133. የዕቆብም ለጣዕረ ሞት በተዳረገበት ጊዜና ለልጆቹ «ከእኔ በኋላ ምንን ትገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ ነበራችሁን? እነርሱም «አንድ የሆነውን አምላክህንና የአባቶችህን የኢብራሂምን፤ የኢስማዒልንና የኢስሃቅንም አምላክ እንገዛለን:: እኛም ለእርሱ ፍጹም ታዛዦች ሆነን እናመልከዋለን።» አሉ።"},{"id":134,"translation":"134. እነኝህ (ከላይ የተወሱት ህዝቦች) በእርግጥ ያለፉ ሕዝቦች ናቸው:: ለእነርሱም የስራቸው ምንዳ አላቸው:: ለእናንተም የስራችሁ (ምንዳ) አላችሁ:: እነርሱ ይሰሩት በነበረው ፈጽሞ አትጠየቁም::"},{"id":135,"translation":"135. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አይሁድና ክርስቲያኖች በየበኩላቸው “አይሁድ ወይም ክርስቲያን ሁኑ ቅንን መንገድ ትመራላችሁና” አሉ:: “አይደለም ይልቁንም የኢብራሂምን ሀይማኖት ቀጥተኛ ሲሆን እንከተላለን፣ ኢብራሂምም ከአጋሪዎችም አልነበረም” በላቸው::"},{"id":136,"translation":"136. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) «በአላህና ወደ እኛ በተወረደው ቁርኣን ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሀቅም፣ ወደ የዕቁብና ወደ ነገዶችም በተወረደው መለኮታዊ መልዕክት ሁሉ በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት፤ በዚያም ነብያት ሁሉ ከጌታቸው በተለገሱት ከእነርሱ አንዱን ከሌላው የማንለይ ስንሆን አመንን:: እኛም (ለአላህ) ፍጹም ታዛዦች ነን።» በሉ።"},{"id":137,"translation":"137. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እናንተ ባመናችሁበት መልኩ ካመኑ በእርግጥ በትክክለኛው ጎዳና ላይ ናቸው:: ከእርሱ ካፈነገጡ ግን እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው:: የእነርሱንም ተንኮል አላህ ይበቃሀል:: እርሱም ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነውና።"},{"id":138,"translation":"138. የአላህን የተፈጥሮ መንከር (እምነት) ያዙ:: በመንከርም ከአላህ ይበልጥ ያማረ ማነው? (ማንም የለም):: እኛም ለእርሱ ብቻ ተገዢዎች ነን (በሉ)፡፡"},{"id":139,"translation":"139. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ጌታችንና ጌታችሁ ሲሆን ለእኛም ስራችን ያለን ስንሆን ለእናንተም ስራችሁ ያላችሁ ስትሆኑ እኛም ስራችንን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች ሆነን ሳለን በአላህ (ሀይማኖት) ትከራከሩናላችሁን?» በላቸው።"},{"id":140,"translation":"140. ወይስ «ኢብራሂምም፣ ኢስማዒልም፣ ኢስሐቅም፣ ያዕቆብም፣ እንዲሁም ነገዶቹም አይሁድ ወይም ክርስቲያኖች ነበሩ» ትላላችሁን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) “እናንተ ናችሁ የምታውቁት? ወይንስ አላህ?” በላቸው:: እርሱ ዘንድ ከአላህ የሆነችን ምስክርነት ከደበቀ ይበልጥ አጥፊ ማነው? አላህ የምትፈጽሙትን ሁሉ ዘንጊ አይደለም።"},{"id":141,"translation":"141. እነዚህ ያለፉ ሕዝቦች ናቸው:: ለእነርሱ የሰሩት አላቸው:: ለእናንተም የሰራችሁት አላችሁ:: እነርሱ ይሰሩት ከነበሩት ሁሉ አትጠየቁም::"},{"id":142,"translation":"142. ቂል የህብረተሰብ ክፍሎች «ከዚያች ከነበሩባት ቂብላቸው (አቅጣጫቻቸው) ምን አዞራቸው?» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ምስራቁም ምዕራቡም የአላህ ነው:: የሻውንም ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል።» በላቸው።"},{"id":143,"translation":"143. እንደዚሁም (እንደመራናችሁ) ሁሉ በሰዎች ላይ መስካሪዎች ልትሆኑና መልዕክተኛዉም (ሙሐመድ) በእናንተ ላይ መስካሪ ይሆን ዘንድ መካከለኞች (ምርጥ) ማህበረሰብ (ህዝቦች) አደረግናችሁ:: ያችንም በእርሷ ላይ የነበርክባትን አቅጣጫ መልዕክተኛውን የሚከተለውን ሰው ወደ ክህደት ከሚመለሰው ሰው ልናውቅ (ልንለይ) (ልንገልጽ) እንጂ ቂብላን አላደረግናትም:: እርሷም በዚያ አላህ በመራቸው ሰዎች ላይ በስተቀር በእርግጥ ከባድ ናት:: አላህም እምነታችሁን (ስግደታችሁን) የሚያጠፋ አይደለም:: አላህም ለሰዎች በጣም ሩህሩህና አዛኝ ነው::"},{"id":144,"translation":"144. የፊትህን ወደ ሰማይ ማንጋጠጥክን በእርግጥ ተመልክተናል:: እናም ወደ ምትወዳት (ከዕባ) ቂብላ እናዞርሃለን:: ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ ወደ ካዕባ አቅጣጫ አዙር:: (ሙስሊሞች ሆይ!) የትም ስፍራ ብትሆኑ ስትሰግዱ ፊቶቻችሁን ወደ ካዕባ አቅጣጫ አዙሩ:: እነዚያ መጽሐፉን የተሰጡት እርሱ ከጌታቸው ሲሆን እውነት መሆኑን ያውቃሉ:: አላህ ከሚሰሩት ስራ ዘንጊ አይደለም፡፡"},{"id":145,"translation":"145.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያ መጽሐፍን ለተሰጡት ሕዝቦች የምትችለውን ያህል ተዓምር (መረጃ) ሁሉ ብታቀርብላቸው እንኳ ቂብላህን አይከተሉም:: አንተም ቂብላቸውን ተከታይ አይደለህም:: ከፊላቸዉም የከፊሉን ቂብላ አይከተሉም:: ከእውቀትም (ራእይ) ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ያን ጊዜ አንተ ከአጥፊዎች ትሆናለህ::"},{"id":146,"translation":"146. እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ሰዎች ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ ሁሉ (ሙሐመድን) ያውቁታል:: ከእነርሱም የተለዩ ክፍሎች እነርሱ የሚያውቁ ሲሆኑ እውነቱን በእርግጥ ይደብቃሉ::"},{"id":147,"translation":"147. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ከጌታህ የሆነ እውነት ነው:: እናም ከተጠራጣሪዎችም አትሁን::"},{"id":148,"translation":"148. ለሁሉም ለስግደት ፊታቸዉን የሚያዞሩባት አቅጣጫ አላቸው:: ወደ መልካም ስራዎችም ተሽቀዳደሙ:: የትም ስፍራ ብትሆኑ አላህ ሁላችሁንም ያመጣችኋል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::"},{"id":149,"translation":"149. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከየትም ለጉዞ ከወጣህበት ስፍራ ሁነህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ አቅጣጫ አዙር:: እርሱም ከጌታህ የሆነ እርግጠኛ እውነት ነው:: አላህም ከምትሰሩት ስራ ሁሉ ዘንጊ አይደለም::"},{"id":150,"translation":"150.ከየትም ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን ወደ ተከለለው መስጊድ አግጣጫ አዙር፡፡ በየትም ስፍራ ብትኾኑ ለሰዎቹ እነዚያ ከነሱ የበደሉት ሲቀሩ (ሃይማኖታችንን ይክዳሉ ቂብላችንን ይከተላሉ በማለት) በናንተ ላይ መከራከሪያ እንዳይኖራቸው ፊቶቻችሁን ወደ አግጣጫው አዙሩ፡፡ አትፍሩዋቸውም፤ ፍሩኝም፤ (በዚህም ያዘዝኳችሁ መከራከሪያ እንዳይኖራቸው) በናንተም ላይ ጸጋየን እንድሞላላችሁና (ወደ እውነትም) እንድትመሩ ነው፡፡"},{"id":151,"translation":"151. ከመካከላችሁ ከናንተ የሆነን በእናንተ ላይ አናቅጻችንን የሚያነብላችሁ እና የሚያጠራችሁ መጽሐፉንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁን መልእክተኛ እንደላክን ሁሉ ጸጋን ሞላንላችሁ።"},{"id":152,"translation":"152. አስታውሱኝ አስታውሳችኋለሁና:: አመስግኑኝ አትካዱኝም::"},{"id":153,"translation":"153. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ታጋዙ (ጥንካሬን ፈልጉ):: አላህም ከታጋሾች ጋር ነውና::"},{"id":154,"translation":"154. በአላህ መንገድ (ለሀይማኖቱ) የሚገደሉትን «ሙታን ናቸው።» አትበሉ:: በእውነቱ ሕያው ናቸውና:: እናንተ ግን አትገነዘቡትም::"},{"id":155,"translation":"155. ከፍርሀትና ከርሀብም ከሀብት፣ ከሕይወትና ከአዝመራ በመቀነስም በእርግጥ እንሞክራችኋለን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ታጋሾችንም (በገነት) አብስር::"},{"id":156,"translation":"156. እነዚያ መከራ በነካቸቻው ጊዜ «እኛ ለአላህ ነን። እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን።» የሚሉትን አብስር።"},{"id":157,"translation":"157. እነዚያ በእነርሱ ላይ ከጌታቸው የሆኑ ምህረቶችና ችሮታም አሉ:: እነርሱም ወደ ቀናው መንገድ እውነት ተመሪዎቹ እነርሱው ናቸው።"},{"id":158,"translation":"158. የሶፋና የመርዋ (ጋራዎች) የአላህን ትዕዛዝ ከመፈጸሚያ ጉልህ ቦታዎች (ምልክቶች) ናቸው:: ካዕባን በሐጅ ወይም በዑምራ ስራ ምክኒያት የጎበኘ ሁሉ በሁለቱ ጋራዎች መካከል በመመላለሱ ምንም ኃጢአት የለበትም:: መልካምንም ስራ በፈቃደኝነት የሰራ (ሁሉ አላህ ይመነዳዋል):: አላህ አመሰጋኝና ሁሉን አዋቂ ነውና::"},{"id":159,"translation":"159. እነዚያ (ስለነብዩ ሙሐመድና ሌሎችም) ከአናቅጽና ቅን መመሪያዎች ያወረድነውን ለሰዎች በመጽሐፍ ከገለጽነው በኋላ የሚደብቁትን ሁሉ አላህ ይረግማቸዋል:: ረጋሚዎችም ሁሉ ይረግሟቸዋል::"},{"id":160,"translation":"160. እነዚያ የተጸጸቱ፤ (ያበላሹትን) ያስተካከሉና (የደበቁትንም) የገለጹ ሲቀሩ:: የእነርሱን ጸጸትንማ እቀበላለሁ:: እኔም ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነኝ::"},{"id":161,"translation":"161. እነዚያ በአላህ የካዱና በክህደታቸው ላይ እያሉ የሞቱ ሰዎች በእነርሱ ላይ የአላህ፤ የመላዕክትና የመላው የሰው ዘር ሁሉ እርግማን አለባቸው::"},{"id":162,"translation":"162. በእርግማን ውስጥም ሁልጊዜ ዘውታሪዎች ይሆናሉ:: ቅጣቱ ከእነርሱ አይቃለልም። ጊዜም አይሰጡም::"},{"id":163,"translation":"163. (ሰዎች ሆይ!) አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: ከእርሱም ሌላ (ትክክለኛ) አምላክ የለም:: እርሱም እጅግ በጣም ሩህሩህና በጣም አዛኝ ነው::"},{"id":164,"translation":"164. የሰማያትና የምድር አፈጣጠር፤ የሌሊትና ቀንም መፈራረቅ (መተካካት)፤ ያችም ሰዎችን የሚጠቅም ነገር (ተጭና) በባህር ላይ የምትንሳፈፈው መርከብ፤ አላህም ከሰማይ ባወረደው ውሃና በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው በማድረጉ በእርሷም ውስጥ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በመበተኑ፤ ንፋሶችንም በየአቅጣጫው የሚያገላብጥ መሆኑ እንዲሁም በሰማይና በምድር በሚነዳው ዳመና ለሚያውቁ ሕዝቦች በእርግጥ አያሌ ተዐምራት አሉ።"},{"id":165,"translation":"165. ከሰዎች መካከል ከአላህ ሌላ ባላንጣዎችን/ ጣዖታትን/ አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ሆነው የሚይዙ አሉ። እነዚያ ያመኑት ግን አላህን ከምንም በላይ ይወዳሉ:: እነዚያም የበደሉት ሰዎች ቅጣትን በትንሳኤ ቀን ባዩ ጊዜ ሀይል ሁሉ ለአላህ ብቻ መሆኑንና አላህም ቅጣቱ ብርቱ እንደሆነ ይገነዘባሉ:: በዚህች ዐለም ቢያውቁ ኖሮ (ባላንጣዎችን በመያዛቸው በተጸጸቱ ነበር)።"},{"id":166,"translation":"166. (ይህም የሚሆነው) እነዚያ አስከታዮች ተከታዮቻቸውን በካዱበትና የሲዖልን ቅጣት ባዩ ጊዜ፤ በእነርሱም መካከል የግንኙነት መስመሮች ሁሉ በሚበጠስበት ጊዜ ነው።"},{"id":167,"translation":"167. እነዚያም የተከተሉት «ለእኛ (ወደ ቅርቢቱ ዓለም) አንዲት ጊዜ መመለስ በኖረችንና ከእኛ እንደተጥራሩ ከእነርሱ በተጥራራን እንመኛለን» ይላሉ፡፡ እንደዚሁ አላህ ሥራዎቻቸውን በነርሱ ላይ ጸጸቶች አድርጎ ያሳያቸዋል፡፡ እነርሱም ከእሳት ወጪዎች አይደሉም፡፡"},{"id":168,"translation":"168. እናንት ሰዎች ሆይ! በምድር ካለው ነገር የተፈቀደና ጣፋጭ የሆነን ምግብ ብሉ:: የሰይጣንንም ዱካዎች (እርምጃዎች) አትከተሉ:: እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና::"},{"id":169,"translation":"169. እርሱ የሚያዛችሁ በኃጢአትና በጸያፍ ነገርና በአላህ ላይ የማታውቁትን እንድትናገሩ ነው።"},{"id":170,"translation":"170. ለእነርሱም «አላህ ያወረደውን ተከተሉ በተባሉ ጊዜ የለም አባቶቻችንን በእርሱ ላይ ያገኘንበትን ነገር ብቻ እንከተላለን» ይላሉ:: አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና ወደ እውነት የማይመሩም ቢሆኑ ይከተሏቸዋልን?"},{"id":171,"translation":"171. የእነዚያም በአላህ የካዱት ምሳሌ ልክ እንደዚያ ድምጽንና ጥሪን እንጂ ሌላን በማይሰማ እንሰሳ ላይ እንደሚጮህ (እረኛ) ብጤ ነው:: እነርሱ (እውነትን የማይሰሙ) ደንቆሮዎች፤ (ሐቅን የማይናገሩ) ዲዳዎች፤ (ትክክለኛውን መንገድ የማያዩ) እውሮች ናቸው:: ምንንም ነገር የሚገነዘቡ አይደሉም::"},{"id":172,"translation":"172. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሰጠናችሁ ሲሳዮች መካከል ጥሩውን ተመገቡ:: አላህንም በብቸኝነት የምታመልኩት ከሆናችሁ እሱኑ ብቻ አመስግኑት::"},{"id":173,"translation":"173. (አላህ) በእናንተ ላይ እርም ያደረገባችሁ በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ስጋንና ከአላህ ሌላ በሆነ ስም የታረደን ስጋ ብቻ ነው:: ተገዶ ችግሩን ለማስወገድ ያክል ብቻ ሽፍታና ወሰን አላፊ ሳይሆን (ቢመገብ) በእርሱ ላይ ምንም ሀጢአት የለበትም:: አላህ መሐሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":174,"translation":"174. እነዚያ አላህ ካወረደው መጽሐፍ (የትኛውንም ክፍል) የሚደብቁ፤ በሱ (በደበቁትም) ጥቂትን ዋጋ የሚለውጡ፤ በሆዶቻቸው ውስጥ እሳትን እንጂ አይበሉም:: አላህም በትንሳኤ ቀን አያናግራቸዉም:: ከኃጢአትም አያጠራቸዉምም:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":175,"translation":"175. እነዚህ እነዚያ ስህተትን በቅንነት ቅጣትንም በምህረት የለወጡ ናቸው:: በእሳት ላይ ምን ታጋሽ አደረጋቸው?!"},{"id":176,"translation":"176. ይህም አላህ መጽሐፍን በእውነት ያወረደ በመሆኑና (በእርሱም በመካዳቸው ነው):: እነዚያም በመጽሐፉ የተለያዩት ከእውነት በራቀ ውዝግብ ውስጥ ናቸው::"},{"id":177,"translation":"177. መልካምነት ፊቶቻችሁን ወደ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞራችሁ አይደለም። መልካምነት በአላህ፣ በመጨረሻው ቀን፣ በመላዕክት፣ በመጸሐፍት በነብያት ያመነ፤ ገንዘብንም ምንም ያህል የነዋይ (ገንዘብ) ፍቅር ቢኖረዉም ለዝምድና ባለቤቶች፣ ለየቲሞች፣ ለሚስኪኖች፣ ለመንገደኞች፣ ለለማኞች፣ ባሪያዎችን ነፃ ለማውጣት የሰጠ፤ ሶላትን ደንቡን ጠብቆ የሰገደና ዘካንም ያወጣ ነው:: እንዲሁም ቃልኪዳን በገቡ ጊዜም ቃልኪዳናቸውን የሚሞሉ በችግር፣ በበሽታና በፍልሚያ ጊዜ ታጋሾች ናቸው። እነዚህ እነዚያ እውነትን የያዙ መሆናቸውን በተግባር አረጋግጠዋል:: አላህን የሚፈሩም ናቸው።"},{"id":178,"translation":"178. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ግድያን በተመለከተ አጸፋዊ እርምጃ በእናንተ ላይ ተደንግጓል:: (እርሱም) ነፃ ሰውን በነፃ መግደል፤ ባሪያን በባሪያ መግደል፤ ሴትን በሴት መግደል::(ነው) ከሟች ወንድሙ ደም ትንሽ ነገር እንኳን ምህረት የተደረገለት ሰው በመሃሪው የሟች ወገን ላይ ካሳውን በመልካም መከታተል ሲኖርበት ምህረት የተደረገለት ገዳይም የነፍስ ዋጋውን ለእርሱ በመልካም አኳኋን መክፈል አለበት:: ይህ ከጌታችሁ የሆነ ማቃለልና እዝነት ነው:: ከዚህም በኋላ ህግን የተላለፈ ሰው እርሱ አሳማሚ ቅጣት ይጸናበታል::"},{"id":179,"translation":"179. እናንተ ባለ አእምሮዎች ሆይ! በአጸፋዊ እርምጃ ህግ ሕይወትን ትጎናጸፋላችሁ:: ይህም ግድያን ከመፈጸም ልትጠነቀቁ ዘንድ ነው።"},{"id":180,"translation":"180. በማንኛዉም ላይ ሞት በመጣበት ጊዜና ቀሪ ሀብት ያለው እንደሆነ ለወላጆችና ለቅርብ ዘመዶች በአግባቡ መናዘዝ በእናንተ ላይ ተደንግጓል:: ይህ አላህን በሚፈሩ ላይ መፈጸም ያለበት ግዴታ ነው::"},{"id":181,"translation":"181. (ኑዛዜውን) ከሰማው በኋላ የለወጠው ኃጢአቱ በእነዚያ በሚለውጡት ላይ ብቻ ነው:: አላህም ሁሉን ሰሚ ሁሉን አዋቂ ነውና::"},{"id":182,"translation":"182. ከተናዛዥም በኩል (ከእውነት) መዘንበልን ወይም (ከሲሶ የመጨመር) ኃጢአትን የፈራ (ያወቀ) ከዚያም በመካከላቸው ያስታረቀ በእርሱ ላይ ምንም ኃጢአት የለበትም:: አላህ በጣም መሀሪና በጣም አዛኝ ነውና።"},{"id":183,"translation":"183. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ፆም በእነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ ግዴታነቱ እንደተፃፈ ሁሉ በእናንተም ላይ ተደነገገ:: ልትጠነቀቁ ይከጀላልና።"},{"id":184,"translation":"184. ውስን ቀናትን ጹሙ። ከናንተም ውስጥ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው ባልፆማቸው ቀናት ልክ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸውን ቀናት መፆም አለበት:: እነዚያ ለመፆም ከአቅም በላይ ችግር የገጠማቸው ሰዎች ደግሞ አፍጥረው ለየቀኑ እንድ ድሃን የአንድ ጊዜ ምግብ ማብላት ይኖርባቸዋል:: ከዚህ በላይ ቤዛን በመጨመር መልካምንም ስራ የፈቀደ ሰው (እርሱ ፈቅዶ መጨመሩ ለራሱ) በላጭ ተግባር ነው:: ግና በመንገድ ላይ ሆናችሁ መፆማቸሁ ለእናንተ የበለጠ ነው:: የምታውቁ ብትሆኑ ትመርጡታላችሁ::"},{"id":185,"translation":"185. (ያ እንድትጾሙት የተደነገገላችሁ ወር) በእርሱ ዉስጥ ለሰዎች መሪ ሐቅን መንገድና እውነትን ከዉሸት የሚለየው ገላጭ ቁርአን የተወረደበት የረመዷን ወር ነው:: ከናንተ መካከል ወሩን ያገኘ ሁሉ ይጹመው:: በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው ካፈጠረ ከሌሎች ቀናት ባልፆማቸው ቀናት ቁጥሮች ልክ መፆም አለበት:: አላህ ሁልጊዜም ለእናንተ ገሩን ነገር ይሻል እንጂ በእናንተ ላይ ጫናን መፍጠርን አይሻምና ነው። ለፆም የተወሰኑትን ቀናት ልትሞሉና አላህን ቅንኑ መንገድ ስለመራችሁ ልታከብሩትና ልታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገገላችሁ)"},{"id":186,"translation":"186. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባሮቼ ስለ እኔ በጠየቁህ ጊዜ እኔ ቅርብ ነኝ:: የለማኝን ጸሎትም በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ:: ስለዚህ ወደ ቀናው መንገድ ይመሩ ዘንድ ለእኔ ብቻ ይታዘዙ:: በእኔም ብቻ ይመኑ። (በላቸው።)"},{"id":187,"translation":"187. (ሙስሊሞች ሆይ!) በፆም ሌሊት ከሚስቶቻችሁ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ተፈቀደላችሁ:: እነርሱ ለእናንተ ልብሶች ናቸው:: እናንተም ለእነርሱ ልብሶች ናችሁና:: አላህ በዚህ ረገድ ነፍሶቻችሁን በማታለል ላይ መሆናችሁን ያውቃል::በእናንተም ላይ ተመለሰላችሁ፡፡ ከእናንተም ይቅርታ አደረገ፡፡ አሁን ተገናኙዋቸው፡፡ አላህም ለናንተ የጻፈላችሁን ነገር (ልጅን) ፈልጉ፡፡ ነጩ የንጋት ገመድ ከጥቁሩ የሌሊት ገመድ ለእናንተ እስከሚገለጽላችሁ ድረስ ብሉ:: ጠጡም:: ከዚያም ፆምን እስከ ሌሊቱ ድረስ ሙሉ:: እናንተ በመስጊዶች ተቀማጮች ኢዕቲካፍ ላይ ስትሆኑ ግን ሚስቶቻችሁን አትገናኙዋቸው:: ይህች የአላህ ህግጋት ናትና ለመተላለፍ አትቅረቧት:: ልክ እንደዚሁ አላህ አናቅጽን ለሰዎች ያብራራል:: እነርሱ የተከለከሉትን ሊጠነቀቁ ይከጅላልና::"},{"id":188,"translation":"188. ገንዘቦቻችሁንም በመካከላችሁ በከንቱ (ያለ አግባብ) አትብሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትኾኑ ከሰዎች ገንዘቦች ከፊልን በኃጢኣት ትበሉ ዘንድ ወደ ዳኞች አትጣሏት፡፡"},{"id":189,"translation":"189. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለለጋ ጨረቃ መለዋወጥ ይጠይቁሃል። «ይህ ክስተት ሰዎች ጊዜን ለመለካት የሚጠቀሙበትና የሐጅንም ወቅት ለማወቅ የሚረዳ ምልክት ነው:: መልካም ስራ ቤቶችን ከጀርባዎቻቸው መግባታችሁ አይደለም:: ይልቁንም የመልካም ስራ ባለቤት አላህን የሚፈራው ነው:: ቤቶችንም በፊት በሮቻቸው በኩል ግቡ:: አላህንም ፍሩ ከጀሀነም ቅጣት ልትድኑ ዘንድ።» በላቸው።"},{"id":190,"translation":"190. (ትክክለኛ አማኞች ሆይ!) እነዚያን የሚጋደሏችሁን ከሓዲያን በአላህ መንገድ ተጋደሉ:: ነገር ግን ድንበር አትለፉ :: አላህ ድንበር አላፊዎችን አይወድምና፡፡"},{"id":191,"translation":"191. ባገኛችኃቸዉም ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው:: ካስወጧችሁም ስፍራ አስወጧቸው:: ፈተና (ሁክት) ከመግደል የከፋ ነውና:: በተከበረው መስጊድም ዘንድ በእርሱ ውስጥ እስከሚጋደሏችሁ ድረስ በእርሱ ውስጥ አትጋደሏቸው:: ከተጋደሏችሁ ግን ግደሏቸው:: የከሓዲያን ቅጣት ልክ እንደዚህ ነው።"},{"id":192,"translation":"192. ከውጊያ ከታቀቡ ግን አላህ መሀሪና አዛኝ ነው፡፡"},{"id":193,"translation":"193. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ፈተና (ሁከት) እስኪወገድና ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስኪሆን ድረስ ተጋደሏቸው:: ከታቀቡ ግን የሀይል እርምጃ ድንበርን ባለፉ ላይ እንጂ (በሰላማዊ ላይ) አይጸናም::"},{"id":194,"translation":"194. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የተከበረው ወር በተከበረው ወር አንፃር ነው::ክብሮችም ሁሉ ተመሳሳዮች ናቸው፡፡ (ፍትሃዊ አጸፋዊ እርምጃ የተከበረን ህግ በጣሱ ላይ ተደንግጓል):: ወሰን ያለፈባችሁን በእናንተ ወሰን ባለፈው ቢጤ ወሰን ያለፈውን ያህል በእርሱም ላይ ወሰን እለፉበት:: አላህንም ፍሩ:: አላህ እርሱን ከሚፈሩት ጋር መሆኑንም እወቁ::"},{"id":195,"translation":"195. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በአላህ መንገድ ላይ ለግሱ:: ራሳችሁንም በገዛ እጃችሁ ለጥፋት አትዳርጉ:: በበጎ ስራም ላይ ጽኑ:: አላህ በጎ ሰሪዎችን ሁሉ ይወዳልና።"},{"id":196,"translation":"196. ሐጅንና ዑምራን ለአላህ ብቻ ብላችሁ በትክክል ፈጽሙ:: ከጀመራችሁ በኋላ ብትታጉዱም ከመስዋአት የቻላችሁትን መሰዋት አለባችሁ:: መስዋእቱ ከመታረጃው ስፍራ እስኪደርስ ድረስም ራሶቻችሁን አትላጩ:: ከናንተም ውስጥ በሐጅ ላይ ሁኖ የታመመ ወይም በራስ ቅሉ ላይ ጉዳት የደረሰበት ሰው ቢላጭ ከመፆም ወይም መስዋዕትን ቤዛ መስጠት አለበት:: ጸጥታም ባገኛችሁ ጊዜ እስከ ሐጅ መፈጸሚያ ቀን ድረስ በዑምራ አስቀድሞ በመፈጸም የተገላገለ ሰው ከመስዋእቱ የተገራውን (የቻለዉን) መሰዋት አለበት:: ያላገኘም ሰው ሶስትን ቀናት በሐጅ (ወራት) ላይ ሰባትንም ቀናት ደግሞ በተመለሳችሁ ጊዜ መፆም አለበት:: እነዚህ ሙሉ አስር (ቀናት) ናቸው:: ይህም (ህግ) ቤተሰቦቹ ከቅዱሱ መስጊድ አቅራቢያ ላልሆኑ ነው:: አላህንም ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ መሆኑንም እወቁ።"},{"id":197,"translation":"197. ሐጅ የሚፈጸመው በተወሰኑ የታወቁ ወራት ነው:: እናም በእነርሱ ውስጥ ሐጅን ለመስራት ግዴታ የገባ ሰው በሐጅ ክንውን ውስጥ እያለ ሴትን መገናኘት፤ በአላህ ላይ ማመጽና ክርክር አያደርግም:: (ሙስሊሞች ሆይ!)የምትሰሩትን ሁሉ አላህ ያውቀዋል። ስንቅም ያዙ:: ከስንቅ ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው:: የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! እኔን ብቻ ፍሩኝ።"},{"id":198,"translation":"198. በሐጅ ጊዜ (በስራ) ከጌታችሁ ችሮታን በመፈለጋችሁ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: ከአረፋት በተንቀሳቀሳችሁም ጊዜ መሸዐረል ሀራም ዘንድ ስትደርሱ አላህን አውሱ:: ወደ ቀናው የኢስላም መንገድ ስለመራችሁም አውሱት:: ቀደም ሲል በእርግጥ ከተሳሳቾች ነበራችሁ።"},{"id":199,"translation":"199. ከዚያ ሰዎች ከተንቀሳቀሱበት ስፍራ ተንቀሳቀሱ :: የአላህንም ምህረት ለምኑ:: አላህ በእጅጉ መሀሪና አዛኝ ነውና፡፡"},{"id":200,"translation":"200. የሐጅ ስራዎቻችሁን በፈጸማችሁ ጊዜ አባቶቻችሁን እንደምታወሱ ወይም ከእርሱም ይበልጥ በበረታ አላህን አውሱ:: ከሰዎችም መካከል፡- «ጌታችን ሆይ! በምድረ ዓለም መልካም እድልን ስጠን።» የሚል ሰው አለ:: ለእርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ምንም ድርሻ የለዉም::"},{"id":201,"translation":"201. ከእነርሱም መካከል «ጌታችን ሆይ! በምድር ዓለም ደግን ነገር (ጸጋን) በመጨረሻይቱ ሀገርም ደግን ነገር (ገነትን) ስጠን:: ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን።» የሚሉ አሉ።"},{"id":202,"translation":"202. እነዚያ ከሰሩት በጎ ስራ ድርሻ አላቸው:: አላህም ምርመራው ፈጣን ነው፡፡"},{"id":203,"translation":"203. (ሙስሊሞች ሆይ!) በእነዚያ በተወሰኑ ቀናት ውስጥ አላህን አውሱ:: በሁለት ቀናት ውስጥ ለመሄድ የተቻኮለ ሰው በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም:: የቆየም ሰው ኃጢአት የለበትም:: ይህም (ምህረት) አላህን ለፈራ ሰው ሁሉ ነው:: አላህንም ፍሩ:: እናንተ ወደ እርሱ የምትሰበሰቡ መሆናችሁንም እወቁ::"},{"id":204,"translation":"204. ከሰዎችም መካከል እርሱ ክርክረ ብርቱ ሲሆን በቅርቢቱ ሕይወት ንግግሩ የሚያስደስትህ (የሚደንቅህ) ፤ በልቡ ውስጥ በሚያጠነጥነውም አላህን የሚያስመሰክር ሰው አለ።"},{"id":205,"translation":"205. (ካንተ) በዞረ ጊዜ በውስጧ ሊያበላሽና አዝመራንና እንሰሳዎችን ሊያጠፋ በምድር ላይ ይሮጣል:: አላህም ጥፋትን አይወድም፡፡"},{"id":206,"translation":"206. ለእርሱ “አላህን ፍራ” በተባለም ጊዜ ትዕቢት (በኃጢአት ስራ ላይ) ይገፋፋዋል። ገሀነምም ለእሱ በቂው ናት:: እርሷም በእርግጥ የከፋች ምንጣፍ ናት::"},{"id":207,"translation":"207. ከሰዎችም ውስጥ የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲል ነፍሱን የሚሸጥም ሰው አለ:: አላህም ለባሮቹ በጣም ሩህሩህ ነው።"},{"id":208,"translation":"208. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም ወደ አላህ መንገድ እስልምና ጠቅልላችሁ ግቡ:: የሰይጣንን እርምጃዎችም አትከተሉ፤ እርሱም ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና።"},{"id":209,"translation":"209. ግልጽ ማስረጃዎች ከመጡላችሁ በኋላ እውነትን ከመቀበል ብታፈገፍጉ አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ መሆኑን እወቁ።"},{"id":210,"translation":"210. አላህ በዳመና ጥላዎች ዉሥጥ ሆኖ እና መላዕክቱ ከያቅጣጫው ወደ እነርሱ እንዲመጡና ጉዳዩ እንዲወሰን እንጂ ሌላ ምንን ይጠባበቃሉ:: ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ።"},{"id":211,"translation":"211. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የኢስራኢል ልጆችን ምን ያህል ግልጽ ተዐምር እንደሰጣናቸው ጠይቃቸው:: የአላህን ጸጋ ከመጣለት በኋላ ለሚለውጥ (ሰው አላህ ይቀጠዋል) አላህ ቅጣተ ብርቱ ነው።"},{"id":212,"translation":"212. ለእነዚያ ለካዱት ባመኑት የሚሳለቁ ሲሆኑ ቅርቢቱ ሕይወት ተሸለመችላቸው:: እነዚያ አላህን የሚፈሩት በትንሳኤ ቀን ከበላያቸው ናቸው:: አላህም ለፈለገው ገጸ በረከቱን ያለገደብ ይሰጣልና::"},{"id":213,"translation":"213. ሰዎች ሁሉ (አላህን አንድ በማድረግ) አንድ ሕዝብ ነበሩ:: (ከዚያም ተለያዩ):: ከዚያም አላህ ነብያትን ለመልካም ሰዎች በገነት አብሳሪዎችና ለመጥፎ ሰዎች ደግሞ ከእሳት አስጠንቃቂዎች አድርጎ ላከ:: ከነሱ ጋርም ከሰዎቹ መካከል በዚያ እነርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ መጽሐፍትን በእውነት አወረደ:: በእርሱ ግልጽ አስረጂዎች ከመጡላቸው በኋላ በመካከላቸው በተፈጠረው ምቀኝነት ሰበብ እነዚያው መጽሐፍትን የተሰጡት ሰዎች እንጂ አልተለያዩበትም:: አላህ እነዚያን በአላህ ያመኑትን ሰዎች በእነርሱ የተለያዩበትን እውነታ ይገነዘቡ ዘንድ በፈቃዱ መራቸው:: አላህ የሚሻውን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል።"},{"id":214,"translation":"214. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት አማኞችን ያጋጠመ መከራ የመሰለ ሳይመጣባችሁ ገነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? መልዕክተኛውና እነዚያ ከእርሱ ጋር ያመኑት «የአላህ እርዳታ መቼ ነው?» እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ደረሰባቸው:: ተርበደበዱም። (ሙስሊሞች ሆይ! ) አስተውሉ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው (አልናቸው)።"},{"id":215,"translation":"215. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምንን እንደሚለግሱ ይጠይቁሃል። «ከየትኛዉም ሀብት የምትለግሱት ለወላጆች፣ ለቅርብ ዘመዶች፣ ለየቲሞች፣ ለድሆችና ለመንገደኞች (ሊሆን ይገባል።) ከበጎ ነገርም ማንኛውንም ብትሰሩ አላህ እርሱን አዋቂ ነው።»በላቸው፡፡"},{"id":216,"translation":"216. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከሓዲያንን መጋደል በእናንተ ዘንድ የሚጠላ ቢሆንም በእናንተ ላይ በግዴታነት ተደነገገ:: አንድ ነገር ለእናንተ ጥሩ ቢሆንም ምናልባት ትጠሉት ይሆናል:: አንድንም ነገር እርሱ ለእናንተ መጥፎ ሆኖ እያለ ትወዱት ይሆናል:: አላህም የሚሻላችሁን ያውቃል:: እናንተ ግን አታውቁም::"},{"id":217,"translation":"217. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በተከበረው ወር ስለመጋደል ይጠይቁሃል። «በእነርሱ ውስጥ መጋደል ትልቅ ኃጢአት ነው:: ግን ከአላህ መንገድ ሰዎችን መከልከል፤ በእርሱም መካድ፤ ከተከበረው መስጊድ ማገድ፤ ባለቤቶቹንም ከእርሱ ማፈናቀል አላህ ዘንድ ይበልጥ የተለቀ ወንጀል ነው:: ፈተናም (በአላህ ማጋራትም) ከመግደል ይበልጥ ከባድ ነው» በላቸው። ከሓዲያን ቢችሉ ከሃይማኖታችሁ እስኪመልሷችሁ ድረስ የሚዋጓችሁ ከመሆን አይቦዝኑም:: ከናንተ ውስጥ ከሀይማኖቱ የሚመለስና እርሱ ከሃዲ ሆኖ የሚሞት ሁሉ እነዚያ በቅርቢቱ ሀገርም ሆነ በመጨረሻይቱ ሀገር በጎ ስራቸው ተበላሸች:: እነዚህ የእሳት ጓዶች ናቸው:: በእርሷም ውስጥ ለዘላለም ይዝወትራሉ።"},{"id":218,"translation":"218. እነዚያ ያመኑና ከሀገራቸው የተሰደዱ፤ በአላህ መንገድ ላይም የተጋደሉ፤ እነዚያ የአላህን እዝነት ይከጅላሉ:: አላህም እጅግ መሀሪና አዛኝ ነውና፡፡"},{"id":219,"translation":"219. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አዕምሮን ስለሚያሰክር መጠጥና ስለ ቁማር ይጠይቁሃል:: «በሁለቱም ትልቅ ኃጢአትነትና ለሰዎችም ጥቅም አለባቸው:: ኃጢአታቸው ግን ከጥቅማቸው በጣም የገዘፈ ነው።» በላቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምንን እንደሚመጸውቱም (መጠኑን) ይጠይቁሀል:: «የተረፋችሁን መጽውቱ።» በላቸው:: እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡"},{"id":220,"translation":"220. በዱኒያም በአኼራም ታስተነትኑ ዘንድ ይገልፅላችኃል። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለየቲሞችም ይጠይቁሀል:: «የእነርሱን ሁኔታ ማሻሻል በላጭ ነው:: የእነርሱ ጉዳይ ከናንተ ጋር ብትቀላቅሉም ወንድሞቻችሁ ናቸው:: አላህም አጥፊውን ከአልሚው ለይቶ ያውቃል:: አላህም በፈለገ ኖሮ መፈናፈኛ ያሳጣችሁ (ባስቸገራችሁ) ነበር:: አላህ በሁሉም ነገር አሸናፊና ጥበበኛ ነው በላቸው::"},{"id":221,"translation":"221. (ሙስሊሞች ሆይ!) አጋሪዎችን ሴቶችን በአላህ እስከሚያምኑ ድረስ አታግቧቸው:: አጋሪይቱ ነፃ ሴት ምንም ብትስባችሁ እንኳ ያመነችው ባሪያ ሴት በእርግጥ ለእናንተ በላጭ ናት:: ለአጋሪዎቹ እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው:: ከአጋሪ ወንድ ምንም ቢስባችሁ አማኝ ባሪያዎች ለእናንተ በላጭ ናቸው:: እነዚያ አጋሪዎች ወደ እሳት ይጠራሉ:: አላህ ደግሞ ወደ ገነትና ወደ ምህረት ይጠራል:: ህግጋቱንም ለሰዎች ሊገሰጹ ዘንድ ይገልፅላቸዋል፡፡"},{"id":222,"translation":"222. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለ ሴቶች የወር አበባ ይጠይቁሃል:: «እርሱ ጎጂ (አጸያፊ) ነው። እናም ሚስቶቻችሁን በወር አበባቸው ጊዜ ራቁዋቸው፤ ደሙ ቆሞ ንጹህ እስከሚሆኑ ድረስ ለግንኙነት በፍጹም አትቅረቧቸው:: ንጹህ በሆኑ ጊዜም አላህ ባዘዛችሁ ቦታ ተገናኟቸው:: አላህ ከኃጢአት ተመላሾችንና ንጽህናን የሚጠብቁትን ይወዳልና።» በላቸው::"},{"id":223,"translation":"223. ሚስቶቻችሁ ለእናንተ እርሻ ናቸው:: እናም እርሻዎቻችሁን በፈለጋችሁት ሁኔታ ግንኙነት ፈጽሙ:: ለነፍሶቻችሁ መልካም ስራን አስቀድሙ:: አላህንም ፍሩ:: እናንተም ከእርሱ ጋር የምትገናኙ መሆናችሁን እውቁ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማኞችንም በገነት አብስራቸው::"},{"id":224,"translation":"224. (ሙስሊሞች ሆይ!) በአላህ ስም የፈጸማችሁት መሀላ በጎ ከመዋል አላህን ከመፍራትም ወይም በሰዎች መካከል እርቀ ሰላም ከማውረድ ግርዶ አታድርጉ:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነውና::"},{"id":225,"translation":"225. ያለ አስተውሎት በምትፈጽሙት መሐላዎቻችሁ አላህ አይቀጣችሁም:: ግን ልቦቻችሁ በጽኑ ባሰቡበት መሐላዎቻችሁ ይይዛችኋል:: አላህ በጣም መሀሪ፤ ታጋሽ ነውና::"},{"id":226,"translation":"226. እነዚያ ሚስቶቻቸውን ላለመገናኘት የሚምሉ ወንዶች ሁሉ ለማሰላሰያ ጊዜ አራት ወራት አላቸው:: እናም መሀላቸውን ቢያጥፉና ቢመለሱ አላህ መሀሪና አዛኝ ነው::"},{"id":227,"translation":"227. ፍችን ለመፈጸም ጽኑ ውሳኔ ላይ ከደረሱ ደግሞ (ይፋቱ):: አላህም ሁሉን ሰሚ ሁሉንም አዋቂ ነዉና::"},{"id":228,"translation":"228. የተፈቱ ሴቶችም በራሳቸው ሶስትን የወር አበባ ይጠብቁ። በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑ ከሆኑ አላህ በማህጸኖቻቸው ውስጥ የፈጠረውን ጽንስ ሊደብቁ አይፈቀድላቸዉም:: ባሎቻቸዉም እርቅን ከፈለጉ በእነዚህ ወራት ውስጥ የመመለስ መብታቸው ቅድሚያ ነው:: ለሴቶች ግዳጅ እንዳለባቸው ሁሉ ፍትሀዊ መብትም አላቸው:: ይሁንና ወንዶች (የበለጠ ሀላፊነትን ስለሚሸከሙ) ብልጫ አላቸው። (ተጥሎባቸዋል):: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":229,"translation":"229. የመመለስ እድል የሚሰጠው ፍቺ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው:: ከዚያም በመልካም መያዝ ወይም በበጎ አኳኋን ማሰናበት ነው:: (ባሎች ሆይ!) የአላህን ህግጋት ያለማክበር ስጋት ካልኖረባቸው በስተቀር ከሰጣችኋቸው ነገር ምንንም ልትወስዱ ለእናንተ አይፈቀድላችሁም:: የአላህን ሕግጋት አለመጠበቃቸውን ብትገነዘቡ ነፃ ለማውጣት በምትፈጽመው ነገር በሁለቱም ላይ ኃጢአት የለባቸዉም:: እኒህ የአላህ ሕግጋት ናቸው:: አትተላለፏቸው:: እነዚያ እነርሱ የአላህን ሕግጋት የሚተላለፉ ሁሉ (በደለኞች) አጥፊዎች ናቸው::"},{"id":230,"translation":"230. ከዚያም ለሶስተኛ ጊዜ ከፈታት በኋላ ሌላን ባል እስካላገባች (ከዚያም እስካልተፈታች ወይም እስካልሞተባት) ድረስ ለእርሱ አትፈቀደለትም:: ሁለተኛው ባል ከፈታት የአላህን ሕግጋት እንደሚጠብቁ ተስፋ ካደረጉ በመማለሳቸው በሁለቱም ላይ ኃጢኣት የለባቸውም:: እነኚህ የአላህ ሕግጋት ናቸው:: ለሚያውቁ ሕዝቦች ሁሉ ያብራራላቸዋል::"},{"id":231,"translation":"231. (ሙስሊሞች ሆይ!) ሚስቶቻችሁን በፈታችሁ እና የኢዳ ጊዜያቸውን ለማገባደድ በቀረቡ ጊዜ በመልካም መልሷቸው:: ወይም በመልካም ሁኔታ ያለ አንድ ጉዳት አሰናብቷቸው:: ለመጉዳትም ወሰን ታልፉባቸው ዘንድ አትያዟቸው:: ይህን የሚሰራም ነፍሱን በእርግጥ በደለ:: የአላህን አናቅጽ ማላገጫ አታድርጉ:: አላህ በእናንተ ላይ የዋለውን ጸጋ፤ በእርሱ ሊገስፃችሁም ያወረደውን መጽሐፍ (ቁርኣንን) እና ጥበብንም (ሱናን) አስታውሱ:: አላህንም ፍሩ:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ አዋቂ መሆኑንም እወቁ::"},{"id":232,"translation":"232. ሚስቶቻችሁን በፈታችሁ እና የኢዳ ጊዜያቸውን በጨረሱ ጊዜ ጥንዶቹ በመካከላቸው ሕጋዊና ፍትሀዊ የጋራ ስምምነት ላይ ከደረሱ ባሎቻቸውን ከማግባት አታስተጓጉሏቸው:: ይህ ከናንተ መካከል በአላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን ሁሉ ይገሰጽበታል:: ይህ ለእናንተ በላጭና አጥሪ ነው:: አላህ ያውቃል:: እናንተ ግን አታውቁም::"},{"id":233,"translation":"233. እናቶች ልጆቻቸውን ሁለት ሙሉ ዓመታትን ያጠባሉ:: ይህም ማጥባትን የተሟላ ለማድረግ ለፈለገ ሰው ነው:: በአባት ላይ ምግባቸውንና ልብሳቸውን የማቅረብ ግዴታ አለበት:: ማንም ነፍስ ከችሎታዋ በላይ አትገደድምና:: እናት በልጇ ምክኒያት ጉዳት እንዲደርስባት አይደረግም:: አባትም በልጁ ምክንያት እንዲንገላታ መሆን የለበትም:: በወራሽም ላይ የዚሁ ተመሳሳይ ሀላፊነት አለበት:: ወላጆቹ በመልካም ፈቃድ ልጁን ከጡት መነጠል (ማስጣል) ቢፈልጉ በሁለቱም መማከር በሁለቱም ላይ ኃጢአት የለባቸዉም:: ለልጆቻችሁ አጥቢዎችን ብትቀጥሩ ተስፋ የሰጣችሁትን ክፍያ በአግባቡ እስከሰጣችሁ ድረስ በማስጠባታችሁ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህን ፍሩ:: አላህ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች መሆኑን እወቁ፡፡"},{"id":234,"translation":"234. (ወንዶች ሆይ!) እነዚያ ከናንተ ውስጥ የሚሞቱና ሚስቶችን የሚተው ሚስቶቻቸው በራሳቸው አራት ወር ከአስር ቀናትን ከጋብቻ ይታገሱ:: ጊዜያቸውንም በጨረሱ ጊዜ በራሳቸው ተነሳሽነት በሚፈጽሙት ሕጋዊ ተግባር በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::"},{"id":235,"translation":"235. (ወንዶች ሆይ!) ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች የጋብቻ (አሽሙር) ፍንጭ በመስጠታችሁ ወይም እንዲህ ዓይነቱን ሀሳብ በውስጣችሁ በማሰባችሁ ምክንያት በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህ እናንተ በእርግጥ እንዲህ ዓይነቱን ሀሳብ እንደምታስተናግዱ ቀድሞውኑ ያውቃል:: ስለዚህ (አሽሙር) ፍንጭ መስጠትንና ማሰብን ፈቀደላችሁ:: ግና በሕግ የታወቀን ጨዋ ንግግር የምትነጋገሩ ካልሆናችሁ በስተቀር የተፃፈው የኢዳ ጊዜው እስከሚደርስ ድረስ ለትዳር እንደምትፈልጓቸው በሚስጥር ቃል አትግቡላቸው:: ጋብቻን ለመዋዋልም ቁርጥ ሀሳብ አታድርጉ:: አላህ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉን ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑን እወቁ:: ተጠንቀቁም፤ አላህ መሀሪና ታጋሽ መሆኑንም እወቁ::"},{"id":236,"translation":"236. (ባሎች ሆይ!) ሴቶችን ግንኙነት ከማድረግ በፊት ወይም ለእነርሱ መህርን ሳትወስኑላቸው ብትፈቷቸው በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም:: ነገር ግን ሀብታምም ደሃም እንደየአቅማቸው ይካሷቸው:: ይህ አቅምን መሰረት ያደረገ ካሳ በቅን ሰዎች ላይ የተደነገገ ህግ ነው::"},{"id":237,"translation":"237. (ባሎች ሆይ!) ለሚስቶቻችሁ መህርን የወሰናችሁላቸው ስትሆኑ ሳትገናኟቸው በፊት ብትፈቷቸው ራሳቸው ይቅር ካላሉ ወይም ያ የጋብቻ ውል በእጁ የሆነ ባል ካላግራራ በስተቀር ከወሰናችሁት ግማሹን መስጠት ግድ ሆኖባችኋል:: ሁላችሁም ይቅር መባባላችሁ ወደ አላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው:: አንዱ ለሌላው በጎ መዋልን አይዘንጋ:: አላህም የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::"},{"id":238,"translation":"238. (ሙስሊሞች ሆይ!) ሶላቶችን በተለይ መካከለኛይቱን ሶላት ወቅታቸውንና ስርዓታቸውን ጠብቃችሁ ስገዱ:: በሙሉ ታዛዥነትም ለአላህ ቁሙ::"},{"id":239,"translation":"239. (ሙስሊሞች ሆይ!) የደህንነት ስጋት ሲኖር በእግር እየሄዳችሁም ሆነ ተሳፍራች ስገዱ:: ሰላም ሲሰፍን በተለመደው ሥርዓት (ስገዱ።) ታውቁት ያልነበራችሁትን እንዳሳወቃችሁ ሁሉ አላህን በአግባቡ አውሱ (ስገዱ)::"},{"id":240,"translation":"240. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እነዚያ ከናንተ ውስጥ ሚስቶችን ትተው የሚሞቱ ሁሉ ለሚስቶቻቸው ከየቤቶቻቸው የማይወጡ ሆነው ሳለ ዓመት ድረስ ወጫቸው እንዲሸፈን መናዘዝ ይኖርባቸዋል:: ሚስቶች በፈቃዳቸው ከቤት ቢወጡ ግን ደንብ ጠብቀውና ኃላፊነትን ወስደው በሰሩት ጉዳይ ላይ በሟች ዘመዶች ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::"},{"id":241,"translation":"241. ለተፈቱ ሴቶች ሁሉ በፈችው ባል ችሎታ መጠን ዳረጎት (የገንዘብ ድጎማ) ይሰጣቸዋል:: ይህ አላህን በሚፈሩ ሰዎች ሁሉ ላይ ተደንግጓል::"},{"id":242,"translation":"242. ልክ እንደዚሁ አላህ አናቅጽን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ ያብራራላችኋል::"},{"id":243,"translation":"243. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብዙ ሺህ ሆነው ሞትን በመፍራት ከሀገሮቻቸው የወጡ ሰዎችን ታሪክ አላየህምን (አላወክምን?) አላህ ለእነርሱ «ሙቱ» አላቸው:: ሞቱም:: ከዚያ እንደገና ነፍስ ዘራባቸው:: አላህም ለሰዎች እጅግ ቸር ነው:: ይሁንና አብዛሀኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም::"},{"id":244,"translation":"244. (ሙስሊሞች ሆይ!) በአላህ መንገድ ላይ ተጋደሉ:: አላህ ሁሉን ሰሚ ሁሉንም አዋቂ መሆኑንም እወቁ::"},{"id":245,"translation":"245. ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና አላህም ብዙ እጥፍ ድርብ አድርጎ እንዲከፍለው የሚሻ ማን ነው? አላህ ለፈለገው ሰው ሲሳዩን ያጠብበታል፤ ለፈለገው ደግሞ ያሰፋለታልም:: ወደ እርሱ ብቻ ትመለሳላችሁ::"},{"id":246,"translation":"246. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከኢስራኢል ልጆች ከሙሳ ዘመን በኋላ ወደ ነበሩት የቤተ-ኢስራኢል ቅምጥሎች ተልኮላቸው ለነበረው ለነብያቸው «ለእኛ ንጉስን ሹምልን እና በአላህ መንገድ እንዋጋ።» ባሉ ጊዜ የሆነውን አላየህምን? እሱም «መዋጋት ቢፃፍባችሁ አትዋጉ ይሆናል።» አላቸው:: እነርሱም «ከአገሮቻችንና ከልጆቻችን ተባረን ሳለ በአላህ መንገድ የማንዋጋበት ምን ምክንያት አለን?» አሉ:: በእነርሱ ላይ መዋጋት በተፃፈባቸው ጊዜ ግን ከእነርሱ ጥቂቶች ሲቀሩ ከመዋጋት አፈገፈጉ:: አላህ አጥፊዎችን ሁሉ በሚገባ ያውቃቸዋል::"},{"id":247,"translation":"247. ነብያቸው ‹‹አላህ ጧሉትን ንጉስ አድርጎ በእርግጥ ላከላችሁ›› አላቸው:: እነርሱም፡- «ሰፊ ሀብትም ያልተሰጠ እኛም ከእርሱ ይልቅ ለንግስና ተገቢዎች ስንሆን እርሱ በእኛ ላይ እንዴት ይነግሣል?» አሉ:: ነብያቸዉም፡- «አላህ በእናንተ ላይ መረጠው እውቀትና የሰውነት ጥንካሬም አጎናጽፎታል:: አላህ ንግስናውን ለሚሻለት ሰው ይሰጣል:: አላህ ችሮታው ሰፊና አዋቂ ነው።» አላቸው።"},{"id":248,"translation":"248. በተጨማሪም ነብያቸው እንዲህ አላቸው:: «የንግስናው ምልክት መላእክት የሚሸከሙት ሳጥን ወደ እናንተ ይመጣል:: በውስጡ ለናንተ እርጋታን የሚፈጥርና የሙሳ እና የሀሩን ቤተሰብ የተውት ቅርስም ይገኝበታል:: በዚህም ውስጥ ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ ከባድ ተዐምር አለላችሁ።»"},{"id":249,"translation":"249. ጧሉትም በሰራዊቱ ታጅቦ በመጣ ጊዜ ‹‹አላህ በወንዝ ውሃ ይፈትናችኃል:: እናም ከእርሱ የጠጣ ሰው ሁሉ ከእኔ አይደለም:: እሱን ያልቀመሰው ሰው ግን በእጁ አንድ እፍኝ ያህል የዘገነ ሰው ብቻ ሲቀር እርሱ ከእኔ ነው›› አለ:: ከእነርሱም መካከል ጥቂቶች ሲቀሩ ከእርሱ ጠጡ:: እርሱና እነዚያ ከእርሱ ጋር ያመኑት ወንዙን ባለፉት ጊዜ፡- «ጃሉትን (ጎልያድን) እና ሰራዊቱን ለመዋጋት በቂ ችሎታና ጥንካሬ የለንም።» አሉት:: እነዚያ ከአላህ ጋር እንደሚገናኙ የሚያረጋግጡትም «ጥቂት ቡድን በአላህ ፈቃድ ብዙውን ቡድን ያሸነፈበት አጋጣሚ ብዙ ነው:: አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና።» አሉ።"},{"id":250,"translation":"250. ለጃሉትና ለሰራዊቱ በተሰለፉም ጊዜ፡- «ጌታችን ሆይ! ትግስትን ለግሰን:: እግሮቻችንን አጽናልን:: በከሓዲያን ሕዝቦችም ላይ እርዳን።» አሉ።"},{"id":251,"translation":"251. እናም በአላህ ፈቃድ ድል መቷቸው:: ነብዩ ዳውድም ጃሉትን ገደለ:: ለዳውድ ንግሥናን፤ ጥበብን እና ነብይነትን አላህ ሰጣቸው:: ከሚሻው ነገር ሁሉ አሳወቀው:: አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መመለሱ (መከላከሉ) ባልነበረ ኖሮ ምድር በጠቅላላ በተበላሸች ነበር:: ግን አላህ በዓለማት ላይ የችሮታ ባለቤት ነው::"},{"id":252,"translation":"252. እነዚህ አናቅጽ በእውነት ባንተ ላይ የምናነባቸው ሲሆኑ የአላህ አናቅጽ ናቸው:: አንተም በእርግጥ ከመልዕክተኞቹ መካከል አንዱ ነህ::"},{"id":253,"translation":"253. እነዚያን መልዕክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን:: ከእነርሱ መካከልም አላህ ያነጋገረው አለ:: ከፊሎቻቸውንም በደረጃ ከሌሎች ከፍ አድርጓል:: የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ተዐምራት ሰጠነው:: በቅዱስ መንፈስም (በመላኩ ጂብሪል) አበረታነው:: አላህ በፈለገ ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ በኋላ የነበሩት መረጃው ከመጣላቸው በኋላ እርስ በእርሳቸው ባልተዋጉ ነበር:: ግን ተለያዩ:: በመሆኑም ከመሀከላቸው ትክክለኛ አማኝ ክፍል አለ:: ከመሀከላቸዉም ከሃዲ አለ:: አላህ በፈለገ ኖሮ እርስ በእርሳቸው ባልተዋጉ ነበር:: አላህ ግን የሚሻውን ሁሉ ይሰራል::"},{"id":254,"translation":"254. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ያ ንግድ፤ ወዳጅነትም ሆነ ምልጃ የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ:: በዳዮች ማለት ከሓዲያን ናቸው::"},{"id":255,"translation":"255. አላህ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: አላህ ምንግዜም ሕያው፤ በራሱ የተብቃቃ ነው:: ማንጎላጀትም ሆነ እንቅልፍ አትይዘዉም:: በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: ያ እርሱ ዘንድ በፍቃዱ ቢሆን እንጂ የሚያማልድ ማን ነው? (ከፍጡራን) ሁሉ በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ጠንቅቆ ያውቃል:: በሻው ነገር እንጂ ከእውቀቱ (ፍጡራን) በምንም ነገር አያካብቡም:: መንበሩ የሰማያትንና የምድርን ስፋት ይበልጣል:: ጥበቃቸዉም አያቅተዉም:: እርሱ የሁሉ የበላይና ታላቅ ነው::"},{"id":256,"translation":"256. በሃይማኖት ማስገደድ የለም:: ቅኑ መንገድ ከጠማማው መንገድ በእርግጥ ተገለጠ:: በጣኦት (ባዕድ አምልኮ) የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ሁሉ የማትበጠስ ጠንካራ ገመድን ጨብጧል:: አላህ ሁሉን ሰሚ ሁሉንም አዋቂ ነውና።"},{"id":257,"translation":"257. አላህ የአማኞች ወዳጅ ነው:: ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል:: እነዚያ አላህን የካዱት ግን ረዳቶቻቸው ጣኦታት ናቸው:: ከብርሃን ወደ ጨለማ ይመሯቸዋል:: እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው::"},{"id":258,"translation":"258. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን አላህ ንግስናን ስለ ሰጠውና በጌታው ጉዳይ በኢብራሂም ላይ ክርክር ስለ ከፈተው ሰው (ታሪክ) መረጃ አላየህምን? ኢብራሂም፡-‹‹ጌታዬ ያ የፈለገውን ሕያው የሚያደርግና የፈለገውን የሚገድል ነው›› ሲለው «እኔም የፈለኩትን ህያው አደርጋለሁ፤ የፈለኩትን እገድላለሁ» አለ:: ኢብራሂምም፡- «አላህ ጸሐይን በምስራቅ በኩል ያወጣል:: እስኪ አንተ ከምዕራብ በኩል አምጣት» አለው:: ያም የካደ ሰው ዋለለ (መልስ አጣ):: አላህ ግፈኛ ሕዝቦችን ሁሉ አይመራምና::"},{"id":259,"translation":"259. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወይም ያንን ሙሉ በሙሉ በፈራረሰች ከተማ ያለፈውን ሰው ተሞክሮ አላገናዘብክምን? ‹‹ይህችን ከተማ ከሞተች በኃላ አላህ እንዴት ሕያው ያደርጋታል? አለ:: ከዚያ አላህ ገደለውና መቶ ዓመትን አቆየው:: ከዚያ አስነሳው «ምን ያህል ቆየህ?» አለው:: «አንድ ቀን ወይም የቀንን ከፊል ቆይቻለሁ» አለ:: «ይልቁንም መቶ ዓመት ነው የቆየኸው:: ወደ ምግብህና ወደ መጠጥህም ተመልከት:: አንዱም አልተለወጠም:: ወደ አህያህም ተመልከት:: ለሰው ልጅም ተዐምር ልናደርግህ ዘንድ ይህንን ሰራን፤ ወደ አጽሞቿም እንዴት እንደምናስነሳት ከዚያ ስጋን እንዴት እንደምናለብሳት ተመልከት።» አለው:: ለእርሱም ማስረጃ በገለጸለት ጊዜ ‹‹አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን አውቃለሁ›› አለ::"},{"id":260,"translation":"260. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም «ጌታዬ ሆይ! ሙታንን እንዴት ሕያው እንደምታደርግ እስቲ አሳየኝ» ባለ ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውስ:: አላህ፡- «አላመንክምን?» አለው:: ኢብራሂምም «በፍጹም (አይደለም) አምኛለሁ:: ግን ልቤ ሙሉ በሙሉ እንዲረጋጋ ነው።» አለው:: አላህም፡- «አራት ወፎችን ያዝና ወደ አንተ ሰብስባቸው:: ከዚያ ቆራርጣቸው:: ከዚያም በየኮረብታው ሁሉ ላይ ከእነርሱ ቁራጭ ቁራጭ አካላቸውን አስቀምጥ:: ከዚያም ጥራቸው በፍጥነት ወደ አንተ ይመጣሉ:: አላህ አሸናፊና ጥበበኛ መሆኑን እወቅ።» አለው::"},{"id":261,"translation":"261. እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ሰዎች ልግስና ምሳሌ በየዘለላው ሁሉ መቶ ቅንጣት ያለባቸውን ሰባት ዘለላዎች እንዳበቀለች አንዲት ፍሬ ምሳሌ ነው:: አላህ ለሚሻው ሁሉ አባዝቶ ይለግሳል:: አላህ ችሮታው ሰፊና አዋቂ ነውና::"},{"id":262,"translation":"262. እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ከዚያ በሰጡት ነገር መመፃደቅና ማስከፋት የማያስከትሉ ሁሉ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አለላቸው:: በእነርሱም ላይ ስጋትም የለባቸዉም። አይተክዙምም።"},{"id":263,"translation":"263. መልካም ንግግርና ይቅር ባይነት ብቻ ማስከፋት ከሚከተለው ምጽዋት በላጭ ነው:: አላህ በራሱ ተብቃቂና ታጋሽ ነውና::"},{"id":264,"translation":"264. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደ እነዚያ ገንዘብን ለሰዎች ለማሳየት ሲል እንደሚሰጠውና በአላህና በመጨረሻው ቀን እንደማያምነው ሰው ምጽዋቶቻችሁን በመመፃደቅና ተረጂውን በማስከፋት አታበላሹ:: የዚህ አይነቱም ድርጊት ምሳሌው በላዩ ላይ አፈር እንዳረፈበት ለስላሳ ድንጋይ ሲሆን እሱም ሀይለኛ ዝናብ አግኝቶት እንደተራቆተ ብጤ ነው:: እነኝህ አይነት ሰዎች ከሰሩት ነገር በምኑም ሊጠቀሙ አይችሉም:: አላህ ከሓዲያን ሕዝቦችን በፍጹም ወደ ቀናው መንገድ አይመራምና::"},{"id":265,"translation":"265. የእነዚያ የአላህን ውዴታ ለመፈለግና ከነፍሶቻቸው እምነትን ለማረጋገጥ ብለው ገንዘቦቻቸውን የሚለግሱት ምሳሌያቸው በተስተካከለች ከፍተኛ ቦታ ላይ እንዳለች አትክልት ሲሆን ይህች አትክልት ከፍተኛ ዝናብ አግኝታ እጥፍ ድርብ ምርት እንደሰጠች ከፍተኛ ዝናብ ባታገኝ እንኳን ካፊያ ብቻ እንደሚበቃት የአትክልት አይነት ይመስላል:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::"},{"id":266,"translation":"266. ከናንተ አንዳችሁ ሁሉን ዓይነት ምርት የምትሰጥ ከስሯ ወንዞች የምፈሱባት የዘንባባዎችና የወይኖች የአትክልት ቦታ ልትኖረው እርጅናም ሊነካውና በእነርሱም ደካሞች ረዳት የለሽ ህፃናት ያሉት ሲሆኑ በውስጡ እሳት ያለበት ውርጭ ምርቱ ላይ አደጋ ሊያደርስበት እና ልትቃጠልበት ይወዳልን? ልክ እንደዚሁ አላህ አናቅጽን ለእናንተ ያብራራል:: ልታስተነትኑ ይከጀላልና::"},{"id":267,"translation":"267. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ካፈራችሁትና ከዚያ ለእናንተ ከምድር ካወጣንላችሁ ከመልካሙ ለግሱ:: መጥፎውንም ለመስጠት አታስቡ:: እርሱን ለራሳችሁ አይኖቻችሁን ጨፍናችሁ እንጂ የማትወስዱት ስትሆኑ ከእርሱ (ከመጥፎ) ትሰጣላችሁን? አላህ ተብቃቂና ምስጉን መሆኑን እወቁ::"},{"id":268,"translation":"268. ሰይጣን እንዳትለግሱ በድህነት ያስፈራራችኋል:: በመጥፎም ያዛችኋል:: አላህ ከእርሱ የሆነን ምህረትና ችሮታን ሊያጎናጽፋችሁ ተስፋ ሰጥቷችኋል:: አላህ ችሮታው ሰፊና ሁሉን አዋቂ ነው::"},{"id":269,"translation":"269. አላህ ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል:: ጥበብንም የሚስ-ሰጥ ሰው ሁሉ ብዙ መልካም ነገርን በእርግጥ ተሰጥቷል:: የአዕምሮ ባለቤቶች እንጂ ሌላው አይገሰጽም::"},{"id":270,"translation":"270. ከምጽዋት ማንኛውንም የለገሳችሁትን ወይም ከስለት የተሳላችሁትን አላህ ጠንቅቆ ያውቀዋል:: ለበዳዮች (ግፈኞች) ሁሉ ምንም አይነት ረዳቶች የሏቸዉም::"},{"id":271,"translation":"271. ምጽዋቶችን ብትገልጹ እርሷ ምንኛ መልካም ተግባር ናት:: ብትደብቋትና ለድሆች ብትሰጧት እርሱ ለእናንተ በላጭ ነው:: ከኃጢአቶቻችሁ ከእናንተ ያብሳል:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::"},{"id":272,"translation":"272. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ማቅናት ባንተ ላይ ግዴታ የለብህም:: አላህ ግን የሚሻውን ሰው ያቀናል:: የምትለግሱት ገንዘብ ሁሉ ምንዳው ለነፍሶቻችሁ ብቻ ነው:: የአላህን ውዴታውን በመፈለግ እንጂ ምንንም አትለግሱ:: ከገንዘብም የምትለግሱት ሁሉ ምንዳው ወደ እናንተ ይሞላል:: እናንተም ቅንጣት ያህል አትበደሉም፡፡"},{"id":273,"translation":"273. (ምጽዋት የምትሰጡት ዘካና ልገሳ) ለእነዚያ በአላህ መንገድ በግል ሕይወታቸው ከመንቀሳቀስ (ለታገዱት) ፋታ ላጡ ድሆች ነው:: መሬት ውስጥ መጓዝ (ልመና) አይችሉም:: ከቁጥብነታቸው የተነሳ ውስጣቸውን የማያውቅ ሰው ሁሉ ሀብታሞች ናቸው ብሎ ይገምታቸዋል:: በምልክታቸው ታውቃቸዋለህ:: ሰዎችን በችክታ አይለምኑም:: ከገንዘብም የምትለግሱትን ሁሉ አላህ ሁሉን አዋቂ ነው፡፡"},{"id":274,"translation":"274. እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በሌሊትና በቀን በድብቅም ሆነ በግልጽ የሚለግሱ ሰዎች ሁሉ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ዋጋቸው ይስ-ሰጣቸዋል:: በእነርሱም ላይ ምንም ይደርስብናል ብለው ፍርሀት የለባቸዉም:: ምንም ነገር ያመልጠናል ብለው አያዝኑም፡፡"},{"id":275,"translation":"275. እነዚያ አራጣን የሚበሉ ሁሉ ያ ሰይጣን ሰፍኖበት ራሱን የሚስት ሰው ከአውድቅቱ እንደሚነሳ አይነት ሁነው እንጂ ከመቃብራቸው አይነሱም:: ይህም የሆነው እነርሱ መሸጥ ልክ እንደ አራጣ ነው በማለታቸው ነው:: አላህ ግን መሸጥን ፈቅዷል:: አራጣን እርም አድርጓል:: ከጌታው ግሳጼ የመጣለት እና ከዚያ የተከለከለ ሰው ሁሉ ከዚህ አዋጅ በፊት ያካበተውን እንደያዘ መቆየት ይችላል:: የወደፊት እጣፈንታው ወደ አላህ ነው:: አራጣን ወደ መብላት የተመለሱ ሰዎች እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘወታሪዎች ናቸው::"},{"id":276,"translation":"276. አላህ የአራጣን ገንዘብ ያከስማል (በረከቱን ያጠፋል):: መልካም ልገሳዎችን ያፋፋል:: አላህም ኃጢአተኛንና ከሓዲን ሁሉ አይወድምና፡፡"},{"id":277,"translation":"277. እነዚያ ያመኑና መልካም ስራዎችንም የሰሩ፤ ሶላትን አስተካክለው የሰገዱና ዘካንም የሰጡ እነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፤ በእነርሱም ላይ ምንም ይደርስብናል ብለው ፍርሀት የለባቸዉም:: ምንም ነገር ያመልጠናል ብለው አያዝኑምም::"},{"id":278,"translation":"278. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ:: ከአራጣም የቀረውን አትውሰዱ:: ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ (ተጠንቀቁ)::"},{"id":279,"translation":"279. የታዘዛችሁትን ባትሰሩ ከአላህና ከመልዕክተኛ ጦርነት ታውጆባችኋል:: ከወለዳዊ ድርጊታችሁ ብትታቀቡ ግን አንጡራ ገንዘባችሁ ለእናንተው እንደተጠበቀ ነው:: ሌሎችን አትበድሉም አትበደሉምም::"},{"id":280,"translation":"280. የድህነት ባለቤት ባለዕዳ ሰው ቢኖር ገንዘብ እስኪያገኝ ድረስ ማቆየት ነው:: (የእፎይታ ጊዜ ይሰጠው) ስጡት:: እዳውን በበጎ አድራጊነት ሙሉ በሙሉ ብትሰርዙለትም ለእናንተ በላጭ ነው። የምታውቁ ብትሆኑ (ትሰሩታላችሁ)::"},{"id":281,"translation":"281. ያን ወደ አላህ የምትመለሱበትን ቀን ፍሩ:: ሁሉም ነፍስ ያኔ ከሰራቸው አኳያ ዋጋዋን ታገኛለች:: በዚያ ዕለት (በሱ ዉስጥ) ተበዳይ ወገኖች ፈጽሞ አይኖሩም::"},{"id":282,"translation":"282. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ በእዳ በተዋዋላችሁ ጊዜ ፃፉት:: ጸሐፊዉም በመካከላችሁ በትክከል ይፃፍ:: ጸሐፊም አላህ ልክ እንዳሳወቀው መፃፍን ለመፃፍ እንቢ አይበል:: ይፃፍም:: ያም በእርሱ ላይ እዳ ያለበት ሰው በቃሉ ያለበትን እዳ ያስጽፍ:: ጌታውን አላህን ይፍራ:: ካለበት እዳ ምንም አያጉድል:: ያም በእርሱ ላይ እዳው ያለበት የአእምሮም ሆነ የአካል መታወክ ካለበት ወይም በቃሉ ማስፃፍን የማይችል ከሆነ ወኪሉ በትክክል ያስጽፍለት:: ከወንዶቻችሁ ሁለትን ምስክሮች አስመስክሩ:: ሁለትም ወንዶች በስፍራው ካልተገኙ ግን ለምስክርነት በቂ የሆነ አንድ ወንድና አንደኛዋ ስትረሳ አንደኛይቱ ሌላዋን ታስታውሳት ዘንድ ሁለት ሴቶች ይመስክሩ:: ምስክሮችም በተጠሩ ጌዜ ከመመስከር እንቢ አይበሉ:: (እዳው) ትንሽ ወይም ትልቅ ቢሆንም እስከጊዜው ድረስ ከመፃፍ አትሰልቹ:: ይህ አላህ ዘንድ በጣም ትክክል ለምስክርነቱም ተዐማኒነት የሚያጎናጽፍ ጥርጣሬንም ለማስወገድ በጣም የተመቸ አሰራር ነው:: በመካከላችሁ እጅ በእጅ በምትለዋወጡት ንግድ ላይ ግን ባትጽፏት በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም:: በተሻሻጣቸሁ ጊዜ አስመስክሩ:: ጸሐፊም ሆነ ምስክር ባለጉዳዩ ጉዳት ሊያደርስባቸው አይገባም:: ይህንን ብትሰሩ በእናንተ በኩል የሚመጣ አመጽ ነው:: አላህን ፍሩ:: አላህ ያሳውቃችኋል:: አላህ ሁሉንም ነገር አዋቂ ነውና፡፡"},{"id":283,"translation":"283. በጉዞ ላይ ብትሆኑና ጸሐፊ ባታገኙ በእጅ የተጨበጡ መተማመኛዎችን ያዙ:: ከፊላችሁ ከፊሉን ቢያምን ያ የታመነው ሰው አደራውን በትክክል ያድርስ:: አላህንም ጌታውን ይፍራ:: ምስክርነትንም አትደብቁ። ምስክርነትን የሚደብቃት ልበ ኃጢአተኛ ነው:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነውና::"},{"id":284,"translation":"284. በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለ ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ብትገልጹት ወይም ብትደብቁት አላህ በእርሱ ይቆጣጠራችኋል የሚሻውን ሰው ይምራል:: የሚሻውንም ሰው ይቀጣል:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና:: ይተሳሰባችኋል፡፡"},{"id":285,"translation":"285. መልዕክተኛው (ሙሐመድ) ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደለት (ቁርኣን) አምኗል:: አማኞችም እንደዚሁ አመኑ:: ሁሉም በአላህ፣ በመልዕክቱ፣ በመጽሐፉትና በመልዕክተኞቹ «ከእነርሱ በአንዱም መካከል አንለይም (አንክድም)» የሚሉ ሲሆኑ አመኑ:: «የአላህን ትዕዛዛትንም ሰማን ታዘዝንም። ጌታችን ሆይ! ምህረትህን እንሻለን :: የሁሉም መመለሻ ወደ አንተው ብቻ ነው። አሉም::"},{"id":286,"translation":"286. አላህ የትኛዋንም ነፍስ ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም:: ነፍስ ሁሉ ለሰራችው መልካም ስራ ሁሉ ተገቢው ምንዳ አላት:: በእርሷም ላይ ባፈራችው (ኃጢአት) ተገቢው ቅጣት አለባት:: (ሙስሊሞች) «ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንሳሳት (አትቅጣን):: ጌታችን ሆይ! ከባድ ሸክምን ከእኛ በፊት በነበሩት ህዝቦች ላይ እንደጫንከው ሁሉ በእኛ ላይ አትጫንብን:: ጌታችን ሆይ! ለእኛ ችሎታ የሌለንን ነገር አታሸክመን:: ለእኛም ይቅርታ አድርግልን:: ለእኛም ምህረትን አድርግልን:: እዘንልንም:: ረዳታችን አንተ ብቻ ነህና:: በከሓዲ ሕዝቦች ላይም ድልን አጎናጽፈን።» (በሉ።)"}]},{"id":3,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚም፤"},{"id":2,"translation":"2. አላህ ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: አላህ ህያው፤ በራሱ የተብቃቃና የሁሉ ነገር አስተናባሪ (የፍጡራን ተንከባካቢ) ነው::"},{"id":3,"translation":"3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ቁርኣንን ከእርሱ በፊት ያሉትን መጽሐፍት የሚያረጋግጥ ሲሆን ባንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደው። ከቁርኣን በፊትም ለሰዎች መሪ አድርጎ ተውራትንና ኢንጅልን አውርዷል።"},{"id":4,"translation":"4. ከቁርኣን በፊትም ለሰዎች መሪ አድርጎ ተውራትንና ኢንጅልን አውርዷል። (በእውነትና በውሸት መካከል መለያ የሆነውን) ፉርቃንንም አወረደ። እነዚያ በአላህ አናቅጽ የካዱ ሁሉ ብርቱ ቅጣት አለባቸው። አላህ ሁሉን አሸናፊ፤ አስተባባዮችን ተበቃይም ነውና።"},{"id":5,"translation":"5. አላህ በምድርም ሆነ በሰማይ ምንም ነገር አይሸሸግበትም።"},{"id":6,"translation":"6. በማህጸኖች ውስጥ እንደፈለገው አድርጎ የሚቀርፃችሁ እርሱው ነው። ከእርሱ ከአሸናፊዉና ከጥበበኛው ጌታ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ በፍጹም የለም።"},{"id":7,"translation":"7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያ ባንተ ላይ መጽሐፍን-(ቁርኣንን) ያወረደ ነው:: ከመጽሐፉም ውስጥ ግልጽ የሆኑ አናቅጽ አሉ:: እነርሱም የመጽሐፉ መሰረቶች ናቸው። ሌሎች ደግሞ አሻሚ ትርጉም ያላቸው አሉ:: እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሌሎችን ለማሳሳት በማሰብና ትርጉሙን በሻቸው ለመለወጥ ሲሉ አሻሚ ትርጉም (ተመሳሳይነት) ያሏቸውን አናቅጽ ብቻ ይከታተላሉ። ትክክለኛ ትርጉማቸውን አላህ ብቻ እንጂ ሌላ ማንም አያውቀዉም:: እነዚያ በእውቀት የጠለቁት ግን «በእርሱ አምነናል። ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው።» ይላሉ። የአእምሮ ባለቤቶች እንጂ አይገሰጽም።"},{"id":8,"translation":"8. (እነርሱም የሚሉ ናቸው:) «ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን ወደ መጥፎ አታዘንብልብን:: ካንተ ዘንድ የሆነን ችሮታ ስጠን:: አንተ በጣም ለጋስ ነህና።"},{"id":9,"translation":"9. «ጌታችን ሆይ! አንተ በዚያ ለመምጣቱ ጥርጥር በሌለበት ቀን ሰውን ሁሉ ሰብሳቢ ነህ:: ምን ጊዜም አላህ ቀጠሮን አያፈርስምና»::"},{"id":10,"translation":"10. እነዚያ የካዱትን ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው ከአላህ (ቅጣት) አያስጥሏቸዉም። እነዚያም እነርሱ የእሳት ማገዶዎች ናቸው።"},{"id":11,"translation":"11. ምሳሊያቸው ልክ እንደ ፈርዖን ቤተሰቦችና እንደነዚያ ከበፊታቸዉም እንደነበሩት ሕዝቦች ልማድ ነው:: በአናቅጻችን አስተባበሉ:: እናም አላህ በኃጢአቶቻቸው ቀጣቸው:: አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና::"},{"id":12,"translation":"12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያ በአላህ ለካዱ ሰዎች «በቅርብ ጊዜ ትሸነፋላችሁ:: ከዚያም በገሀነም ትሰበሰባላችሁ:: ምንጣፊቱም (ገሀነም) ምን ትከፋ!» በላቸው::"},{"id":13,"translation":"13. በእነዚያ (የበድር) ቀን በተጋጠሙት ሁለት ቡድኖች ለእናንተ ብዙ ተዓምራት አሉ:: አንደኛዋ ቡድን በአላህ መንገድ ትጋደላለች:: ሌላይቱ ቡድን ደግሞ ከሓዲ ናት። በዓይን አስተያየት እጥፋቸው ሆነው ያዩዋቸዋል (በቁጥር የነርሱ እጥፍ ሁነው በአይናቸው ተመለከቷቸው)። አላህ በእርዳታው የሚሻውን ሁሉ ያበረታልና። በዚህ ውስጥ ለማስተዋል ባለቤቶች ሁሉ በእርግጥ መገሰጫ አለበት::"},{"id":14,"translation":"14. ከሴቶች፣ ከወንዶች ልጆች፣ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከተከማቹ ገንዘቦች፣ ከተሰማሩ ፈረሶች፣ ከግመል ከከብትና ከፍየል፣ ከአዝመራም የሆኑ ፍላጎቶችን መውደድ ለሰዎች ተሸለመላቸው (ሰዎች ዘንድ የተወደዱ ተደረገላቸው)። ይህ ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጠቃቀሚያ ብቻ ነው:: አላህ ግን እርሱ ዘንድ መልካም የሆነ መመለሻ (ገነት) አለው::"},{"id":15,"translation":"15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከዚህ ከተዋበላችሁ ጉዳይ የሚበልጥን ልንገራችሁን? እርሱም ለእነዚያ አላህን ለሚፈሩ ሁሉ በጌታቸው ዘንድ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ሁልጊዜ ነዋሪዎች ሲሆኑ ንጹህ ሚስቶችና ከአላህ የሆነ ውዴታም አለላቸው:: አላህም ባርያዎቹን ተመልካች ነው።» በላቸው።"},{"id":16,"translation":"16. (እነርሱም) እነዚያ «ጌታችን ሆይ! እኛ ባንተ አመንን። ኃጢአቶቻችንን ማርልን። የእሳትን ቅጣት ጠብቀን።» የሚሉ ናቸው።"},{"id":17,"translation":"17. እነርሱም ታጋሾች፤ እውነተኞች፤ ታዛዦች፤ ለጋሾችና በሌሊት መጨረሻዎች ሰዓታት ላይ አላህን ምህረት የሚለምኑ ናቸው::"},{"id":18,"translation":"18. አላህ (በማስተካከል) ቀጥ ያለ ሲሆን ከእርሱ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የሌለ መሆኑን መሰከረ። መላዕክትና የእውቀት ባለቤቶችም መሰከሩ። ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም:: እርሱ ሁሉን አሸናፊውና ጥበበኛው ነው።"},{"id":19,"translation":"19. አላህ ዘንድ የተወደደው ሀይማኖት ኢስላም ብቻ ነው:: እነዚያ መጽሐፉን የተሰጡ ሰዎች በመካከላቸው ባለው ምቀኝነት እውቀቱ ከመጣላቸው በኋላ እንጂ አልተለያዩም:: በአላህ አናቅጽ ለሚክድ ሁሉ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው።"},{"id":20,"translation":"20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢከራከሩህም «ፊቴን ለአላህ ብቻ ሰጠሁ። የተከተሉኝም እንደዚሁ ለአላህ ብቻ ሰጡ።» በላቸው:: ለእነዚያም መጽሐፉን ለተሰጡ ሰዎችና ለመሃይማኑ (ዐረቦች)፡- «ሰለማችሁን?» በላቸው:: ቢሰልሙም በእርግጥ ወደቀናው መንገድ ተመሩ:: እምቢ ቢሉ ግን ባንተ ላይ ያለብህ መልዕክትን ማድረስ ብቻ ነው:: አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና።"},{"id":21,"translation":"21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ አናቅጽ የሚክዱ፤ ነብያትንም ያለ አግባብ የሚገድሉ፤ ከሰዎችም ውስጥ እነዚያን በትክክለኛነት የሚያዙትን የሚገድሉ በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው::"},{"id":22,"translation":"22. እነዚያ በቅርቢቱም ሆን በመጨረሻይቱ ዓለም ስራዎቻቸው የተበላሹ ናቸው:: ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም::"},{"id":23,"translation":"23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ከመጽሐፍ (ትምህርት) ድረሻን ወደ ተሰጡት ሰዎች አላየህምን? ወደ አላህ መጽሐፍ በመካከላቸው ይፈርድ ዘንድ ይጠራሉ:: ከዚያ ከእነርሱ ገሚሶቹ (ከፊሎቹ) እውነቱን ወደ ጎን የተው ሆነው ይሸሻሉ::"},{"id":24,"translation":"24. ይህም እነርሱ «የገሀነም እሳት የተቆጠሩ ቀናትን ብቻ እንጂ አትነካንም።» በማለታቸው ነው:: በሀይማኖታቸዉም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር አታለላቸው::"},{"id":25,"translation":"25. በእርሱ መምጣት ጥርጥር የሌለበት በሆነው ቀን በሰበሰብናቸውና ነፍስ ሁሉ የሰራችውን ስራ በተሞላች ጊዜ እንዴት ይሆናሉ? እነርሱም ቅንጣትንም አይበደሉም::"},{"id":26,"translation":"26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በል: «የንግስና ባለቤት የሆንከው አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግስናን ትሰጣለህ:: ከምትሻዉም ሰው ንግስናን ትገፋለህ:: የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ:: የምትሻውንም ሰው ደግሞ ታዋርዳለህ:: መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ብቻ ነው:: አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና።"},{"id":27,"translation":"27. «ሌሊቱን በቀን ውስጥ ታስገባለህ:: ቀኑንም በሌሊት ውስጥ ታስገባለህ:: ሕያውንም ከሙት ታወጣለህ:: ሙታንንም ከሕያው ታወጣለህ፤ ለምትሻውም ሁሉ መጠን የለሽ ሲሳይ ትሰጣለህ።» በል።"},{"id":28,"translation":"28. አማኞች ከሓዲያንን ከአማኞች ሌላ ረዳቶች አድርገው አይያዙ። ይህንን የሚሰራ ከአላህ ሀይማኖት በምንም ውስጥ አይደለም:: ከእነርሱ መጠበቅን ብትጠበቁ እንጂ:: አላህ ከእርሱው ያስጠነቅቃችኋል:: መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነውና።"},{"id":29,"translation":"29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ብትደብቁት ወይም ብትገልጹት አላህ ያውቀዋል:: በሰማያት ውስጥ ያለውንና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል:: አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።» በል።"},{"id":30,"translation":"30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያን ነፍስ ሁሉ ከመልካም ነገር የሰራችውን የቀረበ ሆኖ የምታገኝበትን ቀን (አስታውስ):: ከመጥፎም የሰራችው በእርሷና በኃጢአቱ መካከል በጣም የሰፋ ርቀት ቢኖር ትመኛለች:: አላህ እራሱን ያስጠነቅቃችኋል:: አላህ ለባሮቹ ሩህሩህ ነውና::"},{"id":31,"translation":"31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)፡- «አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ እኔን ተከተሉኝ:: አላህም ይወዳችኋል፤ ኃጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።» በላቸው።"},{"id":32,"translation":"32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)፡- «አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ። ብሸሹም አላህ ከሓዲያንን አይወድም» በላቸው።"},{"id":33,"translation":"33. አላህ (ነብዩ) አደምን፣(ነብዩ) ኑህን፣(የነብዩ) ኢብራሂምን ቤተሰብ እና የዒምራንን ቤተሰብ ከአለማት አበለጣቸው (መረጣቸው)።"},{"id":34,"translation":"34. እኒህን ቤተሰቦች ከፊሉ ከከፊሉ የሆነ ዝርያ አድርጎ መረጣቸው። አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነው።"},{"id":35,"translation":"35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዒምራን ባለቤት (ሀና) «ጌታዬ ሆይ! በሆዴ ውስጥ ያለውን ጽንስ ከሥራ ነፃ የተደረገ ሲሆን ላንተ አገልግሎት ይውል ዘንድ ተሳልኩ:: እናም ተቀበለኝ:: አንተ ሰሚና አዋቂ ነህና።» ባለች ጊዜ የሆነውን አስታውሱ በላቸው።"},{"id":36,"translation":"36. በወለደቻትም ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! ሴት ሆና ወለድኳት።» አለች። አላህ የወለደችውን ምንነት አዋቂ ነው:: የተመኘችው ወንድ እንደ ወለደቻት ሴት የሚሆን አልነበረም:: «መርየምም ብዬ ስም አወጣሁላት:: እኔም እርሷንና ዝርያዋን ከተረገመው ሰይጣን ተንኮል ባንተ እጠብቃቸዋለሁ።» አለች።"},{"id":37,"translation":"37. ጌታዋም በመልካም አቀባበል ተቀበላት:: በመልካም አስተዳደግም አፋፋት:: ከዚያም ዘከርያ አሳደጋት:: ዘከርያም ወደ ምኩራቧ በሷ ላይ በገባ ቁጥርም እርሷ ዘንድ ሲሳይን አገኘ:: «መርየም ሆይ! ይህ ለአንቺ ከየት ነው የሚመጣልሽ?» አላት። «እርሱ የሚመጣልኝ ከአላህ ዘንድ ነው:: አላህ እኮ ለሚሻው ሁሉ ሲሳዩን ያለ ሂሳብ ይሰጣል።» አለችው።"},{"id":38,"translation":"38. እዚያ ዘንድም ዘከርያ ጌታውን እንደዚህ በማለት ለመነ: «ጌታዬ ሆይ! ካንተ ዘንድ መልካም ዘርን ለእኔ ስጠኝ:: አንተ ጸሎትን ሰሚ ነህና» አለ።"},{"id":39,"translation":"39. እርሱም በዱዓ ማድረጊያ ክፍል ቆሞ ዱዓ ሲያደርግ መላዕክት:- «አላህ በየህያ: ከአላህ በሆነ ቃል የሚያረጋግጥ፣ በላጭ፣ ከሴት ጋር የማይገናኝ ድንግልና ከደጋጎቹም አንዱ ሲሆን ያበስርሃል።» በማለት መላዕክት ጠሩት።"},{"id":40,"translation":"40. ዘከርያም «ጌታዬ ሆይ! እኔ እርጅና የደረሰብኝ ሚስቴም መካን ስትሆን እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለ። መልአኩም: «ልክ እንደዚሁ ነው። አላህ የሚሻውን ነገር ሁሉ ይሰራልና።» አለው።"},{"id":41,"translation":"41. ዘከርያም «ጌታዬ ሆይ! ለእዚህ ነገር ምልክትን አድርግልኝ።» አለ:: «ምልክትህ ሶስት ቀን በጥቅሻ እንጂ ሰዎችን አለማናገርህ ነው:: በዚያ ጊዜ ጌታህን በብዙ አውሳ:: በማታና በጠዋትም አወድሰው።» አለው።"},{"id":42,"translation":"42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላእክትም ባሉ ጊዜ: «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ:: ከነውሮች ሁሉ አጸዳሸ:: ከዓለማት ሴቶችም መካከል መረጠሸ።"},{"id":43,"translation":"43. «መርየም ሆይ! ለጌታሽ ታዘዢ:: ስገጂም:: ከአጎንባሾች ጋርም ሁነሽ አጎንብሺ።» (ያለበትን ታሪክ ለህዝቦችህ አውሳ።)"},{"id":44,"translation":"44.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ታሪክ ወደ አንተ ከምናወርደው ከሩቅ ወሬ ነው:: መርየምን ማን እንደሚያሳድግ ብዕሮቻቸውን ለዕጣ በጣሉ ጊዜ አንተ እነርሱ ዘንድ አልነበርክም:: በሚከራከሩም ጊዜ እነርሱ ዘንድ አልነበርክም::"},{"id":45,"translation":"45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላዕክትም «መርየም ሆይ! አላህ ከእርሱ በሆነው ቃል የሚፈጠር ስሙ አል መሲህ ዒሳ የመርየም ልጅ በሚባል፤ በዚህ ዓለምም ሆነ በመጨረሻው ዓለም የተከበረና ከባለሟሎቹ አንዱ በሆነ ልጅ ያበስርሻል። (ባላት ጊዜ እዚያ ቦታ አልነበርክም) ::"},{"id":46,"translation":"46. «እርሱም ገና በህፃንነቱ ካደገም በኋላ ሰዎችን ያነጋግራል:: ከመልካሞቹም አንዱ ነው።» (አላት)።"},{"id":47,"translation":"47. እርሷም «ጌታዬ ሆይ! ማንም ሰው በትዳርም ሆነ በዝሙት ሳይነካኝ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለች:: መልአኩ ጅብሪልም አላት: «እነደዚሁ ነው። አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል። የአንድን ነገር መሆን በፈለገ ጊዜ የሚለው ‹ሁን› ብቻ ነው። ወዲያውኑም ያ ነገር ይሆናል።"},{"id":48,"translation":"48. «ጽሕፈትንና ጥበብን፤ ተውራትንና ኢንጂልንም ያስተምረዋል።"},{"id":49,"translation":"49.«ወደ ኢስራኢል ልጆችም መልዕክተኛ ያደርገዋል። ይላልም: ›, ‹እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዐምር መጣሁላችሁ:: እኔ ለእናንተ ከጭቃ የወፍ ቅርጽ አይነት እፈጥራለሁ:: በእርሱም እተነፍስበታለሁ:: ከዚያም በአላህ ፈቃድ ወፍ ይሆናል:: እውር ሆኖ የተወለደንም ለምጸኛንም በአላህ ፈቃድ አድናለሁ:: ሙታንንም በአላህ ፍቃድ አስነሳለሁ:: የምትበሉትንና በየቤቶቻችሁ የምታደልቡትን ሁሉ እነግራችኋለሁ:: (መረጃዎችን አገናዝባችሁ) የምታምኑ እንደሆናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ ግልጽ ተዐምር አለበት።"},{"id":50,"translation":"50.«‹ከእኔ በፊት የነበረውን ተውራትን ያረጋገጥኩ ስሆን ያንም በእናንተ ላይ እርም የተደረገውን ነገር ከፊሉን ለእናንተ እፈቅድ ዘንድ መጣሁላችሁ:: ከጌታችሁም በሆነ ተዐምር መጣሁላችሁ:: አላህን ፍሩ:: እኔንም ታዘዙኝ።"},{"id":51,"translation":"51.«‹አላህ ጌታዬ የእናንተም ጌታችሁ ነው:: ስለዚህ በብቸኝነት ተገዙት:: ይህ ቀጥተኛው መንገድ ነው።› ይላቸዋል»"},{"id":52,"translation":"52. ዒሳ ከእነርሱ ክህደት በተሰማው ጊዜ፡- «ወደ አላህ የእኔ ረዳቶች የሚሆኑ እነማን ናቸው?» አለ:: ሀዋርያትም አሉ፡- «ዒሳ ሆይ! እኛ የአላህ ረዳቶች ነን:: በአላህ አምነናል:: ትክክለኛና ታዛዦች መሆናችንን መስክር።"},{"id":53,"translation":"53. («ጌታችን ሆይ! ባወረድከው አምነን መልዕክተኛውን ተከትለናል::( እኛንም ባንተ ብቸኛ አምላክነት በነብያት መልዕክተኛነት) ከመስካሪዎች ጋራ መዝግበን።» አሉ።"},{"id":54,"translation":"54.አይሁድም በዒሳ ላይ አደሙ:: አላህ ግን አድማቸውን አከሸፈባቸው። አላህ የአድመኞችን ሴራ በማክሸፍ ከሁሉ የበለጠ ነውና።"},{"id":55,"translation":"55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡- «ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጅህና ከምድር ወደ እኔ አንሽህ ነኝ:: ከነዚያም በእኔ ከካዱ ሰዎች (ተንኮል) አጥሪህ ነኝ። እነዚያ የተከተሉህንም እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ:: ከዚያ የሁላችሁም መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው:: ያን ትለያዩበት በነበራችሁበት ነገርም በመካከላችሁ እፈርዳለሁ።"},{"id":56,"translation":"56.«እነዚያማ የካዱትን በቅርቢቱ ዓለምም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ብርቱ ቅጣትን እቀጣቸዋለሁ:: ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም»"},{"id":57,"translation":"57. እነዚያማ አምነው መልካም ስራዎችን የሰሩትን አላህ ምንዳቸውን ይሞላላቸዋል:: አላህም በዳዮችን አይወድምና።"},{"id":58,"translation":"58.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ተዓምራትና ጥበብን ከያዘው ተግሳጽ በአንተ ላይ የምናነበው ነው።"},{"id":59,"translation":"59. አላህ ዘንድ የዒሳ (ያለ አባት መፈጠሩ) ምሳሌው ልክ እንደ (ያለ አባትና ያለ እናት እንደተፈጠሩት አባታችን) አደም ቢጤ ነው:: አላህ ከአፈር ፈጠረውና ከዚያም «ሁን» አለው። ከዚያ ሰው ሆነ።"},{"id":60,"translation":"60.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውነታው ከጌታህ ዘንድ የመጣልህ እውነት ነው። እናም ከተጠራጣሪዎች አትሁን።"},{"id":61,"translation":"61.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውቀት ከመጣልህ በኋላ በእርሱ (በዒሳ) የተከራከሩህን «ኑ ልጆቻችንንና ልጆቻችሁን፣ ሴቶቻችንንና (ሚስቶቻችንና) ሴቶቻችሁን (ሚስቶቻችሁን)፣ ነፍሶቻችንንና ነፍሶቻችሁን እንጥራና ከዚያ አላህን እንለምን:: የአላህንም ቁጣ በውሸታሞች ላይ እናድርግ።» በላቸው።"},{"id":62,"translation":"62.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ እውነተኛው ታሪክ ነው:: ትክክለኛ አምላክም ከአላህ በስተቀር የለም። አላህም አሸናፊውና ጥበበኛው አምላክ ነው።"},{"id":63,"translation":"63. (ከማመን) እምቢ ቢሉም (አጥፊዎቹ እነርሱ ናቸው።) አላህ አጥፊዎቹን (ከደህናዎቹ) ለይቶ አዋቂ ነው።"},{"id":64,"translation":"64.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ሆነችው ቃል ኑ። (እርሷም) ‹አላህን ብቻ እንጂ ሌላን ላንገዛ፤ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፤ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይዝ› ነው።» በላቸው። (ሙስሊሞች ሆይ!) እምቢ ካሉም «እኛ ሙስሊሞች መሆናችንን መስክሩ።» በሏቸው።"},{"id":65,"translation":"65. እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በኢብራሂም (ዙሪያ) ለምን ትከራከራላችሁ? ተውራትና ኢንጂል ከእርሱ በኋላ እንጂ አልተወረዱ። ልብ አትሉምን?"},{"id":66,"translation":"66 እናንተ እነዚያ እውቀት ባላችሁ ነገር የተከራከራችሁ ናችሁ፡፡ ታዲያ እውቀት በሌላቸሁ ነገር ላይ ለምን ትከራከራላችሁ? አላህ ሁሉን ነገር ያውቃል። እናንተ ግን አታውቁም።"},{"id":67,"translation":"67. ኢብራሂም አይሁድም ሆነ ክርስቲያን አልነበረም:: ግን በቀጥተኛው ሃይማኖት ቀጥ ያለ ሙስሊም ነበር:: ከአጋሪዎችም አልነበረም፡፡"},{"id":68,"translation":"68.በኢብራሂም ይበልጥ ተገቢዎቹ እነዚያ የተከተሉት፤ ይህ ነብይ (ነብዩ ሙሐመድ) እና እነዚያ ያመኑት ብቻ ናቸው፡፡ አላህ የአማኞች ወዳጅ ነው፡፡"},{"id":69,"translation":"69. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከመጽሐፉ ባለቤቶች የተወሰኑት ነፍሶቻቸውን እንጂ የማያሳስቱ ሲሆኑ እናንተን ሊያሳስቷችሁ ተመኙ:: እራሳቸውን እንጂ ማንንም አያሳሳስቱም፡፡ እነርሱ ግን ይህንን እውነታ አያውቁም።"},{"id":70,"translation":"70. እናንተ የመጽሐፍ ባለቤቶች ሆይ! እናንተ የምታውቁ ስትሆኑ በአላህ አናቅጽ ለምን ትክዳላችሁ?"},{"id":71,"translation":"71. እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! እውነትን ከውሸት ጋር ለምን ትቀላቅላላችሁ? እውነቱንም የምታውቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ?"},{"id":72,"translation":"72. ከመጽሐፉ ባለቤቶች የሆኑ ቡድኖችም በዚያ ባመኑት ላይ በተወረደው ቁርኣን «በቀኑ መጀመሪያ ላይ እመኑበትና በቀኑ መጨረሻ ላይ ካዱ። እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና።» አሉ።"},{"id":73,"translation":"73. (አሉም) «ሃይማኖታችሁን ለተከተለ እንጂ አትመኑም።» (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ትክክለኛው መመሪያ የአላህ መመሪያ ብቻ ነው። እናንተ ያገኛችሁትን እድል እንዳያገኙ ወይም በእርሱ ከጌታችሁ ፊት እንዳይሞግቷችሁ በመፍራት ነውን?» በላቸው። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ችሮታ በአላህ እጅ ብቻ ነው። ለሚፈልገውም ይሰጠዋል። አላህም ችሮታው ሰፊና ሁሉን አዋቂ ነው።» በላቸው።"},{"id":74,"translation":"74. በችሮታው የሚሻውን ይመርጣል:: አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና::"},{"id":75,"translation":"75. ከመጽሐፉ ባለቤቶች መካከል በብዙ ገንዘብ ላይ ብታምነው ቅንጣት ሳያጎድል የሚመልስልህ አለ:: ከእነርሱም መካከል በአንድ ዲናር እንኳን ብታምነው ሁል ጊዜም እሱ ላይ የምትጠባበቅ ካልሆንክ በስተቀር የማይመልስልህም አለ:: ይህ «በመሀይማን ህዝቦች ላይ በምናደርገው በደል በእኛ ላይ የምንጠየቅበት መንገድ የለብንም።» ስለሚሉና እነርሱም እያወቁ በአላህ ላይ ውሸትን ስለሚናገሩ ነው።"},{"id":76,"translation":"76 ጉዳዩ እነርሱ እንዳሉት አይደለም (ተጠያቂነት አለባቸው)። ያ በቃል ኪዳኑ የሞላና የተጠነቀቀን ሁሉ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳል።"},{"id":77,"translation":"77. እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳንና በመሀላዎቻቸው ጥቂትን ዋጋን የሚለውጡ ሁሉ በመጨረሻይቱ ዓለም ምንም እድል የላቸዉም:: በትንሳኤም ቀን አላህ አያነጋግራቸዉም:: ወደ እነርሱም አይመለከትም:: አያጸዳቸዉምም:: ከቶውንም ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":78,"translation":"78. ከእነርሱም መካከል ከመጽሐፉ ያልሆነን ነገር ከመጽሐፉ አካል መሆኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙም አሉ:: እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልመጣ (ያልወረደ) ሲሆን «ከአላህ ዘንድ የመጣ (የወረደ) ነው።» ይላሉ። የሚያውቁ ሲሆኑ በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ።"},{"id":79,"translation":"79. ለማንም ሰው አላህ መጽሐፍን፣ ጥበብንና ነብይነትን ሰጥቶት ከዚያ ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ሁኑ።» ሊል አይገባዉም:: ይልቁንም «መጽሐፉን የምታስተምሩና የምታጠኑ በነበራችሁበት በእውቀታችሁ ለራሳችሁ ተግባሪዎች ሁኑ።» ይላቸዋል።"},{"id":80,"translation":"80. መላዕክትንና ነብያትንም አማልክት አድርጋችሁ እንድትይዙ ሊያዛችሁ አይገባም:: (እናንተ) ሙስሊሞች ከሆናችሁ በኋላ በክህደት ያዛችኋልን?"},{"id":81,"translation":"81. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «መጽሐፍንና ጥበብን ሰጥቻችሁ ከዚያ ከናንተ ጋር ላለው መጽሀፍ የሚያረጋግጥ መልዕክተኛ ቢመጣላችሁ በእርሱ እንድታምኑበት እንድትረዱትም።» ሲል አላህ የነቢያትን ቃል ኪዳን በያዘ ጊዜ (የነበረውን ክስተት ለህዝቦችህ አስታውስ)። «አረጋገጣችሁን? በዚህስ ላይ ቃል ኪዳኔን ያዛችሁን?» አላቸው። እነርሱም «አዎ አረጋገጥን» አሉ። «እንግዲያውስ መስክሩ:: እኔም ከናንተ ጋር ከመስካሪዎቹ ነኝ።» አላቸው።"},{"id":82,"translation":"82. እናም ከዚህ በኋላ የሸሹ አመጸኞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው።"},{"id":83,"translation":"83. በሰማያትና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም ሆነ በግድ ለእርሱ የታዘዙና ወደ እርሱ የሚመለሱ ሲሆኑ (ከሓዲያን) ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን?"},{"id":84,"translation":"84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በአላህ አምነናል በእኛም ላይ በተወረደው በቁርኣን (በነብዩ) ኢብራሂም፣ (በነብዩ) ኢስማኢል፣ (በነብዩ) ኢስሀቅ፣ (በነብዩ) የዕቆብና በነገዶች ላይ በተወረደው፣ ለነብዩ ሙሳ ለነብዩ ዒሳና ለነብያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው ሁሉ አምነናል:: በእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም:: እኛ ለእርሱ ብቻ ታዛዦች ነን።» በል።"},{"id":85,"translation":"85. ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሁሉ ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይነት የለዉም:: እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ አንዱ ነው::"},{"id":86,"translation":"86. ከእምነታቸውና መልዕክተኛዉም እውነት መሆኑን ከመሰከሩ፤ የተብራሩ አናቅጽም ከመጡላቸው በኋላ የካዱ ሕዝቦችን አላህ እንዴት ያቀናል? አላህ በዳዮችን ሕዝቦች አያቀናምና።"},{"id":87,"translation":"87. እነዚያን መሰሎች ቅጣታቸው የአላህ፣ የመላዕክትና የሰዎች ሁሉ እርግማን በእነርሱ ላይ መውረዱ ነው።"},{"id":88,"translation":"88. በውስጧ ዘወታሪዎች ሲሆኑ ቅጣቱም ከእነርሱ ላይ አይቃለልላቸዉም:: ጊዜም አይሰጡም::"},{"id":89,"translation":"89. እነዚያ ከዚያ በኋላ ንስሀ የገቡና ስራቸውን ያሳመሩ ሁሉ ሲቀሩ፤ (አላህ እነዚህንማ ይምራቸዋል።) አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":90,"translation":"90. እነዚያ ከእምነታቸው በኋላ የካዱና ከዚያ ክህደትን በክህደት ላይ የጨመሩ ንሰሃቸው ፈጽሞ ተቀባይነት የለዉም:: የተሳሳቱ ማለት እነርሱው ናቸው::"},{"id":91,"translation":"91. እነዚያ የካዱና በክህደታቸው ላይ እንዳሉ የሞቱ፤ ከእነርሱ አንዳቸው ምድርን የሞላ ወርቅ ቤዛ ቢያቀርብም እንኳ ፈጽሞ ተቀባይነት አያገኝም:: እነዚያ ለእነርሱ የሚያሰቃይ ቅጣት አለባቸው:: ለእነርሱም (ከዚህ ቅጣት) የሚያድኗቸው ምንም ረዳቶች የሏቸዉም::"},{"id":92,"translation":"92. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከምትወዱት ነገር እስከምትለግሱ ድረስ የበጎ ስራን ዋጋ (ገነትን) አታገኙም:: ከምንም ነገር ብትለግሱም አላህ ያውቀዋል::"},{"id":93,"translation":"93. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተውራት ከመውረዱ በፊት ኢስራኢል በራሱ ላይ እርም ካደረገው ነገር በስተቀር ምግብ ሁሉ ለኢስራኢል ልጆች የተፈቀደ ነበር። «እውነተኞች ከሆናችሁ እስኪ ተውራትን አምጡና አንብቡት።» በላቸው።"},{"id":94,"translation":"94. ከዚህ በኋላ በአላህ ላይ ውሸትን የቀጣጠፉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ብቻ በዳዮች (በደለኞች) ናቸው::"},{"id":95,"translation":"95. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ እውነትን ተናገረ። (ትክክለኛ የኢብራሂም ወዳጆች ከሆናችሁ) የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን ተከተሉ። ከአጋሪዎችም አልነበረም።» በላቸው።"},{"id":96,"translation":"96. ለሰዎች (ማምለኪያ ይሆን ዘንድ በመሬት ላይ) በመጀመሪያ የተሰራው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲሆን ያ በበካህ (በመካ) ያለው ቤት (ካዕባ) ነው።"},{"id":97,"translation":"97. በውስጡ ግልጽ የሆኑ ተዐምራት አሉበት:: የኢብራሂምም መቆሚያ (የነበረው በዉስጡ አለ::) ወደ እርሱ የገባም ሁሉ ሰላም ይሆናል። በሰዎች ላይ ወደ እርሱ የመሄድን ጣጣ በቻለ ሁሉ ግዴታቸው ሲሆን ቤቱን ሊጎብኙት ለአላህ መብት አለው። በአላህ የካደ (ግን እራሱን እንጂ ማንንም አይጎዳም።) አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነውና።"},{"id":98,"translation":"98.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! አላህ በምትሰሩት ሁሉ ላይ አዋቂ ሲሆን በአላህ ተዐምራቱ ለምን ትክዳላችሁ?» በላቸው።"},{"id":99,"translation":"99. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እናንተ መስካሪዎች ሆናችሁ ከአላህ መንገድ መጥመሟን የምትፈልጉ ስትሆኑ ያመነን ሰው ለምን ትከለክላላችሁ? አላህም ከምትሰሩት ነገር ላይ ሁሉ ዘንጊ አይደለም።» በላቸው።"},{"id":100,"translation":"100. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ መጽሐፍትን ከተሰጡ መካከል ከፊሎቹን ብትታዘዙ ከእምነታችሁ በኋላ ወደ ክህደት ይመልሷችኋል።"},{"id":101,"translation":"101. የአላህ አናቅጽ በእናንተ ላይ እየተነበቡና መልዕክተኛዉም በመካከላችሁ እያለ እንዴት ትክዳላችሁ? በአላህ የሚጠበቅ ሰው ሁሉ ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ተመራ::"},{"id":102,"translation":"102. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ትክክለኛውን ፍራቻ ፍሩት። እናንተም ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጂ አትሙቱ።"},{"id":103,"translation":"103. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የአላህን ጠንካራ የእምነት ገመድም ሁላችሁም ያዙ:: አትለያዩም። ጠበኞች በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋም አስታውሱ:: ይሀውም በልቦቻችሁ መካከል አስማማ በጸጋዉም ወንድማማቾች ሆናችሁ:: በእሳት ጉድጓድ አፋፍ ላይ የነበራችሁ ስትሆኑ ከእርሷም አዳናችሁ:: ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አናቅጽን እንደዚሁ ያብራራል::"},{"id":104,"translation":"104. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከናንተ መካከል ወደ በጎ ነገር የሚጠሩና በመልካም ስራ የሚያዙ፤ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ቡድኖች ይኑሩ:: እነዚያ ከእሳት የሚድኑ እነርሱው ናቸው።"},{"id":105,"translation":"105. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እንደነዚያ ግልጽ ተዐምራት ከመጣላቸው በኋላ እንደተለያዩትና እንደተጨቃጨቁት የመጽሐፉ ባለቤት ሰዎች አትሁኑ:: እነዚያም ለነርሱ ታላቅ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":106,"translation":"106.ያን ፊቶች የሚያበሩበትና ፊቶች የሚጠቁሩበትን የትንሳኤን ቀን አስታውሱ። እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩት ወገኖች «ከእምነታችሁ በኋላ ካዳችሁን? እግዲያዉስ ትክዱ የነበራችሁትን ነገር ቅጣቱን ቅመሱ።» ይባላሉ።"},{"id":107,"translation":"107. እነዚያ ፊቶቻቸው ያበሩት ወገኖች ደግሞ በአላህ ችሮታ ገነት ውስጥ ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘወታሪዎች ናቸው::"},{"id":108,"translation":"108. እነኚህ ባንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው የአላህ አናቅጽ ናቸው:: አላህም ለዓለማት በደልን የሚሻ አይደለም::"},{"id":109,"translation":"109. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለ ሁሉ የአላህ ነው:: ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ።"},{"id":110,"translation":"110. (ሙስሊሞች ሆይ!) ለሰው ልጆች ከተገለፁት ሕዝቦች ሁሉ በላጭ ሆናችሁ:: ይኸዉም በመልካም ነገር ታዛላችሁ:: ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ:: በአላህም አንድነት ታምናላችሁና ነው:: የመጽሐፉ ሰዎችም ልክ እንደናንተው ባመኑ ኑሮ ለእነርሱ የተሻለ በሆነ ነበር። ከእነርሱ መካከል ትክክለኛ አማኞችም አሉ:: አብዛሀኞቻቸው ግን አመጸኞች ናቸው::"},{"id":111,"translation":"111 (ሙስሊሞች ሆይ!) ማስከፋትን እንጂ ፈጽሞ አይጎዷችሁም:: ቢዋጓችሁም ጀርባዎችን ያዞሩላችኋል (ይሸሻሉ)። ከዚያም በምንም ረዳት አያገኙም::"},{"id":112,"translation":"112. በየተገኙበት ስፍራ ከአላህ በሆነ ቃልኪዳን ወይም ከሰዎች በሆነ ቃል ኪዳን የተጠበቁ ካልሆኑ በስተቀር በእነርሱ ላይ ውርደት ተጽፎባቸዋል። ከአላህ በሆነ ቁጣ ተመለሱ። ድህነትም በእነርሱ ላይ ተፅፎባቸዋል። ይህ የሆነውም በአላህ ተዐምራት (አናቅጽ) ይክዱ፤ ነቢያትንም ያላ አግባብ ይገድሉ ስለነበሩ ነው:: ይህም የሆነው በማመፃቸውና ወሰንን ይተላለፉ ስለነበሩ ነው::"},{"id":113,"translation":"113. የመጽሐፉ ባለቤቶች ሁሉ እኩል አይደሉም:: ከመጽሐፉ ባለቤቶች መካከል ቀጥ ያሉና በሌሊት ሰዓቶች እየሰገዱ የአላህን አናቅጽ የሚያነቡ ሕዝቦችም አሉ።"},{"id":114,"translation":"114. በአላህና በመጨረሻዉም ቀን ያምናሉ:: በጽድቅም ነገር ያዛሉ:: ከመጥፎ ነገርም ይከለክላሉ:: ለበጎ ስራዎችም ይጣደፋሉ:: እነርሱ ከደጋግ ሰዎች ናቸው::"},{"id":115,"translation":"115. ከበጎ የሚሰሩትን አይካዱም። (ውድቅ አይደረግባቸዉም::) አላህ ጥንቁቆቹን ሁሉ አዋቂ ነውና።"},{"id":116,"translation":"116. እነዚያ በአላህ የካዱት ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው ከአላህ ቅጣት ምንንም አያድኗቸዉም:: እነዚያም የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::"},{"id":117,"translation":"117. በዚህች በቅርቢቱ ሕይወት የሚለግሱት ነገር ምሳሌው በውስጧ ውርጭ ያለባት ነፋስ ነፍሶቻቸውን የበደሉን ሕዝቦች አዝመራ እንደነካችና እንዳጠፋች ብጤ ነው። አላህም አልበደላቸዉም። ግን እነርሱ ነፍሶቻቸውን በእራሳቸው የሚበድሉ ናቸው እንጂ::"},{"id":118,"translation":"118. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሚስጥረኛን (የልብ ወዳጅ) ከእናንተ ሌላ ከሆኑት አታድርጉ። የእናንተን ጉዳይ ከማበላሸት አይቦዝኑላችሁምና። ጉዳታችሁን ይወዳሉና (ይመኛሉ)። ለእናንተ ያላቸው ጥላቻ ከአፎቻቸው ላይ እንኳ ተገለጸ:: በልቦቻቸው የሚደብቁት ደግሞ ከዚህ ይበልጥ የከፋ ነው:: ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለእናንተ ማብራሪያዎችን በእርግጥ ገለጽን::"},{"id":119,"translation":"119. እናንተ ትወዷቸዋላችሁ:: እነርሱ ግን በፍጹም አይወዷችሁም:: እናንተ በሁሉም መጽሐፍት ታምናላችሁ:: እነርሱ ግን ባገኟችሁ ጊዜ «አምነናል» ይላሉ:: ከናንተ ባገለሉ ጊዜ ግን ከቁጭታቸው የተነሳ በእናንተ ላይ ዐጥቆቻቸውን (ጣቶቻቸውን) ይነክሳሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በቁጭታችሁ ሙቱ። አላህ ልቦች የቋጠሩትን ሁሉ አዋቂ ነውና።» በላቸው።"},{"id":120,"translation":"120. ደግ ነገር ብታገኙ ይከፋቸዋል:: መጥፎ ነገር ቢደርስባችሁ ግን በሷ ይደሰታሉ:: ከታገሳችሁና አላህን ከፈራችሁ ተንኮላቸው ምንም አይጎዳችሁም:: አላህ ለሚሰሩት ሁሉ በዕውቀቱ ከባቢ ነውና::"},{"id":121,"translation":"121. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማኞችን ለውጊያ ስፍራዎች የምታዘጋጅ ሆነህ ከቤተሰብህ በጧት በወጣህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: አላህ ሁሉን ሰሚ ሁሉንም አዋቂ ነውና።"},{"id":122,"translation":"122. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ረዳታቸው ሲሆን ከእናንተ መካከል ሁለት ቡድኖች (ወገኖች) ለመፍራት ባሰቡ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: በአላህ ላይ ብቻ አማኞች ይመኩ::"},{"id":123,"translation":"123. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በበድር ዘመቻ ዕለት እናንተ ጥቂቶች ሆናችሁ ሳለ አላህ በእርግጥ ረዳችሁ:: አላህን ታመሰግኑ ዘንድ ፍሩት::"},{"id":124,"translation":"124. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለአማኞች (እንዲህ) በምትል ጊዜ የሆነውን አስታውስ: «ጌታችሁ በሶስት ሺ መላዕክት የተወረዱ ሲሆኑ ቢረዳችሁ አይበቃችሁምን?"},{"id":125,"translation":"125. «አዎን! ብትታገሱና ብትጠነቀቁ አሁኑኑ በፍጥነት ጠላቶቻችሁ ቢመጡባችሁም ጌታችሁ ምልክት ባላቸው አምስት ሺህ መላዕክት ይረዳችኋል።»"},{"id":126,"translation":"126. አላህ ለእናንተ ብስራትና ልቦቻችሁ በእርሱ እንዲረኩ እንጂ እርዳታውን ለምንም አላደረገዉም:: ድልም አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ዘንድ ብቻ እንጂ ከሌላ ከማንም የሚገኝ አይደለም::"},{"id":127,"translation":"127. (ድልን ያጎናፀፋችሁ) ከእነዚያ ከካዱት ከፊልን ሊቆርጥ (ሊያጠፋ) ወይም ሊያዋርዳቸውና ያፈሩ ሁነው እንዲመለሱ ነው።"},{"id":128,"translation":"128. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ ራሳቸውን በዳዮች ናቸውና አላህ በእነርሱ ላይ ከፈለገም ይቅርታ ቢያደርግ ወይም በጥፋታቸው ቢቀጣቸውም ላንተ በነገሩ ላይ ምንም የለህም።"},{"id":129,"translation":"129. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: ለፈለገው ሰው ይምራል:: የሚፈለገውን ሰው ይቀጣል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":130,"translation":"130. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አራጣን የተነባበሩ እጥፎች ሲሆኑ አትብሉ:: ከገሀነም እሳት ትድኑም ዘንድ (አራጣን በመተው) አላህን ፍሩ::"},{"id":131,"translation":"131. ያችን ለከሓዲያን የተደገሰችውን የገሀነም እሳት ተጠንቀቁ::"},{"id":132,"translation":"132.(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ::"},{"id":133,"translation":"133. ወደ ጌታችሁ ምህረትና ስፋቷ ሰባቱ ሰማያትንና ምድርን ያክል ወደ ሆነችው ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትሆን ተቻኮሉ::"},{"id":134,"translation":"134. ለእነዚያ በድሎትም ሆነ በችግር ጊዜ ለሚለግሱት፤ ቁጭትንም ገቺዎች፤ ለሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለሆኑት፤ አላህ በጎ ሰሪዎችን ሁሉ ይወዳልና::"},{"id":135,"translation":"135. ለእነዚያም መጥፎ ስራን በሰሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለኃጢአቶቻቸው ምህረትን የሚለምኑ ለሆኑት ተደግሳለች:: ከአላህ ሌላ ኃጢአቶችን የሚምር ማን ነው? (አንድም የለም::) በስህተት በሰሩት ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲሆኑ የማይዘወትሩ ለሆኑት ሁሉ ተደግሳለች::"},{"id":136,"translation":"136. እነዚያ ምንዳቸው ከጌታቸው ምህረትና በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችም ናቸው:: የመልካም ሰሪዎች ሁሉ ምንዳ የሆነችው ገነት ምንኛ አማረች!"},{"id":137,"translation":"137. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከእናንተ በፊት በእርግጥ ብዙ አልፈዋል። በምድር ላይ ሂዱና ያስተባባዮች ፍፃሜ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ።"},{"id":138,"translation":"138. ይህ ቁርኣን ለሰዎች ሁሉ ማብራርያ፤ ለጥንቁቆችም መመሪያና ገሳጭ ነው::"},{"id":139,"translation":"139. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እናንተ የበላዮች ናችሁና ትክክለኛ አማኞች እንደሆናችሁ አትድከሙ (አትስነፉ)። አትዘኑም።"},{"id":140,"translation":"140. አማኞች ሆይ! የመቁስል ጉዳት ቢያገኛችሁ ሌሎች ህዝቦችም መሰሉ የመቁሰል ጉዳት አግኝቷቸዋል። እንዲሁ ቀናትን በሰዎች መካከል እናፈራርቃቸዋለን:: አላህ እነዚያን በትክክል በሱ ያመኑትን ሊለይና ከእናንተም መካከል ሰማዕታትን ሊመርጥ እንዲህ አይነት ቀናት እንዲፈራረቁ ያደርጋል:: አላህም በዳዮችን ሁሉ አይወድምና::"},{"id":141,"translation":"141. አላህ እነዚያን በትክክል በእርሱ ያመኑትን ከኃጢአት ሊያጸዳና ከሓዲያንንም ሊያጠፋ ይህንን አደረገ።"},{"id":142,"translation":"142. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) አላህ ከናንተ መካከል እነዚያን የታገሉትንና ታጋሾችን ሳይለይ ገነትን የምትገቡ መሰላችሁን?"},{"id":143,"translation":"143. በጦርነት ላይ መሞትን ሳታገኙት በፊት የምትመኙት ነበራችሁ:: እናንተም በአይናችሁ የምትመለከቱ ስትሆኑ በእርግጥ አያችሁት። (ታዲያ ለምን ሸሻችሁት?)"},{"id":144,"translation":"144. (መልዕክተኛችን) ሙሐመድ ከበፊቱ ብዙ መልዕክተኞች እንዳለፉት የሆነ መልዕክተኛ እንጂ አይደለም:: ታዲያ እሱ ቢሞት ወይ ቢገደል ወደ ኋላችሁ ትገለበጣላችሁን? ወደ ኋላው የሚቀለበስም አላህን ምንም አይጎዳም:: አላህ አመስጋኞቹን ተገቢዉን ይመነዳልና::"},{"id":145,"translation":"145. ማንኛዋም ነፍስ በተወሰነላት ጊዜ በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ አትሞትም። የቅርቢቱን ዓለም ምንዳ የሚፈልግን ሁሉ ከእርሷ እንሰጠዋለን:: የመጨረሻይቱን ዓለም ምንዳ የሚፈልግንም ከእርሷ እንሰጠዋለን:: አመስጋኞችንም በእርግጥ ተገቢውን እንመነዳለን::"},{"id":146,"translation":"146. ከነብያት ሊቃውንት ከእነሱ ጋር ሆነው የተዋጉ ብዙ አሉ። እናም በአላህ መንገድ ለሚደርስባቸው ነገር ምንም አልፈሩም:: አልደከሙም:: ለጠላት አልተዋረዱም:: አላህም ትዕግስተኞቹን ይወዳል::"},{"id":147,"translation":"147. ንግግራቸዉም «ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንና በነገራችን ሁሉ ወሰን ማለፋችንን ማርልን። ጫማዎቻችንንም አደላድል:: በከሓዲያን ሕዝቦች ላይም እርዳን።» ማለታቸው እንጂ ሌላ አልነበረም።"},{"id":148,"translation":"148. አላህ የቅርቢቱን ዓለም ምንዳና የመጨረሻይቱን መልካም ምንዳ ሰጣቸው:: አላህ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ ይወዳልና::"},{"id":149,"translation":"149. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን በአላህ የካዱትን ብትታዘዙ ወደ ኋላችሁ ይመልሷችኋል። ከከሳሪዎቹም ትሆናላችሁ።"},{"id":150,"translation":"150. ይልቁን አላህ ብቻ ረዳታችሁ ነው:: እርሱ ከረዳቶች ሁሉ በላጭ ነውና::"},{"id":151,"translation":"151. በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ አላህ በእሱ አስረጂ ያላወረደበትን ነገር በአላህ በማጋራታቸው ምክንያት ፍርሃትን እንጥላለን:: መኖሪያቸዉም የገሀነም እሳት ናት:: የበዳዮች መኖሪያ የሆነችው ገሀነምም መኖሪያነቷ ምን ትከፋ!"},{"id":152,"translation":"152. በእርግጥ አላህ በፈቃዱ ጠላቶቻችሁን በምትጨፈጭፏቸው ጊዜ ቃልኪዳንን በእርግጥ አረጋገጠላችሁ:: የምትወዱትንም ነገር ካሳያችሁ በኋላ በፈራችሁ፣ በትዕዛዙም በተጨቃጨቃችሁና ባመፃችሁም ጊዜ (ግን እርዳታውን ከለከላችሁ):: ከናንተ ውስጥ ቅርቢቱን ዓለም የሚሻ አለ:: ከናንተም ውስጥ የመጨርሻይቱን ዓለም የሚሻ አለ:: ከዚያም ሊሞክራችሁ ከእነርሱ አዞራችሁ:: በእርግጥም ለእናንተ ይቅርታ አደረገላችሁ:: አላህ ሁልጊዜም በአማኞች ላይ የችሮታ ባለቤት ነውና::"},{"id":153,"translation":"153. (የመልዕክተኛችን ሙሐመድ ባልደረቦች ሆይ!) መልዕክተኛው ከኋላችሁ ሁኖ እየጠራችሁ የማትዞሩ ሆናችሁ በርቀት በምትሸሹ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: ባመለጣችሁ እድልና በደረሰባችሁም ነገር አለማዘንን ሊያስተምራችሁ በሀሳብ ላይ ሀሳብን አደረሰባችሁ:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውሰጠ አዋቂ ነው::"},{"id":154,"translation":"154. ከዚያም ከጭንቅ በኋላ ጸጥታን ከናንተ ከፊሎችን የሚሸፍንን እንቅልፍ በእናንተ ላይ አወረደ:: ከፊሎችንም ነፍሶቻቸው በእርግጥ አሳሰቧቸው:: እውነት ያልሆነውን የመሀይምነትን መጠራጠር በአላህ ላይ ይጠራጠራሉ:: «በነገሩ ላይ ምንም የመወሰን መብት አለን? (የለንም።») ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመወሰን መብት ሁሉ የአላህ ብቻ ነው።» በላቸው:: ላንተ ግልጽ የማያደርጉትን በልቦቻቸው ውስጥ ይደብቃሉ:: «የመወሰን መብት ቢኖረን ኖሮ በዚህ ቦታ ላይ ባልተገደልን ነበር» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በቤታችሁ ውስጥ በሆናችሁም ኖሮ እነዚያ በእነርሱ ላይ መገደል የተጸፈባቸው ወደየመውደቂያቸው በወጡ ነበር።» በላቸው:: አላህ ፍርዱን ሊፈጽምና በደረቶቻችሁም ውስጥ ያለውን ሊፈትን በልቦቻችሁም ውስጥ ያለውን ነገር ሊገልጽ ይህንን ሰራ:: አላህ በደረቶች ውስጥ ያለውን ሁሉ ነገር ሳይቀር አዋቂ ነውና::"},{"id":155,"translation":"155.(የመልዕክተኛችን ባልደረቦች ሆይ!) እነዚያ ሁለቱ ቡድኖች በተገናኙ ቀን ከናንተ የሸሹትን ሰዎች በዚያ በሰሩት ከፊል ምክንያት ያሳሳታቸው ሰይጣን ነው:: አላህ ከእነርሱ በእርግጥ ይቅር ብሏል:: አላህ መሀሪና ለቅጣት የማይቸኩል ታጋሽ ነውና።"},{"id":156,"translation":"156. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እነደነዚያ በአላህ እንደካዱትና ስለ ወንድሞቻቸው በምድር ላይ በተጓዙና ወይም ዘማቾች በሆኑ ጊዜ እኛ ዘንድ በነበሩ ኖሮ ባልሞቱ ባልተገደሉም ነበር እንደሚሉት ሰዎች አትሁኑ:: አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ጸጸት ያደርግባቸው ዘንድ ይህንን አሉ:: አላህ የፈለገውን ሕያው ያደርጋል:: የፈለገውን ይገድላልም:: አላህ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነው::"},{"id":157,"translation":"157. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በአላህ መንገድ ላይ ስትዋጉ ብትገደሉ ወይም ብትሞቱ ከአላህ የሆነው ምህረትና እዝነት እነርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት ሁሉ የእናንተ ምንዳ በላጭ ነው::"},{"id":158,"translation":"158. በጂሃድ ብትሞቱ ወይም ብትገደሉ ወደ አላህ ብቻ ትሰበሰባላችሁ::"},{"id":159,"translation":"159. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ ችሮታ ለዘብክላቸው:: አመለ መጥፎና ልበ ደረቅ በሆንክ ኖሮ ከአጠገብህ በተበተኑ ነበር:: ከእነርሱም ጥፋት ይቅር በል:: ለእነርሱም ከአላህ ምህረትን ለምንላቸው:: በሁሉም ነገር ላይ አማክራቸው:: ከዚያ ቁርጥ ሀሳብ ባደረገክ ጊዜ በአላህ ላይ ብቻ ተመካ:: አላህ በእርሱ ላይ ብቻ ተመኪዎችን ይወዳልና::"},{"id":160,"translation":"160. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ከረዳችሁ እናንተን የሚያሸንፍ የለም:: እርሱ ካዋረዳቸሁ ደግሞ ከእርሱ ማዋረድ በኋላ የሚረዳችሁ ያ ማን ነው? አማኞች በአላህ ላይ ብቻ ይመኩ።"},{"id":161,"translation":"161. የምርኮን ገንዘብ መደበቅ ከነብይ የሚሆን አይደለም። የምርኮን ገንዘብ የሚደብቅም በትንሳኤ ቀን የደበቀውን ነገር ተሸክሞ ይመጣል:: ከዚያ ነፍስ ሁሉ የስራዋን ዋጋ ትመነዳለች:: እነርሱም አይበደሉም።"},{"id":162,"translation":"162. የአላህን ውዴታ የተከተለ ሁሉ የአላህን ቁጣ እንዳተረፈና መኖሪያውም ገሀነም እንደሆነው ነውን? ገሀነም ማረፊያነቱ እጅግ ከፋ!"},{"id":163,"translation":"163. ሁሉም በአላህ ዘንድ ባለ ልዩ ልዩ ደረጃዎች ናቸው:: አላህ የሚሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::"},{"id":164,"translation":"164. አላህ በአማኞች ላይ ከመካከላቸው የሆነን፤ በእነርሱም ላይ አናቅጽን የሚያነብ፤ ከርክሰት የሚያጠራቸው፤ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን መልዕክተኛ በላከላቸው ጊዜ በእርግጥ ለገሰላቸው:: እነርሱም ከዚያ በፊት ግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ::"},{"id":165,"translation":"165. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ ያደረሳችሁትን ጥቃት ግማሽ በአገኛችሁ (በደረሰባችሁ) ጊዜ ይህ ከየት ነው የመጣብን አላችሁን? እርሱ ከነፍሶቻችሁ ዘንድ ነው:: አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።» በላቸው።"},{"id":166,"translation":"166. (የመልዕክተኛችን ባልደረቦች ሆይ!) ያ ሁለት ቡድኖች በተጋጠሙ ቀን የደረሰባችሁ በአላህ ፈቃድ ብቻ ነው:: የአማኞችን አቋም ሊፈትንና ማንነታቸውን ሊገልጽ ነው።"},{"id":167,"translation":"167. እነዚያንም የነፈቁትንና «ኑ በአላህ መንገድ ተጋደሉ ወይም ተከላከሉ።» የተባሉትን ሊገልጽ ነው ይህን ያደረገው። አስመሳዮቹም «ውጊያን ብናውቅ ኖሮ በተከተልናችሁ ነበር።» አሉ:: እነርሱም ያን ጊዜ ከእምነት ይልቅ ወደ ክህደት የቀረቡ ናቸው:: በልቦቻቸው የሌለውን በአፎቻቸው ይናገራሉ። አላህም የሚደብቁትን ሁሉ አዋቂ ነው።"},{"id":168,"translation":"168. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ ከትግል ወደ ኋላ የቀሩ ሲሆኑ ለወንድሞቻቸው «እኛን በታዘዙን ኖሮ ባልተገደሉ ነበር።» ያሉ ናቸው:: «እውነተኞችም ከሆናችሁ እስቲ ከነፍሶቻችሁ ላይ ሞትን ገፍትሩ።» በላቸው።"},{"id":169,"translation":"169. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም በአላህ መንገድ የተገደሉትን ሰማዕታት ሙታን አድርገህ አትገምታቸው:: በእርግጥ እነርሱ ጌታቸው ዘንድ ሕያው ናቸውና:: ከጌታቸው ዘንድም ሲሳይ ይለገሳሉ::"},{"id":170,"translation":"170. አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ተደሳቾች (ሲሆኑ ይመገባሉ):: በእነዚያም ከኋላቸው ገና ባልተከተሏቸውም (ባልሞቱትም እንደነርሱው ከተሰው) በእነርሱ ላይ ስጋትም ትካዜም የሌለባቸው ለመሆናቸው ይደሰታሉ።"},{"id":171,"translation":"171. በአላህ ጸጋ፤ ችሮታና የአማኞችን ምንዳ የማያጠፋ በመሆኑም ይደሰታሉ።"},{"id":172,"translation":"172. እነዚያን የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸው በኋላ ለአላህና ለመልዕክተኛው የታዘዙት ከእነርሱ መካከል በጎ ተግባርን ለሰሩና አላህንም ለፈሩት ሁሉ ታላቅ ምንዳ አለላቸው።"},{"id":173,"translation":"173. እነዚያም ሰዎች ለእነርሱ «ጠላቶች ለእናንተ ጦርን እንደገና አከማችተዋልና ፍሯቸው።» ያሏቸውና ይህም በእምነት ላይ እምነትን የጨመረላቸው ቃላቸዉም «በቂያችን አላህ ነው፤ እርሱም ምን ያምር መጠጊያ ነው!» ያሉ ናቸው።"},{"id":174,"translation":"174. ከዚያም የአላህን ጸጋና ችሮታ ይዘው ምንም ክፉ ነገር ሳይነካቸው በሰላም ተመለሱ:: የአላህን ውዴታም ተከተሉ:: አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና::"},{"id":175,"translation":"175. ይህ የሚያስፈራራችሁ ሰይጣን ብቻ ነው። ወዳጆቹን ያስፈራራችኋል። (አማኞች ሆይ!) የሰይጣንን ወዳጆችን አትፍሯቸው:: ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁም እኔን ብቻ ፍሩኝ::"},{"id":176,"translation":"176. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የእነዚያ ወደ ክህደት የሚቻኮሉ ሰዎች አድራጎት (ተግባር) አያሳዝንህ:: እነርሱ ፈጽሞ አላህን በምንም አይጎዱትምና:: አላህ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ እድልን ላያደርግ ይሻልና:: ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":177,"translation":"177. እነዚያ ክህደትን በእምነት የለወጡ ክፍሎች ሁሉ አላህን በምንም ነገር ፈጽሞ አይጎዱትም:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":178,"translation":"178. እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች ሁሉ እነርሱን ማዘግየታችንን ለነፍሶቻችን ደግ ነገር ነው ብለው አያስቡ:: እነርሱን የምናዘገያቸው ኃጢአትን እንዲጨምሩ ብቻ ነውና:: ለእነርሱም አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":179,"translation":"179. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) አላህ መጥፎውን ከመልካሙ እስከሚለይ ድረስ አማኞችን እናንተ ባላችሁበት ሁኔታ ላይ የሚተዋቸው አይደለም:: አላህም ሩቁን ነገር የሚያሳውቃችሁ አይደለም:: ግን አላህ ከመልዕክተኞቹ የሚሻውን ይመርጣል:: እናም በአላህና በመልዕክተኞቹም እመኑ:: ብታምኑና ብትጠነቀቁ ለእናንተ ታላቅ ምንዳ አለላችሁ::"},{"id":180,"translation":"180. እነዚያ አላህ ከችሮታው ከሰጣቸው ገንዘብ የሚነፍጉ ሰዎች ንፉግነት ደግ ተግባር አይምሰላቸው:: ይልቁንም እርሱ ለእነርሱ መጥፎ ባህሪ ነው:: ያንን በእርሱ የነፈጉበት ገንዘብ በትንሳኤ ቀን (እባብ ሆኖ) በአንገታቸው ይጠለቃሉ:: የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ ብቻ ነው:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::"},{"id":181,"translation":"181. አላህ የእነዚያን «አላህ ድሃ ነው እኛ ግን ከበርቴዎች ነን።» ያሉትን ሰዎች ቃል በእርግጥ ሰማ:: ያንን ያሉትንና ነብያትን ያለ ህግ መግደላቸውንም በእርግጥ እንጽፋለን:: «የማቃጠልንም ስቃይ ቅመሱ።» እንላቸዋለን።"},{"id":182,"translation":"182. ያ ስቃይ እጃችሁ ባሳለፉት ስራና አላህም ለባሮቹ በዳይ ባለመሆኑ ነው::"},{"id":183,"translation":"183. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ይህን ቃል የተናገሩት: «ለማንኛዉም መልዕክተኛ እሳት የምትበላው ቁርባን እስከሚያመጣልን ድረስ በሱ እንዳናምን አላህ ወደ እኛ አዝዟል።» ያሉ ናቸው:: «ብዙ መልዕክተኞች ከእኔ በፊት በግልጽ ተዓምራትና በዚያ ባላችሁት ቁርባን በእርግጥ መጥተውላችኋል:: እውነተኞች ከሆናችሁ ታዲያ ለምን ገደላቸኃቸው?» በላቸው::"},{"id":184,"translation":"184. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ካንተ በፊትም በግልጽ ተዐምራት፣ በጽሁፎች፣ በብሩህ መጽሐፍም የመጡ መልዕክተኞችም በእርግጥ (በእነርሱ መሰሎች) ተስተባብለዋል::"},{"id":185,"translation":"185. ነፍስ ሁሉ ሞትን በእርግጥ ቀማሽ ናት:: ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሳኤ ቀን ብቻ ነው:: ከእሳት እንዲርቅ ተደርጎ ገነት እንዲገባ የተደረገም በእርግጥ ምኞቱን አገኘ:: የቅርቢቱ ሕይወት ማታለያ እንጂ ሌላ አይደለችም::"},{"id":186,"translation":"186. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ ትፈተናላችሁ:: ከእነዚያ ከናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡትም ከእነዚያ በአላህ ካጋሩትም ቡድኖች ብዙ መጥፎ ነገሮችን ትሰማላችሁ:: ብትታገሱና ብትጠነቀቁ (በጣም ጥሩ ነው።) ይህ ተግባር ከታላላቅ ነገሮች አንዱ ነው።"},{"id":187,"translation":"187. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የእነዚያ መጽሐፍን የተሰጡትን ለሰዎች በእርግጥ «ልታብራሩት እንጂ ላትደብቁት» በማለት የያዘባቸውን ቃል ኪዳን አስታውስ:: እናም በጀርባዎቻቸው በኋላ ወረወሩት:: በእርሱም ጥቂትን ዋጋ ገዙበት:: የሚገዙትም ነገር ከፋ!"},{"id":188,"translation":"188. እነዚያን በሰሩት ነገር የሚደሰቱና ባልሰሩትም መመስገንን የሚወዱ ሰዎችን ከቅጣት በመዳን ላይ ናቸው ብለህ አታስባቸው:: ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸውና::"},{"id":189,"translation":"189. የሰማያትና የምድር ንግስና ለአላህ ብቻ ነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::"},{"id":190,"translation":"190. በሰማያትና በምድር መፈጠር፤ በሌሊትና በቀንም መተካካት ለባለ አእምሮዎች ሁሉ ታላላቅ ምልክቶች አሉት።"},{"id":191,"translation":"191. እነርሱም እነዚያ ቆመው ተቀምጠዉም በጎኖቻቸው ተጋድመዉም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑና (እንዲህም) የሚሉ ናቸው: «ጌታችን ሆይ! ይህን በከንቱ አልፈጠርከዉም ጥራት ይገባህ:: ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን።"},{"id":192,"translation":"192. «ጌታችን ሆይ! አንተ እሳት የምታስገባው ሰው ሁሉ በእርግጥ አዋረድከው:: ለበደለኞች ምንም ረዳቶች የሏቸዉም።"},{"id":193,"translation":"193. «ጌታችን ሆይ! እኛ በጌታችሁ እመኑ በማለት ወደ እምነት የሚጠራን ጠሪ ሰማንና ወዲያዉኑ አመንም::ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንም ማርልን ክፉ ስራዎቻችንንም አብስልን:: ከንጹሆች ሰዎች ጋርም ግደለን::"},{"id":194,"translation":"194. «ጌታችን ሆይ! በመልዕክተኞቹ አማካኝነት የሰጠኸንን፤ የገባህልንን የተስፋ ቃል ስጠን:: በትንሳኤ ቀንም አታዋርደን:: (አታሳፍረን::) አንተ ቀጠሮን አታፈርስምና።»"},{"id":195,"translation":"195. እናም ጌታቸው «እኔ ከናንተ ውስጥ የወንድንም ሆነ የሴትን መልካም ስራ ወሮታ አላጠፋም:: ከፊላችሁ የከፊሉ አካል ነው።» በማለት ልመናቸውን ተቀበላቸው:: እነዚያ ለዲን ሲሉ የተሰደዱ፣ ከአገሮቻቸዉም በግፍ የተባረሩ፣ በመንገዴም (ሁከት የደረሰባቸው)፣ የተጠቁ፣ የተጋደሉ እና የተገደሉም ክፉ ስራዎቻቸውን አብስላቸዋለሁ:: በስሮቻቸዉም ወንዞች የሚፈሰባቸውን ገነቶች አስገባቸዋለሁ:: እነርሱም ከአላህ ዘንድ የሆነን ከፍተኛ ምንዳ ይመነዳሉ:: አላህ እርሱ ዘንድ መልካም ምንዳ አለና::"},{"id":196,"translation":"196. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የእነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች በየአገሮች መንፈላሰስ አያታልህ።"},{"id":197,"translation":"197. አነስተኛ ጥቅም ነው። ከዚያ መኖሪያቸው ገሀነም ናት:: ገሀነም ደግሞ ማረፊያነቷ ምን ትከፋ!"},{"id":198,"translation":"198. እነዚያ ጌታቸውን የፈሩት ግን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ዘወታሪዎች ሲሆኑ አላህ ዘንድ የተሰጡ መስተንግዶዎች አሏቸው:: አላህ ዘንድ ያለውም ምንዳ ለበጎ ሰሪዎች ሁሉ በላጭ ነው::"},{"id":199,"translation":"199. ከመጽሐፉ ባለቤቶች መካከል አላህን ፈሪዎችና በአላህ አናቅጽም ጥቂትን ዋጋ የማይለውጡ ሲሆኑ በአላህና በዚያ ወደ እናንተ በተወረደው ቁርኣን በዚያም ወደ እነርሱ በተወረዱት ልዩ ልዩ መጽሐፍት የሚያምኑ ሰዎች አሉ:: እነዚያ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ተገቢው ምንዳቸው አለላቸው አላህ ምርመራው ፈጣን ነው::"},{"id":200,"translation":"200. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእሳት ቅጣት ትድኑ ዘንድ ታገሱ፣ ተበራቱም፣ በጦር ኬላ ላይ ሆናችሁም ሶላትን ተጠባበቁ:: አላህንም በትክክል ፍሩ::"}]},{"id":4,"verses":[{"id":1,"translation":"1. እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁን፤ ከእርሷም መቀናጆዋን (ሀዋን) የፈጠረውንና ከሁለቱም ብዙ ወንዶችንና ብዙ ሴቶችን የበተነውን ጌታችሁን (አላህን) ፍሩ:: ያንንም በእርሱ የምትጠያየቁበትን አላህን (ከሚያስቆጡ) ተግባራትና ዝምድናዎችን (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ:: አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና::"},{"id":2,"translation":"(እናንተ ኑዛዜ ተቀባዮች ሆይ! ) ለየቲሞች ገንዘቦቻቸውን ስጡ:: (ከመሀከሉም) መጥፎውንም በመልካሙ አትለውጡ:: ገንዘቦቻቸውን ወደ ገንዘቦቻችሁ (በመቀላቀል) አትብሉ:: እርሱ ትልቅ ኃጢአት ነውና::"},{"id":3,"translation":"3. (እናንተ ሙስሊም ወንዶች ሆይ) በናንተ ስር ያሉት ሴት የቲሞችን በማግባታችሁ አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ ከሴቶች መካከል ለእናንተ የመረጣችሁትን (ደስ ያሏችሁን) ሁለት ሁለት ሶስት ሶስትና አራት አራት አግቡ:: በሚስቶች መካከል አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ ግን አንዲትን ሴት ብቻ ወይም ንብረታችሁ የሆኑት ሴት ባሪያዎችን ብቻ (በሚስትነት) ያዙ:: ይህም (ሴትን ልጅ) እንዳትበድሉ በጣም የቀረበ ተግባር ነው::"},{"id":4,"translation":"4. ለሴቶች መህሮቻቸውን ደስተኞች ሆናችሁ ስጧቸው። ለእናንተ ከእርሱ የተወሰነን ነገር ራሳቸው ቢለግሱላችሁ ግን በእርካታና በምቾት ሆናችሁ ብሉት (ተጠቀሙበት)።"},{"id":5,"translation":"5. (ኃላፊዎች ሆይ!) ያን አላህ ለእናንተ መቋቋሚያ (መጠቃቀሚያ) ያደረገላችሁን ገንዘባችሁን (የያዛችሁላቸውን) ለቂሎች (ለአዕምሮ ደካሞች) አትስጧቸው:: ከእርሷም መግቧቸው:: ከእርሷ አልብሷቸዉም:: ለእነርሱም መልካምን ንግግር ተናገሯቸው።"},{"id":6,"translation":"6. (ሙስሊሞች ሆይ!) የቲሞችን ለጋብቻ እስከደረሱ ድረስ ፈትኗቸው:: ከእነርሱም ብልህነትን ብታውቁ ገንዘቦቻቸውን ስጧቸው:: በማባከንና ማደጋቸውን በመሽቀዳደም ገንዘቦቻቸውን አትብሉባቸው:: (ከአሳዳጊዎቹ መካከል) ሀብታም የሆነ ሰው ከገንዘቦቻቸው (ቅንጣት ያህል እንኳን ከመቅረብ) ይከልከል:: ደሃ የሆነ ሰዉም ቢሆን ለድካሙ ብቻ በአግባቡ ይብላ:: ገንዘቦቻቸውን ወደ እነርሱ በሰጣችሁም ጊዜ በእነርሱ ላይ አስመስክሩ:: በተጠባባቂነትም አላህ በቂ ነው::"},{"id":7,"translation":"7. ለወንዶች ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ሲሞቱ ከተውት (ጥሪት ገንዘብ የውርስ) ድርሻ አላቸው:: ለሴቶችም ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተውት ከእርሱ ይነስም ይብዛም (የውርስ) ድርሻ አላቸው:: ለሁሉም የተወሰነ ድርሻ ተደንግጓል::"},{"id":8,"translation":"8. የውርስ ክፍፍልን (ወራሽ ያልሆኑ) የዝምድና ባለቤቶች፤ የቲሞችና ሚስኪኖች በተገኙበት ጊዜ ከእርሱ ለግሱላቸው:: መልካምንም ንግግር ተናገሯቸው::"},{"id":9,"translation":"9. እነዚያ ከኋላቸው ደካማ ዝርያዎችን ቢተው ኖሮ በእነርሱ ላይ ምን ይደርስባቸው ይሆን ብለው የሚሰጉ ሰዎች ሁሉ (በየቲሞችም ላይ) ይህንኑ ይፍሩ:: አላህንም ይፍሩ:: ትክክለኛንም ቃል ይናገሩ::"},{"id":10,"translation":"10. እነዚያ የየቲሞችን ገንዘቦች በግፍ የሚበሉ ሁሉ በሆዶቻቸው ውስጥ የሚበሉት እሳትን ብቻ ነው:: የገሀንም እሳትንም በእርግጥ ይገባሉ::"},{"id":11,"translation":"11. (ሰዎች ሆይ) አላህ በልጆቻችሁ ውርስ (በሚከተለው መልኩ) ያዛችኋል:: ለወንዱ የሁለት ሴቶች ድርሻ ያህል አለው:: (ሁለት ወይም) ከሁለት በላይ የሆኑ ሴቶች ልጆች ብቻ ወራሽ ቢሆኑ ለእነርሱ (ሟቹ) ከተወው (ሀብት) ከሶስት ሁለት እጁ ያገኛሉ (አላቸው):: አንዲት ሴት ወራሽ ብትሆን ደግሞ ለእርሷ የሀብቱ ግማሽ አላት:: ለሟቹ ልጅ ካለው ለአባቱና ለእናቱ ከሁለቱ ለእያንዳንዱ ከስድስት አንድ አላቸው:: ለእርሱ ልጅ ባይኖረውና ወላጆቹ ብቻ ቢወርሱት ለእናቱ ሲሶው አላት:: ለእርሱም ወንድሞችና እህቶች ቢኖሩት ለእናቱ ከስድስት አንድ አላት:: (ይህም ውርስ) የሚከፋፈለው ከተናዘዘው ኑዛዜ ወይም ከእዳው ክፍያ በኋላ ነው:: አባቶቻችሁና ልጆቻችሁ ለእናንተ በመጥቀም ማንኛቸው ይበልጥ ቅርብ እንደሆኑ አታውቁም:: ይህም ከአላህ የተደነገገ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነዉና::"},{"id":12,"translation":"12. ለእናንተም ሚስቶቻችሁ ከተውት ንብረት ለእነርሱ ልጅ ካልኖራቸው ግማሹ አላችሁ:: ለእነርሱም ልጅ ቢኖራቸው ከተውት ሀብት ከአራት አንድ አላችሁ :: (ይህም) በእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከእዳ ክፍያ በኋላ ነው:: ለእናንተም ልጅ ከሌላችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ (ለሚስቶቻችሁ) አንድ አራተኛ አላቸው። ለእናንተም ልጅ ባይኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ (ለሚስቶቻችሁ) ከስምንት አንድ አላቸው:: (ይህም) ከምትናዘዙበት ኑዛዜ ወይም ከእዳ ክፍያ በኋላ ነው:: ወላጆችም ልጅም የሌለውና የጎን ወራሾች የሚወርሱት ወንድ ወይም ሴት ቢገኝ ለእርሱም (ለሟቹ) ከእናቱ በኩል ብቻ የሆኑ ወንድም ወይም እህት ቢኖሩት ከሁለቱ ለእያንደንዳቸው ከስድስት አንድ አላቸው:: ከአንድ የበዙ ቢሆኑ ደግሞ በሲሶው ላይ ተጋሪዎች ናቸው:: ይህም ወራሾቹን የማይጎዳ ሆኖ ከእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከእዳ በኋላ ነው:: ከአላህም የሆነን ኑዛዜ ያዛችኋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ቻይ ነውና።"},{"id":13,"translation":"13. እነዚህ የአላህ ውሳኔዎች ናቸው:: አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዙ ሰዎች ሁሉ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያስገባቸዋል። ይህም ትልቅ እድል ነው።"},{"id":14,"translation":"14. በአላህና በመልዕክተኛው ላይ የሚያምጽ ወሰኖችንም የሚተላለፍ ሁሉ በውስጧ ዘውታሪ ሲሆን ወደ ገሀነም እሳት ያስገባዋል:: ለእርሱም አዋራጅ ቅጣት አለበት።"},{"id":15,"translation":"15. እነዚያ ከሴቶቻችሁ መካከል ዝሙትን የሚሰሩ በእነርሱ ላይ ከናንተ የሆነን አራት ታማኝ ወንዶችን አስመስክሩባቸው:: ከመሰከሩባቸዉም ሞት እስከሚደርስባቸው ወይም አላህ ለእነርሱ ሌላ መንገድን እስከሚያደርግ ድረስ በቤቶች ውስጥ ያዟቸው(እሰሯቸው::)"},{"id":16,"translation":"16. እነዚያ ከእናንተ ውስጥ ዝሙትን የሚሰሩትን አሰቃዩዋቸው (በሚገባ ቅጧቸው):: ቢጸጸቱና ስራቸውን ቢያሳምሩ ግን እነርሱን ተዋቸው (አታሰቃዩዋቸው።) አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና።"},{"id":17,"translation":"17. ጸጸትን መቀበል ከአላህ በኩል ለእነዚያ ኃጢአትን በስህተት ለሚሰሩና ከዚያም ወዲያውኑ ለሚጸጸቱ ነው:: እነዚያንማ አላህ ከእነርሱ ጸጸትን ይቀበላል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና፣"},{"id":18,"translation":"18. ጸጸትን መቀበል ለእነዚያ ኃጢአቶችን ለሚሰሩና ልክ ሞት በመጣባቸው ጊዜ «አሁን ተጸጸትኩ።» ለሚሉና ለእነዚያም ከሓዲያን ሆነው ለሚሞቱ አይደለም:: ለእነርሱማ አሳማሚን ቅጣት አዘጋጅተናል።"},{"id":19,"translation":"19. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሴቶችን ያስገደዳችሁ ሆናችሁ ልትወርሱና ግልጽ የሆነ መጥፎ ስራ ካልሰሩ በስተቀር ከሰጣችኋቸው ከፊሉን ልትወስዱባቸውና ልታጉላሏዋቸው አይፈቀድላችሁም:: በመልካም ተኗኗሯቸው:: ብትጠሏቸዉም እንኳን ታገሱ:: አንድ ነገር ብትጠሉትም አላህ በእርሱ ዉስጥ ብዙ ደግ ነገሮችን ሊያደርግላችሁ ይችላልና::"},{"id":20,"translation":"20. (ባሎች ሆይ!) በሚስት ቦታ ሌላ ሚስትን ለመለወጥ ብትፈልጉ (ለምትፈታው ሴት ቀደም ሲል) ብዙን ገንዘብ የሰጣችኋት እንደሆነ ከእርሷ ምንንም አትውሰዱባት:: በመበደልና ግልጽ በሆነ ኃጢአት ትወስዱታላችሁን?"},{"id":21,"translation":"21. ከፊላችሁ ወደ ከፊሉ የደረሰ ሲሆንና ከናንተ ላይም (ሴቶች) የጠበቀ ቃል ኪዳንን የያዙባችሁ ሲሆኑ እንዴት ትወስዱታላችሁ?"},{"id":22,"translation":"22. (ወንዶች ሆይ!) ከሴቶች መካከል አባቶቻችሁ ያገቧቸውን አታግቡ። ያለፈው ሲቀር። እርሱ መጥፎና የተጠላ ስራ ነውና። መንገድነቱም ከፋ።"},{"id":23,"translation":"23. (ወንዶች ሆይ!) እናቶቻችሁ፤ ሴት ልጆቻችሁ፤ እህቶቻችሁ፤ አክስቶቻችሁ (የአባቶቻችሁ እህቶች)፣ አክስቶቻችሁ (የእናቶቻችሁ እህቶች)፤ የወንድም ሴት ልጆች፤ የእህት ሴት ልጆች፤ እነዚያም ያጠቧችሁ የጡት እናቶቻችሁ፤ የጡት እህቶቻችሁ፤ የሚስቶቻችሁ እናቶች፤ እነዚያም ከጉያዎቻችሁ ያሉት የእነዚያ ግብረ ስጋ ግንኙነት የፈጸማችሁባቸው ሚስቶቻችሁ ሴት ልጆች ልታገቧቸው በእናንተ ላይ እርም ተደረጉባችሁ:: ግብረ ስጋ ግንኙነት ያልፈጸማችሁባቸው የሚስቶቻችሁ ሴት ልጆቻቸውን ብታገቡ ግን በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም:: የእነዚያ ከጀርባዎቻችሁ የሆኑት ወንዶች ልጆቻችሁ ሚስቶችም ሁለት እህትማማቾችን በአንድ መሰብሰብም እንደዚሁ እርም ነው:: ከዚህ በፊት ያለፈው ሲቀር:: እርሱንስ ተምራችኋል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።"},{"id":24,"translation":"24. ባል ያገቡ ሴቶችም በጦርነት እጆቻችሁ በምርኮ የያዟቸው ሲቀሩ (በእናንተ ላይ እርም ናቸው):: ይህን ህግ አላህ በእናንተ ላይ ደነገገ:: ከነዚህ ከተከለከሉት ሌላ ጥብቆች ሆናችሁና ዝሙተኞች ሳትሆኑ በገንዘባችሁ ጋብቻን ልትፈለጉ ለእናንተ ተፈቀደ:: እናም ከእነርሱም መገናኘት የተጠቀማችሁባቸውን ሴቶች መህሮቻቸውን ልትሰጧቸው ግዴታ ነው:: ከመወሰን በኋላ በተዋደዳችሁበት ነገር በእናንተ ላይ ኃጢአት የለም:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":25,"translation":"25. (ወንዶች ሆይ!) ከናንተ መካከል ጥብቆች ምዕመናትን ለማግባት ሀብትን ያልቻለ ሰው እጆቻችሁ ንብረት ካደረጓቸው ከምዕመናት መካከል ወጣቶቻችሁን አገልጋዬች የመረጠውን ያግባ:: አላህ የውስጥ እምነታችሁን ምንነት አዋቂ ነውና:: ከፊላችሁ ከከፊሉ የተራባ ነው:: ባሮችንም ቢሆን እንደዚሁ በአሳዳሪዎቻቸው ፈቃድ ብቻ አግቧቸው:: መህሮቻቸውንም በመልካም መንገድ ስጧቸው:: ጥብቆች ሆነው ዝሙተኛ ያልሆኑ የስርቆሽ ወዳጅንም ያልያዙ እንደሆኑ አግቧቸው:: በማግባት በተጠበቁም ጊዜ መጥፎን ስራ ቢሰሩ በእነርሱ ላይ የተደነገገው ቅጣት በነፃዎቹ ላይ ከተደነገገው ቅጣት ግማሹ ቅጣት አለባቸው:: ያ ከናንተ መካከል ዝሙትን ለፈራ ብቻ ነው:: መታገሳችሁ የተሻለ ነው:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።"},{"id":26,"translation":"26. (አማኞች ሆይ!) አላህ የሃይማኖታችሁን ህግጋት ሊያብራራላችሁ፤ ከናንተ በፊትም የነበሩትን ነብያት ፈለጎች ሊመራችሁ፤ በእናንተም ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::"},{"id":27,"translation":"27. አላህ በእናንተ ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል:: እነዚያ ፍላጎታቸውን የሚከተሉ ግን ከእውነት ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ::"},{"id":28,"translation":"28. አላህ ከናንተ ሊያቃልልላችሁ ይሻል። ሰው ደካማ ሆኖ የተፈጠረ ነውና::"},{"id":29,"translation":"29. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁን በመካከላችሁ ያለ አግባብ አትብሉ:: በእናንተ መካከል በመስማማት የሆነችውን ንግድ ካልሆነች በስተቀር (እሷን ግን ብሉ) :: ነፍሶቻችሁን በራሳችሁ አትግደሉ። አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና::"},{"id":30,"translation":"30. ወሰን በማለፍ እና በመበደል ይህን የሰራ ሁሉ እሳት እናስገባዋለን:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነውና።"},{"id":31,"translation":"31. ትክክለኛ አማኞች ሆይ! ከተከለከላችሁት ወንጀሎች መካክል ታላላቆችን ብትርቁ ትናንሽ ኃጢአቶቻችሁን እናብስላችኋለን:: የተከበረውንም መግቢያ (ገነት) እናስገባችኋለን::"},{"id":32,"translation":"32. አላህ ከፊላችሁን በከፊሉ ያበለጠበትን ጸጋ አትመኙ:: ለወንዶችም ከሰሩት ስራ እድል አለላቸው:: ለሴቶችም ከሰሩት ስራ እንዲሁ እድል አለላቸው:: አላህን ከችሮታው ለምኑት:: አላህ በሁሉ ነገር አዋቂ ነውና::"},{"id":33,"translation":"33. ለሁላችሁም ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተውት ሀብት ወራሾችን አድርገናል:: እነዚያንም (ለመረዳዳትና ለመዋረስ) በመሐላዎቻችሁ የተዋዋላችኋቸውን (ከስድስት አንድ) ድርሻቸውን ስጧቸው:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ (መስካሪ) ነው::"},{"id":34,"translation":"34. ወንዶች ለሴቶች ቋሚና የበላይ አስተዳዳሪዎች ናቸው:: አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና ወንዶች ከገንዘቦቻቸው ለሴቶች በመስጠታቸው ምክኒያት ነው:: መልካሞቹ ሴቶች ማለት ለባሎቻቸው ታዛዦች፤ አላህ ባስጠበቀው ነገር ከባሎቻቸው ሩቅ የሆነውን ጠባቂዎች ናቸው:: እነዚያን ማመፃቸውን የምትፈሩትን ሴቶች መጀመሪያ ገስጿቸው:: ከዚያም በመኝታቸው ተለዩዋቸው:: ከዚያም (በአካሎቻቸው ላይ ሳካ ሳታደርሱ) ምቷቸው:: ከታዘዟችሁ ለመጨቆን ስትሉ በእነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ:: አላህ የሁሉም በላይና ታላቅ ነውና::"},{"id":35,"translation":"35. በመካከላቸውም ጭቅጭቅ መኖሩን ብትፈሩ (ብታውቁ) ከቤተሰቡና ከቤተሰቦቿ የተውጣጡ የቤተ ዘመድ ጉባኤ አዋቅሩ:: ሁለቱም እርቅን ቢሹ አላህ በመካከላቸው ያስማማቸዋል:: አላህ ግልጽንም ሆነ ውስጥንም አዋቂ ነውና::"},{"id":36,"translation":"36. አላህን ተገዙ:: በእርሱ ምንንም አታጋሩ። ለወላጆች፣ ለቅርብ ዝምድና ባለቤቶች፣ ለየቲሞች፣ ለምስኪኖች፣ ለቅርብ ጎረቤት፣ ለሩቅ ጎረቤት፣ ለጎን ባልደረባ፣ ለመንገደኛ፣ እጆቻችሁ ንብረት ላደረጓቸው ባሮች መልካምን ስሩ። አላህ ኩራተኞችንና ጉረኞችን አይወድምና::"},{"id":37,"translation":"37. እነዚያ የሚሰስቱ ንፉጎችና ሰዎችንም በመሰሰት (በንፍግና) የሚያዝዙ አላህ ከችሮታው የሰጣቸውን ጸጋ የሚደብቁ ብርቱን ቅጣት ይቀጣቸዋል። ለከሓዲያንም አዋራጅን ቅጣት አዘጋጅተናል።"},{"id":38,"translation":"38. እነዚያ ለሰዎች ይዩልን ሲሉ ገንዘቦቻቸውን የሚሰጡ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የማያምኑ ይቀጣሉ:: ሰይጣንም የእሱ ጓደኛው የሆነለት ሁሉ ጓደኛነቱ ከፋ!"},{"id":39,"translation":"39. በአላህና በመጨረሻው ቀን ባመኑና አላህ ከሰጣቸዉም ሲሳይ በለገሱ ኖሮ በእነርሱ ላይ ምን ጉዳት ነበረ? አላህ በእነርሱ ሁኔታ አዋቂ ነውና::"},{"id":40,"translation":"40. አላህ የብናኝን ክብደት ያህል እንኳን አይበድልም:: መልካም ስራ ብትሆንም ይደራርባታል:: ከእርሱም ዘንድ ታላቅን ምንዳ ይሰጣል::"},{"id":41,"translation":"41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሕዝቦች ሁሉ መስካሪን ባመጣንና አንተንም በእነዚህ (ባንተ ህዝቦች) ላይ መስካሪ አድርገን በምናመጣህ ጊዜ የከሓዲያን ሁኔታ እንዴት ይሆን?"},{"id":42,"translation":"42. በዚያ ቀን እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎችና መልዕክተኛውን ያልታዘዙት ምድር በእነርሱ ላይ ብትደፋባቸው ይመኛሉ:: ከአላህም ወሬን አይደብቁም።"},{"id":43,"translation":"43. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የምትሉትን ነገር ለይታችሁ አስከምታውቁ ድረስ የሰከራችሁ ሆናችሁ ወደ ሶላት አትቅረቡ:: ጀናባ ስትሆኑም መንገድን አላፊዎች ካልሆናችሁ በስተቀር ሙሉ አካላታችሁን እስከምትታጥቡ ድረስ መስጊድን አትቅረቡ:: በሽተኞች ወይም በጉዞ ላይ ብትሆኑ ወይም ከናንተ አንዱ ከአይነ ምድር ቢጸዳዳ ወይም ከሴቶች ጋር ብትነካኩና ( የግብረስጋ ግንኙነት ብትፈጽሙና) ውሃን ባታገኙ ንጹህ የሆነን የምድር ገጽ (አፈርን) አብሱ:: ከዚያ ፊቶቻችሁንና እጆቻችሁን በእርሱ አብሱ:: አላህ ይቅር ባይና መሀሪ ነውና።"},{"id":44,"translation":"44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ከመጽሐፉ የእውቀት ድርሻን ወደ ተሰጡት ክፍሎች አላየህም? ጥመትን በቅንነት ይገዛሉ:: መንገድንም እንድትሳሳቱ ይፈልጋሉ።"},{"id":45,"translation":"45. (ትክክለኛ አማኞች ሆይ!) አላህ ጠላቶቻችሁን ከናንተ በበለጠ አዋቂ ነው:: ጠባቂነትም በአላህ በቃ:: ረዳትነትም በአላህ በቃ።"},{"id":46,"translation":"46. ከእነዚያ ከአይሁዳውያን መካከል ንግግሮችን ከስፍራዎቹ የሚያጣምሙ አሉ። «ንግግርክን ሰማንና ትእዛዝክን አመጽን፤ የማትሰማም ስትሆን እስቲ ስማ።» ይላሉ:: በምላሶቻቸዉም ለማጣመምና ሃይማኖትንም ለመዝለፍ በማሰብ \"ራዒና\" ይላሉ:: እነርሱም «ሰማንና ታዘዝን፤ ስማን ተመልከተንም።» ባሉ ኖሮ ለእነርሱም መልካምና ትክክለኛ በሆነ ነበር:: ግን በክህደታቸው ምክንያት አላህ ረገማቸው:: ከእነርሱም መካከል ጥቂቶች እንጂ አያምኑም።"},{"id":47,"translation":"47. እናንተ መጽሐፉ የተሰጣችሁ ሰዎች ሆይ! ፊቶችን ሳናዞርና በጀርባዎች ላይ ሳንመልሳቸው ወይም የሠንበትን ባለቤቶች እንደረገምን ሳንረግማችሁ በፊት ከናንተ ጋር ያለውን የሚያረጋግጥ ሆኖ በአወረድነው ቁርኣን እመኑ:: የአላህም ትዕዛዝ ተፈፃሚ ነው።"},{"id":48,"translation":"48. አላህ በእርሱ ማጋራትን ፈጽሞ አይምርም:: ከዚህ በታች (ውጭ) ያለውን ኃጢአት ግን ለሚሻው ሁሉ ይምራል:: በአላህ የሚያጋራ ሁሉ ታላቅን ኃጢአት በእርግጥ ቀጠፈ::"},{"id":49,"translation":"49. ወደ እነዚያ ነፍሶቻቸውን ወደ ሚያጠሩት (ሚያወድሱት) አላየህምን? ይልቁንም አላህ ነው የሚፈልገውን የሚያጠራው። በተምር ፍሬ ስንጥቅ ላይ ያለችን ክር መሳይ ያህልም ቢሆን አይበደሉም።"},{"id":50,"translation":"50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ ላይ ውሸትን እንዴት እንደሚቀጥፉ ተመልከት። ግልጽ ወንጀል በርሱ በቃ።"},{"id":51,"translation":"51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ከመጽሐፉ ድርሻን ወደ ተሰጡት አላየህምን? በድግምትና በጣዖት ያምናሉ። ለእነዚያ በአላህ ለካዱትም እነርሱ በሃይማኖት ከእነዚያ በሙሐመድ ካመኑት ይበልጥ ቀና እንደሆኑ ይናገራሉ።"},{"id":52,"translation":"52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ አላህ የረገማቸው ናቸው:: አላህ የረገመውን ደግሞ ለርሱ ፈጽሞ ረዳት አታገኝለትም።"},{"id":53,"translation":"53. በእውነቱ ለእነርሱ ከንግስናው ፈንታ አላቸውን? ያን ጊዜማ ለሰዎች በተምር ፍሬ ላይ ያለችውን ነጥብ ያህል እንኳን አይሰጡም ነበር።"},{"id":54,"translation":"54. ይልቁንም ለሰዎች አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ላይ ይመቀኛሉን? ለኢብራሂምም ቤተሰቦች መጽሐፍንና ጥበብን በእርግጥ ሰጠን:: ታላቅንም ንግስናን ሰጠናቸው::"},{"id":55,"translation":"55. ከነሱም (ከአይሁድ) መካከል በነብዩ ሙሐመድ ያመነ አለ:: ከእነርሱም ከዚህ እምነት ያፈገፈገ አለ። አቃጣይነት በገሀነም በቃ።"},{"id":56,"translation":"56. እነዚያን በተዐምራታችን የካዱትን ሁሉ በእርግጥ እሳትን እናስገባቸዋለን:: ስቃይን እንዲቀምሱም ቆዳዎቻቸው በተቃጠሉ ቁጥር ሌሎችን ቆዳዎች እንለውጥላቸዋለን:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::"},{"id":57,"translation":"57. እነዚያ በአላህ አንድነት ያመኑና መልካም ስራዎችን የሰሩ ከስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘላለም በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ በእርግጥ እናስገባቸዋለን:: ለእነርሱ በውስጧ ንጹህ ሚስቶችም አሏቸው:: የምታስጠልልን ጥላም እናስገባቸዋለን::"},{"id":58,"translation":"58. አላህ አደራዎችን ወደ የባለቤቶቻቸው እንድታደርሱና በሰዎች መካከል በፈረዳችሁ ጊዜም በትክክል እንድትፈርዱ ያዛችኋል:: አላህ በእርሱ የሚገስፃችሁ ነገር ምን ያምር ነው! አላህ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን ተመልካች ነውና።"},{"id":59,"translation":"59. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ታዘዙ:: መልዕክተኛውን እና ከመካከላችሁም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ:: በማንኛዉም ነገር ብትከራከሩም በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ከሆናችሁ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው መልሱት:: ይህ የተሻለ እና መጨረሻዉም ያማረ ነው::"},{"id":60,"translation":"60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ «ባንተ ላይ በተወረደውና ካንተ በፊትም በተወረደው አምነናል።» ወደ ሚሉት አላየህምን? በእርሱ እንዲክዱ በእርግጥ የታዘዙ ሲሆኑ ወደ ጣኦት መፋረድን ይፈልጋሉ:: ሰይጣንም ከእውነት የራቀን መሳሳት ሊያሳስታቸው ይፈልጋል።"},{"id":61,"translation":"61. ለእነርሱም፡- «አላህ ወደ አወረደው ቁርኣንና ወደ መልዕክተኛው ኑ።» በተባሉ ጊዜ አስመሳዮችን ካንተ በሀይል ሲሸሹ ታያቸዋለህ።"},{"id":62,"translation":"62. እጆቻቸዉም ባስቀደሙት ጥፋት ምክንያት መከራ በደረሰባቸውና ከዚያ «ደግን ሀሳብና ማስማማትን እንጂ ሌላን አልፈለግንም።» በማለት በአላህ የሚምሉ ሆነው ወደ አንተ በመጡ ጊዜ እንዴት ይሆናል?"},{"id":63,"translation":"63. እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው:: ከእነርሱ ራስህን አግልል:: ገስፃቸዉም:: ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ጠልቆ የሚገባ ጠንካራ ቃል ተናገራቸው።"},{"id":64,"translation":"64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ማንንም መልዕክተኛ በአላህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጂ አልላክንም:: እነርሱም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ ወደ አንተ መጥተው አላህን ምህረት በለመኑና መልዕክተኛዉም ለእነርሱ ምህረትን በለመነላቸው ኖሮ አላህን ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ሆኖ ባገኙት ነበር።"},{"id":65,"translation":"65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጉዳዩ እነርሱ እንዳሉት አይደለም:: በጌታህ እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ የሚያስፈርዱህ ሆነው ከዚያ ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አማኝ አይሆኑም::"},{"id":66,"translation":"66. እኛም በእነርሱ ላይ፡- «ነፍሶቻችሁን ግደሉ» ወይም «ከአገሮቻችሁ ውጡ» ማለትን በፃፍን ኖሮ ከእነርሱ ጥቂቶቹ እንጂ ባልሰሩት (ባልተገበሩት) ነበር። የሚገሰጹበትን ነገር በተገበሩት ኖሮ ለእነርሱ መልካምና በእምነታቸው ላይ ለመርጋትም በጣም የበረታ በሆነ ነበር።"},{"id":67,"translation":"67. ያን ጊዜ ደግሞ ከእኛ ዘንድ ታላቅን ምንዳ በሰጠናቸው ነበር።"},{"id":68,"translation":"68. ቀጥተኛውንም መንገድ በእርግጥ በመራናቸው ነበር::"},{"id":69,"translation":"69. አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ፀጋውን ከዋለላቸው ከነብያት፤ ከፃድቃን፤ ከሰማዕታትና ከመልካሞቹ ጋር ይሆናሉ። የእነዚያም ጓደኝነት አማረ።"},{"id":70,"translation":"70. ይህ ችሮታ ከአላህ የተለገሰ ነው:: አዋቂነትም በአላህ በቃ::"},{"id":71,"translation":"71. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጥንቃቄያችሁን ያዙ:: ክፍልፍልም ወይም በአንድ ሆናችሁ ለዘመቻ ውጡ::"},{"id":72,"translation":"72. ከናንተ ውስጥ በእርግጥ ከዘመቻ ወደ ኋላ የሚንጓደድ (የሚጎተት) ሰው አለ:: አደጋም ካገኛችሁ «ከእነርሱ ጋር ተሳታፊ ባለመሆኔ አላህ በእኔ ላይ በእርግጥ ጸጋውን ዋለልኝ።» ይላል።"},{"id":73,"translation":"73. ከአላህ የሆነ ችሮታ ካገኛችሁ ደግሞ በእናንተና በእርሱ መካከል ፍቅር አንዳልነበረ ሁኖ «ታላቅ እድል አገኝ ዘንድ ምን ነው ከእነርሱ ጋር በሆንኩ?» ይላል።"},{"id":74,"translation":"74. እናም እነዚያ ቅርቧን ህይወት በመጨረሻይቱ ሕይወት የሚለውጡ (የሚገዙ) በአላህ መንገድ ይጋደሉ:: በአላህ መንገድ የሚጋደልና ከዚያ የሚገደል ወይም የሚያሸንፍ ሁሉ ታላቅ ምንዳን በእርግጥ እንሰጠዋለን።"},{"id":75,"translation":"75. (አማኞች ሆይ!) በአላህ መንገድና ከወንዶች፣ ከሴቶችና ከልጆችም የሆኑትን እነዚያን፡- «ጌታችን ሆይ! ከዚህች ባለቤቶቿ በዳይ ከሆኑባት ከተማ አውጣን፤ ካንተም ዘንድ ለእኛ አሳዳሪን አድርግልን፤ ካንተ ዘንድም ለእኛ ረዳትን አድርግልን።» የሚሉትን ደካሞች ሰዎች ለማዳን የማትዋጉት ለምንድ ነው?"},{"id":76,"translation":"76. እነዚያ ያመኑት በአላህ መንገድ ይዋጋሉ:: እነዚያ በአላህ የካዱት ደግሞ በጣኦት መንገድ ይዋጋሉ:: እናም (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የሰይጣን ቡድኖችን ተፋለሙ:: የሰይጣን ተንኮል ደካማ ነውና::"},{"id":77,"translation":"77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ለእነርሱ፡- «እጆቻችሁን ከመጋደል ሰብስቡ፤ ሶላትን ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፤ ግዴታ ምጽዋትን ስጡ።» ወደ ተባሉት አላየህምን? በእነርሱ ላይ መጋደል ግዴታ በሆነባቸው ጊዜ ደግሞ ከእነርሱ መካከል ከፊሎቹ ወዲያውኑ ሰዎችን ልክ አላህን እንደሚፈሩ ወይም የበለጠ ይፈራሉ:: «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መጋደልን ለምን ደነገግህ? እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አታቆየንም ኖሯልን?» ይላሉ:: «የቅርቢቱ ሕይወት ጥቅም አነስተኛ ነው:: የመጨረሻይቱ ዓለም ጥቅም ግን አላህን ለሚፈራ ሁሉ በላጭ ነው። በተምር ፍሬ ውስጥ ያለችን ክር መሰል ያህል እንኳ አትበደሉም።» በላቸው።"},{"id":78,"translation":"78. የትም ስፍራ ብትሆኑ ሞት ያገኛችኋል:: በጠነከሩ ህንፃዎች ውስጥም ብትደብቁ እንኳን:: ደግ ነገር ካገኛቸው «ይህ ከአላህ ዘንድ የመጣ ነው።» ይላሉ:: መከራ ካገኛቸው ግን «ይህ ካንተ ዘንድ የመጣ ነው።» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁሉም (ደጉም ክፉዉም) ከአላህ ዘንድ የመጣ ነው።» በላቸው:: እነዚህ ሰዎች ንግግርን ሊረዱ የማይቀርቡት ለምንድን ነው?"},{"id":79,"translation":"79. (የሰው ልጅ ሆይ!) ደግ ነገር የሚያገኝህ ከአላህ ችሮታ ነው:: የሚደርስብህ መከራ ግን ከራስህ ጥፋት የተነሳ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለሰዎች ሁሉ መልዕክተኛ አድርገን ላክንህ:: መስካሪነትም በአላህ በቃ::"},{"id":80,"translation":"80. መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ በእርግጥ አላህን ታዘዘ:: ከትዕዛዝም የሸሸው ጉዳዩ አያሳስብህ:: በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አላክንህምና::"},{"id":81,"translation":"81. አጠገብህ ሲሆኑ የአንተ ታዛዥ ነን ይላሉ:: ካንተ ዘንድ በወጡ ጊዜ ከእነርሱ ከፊሎቹ ከዚያ በአጠገብህ ከሚሉት ሌላን በልቦቻቸው ያሳድራሉ:: አላህ በልቦቻቸው የሚያሳድሩትን ነገር ሁሉ ይጽፋል:: ስለዚህ ተዋቸውና በአላህ ላይ ብቻ ተመካ:: መመኪያነት አላህ ብቻ በቃ::"},{"id":82,"translation":"82. ቁርኣንን አያስተነትኑምን? ከአላህ ሌላ ዘንድ የመጣ በነበረ ኖሮ በውስጡ ብዙ መለያየትን ባገኙ ነበር::"},{"id":83,"translation":"83. ሰላምን ወይም ስጋትን የሚመለከት ወሬ በመጣላቸው ጊዜ እርሱን ያሰራጫሉ (ያጋንናሉ)። ወደ መልዕክተኛውና ከእነርሱ መካከል የጉዳይ ባለቤቶች ወደ ሆኑት አዋቂዎቹ በመለሱት ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ መካከል ነገሩን በትክክል የሚረዱት ክፍሎች ባወቁት ነበር:: በእናንተ ላይ የአላህን ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከጥቂቶቹ በስተቀር ሰይጣንን በተከተላችሁ ነበር።"},{"id":84,"translation":"84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ መንገድ ተዋጋ:: ራስህን እንጂ ሌላን አትገደድም:: አማኞችንም በአላህ መንገድ ላይ በመዋጋት ላይ አደፋፍራቸው:: አላህ የእነዚያን የካዱትን ሰዎች ኃይል ሊከለክል ይከጀላል:: አላህ በሃይል በመያዙ የበረታና ቅጣቱም የጠነከረ ነው::"},{"id":85,"translation":"85. መልካም መታደግን የሚታደግ (ሽምግልናን የሚሸመግል) ሰው ሁሉ ለራሱ ከእርሷ እድል ይኖረዋል:: መጥፎ መታደግንም የሚታደግ ሰው ለእርሱ ከእርሷ ድርሻ ይኖረዋል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው::"},{"id":86,"translation":"86.(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ሰላምታ በቀረበላችሁ ጊዜ ከእርሷ ይበልጥ ባማረ ሰላምታን መልሱ። ወይም እርሷኑ ራሷን መልሷት። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና።"},{"id":87,"translation":"87. አላህ ከእርሱ በስተቀር ትክክለኛ አምላከ የለም:: ወደ ትንሳኤ ቀን በእርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲሆን በእርግጥ ይሰበስባችኋል:: በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው?"},{"id":88,"translation":"88.(አማኞች ሆይ) አላህ በስራዎቻቸው ምክንያት ወደ ክህደት የመለሳቸው ሲሆኑ በሙናፊቆች ጉዳይ እናንተ ለሁለት ቡድን የተከፈላችሁት ምን ሆናችሁ ነው? አላህ ያጠመመውን ሰው ልታቀኑ ታስባላችሁን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያጠመመውን ሰው ለእርሱ መንገድ ፈጽሞ አታገኝለትም::"},{"id":89,"translation":"89. (አማኞች ሆይ) በአላህ እንደ ካዱ ሁሉ እናንተም እንድትክዱና ከእነርሱ ጋር እኩል እንድትሆኑ ተመኙ:: በአላህ መንገድ እስከሚሰደዱ ድረስ ከእነርሱ መካከል ወዳጆችን አትያዙ:: ከእምነት ካፈገፈጉም ማርኳቸው:: ባገኛችኋቸው ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው:: ከእነርሱም ወዳጅንና ረዳትን አትያዙ::"},{"id":90,"translation":"90. እነዚያ በእናተና በእነርሱ መካከል ቃል ኪዳን ወዳላቸው ህዝቦች የሚጠጉ፤ ወይም እናንተን ለመጋደልም ይሁን ወገኖቻቸውን ለመጋደል ልቦቻቸው የተጨነቁ ሆነው ወደ እናንተ የመጡ ሲቀሩ እነዚያንማ አትጋደሏቸው:: አላህ በፈለገ ኖሮ በእናንተ ላይ ሀይል በሰጣቸውና በተዋጓችሁ ነበር:: ቢተዋችሁ ባይዋጓችሁ ወደ እናንተ የእርቅን ሀሳብ ቢያቀርቡ አላህ ለእናንተ በእነርሱ ላይ የመዋጋት መንገድን አላደረገም::"},{"id":91,"translation":"91. ከናንተም ሆነ ከወገኖቻቸው ለመዳን የሚፈልጉ ሌሎች ቡድኖችም ታገኛላችሁ:: ወደ እውከት እንዲመለሱ በተጠሩ ቁጥር በእርሷ ውስጥ ይዘፈቃሉ:: ባይተዋችሁና እርቅን ካላቀረቡላችሁ እጆቻቸውንም ባይሰበስቡ ባገኛችኋቸው ስፍራ ሁሉ ማርኳቸው:: ግደሏቸዉም:: እነዚያን ለእናንተ በእነርሱ ላይ ግልጽ ማስረጃን አድርገንላችኋል::"},{"id":92,"translation":"92. አማኝ በስህተት ካልሆነ በስተቀር አማኝን መግደል አይገባዉም:: አማኝን በስህተት የገደለም አማኝ ባሪያን ነፃ ማውጣትና ምህረት ካላደረጉለት በስተቀር ለቤተሰቦቹ የምትሰጥ ጉማ መክፈል አለበት:: ተገዳዩ ምዕመን ሆኖ ለእናንተ ጠላት ከሆኑ ህዝቦች ዘንድ ቢሆንም አማኝን ባሪያ ነፃ ማውጣት አለበት:: ተገዳዩ በእናንተ እና በእነርሱ መካከል ቃል ኪዳን ካላቸዉም ህዝቦች ጋር ቢሆን ለቤተሰቦቹ የምትሰጥ ጉማና አማኝን ባሪያ ነፃ ማውጣት አለበት:: ይህንን ያላገኘም በተከታታይ ሁለት ወሮችን መፆም አለበት:: ከአላህ የሆነ ጸጸት (ለመቀበል ደነገገላችሁ::) አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::"},{"id":93,"translation":"93. አማኝን አስቦ የሚገድል ቅጣቱ በውስጧ ዘወታሪ ሲሆን ገሀነም ናት:: አላህ በእርሱ ላይ ተቆጣ:: ረገመዉም:: ለእርሱ ከባድ ቅጣትን አዘጋጀቶለታል::"},{"id":94,"translation":"94. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ መንገድ ለመዋጋት በተጓዛችሁ ጊዜ አረጋግጡ:: ሰላምታን ወደ እናንተ ላቀረበ ሰው የቅርቢቱን ሕይወት ጥቅም የምትፈልጉ ሆናችሁ «ትክክለኛ አማኝ አይደለህም።» አትበሉት:: አላህ ዘንድ ብዙ ምርኮዎች አሉና:: እናንተም ከዚህ በፊት ልክ እንደዚሁ ነበራችሁ:: አላህ በእናንተ ላይ ለገሰ:: ስለዚህም አረጋግጡ:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::"},{"id":95,"translation":"95. ከአማኞች የጉዳት ባለቤት ከሆኑት በስተቀር ተቀማጮቹ እና በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውም በነፍሶቻቸውም የሚታገሉት አይስተካከሉም:: በገንዘቦቻቸውም በነፍሶቻቸውም የሚታገሉትን አላህ በተቀማጮቹ ላይ በደረጃ አበለጠ:: ለሁሉም አላህ መልካሚቱን (ገነት) ተስፋ ሰጠ (ቃል ኪዳን ገባ):: ታጋዮቹንም በተቀማጮቹ ላይ አላህ በታላቅ ምንዳ አበለጠ::"},{"id":96,"translation":"96. ከእርሱ ዘንድ በሆኑ ደረጃዎች አበለጠ:: ምህረትንም አደረገ:: እዝነትንም አዘነላቸው:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":97,"translation":"97. እነዚያ ለእምነት ሲሉ ባለመሰደድ ነፍሶቻቸውን በዳዮች ሆነው መላዕክት የገደሏቸው መላዕክት ለእነርሱ «በምን ነገር ላይ ነበራችሁ?» ይሏቸዋል። «በምድር ውስጥ ደካሞች ነበርን።» ይላሉ:: «የአላህ ምድር ትሰደዱባት ዘንድ ሰፊ አልነበረችምን?» ይሏቸዋል። እነዚያም መኖሪያቸው ገሀነም ናት:: ገሀነምም መመለሻነቷ ከፋች።"},{"id":98,"translation":"98. ከወንዶችና ከሴቶች ከህፃኖችም ሲሆኑ ከሀገራቸው ለመውጣት መላን የማይችሉና መንገድንም የማይመሩ ደካሞች ባለመሰደዳቸው ግን ምንም ቅጣት የለባቸዉም::"},{"id":99,"translation":"99. እነዚያ አላህ ከእነርሱ ይቅርታ ሊያደርግ ይሻል:: አላህም ይቅር ባይና መሀሪ ነውና::"},{"id":100,"translation":"100. በአላህ መንገድ የሚሰደድ ሁሉ በምድር ውስጥ ብዙ መሰደጃንና ምቾትን ያገኛል:: ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው ስደተኛ ሆኖ ከቤቱ የሚወጣና ከዚያ በመንገድ ላይ ሞት የሚያገኘው ምንዳው በእርግጥ በአላህ ዘንድ ተረጋገጠ:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":101,"translation":"101.(አማኞች) በምድር ላይ በተጓዛችሁ ጊዜ እነዚያ የካዱት ሊያውኳችሁ እንደሆነ ብትፈሩ ከሶላቶች መካከል ከፊሎችን (ባለ አራት አራት ረካአ የሆኑትን ቁጥራቸውን ወደ ሁለት ሁለት በመቀነስ) ብታሳጥሩ በእናንተ ላይ ኃጢአት የለም። ከሓዲያን ለእናንተ በእርግጥ ግልጽ ጠላቶች ናቸውና።"},{"id":102,"translation":"102.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ) በጦርነት ላይ በመካከላቸው በሆንክና ሶላትን ለእነርሱ ባሰገድካቸው ጊዜ ከእነርሱ አንዱ ቡድን ካንተ ጋር ይቁም:: መሳሪያዎቻቸውንም ይያዙ:: ሱጁድ ባደረጉ ጊዜ ከበስተኋላችሁ ይሁኑ:: ከዚያም እነዚያ ቡድኖች ወደ ግንባር ይሂዱና ያልሰገዱት ሌሎች ቡድኖች ይምጡ :: ከዚያም ካንተ ጋር ይስገዱ:: ጥንቃቄያቸውንና መሳሪያዎቻቸውንም ይያዙ:: እነዚያ በአላህ የካዱት ከትጥቅና ስንቃችሁ ብትዘናጉና በአንድ ጊዜ ቢወሯችሁ ይመኛሉ:: ዝናብ አውኳችሁ ወይም በሽተኛ ሆናችሁ ትጥቃችሁን ብታስቀምጡ በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም:: ጥንቃቄ አድርጉ:: አላህ ለካሐዲያን ሁሉ አዋራጅን ቅጣት አዘጋጀ::"},{"id":103,"translation":"103. ሶላትንም በፈጸማችሁ (በጨረሳችሁ) ጊዜ ቆማችሁ፣ ተቀምጣችሁና በጎኖቻችሁም ተጋድማችሁ አላህን አውሱ:: በተረጋጋችሁ ጊዜ ግን ሶላትን ደንቧን አሟልታችሁ ስገዱ:: ሶላት በአማኞች ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና::"},{"id":104,"translation":"104.ሰዎቹንም ከመፈለግ አትስነፉ:: ስትቆስሉ የምትታመሙ ብትሆኑም እናንተ እንደምትታመሙ ሁሉ እነርሱም ይታመማሉ:: እናንተ ግን እነርሱ የማይከጅሉትን ከአላህ ትከጅላላችሁ:: አላህም ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::"},{"id":105,"translation":"105. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሰዎች መካከል አላህ ባሳወቀህ ልትፈርድ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት አወረድን:: እናም ለከዳተኞች ተከራካሪ አትሁን::"},{"id":106,"translation":"106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህን ምህረት ለምነው:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":107,"translation":"107. ለእነዚያ ነፍሶቻቸውን ስለሚያታልሉት ሰዎች አትከራከር:: አላህ ከዳተኛንና ኃጢአተኛን ሰው አይወድምና::"},{"id":108,"translation":"108. ከሰው ይደበቃሉ:: አላህ በዕውቀቱ ከእነርሱ ጋር ሲሆን ከንግግር የማይወደውን ነገር በልቦቻቸው በሚያሳድሩ ጊዜ ከእርሱ አይደበቁም:: አላህ በሚሰሩት ሁሉ በእውቀቱ ከባቢ ነውና::"},{"id":109,"translation":"109. እነሆ እናንተ እነዚያ በቅርቢቱ ሕይወት ውስጥ ከእነርሱ ተከራከራችሁ:: በትንሳኤ ቀን አላህን ስለ እነርሱ የሚከራከርላቸው ማን ነው? ወይስ ለእነርሱ ሀላፊ የሚሆን ማን ነው?"},{"id":110,"translation":"110. መጥፎ ነገር የሚሰራ ወይም ነፍሱን የሚበድልና ከዚያም ተጸጽቶ አላህን ምህረት የሚለምን ሁሉ አላህን መሀሪና አዛኝ ሆኖ ያገኘዋል::"},{"id":111,"translation":"111. ኃጢአት የሚሰራም የሚሰራው ጥፋት ጉዳቱ በራሱ ላይ ብቻ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":112,"translation":"112. ኃጢአትን ወይም ወንጀልን የሚሰራና ከዚያም በእርሱ ንጹህን የሚሰድብ ቅጥፈትንና ግልጽ ኃጢአትን በቁርጥ ተሸከመ::"},{"id":113,"translation":"113. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባንተ ላይ ባልነበረ ኖሮ ከእነርሱ የሆነ ቡድኖች ሊያሳስቱህ ባሰቡ ነበር:: ነፍሶቻቸውን እንጂ ሌላ አያሳስቱም:: በምንም አይጎዱህም:: አላህ ባንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ:: የማታውቀውን ሁሉ አስተማረህ:: የአላህ ችሮታ ባንተ ላይ ታላቅ ነው::"},{"id":114,"translation":"114. ከውይይቶቻቸው መካከል በምጽዋት ወይም በበጎ ስራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ ከሚያዙ ሰዎች ውይይት በስተቀር በብዙው ውይይት ውስጥ ደግ ነገር የለበትም:: ይህንንም የተባለውን የአላህን ውዴታ በመፈለግ ለሚሰራ ሁሉ ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን::"},{"id":115,"translation":"115. ቅኑ መንገድ ለእርሱ ከተገለጸት በኋላ መልዕክተኛውን የሚቃረንና ከምዕመናኖቹ መንገድ ሌላ የሆነን የሚከተል ሁሉ በመረጠው ጥመት ላይ እንተወዋለን። ወደ ገሀነምም እናስገባዋለን:: መመለሻይቱም ገሀነም ከፋች።"},{"id":116,"translation":"116. አላህ በእርሱ ማጋራትን ፈጽሞ አይምርም:: ከሽርክ በታች (ሌላ) ያለውን ጥፋት ግን ለሚሻው ይምራል:: በአላህ የሚያጋራም ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ::"},{"id":117,"translation":"117. ከእርሱ ሌላ እንስት ጣኦታትን እንጂ አይገዙም:: አመጸኞች ሰይጣንንም እንጂ ሌላን አይገዙም::"},{"id":118,"translation":"118. አላህም የረገመውን (እንዲህ) ያለውንም ሰይጣን እንጂ አይከተሉም: «ከባሮችህ የተወሰነን ድርሻ በእርግጥ እይዛለሁ።"},{"id":119,"translation":"119. «በእርግጥ አጠማቸዋለሁ:: ከንቱን ምኞትም አስመኛቸዋለሁ:: አዛቸዉምና የእንስሶችን ጀሮዎች ይተለትላሉ:: አዛቸዉምና የአላህን ፍጥረት ይለውጣሉ።» (ያለውን ይከተላሉ።) ከአላህ ሌላ ሰይጣንን ረዳት አድርጎ የሚይዝ ግልጽ ኪሳራን በእርግጥ ከሰረ።"},{"id":120,"translation":"120. የማይፈጽመውን ከንቱ ተስፋ ይሰጣቸዋል:: ያስመኛቸዋልም:: ሰይጣን ለማታለል እንጂ ቃል አይገባላቸዉም::"},{"id":121,"translation":"121. እነዚያ የመጨረሻ መኖሪያቸው ገሀነም ናት:: ከእርሷም መሸሻን አያገኙም::"},{"id":122,"translation":"122. እነዚያ በአላህ ያመኑትና በጎ ስራዎችን የሰሩ ሁሉ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘላለም በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ እናስገባቸዋለን:: አላህ እውነተኛን ተስፋ ሰጣቸው:: በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው?"},{"id":123,"translation":"123. ነገሩ በምኞታችሁና በመጽሐፉ ሰዎች ምኞት አይደለም:: መጥፎን የሚሰራ ሁሉ በእርሱ ይመነዳል:: ለእርሱም ከአላህ ሌላ ጠባቂን ረዳትንም አያገኝም::"},{"id":124,"translation":"124. ከወንድ ወይም ከሴት አማኝ ሆነው ከበጎ ስራዎች አንድንም ነገር የሚሰሩ ገነት ይገባሉ:: በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ ያክል እንኳን አይበደሉም።"},{"id":125,"translation":"125. መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን ለአላህ ከሰጠና የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን ከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማን አለ? አላህ ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ አድርጎ ያዘው::"},{"id":126,"translation":"126. በሰማያትና በምድር ያለው ነገር ሁሉ የአላህ ነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ በእውቀት ከባቢ ነው::"},{"id":127,"translation":"127. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ) ስለ ሴቶች ጉዳይ ይጠይቁሃል። «አላህ ስለነሱ ይነግራችኋል:: ያም በመጽሐፍ ውስጥ በእናንተ ላይ የሚነበበው ሲሆን በእነዚያ ከውርስ የተደነገገላቸውን ድርሻ በማትሰጧቸው ሴቶችና ልታገቧቸው በማትፈልጉት የቲሞች ሴቶች ይህንን እንዳታደርጉ፤ ህፃናት ለሆኑትም ደካሞች መብታቸውን እንድትሰጡ፤ ለየቲሞች በትክክል እንድትቆሙ ይነገራችኋል።» በላቸው:: ከበጎም ስራ የሆነን ማንኛውንም ስራ ብትሰሩ አላህ እርሱን አዋቂ ነው::"},{"id":128,"translation":"128. ሴት ልጅ ከባሏ ጥላቻን ወይም ከእርሷ ፊቱን ማዞሩን ብታውቅ እና ከዚያ በመካከላቸው እንደገና ቢስማሙ በሁለቱ ላይ ኃጢአት የለባቸዉም:: መታረቅ መልካም ነውና:: ነፍሶች ሁሉ ንፍገት ተጣለባቸው:: (ባሎች ሆይ!) መልካም ነገር ብትሰሩና ብትጠነቀቁ ግን አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::"},{"id":129,"translation":"129. (ባሎች ሆይ! ) በሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ሴቶች መካከል ምንም እንኳን ብትጓጉ በፍቅር ለማስተካከል አትችሉም። ሆኖም እንደተንጠለጠለች (ገመድ) አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ ወደምትወዷት ሴት ሙሉ መዘንበልን አትንዘንበሉ:: ብታበጁና ብትጠነቀቁ አላህ መሀሪና አዛኝ ነው::"},{"id":130,"translation":"130. ባልና ሚስት በመሀከላቸው በተፈጠረው ችግር ቢለያዩ አላህ ሁሉንም በችሮታው ያብቃቃቸዋል:: አላህ ችሮታው ሰፊና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":131,"translation":"131. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው:: እነዚያንም ከበፊታችሁ መጽሐፍ የተሰጡትን እናንተንም አላህን ፍሩ በማለት በእርግጥ አዘዝን:: ብትክዱም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው አትጎዱትም:: አላህ በራሱ ተብቃቂና ምስጉን ነውና::"},{"id":132,"translation":"132. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: መመኪያነትም በአላህ በቃ::"},{"id":133,"translation":"133. (እናንተ ሰዎች ሆይ!) አላህ ቢሻ ያስወግዳችሁና ሌሎችን በቦታችሁ ላይ ይተካል:: አላህም በዚህ ላይ ቻይ ነው::"},{"id":134,"translation":"134. የቅርቢቱን አለም ምንዳ የሚፈልግ ሁሉ አላህ ዘንድ የቅርቢቱና የመጨረሻይቱ ምንዳ አለ:: አላህ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን ተመልካች ነውና::"},{"id":135,"translation":"135. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በነፍሶቻችሁ ወይም በወላጆችና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢሆንም እንኳ በትክክል ለፍትህ ቋሚዎች ለአላህ መስካሪዎች ሁኑ:: ሀብታም ወይም ድሃ ቢሆንም አላህ ከእነርሱ ለእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው:: እንዳታዳሉም ዝንባሌን አትከተሉ:: ምስክርን ብታጣምሙ ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሰሩት ነገር ላይ ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::"},{"id":136,"translation":"136. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልዕክተኛው በዚያ በመልዕክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍም ከዚያ በፊትም ባወረደው መጽሐፍ እመኑ:: በአላህ፣ በመላዕክቱ፣ በመጽሐፍቱ፣ በመልዕክተኞቹና በመጨረሻውም ቀን የካደ ሁሉ ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ።"},{"id":137,"translation":"137. እነዚያ ያመኑና ከዚያም የካዱ ከዚያም ያመኑ ከዚያም የካዱ ከዚያም ክህደትን የጨመሩ አላህ ለእነርሱ የሚምራቸውና ቅኑን መንገድም የሚመራቸው አይደሉም።"},{"id":138,"translation":"138. አስመሳዮችን ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት ያላቸው መሆኑን አብስራቸው::"},{"id":139,"translation":"139. እነዚያ ከአማኞች ሌላ ከሓዲያንን ወዳጆች አድርገው የሚይዙ ሰዎች እነርሱ ዘንድ ልቅናን ይፈልጋሉን? ልቅና ሁሉ ለአላህ ብቻ ነው::"},{"id":140,"translation":"140. በእናንተ ላይ በመጽሐፉ ውስጥ የአላህን አናቅጽ በእርሷ ሲካድባት በእርሷም ሲላገጥባት በሰማችሁ ጊዜ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከእነርሱ ጋር አትቀመጡ ማለትን በእርግጥ አወረደ:: እናንተ ያን ጊዜ ቢጤያቸው ናችሁና:: አላህ አስመሳዮችንም ከሓዲያንንም በገሀነም ውስጥ ሰብሳቢ ነውና::"},{"id":141,"translation":"141. እነዚያ (አስመሳዮች) በእናንተ ላይ የጊዜ መዘዋወርን የሚጠባበቁ ናቸው:: ለእናንተም ከአላህ የሆነ አሸናፊነት ሲኖራችሁ «ከናንተ ጋር አልነበርንምን?» ይላሉ:: ለከሓዲያን እድል ሲኖር ደግሞ «ከአሁን በፊት እኛ በእናንተ ላይ አልተሾምንባችሁምና (አልተውናችሁምን?) ከአማኞች አደጋስ አልከለከልናችሁምን?» ይላሉ:: አላህ በትንሳኤ ቀን በመካከላችሁ ይፈርዳል:: አላህ ለከሓዲያን በአማኞች ላይ መንገድን በፍጹም አያደርግም::"},{"id":142,"translation":"142. አስመሳዮች አላህን ያታልላሉ:: እርሱም አታላያቸው ነው:: ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾችና ሰዎችን የሚያሳዩ ሆነው ይቆማሉ:: አላህንም ጥቂትን እንጂ አያወሱም።"},{"id":143,"translation":"143. በዚህ መካከል ወላዋዮች ሆነው ይታያሉ:: ወደ እነዚህም ወደ እነዚያም አይደሉም:: አላህም ያሳሳተውን ለእርሱ የቅንነት መንገድን በፍጹም አታገኝለትም::"},{"id":144,"translation":"144. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአማኞች ሌላ ከሓዲያንን ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙ:: ለአላህ በእናንተ ላይ ግልጽ ማስረጃዎችን ልታደርጉ ትፈልጋላችሁን?"},{"id":145,"translation":"(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስመሳዮች በእርግጥ ከእሳት በታችኛዋ አዘቅት ውስጥ ናቸው:: እናም ለእነርሱ ረዳትን አታገኝላቸዉም::"},{"id":146,"translation":"146. እነዚያ የተመለሱና ስራቸውን ያሳመሩ በአላህ የተጠበቁ ሃይማኖታቸውንም ለአላህ ፍጹም ያደረጉት ሲቀሩ:: እነዚያስ ከአማኞች ጋር ናቸው:: ለአማኞችም አላህ ታላቅን ምንዳ በእርግጥ ይሰጣል::"},{"id":147,"translation":"147. ብታመሰግኑና ብታምኑ አላህ እናንተን በመቅጣት ምን ያደርጋል? አላህም ወረታን መላሽ አዋቂ ነው::"},{"id":148,"translation":"148. አላህ በክፉ ንግግር መጮህን ከተበደለ ሰው ጩኸት በስተቀር አይወድም:: አላህ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን አዋቂ ነውና::"},{"id":149,"translation":"149. ደግ ነገርን ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት ወይም ከመጥፎ ነገር (በደል) ይቅርታ ብታደርጉ አላህ ይቅር ባይ እና ቻይ ነው::"},{"id":150,"translation":"150. እነዚያ በአላህና በመልዕክተኞቹ የሚክዱ፤ በአላህና በመልዕክተኞቹም መካከል መለየትን የሚፈልጉና «በከፊሉ እናምናለን በከፊሉ ደግሞ እንክዳለን» የሚሉ ሁሉ በዚህ መካከል መንገድን ሊይዙ የሚፈልጉ፣"},{"id":151,"translation":"151. በእውነቱ እነዚያ ከሓዲያን እነርሱው ናቸው:: ለከሓዲያንም አዋራጅን ቅጣት አዘጋጅተናል::"},{"id":152,"translation":"152. እነዚያ በአላህና በመልዕክተኞቹ ያመኑ፤ ከእነርሱም መካከል በአንዱም ያልለዩ ሰዎች እነዚያ ምንዳዎቻቸው በእርግጥ ይሰጣቸዋል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":153,"translation":"153. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመጽሐፉ ባለቤቶች እነርሱ ላይ ከሰማይ መጽሐፍን እንድታወርድ ይጠይቁሃል:: ከዚህም የከበደን ጥያቄ ከዚህ በፊት ሙሳን በእርግጥ ጠይቀዋል:: «አላህን በግልጽ አሳየን።» ብለዋል:: በበደላቸዉም ምክንያት መብረቅ ያዘቻቸው:: ከዚያም ተዓምራት ከመጡላቸው በኋላ ወይፈኑን አምላክ አድረገው ያዙ:: ከዚያ ያንን ይቅር አልን:: ሙሳንም ግልጽ ስልጣን ሰጠነው::"},{"id":154,"translation":"154. በቃል ኪዳናቸው ምክንያት የጡር ተራራን ከበላያቸው አነሳን:: ለእነርሱም «ደጃፍን ስትገቡ አጎንብሳችሁ ግቡ።» አልን:: ለእነርሱም «በሰንበት ቀን ትዕዛዝን አትተላለፉ።» አልን:: ከእነርሱም ከባድን ቃል ኪዳን ያዝን::"},{"id":155,"translation":"155. ቃል ኪዳናቸውን በማፍረሳቸው፤ በአላህ አናቅጽ በመካዳቸው፤ ነብያትን ያለ አግባብ በመግደላቸውና «ልቦቻችን ሽፍን ናቸው።» በማለታቸውም ምክንያት ረገምናቸው:: በእውነቱ በክህደታቸው ምክንያት አላህ በእርሷ ላይ አተመ:: ስለዚህ ጥቂትን እንጂ አያምኑም::"},{"id":156,"translation":"156. በመካዳቸዉም በመርየም ላይ ከባድ ቅጥፈትን በመናገራቸው ምክንያት ረገምናቸው::"},{"id":157,"translation":"157. «እኛ የአላህ መልዕክተኛ የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳን ገደልን።» በማለታቸውም ረገምናቸው:: አልገደሉትም:: አልሰቀሉትምም:: ግን የተገደለው ሰው ለእነርሱ በዒሳ ተመሰለባቸው:: እነዚያ በእርሱ ጉዳይ የተለያዩት በእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም እርግጠኛ እውቀት የላቸዉም:: በእርግጥም አልገደሉትም::"},{"id":158,"translation":"158. ይልቁንስ አላህ ወደ እርሱ አነሳው:: አላህም አሸናፊና ጥበበኛ ነው::"},{"id":159,"translation":"159. ከመጽሐፉ ባለቤቶች መካከልም ከነብዩ ዒሳ ሞት በፊት በነብዩ ዒሳ በእርግጥ በትክክል የሚያምን እንጂ አንድም የለም:: በትንሳኤ ቀንም ዒሳ በእነርሱ ላይ መስካሪ ይሆናል::"},{"id":160,"translation":"160. ከእነዚያ ከአይሁዳውያን መካከል በፈጸሙት በደልና ሰዎችን ከአላህ መንገድ በብዙ በመከላከላቸው ምክንያት ለእነርሱ ተፈቅደው የነበሩ ጣፋጮች ምግቦችን እርም አደረግንባቸው::"},{"id":161,"translation":"161. ከእርሱ በቁርጥ የተከለከሉ ሲሆኑ አራጣን በመያዛቸውና የሰዎችን ገንዘቦች ያለ አግባቡ በመብላታቸዉም ምክንያት የተፈቀደላቸውን እርም አደረግንባቸው:: ከእነርሱም መካከከል ለከሓዲያን አሳማሚ ቅጣት አዘጋጀን::"},{"id":162,"translation":"162. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ግን ከእነርሱ ውስጥ በእውቀት የጠለቁት ክፍሎችና ትክክለኛ ምዕመናኖቹ ባንተ ላይ በተወረደውና ካንተ በፊት በተወረደው መጽሐፍ ያምናሉ። ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው ሰጋጆቹ፣ ዘካንም ሰጪዎቹ በአላህና በመጨረሻው ቀንም ትክክለኛ አማኞቹን እነዚያ ታላቅ ምንዳን በእርግጥ እንሰጣቸዋለን::"},{"id":163,"translation":"163. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ወደ ኑህና ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነብያት መልዕክታችንን እንዳወረድን ሁሉ ወደ አንተም ቁርኣንን አወረድን:: ወደ ነብዩ ኢብራሂም፤ ወደ ነብዩ ኢስማኢልም፤ ወደ ነብዩ ኢስሃቅም፤ ወደ ነብዩ የዕቆብም፤ ወደ ነገዶችም፤ ወደ ነብዩ ዒሳም፤ ወደ ነብዩ አዩብም፤ ወደ ነብዩ ዩኑስም፤ ወደ ነብዩ ሃሩንና ወደ ነብዩ ሱለይማን አወረድን:: ለነብዩ ዳውድም ዘቡርን ሰጠነው::"},{"id":164,"translation":"164. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚህም በፊት በአንተ ላይ በእርግጥ የተረክናቸውን መልዕክተኞች ባንተ ላይም ያልተረክናቸውንም መልዕክተኞች እንደላክን ሁሉ አንተን ላክንህ:: አላህ ነብዩ ሙሳንም ማነጋገርን አነጋገረው::"},{"id":165,"translation":"165. ከመልዕክተኞች በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ ምንም አስረጂ እንዳይኖራቸው አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርገን መልዕክተኞችን ላክን:: አላህ ሁሉን አሸናፊ፤ ጥበበኛ ነውና::"},{"id":166,"translation":"166. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ግን ባንተ ላይ ባወረደው ቁርኣን ይመሰክራል:: በእውቀቱ አወረደው:: መላዕክቱም ይመሰክራሉ:: መስካሪነትም በአላህ ብቻ በቃ::"},{"id":167,"translation":"167. እነዚያ በአላህ የካዱና ከአላህ መንገድም ሰዎችን ያገዱ ሰዎች ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳቱ::"},{"id":168,"translation":"168. እነዚያ የካዱና የበደሉ አላህ የሚምራቸውና ቅን መንገድን የሚመራቸው አይደለም::"},{"id":169,"translation":"169. ግን በውስጧ ለዘልዓለም ዘወታሪዎች ሲሆኑ የገሀነምን መንገድ ይመራቸዋል:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነው::"},{"id":170,"translation":"170. እናንተ ሰዎች ሆይ! መልዕክተኛው እውነትን ከጌታችሁ አመጣላችሁ:: እናም ባመጣው እመኑ ለእናንተ የተሻለ ይሆናል:: በአላህ ብትክዱም እሱን (ቅንጣት) አትጎዱትም:: በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነውና:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::"},{"id":171,"translation":"171. እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ:: በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ:: የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳ የአላህ መልዕክተኛ ወደ መርየም የጣላት የሁን ቃሉና ከእርሱ የሆነ መንፈስ ብቻ ነው:: በአላህና በመላዕክተኞቹ እመኑ:: «አማልዕክት ሶስት ናቸው።» አትበሉ:: ተከልከሉ:: ለእናንተ የተሻለ ይሆናልና:: አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: ለእርሱም ልጅ ያለው ከመሆን የጠራ ነው:: በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: መመኪያነትም በአላህ በቃ::"},{"id":172,"translation":"172. አል መሲህ ለአላህ ባሪያ ከመሆን ፈጽሞ አይጸየፍም:: ቀራቢዎች የሆኑ መላዕክትም እንዲሁ ለአላህ ባሪያ ከመሆን ፈጽሞ አይጸየፉም:: ወደ አላህ እርሱን ከመገዛት የሚጸየፉና የሚኮሩ ሁሉ አላህ ሁሉንም ወደ እርሱ በእርግጥ ይሰበስባቸዋል::"},{"id":173,"translation":"173. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካም ተግባራትን የሰሩትን ምንዳዎቻቸውን ይሞላላቸዋል:: ከችሮታዉም ይጨምርላቸዋል:: እነዚያን የተጸየፉትና የኮሩትን ግን አሳማሚውን ቅጣት ይቀጣቸዋል:: ከአላህ ሌላ ለእነርሱ ዘመድና ረዳት አያገኙም::"},{"id":174,"translation":"174. እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ዘንድ በእርግጥም አስረጅ መጣላችሁ:: ወደ እናንተም ገላጭ የሆነን ብርሃንን (ቁርኣንን) አወረድን::"},{"id":175,"translation":"175. እነዚያማ በአላህ ያመኑና በእርሱ የተጠበቁ ሰዎች ከእርሱ በሆነው እዝነትና ችሮታ ውስጥ እርግጥ ያስገባቸዋል:: ወደ እርሱም ቀጥተኛ መንገድን ይመራቸዋልም::"},{"id":176,"translation":"176. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይጠይቁሃል: «ወላጆችና ልጅ ሳይኖረው በሚወረስ ሟች ሰው ጉዳይ አላህ ይነግራችኋል።» በላቸው፡፡ ልጅ የሌለው ሰው ቢሞትና ለእርሱ እህት ብትኖረው ለእርሷ ከተወው ንብረት ግማሽ አላት፡፡ እርሱም ለእርሷ ልጅ የሌላት እንደሆነች በሙሉ ይወርሳታል፡፡ ሁለት እህቶች ወይም ከሁለት በላይ ቢሆኑ ግን ከተወው ንብረት ከሶስት ሁለት እጅ አላቸው ፡፡ ወንድሞችና እህቶች ወንዶችና ሴቶች ቢሆኑ ደግሞ ለወንድ የሁለት ሴቶች ድርሻ ያህል አለው ፡፡ አላህ እንዳትሳሳቱ ህግጋትን ለእናንተ ያብራራል ፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነውና፡፡"}]},{"id":5,"verses":[{"id":1,"translation":"1. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ቃልኪዳኖቻችሁን ሙሉ:: በእናንተ ላይ የሚነበበው ብቻ ሲቀር የግመል፤ የከብት፤ የበግና የፍየል እንስሳት ተፈቅዶላችኋል:: በሐጅ ስራ ላይ ሆናችሁ አውሬ ማደንን እንደ ተፈቀደ ሳትቆጥሩ የሚበሉት የዱር እንስሳትም ተፈቅደውላችኋል:: አላህ የሚፈልገውን ሁሉ ነገር ይፈርዳልና::"},{"id":2,"translation":"2. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ምልክቶች ይሆኑ ዘንድ የከለከላቸውን ነገሮች የተፈቀዱ አታድርጉ። የተከበረውንም ወር በውስጡ ጦርነትን በማካሄድ አትድፈሩት:: ወደ መካ የሚነዱትን የመስዋዕት እንስሳትና የሚታበቱባቸውን ገመዶች፤ ከጌታቸው ችሮታንና ውዴታን ፈልገው ወደ ተከበረው ቤት አሳቢዎችንም በክፉ አትንኳቸው:: የሐጅን ስራ ፈጽማችሁ ባጠናቀቃችሁ ጊዜ የዱር አውሬዎችን እንደልባችሁ አድኑ:: ከተከበረው መስጊድ ስለከለከሏችሁ ሰዎችን መጥላታችሁ በእነርሱ ላይ ወሰንን እንድታልፉና ፍትህን እንድታዛቡ አይገፋፉችሁ:: በበጎ ተግባርና አላህን በመፍራት እርስ በእርስ ተባበሩ:: ኃጢአትና ወሰንን በማለፍ ግን አትተባበሩ:: አላህን በትክክል ፍሩ:: አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና::"},{"id":3,"translation":"3. (ስዎች ሆይ!) በክት፤ ደም፤ የአሳማ ስጋ፤ ሲታረድ ከአላህ ስም ሌላ የተወሳበት እንሰሳ፤ ታንቃ የሞተች፤ ተደብድባ የተገደለች፤ ተንከባላ የሞተች፤ በቀንድ ተወግታ የሞተችና አውሬ የበላት ከእነዚህ በሕይወት ላይ እያሉ ደርሳችሁ ያረዳችሁት ብቻ ሲቀር ለጣዖታት የታረደና በአዝላም እድልን መፈለጋችሁ በእናንተ ላይ እርም ተደረገ:: እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን መፈጸም አላህን ማመጽ ነው:: ዛሬ እነዚያ በአላህ የካዱት ከሀይማኖታችሁ ተስፋ ቆረጡ:: ስለዚህ አትፍሩዋቸው:: ይልቁን እኔን ብቻ ፍሩኝ:: ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ:: ጸጋየንም በእናንተ ላይ ፈጸምኩ:: ለእናንተም በሃይማኖትነት ኢስላምን ወደድኩላችሁ:: በርሀብ ወቅት ወደ ኃጢአት ያዘነበለ ሳይሆን እርም የሆኑትን ነገሮች ለመብላት የተገደደ ሰው ሁሉ ለሕይወቱ ማቆያ ያህል ቢበላ ምንም ችግር የለበትም:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።"},{"id":4,"translation":"4.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ሙስሊሞች ) ምን ምን እንደተፈቀደላቸው ይጠይቁሃል:: «ለእናንተ መልካሞች ሁሉ እና እነዚያም አላህ ካሳወቃችሁ አሰልጣኞች ሆናችሁ ያስተማራችኋቸው አዳኞች ውሾች ያደኑት ሁሉ ተፈቀደላችሁ።» በላቸው:: አላህ ካስተማራችሁ እውቀት ታስተምሯቸዋላችሁ:: ከያዙላችሁ ነገር ብሉ:: የአላህንም ስምም አውሱበት:: አላህን ፍሩ:: አላህ ምርመራው ፈጣን ነውና::"},{"id":5,"translation":"5. (አማኞች ሆይ!) ዛሬ መልካም ነገሮች ለእናንተ ተፈቀዱ:: የእነዚያ መጽሐፍን የተሰጡ ሰዎች ምግብም (እርድ) ለእናንተ የተፈቀደ ነው:: ምግባችሁም ለእነርሱ የተፈቀደ ነው:: ከምዕመናት ሴቶችም ጥብቆቹ፤ ከእነዚያ ከናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡ ህዝቦች ሴቶችም መካከል ጥብቆቹ፤ ዝሙተኞችና የሚስጥር ወዳጅ ያዢዎች ሳትሆኑ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ ልታገቧቸው የተፈቀዱ ናቸው:: በአላህ ካመነ በኋላ ከእምነቱ ወደ ክህደት የሚመለስ ሁሉ በእርግጥ ስራው ተበላሸ:: በመጨረሻም ቀን ከከሳሪዎች ነው::"},{"id":6,"translation":"6. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወደ ሶላት ለመግባት ባሰባችሁ ጊዜ ፊቶቻችሁንና እጆቻችሁን እስከ ክርኖቻችሁ ድረስ እጠቡ:: ራሶቻችሁንም በውሃ አብሱ:: እግሮቻችሁን እስከ ቁርጭምጭሚቶች እጠቡ:: ጀናባ ከሆናችሁ ሙሉ ገላችሁን ታጠቡ:: በሽተኞች ወይም በጉዞ ላይ ብትሆኑ ወይም ከናንተ አንዳችሁ ከዓይነ ምድር ቢወጣ ወይም ሴቶችን ብትነኩና (የግብረ ስጋ ግንኙነት ብትፈጽሙና) ውሃን ባታገኙ በንጹህ የምድር አፈር ተይሙም አድርጉ:: ከዚያም ከእርሱ ፊታችሁንና እጆቻችሁን አብሱ:: አላህ በእናንተ ላይ ምንንም ችግር ሊያደርግ አይሻምና:: ይልቁንም አላህን ታመሰግኑት ዘንድ ሊያጠራችሁና ጸጋውን በእናንተ ላይ ሊሞላ ይፈልጋል::"},{"id":7,"translation":"7. በእናንተ ላይ የለገሰውን የአላህን ጸጋና ያንንም «ሰምተናል ታዘናልም» ባላችሁ ጊዜ ያጠበቀባችሁን ቃል ኪዳኑን አስታውሱ:: አላህንም ፍሩ:: አላህ በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነውና።"},{"id":8,"translation":"8. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ የቆማችሁ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ሁኑ:: ሕዝቦችንም መጥላታችሁ ላለማስተካከል አይገፋፋችሁ ፍትሀዊ ሁኑ:: ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው:: አላህን ፍሩ:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::"},{"id":9,"translation":"9. እነዚያ በአላህ ያመኑና በጎ ስራዎችን የሰሩ ሁሉ (አላህ ገነትን ቃል ገባላቸው::) ለእነርሱ ምህረትና ታላቅ ምንዳ አለላቸው::"},{"id":10,"translation":"10. እነዚያ በአላህ የካዱና በአናቅጻችን ያስተባበሉ ሁሉ የእሳት ጓዶች ናቸው::"},{"id":11,"translation":"11. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሕዝቦች እጆቻቸውን ለጥቃት ወደ እናንተ ሊዘረጉ ባሰቡና እጆቻቸውን ከናንተ ላይ በከለከለላችሁ ጊዜ ለእናንተ የዋለላችሁን ጸጋ አስታውሱ:: አላህንም ፍሩ። አማኞች በአላህ ላይ ብቻ ይመኩ::"},{"id":12,"translation":"12. አላህ የኢስራኢል ልጆችን የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዘባቸው:: ከእነርሱም መካከል አስራ ሁለት አለቆችን አስነሳን:: አላህም አላቸው፡- «ከእናንተ ጋር ነኝ። ሶላትን ደንቡን ጠብቃችሁ ብትሰግዱ፤ ግዴታ ምጽዋትንም በትክክል ብትሰጡ፤ በመልዕክተኞቼም በሙሉ ብታምኑና በሚያደርጉት ትግል ብትረዷቸው፤ ለአላህ መልካም ብድርን ብታበድሩ ኃጢአቶቻችሁንም አብስላችኋለሁ:: ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችም በእርግጥ አስገባችኋለሁ:: ከዚህ በኋላ ከናንተ መካከል በአላህ የካደ ግን ከቀጥተኛው መንገድ ተሳሳተ::»"},{"id":13,"translation":"13. ቃል ኪዳናቸውን በማፍረሳቸው ረገምናቸው:: ልቦቻቸውንም ደረቆች አደረግን:: ቃላትን ከቦታዎቻቸው ይለውጣሉ:: ከታዘዙትም ነገር ከፊሉን ተው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ጥቂቶቹ ሲቀሩ ክዳትን ከማየት አትወገድም:: ለእነርሱ ይቅርታ አድርግ:: እለፋቸዉም:: አላህ መልካም ሰሪዎችን ሁሉ ይወዳልና::"},{"id":14,"translation":"14. ከእነዚያም «እኛ ክርስቲያኖች ነን» ካሉት ክፍሎች መካከል የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን:: ሆኖም ከታዘዙበት ነገር ከፊሉን ተው:: ስለዚህም እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብንና ጥላቻን ጣልንባቸው:: አላህም ይሰሩት የነበሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል::"},{"id":15,"translation":"15. እናንተ የመጽሐፍ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ መካከል ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ብዙውንም የሚተው ሲሆን መልዕክተኛችን ሙሐመድ መጣላችሁ:: ከአላህ ዘንድም ብርሃንና ገላጭ የሆነ መጽሐፍ መጣላችሁ::"},{"id":16,"translation":"16. አላህ ውዴታውን የተከተሉትን ሁሉ የሰላምን መንገዶች በእርሱ ይመራበታል:: በፈቃዱም ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል:: ወደ ቀጥተኛዉም መንገድ ይመራቸዋል::"},{"id":17,"translation":"17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ «አላህ ማለት የመርየም ልጅ አልመሲህ ነው።» ያሉ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ በአላህ ካዱ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ የመርየምን ልጅ አልመሲህንና እናቱን እንደዚሁም በምድር ያለን ፍጡር ሁሉ ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳን የሚችል ማን ነው? የሰማያትና የምድር የመካከላቸዉም ንግስና የአላህ ብቻ ነው:: የሚፈልገውን ይፈጥራል:: አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና።» በላቸው።"},{"id":18,"translation":"18. አይሁድና ክርስቲያኖች «እኛ የአላህ ልጆችና ወዳጆቹ ነን።» አሉ። «ታዲያ በኃጢአቶቻችሁ ለምን ይቀጣችኋል? አይደላችሁም:: እናንተ ከፈጠራቸው መካከል የሆናችሁ ሰዎች ናችሁ:: አላህ ለሚሻው ይምራል:: የሚሻውን ይቀጣል:: የሰማያትና የምድር በመካከላቸዉም ያለው ሁሉ ንግስናው የአላህ ብቻ ነው:: መመለሻም ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው።"},{"id":19,"translation":"19. እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! «አብሳሪና አስፈራሪ አልመጣልንም።» እንዳትሉ መልዕክተኞቻችን በተቋረጡበት ጊዜ መመሪያዎችን የሚያብራራ ሆኖ መልዕክተኛችን ሙሐመድ በእርግጥ መጣላችሁ:: አብሳሪና አስፈራሪም በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና።"},{"id":20,"translation":"20. ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን በእናንተ ላይ የዋለውን ጸጋ አስታውሱ፣ በውስጣችሁ ነብያትን ባደረገ፤ ነገስታትም ባደረጋችሁና ከአለማት ህዝብ ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ ።"},{"id":21,"translation":"21. ‹‹ሕዝቦቼ ሆይ! ያችን አላህ ለእናንተ ያደረጋትን የተቀደሰችውን መሬት ግቡ:: ወደ ኋላችሁም አትመለሱ:: ከሳሪዎች ሆናችሁ ትመለሳላችሁና›› (ባሉ ጊዜ የሆነዉን አስታውስ)::"},{"id":22,"translation":"22. «ሙሳ ሆይ! በእርሷ ውስጥ ሀያላን ህዝቦች ስላሉ ከእርሷ እስከሚወጡ ድረስ ፈጽሞ አንገባትም:: ከወጡ ግን ገቢዎች ነን።» አሉ።"},{"id":23,"translation":"23. ከእነዚያ አላህን ከሚፈሩትና አላህ ጸጋውን ከለገሰላቸው ሰዎች መካከል ሁለት ሰዎች «በእነርሱ በሀያሎቹ ላይ በሩን ግቡ:: በገባችሁ ጊዜ እናንተ አሸናፊዎች ናችሁ:: ትክክለኛ አማኞችም እንደሆናችሁ በአላህ ላይ ብቻ ተመኩ።» አሏቸው።"},{"id":24,"translation":"24. «ሙሳ ሆይ! እነርሱ በውስጧ እስካሉ ድረስ ፈጽሞ ምንጊዜም አንገባም:: ስለዚህ አንተና ጌታህ ሂዱና ተዋጉ:: እኛ እዚህ ተቀማጮች ነን።» አሉ።"},{"id":25,"translation":"25. ሙሳም «ጌታዬ ሆይ! እኔ ራሴንና ወንድሜን እንጂ ማንንም ላስገድድ አልችልም። ስለዚህ በእኛና በአመጸኞቹ ሕዝቦች መካከል ተገቢ ፍርድህን ስጥ።» አለ።"},{"id":26,"translation":"26. አላህም: «ያቺ የተቀደሰችው መሬት በእነርሱ ላይ ለአርባ አመት ያህል እርም ናት። በምድረ በዳ ይንከራተታሉ። (ሙሳ ሆይ!) በአመጸኞችም ሕዝቦች ላይ አትዘን።» አለው።"},{"id":27,"translation":"27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱ ላይ የአደምን ሁለት ልጆች ወሬ (ማለትም) ሁለቱም ቁርባን ባቀረቡና አላህ ከአንደኛቸው ቁርባኑን ተቀብሎ ከሌላው ባልተቀበለበት ጊዜ የሆነውን ታሪክ አንብብላቸው:: ተቀባይነት ያጣው ወንድሙን «እገድልሃለሁ።» አለው። (የተዛተበትም) አለ: «አላህ የሚቀበለው እኮ ከጥንቁቆቹ ብቻ ነው።"},{"id":28,"translation":"28. «ልትገድለኝ እጅህን ወደ እኔ ብትዘረጋ እንኳን እኔ ልገድልህ እጄን ወደ አንተ የምዘረጋ አይደለሁም:: እኔ የአለማቱን ጌታ አላህን እፈራለሁና።"},{"id":29,"translation":"29. «እኔ በኃጢአቴና በኃጢአትህ ወደ ጌታህ ልትመለስና ከእሳት ጓዶች አንዱ ልትሆን እሻለሁ:: ይህም የበደለኞች ቅጣት ነው።» አለ።"},{"id":30,"translation":"30. ነፍሱም ወንድሙን መግደሉ አስቻላትና(አስዋበችለት) ገደለው። ከከሳሪዎችም ሆነ።"},{"id":31,"translation":"31. ዘንድ አላህ መሬትን የሚጭር ቁራ ላከለት የወንድሙን ሬሳ እንዴት እንደሚቀብር ሊያሳየው። «ወይኔ የወንድሜን ሬሳ እቀብር ዘንድ እንደዚህ ቁራ መሆን እንኳን አቃተኝን?» አለ። ከዚያም ከጸጸተኞች ሆነ።"},{"id":32,"translation":"32. በዚህ ምክንያት በኢስራኢል ልጆች ላይ «አንዲትን ንጹህ ነፍስን (ያልገደለችን) ወይም በምድር ላይ ምንንም ያላጠፋችን ነፍስ የገደለ ሁሉ ሰዎችን ሁሉ እንደገደለ ነው:: አንዲትን ነፍስ ህያው ያደረጋትም ሰዎችን ሁሉ ህያው እንዳደረገ ነው።» ማለትን ደነገግን። መልዕክተኞቻችንም ግልጽን ተዐምራት አምጥተውላቸዋል። ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ብዙዎቹ በምድር ላይ ወሰንን አላፊዎች ናቸው።"},{"id":33,"translation":"33. የእነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን የሚዋጉ፤ በምድርም ላይ ለጥፋት የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ቅጣት መገደል ወይም መሰቀል ወይም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በማፈራረቅ መቆረጥ ወይም ከሀገር መባረር ነው:: ይህ ቅጣት ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት ነው:: በመጨረሻይቱም ዓለም ከባድ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":34,"translation":"34. (ሙስሊሞች ሆይ!) (ይህ ተግባር የሚፈጸመው) እነዚያ በእነርሱ ላይ ከመቻላችሁ በፊት የተጸጸቱት ሲቀሩ (ነው)፤ አላህም መሀሪና አዛኝ መሆኑን እወቁ።"},{"id":35,"translation":"35. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ:: ወደ እርሱም የሚያቀርባችሁን ነገር ሁሉ ፈልጉ:: ትድኑ ዘንድም በእርሱ መንገድ ላይ ብቻ ታገሉ::"},{"id":36,"translation":"36. እነዚያ የካዱት በምድር ላይ ያለ ነገርን ሁሉ እና ከርሱ ጋርም መሰሉ ተጨምሮላቸው ከትንሳኤ ቀን ቅጣት ነፃ ለመሆን እርሱን ቤዛ ቢሰጡ እንኳን ተቀባይነት አያገኙም። ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።"},{"id":37,"translation":"37. ከእሳት ሊወጡ ይፈልጋሉ:: እነርሱ ግን ሁልጊዜም ከእርሷ ወጪዎች አይደሉም:: ለእነርሱ ዘውታሪ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":38,"translation":"38. የወንድ ሌባንና የሴት ሌባን ለሰሩት ወንጀል ከአላህ የሆነ መቀጫ ሲሆን እጆቻቸውን ቁረጡ:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":39,"translation":"39. ከበደለ በኋላ የተጸጸተና ስራውን ያሳመረ ሁሉ አላህ ጸጸቱን ይቀበለዋል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":40,"translation":"40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና የእሱ ብቻ መሆኑን አላወክምን? የሚሻውን ሰው ይቀጣል:: ለሚሻውም ሰው ይምራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡"},{"id":41,"translation":"41. መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እነዚያ ወደ ክህደት የሚቻኮሉ ሆነው ልቦቻቸው ሳያምኑ በአፎቻቸው ብቻ «አመንን» ካሉት አስመሳዮችና ከእነዚያም አይሁዶቹ አያሳዝኑህ:: እነርሱ ውሸትን ብቻ አድማጮች ናቸውና:: ገና ወደ አንተ ላልመጡ ለሌሎች ሕዝቦች አድማጮች ናቸው:: ንግግሮችንም ከስፍሮቻቸው ወደ ሌላ በመቀየር መልዕክት ያጣምማሉ። «ይህንን የተጣመመውን ከተሰጣችሁ ያዙት:: ካልተሰጣችሁም ተጠንቀቁ።» ይላሉ:: አላህ መፈተንን የሚሻበትን ሰው ሁሉ ለእርሱ ከአላህ ለመከላከል ፍጹም አትችልም:: እነዚያ ማለት አላህ ልቦቻቸውን ማጥራትን ያልሻላቸው ሰዎች ናቸው:: ለእነርሱም በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አለባቸው:: ለእነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለምም ሌላ ከባድ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":42,"translation":"42. እነርሱ ውሸትን አድማጮች፤ እርም የሆኑ ነገሮችን በላተኞች ናቸው:: እናም ለዳኝነት ወደ አንተ ዘንድ ከመጡ በመካከላቸው በትክክል ፍረድ። ወይም ተዋቸው:: ብትተዋቸው በምንም አይጎዱሁም:: ከፈረድክ ግን በመካከላቸው በትክክል ፍረድ:: አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና::"},{"id":43,"translation":"43. እነርሱ ዘንድ በውስጧ የአላህ ፍርድ ያለባት ተውራት እያለ እንዴት ያስፈርዱሃል? ከዚያ በኋላ ይሸሻሉ። እነዚያ በፍጹም ትክክለኛ አማኞች አይደሉም::"},{"id":44,"translation":"44. ተውራትን በውስጡ ለሰዎች መመሪያና ብርሃን ያለባት ሲሆን አወረድነው:: እነዚያ ትዕዛዙን የተቀበሉት ነብያት በአይሁዳውያን ላይ በእርሱ ይፈርዳሉ:: ሊቃውንቱና አዋቂዎቹም ከአላህ መጽሐፍን እንዲጠብቁ በተደረጉትና በእርሱ ላይ መስካሪዎቹ በመሆናቸው እንዲሁ በሱ ይፈርዳሉ:: እናም ሰዎችን አትፍሩ:: እኔን ብቻ ፍሩኝ:: በአንቀፆቼም አነስተኛን ዋጋ አትለውጡ አትግዙ:: እነዚያ አላህ ባወረደው መመሪያ ያልፈረዱ ሁሉ ከሓዲያን ማለት እነርሱው ናቸው::"},{"id":45,"translation":"45. በእነርሱም ላይ በውስጡ ነፍስን በነፍስ፤ አይንን በአይን፤ አፍንጫን በአፍንጫ፤ ጆሮን በጆሮ፤ ጥርስን በጥርስ፤ ይያዛል:: ቁስሎችንም ማመሳሰል አለባቸው ብለን ደነገግን:: ይህንን መብቱን ይቅር ያለ ሁሉ እርሱ ለኃጢአቱ ማሰረዣው ነው:: አላህ ባወረደው መመሪያ የማይፈርዱ ሁሉ እነዚያ በደለኞቹ ማለት እነርሱ ናቸው::"},{"id":46,"translation":"46. በነብያቶች ፈለግ ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን በስተፊቱ ያለውን ተውራትን አረጋጋጭ ሲሆን አስከተልን:: ኢንጅልም በውስጡ ቀጥተኛ መመሪያና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለውን ተውራትን የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆቹም መሪና ገሳጭ ሲሆን ሰጠነው::"},{"id":47,"translation":"47. የኢንጂል ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ህግ ይፍረዱ:: አላህ ባወረደው የማይፈርዱ አመጸኞች ማለት እነርሱው ናቸው::"},{"id":48,"translation":"48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! )ከበፊቱ የነበረውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ አድርገን ባንተ ላይ ቁርኣንን አወረድን:: እናም በመካከላቸው አላህ ባወረደው ህግ ፍረድ:: እውነቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል:: ለሁላችሁም ህግንና መንገድን አደረግን:: አላህ በፈለገ ኖሮ አንድ ሕዝብ ባደረጋችሁ ነበር:: ግን በሰጣችሁ ሕግጋት ሊሞክራችሁ ነው ለእያንዳንዳችሁ መንገዶችን ያደረገው:: እናም በጎ ስራዎችን ለመስራት ተሽቀዳደሙ:: የሁላችሁም መመለሻ ወደ አላህ ብቻ ነው:: ከዚያ በእርሱ ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር እውነታ ይነግራችኋል::"},{"id":49,"translation":"49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመካከላቸው አላህ ባወረደው ህግ ፍረድ እንጂ ፈላጎቶቻቸውን አትከተል:: አላህ ወደ አንተ ካወረደው ከከፊሉ እንዳያሳስቱህ ተጠንቀቃቸው ማለትን አወረድን:: ከውሳኔው እምቢ ብለው ቢዞሩም አላህ የሚሻው በከፊሉ ኃጢአታቸው ሊቀጣቸው መሆኑን እወቅ:: ከሰዎቹ ብዙዎቹም አመጸኞች ናቸው::"},{"id":50,"translation":"50. ለመሆኑ የመሀይምነትን ፍርድ ይፈልጋሉን? ለሚያረጋግጡ ህዝቦች ሁሉ ከአላህ ይበልጥ ፍርዱ ያማረ ማን ነው?"},{"id":51,"translation":"51. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አይሁድንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አታድርጓቸው:: ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸውና:: ከናንተ ውስጥ እነርሱን ረዳቶቹ (ወዳጆቹ) የሚያደርጋቸው ከእነርሱው ነው:: አላህ አመጸኞችን ህዝቦች አያቀናም።"},{"id":52,"translation":"52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ የንፍቅና በሽታ ያለባቸውን ሰዎች «የጊዜ መለዋወጥ እንዳያገኘን እንፈራለን።» የሚሉ ሆነው አይሁድን ለመርዳት ሲቻኮሉ ታያቸዋለህ:: አላህ ድል መቀዳጀትን ወይም ከእርሱ ዘንድ የሆነን ነገር ሊያመጣና ከዚያ በነፍሶቻቸው ውስጥ በደበቁት ነገር ተጸፃቾች እንደሚሆኑ ይከጀላል።"},{"id":53,"translation":"53. እነዚያ ያመኑት ሰዎች «እነዚያ ‹ከናንተ ጋር ነን› ብለው የጠነከረ መሀላቸውን በአላህ የማሉት እነዚህ ናቸውን?» ይላሉ:: ስራዎቻቸዉም ተበላሹ:: ከሳሪዎችም ሆኑ::"},{"id":54,"translation":"54. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ውስጥ ከሃይማኖቱ ወደ ክህደት የሚመለስ ሁሉ አላህ በእርሱ ስፍራ የሚወዳቸውና የሚወዱትን በምዕምናን ላይ ትሁቶች፤ በከሓዲያን ላይ ሀያላን፤ የሆኑትንና በአላህ መንገድ የሚታገሉን የወቃሽንም ወቀሳ የማይፈሩ ህዝቦችን ያመጣል:: ይህ የአላህ ችሮታ ነው:: ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል:: አላህ ችሮታው ሰፊ ሁሉንም አዋቂ ነውና።"},{"id":55,"translation":"55. (አማኞች ሆይ!) ረዳታችሁ አላህና መልዕክተኛው እንደዚሁም እነዚያ በአላህ ያመኑት ናቸው:: እነርሱ ማለት እነዚያ ሶላትን በደንቡ የሚሰግዱ እነርሱም (ለአምልኮ) የሚያጎነብሱ ሆነው ምጽዋትን የሚሰጡ ናቸው::"},{"id":56,"translation":"56. አላህን፤ መልዕክተኛውንና እንደዚሁ እነዚያ በአላህ ያመኑትን ሰዎች የሚወዳጅ (ከአላህ ጭፍሮች ይሆናል።) የአላህ ጭፍሮች ደግሞ አሸናፊዎቹ ናቸው::"},{"id":57,"translation":"57. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ ከበፊታችሁ መጽሐፉን ከተሰጡትና ከእነዚያ ሃይማኖታችሁን መሳለቂያና መጫዎቻ ካደረጉት ከሓዲያን መካከል ወዳጆች አታድርጉ:: ትክክለኛ አማኞች እንደሆናችሁ አላህን ብቻ ፍሩ::"},{"id":58,"translation":"58. (ሙስሊሞች ሆይ!) ወደ ሶላት በጠራችሁም ጊዜ ጥሪዋን መሳለቂያና መጫዎቻ ያደርጓታል። ይህ እነርሱ የማያስተውሉ ህዝቦች በመሆናቸው ነው።"},{"id":59,"translation":"59. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በአላህና ወደኛ በተወረደው በፊትም በተወረደው ለማመናችን አብዛኞቻችሁም አመጸኞች ለመኾናችሁ እንጅ (ሌላን ነገር) ከኛ ትጠላላችሁን?» በላቸው፡፡"},{"id":60,"translation":"60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ዘንድ ቅጣቱ ከዚህ ሁሉ የከፋን ነገር ልንገራችሁን?» በላቸው:: እርሱም «አላህ የረገማቸውና በእነርሱም ላይ የተቆጣባቸው ናቸው:: ከመካከላቸዉም ዝንጀሮዎችና ከርከሮዎች ያደረጋቸው ጣዖትንም የተገዙ ሰዎች ሃይማኖት ነው:: እነዚያ በጣም በከፋ ስፍራ ናቸው:: ከቀጥተኛዉም መንገድ በጣም የተሳሳቱ ናቸው።»"},{"id":61,"translation":"61. ( አማኞች ሆይ!) ወደ እናንተ በመጡ ጊዜ ከክህደት ጋር ሁነው የገቡ ከእርሱ (ከክህደቱ) ጋር ሁነውም የወጡ ሲሆኑ ልክ እንደናንተ «አምነናል» ይላሉ:: አላህ ያንን ይደብቁት የነበረውን ነገር ሁሉ ጠንቅቆ አዋቂ ነው::"},{"id":62,"translation":"62. (መልዕክተኛችን መሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ ብዙዎቹን በኃጢአትና በበደል እርምንም የሆነ ለመብላት ሲጣደፉ ታያቸዋለህ:: ይሰሩት የነበረው በጣም ከፋ!"},{"id":63,"translation":"63. ቀሳውስቱና ሊቃውንቱ ከኃጢአት ንግግራቸውና እርምን ከመብላታቸው አይከለክሏቸዉም ኖሯልን? ይሰሩት የነበረው በጣም ከፋ!"},{"id":64,"translation":"64. አይሁድ «የአላህ እጅ የታሰረ ነው።» አሉ:: እጆቻቸው ይታሰሩ:: ባሉትም ነገር ይረገሙ። ይልቁንም የአላህ ሁለቱም እጆቹ የተዘረጉ ናቸው:: እንደፈለገ ይለግሳል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው ቁርኣን ከእነርሱ መካከል ለብዙዎቹ ትዕቢትንና ክህደትን በእርግጥ ይጨምርባቸዋል:: በአይሁድ መካከል ጠብንና ጥላቻን እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ አደረግን:: ለጦር እሳትን ባቀጣጠሉ ቁጥር አላህ ያጠፋባቸዋል:: በምድር ውስጥ ለማበላሸት ይሮጣሉ:: አላህም አበላሾችን ሁሉ አይወድም።"},{"id":65,"translation":"65. የመጽሐፉ ባለቤቶች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ ከእነርሱ ኃጢአቶቻቸውን በእርግጥ ባበስንና የመጠቀሚያ ገነቶችን በእርግጥ ባስገባናቸው ነበር።"},{"id":66,"translation":"66. እነርሱ ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታቸው ወደ እነርሱ የተወረደውን መጽሐፍ በሰሩበት ኖሮ ከበላያቸውና ከእግሮቻቸው ስር በተመገቡ ነበር:: ከእነርሱ መካከል ትክክለኛ ህዝቦች አሉ:: ከእነርሱ መካከል ብዙዎቹ ግን የሚሰሩት ነገር ከፋ!"},{"id":67,"translation":"67. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ቁርኣን አድርስ:: ይህን ባትሰራ ግን የጌታህን መልዕክቱን አላደርስክም:: አላህም ከሰዎች (ተንኮል) ይጠብቅሃል:: አላህ ከሓዲያን ሕዝቦችን አያቀናም።"},{"id":68,"translation":"68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የመጽሐፍ ባለቤቶች ሆይ! ተውራትን፤ ኢንጂልን እና ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ቁርኣንን እስከምትሰሩባቸው ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም።» በላቸው:: ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው ቁርኣን ከእነርሱ ብዙዎቹን ትዕቢትንና ክህደትን በእርግጥ ይጨምርባቸዋል:: በካሐዲያን ህዝቦች ላይ አትዘን።"},{"id":69,"translation":"69. እነዚያ ያመኑ፤ አይሁዳዊያን፤ ሳቢያኖችና ክርስቲያኖች ከእነርሱ መካከል በአላህና በመጨረሻው ቀን በትክክል ያመኑና መልካምን የሰሩ ሁሉ በእነርሱ ላይ ስጋት የለባቸዉም። አይተክዙምም።"},{"id":70,"translation":"70. የኢስራኢል ልጆች የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዝንባቸው:: ወደ እነርሱም መልዕክተኞችን ላክን:: ነፍሶቻቸው በማትወደው ነገር መልዕክተኛ በመጣላቸው ቁጥር ከፊሉን አስተባበሉ:: ከፊሉንም ይገድላሉ::"},{"id":71,"translation":"71. በእነርሱ ላይ ፈተና አለመኖሩዋን ጠረጠሩምና ታወሩ ደነቆሩም:: ከዚያም አላህ ከእነርሱ ላይ ጸጸትን ተቀበለ:: ከዚያም ከእነርሱ ብዙዎቹ እንደገና ታወሩ ደነቆሩ:: አላህ የሚሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነው::"},{"id":72,"translation":"72. እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲህ ነው።» ያሉ በእርግጥ በአላህ ካዱ:: አል መሲህም አለ፡- «የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ብቻ ተገዙ:: እነሆ በአላህ የሚያጋራ ሰው ሁሉ አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ:: መኖሪያዉም እሳት ናት:: ለበዳዩችም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም::"},{"id":73,"translation":"73. እነዚያ «አላህ የሶስት ሶስተኛ ነው።» ያሉ በእርግጥ ሁሉ ካዱ። ከአምላክም አንድ አምላክ ብቻ እንጂ ሌላ አምላክ የለም:: ከሚሉትም ነገር ካልተከለከሉ እነዚያን የካዱትን ሁሉ አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል።"},{"id":74,"translation":"74. ለመሆኑ እንደነዚህ አይነቶች ወደ አላህ አይመለሱምና ምህረትን አይለምኑትምን? አላህ መሀሪና አዛኝ ነው::"},{"id":75,"translation":"75. የመርየም ልጅ አልመሲህ ከበፊቱ ብዙ መልዕክተኞች የቀደሙት መልዕክተኛ እንጂ ሌላ አይደለም:: እናቱም በጣም እውነተኛ አማኝ ናት:: ሁለቱም ምግብን የሚበሉ ነበሩ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አናቅጽን ለከሓዲያን እንዴት እንደምናብራራና ከዚያ እነርሱ ከእውነት እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት::"},{"id":76,"translation":"76. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከአላህ ሌላ ለእናንተ መጉዳትንና መጥቀምን የማይችልን ትገዛላችሁን? አላህ እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነው።» በላቸው።"},{"id":77,"translation":"77. (መልዕክተኛች ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ውጭ ወሰንን አትለፉ:: ፊትም የተሳሳቱትንና ብዙዎቹን ህዝቦች ያሳሳቱትን ከቀጥተኛው መንገድም አሁን የተሳሳቱትን ህዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች (ስሜቶች) አትከተሉ።» በላቸው::"},{"id":78,"translation":"78. ከኢስራኢል ልጆች መካከል እነዚያ በአላህ የካዱት በዳውድና በመርየም ልጅ ዒሳ አንደበት ተረገሙ:: ይህም የአላህን ትዕዛዝ በመጣሳቸውና ወሰን የሚያልፉ በመሆናቸው ነው።"},{"id":79,"translation":"79. ይሰሩት ከነበረው መጥፎ ነገር አይከላከሉም ነበር:: ይሰሩት የነበረው ነገር በእርግጥ ከፋ!"},{"id":80,"translation":"80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ ብዙዎቹን ከእነዚያ ከካዱት ጋር ሲወዳጁ ታያለህ:: በእነርሱ ላይ አላህ በመቆጣቱ ለእነርሱ ነፍሶቻቸው ያስቀደሙት ስራ በጣም ከፋ። እነርሱም በቅጣቱ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው።"},{"id":81,"translation":"81. በአላህና በነቢዩ ወደርሱም በተወረደው ቁርኣን የሚያምኑ በኾኑ ኖሮ ወዳጆች አድርገው ባልያዙዋቸው ነበር፡፡ ግን ከእነርሱ ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው::"},{"id":82,"translation":"82. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አይሁድና እነዚያ በአላህ ያጋሩት ለእነዚያ ላመኑት በጠላትነት ከሌሎች ሁሉ የበረቱ ሆነው ታገኛቸዋለህ:: ከእነርሱ መካከል እነዚያ «እኛ ክርስቲያኖች ነን።» ያሉትን ደግሞ ለእነዚያ ላመኑት በወዳጅነት ይበልጥ የቀረቧቸው ሆነው ታገኛቸዋለህ:: ይህም ከእነርሱ መካከል ቀሳውስትና መነኮሳት በመኖራቸውና እነርሱም የማይኮሩ በመሆናቸው ነው::"},{"id":83,"translation":"83. ወደ መልዕክተኛው የተወረደውን ቁርኣን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከመረዳታቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን ሲያፈሱ ታያለህ:: ይላሉም: «ጌታችን ሆይ! ባንተ አምነናልና ከመስካሪዎች ጋር ፃፈን።"},{"id":84,"translation":"84. «ጌታችን ከመልካም ሰሪዎች ጋር ገነትን ሊያስገባን የምንከጅል ስንሆን በአላህና ከእርሱ በመጣልን እውነት ሁሉ የማናምንበት ምን ምክንያት አለን?» (ይላሉ።)"},{"id":85,"translation":"85. እናም ባሉት ምክንያት አላህ በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶችን በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ መነዳቸው። ይህም የበጎ ሰሪዎች ዋጋ ነው።"},{"id":86,"translation":"86. እነዚያም የካዱና በአናቅጻችን ያስተባበሉ ሁሉ የእሳት ጓዶች ናቸው::"},{"id":87,"translation":"87. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ለእናንተ የፈቀደላችሁን ጣፋጮች በራሳችሁ ላይ እርም አታድርጉ:: ወሰንንም አትለፉ:: አላህ ወሰን አላፊዎችን ሁሉ አይወድምና::"},{"id":88,"translation":"88. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ የተፈቀደ ጥሩ ሲሆን ብሉ። ያንን ያመናችሁበት ጌታችሁን አላህንም ፍሩ።"},{"id":89,"translation":"89. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ከመሀሎቻችሁ መካከል በውድቁ አይዛችሁም:: ባሰባችሁበት መሀላ ግን ይይዛችኋል:: እናም መሀላዎችን ባፈረሳችሁ ጊዜ ማሰረዣው ቤተሰቦቻችሁን ከምትመግቡት ከመካከለኛው ምግብ ለአስር ሚስኪኖች ማብላት ወይም እነርሱን ማልበስ ወይም የአንዲትን ባሪያ ጫንቃን ነፃ ማውጣት ነው:: ከተባሉት አንዱንም ያለገኘ ሶስት ቀናትን መፆም ብቻ ነው:: ይህ በማላችሁና መሀላዎቻችሁን ባፈረሳችሁ ጊዜ ማሰረዣው ነው:: መሀላዎቻችሁንም ጠብቁ:: ልክ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ አናቅጽን ያብራራል:: እናንተም ልታመሰግኑት ይከጀላልና::"},{"id":90,"translation":"90. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ፤ የቁማር ጫዎታ፤ ጣዖታትን መገዛት እና አዝላምም ከሰይጣን ስራ የሆነ እና እርኩስ ተግባር ብቻ ናቸው። ትድኑ ዘንድም ራቁት።"},{"id":91,"translation":"91. ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር አማካኝነት በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጭርና አላህን ከማውሳትና ከስግደት ሊያግዳችሁ ብቻ ነው:: ታዲያ እናንተ ከእነዚህ ነገሮች ተከልካዩች ናችሁን?"},{"id":92,"translation":"92. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህን ብቻ ታዘዙ:: መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: ተጠንቀቁ:: ብትሸሹም በመልዕክተኛችን ላይ ያለበት በግልጽ መልዕክቱን ማድረስ ብቻ መሆኑን እወቁ::"},{"id":93,"translation":"93. በእነዚያ በአላህ ባመኑትና በጎ ስራዎችን በሰሩት ላይ ከተጠነቀቁና ካመኑ መልካምን ከሰሩ፤ ከዚያም ከተጠነቀቁና ካመኑ፤ ከዚያም ከተጠነቀቁና ስራንም ካሳመሩ ከመከልከሉ በፊት በተመገቡት ነገር ኃጢአት የለባቸዉም። አላህ ስራቸውን አሳማሪዎቹን ሁሉ ይወዳልና።"},{"id":94,"translation":"94. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ በሐጅ ጊዜ እጆቻችሁና ጦሮቻችሁ (በሚያገኙት) በሚያድኑት ታዳኝ አውሬ አላህን በሩቁ ሆኖ የሚፈራውን ሰው ሊገልጽ ይሞክራችኋል:: ከዚያ በኋላ ወሰንን ያለፈና ያደነ ሰው ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለበት::"},{"id":95,"translation":"95. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እናንተ በሐጅ ስራ ውስጥ ስትሆኑ አውሬን አትግደሉ:: ከናንተም እያወቀ አውሬን የገደለ ሰው ቅጣቱ ከናንተ መካከል ሁለት የፍትሀዊነት ባለቤቶች የሚፈርዱበትና ወደ ካዕባ ደራሽ መስዋዕት ሲሆን ከቤት እንሰሳዎች የገደለውን ነገር ብጤ መስጠት ወይም ሚስኪኖችን ማብላት ወይም የዚህን ልክ መፆም ማሰረዣው ነው:: ይህም የስራውን ከባድ ቅጣት እንዲቀምስ ነው:: ሳይከለከል በፊት ላለፈው ነገር አላህ ይቅርታ አደረገ:: ወደ ጥፋቱ የተመለሰን ሁሉ አላህ ይበቀለዋል:: አላህ አሸናፊና የብቀላ ባለቤት ነው::"},{"id":96,"translation":"96. ሙስሊሞች ሆይ! የባህር እንሰሳና ምግቡ ለእናንተና ለመንገደኞች ሁሉ መጠቀሚያ ይሆን ዘንድ ተፈቀደላችሁ:: በሐጅ ላይ እስካላችሁ ድረስ ግን የየብስ አውሬ በእናንተ ላይ እርም ተደረገ:: ያንን ወደ እርሱ የምትሰበሰቡበትን አላህን ፍሩ::"},{"id":97,"translation":"97. አላህ ያ የተከበረውን ቤት ካዕባን፤ ክልክል የሆነውን ወር፤ ወደ መካ የሚወስደውን መስዋዕቱንና ባለ ምልክቶቹን መንጋዎች ለሰዎች እምነት (ዋልታ) መቋቋሚያ አደረገ:: ይህ የሆነው አላህ በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑንና ሁሉን ነገር አዋቂ መሆኑን እንድታውቁ ዘንድ ነው::"},{"id":98,"translation":"98. (ሰዎች ሆይ!) አላህ ቅጣተ ብርቱም መሀሪና አዛኝም መሆኑን እወቁ።"},{"id":99,"translation":"99. በመልዕክተኛው ላይ መልዕክቱን ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትም:: አላህ የምትገልጹትንም ሆነ የምትደብቁትን ሁሉ ያውቃል::"},{"id":100,"translation":"100. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመጥፎው ነገር ብዛቱ ቢያስገርምህ እንኳ መጥፎና ጥሩው መቼም አይስተካከሉም። ባለ ልቦች ሆይ! ትድኑ ዘንድ አላህን ብቻ ፍሩ።» በላቸው።"},{"id":101,"translation":"101. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ ቢገለጹ ከሚያስከፏችሁ ነገሮች አትጠይቁ:: ቁርኣንም በሚወርድበት ጊዜ ከእርሷ ብትጠይቁ ለእናንተ ትገለፃለች:: ከእርሷ ግን አላህ ይቅርታ አደረገ:: አላህ መሀሪና ታጋሽ ነውና።"},{"id":102,"translation":"102. ከናንተ በፊት የነበሩ ሕዝቦች ተመሳሳዩን ጠየቁ። ከዚያም (በትክክል ባለመፈጸማቸው ምክንያት) ከካሐዲያን ሆኑ።"},{"id":103,"translation":"103. አላህ «በሒራ»፤ «ሳኢባ»፤ «ወሲላ»ና «ሐም» የተባሉ ነገሮች ከሸሪዓ አላደረገም:: ግን እነዚያ የካዱት ህዝቦች በአላህ ላይ ውሸትን ይቀጥፋሉ:: አብዛሀኞቻቸውም አያስተውሉም። (1)","footnotes":"(1) እነዚህ አላህ መንገድ ያላደረገላቸው ሙሽሪኮች ለጣዖቶቻቸው የምሰጧቸው የእንስሳት ስሞች ናቸው።\n በሂራ፡- የተወሰነ ቁጥር ጥጃዎችን ከወለደች በኋላ ጆሮዋን ቆርጠው ለታቦት የሚተውትና የማይገለገሉባት እንስሳ ነች።\nሳኢባ፡- ለታቦት የሚታውትና የማይገለገሉባት እንስሳ ነች።\nዋሲላብ፡- ብዙ ሴቶችን በተከታታይ ከወለደች በኋላ ለታቦት የሚትታው እንሰሳ ነች። \n ሃም፡- የተወሰነ መጠን ያለው የወለደ (ያስወለደ) እና ከዚያ በኋላ ለታቦት የሚታው ወይፈን ነው። ይህ ሁሉ አላህ መንገድ ያላደረገ ውሸት ነው።"},{"id":104,"translation":"104. «አላህ ወደ አወረደውና ወደ መልዕክተኛው ኑ» በተባሉ ጊዜ «አባቶቻችንን ያገኝንበት መንገድ ይበቃናል።» ይላሉ:: አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና ወደ ቀናው መንገድ የማይመሩ ቢሆኑም ይበቃቸዋልን?"},{"id":105,"translation":"105. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁን (ማዳን ኃላፊነቱ) በራሳችሁ ላይ ነው። ራሳችሁን ወደቀናው መንገድ ከመራችሁ የሌሎች መሳሳት እናንተን አይጎዳችሁም:: የሁላችሁም መመለሻ ወደ አላህ ነው። እናም ትሰሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል።"},{"id":106,"translation":"106. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አንዳችሁ ሞት በመጣበት ጊዜ በኑዛዜ ወቅት በመካከላችሁ ለምስክርነት ከናንተ መካከል ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶች የሆኑ ሰዎች፤ ወይም በምድር ብትጓዙና የሞት አደጋ ብትነካችሁ ከሌሎቻችሁ የሆኑ ሁለት ሌሎች ሰዎች መመስከር ነው:: ብትጠራጠሩም ከአስር ሶላት በኋላ አቁሟቸውና «የሚመሰክርለት ሰው የዝምድና ባለቤት ቢሆንም እንኳን በእርሱ ዋጋን አንገዛም:: የአላህን ምስክርነት አንደብቅም:: ያን ጊዜማ ደብቀን ብንገኝ ከኃጢአተኞች ነን።» ብለው በአላህ ስም ይምላሉ::"},{"id":107,"translation":"107. ሆኖም እነርሱ ኃጢአት (በውሸት ምስክርነት) የተገቡ መሆናቸው ቢታወቅ ከእነዚያ ከሟቹ ቅርብ ዘመዶች ውርስ ከተገባቸው ሁለት ሌሎች ሰዎች በስፍራቸው በምስክሮች ስፍራ ይቆሙና «ምስክርነታችን ከእነርሱ ምስክርነት ይልቅ እውነት ነው ወሰንም አላለፍንም። ያን ጊዜ እኛ ከበዳዩቹ ነን።» ሲሉ በአላህ ይምላሉ።"},{"id":108,"translation":"108. ይህ (አሰራር) ምስክርነት በተገቢው ላይ ለማምጣታቸው ወይም ከመሀላዎቻቸው በኋላ የመሀላዎቹ ወደ ወራሾች መመለስን ለመፍራት በጣም የቀረበ ነው:: አላህን ብቻ ፍሩ:: እሱን ብቻ ስሙትም:: አላህ አመጸኛ ሕዝቦችን አይመራምና::"},{"id":109,"translation":"109. (መልዕክተኛችን ሆይ!) አላህ መልዕክተኞቹን ሰብስቦ እንዲህ ባለ ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ፡- «ሕዝቦቻችሁ ምን መለሱላችሁ?» መልዕክተኞቹም: «እኛ እውቀቱ የለንም:: ሩቅ ሚስጥሮችን ሁሉ የምታውቀው አንተው ነህ።» ይላሉ።"},{"id":110,"translation":"110. አላህ እንዲህ በሚልበት ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ላንተና ለእናትህ የዋልኩላችሁን ውለታ አስታውስ:: በሩሀል ቁዱስ (በጅብሪል) አጠነከርኩህ:: በሕጻንነትህም አድገህም ሰዎችን ማናገር ቻልክ። መጽሐፉንና ጥበብን ተውራትንና ኢንጂልንም አስተማርኩህ:: ከጭቃም የወፍ ቅርጽ ዓይነት በፈቃዴ መሥራት ቻልክ:: በሷ ውስጥ ነፈህ:: በፈቃዴም እውነተኛ በራሪ ሆነች:: እውር ሆኖ የተወለደንና ለምጻምን በፈቃዴ መፈወስ ቻልክ:: ሟችንም በፈቃዴ አስነሳህ:: የኢስራኢልንም ልጆች ግልጽ መረጃ ባመጣህላቸው ጊዜ ሊያጠቁህ ሲያስቡ አቀብኩልህ:: ከመካከላቸዉም እነዚያ በአላህ የካዱት ‹ይህ ግልጽ ድግምት ነው› አሉ:: ይህን ሁሉ ውለታዬን አስታውስ::"},{"id":111,"translation":"111. «ለሃዋሪያቱም፡- ‹በእኔና በመልዕክተኛዬ እመኑ።› የሚል ራዕይ በገለጽኩ ጊዜም የሆነውን አስታውስ። ‹አምነናል:: እኛ ሙስሊሞች ለመሆናችን ምስክር ሁን› አሉም።"},{"id":112,"translation":"112. «ሃዋሪያቶቹም፡- ‹የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ጌታህ ከሰማይ ማዕድ ሊያወርድልን ይቻላልን?› ባሉ ጊዜ የሆነውን አስታውስ። ዒሳም፡-‹ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ አላህን ብቻ ፍሩ።› አለ።"},{"id":113,"translation":"113. «‹ከእርሱ ልንመገብ ልቦቻችንም እርካታን ይጎናጸፉ ዘንድ ብቻ ነው ይህን የጠየቅነው:: የነገርከንም ተጨባጭ እውነት መሆኑን ልናውቅና ለዚህም መስካሪዎች ለመሆን ፈልገን ነው።› አሉ::"},{"id":114,"translation":"114. «የመርየም ልጅ ዒሳም፡- ‹ጌታችን አላህ ሆይ! ከሰማይ ማዕድን አውርድልን ለእኛ ለመጀመሪያዎቻችንና ለመጭዎቹም ትውልዶች በዓል (የደስታ እለት) ካንተ የሆነችም ተዐምር ትሆንልን ዘንድ :: ሲሳይንም ለግሰን:: አንተ ከለጋሾች ሁሉ የበለጥክ ለጋሽ ነህና› አለ።»"},{"id":115,"translation":"115. አላህም፡- «ማዕዷን አወርድላችኋለሁ:: ግና ከዚህ ተአምር በኋላ ከመካከላችሁ በእኔ ለካዱት ሁሉ በዓለማት ላይ ማንንም የማልቀጣውን አስከፊ ቅጣት እቀጣቸዋለሁ።» አለ።"},{"id":116,"translation":"116. (መልዕክተኛች ሙሐመድ ሆይ!) አላህ፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ሰዎችን ‹እኔንና እናቴን ከአላህ ውጭ ሁለት አማልዕክት አድርጋችሁ ያዙን።› ብለሃልን?» በሚለው ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ:: ዒሳም አለ፡- «ክብርና ልዕልና ላንተ ብቻ ይሁን! ለእኔ ልለው የማይገባኝን ነገር ማለቴ ፈጽሞ አግባብ አይደለም:: ይህን ተናግሬ ከሆነም ታውቀዋለህ:: አንተ በውስጤ ያለውን ሁሉ ጠንቅቀህ ታውቃለህ:: እኔ ግን ባንተ ውስጥ ያለውን አላውቅም:: አንተ ሩቅ ሚስጥራትን ሁሉ አዋቂ ነህና::"},{"id":117,"translation":"117. «የነገርኳቸው ያን ያዘዝከኝን ብቻ ነው:: ‹የእኔም የእናንተም ጌታ የሆነውን አላህን ብቻ አምልኩ ነው› ያልኳቸው:: በመካከላቸው በነበርኩበት ወቅት ስለ እነርሱ መስካሪ ነበርኩ:: እንዳርግ ካደረግከኝ በኋላ ግን የእነርሱ ጠባቂና ተቆጣጣሪ አንተው ብቻ ነበርክ:: አንተ በሁሉም ነገር ላይ መስካሪ ነህና።"},{"id":118,"translation":"118. «ብትቀጣቸው እነርሱ የአንተው ባሮችህ ናቸው:: ብትምራቸው ደግሞ አንተ ኃያልና ጥበበኛ ነህ።» ይላል።"},{"id":119,"translation":"119. አላህም እንዲህ ይላል፡- «ይህ ቀን እውነቱ ለእውነተኞች የሚጠቅምበት ቀን ነው::» ለእውነተኞች ከስሮቿ ወንዞች የሚፈሱባት ገነት ተዘጋጅቶላቸዋል:: በውስጧም ለዝንተ ዓለም ይኖራሉ:: አላህ በእነርሱ ተግባር ተደስቷል:: እነርሱም በእርሱ ችሮታ ተደስተዋል:: ይህ ታላቅ ስኬት ነውና::"},{"id":120,"translation":"120. የሰማያት የምድርና በውስጣቸው ያሉ ፍጡራን ሁሉ ባለቤትነት የአላህ ብቻ ነው:: እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው።"}]},{"id":6,"verses":[{"id":1,"translation":"1.ምስጋና ሁሉ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረ ጨለማዎችንና ብርሃንን ላደረገው ለአላህ የተገባ ነው:: ከዚያም እነዚያ በእርሱ የካዱ ሁሉ ጣዖታትን ከጌታቸው ጋር ያስተካክላሉ::"},{"id":2,"translation":"2. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ከጭቃ የፈጠራችሁ ከዚያም የሞት ጊዜን የወሰነ ነው:: እርሱም ዘንድ ለትንሳኤ የተወሰነ ጊዜ አለ:: ከዚያም እናንተ በመቀስቀሳችሁ ትጠራጠራላችሁን?"},{"id":3,"translation":"3. እርሱም ያ በሰማያትም በምድርም ሊገዙት የሚገባው አላህ ነው:: (ሰዎች ሆይ!) ሚስጥራችሁንም ሆነ ግልፃችሁን ጠንቅቆ ያውቃል። የምትሰሩትን ሁሉ ጠንቅቆ ያውቃል::"},{"id":4,"translation":"⒋ ከጌታቸው አናቅጽ አንዱም አይመጣላቸዉም ከእርሱ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጂ::"},{"id":5,"translation":"5. ቁርኣን በመጣላቸው ጊዜም በእርግጥ አስተባበሉ:: ግን የእዚያ በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ነገር ዜናዎች ቅጣት ይመጣባቸዋል።"},{"id":6,"translation":"6. ከበፊታቸው ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች መካከል ብዙዎቹን ማጥፋታችንን አላዩምን? ለእናንተ ያላስመቸነውን ለእነርሱ በምድር ውስጥ አስመቸናቸው:: በእነርሱም ላይ ዝናብን የተከታተለ ሲሆን ላክን:: ወንዞችንም በስራቸው እንዲፈሱ አደረግን:: በኃጢአቶቻቸዉም ምክንያት አጠፋናቸው:: ከኋላቸዉም ሌሎችን ሰዎች በየክፍለ ዘመኑ አስገኘን::"},{"id":7,"translation":"7. በእነርሱ ላይ በወረቀት የተፃፈን መጽሐፍ ባወረድንና በእጆቻቸው በነኩት ኖሮ እነዚያ ከሓዲያን «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።» ባሉ ነበር::"},{"id":8,"translation":"8. «በእርሱ (በሙሐመድ) ላይ መልአክ ለምን አይወረድለትም?» አሉ። ነገር ግን መላዕክን ባወረድንለትና (ባያምኑ ኖሮ) የጥፋታቸው ነገር በተፈረደ ነበር:: ከዚያም አይቆዩም ነበር::"},{"id":9,"translation":"9. መልዕክተኛውን ከመላዕክት መካከል ባደረግነው ኖሮ ወንድ ሰው አድርገን በመላክ በእነርሱ ላይ የሚያመሳስሉትን ነገር ባመሳሰልንባቸው ነበር።"},{"id":10,"translation":"10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት በነበሩ መልዕክተኞችም ላይ ተላግጧል:: እናም በእነዚያ ባላገጡት ላይ ያላገጡበት ውጤት በእነርሱ ላይ ተፈጽሟል::"},{"id":11,"translation":"11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ከሓዲያንን) «በምድር ላይ ሂዱና የእነዚያን የአስተባባዮችን መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ።» በላቸው::"},{"id":12,"translation":"12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው: «በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የማን ነው?» በላቸውም: «የአላህ ብቻ ነው። አላህ በራሱ ላይ እዝነትን ፃፈ:: በዚያ ጥርጥር በሌለበት በትንሳኤ ቀን ይሰበስባችኋል:: እነዚያ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ማለት እነርሱው ናቸው። እናም አያምኑም።"},{"id":13,"translation":"13. «በሌሊትም ሆነ በቀን ጸጥ ያለው ሁሉ የእርሱው ነው:: እርሱም ሰሚውና አዋቂው ነው።»"},{"id":14,"translation":"14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከሆነው አላህ እርሱ ፍጡርን የሚመግብና ለራሱ የማይመገብ አምላክ ሲሆን ሌላን አምላክ እይዛለሁን?» በላቸው። «እኔ መጀመሪያ ትዕዛዝን ከተቀበለ ሰው እንድሆን ታዘዝኩ:: ‹ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትሁን።› ተብያለሁ።» በላቸው::"},{"id":15,"translation":"15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ በጌታዬ ላይ ባምጽ የዚያን የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ።» በላቸው።"},{"id":16,"translation":"16. በዚያ ቀን ከእርሱ ላይ ቅጣት የሚመለስለት ሰው ሁሉ በእርግጥ አላህ አዘነለት:: ይህም ግልጽ ስኬት ነው።"},{"id":17,"translation":"17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ችግር ቢያደርስብህ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ማንም አስወጋጅ የለም:: በጎ ነገርን ቢሰጥህም እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው::"},{"id":18,"translation":"18. እርሱ ከባሮቹ በላይ ሲሆን ሁሉን አሸናፊ ነው:: እርሱ ጥበበኛውና ውስጠ አዋቂው ነው።"},{"id":19,"translation":"19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከምስክርነት ሁሉ ይበልጥ ታላቁ የትኛው ነው?» በላቸው። «አላህ፤ በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ ነው። ይህም ቁርኣን እናንተንና የደረሰውንም ሁሉ ላስፈራራበት ወደ እኔ ተወረደ:: ከአላህ ጋር ሌሎች አማልክት መኖራቸውን እናንተ ትመሰክራላቸሁን?» በላቸው:: «እኔ ግን ፈጽሞ በዚህ አልመሰክርም።» በላቸው:: «እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እኔም በአላህ ከምታጋሩት ሁሉ ንጹህ ነኝ።» በላቸው።"},{"id":20,"translation":"20. እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው አይሁድና ክርስቲያኖች ልክ ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ ሁሉ ሙሐመድንም በትክክል ያውቁታል:: እነዚያ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩት እነርሱ ፈጽሞ አያምኑም::"},{"id":21,"translation":"21. በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም በአናቅጽ ካስተባበለ ይበልጥ በደለኛ ማን ነው? እነሆ በደለኞች አይድኑም።"},{"id":22,"translation":"22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሁላቸውንም በምንሰበሰብበትና ከዚያም ለእነዚያም በአላህ ላጋሩት፤ «‹እነዚያም ለአላህ ተጋሪዎች ናቸው› ብላችሁ ታስቧቸው የነበሩት ተጋሪዎቻችሁ የት ናቸው?» የምንልበትን ቀን (አስታውስ)።"},{"id":23,"translation":"23. ከዚያም የፊትና መልሳቸው «በጌታችን በአላህ ይሁንብን አጋሪዎች አልነበርንም።» ማለት እንጂ ሌላ አይሆንም።"},{"id":24,"translation":"24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በነፍሶቻቸው ላይ እንዴት እንደዋሹና ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር ሁሉ ከእነርሱ እንዴት እንደተሰወረባቸው ተመልከት::"},{"id":25,"translation":"25. ከእነርሱ መካከል ወደ አንተ የሚያዳምጥ ሰው አለ:: በልቦቻቸው ላይ እንዳያውቁት ሽፋኖችን፤ በጆሮዎቻቸዉም ላይ እንዳይሰሙት ድንቁርናን አደረግን:: ተዐምርን ሁሉ እንኳን ቢያዩ በእርሷ አያምኑም:: ወደ አንተ በመጡ ጊዜ የሚከራከሩህ ሆነው እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች «ይህ ቁርኣን የቀድሞዎቹ ሰዎች ጹሑፍ ተረቶች ስብስብ እንጂ ሌላ አይደለም።» ይላሉ::"},{"id":26,"translation":"26. እነርሱም ሰዎችን ከእርሱ ይከልክላሉ፤ ከእርሱም ይርቃሉ፤ በዚህም ተግባራቸው ነፍሶቻቸውን እንጂ ሌላን አያጠፉም:: ግን አያውቁም::"},{"id":27,"translation":"27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእሳትም ላይ እንዲቆሙ በተደረጉ ጊዜ «ምን ነው ወደ ምድረ ዓለም በተመለስንና በጌታችን አናቅጽ ባላስተባበልን ከትክክለኛ አማኞችም ጋር በሆንን ዋ! ምኞታችን።» ባሉ ጊዜ ብታይ ኖሮ (የሚያስደነግጥህን ነገር ባየህ ነበር)"},{"id":28,"translation":"28. ይልቁንስ ከዚህ በፊት ይደብቁት የነበሩት ነገር ሁሉ ለእነርሱ ተገለጸ:: ወደ ምድረ ዓለም በተመለሱም ኖሮ ወደ ተከለከሉት ነገር በተመለሱ ነበር:: እነርሱ ሐሰተኞች ናቸው።"},{"id":29,"translation":"29. «ሕይወት ማለት ቅርቢቱ ሕይወታችን እንጂ ሌላ አይደለችም:: እኛም ፈጽሞ ተቀስቃሾች አይደለንም።» አሉ።"},{"id":30,"translation":"30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጌታቸው ዘንድ ለምርመራ እንዲቆሙ በተደረጉ ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ባየህ ነበር::) «ይህ እውነት አይደለምን?» ይላቸዋል:: እነርሱም «በጌታችን ይሁንብን እውነት ነው።» ይላሉ:: «እናም ትክዱት በነበራችሁት ምክንያት ቅጣቱን ቅመሱ።» ይላቸዋል::"},{"id":31,"translation":"31. እነዚያ ከአላህ ጋር መገናኘትን ያስተባበሉ ሁሉ በእርግጥ ከሰሩ:: ስዓቲቱም በድንገት በመጣችባቸው ጊዜ እነርሱ ኃጢአቶቻቸውን በጀርባዎቻቸው ላይ የሚሸከሙ ሲሆኑ «በምድረ ዓለም ባጓደልነው ነገር ላይ ዋ ጥፋታችን!» ይላሉ። አዋጅ ያ የሚሸከሙት ነገር ምንኛ ከፋ!"},{"id":32,"translation":"32. የቅርቢቱ ሕይወት ማለት ጨዋታና ላግጣ እንጂ ሌላ አይደለችም። የመጨረሻይቱ አገር (ገነት) ግን ለእነዚያ ለሚጠነቀቁት ሰዎች ሁሉ በጣም በላጭ ናት። አታውቁምን? (አትገነዘቡምን)?"},{"id":33,"translation":"33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ የሚሉህ ነገር እንደሚያሳዝንህ በእርግጥ እናውቃለን:: እነርሱ በእርግጥ አያስተባብሉህም:: ግን በዳዮች በአላህ አናቅጽ ይክዳሉ::"},{"id":34,"translation":"34. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከበፊትህ የነበሩት መልዕክተኞች ተስተባብለዋል:: በተስተባበሉበትም ነገርና በተሰቃዩት ላይ እርዳታችን እስከመጣላቸው ድረስ ታገሱ:: የአላህን ቃላት የሚለዉጥ የለም:: ከመልዕክተኞቹም ወሬ (የምትረጋጋበት) በእርግጥ መጣልህ::"},{"id":35,"translation":"35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢስላምን መተዋቸው ባንተ ላይ ከባድ ቢሆንብህም በምድር ውስጥ ቀዳዳን ወይም በሰማይ ውስጥ መሰላልን ልትፈልግና ተዓምር ልታመጣላቸው ከቻልክ ሞክር:: አላህ በፈለገ ኖሮ ሁሉንም በቅኑ መንገድ ላይ በሰበሰባቸው ነበር:: ስለዚህ ከተሳሳቱት ሰዎች በፍጹም አትሁን::"},{"id":36,"translation":"36. ጥሪን የሚቀበሉት እነዚያ የሚሰሙት ብቻ ናቸው:: ሙታንማ አላህ ይቀሰቅሳቸዋል:: ከዚያም ወደ እርሱ ብቻ ይመለሳሉ::"},{"id":37,"translation":"37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን «ከጌታው በእርሱ ላይ ለምን ተአምር አልተወረደለትም?» አሉ:: «አላህ ተአምርን ለማውረድ ቻይ ነው:: ግን አብዛኞቻቸው ይህን እውነታ አያውቁም።» በላቸው::"},{"id":38,"translation":"38. በምድር ላይ የሚሄድ ተንቀሳቃሽም ሆነ በሁለት ክንፎቹ የሚበር ሁሉ መሰሎቻችሁ ሕዝቦች እንጂ ሌላ አይደሉም:: በመጽሐፉ ውስጥ ምንንም ነገር አልተውንም:: ከዚያ ሁሉም ወደ ጌታቸው ይሰበሰባሉ::"},{"id":39,"translation":"39. እነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉ ሁሉ እውነትን የማይሰሙ ደንቆሮዎች፤ ሐቅን የማይናገሩ ዲዳዎችና በጨለማዎች ውስጥ ያሉ ናቸው:: አላህ መጥመሙን የሚሻበትን ሰው ያጠመዋል:: ወደ ቀናው መንገድ መመራቱን የሚሻለትን ሰው ደግሞ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ያደርገዋል::"},{"id":40,"translation":"40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የአላህ ቅጣት ቢመጣባችሁ ወይም ትንሳኤ ብትመጣባችሁ ከአላህ ሌላ ትጠራላችሁን? እውነተኞች ከሆናችሁ (እስኪ ንገሩኝ።)» በላቸው።"},{"id":41,"translation":"41. «በፍፁም። እውነታው እርሱን ብቻ ትጠራላችሁ:: ቢሻ ወደ እርሱ የምትጠሩበትን ነገር ያስወግድላችኋልና የምታጋሩትንም ሁሉ ትረሱታላችሁ።» በላቸው::"},{"id":42,"translation":"42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለነበሩት ሕዝቦች አያሌ መልዕክተኞችን በእርግጥ ላክን:: (ከዚያም እንቢተኛ ሆኑ::) ለእኛ ይተናነሱም ዘንድ በድህነትና በችግር ቀጣናቸው::"},{"id":43,"translation":"43. ታዲያ ቅጣታችን በመጣባቸው ጊዜ አይተናነሱም ኖሯልን? ነገር ግን ልቦቻቸው ደረቁ:: ይሰሩት የነበሩትንም መጥፎ ነገር ሰይጣን መልካም ነገር አስመስሎ አሳያቸው።"},{"id":44,"translation":"44. በእርሱ ይገሰጹበት የነበረውን ነገር በዘነጉ ጊዜ ለእነርሱ የሁሉን ነገር ደጃፎችን ከፈትንላቸውና በኑሮ አስመቸናቸው:: በተሰጡትም ነገር በተደሰቱ ጊዜ በድንገት ያዝናቸው:: ወዲያውኑም እነርሱ ተስፋ ቆራጮች ሆኑ።"},{"id":45,"translation":"45. የእነዚያ የበደሉት ሕዝቦች መጨረሻ ተቆረጠ:: ምስጋና ሁሉ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው::"},{"id":46,"translation":"46.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እስቲ ንገሩኝ አላህ መስሚያችሁንና ማያዎቻችሁን ቢወሰድባችሁና በልቦቻችሁ ላይ ቢያትም ከአላህ ሌላ እርሱኑ የሚያመጣላችሁ አምላክ ማን ነው?» በላቸው:: አናቅጽን እንዴት እንደምናብራራና ከዚያም እነርሱ እንዴት መንገዱን እንደሚስቱ ተመልከት::"},{"id":47,"translation":"47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እስቲ ንገሩኝ የአላህ ቅጣት ድንገት ወይም በይፋ ቢመጣባችሁ ከአመጸኛ ህዝቦች ሌላ ይጠፋልን?» በላቸው::"},{"id":48,"translation":"48. መልዕክተኞችንም በመልካም አብሳሪና ከመጥፎ አስፈራሪ አድርገን እንጂ አንልክም:: እናም በእነርሱ ያመኑና በጎ ተግባርን የሰሩ ሁሉ ስጋት የለባቸዉም። አይተክዙምም።"},{"id":49,"translation":"49. እነዚያ አናቅጻችንን ያስተባበሉት ደግሞ በአመፃቸው ምክንያት ቅጣት ያገኛቸዋል።"},{"id":50,"translation":"50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልላችሁም:: ሩቅ ሚስጥርንም አላውቅም:: መልዓክ ነኝም አልልም:: ወደ እኔ የሚወርድልኝን መልዕክት ብቻ እንጂ ሌላን አልከተልም።» በላቸው። «እውርና የሚያይ ይስተካከላሉን? አታስተነትኑምን!» በላቸው።"},{"id":51,"translation":"51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ከአላህ ሌላ ወዳጅና አማላጅ የሌላቸው ሲሆኑ ወደ ጌታቸው መሰብሰብን የሚፈሩትን ሰዎች ይጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ(ቁርኣን) አስፈራራ::"},{"id":52,"translation":"52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያን የጌታቸውን ፊት የሚሹ ሆነው በጧትና በማታ የሚጠሩትን አማኞች ከአጠገብህ አታባር:: እነርሱን መቆጣጠር ባንተ ላይ ምንም የለብህም:: አንተንም መቆጣጠር በእነርሱ ላይ ምንም የለባቸዉም::ታባርራቸውና ከበደለኞችም ትኾን ዘንድ (አታባር)።"},{"id":53,"translation":"53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁም «ከመካከላችን አላህ በእነርሱ ላይ ችሮታውን የለገሳቸው እነዚህ ናቸውን?» ይሉ ዘንድ ከፊላቸውን በከፊሎች ሞከርን:: አላህ አመስጋኞቹን ከሁሉም በላይ አዋቂ አይደለምን?"},{"id":54,"translation":"54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በተዐምራታችን የሚያምኑት ሰዎች ሁሉ ወደ አንተ በመጡ ጊዜ «ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን:: ጌታችን በራሱ ላይ እዝነትን ፃፈ:: እነሆ ከናንተ ውስጥ ስህተትን ስራ የሰራና ከዚያ ተጸጽቶ ወዲያውኑ ስራውን ላሳመረ እርሱ (አላህ) መሀሪና አዛኝ ነው።» በላቸው።"},{"id":55,"translation":"55. ልክ እንደዚሁም እውነቱ እንዲገለጽና የወንጀለኞችም መንገድ ትብራራ ዘንድ አናቅጽን እንገልፃለን::"},{"id":56,"translation":"56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸውን (ባዕድ አማልክት) ከመገዛት ተከልክያለሁ።» በላቸው። «ዝንባሌያችሁንም አልከተልም:: ያን ካደረኩኝ በእርግጥ ተሳሳትኩ:: እኔም ከተመሪዎቹ አይደለሁም።» በላቸው።"},{"id":57,"translation":"57. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እኔ ከጌታዬ በመጣልኝ ግልጽ ማስረጃ ላይ ነኝ:: እናንተ ግን በእርሱ አስተባበላችሁ:: ያ የምትቻኮሉበት ቅጣት ውሳኔ እኔ ዘንድ አይደለም:: ፍርዱ ለአላህ ብቻ ነው:: አላህ እውነቱን ይፈርዳል:: እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነውና።» በላቸው።"},{"id":58,"translation":"58. «ያ የምትቻኮሉበት ቅጣት እኔ ዘንድ በሆነ ኖሮ በእኔና በእናንተ መካከል ነገሩ (ቅጣታችሁ) በተፈጸመ ነበር:: አላህ በደለኞችን አዋቂ ነው።» በላቸው::"},{"id":59,"translation":"59. የሩቅ ሚስጥሮች መክፈቻዎች ሁሉ እርሱ ዘንድ ብቻ ናቸው:: ከእርሱ በስተቀር ማንም አያውቃቸዉም:: በየብስና በባህር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል:: አንዲትም ቅጠል አትረግፍም አላህ የሚያውቃት ብትሆን እንጂ:: በመሬት ጨለማዎች ውስጥ ቅንጣት እርጥብም ሆነ ደረቅ አንድም ነገር የለም ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢሆን እንጂ::"},{"id":60,"translation":"60. እርሱ (አላህ) ያ በሌሊት የሚያስተኛችሁ በቀን የሰራችሁትንም ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈጸም ዘንድ በቀን ውስጥ የሚቀሰቅሳችሁ ነው:: ከዚያም መመለሻችሁ ወደ እርሱ ብቻ ነው:: ከዚያም ትሰሩት የነበራችሁትን ነገር ሁሉ ይነግራችኋል::"},{"id":61,"translation":"61. እርሱ ከባሮቹ በላይ ሲሆን ሁሉን አሸናፊ ነው:: በእናንተ ላይም ተጠባባቂዎች መላዕክትን ይልካል:: አንዳችሁንም የሞት ሰዓቱ በመጣበት ጊዜ የሞት መልዕክተኞቻችን ትዕዛዛትን የማያጓድሉ ሲሆኑ ይገድሉታል::"},{"id":62,"translation":"62. ከዚያም እውነተኛ ወደ ሆነው ጌታቸው ወደ አላህ ይመለሳሉ:: (ሰዎች ሆይ!) አስትዉሉ! አዋጅ ፍርዱ ለእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም ከተቆጣጣሪዎች ሁሉ ይበልጥ ፈጣን ነው::"},{"id":63,"translation":"63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያ ከየብስና ከባህር ጨለማዎች በግልጽና በሚስጢር ‹ከዚህ ቢያድነን ከአመስጋኞች እንሆናለን› ስትሉ የምትጠሩት ስትሆኑ የሚያድናችሁ ማን ነው?» በላቸው።"},{"id":64,"translation":"64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ከእርሷና ከጭንቅም ሁሉ ያድናችኋል:: ከዚያ እናንተ በእሱ ባዕድ አምላክን ታጋራላችሁ።» በላቸው።"},{"id":65,"translation":"65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እርሱ (አላህ) ከበላያችሁ ወይም ከእግሮቻችሁ በታች ቅጣትን በእናንተ ላይ ሊልክ ወይም የተለያዩ ሕዝቦች ስትሆኑ ሊያደባልቃችሁና ከፊላችሁን የከፊሉን ጭካኔ ሊያቀምስ ቻይ ነው።» በላቸው። ይገነዘቡ ዘንድ አናቅጽን እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት።"},{"id":66,"translation":"66. እርሱ(ቁርኣን) ከአላህ የመጣ እውነት ሲሆን ህዝቦችህ ግን አስተባበሉት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም።» በላቸው::"},{"id":67,"translation":"67. ለየወሬ ሁሉ የሚደርስበት መፈጸሚያ ጊዜ አለው:: ወደ ፊትም በትክክል ታውቁታላችሁ::"},{"id":68,"translation":"68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ አናቅጻችንን ለማስተባበል ወደ ክርክር የሚገቡትን ሰዎች በምታይ ጊዜ በሌላ ወሬ እስከሚገቡ ድረስ ተዋቸው:: ሰይጣንም መከልከልህን ቢያስረሳህና አብረሀቸው ሆነህ እንኳን ካስታወስክ በኋላ ከበደለኞች ሕዝቦች ጋር አትቀመጥ::"},{"id":69,"translation":"69. እነዚያም በሚጠነቀቁት ህዝቦች ላይ በሂሳባቸው ምንም የለባቸዉም:: ግን ይጠነቀቁ ዘንድ መገሰጽ አለባቸው::"},{"id":70,"translation":"70. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም ሃይማኖታቸውን ጨዋታና ቀልድ አድርገው የያዙትንና ቅርቢቱ ሕይወት ያታለለቻቸውን ተዋቸው:: ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ እንዳትጠፋ በእርሱ (በቁርአን) አስታውስ:: ለእርሷ ከአላህ ሌላ ወዳጅም ሆነ አማላጅ ማንም የላትም:: ፊዳ የተባለን ሁሉ ብትከፍል እንኳን ተቀባይነት የላትም:: እነዚያ በሰሩት ስራ የተጠፉት ናቸው:: በክህደታቸው ምክንያት ከፈላ ውሃ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":71,"translation":"71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከአላህ ሌላ የማይጠቅምንና የማይጎዳን እንገዛለን? አላህ በቀናው መንገድ ከመራን በኋላ የኋሊት እንመለሳለን? እንደዚያ በምድር ላይ የዋለለ ሲሆን ሰይጣናት አሳስተውት ለእርሱ ‹ወደ እኛ ና› እያሉ ወደ ቅን መንገድ የሚጠሩ ወዳጆች ቢኖሩትም (እንደማይከተላቸው) እንሆናለንን?» በላቸው:: «የአላህ መንገድ ቀጥተኛው መንገድ ነው:: ለዓለማት ጌታ ልንገዛም ታዘዝን።» በላቸው::"},{"id":72,"translation":"72. «ሶላትን በትክክል ስገዱ አላህን ፍሩትም።» (ተብለን ታዘናል በላቸው።) እርሱ ወደ እርሱ የምትሰበሰቡበት አምላክ ነው።"},{"id":73,"translation":"73. እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በትክክል የፈጠረ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁን» የሚልበትንና ወዲያዉም የሚሆንበትን ቀን አስታውስ:: ቃሉም እውነት ነው:: በቀንዱ በሚነፋበት ቀንም ንግስናው የእርሱ ብቻ ነው:: ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ ነው:: እርሱም ጥበበኛውና ውስጠ አዋቂው ነው::"},{"id":74,"translation":"74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም ለአባቱ ለአዘር፡- «ጣኦትን አማልክት ታደርጋለህን? እኔ አንተንም ወገኖችህንም ግልጽ ጥመት ውስጥ ሆናችሁ አየኋችሁ።» ባለው ጊዜ የሆነውን አስታውስ::"},{"id":75,"translation":"75. ልክ በዚህ አኳኋን ኢብራሂም ጽኑ እምነት ይኖረው ዘንድ የሰማያትንና የምድርን ግዛት አሳየነው::"},{"id":76,"translation":"76. ሌሊቱ በጽልመቱ በሸፈነው ጊዜ አንድ ኮከብ አየ። «ይህ ጌታዬ ነው» አለም:: ኮከቡ በጠለቀ ጊዜም፡- «ጠላቂዎችን አልወድም» አለ::"},{"id":77,"translation":"77. ጨረቃውን ደምቆ ባየ ጊዜም፡- «ይህ ጌታዬ ነው።» አለ:: ጨረቃውም በጠለቀ ጊዜ፡- «ጌታዬ ቅኑን ጎዳና ካልመራኝ መንገድ ከተሳሳቱ ሰዎች እሆናለሁ።» አለ።"},{"id":78,"translation":"78. ጸሐይዋንም ደምቃ ጮራዋን ባየ ጊዜ፡- «ይህ ጌታዬ ነው። ይህ በጣም ትልቅ ነው።» አለ:: በጠለቀችም ጊዜ (አንዲህ) አለ፡- «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ከምታጋሩት ሁሉ የጠራሁ ነኝ።"},{"id":79,"translation":"79. «እኔ ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት የተዘነበልኩ ስሆን ፊቴን ሰማያትንና ምድርን ወደ ፈጠረው አምላክ አላህ አዙሬያለሁ:: እናም ከአጋሪዎችም አይደለሁም።» (አለ)።"},{"id":80,"translation":"80. ወገኖቹም ተከራከሩት። (እርሱም) አላቸው: «በእርግጥ የመራኝ ስሆን በአላህ ጉዳይ ትከራከሩኛላችሁን? በእርሱም የምታጋሩትን ነገር አልፈራም:: ግን ጌታዬ ቢሻ (ያገኘኛል):: ጌታዬም ሁሉንም ነገር በእውቀቱ ሰፋ። አትገነዘቡምን?"},{"id":81,"translation":"81. «በእናንተ ላይ በእርሱ ማስረጃ ያላወረደበትን እናንተ ማጋራታችሁን የማትፈሩ ስትሆኑ የምታጋሩትን ጣዖት እንዴት እኔ እፈራለሁ?! የምታውቁም ብትሆኑ ከሁለቱ ክፍሎች ደህና ለመሆን ይበልጥ ተገቢው ማንኛው ነው?» አለ።"},{"id":82,"translation":"82. እነዚያ በአላህ ያመኑና እምነታቸውን በእሱ በማጋራት ያልቀላቀሉ ሁሉ እነዚያ ለእነርሱ የተሟላ ደህንነት አለላቸው:: ወደ ቀናው መንገድ የተመሩም እነርሱው ናቸው::"},{"id":83,"translation":"83. እነዚህ ማስረጃዎቻችን ናቸው:: ለኢብራሂም በህዝቦቹ ላይ አስረጅ እንዲሆኑ ሰጠነው:: የምንፈልገውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ጥበበኛና አዋቂ ነውና::"},{"id":84,"translation":"84. ለእርሱም ልጁን ነብዩ ኢስሀቅንና የልጅ ልጁን ነብዩ የዕቆብን ሰጠነው:: ሁሉንም ወደ ቀናው መንገድ መራናቸው:: ኑህንም ከእነርሱ በፊት ወደ ቀናው መንገድ መራነው:: ከዘሮቹም ነብዩ ዳውድንም፤ ነብዩ ሱለይማንንም፤ ነብዩ አዩብንም፤ ነብዩ ዮሱፍንም፤ ነብዩ ሙሳንና፤ ነብዩ ሀሩንንም መራን:: በጎ ሰሪዎችን ሁሉ ልክ እንደዚሁ እንመነዳለን::"},{"id":85,"translation":"85. ዘከርያን፤ ያህያን፤ ዒሳን፤ ኢልያስንም ወደ ቀናው መንገድ መራን:: ሁሉም ከመልካሞቹ ናቸው::"},{"id":86,"translation":"86. ነብዩ ኢስማኢልንም፤ ነብዩ አል የሰዕንም፤ ነብዩ ዩኑስንም፤ ነብዩ ሉጥንም መራን:: ሁሉንም በዓለማት ላይ አበለጥናቸው::"},{"id":87,"translation":"87. ከአባቶቻቸዉም፣ ከዘሮቻቸዉም፣ ከወንድሞቻቸዉም ብዙዎችን መራን:: መረጥናቸዉም:: ወደ ቀጥታኛዉም መንገድ መራናቸው::"},{"id":88,"translation":"88. ይህ የአላህ መመሪያ ነው:: በእርሱ ከባሮቹ የሚሻውን ወደ ቀናው መንገድ ይመራበታል:: በአላህ ባጋሩም ኖሮ ይሰሩት የነበሩት መልካም ተግባር ሁሉ ከእነርሱ በታበሰባቸው ነበር::"},{"id":89,"translation":"89. እነዚህ እነዚያ መጽሐፍትንና ጥበብን ነብይነትንም የሰጠናቸው ሰዎች ናቸው:: እነዚህ የመካ ከሓዲያን በእርሷ ቢክዱም በእርሷ የማይክዱ ሕዝቦችን አዘጋጅተንላታል::"},{"id":90,"translation":"90. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ ነብያት እነዚያ አላህ የመራቸው ናቸው:: ስለሆነም ፈለጋቸውን ተከተል:: «በእርሱ (በቁርኣን) ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም:: እርሱ ለዓለማት ግሳጼ ሊሆን የወረደ እንጂ ሌላ አይደለም።» በላቸው::"},{"id":91,"translation":"91. (ከሓዲያን) «አላህ በሰው ላይ ምንም አላወረደም።» ባሉ ጊዜ አላህን ተገቢውን ክብሩን አላከበሩትም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዲህ በላቸው «ያንን ለሰዎች ብርሃንና ቅን መመሪያ ሆኖ ሙሳ ያመጣውን መጽሐፍ ክፍልፍሎች የምታደርጉት ስትሆኑ ማን አወረደው? (የወደዳችኋትን) ትገልጿታላችሁ ብዙውንም ትደብቃላችሁ፤ እናንተም ሆናችሁ አባቶቻችሁም ያላወቃችሁትን ተስተማራችሁ::» (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ አወረደው።» በላቸው:: ከዚያም በውሸታቸው ውስጥ የሚጫወቱ ሲሆኑ ተዋቸው::"},{"id":92,"translation":"92. ይህ ያወረድነው ብሩክና ያንንም በፊት የነበረውን (መጽሐፍ) አረጋጋጭ መጽሐፍ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የከተሞችንም እናት (መካን) ኗሪዎችን እና በዙሪያዋ ያሉትንም ሰዎች ልታስጠነቅቅበት አወረድነው:: እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የሚያምኑት ሰዎች እነርሱ በሶላታቸው የሚጠባበቁ ሲሆኑ በእርሱ ያምናሉ::"},{"id":93,"translation":"93. በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም ወደ እርሱ ምንም ያልተወረደለት ሲሆን «ወደ እኔ ተወረደልኝ።» ካለና «አላህ ያወረደውን አይነት ማውረድም በእርግጥ እችላለሁ።» ካለ ይበልጥ እራሱን በዳይ ማን ነው? በደለኞችን በሞት መከራዎች ውስጥ በሆኑ ጊዜ መላዕክት እጆቻቸውን ዘርጊዎች ሆነው (ለቅጥጥብ) «ነፍሶቻችሁን አውጡ:: ከአላህ ላይ እውነትን ያልሆነን ነገር ትናገሩም የነበራችሁና በአናቅጽም ላይ ትኮሩ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬ የውርደት ቅጣት ትመነዳላችሁ» በሚሏቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ባየህ ነበር)::"},{"id":94,"translation":"94. «በመጀመሪያ ጊዜ ልክ እንደፈጠርናችሁ ሆናችሁ የሰጠናችሁን ሁሉ ከጀርባዎቻችሁ ኋላ የተዋችሁ ስትሆኑ ለየብቻችሁ ሆናችሁ በእርግጥ ወደ እኛ መጣችሁ:: እነዚያንም እነርሱ በእናንተ (ጉዳይ) ለአላህ ተጋሪዎቹ ናቸው:: የምትሏቸውን አማላጆቻችሁን ከናንተ ጋር አናይም:: ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ:: ከናንተም ያ ያማልደናል የምትሉት ሁሉ ጠፋ» (ይባላሉ።)"},{"id":95,"translation":"95. አላህ የፍሬና የዛፍ ቅንጣትን ፈልቃቂ ነው:: ከሙት ነገር ሕያውን ያወጣል:: ከሕያዉም ነገር ሙትን አውጭ ነው:: ይህ አላህ ጌታችሁ ነው:: ታዲያ እንዴት ከእውነት ትሸሻላችሁ (ትርቃላችሁ)?"},{"id":96,"translation":"96. ጎሕን ከጽልመት ጨለማ ፈልቃቂ፤ ሌሊቱን ማረፊያ፤ ጸሐይንና ጨረቃን ለጊዜ ስሌት መጠቀሚያ ያደረገ አምላክ ነው:: ይህ የዚያ የአሸናፊውና የሁሉን አዋቂው አምላክ ውሳኔ ነው::"},{"id":97,"translation":"97. አላህ ያ በየብስና በባህር ጨለማዎች ውስጥ ራሳችሁን መምራት ትችሉ ዘንድ ከዋክብትን የፈጠረላችሁ አምላክ ነው:: ለሚያውቁ ሁሉ አናቅጽን በሚገባ አብራርተናል::"},{"id":98,"translation":"98. (ሰዎች ሆይ! ) እርሱ (አላህ) ያ ከአንዲት ነፍስ ያስገኛችሁ አምላክ ነው:: በማሕጸን ውስጥ ማረፊያንና ምድር ላይም መኖሪያን አመቻቸላችሁ:: መገንዘብ ለሚችሉ ሁሉ አናቅጽን በሚገባ አብራርተናል::"},{"id":99,"translation":"99. እርሱ (አላህ) ያ ከሰማይ ውሃን ያወረደ አምላክ ነው:: በእርሱም የሁሉንም ዓይነት እጽዋት አበቀልን:: የተደራረበን ቅንጣት የምናወጣበትን ለምለም አዝመራም ከርሱ አወጣን:: ከዘንባባ እንቡጥም የተቀራረቡ የሆኑ ዘለላዎችን አወጣን:: የወይን አትክልት ቦታዎችን አዘጋጀን:: ቅጠሎቻቸው የሚመሳሰሉ ፍሬዎቻቸው ግን የማይመሳሰሉ የሆኑትን የዘይቱን(ወይራ) እና የሩማን እጽዋትም ከሰማይ ባወረድነው ዝናብ አበቀልን:: (የሰው ልጆች ሆይ!) ፍሬውን ባፈራና በበሰለ ጊዜ እስቲ ተመልከቱት:: እጅግ አስደናቂ ሆኖ ታገኙታላችሁ:: በእነዚህ ክስተቶች ውስጥ በትክክል በአላህ ለሚያምኑ ሰዎች ሁሉ በርካታ ተአምራት አሉበት::"},{"id":100,"translation":"100. (ሰዎች) የፈጠራቸው አላህ ሲሆን አጋንንትን በመታዘዝ ለእርሱ ተጋሪዎች አደረጉ:: ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆች አለው በማለት ያለ ዕውቀት በእርሱ ላይ ቀጠፉ:: አላህ ጥራት የተገባውና ከሚሉት ነገር ሁሉ የላቀ ነው::"},{"id":101,"translation":"101. እርሱ ሰማያትንና ምድርን ያለ ብጤ ፈጣሪ ነው:: ለእርሱም ሚስት የሌለው ሲሆን እንዴት ለእርሱ ልጅ ይኖረዋል? ሁሉንም ነገር ፈጠረ:: እርሱ ሁሉንም ነገር አዋቂ ነውና::"},{"id":102,"translation":"102. ይህ ጌታችሁ አላህ ነው:: ከእርሱ በስተቀር አምላክ የለም:: ሁሉን ነገር ፈጣሪ ነው:: ስለዚህ እርሱን ብቻ ተገዙት:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነውና::"},{"id":103,"translation":"103. አይኖች አያገኙትም:: እርሱ ግን አይኖችን ያያል:: እርሱም ሩህሩህና ውስጠ አዋቂ ነው::"},{"id":104,"translation":"104. (ሰዎች ሆይ!) «ከጌታችሁ ዘንድ ብርሃኖች በእርግጥ መጡላችሁ:: እውነቱን የተመለከተ ሰው ጥቅሙ ለነፍሱ ብቻ ነው:: የታወረም ሰው ጉዳቱ በራሱ ላይ ብቻ ነው:: እኔ በእናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም።» በላቸው::"},{"id":105,"translation":"105. ልክ እንደዚሁ ገምግመው «መጽሐፍ አጥንተሃል» እንዲሉና ለሚያውቁ ህዝቦች ቁርኣንን እንድናብራራ አናቅጽን እንገልፃለን።"},{"id":106,"translation":"106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ብቻ ተከተል:: ከእርሱ በስተቀር ትክክለኛ አምላክ የለም:: አጋሪዎችንም ተዋቸው::"},{"id":107,"translation":"107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በፈለገ ኖሮ እነርሱ ጣኦትን ባላጋሩ ነበር:: በእነርሱም ላይ ጠባቂ አላደረግንህም:: አንተም በእነርሱ ላይ ኃላፊ አይደለህም::"},{"id":108,"translation":"108. (ሙስሊሞች ሆይ!) እነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚገዟቸውን ጣዖታትን አትስደቡ:: እነርሱም ድንበርን በማለፍ ያለ እውቀት አላህን ይሰድባሉና:: ልክ እንደዚሁ ለህዝቦች ሁሉ ስራቸውን ደግ አስመሰልንላቸው:: ከዚያም መመለሻቸው ወደ ጌታቸው ብቻ ነው:: ይሰሩት የነበሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል::"},{"id":109,"translation":"109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተዐምር ብትመጣላቸው በእርሷ በቁርጥ እንደሚያምኑ ጥብቅ መሀላዎቻቸውን በአላህ ማሉ:: «ተዓምራትም ሁሉ የሚከሰቱት ከአላህ ብቻ ነው። እርሷ በመጣች ጊዜም አለማመናቸውን ወይም ማመናቸውን ምን አሳወቃችሁ?» በላቸው::"},{"id":110,"translation":"110. በመጀመሪያም ጊዜ በእርሱ እንዳላመኑ ሁሉ ልቦቻቸውንና አይኖቻቸውን እናገላብጣለን:: በጥመታቸዉም ውስጥ የሚዋልሉ ሲሆኑ እንተዋቸዋለን::"},{"id":111,"translation":"111. እኛ ወደ እነርሱ መላዕክትን ባወረድንም ኖሮ ሙታንን ባነጋገሩዋቸውና ነገሩን ሁሉ በቡድን በቡድን በእነርሱ ላይ በሰበሰብንም ኖሮ አላህ ካልሻ በስተቀር የሚያምኑ ባልሆኑ ነበር:: ግን አብዛኞቻቸው ይህንን እውነታ ይስታሉ::"},{"id":112,"translation":"112. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንደዚሁም ለነብያት ሁሉ ከሰውና ከጋኔን የሆኑን ሰይጣናት ጠላት አደረግን:: ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ለማታለል የተዋበን ንግግር ይጥላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በፈለገ ኖሮ ይህን ጸያፍ ተግባር ባልሰሩት ነበር:: ከቅጥፈታቸዉም ጋር ተዋቸው::"},{"id":113,"translation":"113. ሊያታልሉ የሚጥሩትና የነዚያም በመጨረሻይቱ ህይወት የማያምኑት ሰዎች ልቦች ወደ እርሱ እንዲያዘነብሉ፤ እንዲወዱትና እነርሱ ይቀጥፉ የነበሩትንም እንዲቀጣጥፉ ነው::"},{"id":114,"translation":"114. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱ ያ መጽሐፍን የተብራራ ሆኖ ወደ እናንተ ያወረደ ሲሆን ከአላህ ሌላ ዳኛን እፈልጋለሁን? በላቸው:: እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ሰዎች ቁርኣን ከጌታህ ዘንድ በእውነት የተወረደ መሆኑን በትክክል ያውቃሉ:: እናም ከተጠራጣሪዎቹ አትሁን::"},{"id":115,"translation":"115. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ ቃላት እውነተኛና ትክክለኛ ስትሆን ተፈጸመች:: ለቃላቱ ምንጊዜም ለዋጭ የለም:: እርሱ ሰሚውና አዋቂው ነው።"},{"id":116,"translation":"116. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በምድር ካሉት መካከል አብዛኞቹን ብትከተል የአላህን መንገድ ያሳስቱሀል:: ጥርጣሬን እንጂ ሌላን አይከተሉምና:: እነርሱም የሚዋሹ እንጂ ሌላ አይደሉም::"},{"id":117,"translation":"117. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ከመንገዱ የሚሳሳቱትን አዋቂ ነው:: እርሱም ተመሪዎቹን እንዲሁ አዋቂ ነው::"},{"id":118,"translation":"118. (ሰዎች ሆይ!) በአናቅጹም አማኞች እንደሆናችሁ ሲታረድ የአላህ ስም በእርሱ ላይ የተወሳበትን እንሰሳ ብቻ ብሉ::"},{"id":119,"translation":"119. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱን መብላት ካልተገደዳችሁበት በስተቀር በእናንተ እርም የተደረገውን ለእናተ አላህ በእርግጥ የዘረዘረ ሲሆን ከዚያ በእርሱ ላይ የአላህ ስም ከተጠራበት የማትበሉት ምን ምክንያት አላችሁ? ብዙዎቹም ያለ እውቀት በዝንባሌዎቻቸው ብቻ ያሳስታሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ወሰን አላፊዎቹን አዋቂ ነውና::"},{"id":120,"translation":"120. የኃጢአትን ግልጹንም ድብቁንም ተው:: እነዚያ ኃጢአትን የሚሰሩ ሁሉ ይሰሩት በነበሩበት ነገር በእያንዳንዱ በእርግጥ ይመነዳሉ።"},{"id":121,"translation":"121. (ሙስሊሞች ሆይ!) በእርሱ ላይ የአላህ ስም ያልተወሳበትን አትብሉ:: እርሱም በእርግጥ አመጽ ነው:: ሰይጣናትም ወደ ወዳጆቻቸው በክትን በመብላት ይከራከሯችሁ ዘንድ ያሾከሹካሉ:: ታዲያ ብትታዘዟቸው በእርግጥ አጋሪዎች ናችሁ::"},{"id":122,"translation":"122. ሙት የነበረና ከዚያም ህያው አድርገነው ለርሱም በሰዎች መካከል የሚሄድበትን ብርሃን ያደረግንለት በጨለማዎች ውስጥ ምንጊዜም የማይወጣ ሆኖ እንዳለው ብጤ ነውን? ልክ እንደዚሁ ለከሓዲያን ሁሉ ይሰሩት የነበሩት ነገር ተዋበላቸው::"},{"id":123,"translation":"123. ልክ እንደዚሁ በየከተማይቱ ውስጥ ታላላቅ ወንጀለኞቿ በውስጧ እንዲያሴሩ አደረግን። በነፍሶቻቸው ላይ እንጂ በሌላ ላይ አያሴሩም:: ግን ይህን እውነታ አያውቁም።"},{"id":124,"translation":"124. ተዓምር በመጣላቸውም ጊዜ «የአላህ መልዕክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ:: አላህ መልዕክቱን የሚያደርግበትን ስፍራ አዋቂ ነው:: እነዚያን በአላህ ያመጹ ሰዎች ይዶልቱት በነበሩት ነገር አላህ ዘንድ ውርደትና ብርቱ ቅጣት ያገኛቸዋል::"},{"id":125,"translation":"125. አላህ ሊመራው የሚሻውን ሁሉ ልቡን ለኢስላም ይከፍትለታል:: ሊያጠመው የሚሻውን ደግሞ ልቡን ጠባብና ተቸጋሪ ወደ ሰማይ ለመውጣት እንደሚታገል ያደርገዋል:: ልክ እንደዚሁ አላህ በእነዚያ በማያምኑት ሰዎች ላይ ርክሰትን ያደርጋል::"},{"id":126,"translation":"126. ይህ ያለህበት መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን የጌታህ መንገድ ነው:: ለሚያስታውሱ ህዝቦች አናቅጽን እርግጥ ዘርዝረናል::"},{"id":127,"translation":"127. ለእነርሱም በጌታቸው ዘንድ የሰላም ሀገር አለላቸው። እርሱ ይሰሩት በነበሩት ምክንያትም ረዳታቸው ነው::"},{"id":128,"translation":"128. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሁሉንም በአንድ ቦታ በሚሰበስባቸው ቀን የሚሆነውን አስታውስ:: «የአጋንንት ቡድኖች ሆይ! ከሰዎች ቡድንን በማጥመም በእርግጥ አበዛችሁ።» ይባላሉ:: ከሰዎችም መካከል የሆኑት ወዳጆቻቸው «ጌታችን ሆይ! ከፊላችን በከፊሉ ተጠቀመ:: ያንን ለእኛ የወሰንክልንን ጊዜያችንን ደረስን።» ይላሉ:: «እሳቲቱ አላህ የሻው ጊዜ ሲቀር በውስጧ ዘወታሪዎች ስትሆኑ መኖሪያችሁ ናት።» ይላቸዋል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ጥበበኛና አዋቂ ነው::"},{"id":129,"translation":"129. ልክ እንደዚሁ አንዳንድ በደለኞችን ይሰሩት በነበሩት ጥፋት ምክንያት በከፊሎች ላይ እንሾማለን::"},{"id":130,"translation":"130. «የአጋንትና የሰዎች ቡድኖች ሆይ! አንቀፆቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን ቅጣት ማግኘትን የሚያስፈራሯችሁ ከናንተው የሆኑ መልዕክተኞች አልመጡላችሁም ነበርን?» ይባላሉ:: «በነፍሶቻችን ላይ መሰከርን።» ይላሉ። የዱንያ ህይወት አታለለቻቸው። በነፍሶቻቸው ላይ እነርሱ ከሓዲያን የነበሩ መሆናቸውንም በራሳቸው መሰከሩ።"},{"id":131,"translation":"131. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ የሆነው ጌታህ ከተሞችን ባለቤቶችዋ (ማስጠንቀቂያ ያልመጣላቸው) ዘንጊዎች ሆነው ሳሉ በበደል ምክንያት አጥፊ ባለመሆኑ ነው።"},{"id":132,"translation":"132. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለሁሉም ከሰሩት (አንፃር) የተበላለጡ ደረጃዎች አሏቸው:: ጌታህም ከሚሰሩት ስራ ዝንጉ አይደለም::"},{"id":133,"translation":"133. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም በራሱ ተብቃቂ የእዝነት ባለቤት ነው:: ቢሻ ከምድረ ገጽ ያጠፋችኋል:: ከሌሎች ህዝቦችም ዘሮች እንዳስገኛችሁ ሁሉ ከበኋላችሁም የሚሻውን ሰው ይተካል::"},{"id":134,"translation":"134. (ሰዎች ሆይ!) የምትቀጠሩት ሁሉ በእርግጥ መጪ ነው:: እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም::"},{"id":135,"translation":"135. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ህዝቦቼ ሆይ! በችሎታችሁ ላይ ስሩ እኔ በችሎታዬ ላይ ሰሪ ነኝና:: ምስጉኒቱ ሀገር ገነት ለእርሱ የምትሆንለት ሰው ማን እንደሆነ ወደፊት ታውቃላችሁ:: እነሆ በደለኞች ሁሉ ምንጊዜም አይድኑም።» በላቸው::"},{"id":136,"translation":"136. አጋሪዎች ለአላህ ከፈጠራቸው ፍጡራን ከአዝመራውም ከግመል፣ ከከብት፣ ከፍየል፤ ከበጉም ድርሻን አደረጉለት:: በሀሳባቸዉም «ይህ የአላህ ነው፤ ይህ ደግሞ ለተጋሪዎቻችን ነው።» አሉ። ለተጋሪዎቻቸው የሆነው ነገር ወደ አላህ ምንጊዜም አይደርስም:: ለአላህ የሆነው ነገር ግን ወደ ተጋሪዎቹ ይደርሳል አሉ። የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ!"},{"id":137,"translation":"137. ልክ እንደዚሁ ከአጋሪዎች ለብዙዎቹ ሊያጠፏቸውና ሀይማኖታቸውንም በነሱ ላይ ሊያቀላቅሉባቸው ዘንድ ልጆቻቸውን መግደልን ተጋሪዎቻቸው ጣኦታቱ አሳመሩላቸው:: አላህም በሻ ኖሮ (ይህን ጸያፍ ተግባር) ባልሰሩት ነበር:: እናም ከቅጥፈታቸው ጋር ተዋቸው::"},{"id":138,"translation":"138. በሀሳባቸውም «እነዚህ እርም የሆኑ ለማዳ እንሰሳና አዝመራ ናቸው:: የምንሻለት ሰው እንጂ ሌላ ማንም አይበላቸዉም:: እነዚህ ደግሞ ጀርባዎቻቸው እርም የተደረገ ለማዳ እንሰሳ ናቸው:: አይጫኑም:: እነዚህ ሲታረዱ በእነርሱ ላይ የአላህን ስም የማይጠሩባቸዉም እንሳሳት ናቸው።» አሉ:: በእርሱ ላይ ለመቅጠፍ ነገሩን ወደ አላህ አስጠጉ:: ይቀጥፉት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይቀጣቸዋል::"},{"id":139,"translation":"139. «በእነዚህ እንስሳት ሆዶች ውስጥ ያለው ጽንሱ ሁሉ ለወንዶቻችን ብቻ በተለይ የተፈቀደ ነው:: በሚስቶቻችን ላይ ግን እርም የተደረገ ነው:: ሙት ሆኖ ቢወለድ ግን ወንዶቹም ሆነ ሴቶች በእርሱ ላይ ተጋሪዎች ናቸው።» አሉ:: ይህን በመቅጠፋቸው አላህ በእርግጥ ይቀጣቸዋል:: እርሱ ጥበበኛና አዋቂ ነውና::"},{"id":140,"translation":"140. እነዚያ ያለ እውቀት በሞኝነት ልጆቻቸውን የገደሉና አላህም የሰጣቸውን ሲሳይ በአላህ ላይ በመቅጠፍ በራሳቸው ላይ እርም ያደረጉ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ ከሰሩ:: ተሳሳቱም:: ወደ ትክክለኛው መንገድም የተመሩ አልነበሩም::"},{"id":141,"translation":"141. አላህ ያ (በሀረጉ) ዳስ የሚያደርግላቸውንና ዳስ የማያደርግላቸውን አትክልቶች የፈጠረ ነው:: የተምርን ዛፍ፣ አዝመራን፣ ፍሬዎቹ የተለያዩ ሲሆኑ ወይራንና ሩማንንም ቅጠላቸው ተመሳሳይና ጣዕማቸው የማይመሳሰል ሲሆኑ ፈጠረ:: (ሰዎች ሆይ!) ባፈራ ጊዜም ከፍሬው ብሉ:: ባጨዳዉም ቀን ተገቢውን (ዘካ) ለተገቢው ስጡለት:: አታባክኑም:: አላህ አባካኞችን አይወድምና::"},{"id":142,"translation":"142. ከለማዳ እንሰሳዎችም የሚጫኑትንም የማይጫኑትንም ፈጠረ:: (ሰዎች ሆይ!) አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ብሉ:: የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ:: እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና::"},{"id":143,"translation":"143. ስምንትን ዓይነቶች፤ ከበግ ሁለትን (ወንድና ሴትን) ከፍየልም ሁለትን ፈጠረ:: «ከሁለቱም ክፍሎች አላህ ወንዶችን ብቻ እርም አደረገን? ወይንስ ሴቶችን ብቻ? ወይስ በእርሱ ላይ የሁለቱ ሴቶች ማህጸኖች ያጠቃለሉትን እርም አደረገ? እውነተኞች እንደሆናችሁ በእውቀት (በአስረጂ) ንገሩኝ» በላቸው::"},{"id":144,"translation":"144. ከግመል ሁለትን፤ ከከብት ሁለትን ፈጠረ። «አላህ ከሁለቱ ወንዶችን ብቻ እርም አደረገን? ወይንስ ሴቶችን ብቻ? ወይስ የሁለቱ ሴቶች ማህጸኖች ያጠቃለሉትን? በእውነቱ አላህ በዚህ ነገር ባዘዛችሁ ጊዜ በቦታው ነበራችሁን? ሰዎችን ያለ እውቀት ሊያጠም በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጠፈ ሰው ይበልጥ በደለኛ ማን ነው? አላህ በደለኞችን ህዝቦች ቅኑን መንገድ አይመራም::» በላቸው።"},{"id":145,"translation":"145. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ወደ እኔ በተወረደው ቁርኣን ውስጥ በክት ወይም የፈሰሰ ደም፤ ወይም የአሳማ ስጋ እርሱ እርኩስ ነውና፤ ወይም በአመጽ ከአላህ ስም ሌላ በእርሱ ላይ የተወሳበት ካልሆነ በስተቀር ተመጋቢ ላይ እርም የሆነ ነገር አላገኝም። አመጸኛና ወሰን ያለፈ ሳይሆን የተገደደ ሰው ከተወሱት ነገሮች ነፍስን የማዳን ያህል ቢበላ ኃጢአት የለበትም:: ጌታህ መሀሪና አዛኝ ነውና።» በላቸው።"},{"id":146,"translation":"146. በአይሁዳውያን ላይ የጥፍር ባለቤት እንስሳትን ሁሉ እርም አደረግንባቸው:: ከከብት፤ ከፍየልና ከበግ ሞራዎቻቸውን፤ ጀርባዎቻቸው ወይም አንጀቶቻቸው የተሸከሙት ወይም በአጥንት የተቀላቀሉ ስብ ሲቀር በእነርሱ ላይ እርም አደረግን:: በአመፃቸው ምክንያት ይህን በማድረግ ቀጣናቸው:: እኛም እውነተኞች ነን::"},{"id":147,"translation":"147. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉልህ፡- «ጌታችሁ የሰፊ ችሮታ ባለቤት ነው:: ብርቱ ቅጣቱም ከአመጸኞች ህዝቦች ላይ አይመለስም።» በላቸው።"},{"id":148,"translation":"148. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያ በአላህ ያጋሩት ሰዎች አላህ በሻ ኖሮ እኛም ሆነ አባቶቻችን በአላህ ባላጋራንና አንዳችንም ነገር እርም ባላደረግን ነበር።» ይላሉ:: ልክ እነዚህ እንደ አስተባበሉህ ሁሉ እነዚያ ከበፊታቸው የነበሩ ሕዝቦችም ብርቱ ቅጣታችንን እስከ ቀመሱ ድረስ አስተባበሉ:: «ለእኛ ታስተምሩን ዘንድ ማጋራታችሁን ለመውደዱ እናንተ ዘንድ እውቀት አለን? ጥርጣሬን እንጂ ሌላ አትከተሉም:: እናንተ ዋሾዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።» በላቸው።"},{"id":149,"translation":"149. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የተሟላው ማስረጃ የአላህ ማስረጃ ብቻ ነው:: በፈለገ ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር።» በላቸው።"},{"id":150,"translation":"150. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያ አላህ ይህንን እርም ማድረጉን የሚመሰክሩትን ምስክሮቻችሁን እስቲ አምጡ።» በላቸው:: ቢመሰክሩም ከእነርሱ ጋር አትመስክር:: የእነዚያን በአናቅጻችን ያስተባበሉትን፤ የእነዚያንም በጌታቸው ሌላን የሚያስተካክሉ ሲሆኑ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑትን ሰዎች ዝንባሌዎች አትከተል::"},{"id":151,"translation":"151. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸውም: «ኑ ጌታችሁ በእናተ ላይ እርም ያደረገውን ነገርና (በእርሱም ያዘዛችሁን) ላንብብላችሁ። እርሱም በአላህ ምንንም ነገር አታጋሩ:: ለወላጆቻችሁም በጎ ስራን ስሩ:: ልጆቻችሁንም ድህነትን ፈርታችሁ አትግደሉ:: እኛ እናንተንም ሆነ እነርሱን እንመግባችኋለንና:: ወደ ግልፅም ይሁን ድብቅ መጥፎ ስራ አትቅረቡ:: ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በሀቅ ቢሆን እንጂ አትግደሉ:: ይሀችሁ! ታውቁ ዘንድ በእርሱ አዘዛችሁ።"},{"id":152,"translation":"152. «የየቲምንም ገንዘብ አካለ መጠን እስኪድረስ ድረስ በመልካም ሁኔታ እንጂ አትቅረቡ:: ስፍርንና ሚዛንንም በትክከል ሙሉ:: ማንኛዋም ነፍስ የችሎታዋን ያህል እንጂ አናስገድድም:: በተናገራችሁ ጊዜ በዘመዶቻችሁ ላይ ቢሆንም እንኳ እውነትን በመናገር አስተካክሉ:: በአላህ ቃል ኪዳን ሙሉ:: ይሀችሁ ትገሰጹ ዘንድ አላህ በእርሱ አዘዛችሁ።"},{"id":153,"translation":"153. «ይህ ቀጥተኛው መንገዴ ነው:: እናም እርሱን ብቻ ተከተሉ:: የተለያዩ የጥመት መንገዶችንም አትከተሉ:: ከቀጥተኛው የርሱ መንገድ እናንተን ይለያይዋችኋልና:: ይሀችሁ ትጠነቀቁ ዘንድ አላህ በእርሱ አዘዛችሁ።»"},{"id":154,"translation":"154. ከዚያ ለሙሳ መፅሀፍ ሰጠነው መልካም በሰራው ላይ ጸጋችንን ለማሟላት፤ ነገርንም ሁሉ ለመዘርዘር፤ ለህዝቦቹም መሪና እዝነት ይሆን ዘንድ:: እነርሱ ከጌታቸው በመገናኘት ጉዳይ ሊያምኑ ይከጀላልና::"},{"id":155,"translation":"155. ይህ ያወረድነው የሆነ የተባረከ መጽሐፍ ነው:: እናም ተከተሉት፤ ይታዘንላችሁም ዘንድ ከክህደት ተጠንቀቁ።"},{"id":156,"translation":"156. (ያወረድነውም) «መጽሐፍ የተወረደው ከፊታችን በነበሩ ሁለቱ ህዝቦች ላይ ብቻ ነው:: እኛም ከንባባቸው ዘንጊዎች ነበርን» እንዳትሉም ነው።"},{"id":157,"translation":"157. ወይም «እኛ መጽሐፍ በእኛ ላይ በተወረደ ኖሮ ከእነርሱ ይበልጥ የተመራን እንሆን ነበር።» እንዳትሉም ነው:: ስለዚህም ከጌታችሁ ግልጽ ማስረጃ፤ መመሪያ እና እዝነት በእርግጥ መጣላችሁ:: በአላህ አናቅጽ ካስተባበለና ከእርሱም ከዞረ ሰው ይበልጥ ራሱን በዳይ ማን ነው? እነዚያን አናቅጽን የሚተውትን ይተውት በነበሩት አንቀጽ ምክንያት ብርቱ ቅጣት በእርግጥ እንቀጣቸዋለን::"},{"id":158,"translation":"158. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን መላዕክት ልትመጣላቸው ወይንም ጌታህ ሊመጣ ወይም ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ ሊመጣ እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ የሚመጣበት ቀን ግን ከዚያ በፊት አማኝ ያልነበረች ነፍስ ሁሉ ወይም አምና በእምነቷ በጎ ያልሰራች ነፍስ ሁሉ እምነቷ (ጸጸቷ) አይጠቅማትም:: «ያን ቀን እናንተም ተጠባበቁ እኛም ተጠባባቂዎች ነን።» በላቸው::"},{"id":159,"translation":"159. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነዚያ ሃይማኖታቸውን ከለያዩና ቡድን ቡድን ከሆኑ (ሰዎች) ጋር አይደለህም:: ነገራቸው ወደ አላህ ብቻ ነው:: ከዚያም ይሰሩት የነበሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል::"},{"id":160,"translation":"160. መልካምን ስራ የሰራ ሁሉ ለእርሱ አስር እጥፍ ምንዳ አሉት:: ክፉ ስራን የሰራ ግን መሰሏን ብቻ እንጂ አይመነዳም:: እነርሱም ቅንጣት አይበደሉም::"},{"id":161,"translation":"161. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ጌታዬ ወደ ቀጥተኛው መንገድ፤ የተስተካከለ ወደሆነው ሃይማኖት የኢብራሂም መንገድ መራኝ:: እሱም ከአጋሪዎች አልነበረም።» በል።"},{"id":162,"translation":"162.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው: «ስግደቴ፤ መገዛቴ (መስዋዕቴ)፣ ሕይወቴ፤ ሞቴ የሚገባው ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ነው።"},{"id":163,"translation":"163. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለእርሱ (ለአላህ) አጋር የለዉም:: በዚህ (አላህን ከተጋሪ በማጥራት) ታዘዝኩ:: እኔ የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ።» በል።"},{"id":164,"translation":"164. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ የሁሉ ጌታ ሲሆን ከአላህ በስተቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? ነፍስ ሁሉ በራሷ ላይ እንጂ ክፉን አትሰራም:: ወንጀለኛ ነፍስ ሁሉ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢአት አትሸከምም:: ከዚያ መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ነው:: ከዚያም ትለያዩበት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል» በላቸው።"},{"id":165,"translation":"165. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ (አላህ) ያ በምድር ላይ ምትኮች ያደረጋችሁ በሰጣችሁም ጸጋ ሊፈትናችሁ ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በደረጃዎች ከፍ ያደረገ ሃያል ጌታ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ቅጣቱ ፈጣን ነው:: አላህ እጅግ መሀሪና ሩህሩህ ነው::"}]},{"id":7,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚም፤ ሷድ::"},{"id":2,"translation":"2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ልታስጠነቅቅበትና ለምእመናንም መገሰጫ እንዲሆን ወደ አንተ የተወረደ ቁርኣን ነው:: ስለዚህ ልብህ ውስጥ ከእርሱ ጭንቀት አይኑር::"},{"id":3,"translation":"3. (ሰዎች ሆይ! ) ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደላችሁን መልዕክት ተከተሉ:: ከአላህ ሌላ ረዳቶችን አትከተሉ:: ጥቂትን ብቻ ትገሰፃላችሁ::"},{"id":4,"translation":"4. ከከተማ (ሰዎች) መካከል ልናጠፋቸው የፈለግነውንና ወዲያውኑ ብርቱ ቅጣታችን ሌሊት ወይም ቀን እነርሱ በቀትር አርፈው ሳሉ የመጣባቸው ብዙ ህዝቦች ናቸው::"},{"id":5,"translation":"5. ቅጣታችንም በመጣባቸው ጊዜ ጸሎታቸው «እኛ በደለኞች ነበርን።» ከማለት በስተቀር ሌላ አልነበረም::"},{"id":6,"translation":"6. ከዚያ ወደ እነርሱ የተላከባቸውን ህዝቦችና መልዕክተኞቹንም እንጠይቃቸዋለን::"},{"id":7,"translation":"7. ከዚያም በእነርሱ ላይ የነበሩትን ሁሉ ከእውቀት ጋር እንተርክላቸዋለን:: ከእነርሱ የራቅን አልነበርንምና::"},{"id":8,"translation":"8. የዚያን ቀኑ ሚዛን ትክክለኛ ነው:: እናም እነዚያ ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸውም እነዚያ እነርሱ የፈለጉትን ያገኙ እነርሱ ብቻ ናቸው::"},{"id":9,"translation":"9. እነዚያ ሚዛኖቻቸው የቀለሉባቸውም በአናቅጻችን ይክዱ በነበሩት ምክንያት ነፍሶቻቸውን ያከሰሩት ናቸው።"},{"id":10,"translation":"10. (ሰዎች ሆይ! ) በምድር ላይ በእርግጥም አስመቸናችሁ:: በእርሷም ላይ ለእናንተ መኖሪያዎችን አደረግንላችሁ። ጥቂትን ብቻ ታመሰግናላችሁ።"},{"id":11,"translation":"11. በእርግጥም ፈጠርናችሁ:: ከዚያም ቀረጽናችሁ:: ከዚያም ለመላዕክት « ለአደም ስገዱ።» አልን:: ወዲያዉም ሁሉም ሰገዱ:: ኢብሊስ ብቻ ሲቀር:: እሱማ ከሰጋጆቹ አልሆነም::"},{"id":12,"translation":"12. አላህም «ዲያብሎስ ሆይ! ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ?» አለው:: ዲያብሎስም «እኔ ከእርሱ የበለጥኩ ነኝ:: እኔን ከእሳት ፈጠርከኝ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው።» አለ።"},{"id":13,"translation":"13. (አላህም) «ከእርሷ ውረድ:: በእርሷ ውስጥ ልትኮራ አይገባህምና:: ውጣም:: አንተ ከወራዶቹ ነህና።» አለው::"},{"id":14,"translation":"14. (ኢብሊስም): «እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ።» አለ::"},{"id":15,"translation":"15. አላህ «አንተ ከሚቆዩት ነህ።» አለው።"},{"id":16,"translation":"16. (ኢብሊስም) አለ: «ስላጠመምከኝም ለእነርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ በእርግጥ እቀመጥባቸዋለሁ።"},{"id":17,"translation":"17. «ከዚያም ከበስተፊቶቻቸው፤ ከየኋላቸዉም፤ ከየቀኞቻቸውና ከየግራዎቻቸዉም በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ:: አብዛኞቻቸውንም አመስጋኞች ሆነው አታገኛቸዉም።» አለ።"},{"id":18,"translation":"18. «የተጠላህ ብራሪ ስትሆን ከእርሷ ውጣ:: ከእነርሱ መካከልም አንተን ከተከተሉህ እና አንተንም ሁላችሁንም ገሀነምን በእርግጥ በእናንተ እሞላታለሁ።» አለው።"},{"id":19,"translation":"19. ‹‹አደም ሆይ! አንተና ሚስትህ በገነት ውስጥ ተቀመጡ:: በእርሷም ዉስጥ እንደፈለጋችሁ ተመገቡ:: ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ:: ራሳቸውን ከሚበድሉት ትሆናላችሁና።» አላቸው።"},{"id":20,"translation":"20. ሰይጣንም ከሀፍረተ ገላቸው የተሸሸገውን ሊገልጽባቸው በድብቅ ንግግር ጎተጎታቸው። «ጌታችሁ እኮ መልአኮች እንዳትሆኑ ወይም ከዘላለም ኗዋሪዎቹ እንዳትሆኑ እንጂ ከዚህች ዛፍ አልከለከላችሁም።» አላቸው።"},{"id":21,"translation":"21. «እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሯችሁ ነኝ።» ሲልም ማለላቸው።"},{"id":22,"translation":"22. በማታለልም አዋረዳቸው:: ከዛፊቱም በቀመሱ ጊዜ ሀፍረተ ገላቸው የሁለቱም ተገለጠባቸው:: ከገነት ቅጠልም በላያቸው ላይ ይደርቱ (ይለጥፉ) ጀመር:: ጌታቸዉም «ይህችን ዛፍ አልከለከልኳችሁም ነበርን? ሰይጣንም ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነው አላልኳችሁም ነበርን?» ሲል ጠራቸው።"},{"id":23,"translation":"23. «ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በደልን:: ባትምረንና ባታዝንልን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንሆናለን።» አሉ።"},{"id":24,"translation":"24. (አላህም) «ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲሆን ከዚህ ዉጡ ወደ ምድር ውረዱ:: ለእናንተም በምድር ላይ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ።» አላቸው።"},{"id":25,"translation":"25. «በእርሷ ላይ ትኖራላችሁ:: በእርሷም ላይ ትሞታላችሁ:: ከእርሷም ውስጥ ትወጣላችሁ።» አላቸው።"},{"id":26,"translation":"26. የአደም ልጆች ሆይ! ሀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስና ጌጥን በእርግጥ በእናንተ ላይ አወረድን:: አላህን የመፍራትም ልብስም እርሱ የተሻለ ነው:: ይህ ከአላህ ተዓምራት ነው:: ይገሰጹ ዘንድ አወረደላቸው::"},{"id":27,"translation":"27. የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣን አባታችሁንና እናታችሁን ሀፍረተ ገላቸውን ሊያሳያቸው ልብሶቻቸውን ከእነርሱ የገፈፋቸው ሲሆን ከገነት እንዳወጣቸው ሁሉ እናንተንም አይሞክራችሁ:: እነሆ እርሱ ከነሰራዊቱ ከማታዩዋቸው ስፍራ ሁነው ያያቹሀልና: እኛ ሰይጣናትን ለእነዚያ ለማያምኑት ወዳጆች አድርገናል::"},{"id":28,"translation":"28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መጥፎንም ሥራ በሠሩ ጊዜ፡- «በእርሷ ላይ አባቶቻችንን አገኘን:: አላህም በእርሷ አዞናል።» ይላሉ። «አላህ በመጥፎ ነገር አያዝም፤ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን?» በላቸው።"},{"id":29,"translation":"29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ በማስተካከል በፍትህ አዘዘ:: በየመስገጃ ቦታ ዘንድም ፊቶቻችሁን እርሱን ለመገዛት አስተካክሉ:: ሃይማኖትንም ለእርሱ ብቻ ፍጹም አድርጋችሁ አምልኩት:: መጀመሪያ እርሱ እንደፈጠራችሁ በመጨረሻም ወደ እርሱ ትመለሳላችሁና።» በላቸው።"},{"id":30,"translation":"30. ከፊሉን ወደ ቅን መንገድ መራ:: ከፊሎቹ ደግሞ በእነርሱ ላይ ጥመት ተረጋግጦባቸዋል:: እነርሱ ሰይጣናትን ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋልና:: እነርሱም ቅኑን መንገድ የተመሩ እንደሆኑ ያስባሉ::"},{"id":31,"translation":"31. የአደም ልጆች ሆይ! ሀፍረተ ገላችሁን የሚሸፍኑትን ጌጦቻችሁን በየመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ:: ብሉም ጠጡም:: ግን አታባክኑ:: እርሱ (አላህ) አባካኞችን አይወድምና::"},{"id":32,"translation":"32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያችን ለባሮች የፈጠራትን የአላህን ጌጥ ከሲሳይ ጥሩዎቹን እርም ያደረገ ማን ነው?» በላቸው። «እርሷ በትንሳኤ ቀን ለነዚያ በትክክል ላመኑት ብቻ ስትሆን በቅርቢቱ ህይወትም ተገቢያቸው ናት።» በላቸው:: ልክ እንደዚሁ ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን እናብራራለን::"},{"id":33,"translation":"33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ እርም ያደረገው የተገለጸም ሆነ የተደበቀን መጥፎ ስራን፣ ኃጢአትን፤ ያለ አግባብ መበደልንም፣ በእርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን ጣኦት በአላህ ማጋራታችሁንና በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው።» በላቸው።"},{"id":34,"translation":"34. ለህዝቦች ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸው። እናም ጊዜያቸው በደረሰ ወቅት አንዲትንም ሰዓት አይዘገዩም። ከጊዜያቱም አይቀድሙም::"},{"id":35,"translation":"35. (የአደም ልጆች ሆይ!) ከናንተ መካከል አንቀፆቼን የሚያነቡላችሁ መልዕክተኞች ቢመጡላችሁ ከናንተ ክህደትን የተጠነቀቁና በጎንም ተግባር የሠሩ ሁሉ ምንም ፍርሀት የለባቸዉም:: ምንም አያዝኑምም::"},{"id":36,"translation":"36. እነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉና ከእርሷ የኮሩ ሁሉ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::"},{"id":37,"translation":"37. በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጠፈ ወይም በአናቅጹ ካስተባበለ ይበልጥ በዳይ ማን ነው? እነዚያ ከተጻፈላቸው ከመጽሐፉ ውስጥ ሲሆን ድርሻቸው ያገኛቸዋል:: የሞት መልዕክተኞቻችንም የሚገድሏቸው ሆነው በመጡባቸው ጊዜ «ከአላህ ሌላ ትገዟቸው የነበራችሁት የት አሉ?» ይሏቸዋል:: «ከእኛ ተሰወሩብን» ይላሉ:: እነርሱም ከሓዲያን እንደነበሩ በነፍሶቻቸው ላይ ይመሰክራሉ::"},{"id":38,"translation":"38. «ከጋኔንና ከሰዉም ከናንተ በፊት በእርግጥ ካለፉት ህዝቦች ጋር ሆናችሁ እሳት ውስጥ ግቡ።» ይላቸዋል:: አንዲቱ ቡድን ህዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር ያሳሳተቻትን ብጤዋን ቡድን ትረግማለች:: መላዉም በውስጧ ተሰብስበው በተገናኙ ጊዜ የኋለኛይቱ (ተከታዮች) ቡድን ለመጀመሪያይቱ (ለአስከታዮች) ቡድን፡- «ጌታችን ሆይ! እነዚህ አሳሳቱን ከእሳትም ስቃይ እጥፍን ስጣቸው።» ትላለች:: አላህም፡- «ለሁሉም እጥፍ አለው ግን አታውቁም።» ይላቸዋል።"},{"id":39,"translation":"39. መጀመሪያይቱ ቡድንም ለኋለኛይቱ ቡድን «ለእናንተ በእኛ ላይ ምንም ብልጫ አልነበራችሁም ትላለች:: ትሠሩትም በነበራችሁት ቅጣቱን ቅመሱ።» ይሏቸዋል።"},{"id":40,"translation":"40. እነዚያ አናቅጻችንን ያስተባበሉና ከእርሷም የኮሩ ሁሉ ለእነርሱ የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸዉም:: ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባ ድረስም ወደ ገነት አይገቡም:: ልክ እንደዚሁ አመጸኞችን እንቀጣለን::"},{"id":41,"translation":"41. ለእነርሱም በሥራቸው ምክንያት ከገሀነም እሳት ምንጣፍ ከበላያቸዉም የእሳት መሸፈኛዎች አሉባቸው:: ልክ እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን::"},{"id":42,"translation":"42. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካሞችን የሰሩ ማንኛውንም ነፍስ የችሎታዋን እንጂ አናስገድድም:: እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::"},{"id":43,"translation":"43. በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ጥላቻም እናስወግዳለን:: ወንዞች በሥሮቻቸው ይፈሳሉ:: «ለዚያም ወደዚህ ላደረሰን ሥራ ለመራን ለአላህ ብቻ ምስጋና ይገባው:: አላህ ባልመራን ኖሮ ወደዚህ አንመራም ነበር:: የጌታችን መልዕክተኞች በእውነት ላይ ሲሆኑ መጥተውልናል።» ይላሉ:: «ይህ ገነት ትሠሩት በነበራችሁት እንድትወርሱት የተደረጋችሁት ነው።» በማለት ይጠራሉ::"},{"id":44,"translation":"44. የገነት ሰዎች የእሳት ሰዎችን «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ሆኖ አገኘን እናንተስ ጌታችሁ የዛተባችሁን እውነት ሆኖ አገኛችሁትን?» ሲሉ ይጣራሉ:: የእሳት ሰዎችም «አዎን አገኘን» ይላሉ:: በመካከላቸዉም «የአላህ እርግማን በበደለኞች ላይ ይሁን» ሲል አዋጅ ነጋሪ ያውጃል::"},{"id":45,"translation":"45. በደለኞች ማለት እነዚያ ከአላህ መንገድ ሌሎችን ክፍሎች የሚከለክሉና የአላህ መንገድ እንድትጣመም የሚፈልጉ በመጨረሻዋ ዓለም ከሓዲያን የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው::"},{"id":46,"translation":"46. በገነት ሰዎችና በገሀነም ሰዎች መካከል አዕራፍ የሚባል ከባድ መጋረጃ አለ:: በአዕራፍ ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቁ ሰዎች አሉ:: የገነትን ሰዎችን «ሰላም ለእናንተ ይሁን» በማለት ይጣራሉ:: የአዕራፍ ሰዎች ገነት መግባትን የሚከጅሉ ሲሆኑ ገና እንዲገቡ አልተደረጉም::"},{"id":47,"translation":"47. ዓይኖቻቸው ወደ እሳት ሰዎች አቅጣጫ በተዞሩ ጊዜም፡- «ጌታችን ሆይ! እባክህ ከበደለኞች ጋር አታድርገን።» ይላሉ::"},{"id":48,"translation":"48. የአዕራፍ ሰዎች በምልክታቸው የሚያውቋቸውን ታላላቅ ሰዎች ይጠራሉ:: «ክምችታችሁና (ብዛታችሁና) ኩራታችሁ ምን ጠቀማችሁ?» ይሏቸዋል::"},{"id":49,"translation":"49. «እነዚያ የአላህ ችሮታው አይደርሳቸዉም ብላችሁ የማላችሁት ወገኖች ናቸውን? ገነትን ግቡ:: (አሁን ግን) ፍርሃት የለባችሁም:: እናንተም አታዝኑም።» (ተባሉ ይሏቸዋል::)"},{"id":50,"translation":"50. የእሳት ሰዎች የገነት ሰዎችን «በእኛ ላይ ውሃ ወይም አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ እባካችሁ ጣሉልን (አፍስሱልን)።» ብለው ይጠሯቸዋል:: የገነት ሰዎችም «እነዚህ ሲሳዮች እኮ አላህ በከሓዲያን ላይ እርም አድርጓቸዋል።» ይሏቸዋል።"},{"id":51,"translation":"51. ለእነዚያ ሃይማኖታቸውን መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው የያዙና የቅርቢቱ ህይወት ያታለለቻቸው የዚህን ቀን መገናኘታቸውን እንደ ረሱና በተአምራታችን ይክዱ እንደ ነበሩ ሁሉ ዛሬ እኛም እንረሳቸዋለን (እንተዋቸዋለን)::"},{"id":52,"translation":"52. ከእውቀት ጋር የዘረዘርነው የሆነን መጽሐፍ ለሚያምኑ ህዝቦች መመሪያና እዝነት ሲሆን አመጣንላቸው።"},{"id":53,"translation":"53. የዛቻውን ፍጻሜዉን እንጂ ሌላ ይጠባበቃሉን? (አይጠባበቁም):: ፍጻሜው በሚመጣበት ቀን ግን እነዚያ ከመምጣቱ በፊት የረሱት ሰዎች «የጌታችን መልዕክተኞች በእውነት መጥተዋል። ለእኛስ ያማልዱን ዘንድ አማላጆች አሉን? ወይስ ከዚያ እንሠራው ከነበርነው የተለየ ስራ እንድንሰራ ዘንድ ዕድሉ ይሰጠናልን?» ይላሉ:: በእርግጥም ራሳቸውን ይከስራሉ:: ይቀጥፉት የነበረው ሁሉ ከንቱ ሆኖ ያገኙታል::"},{"id":54,"translation":"54. (ሰዎች ሆይ) ጌታችሁ አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረና ከዚያም በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ ነው። ቀኑንም በሌሊቱ ይሸፍነዋል:: ሁለቱም እርስ በእርስ በፍጥነት ይፈላለጋሉ:: ጸሐይ ጨረቃና ከዋክብት በትዕዛዙ የተገሩ ናቸው። አስተውሉ! መፍጠርም ማዘዝም የእርሱ (የአላህ) ነው:: የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ክብሩ ላቀ::"},{"id":55,"translation":"55. ጌታችሁን ተናንሳችሁና ተዋርዳችሁ በድብቅ ለምኑት:: እርሱ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና::"},{"id":56,"translation":"56. ምድር ከተበጀች በኋላ አታበላሿት:: አላህን ፈርታችሁና ከጅላችሁ ተገዙት:: የአላህ እዝነት ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ ቅርብ ነውና::"},{"id":57,"translation":"57. አላህ ያ ንፋሶችን ከዝናብ በፊት አብሳሪዎች አድርጎ የሚልክ ነው:: ከባዶችንም ደመናዎች በተሸከሙ ጊዜ ሙት ወደ ሆነ አገር እንነዳዋለን:: በእነርሱም ውሃን እናወርዳለን:: እናም ከፍሬዎች ሁሉ በእነርሱ እናወጣለን:: ልክ እንደዚሁ ሙታንን ከመቃብር እናስወጣለን:: ይህን የምንለው ትገነዘቡ ዘንድ ነው::"},{"id":58,"translation":"58. መልካሙ አገር በጌታው ፈቃድ በቃዩ ያማረ ሆኖ ይወጣል። ያ መጥፎ የሆነው አገር ደግሞ በቃዩ ደካማ ሆኖ እንጂ አይወጣም:: ልክ እንደዚሁ ለሚያመሰግኑ ህዝቦች ተዓምራትን እናብራራለን።"},{"id":59,"translation":"59. ኑሕን ወደ ወገኖቹ ላክነው፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ለእናንተ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ።» አላቸው።"},{"id":60,"translation":"60. ከህዝቦቹ መካከል መሪዎቹ «እኛ በግልጽ ስህተት ውስጥ ሆነህ እናይሀለን።» አሉት።"},{"id":61,"translation":"61. ኑሕም አለ: «ወገኖቼ ሆይ! ምንም መሳሳት የለብኝም። ግን እኔ ከዓለማት ጌታ መልዕክተኛ ነኝ።"},{"id":62,"translation":"62. «የጌታዬን መልዕክቶች አደርስላችኋለሁ:: ለናንተም እመክራችኋለሁ:: ከአላህ በኩልም የማታውቁትን አውቃለሁ::"},{"id":63,"translation":"63. «አላህን ልትፈሩና ይታዘንላችሁም ዘንድ ከናንተው ጎሳ መካከል በሆነ ሰው ላይ እንዲያስጠነቅቃችሁ ከጌታችሁ ግሳጼ ስለመጣላችሁ ትደነቃላችሁን?» አላቸው።"},{"id":64,"translation":"64. ወዲያዉም አስተባበሉት:: እርሱንና እነዚያን ከእርሱ ጋር ያሉትንም በታንኳዋ ውስጥ አዳንናቸው:: እነዚያን በአናቅጻችን ያስተባበሉትን ግን በባህር አሰመጥናቸው:: እነርሱ ልበ እውራን ህዝቦች ነበሩና::"},{"id":65,"translation":"65. ወደ ዓድ ህዝቦችም ወንድማቸውን ሁድን ላክን። «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: የአላህን ቅጣት አትፈሩምን?» አላቸው።"},{"id":66,"translation":"66. ከህዝቦቹ መካከል መሪዎቹም «እኛ በሞኝነት ላይ ሆነህ እናይሀለን:: እኛ ከውሸተኞቹ ነህ ብለንም እንጠረጥርሀለን።» አሉት።"},{"id":67,"translation":"67. እርሱም አላቸው፡- «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ሞኝነት የለብኝም:: ግን እኔ ከአለማት ጌታ የተላኩ ነኝ።"},{"id":68,"translation":"68. «የጌታዬን መልዕክቶች አደርስላችኋለሁ። እኔም ለእናንተ ታማኝና መካሪ ነኝና።"},{"id":69,"translation":"69. ያስጠነቅቃችሁ ዘንድ ከናንተው መካከል በሆነ ሰው ከጌታችሁ የሆነ ግሳጼ ስለመጣባችሁ ትደነቃላችሁን? ከኑህ ህዝቦች በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በፍጥረትም ግዙፍነትን በጨመረላችሁ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: የሻችሁትን ታገኙ ዘንድ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ::"},{"id":70,"translation":"70. «አላህን አንድ አድርገን ብቻውን እንድንገዛውና አባቶቻችን ይገዟቸው የነበሩትን አማልክት እንድንተው መጣህብን? እውነተኛ ከሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት እስቲ አምጣብን።» አሉ።"},{"id":71,"translation":"71. «ከጌታችሁ የሆነ ቅጣትና ቁጣ በእናንተ ላይ በእውነት ተረጋገጠ:: እናንተና አባቶቻችሁ አማልክት ብላችሁ በጠራችኋቸው ስሞች አላህ በእነርሱ ምንም ማስረጃ ላላወረደባቸው ትከራከሩኛላችሁን? ተጠባበቁ እኔም ከናንተ ጋር ከተጠባባቂዎቹ ነኝና።» አለ::"},{"id":72,"translation":"72. እርሱንና እነዚያን አብረውት የነበሩትን በችሮታችን ከቅጣት አዳናቸው::የእነዚያንም በተአምራታችን ያስተባበሉትንና አማኞች ያልነበሩትን መሠረት ቆረጥን፡፡"},{"id":73,"translation":"73. ወደ ሰሙድ ህዝቦችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን:: «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ምንም አምላክ የላችሁም:: እውነተኛ ለመሆኔ ከጌታችሁ የሆነች ምልክት በእርግጥ መጥታላችኋለች:: ይህች ለእናንተ ተዓምር ስትሆን የአላህ ግመል ናትና ተዋት:: በአላህ ምድር ውስጥ እንደፈለገች ትብላ፤ ትጠጣም:: በክፉ አትንኳትም:: አሳማሚ ቅጣት ይይዛችኋልና።» አለ።"},{"id":74,"translation":"74. ከዓድ ህዝቦችም በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በምድሪቱም ላይ ባስቀመጣችሁ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: ከሜዳዎቿ ሸክላ ሕንጻዎችን ትገነባላችሁ:: ከተራራዎቿም ቤቶችን ትጠርባላችሁ:: ስለዚህ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ:: በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ::"},{"id":75,"translation":"75. ከወገኖቹ መካከል እነዚያ የኮሩት መሪዎች ለእነዚያ ለተሸነፉት በተለይም ከእነርሱ ላመኑት ክፍሎች: «ሷሊህ ከጌታው መላኩን ታውቃላችሁን?» አሏቸው:: እነርሱም «አዎን እናውቃለን:: እኛ እርሱ በተላከበት ነገር ሁሉ ትክክለኛ አማኞች ነን» አሉ።"},{"id":76,"translation":"76. እነዚያ የኮሩት እኛ ግን «በዚያ ባመናችሁበት ነገር ከሓዲያን ነን።» አሉ።"},{"id":77,"translation":"77. እናም ወዲያው ግመሊቱን ወጓትና ከጌታቸው ትዕዛዝ ወጡ:: «ሷሊህ ሆይ! ከመልዕክተኞቹ እንደሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት እስቲ አምጣብን።» አሉ።"},{"id":78,"translation":"78. ወዲያዉም የምድር መንቀጥቀጥ ያዘቻቸው:: በየቤቶቻቸዉም ውስጥ ተደፍተው አደሩ::"},{"id":79,"translation":"79. ሷሊህም ከእነርሱ ዞረና «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልዕክት በእርግጥ አደረስኩላችሁ:: ለእናንተም መከርኳችሁ:: ግን እናንተ መካሪዎችን አትወዱም።» አለ።"},{"id":80,"translation":"80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሉጥም ለሕዝቦቹ (እንዲህ) ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ: «ከዓለማት ከናንተ በፊት አንድም ህዝብ ያልፈጸመውን አስቀያሚ ሥራ ትሠራላችሁን?"},{"id":81,"translation":"81. «እናንተ ከሴቶች ሌላ ወንዶችን በመከጀል ትመጡባቸዋላችሁ። ይልቁንም እናንተ ወሰንን አላፊ ሕዝቦች ናችሁ።»"},{"id":82,"translation":"82. የሕዝቦቹም መልስ «ሉጥንና ተከታዮቹን ከከተማችሁ አውጧቸው:: እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸው።» ከማለት ውጭ ሌላ አልነበረም::"},{"id":83,"translation":"83. ከዚያም እርሱንና ቤተሰቦቹን አዳንናቸው ሚስቱ ብቻ ስትቀር:: እርሷማ ለጥፋት ከቀሩት ሰዎች ሆነች::"},{"id":84,"translation":"84. በእነርሱ ላይ የእሳት ዝናብን አዘነብንባቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የኃጢአተኞች መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት::"},{"id":85,"translation":"85. ወደ መድየን ሕዝብም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን። አላቸዉም: «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ በስተቀር ምንም አምላክ የላችሁም:: ከጌታችሁ ዘንድ ግልጽ ማስረጃ መጥቶላችኋል:: ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ:: የሰዎችንም ገንዘቦቻቸውን አታጉድሉባቸው:: ምድርንም ከተበጀች በኋላ አታበላሹ። አማኞች ከሆናችሁ ይህ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው::"},{"id":86,"translation":"86. «ሰዎችን የምታስፈራሩ፤ ከአላህም መንገድ በእርሱ ያመኑትን የምታግዱና የአላህን መንገድ መጥመሟንም የምትፈልጉ ሆናችሁ በየመንገዱ አትቀመጡ:: ጥቂቶች በነበራችሁና ባበዛችሁ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: የአጥፊ ህዝቦች መጨረሻ እንዴት እንደነበረም ተመልከቱ::"},{"id":87,"translation":"87. «ከናንተም መካከል እኔ በተላኩበት ያመኑ ቡድኖችና ያላመኑ ቡድኖች ቢኖሩ በመካከላችን አላህ እስከሚፈርድ ታገሡ:: እርሱ ከፈራጆች ሁሉ እጅግ በላጭ ነው።»"},{"id":88,"translation":"88. ከህዝቦቹ መካከል እነዚያ የኮሩት መሪዎችም፡- «ሹዐይብ ሆይ! አንተንና እነዚያን ካንተ ጋር ያመኑትን ከከተማችን እናወጣችኋለን ወይም ወደ ሃይማኖታችን መመለስ አለባችሁ።» አሉ:: እርሱም አላቸው: «የጠላንም ብንሆን?"},{"id":89,"translation":"89. «አላህ ከእርሷ ከአዳንን በኋላ ወደ ሃይማኖታችሁ ብንመለስ በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፍን:: አላህ ጌታችን ካልሻም በስተቀር ወደ እርሷ ልንመለስ አይገባንም:: የጌታችን እውቀቱ ከሁሉ ሰፋ:: በአላህ ላይ ብቻ ተመካን:: ጌታችን ሆይ! በእኛና በወገኖቻችን መካከል ፍረድ:: አንተም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነህና።» አለ።"},{"id":90,"translation":"90. ከወገኖቹም መካከል እነዚያ በአላህ የካዱት መሪዎች ለሕዝቡ «ሹዐይብን ብትከተሉ እናንተ ያኔ ከሳሪዎች ናችሁ።» አሉ።"},{"id":91,"translation":"91. ወዲያውኑ የምድር መንቀጥቀጥ ያዘቻቸው:: በየቤታቸው ውስጥ ተደፍተው አደሩ::"},{"id":92,"translation":"92. እነዚያ ሹዓይብን ያስተባበሉት ሰዎች በእርሷ እንዳልነበሩባት ሆኑ:: እነዚያ ሹዓይብን ያስተባበሉት ከሳሪዎቹ እነርሱው ሆኑ::"},{"id":93,"translation":"93. ሹዐይብም ትቷቸው ከእነርሱ ዞረና «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልእክቶች በእርግጥ አደረስኩላችሁ። ለእናንተም መከርኩ:: ታዲያ በከሃዲ ሰዎች ላይ እንዴት አዝናለሁ?» አለ::"},{"id":94,"translation":"94. በየትኛዉም ከተማ ለአላህ ይተናነሱ ዘንድ በድህነትና በችግር የያዝናቸው ብንሆን እንጂ አንድንም ነብይ አልላክንም::"},{"id":95,"translation":"95.ከዚያም እስከበዙና «አባቶቻችንን ድህነትና በሺታ በእርግጥ ነክቷቸዋል፡፡ (ይኽም የጊዜ ልማድ ነው)» እስካሉ ድረስ በመጥፎው ስፍራ በጎውን ለወጥን፡፡ ወዲያውም እነርሱ የማያውቁ ኾነው በድንገት ያዝናቸው፡፡"},{"id":96,"translation":"96. የከተሞቹ (ሰዎችም) በትክክል ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነርሱ ላይ ከሰማይና ከምድር በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር:: ግን አስተባበሉ:: ይሠሩት በነበሩትም ኃጢአት ምክኒያት ቀጣናቸው::"},{"id":97,"translation":"97. የከተሞቹ (ሰዎች) የተኙ ሆነው ቅጣታችን ሌሊት ሊመጣባቸው አይፈሩምን?"},{"id":98,"translation":"98. የከተሞቹ ሰዎችም የሚጫወቱ ሆነው ሳሉ ቅጣታችን ቀን በረፋዱ ሊመጣባቸው አይፈሩምን?"},{"id":99,"translation":"99. የአላህን ማዘናጋት አይፈሩምን? ተማመኑን? የአላህን ማዘናጋት ከከሳሪዎች ሕዝቦች በስተቀር ማንም የሚተማመን የለም::"},{"id":100,"translation":"100. ለእነዚያ ምድርን ከባለቤቶቿ ጥፋት በኋላ ለሚወርሱት ብንሻ ኖሮ በኃጢአቶቻቸው ምክኒያት የምንቀጣቸው መሆናችን አልተገለጸላቸዉምን? በልቦቻቸውም ላይ እናትማለን:: ስለዚህም እነርሱ አይሰሙም::"},{"id":101,"translation":"101. እነዚህ ከተሞች ከወሬዎቻቸው ባንተ ላይ እንተርካለን:: መልዕክተኞቻቸዉም በግልጽ ተዓምራት መጥተውላቸዋል:: ከመምጣታቸው በፊት ባስተባበሉትም ነገር የሚያምኑ አልሆነም:: ልክ እንደዚሁ አላህ በከሓዲያን ልቦች ላይ ያትማል::"},{"id":102,"translation":"102. ለብዙዎቻቸው በቃል ኪዳናቸው መሙላትን አላገኘንም:: ይልቁንም አብዛኞቻቸውን አመጸኞች ሆነው አገኘናቸው::"},{"id":103,"translation":"103. ከዚያም ከበኋላቸው ነብዩ ሙሳን ወደ ፈርዖንና ወደ መማክርቶቹ ተዓምራታችንን አስይዘን ላክነው:: በእርሷም ካዱ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የአጥፊዎች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ እስቲ ተመልከት::"},{"id":104,"translation":"104. ሙሳም አለ፡- «ፈርዖን! ሆይ እኔ ከዓለማት ጌታ የተላኩ መልክተኛ ነኝ?"},{"id":105,"translation":"105. «በአላህ ላይ ከእውነት በስተቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው:: ከጌታችሁ ተዓምር ይዤ መጥቻለሁና የኢስራኢል ልጆችን ከእኔ ጋር ልቀቅ።» አለ።"},{"id":106,"translation":"106. ፈርዖንም፡ «በተዓምር የመጣህ ከሆንክና ከእውነተኞቹ ከሆንክ እስቲ አምጣት።» አለው።"},{"id":107,"translation":"107. ሙሳም ዘንጉን ምድር ላይ ጣለ:: እርሷም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ሆነች::"},{"id":108,"translation":"108. እጁንም አወጣ:: እርሷም ወዲያውኑ ለተመልካቾች ነጭ ሆነች::"},{"id":109,"translation":"109. ከፈርዖን ሰዎች መማክርቶቹም አሉ፡ «ይህ በእርግጥ አዋቂ ድግምተኛ ነው።"},{"id":110,"translation":"110. «ከምድራችሁ ሊያወጣችሁ ይሻል።» አሉ። (ፊርዓውንም) «ታዲያ ምን? ታዛላችሁ?» አለ።"},{"id":111,"translation":"111. እነርሱም አሉ: «እርሱንና ወንድሙን አቆያቸው:: ወደ ከተሞቹ ሁሉ ሰብሳቢዎችን ላክ::"},{"id":112,"translation":"112. «አዋቂ ድግምተኞችን ሁሉ ያመጡልሃልና።» አሉ።"},{"id":113,"translation":"113. ድግምተኞቹም ወደ ፈርዖን መጡና «እኛ አሸናፊዎች ብንሆን ለኛ ክፍያ አለን?» አሉ።"},{"id":114,"translation":"114. ፈርዖንም: «አዎን። እናንተ እኔ ዘንድ ከባለሟሎቹ ትሆናላችሁ።» አላቸው።"},{"id":115,"translation":"115. እነርሱም «ሙሳ ሆይ! ዘንግህን በፊት ትጥላለህ ወይስ ፊት ጣዮቹ እኛ እንሁን?» አሉት።"},{"id":116,"translation":"116. ሙሳም «በፊት እናንተ ጣሉ።» አላቸው:: ከዚያም ገመዶቻቸውን በጣሉ ጊዜ የሰዎቹን ዓይኖች ደገሙባቸውና አስፈራሯቸው:: ትልቅ ድግምትንም አመጡ::"},{"id":117,"translation":"117. ወደ ሙሳም «ዘንግህን ጣል» ስንል ላክንበት (ጣላትም) ወዲውኑም የሚቀጣጥፉትን ማታለያ ሁሉ መዋጥ ጀመረች::"},{"id":118,"translation":"118. እውነቱም ተገለጸ:: ይሠሩት የነበሩት ድግምትም ተበላሸ::"},{"id":119,"translation":"119. እዚያ ላይ ተሸነፉና ወራዶች ሆነው ተመለሱ::"},{"id":120,"translation":"120. ድግምተኞቹም ሰጋጆች ሆነው ሱጁድ ወረዱ::"},{"id":121,"translation":"121. አሉም: «በዓለማት ጌታ አመንን።"},{"id":122,"translation":"122. «በሙሳና በሃሩን ጌታ።»"},{"id":123,"translation":"123. (ፊርዓውንም) አለ፡ «እኔ ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት በእርሱ አመናችሁን? ይህ በከተማይቱ ውስጥ ሰውን ከእርሷ ለማውጣት የተስማማችሁበት ተንኮል ነው:: ወደፊት የሚደርሰባችሁን ታውቃላችሁ።"},{"id":124,"translation":"124. «እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማፈራረቅ በእርግጥ እቆራርጣለሁ:: ከዚያም ሁላችሁንም በእንጨት ላይ እስቅላችኋለሁ።» አለ።"},{"id":125,"translation":"125. እነርሱም አሉ: «እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን።"},{"id":126,"translation":"126. «የጌታችን ተዓምራት በመጡልን ጊዜ ከማመናችን በስተቀር ከእኛ አትጠላም:: ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ:: ሙስሊሞችም ሆነን ግደለን።» አሉ።"},{"id":127,"translation":"127. ከፈርዖን ሰዎች ቅምጥሎቹ ለፈርዖን: «ሙሳንና ሰዎችን በምድር ላይ እንዲያበላሹና ሙሳም አንተንና አምልኮትህን እንዲተው ትተዋቸዋለህን?» አሉ:: እሱም «ወንዶች ልጆቻቸውን እንገድላለን:: ሴቶቻቸውንም እናስቀራለን:: እኛም ከበላያቸው ነን አሸናፊዎች ነን» አለ።"},{"id":128,"translation":"128. ሙሳም ለሰዎቹ፡- «በአላህ ታገዙ፤ ታገሱም። ምድር ለአላህ ናትና ከባሮቹ መካከል ለሚሻው ያወርሳታል:: ምስጉኗም ፍጻሜ ለጥንቁቆቹ ናት።» አላቸው።"},{"id":129,"translation":"129. ህዝቦቹም «አንተ ከመምጣትህ በፊትም ሆነ ከመጣህልን በኋላ ተሰቃየን።» አሉት:: ሙሳም «ጌታችሁ ጠላቶቻችሁን ሊያጠፋና እንዴት እንደምትሰሩ ይመለከት ዘንድ በምድር ላይ ሊተካችሁ ይከጀላል።» አላቸው።"},{"id":130,"translation":"130. የፈርዖንንም ቤተሰቦች እንዲገሰጹ በድርቅና የፍራፍሬ ምርታቸውን በመቀነስ በእርግጥ ቀጣናቸው::"},{"id":131,"translation":"131. ምቾት በመጣችላቸው ጊዜ «ይህች ለእኛ ተገቢ ናት።» ይላሉ። ክፋት ባገኛቸው ጊዜ ግን ሙሳና አብረውት ያሉት ክፉ ገዶቻቸው እንደሆኑ ያስባሉ። አስተውሉ! ክፉ እድላቸው (ገደቢስነታቸው) ከአላህ ዘንድ ነው:: አብዛኞቻቸው ግን ይህን አያውቁም::"},{"id":132,"translation":"132. «በማንኛይቱም ተዓምር ልትደግምብን ብታመጣም የምናምንልህ አይደለንም።» አሉ።"},{"id":133,"translation":"133. ወዲያዉም የውሃን ማጥለቅለቅ፤ አንበጣን፤ ቅማልን፤ እንቁራሪቶችን፤ ደምን፤ የተለያዩ ተዓምራት ሲሆኑ በእነርሱ ላይ ላክን:: እነርሱ ግን ኮሩም:: ተንኮለኞችም ህዝቦች ነበሩ::"},{"id":134,"translation":"134. በእነርሱ ላይ ቅጣቱ በወደቀባቸውም ጊዜ «ሙሳ ሆይ! ጌታህን ላንተ ቃል ኪዳን በገባልህ መሠረት ለምንልንና ከእኛ ቅጣቱን ብታነሳልን ላንተ እናምንልሀለን:: የኢስራኢልን ልጆችም ካንተ ጋር እንለቃለን።» አሉ።"},{"id":135,"translation":"135. ለሚደርሱበት የተወሰነ ጊዜ ድረስ ቅጣትን ከእነርሱ ላይ ባነሳን ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ቃላቸውን አፈረሱ::"},{"id":136,"translation":"136. እነርሱም በተዓምራታችን ስላስተባበሉና ከእርሷ ዘንጊዎች ስለሆኑ ተበቀልናቸው:: በባህር ውስጥም አሰመጥናቸው::"},{"id":137,"translation":"137. እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ህዝቦች ያቺን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምስራቋንም ምዕራቧንም አወረስናቸው:: መልዕክተኛችን ሆይ! የጌታህ መልካሚቱ ቃል በኢስራኢል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች:: ፈርዖንና ሰዎቹ ይሰሩት የነበረውን ህንጻና ዳስ ያደርጉት የነበረውንም አፈረስን::"},{"id":138,"translation":"138. የኢስራኢል ልጆችን ባህሩን አሻገርናቸው:: ለእነርሱ በሆኑ ጣኦታት መገዛት ላይ በሚዘወትሩ ህዝቦች አጠገብ አለፉም:: «ሙሳ ሆይ! ለእነርሱ ለሰዎቹ አማልክት እንዳሏቸው ሁሉ ለኛም አምላክን አድርግልን።» አሉት:: «እናንተ የምትሳሳቱ ህዝቦች ናችሁ።» አላቸው።"},{"id":139,"translation":"139. «እነዚህ እነርሱ በውስጡ ያሉበት ነገር ጠፊ ነው:: ይሰሩት የነበሩትም ብልሹ ነው።» አላቸው።"},{"id":140,"translation":"140. «እርሱ ከዓለማት ያበለጣችሁ ሲሆን ከአላህ ሌላ የምትገዙትን አምላክ እፈልግላችኋለሁን?» አለ::"},{"id":141,"translation":"141. የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ከፈርዖንም ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት የሚያቀምሷችሁ ወንዶች ልጆቻችሁንም የሚገድሉ ሴቶቻችሁንም የሚተው ሲሆኑ ባዳንናችሁ ጊዜ (የሆነዉን አስታውሱ):: በዚህ ውስጥ ከጌታችሁ የሆነ ከባድ ፈተና አለበት::"},{"id":142,"translation":"142. ነብዩ ሙሳን ሰላሳን ሌሊት (ሊፆምና ልናነጋግረው) ቀጠርነው:: በአስርም (ሌሊት) ሞላናት:: የጌታዉም ቀጠሮ አርባ ሌሊት ሲሆን ተፈጸመ:: ሙሳም ለወንድሙ ለሀሩን «በህዝቦቼ ላይ ተተካኝና አሳምር:: የአጥፊዎችን መንገድ አትከተል።» አለው::"},{"id":143,"translation":"143. ሙሳ ለቀጠሮው በመጣና ጌታዉም ባነጋገረው ጊዜ፡ «ጌታዬ ሆይ! በእርግጥ ራስህን አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና።» አለ። (አላህም)፡- «እኔን በፍጹም አታየኝም:: ግን ወደ ተራራው ተመልከትና በስፍራው ከረጋ አንተም ታየኛለህ።» አለው:: ጌታዉም ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው:: ሙሳም ጮኸና ወደቀ:: በአንሰራራም ጊዜ «ጌታዬ ጥራት ይገባህ ወደ አንተ ተመለስኩ:: እኔም በጊዜያቴ የአማኞች መጀመሪያ ነኝ።» አለ።"},{"id":144,"translation":"144. አላህም አለ፡- «ሙሳ ሆይ! እኔ በመልዕክቶቼና በማናገሬ በሰዎች ላይ መረጥኩህ:: የሰጠሁህንም ያዝ። ከአመስጋኞችም ሁን።» አለው።"},{"id":145,"translation":"145. ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከሁሉ ነገር ግሳጼንና ለሁሉ ነገር ማብራራትን ጻፍንለትና አልንም: «በብርታትም ያዛት። ሕዝቦችህንም በመልካሟ እንዲይዙ እዘዛቸው። የአመጸኞቹን አገር በእርግጥ አሳያችኋለሁ።»"},{"id":146,"translation":"146. እነዚያን ያለ አግባብ በምድር ላይ የሚኮሩትን ከአንቀፆቼ በእርግጥ አዞራቸዋለሁ:: ተዓምርንም ሁሉ ቢያዩ እንኳን አያምኑም:: ቅንንም መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው አይዙትም:: ግን የጥመትን መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው ይይዙታል:: ይህ እነርሱ በአንቀፆቻችን ስለ አስተባበሉና ከእርሷም ዘንጊዎች ስለሆኑ ነው::"},{"id":147,"translation":"147. እነዚያም በአናቅጻችንና መጨረሻይቱን ዓለም በመገናኘት ያስተባበሉት ሥራዎቻቸው ተበላሹ:: ይሰሩት የነበረውን እንጂ ይመነዳሉን?"},{"id":148,"translation":"148. የሙሳም ህዝቦች ከእርሱ መሄድ በኋላ ከጌጦቻቸው በወይፈን ቅርጽ የተቀረጸውን እና የራሱ የሆነ ድምጽ የነበረውን አካል አምላክ አድርገው ያዙት:: እርሱ የማያናግራቸው መንገድን የማይመራቸው መሆኑን አይመለከቱምን? አምላክ አደረጉት:: በዳዮችም ሆኑ::"},{"id":149,"translation":"149. በተጸጸቱና እነርሱም በእርግጥ የተሳሳቱ መሆናቸውን ባዩ ጊዜ «ጌታችን ካላዘነልንና ካልማረን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንሆናለን።» አሉ::"},{"id":150,"translation":"150. ሙሳ እየተቆጣና እያዘነ ወደ ህዝቦቹ በተመለሰ ጊዜ «በእኔ ቦታ የተካችሁት ነገር ምንኛ ከፋ! የጌታችሁን ትዕዛዝ ተቻኮላችሁን?» አላቸውና ሰሌዳዎቹንም ጣላቸው። የወንድሙን የራስ ጸጉር ወደ እርሱ እየጎተተው ያዘ:: ወንድሙም፡- «የእናቴ ልጅ ሆይ! ህዝቦቹ ናቁኝ ሊገድሉኝም ተቃረቡ:: ስለዚህ በእኔ ጠላቶችን አታስደስትብኝ። ከአመጸኞች ህዝቦችም ጋር አታድርገኝ።» አለው።"},{"id":151,"translation":"151. ሙሳም፡- «ጌታዬ ሆይ! ለኔም ለወንድሜም ማረን:: በእዝነትህ ውስጥም አስገባን። አንተም ከአዛኞቹ ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህና።» አለ::"},{"id":152,"translation":"152. እነዚያ ወይፈኑን አምላክ ያደረጉት ሰዎች ከጌታቸው ዘንድ ቁጣ በቅርቢቱም ህይወት ውርደት ያገኛቸዋል:: ቀጣፊዎችን ልክ እንዲዚሁ እንቀጣለን::"},{"id":153,"translation":"153. እነዚያም ኃጢአቶችን የሠሩ ከዚያም በኋላ የተጸጸቱና በአላህ ያመኑ ጌታህ ከእርሷ በኋላ መሀሪና አዛኝ ነው:: (ጸጸታቸውን ይቀበላቸዋል)::"},{"id":154,"translation":"154. ሙሳም ቁጣው በበረደ ጊዜ ሰሌዳዎቹን አነሳቸው:: በግልባጫቸውም ውስጥ ለእነዚያ እነርሱ ጌታቸውን ለሚፈሩት ሰዎች ሁሉ መምሪያና እዝነት አለባቸው::"},{"id":155,"translation":"155. ሙሳም ከህዝቦቹ መካከል ለቀጠሯችን ሰባ ሰዎችን መረጠ:: ከዚያ ብርቱ የምድር እንቅጥቃጤ በደረሰባቸው ጊዜ ሙሳ አለ፡- «ጌታዬ ሆይ! ብትፈልግ ኖሮ ከአሁን በፊት ባጠፋሀቸው ነበር:: እኔንም ባጠፋኸኝ ነበር:: ከእኛ መሀከል ቂሎቹ በሠሩት ጥፋት ታጠፋናለህን? ፈተናይቱ የአንተ ፈተና እንጂ ሌላ አይደለችም:: በእርሷ የምትሻውን ታሳስታለህ። የምትሻውንም ታቀናለህ:: አንተ ረዳታችን ነህና:: ለእኛ ምህረት አድርግልን። እዘንልንም:: አንተ ከመሀሪዎች ሁሉ በላጭ ነህና::"},{"id":156,"translation":"156. «ጌታችን ሆይ! ለእኛ በዚች በቅርቢቱ ዓለም መልካሟን በመጨረሻይቱም ዓለም መልካሟን ጻፍልን:: እኛ ወደ አንተ ተመልሰናል።» (ሲል ሙሳ ጌታውን ለመነ):: አላህም አለ: «ቅጣቴ በእርሱ ልቀጣው የምፈልገውን ሰው እቀጣበታለሁ:: ችሮታዬ ከሁሉም ነገር የሰፋ ነው:: ለእነዚያ ለሚጠነቀቁ ዘካንም ለሚሰጡ ለእነዚያም በአናቅጻችን ለሚያምኑ ሁሉ በእርግጥ እጽፈዋለሁ::»"},{"id":157,"translation":"157. ለእነዚያ ያንን እነርሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብን መልዕክተኛ የሚከተሉ ለሆኑ (ሁሉ በእርግጥ እጽፋታለሁ):: በበጎ ሥራ ያዛቸዋል:: ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል:: መልካም ነገሮችንም ለእነርሱ ይፈቅድላቸዋል:: መጥፎ ነገሮችንም በነሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል:: ከእነርሱም ላይ ሸክማቸውንና እነዚያንም በእነርሱ ላይ የነበሩትን እንደ እንዛዝላ ይከብዱ የነበሩ ከባድ ህግጋትን ያነሳላቸዋል:: እነዚያ በእርሱ ያመኑ፤ ያከበሩት፤ የረዱትና ያንን ከርሱ ጋር የተወረደውን ብርሃን የተከተሉ ሁሉ እነዚያ እነርሱ ከቅጣት የሚድኑ ናቸው::"},{"id":158,"translation":"158. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ ወደ ሁላችሁም የአላህ መልዕክተኛ ነኝ:: እርሱም ያ የሰማያትና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነ ነው:: እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም:: ህያው ያደርጋል:: ይገድላልም:: በአላህ በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ በሆነው መልዕክተኛውም እመኑ:: ወደ ቅኑ መንገድ ትመሩ ዘንድም ተከተሉት።» በላቸው::"},{"id":159,"translation":"159. ከሙሳ ህዝቦች መካከል በእውነት የሚመሩና በእውነት ፍርድን የሚያስተካከሉ ቡድኖችም አሉ::"},{"id":160,"translation":"160. የሙሳን ህዝቦች አስራ ሁለት ነገዶች አድርገን ከፋፈልናቸው:: ወደ ሙሳም ወገኖቹ ውሃን በፈለጉበት ጊዜ ድንጋዩን በበትርህ ምታው ስንል ላክን:: (መታዉም) አስራ ሁለት ምንጮች ፈለቁ:: ሰዎቹ ሁሉ መጠጫቸውን በእርግጥ አወቁ:: በእነርሱም ላይ ዳመናን አጠለልን:: በእነርሱም ላይ \"መንን\" እና ድርጭትን አወረድን:: «ከሰጠናችሁም መልካም ሲሳይ ብሉ።» አልን:: ጸጋዎቻችንን በመካዳቸው አልበደሉንም:: ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ህዝቦች ነበሩ::"},{"id":161,"translation":"161. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለነርሱም «በዚች ከተማ ተቀመጡ:: ከእርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ ብሉ:: ‹የምንፈልገው የኃጢታችንን መርገፍ ብቻ ነው።› በሉም:: የከተማይቱን በር አጎንብሳችሁ ግቡ ኃጢአቶቻችሁን ለእናንተ እንምራለንና:: በጎ ለሠሩት ሰዎች በእርግጥ እንጨምራለን።» ባልን ጊዜ የሆነውን አስታውስ።"},{"id":162,"translation":"162. ከእነርሱም ውስጥ እነዚያ ራሳቸውን የበደሉ ሰዎች ከዚያ ለእነርሱ ከተባለው ሌላ የሆነን ቃል ለወጡ:: በእነርሱም ላይ ይበድሉ በነበሩት በደል ምክንያት መአትን ከሰማይ ላክንባቸው::"},{"id":163,"translation":"163. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያም በባህሩ ዳርቻ ከነበረችው ከተማ በቅዳሜ ቀን ወሰን ባለፉ ጊዜ በሰንበታቸው ቀን አሳዎቻቸው የተከማቹ ሆነው በሚመጡላቸው ጊዜ የሆነውን ጠይቃቸው:: ሰንበትንም በማያከብሩበት (በሌላው) ቀን አይመጡላቸዉም:: ልክ እንደዚሁ በአመፃቸው ምክንያት እንሞክራቸዋለን::"},{"id":164,"translation":"164. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ከፊሎቹ ህዝቦች «አላህ አጥፊያቸው ወይም በብርቱ ቅጣት ቀጫቸው የሆኑትን ህዝቦች ለምን ትገስጻላችሁ?» ባሉ ጊዜ ገሳጮቹም «በጌታችሁ ዘንድ በቂ ምክንያት እንዲሆንና እነርሱም ቢከለከሉ ብለን ነው።» ባሉበት ጊዜ የሆነውን አስታውስ::"},{"id":165,"translation":"165. የተገሰጹበትንም ነገር በተው ጊዜ እነዚያን ከክፉ የሚከለክሉትን ክፍሎች አዳንን:: እነዚያንም የበደሉትን ሰዎች ያምጹ በነበሩበት ምክንያት በብርቱ ቅጣት ቀጣናቸው::"},{"id":166,"translation":"166. ከእርሱም ከተከለከሉት ነገር በኮሩ ጊዜ ለእነርሱ «ወራዶች ዝንጀሮዎች ሁኑ።» አልን:: (ሆኑም)::"},{"id":167,"translation":"167. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እስከ ትንሳኤ ቀን ክፉ ቅጣትን የሚያቀምሳቸውን ወገን በነሱ ላይ በእርግጥ የሚልክ መሆኑን ባስታወቀ ጊዜ (የሆነውን አስታውሳቸው):: ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ፈጣን ነው:: እርሱም በእርግጥ እጅግ መሀሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":168,"translation":"168. (የኢስራኢልን ልጆችን) በምድር ላይ የተለያዩ ህዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው:: ከእነርሱ መልካሞች አሉ:: ከእነርሱም ከዚያ ሌላ የሆኑ አሉ:: ይመለሱ ዘንድም በተድላዎችና በመከራዎቻች ሞከርናቸው::"},{"id":169,"translation":"169. ከኋላቸዉም መጽሐፉን የወረሱ መጥፎ ምትኮች በእነርሱ ቦታ ተተኩ:: የዚህም የቅርቡን ጠፊ ጥቅም ይይዛሉ:: ብጤዉም ጥቅም ቢመጣላቸው የሚይዙት ሲሆኑ «በሠራነው ለእኛ ምህረት ይደርግልናል።» ይላሉ:: በአላህ ላይ በእውነት በስተቀር እንዳይናገሩ በእነርሱ ላይ የመጽሐፉ ቃል ኪዳን አልተያዘባቸዉምን? በእርሱ ውስጥ ያለውንም አላነበቡምን? የመጨረሻይቱን አገር ለእነዚያ ጌታቸውን ለሚፈሩት ሰዎች ሁሉ በላጭ ናት:: አታውቁምን?"},{"id":170,"translation":"170. እነዚያም መጽሐፉን ጠብቀው የሚይዙ፤ ሶላትንም በደንቡ የሰገዱ ሁሉ (ምንዳቸውን እንከፍላቸዋለን):: እኛ የመልካም ሠሪዎችን ምንዳ አናጠፋምና::"},{"id":171,"translation":"171. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጡርን ተራራ ነቅለን ከበላያቸው እንደ ጥላ ሆኖ ባነሳነውና እርሱም በእነርሱ ላይ ወዳቂ መሆኑን ባረጋገጡ ጊዜ የሆነውን( አስታውስ):: «የሰጠናችሁን በብርታት ያዙ:: ትጠነቀቁም ዘንድ በዉስጡ ያለውን ተገንዘቡ።» አልን::"},{"id":172,"translation":"172. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው ዘሮቻቸውን ባወጣና «ጌታችሁ አይደለሁምን?» ሲል በነፍሶቻቸው ላይ ባስመሰከራቸው ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: «ጌታችን ነህ መሰከርን» አሉ። በትንሳኤ ቀን «ከዚህ ቃል ኪዳን ዘንጊዎች ነበርን» እንዳትሉ።"},{"id":173,"translation":"173. ወይም «ጣኦታትን ያጋሩት ከኛ በፊት የነበሩት አባቶቻችን ብቻ ናቸው:: እኛም ከእነርሱ በኋላ የሆንን ዘሮች ነበርን አጥፊዎቹ በሠሩት ጥፋት እኛን ታጠፋናለህን?» እንዳትሉ አስመሰከርናችሁ::"},{"id":174,"translation":"174. ልክ እንደዚሁም (እንዲያስቡ) እንዲመለሱም አናቅጽን እናብራራለን::"},{"id":175,"translation":"175. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያን ተዓምራታችንን የሰጠነውንና ከዚያ እርሱም ከእርሷ የወጣውን ሰይጣንም ያስከተለውን በዚህም ምክንያት ከጠማሞቹ የሆነውን ሰው ወሬ በእነርሱ ላይ አንብብላቸው::"},{"id":176,"translation":"176. ብንፈልግ ኖሮ በእርሷ ከፍ ባደረግነው ነበር:: እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ:: ፍላጎቱንም ተከተለ:: ብጤዉም ብታባርረዉም ባታባርረዉም ምላሱን አውጥቶ እንደሚያለከልክ ውሻ ነው:: ይህ የእነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉት ህዝቦች ምሳሌ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው::"},{"id":177,"translation":"177. የእነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉትና ነፍሶቻቸውን ይበድሉ የነበሩት ሰዎች ምሳሌ ከፋ::"},{"id":178,"translation":"178. አላህ የሚያቀናው ሰው ሁሉ ቅን ማለት እርሱው ነው:: የሚያጠማቸዉም ሰዎች እነዚያ ከሳሪዎቹ ማለት እነርሱው ናቸው::"},{"id":179,"translation":"179. ከአጋንንትም ሆነ ከሰዎች መካከል ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን:: ለእነርሱ የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው:: ለእነርሱም የማያዩባቸው ዓይኖች አሏቸው:: ለእነርሱም የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሏቸው:: እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው:: ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ህዝቦች ናቸው:: እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱው ናቸው::"},{"id":180,"translation":"180. ለአላህ መልካም ስሞች አሉት:: (ዱዓ ስታደርጉ) በእርሷ ጥሩት:: እነዚያን ስሞቹን የሚያጣምሙትን ክፍሎች ተዋቸው:: ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ::"},{"id":181,"translation":"181. ከፈጠርናቸዉም መካከል በእውነት የሚመሩና በእውነት ፍርድን የሚያስተካክሉ ህዝቦችም አሉ::"},{"id":182,"translation":"182. እነዚያን በአናቅጻችን ያስተባበሉትን ሰዎች ከማያውቁት ስፍራ ቀስ በቀስ እናዘናጋቸዋለን::"},{"id":183,"translation":"183. ለእነርሱም ጊዜ እሰጣቸዋለሁ:: ጥበቤ ብርቱ ነውና::"},{"id":184,"translation":"184. በነብያቸው በሙሐመድ ምንም እብደት የሌለበት መሆኑን አያስተውሉምን? እርሱ ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለም::"},{"id":185,"translation":"185. በሰማያትና በምድር ግዛት ውስጥ ከማንኛዉም ነገር አላህ በፈጠራቸው ሁሉ የሞት ጊዜያቸዉም በእርግጥ መቅረቡ የሚፈራ መሆኑን አያስተውሉምን? ለመሆኑ እነርሱ ከቁርኣን ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ::"},{"id":186,"translation":"186. አላህ የሚያጠመውን ለእርሱ ምንም አቅኝ የለዉም:: በጥመታቸዉም ውስጥ የሚዋልሉ ሲሆኑ ይተዋቸዋል::"},{"id":187,"translation":"187. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ትንሳኤ መቼ እንደምትመጣ ይጠይቁሃል:: «እውቀቷ በጌታዬ ዘንድ ብቻ ነው:: በመከሰቻዋ ጊዜም እርሱ እንጂ ሌላ አይገልጽላችሁም:: በሰማያትና በምድርም ከበደች:: በድንገት ቢሆን እንጂ አትመጣባችሁም።» በላቸው:: ስለ እርሷ በደንብ እንደተረዳ አድርገው ይጠይቁሃል:: «እውቀቷ ግን አላህ ዘንድ ብቻ ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች ይህን ነገር ጠንቅቀው አያውቁም።» በላቸው።"},{"id":188,"translation":"188. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ የፈለገዉን በስተቀር ለራሴ ጥቅምንም ሆነ ጉዳት ማምጣት አልችልም:: የሩቅን ሚስጥር የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ሁሉ ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር:: እኔም ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» በላቸው::"},{"id":189,"translation":"189. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁና ከእርሷም መቀናጆዋን ወደ እርሷ ይረካ ዘንድ የፈጠረ ነው:: በተገናኛትም ጊዜ ቀላልን እርግዝና አረገዘች:: ጽንሱን ይዛው ሄደች:: ባረገዘችም ጊዜ «ደግን ልጅ ብትሰጠን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንሆናለን።» ሲሉ ጌታቸውን አላህን ለመኑ::"},{"id":190,"translation":"190. መልካምን ልጅ በሰጣቸዉም ጊዜ በሰጣቸው ልጅ (ስም) ለእርሱ ተጋሪዎችን አደረጉለት:: አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ላቀ::"},{"id":191,"translation":"191. ምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱ ራሳቸው የሚፈጠሩትን ፍጡሮች በአላህ ያጋራሉን?"},{"id":192,"translation":"192. ለነርሱም መርዳትንም የማይችሉትን፤ ነፍሶቻቸውንም እንኳን የማይረዱትን ያጋራሉን?"},{"id":193,"translation":"193. ወደ ቅን መንገድ ብትጠሯቸዉም አይከተሏችሁም:: ብትጠሯቸው ወይም ዝምተኞች ብትሆኑም በእናንተ ላይ እኩል ነው::"},{"id":194,"translation":"194. (ከሀዲያን ሆይ!) እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣኦቶች ብጤዎቻችሁ የአላህ ባሮች ናቸው:: እውነተኞች ከሆናችሁ እስቲ ጥሯቸውና ለእናንተ ይመልሱላችሁ:: (መመለስ አይችሉም።)"},{"id":195,"translation":"195. ለእነርሱ የሚሄዱባቸው እግሮች አሏቸውን? ወይስ የሚጨብጡባቸው እጆች አሏቸውን? ወይንስ እነርሱ የሚያዩባቸው አይኖች አሏቸውን? ወይንስ እነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች አሏቸዉን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያጋራችኃቸውን ጥሩና ከዚያም አሲሩብኝ:: ጊዜም አትስጡኝ።» በላቸው::"},{"id":196,"translation":"196. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ በላቸው) «የእኔ ረዳቴ ያ ቁርኣንን ያወረደልኝ አላህ ብቻ ነው:: እርሱ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ ይረዳልና።"},{"id":197,"translation":"197. (አጋሪዎች ሆይ! ) «እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣኦታት ሁሉ ሊረዷችሁ ፍጽሞ አይችሉም:: ነፍሶቻቸውንም እንኳን አይረዱም።»"},{"id":198,"translation":"198. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ቀናው መንገድ እንዲመሩ ብትጠሯቸው አይሰሙም። እነርሱንም የማያዩ ሲሆኑ ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ::"},{"id":199,"translation":"199. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይቅርባይነትን ያዝ:: በመልካምም እዘዝ:: ባለጌዎቹንም ተዋቸው::"},{"id":200,"translation":"200. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሰይጣን የተንኮል ጉትጎታ ቢያጋጥምህ በአላህ ብቻ ተጠበቅ:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነው::"},{"id":201,"translation":"201.እነዚያ የተጠነቀቁት ከሰይጣን የኾነ ዘዋሪ በነካቸው ጊዜ (ጌታቸውን) ይገነዘባሉ:: ወዲያዉም እነርሱ ተመልካቾች ይሆናሉ:"},{"id":202,"translation":"202. ወንድሞቻቸዉም ጥመትን ይጨምሩላቸዋል:: ከዚያም እነርሱ አይገቱም::"},{"id":203,"translation":"203. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተዓምርም ባላመጣህላቸው ጊዜ «በራስህ ለምን አትመርጣትም።» ይላሉ:: «ከጌታዬ ወደ እኔ የተወረደውን ብቻ ነው የምከተለው:: ይህ ቁርኣን ከጌታችሁ የተወረደ ሲሆን ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ መረጃ፤ መመሪያና እዝነት ነው።» በላቸው::"},{"id":204,"translation":"204. (ሙስሊሞች ሆይ!) ቁርኣን በሚነበብበት ጊዜ እርሱን በጥሞና አድምጡ:: ጸጥም በሉ። ይታዘንላችኋልና።"},{"id":205,"translation":"205. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህን በሚስጥር ተናንሰህና ፈርተህ ከጩኸት በታች በሆነ ድምጽ በጥዋትና በማታ አውሳው:: ከዘንጊዎቹም አትሁን::"},{"id":206,"translation":"206. እነዚያ በጌታህ ዘንድ ያሉት መላዕክት እንኳን እርሱን ከመገዛት ፈጽሞ አይኮሩም:: ሁል ጊዜም ያወድሱታል:: ለእርሱም ብቻ ይሰግዳሉ::"}]},{"id":8,"verses":[{"id":1,"translation":"1.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጦርነት ከተማረኩ ገንዘቦች ይጠይቁሃል። «በጦርነት የተዘረፉ ገንዘቦች የአላህና የመልዕክተኛው ናቸው:: ስለዚህ አላህን ፍሩ:: በመካከላችሁ ያለውንም ሁኔታ አሳምሩ:: ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ።» በላቸው።"},{"id":2,"translation":"2. ፍጹም ትክክለኛ አማኞች ማለት እነዚያ አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩ፤ በእነርሱም ላይ የቁርኣን አናቅጽ በተነበቡ ጊዜ እምነትን የሚጨምሩላቸውና በጌታቸው ላይ ብቻም የሚመኩት ብቻ ናቸው::"},{"id":3,"translation":"3. እነዚያ ሰላትንም (ወቅቱን ጠብቀውና ደንቡን አሟልተው) የሚሰግዱና ከሰጠናቸዉም ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው::"},{"id":4,"translation":"4. እነዚያ ትክክለኛ አማኞች ማለት እነርሱው ናቸው:: ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ብዙ ደረጃዎች፤ የአላህ ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አለላቸው::"},{"id":5,"translation":"5. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ይህ በምርኮ ክፍያ ሂደት ላይ የታየው የከፊሉ ሰው መጥላት ምሳሌው) ከአማኞች ከፊሉ እየጠሉ ጌታህ ከቤትህ በእውነት ላይ ሆነህ እንዳወጣህ ምሳሌ ነው::"},{"id":6,"translation":"6.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ እያዩ ወደ ሞት እንደሚነዱ ሆነው በእውነቱ ነገር ላይ በመጋደል ግዴታነት ከተገለጸላቸው በኋላ ይከራከሩሃል::"},{"id":7,"translation":"7. (እናንተ ተከራካሪዎች ሆይ!)፤ አላህ ከሁለቱ ቡድኖች አንደኛዋን ለእናንተ ናት ሲል ተስፋ በሰጣችሁና የኃይል ባለቤት ያልሆነችውን የነጋዴይቱን ቡድን ለእናንተ ልትሆን በወደዳችሁ ጊዜ አላህም በተስፋ ቃላቱ እውነቱን ማረጋገጡን ሊገልጽና የካሓዲያንንም መጨረሻ ሊቆርጥ በፈለገ ጊዜ (የሆነውን አስታውስ)::"},{"id":8,"translation":"8. ይህንንም ያደረገው አጋሪዎቹ ቢጠሉም እውነቱን ሊያረጋግጥና ክህደትን ሊያጠፋ ነው::"},{"id":9,"translation":"9. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከጌታችሁ እርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ «እኔ በሺህ መላዕክት ተከታታዮች ሲሆኑ እረዳችኋለሁ።» ሲል ለእናንተ የተቀበላችሁን አስታውሱ።"},{"id":10,"translation":"10. አላህ ይህንን እርዳታ ለብስራትና ልቦቻችሁ በእርሱ ሊረኩበት እንጂ ለሌላ አላደረገዉም:: ድልም የሚገኘው ከአላህ ዘንድ ብቻ ነው:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":11,"translation":"11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) ከእርሱ በሆነው ጸጥታ በጦር ግንባር በእንቅልፍ በሸፈናችሁና ውሃውንም በእርሱ ሊያጠራችሁ፤ የሰይጣንንም ጉትጎታ ከናንተ ላይ ሊያስወግድላችሁ፤ ልቦቻችሁንም በትዕግሥት ሊያጠነክርላችሁ፤ በእርሱም ጫማዎችን በአሸዋው ላይ ሊያደላድልላችሁ በእናንተ ላይ ከሰማይ ዝናብን ባወረደ ጊዜ የሆነውን አስታውስ::"},{"id":12,"translation":"12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ወደ መላዕክቱ «እኔ በእርዳታዬ ከናንተ ጋር ነኝና እነዚያን በእኔ ያመኑትን ሰዎች አጽናኑ:: በእነዚያ በአላህ በካዱት ልቦች ውስጥ ደግሞ ፍርሀትን እጥላለሁ:: ከአንገቶችም በላይ እራሶችን ምቱ:: ከእነርሱም የቅርንጫፎችን መለያ ( አትቆች) ሁሉ ምቱ።» ሲል ያወረደውን አስታውስ።"},{"id":13,"translation":"13. ይህ የሆነው በአላህና በመልዕክተኛው ስለካዱ ነው:: አላህንና መልዕክተኛውን ለሚቃወም ሁሉ አላህም ቅጣቱ ብርቱ ነው::"},{"id":14,"translation":"14. (ከሓዲያን ሆይ!) ይህ ቅጣታችሁ ነው:: እናም ቅመሱት:: ለከሓዲያን የገሀነም እሳት ቅጣት በእርግጥ አለባቸው::"},{"id":15,"translation":"15. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን በአላህ የካዱትን ለጦር ሲጓዙ ባገኛቹኋቸው ጊዜ ጀርባዎችን አታዙሩላቸው::"},{"id":16,"translation":"16. ያን ጊዜ ለግድያ ለመዘዋወር ወይም ወደ ሰራዊት ለመቀላቀል ሳይሆን ጀርባውን የሚያዞርላቸው ሰው ሁሉ ከአላህ የሆነን ቁጣ አትርፏል። መኖሪያዉም ገሀነም ናት:: የገሀነም መመለሻነትም ከፋ!"},{"id":17,"translation":"17. እናንተ አልገደላችኋቸዉም:: ግን አላህ ገደላቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጭብጥን አፈር በወረወርክም ጊዜ አንተ አልወረወርክም:: ግን አላህ ወረወረ። አማኞችን ሁሉ ከእርሱ የሆነን መልካም ፈተናን ለመፈተን ይህንን አደረገ። አላህም ሁሉን ሰሚ፤ ሁሉንም አዋቂ ነውና::"},{"id":18,"translation":"18. ይህ ከአላህ የተቸረ ዕውነት ነው:: አላህ የከሓዲያንን ሁሉ ተንኮል አድካሚ ነውና::"},{"id":19,"translation":"19. (ከሓዲያን ሆይ!) ፍትሕን ብትጠይቁ ፍትሁ በእርግጥ መጥቶላችኋል:: ክሕደትና መዋጋታችሁን ብትከለከሉም እርሱ ለእናንተ የተሻለ ነው:: ወደ መጋደል ብትመለሱም እንመለሳለን:: ሰራዊታችሁ ብትበዛም እንኳ ለእናንተ ምንም አትጠቅማችሁም:: አላህ ሁልጊዜም ከትክክለኛ አማኞች ጋር ነውና::"},{"id":20,"translation":"20. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ:: እናንተም እየሰማችሁ ከእርሱ አትሽሹ::"},{"id":21,"translation":"21. እንደነዚያም የማይሰሙ ሲሆኑ ሰማን እንዳሉትም አትሁኑ::"},{"id":22,"translation":"22. ከተንቀሳቃሾች ፍጡራን ሁሉ አላህ ዘንድ መጥፎዎች ማለት እነዚያ ሐቅን የማይሰሙ ደንቆሮዎቹ፣ እውነትን የማይናገሩና እውነታን የማያስተውሉት ናቸው::"},{"id":23,"translation":"23. በውስጣቸው ደግ መኖሩን አላህ ባወቀ ኖሮ የመረዳትን መስማት ያሰማቸው ነበር:: ደግ የሌለባቸው መሆኑን እያወቀ ባሰማቸዉም ኖሮ እነርሱ እውነትን የተዉ ሆነው በሸሹ ነበር።"},{"id":24,"translation":"24. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! (መልዕክተኛው) ህያው ወደ የሚያደርጋችሁ (እምነት) በጠራችሁ ጊዜ ለአላህና ለመልዕክተኛው ታዘዙ:: አላህ በሰውየውና በልቡ መካከል የሚጋርድ መሆኑንና ወደ እርሱም የምትሰበሰቡ መሆናችሁንም እወቁ::"},{"id":25,"translation":"25. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከናንተ መካከል እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትጎዳን ፈተና ተጠንቀቁ:: አላህ ቅጣቱ ብርቱ መሆኑንም እወቁ::"},{"id":26,"translation":"26. (ሙስሊሞች ሆይ!) እናንተ በምድር ላይ የተናቃችሁ ጥቂቶች ሆናችሁ ሳላችሁ ሰዎች ሊነጥቋችሁ የምትፈሩ ስትሆኑ ያስጠጋችሁን፤ በእርዳታዉም ያበረታችሁን፤ ከመልካሞች ሲሳዮችም ታመሰግኑ ዘንድ የሰጣችሁን አላህን አስታውሱ::"},{"id":27,"translation":"27. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልዕክተኛውን አትካዱ:: አደራዎቻችሁንም እያወቃችሁ አትካዱ::"},{"id":28,"translation":"28. ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ለፈተና ብቻ መሆናቸውንና አላህ ዘንድ ታላቅ ምንዳ ያለ መሆኑን ዕወቁ።"},{"id":29,"translation":"29. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብትፈሩ የእውነት መለያ ብርሃንን ያደርግላችኋል:: ክፉ ሥራዎቻችሁንም ከናንተ ላይ ያብስላችኋል:: እናንተንም ይምርላችኃል:: አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና::"},{"id":30,"translation":"30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ የካዱ ሰዎች ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም ከመካ ሊያስወጡህ ባንተ ላይ ባሴሩብህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ያሴራሉም:: አላህም ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል:: አላህ ግን ከሴረኞቹ ሁሉ በላይ ነውና::"},{"id":31,"translation":"31. አናቅጻችን በነርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜም: «በእርግጥ ሰምተናል። በሻን ኖሮ የዚህን አባባል ተመሳሳይ ባልን ነበር:: ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም።» ይላሉ።"},{"id":32,"translation":"32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታችን ሆይ! ይህ እርሱ ካንተ ዘንድ የተወረደ እውነት እንደሆነ በእኛ ላይ ከሰማይ ድንጋዮችን አዝንብብን ወይም አሳማሚ ቅጣትን አምጣብን።» ባሉጊዜ (የሆነውን አስታውስ)።"},{"id":33,"translation":"33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ በመካከላቸው እያለህ አላህ የሚቀጣቸው አይደለም። እነርሱም ምሕረትን የሚለምኑት ሲሆኑ አላህ የሚቀጣቸው አይደለም።"},{"id":34,"translation":"34. እነርሱ ከተከበረው መስጊድ የሚከለክሉ ሲሆኑ አላህ የማይቀጣቸው ለመሆኑ ለእነርሱ ምን ዋስትና አላቸው? የቤቱ ጠባቂዎቹ አልነበሩም:: ጠባቂዎቹም ክሕደትን ተጠንቃቂዎቹ እንጂ ሌሎቹ አይደሉም:: ግን አብዛኛዎቹ አያውቁም::"},{"id":35,"translation":"35. በከዕባ ውስጥ ስግደታቸውም ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም። «ትክዱት በነበራችሁትም ነገር ቅጣትን ቅመሱ» (ይባላሉ)::"},{"id":36,"translation":"36. እነዚያ የካዱት ከአላህ መንገድ ሊከለክሉ ገንዘቦቻቸውን ያወጣሉ:: በእርግጥም ያወጡታል:: ከዚያ ግን በእነርሱ ላይ ጸጸት ይሆንባቸዋል:: ከዚያም ይሸነፋሉ:: እነዚያም የካዱት ሁሉ ወደ ገሀነም ይሰበሰባሉ::"},{"id":37,"translation":"37. አላህ መጥፎውን ነገር ከመልካሙ ሊለይ መጥፎውንም ከፊሉን በከፊሉ ላይ ሊያደርግና በአንድ ላይ ሊያነባብረው በገሀነም ውስጥም ሊያደርገው (ይሰበሰባሉ):: እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው::"},{"id":38,"translation":"38. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያ በአላህ ለካዱት ቢከለከሉ ለእነርሱ በእርግጥ ያለፈውን ሥራ ምሕረት እንደሚደረግላቸው፤ ወደ መጋደል ቢመለሱም (እንደምናጠፋቸው ንገራቸው)። የቀድሞዎቹ ሕዝቦች ልማድ በእርግጥ አልፏልና።"},{"id":39,"translation":"39. ሁከት እስከሚጠፋና ሃይማኖት ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚሆንም ድረስ ተጋደሏቸው:: ቢከለከሉም አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው::"},{"id":40,"translation":"40. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከእምነት ቢዞሩም አላህ ረዳታችሁ መሆኑን እወቁ:: እርሱ ምን ያምር ጠባቂ! ምን ያምርም ረዳት ነው!"},{"id":41,"translation":"41.(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከማንኛዉም ነገር በጦርነት ከካሓዲያን የማረካችሁትም ሁሉ አንድ አምስተኛው ለአላህና ለመልዕክተኛው፤ ለነብዩ የዝምድና ባለቤቶች፤ ለየቲሞች፤ ለሚስኪኖች፤ ለመንገደኞችም የተገባ መሆኑን እወቁ:: በአላህና በዚያም እውነትና ውሸት በተለየበት ቀን ሁለቱ ቡድኖች በተገናኙበት (በበድር) ቀን ባገልጋያችን ላይ ባወረድነውም የምታምኑ እንደ ሆናችሁ ይህንን እወቁ:: አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።"},{"id":42,"translation":"42. (ሙስሊሞች ሆይ!) እናንተ በቅርቢቱ ዳርቻ ሁናችሁ እነርሱ ደግሞ በሩቂቱ ዳርቻ ሆነው የነጋዴዎቹም ቡድን ከናንተ በታች ሲሆኑ በሰፈራችሁ ጊዜ ያደረግንላችሁን አስታውሱ:: በተቃጠራችሁም ኖሮ ግን በቀጠሮው በተለያያችሁ ነበር:: ግን አላህ ሊሠራው የሚገባውን ነገር ሊፈጽምና የሚጠፋም ከአስረጅ መድረስ በኋላ እንዲጠፋ፤ ሕያው የሚሆንም ከአስረጅ መድረስ በኋላ ሕያው እንዲሆን ያለቀጠሮ አጋጠማችሁ:: አላህ በእርግጥ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነውና::"},{"id":43,"translation":"43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሕልምህ እነርሱን ጥቂት አድርጎ ባሳየህ ጊዜ አስታውስ:: እነርሱን ብዙ አድርጎ ባሳየህም ኖሮ በፈራችሁና በነገሩ በተጨቃጨቃችሁ ነበር ግን አላህ አዳናችሁ:: እርሱ በደረቶች ውስጥ ያለን ሁሉ አዋቂ ነውና::"},{"id":44,"translation":"44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህም ሊሠራው የሚገባን ነገር ይፈጽም ዘንድ በተጋጠማችሁ ጊዜ እነርሱን በዓይኖቻችሁ ጥቂት አድርጎ ያሳያችሁንና በዓይኖቻቸውም ላይ ያሳነሳችሁን (አስታውሱ)፡፡ ነገሮቹም ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ፡፡"},{"id":45,"translation":"45. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሰራዊትን በገጠማችሁ ጊዜ እርጉ (መክቱ):: አላህንም በብዙው አውሱ:: በእርግጥ ትድናላችሁና::"},{"id":46,"translation":"46. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ :: አትጨቃጨቁም ትፈራላችሁና ኃይላችሁም ትሄዳለችና:: ታገሡም አላህ በእርዳታው ከትዕግሥተኞች ጋር ነውና::"},{"id":47,"translation":"47. እንደ እነዚያ ለትዕቢትና ለሰዎች ይዩልኝ ሲሉ ከአላህም መንገድ ለማገድ ከሀገራቸው እንደወጡት ሰዎች አትሁኑ:: አላህ በሚሠሩት ሁሉ በእውቀቱ ከባቢ ነውና::"},{"id":48,"translation":"48. ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ባሳመረላቸውና «ዛሬ ለእናንተ ከሰዎች አሸናፊ የላችሁም:: እኔም ለእናንተ ረዳት ነኝ።» ባለ ጊዜም (የሆነውን አስታውስ):: ሁለቱ ቡድኖችም በተያዩ ጊዜ ወደኋላው አፈገፈገ:: «እኔ ከናንተ ንጹህ ነኝ:: እኔ እናንተ የማታዩትን አያለሁ:: እኔ አላህን እፈራለሁ:: አላህም ቅጣተ ብርቱ ነው።» አላቸው::"},{"id":49,"translation":"49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስመሳዮችና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ሰዎች «እነዚህን ሙስሊሞች ሃይማኖታቸው አታለላቸው።» ባሉ ጊዜ (የነበረውን አስታውስ):: በአላህ ላይ የሚጠጋ (ሁልጊዜም ያሸንፋል):: አላህ ሁሉንም አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":50,"translation":"50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም በአላህ የካዱትን ሰዎች መላዕክት ፊቶቻቸውንና ጀርቦቻቸውን እየመቱ «የቃጠሎን ስቃይ ቅመሱ።» እያሉ በሚገድሏቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር)::"},{"id":51,"translation":"51. «ይህ እጆቻችሁ ባስቀደሙት ምክንያት አላህ ለባሮቹ በዳይ ባለመሆኑ ነው።» ይባላሉ።"},{"id":52,"translation":"52. የእነዚያ ሰዎች ልማድ እንደ ፈርዖን ቤተሰብና እንደነዚያም ከእነርሱ በፊት እንደ ነበሩት ህዝቦች ልማድ ነው:: በአላህ አናቅጽ ካዱ:: አላህም በኃጢአቶቻቸው ያዛቸው:: አላህ ሀይለኛና ቅጣተ ብርቱ ነውና::"},{"id":53,"translation":"53. ይህ ቅጣት አላህ በሕዝቦች ላይ የለገሰውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን ነገር እስከሚለውጡ ድረስ የማይለውጥ በመሆኑ ምክንያት ነው:: አላህም ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነውና::"},{"id":54,"translation":"54. እንደ ፈርዖን ቤተሰቦችና እንደእነዚያ ከእነርሱ በፊት እንደ ነበሩት ልማድ (እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥባቸዉም)። በጌታቸው ታዓምራት አስተባበሉና በኃጢአቶቻቸው አጠፋናቸው:: የፈርዖንን ቤተሰቦች አስመጥናቸው:: ሁሉም በዳዮች ነበሩና::"},{"id":55,"translation":"55. ከሚንቀሳቀሱ እንስሳዎች ሁሉ አላህ ዘንድ ይበልጥ ክፉዎቹ እነዚያ የካዱት ሰዎች ናቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያምኑም።"},{"id":56,"translation":"56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ከእነርሱ ቃል ኪዳን የያዝክባቸውና ከዚያም በየጊዜው ቃል ኪዳናቸውን የሚያፈርሱ ናቸው:: እነርሱም አይጠነቀቁም::"},{"id":57,"translation":"57. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጦር ላይ ብታገኛቸው በእነርሱ ቅጣት ምክንያት ሌሎቹ ከሓዲያን ይገሠጡ ዘንድ ከኋላቸው ያሉትን በትንባቸው::"},{"id":58,"translation":"58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሕዝቦችም በኩል ክህደትን ብትፈራ የቃል ኪዳኑን መፍረስ በማወቅ በኩል ተመሳሳይ ሆናችሁ ቃል ኪዳናቸውን ወደ እነርሱ ጣልላቸው:: አላህ ከዳተኞችን ሁሉ አይወድምና::"},{"id":59,"translation":"59. እነዚያም የካዱት ከአላህ ቅጣት ያመለጡ መሆናቸውን አያስቡ:: እነርሱ አያቅቱምና (አያሸንፉምና)::"},{"id":60,"translation":"60. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ለእነርሱ ከማንኛውም ኃይልና ከታጀቡ ፈረሶች የቻላችሁትን ሁሉ በእርሱ የአላህን ጠላትና ጠላታችሁን ሌሎችንም ከእነርሱ በስተቀር ያሉትን የማታውቋቸውን አላህ ብቻ የሚያውቃቸውን አስመሳዮች የምታሸብሩበት ስትሆኑ አዘጋጁላቸው:: ከማንኛዉም ነገር በአላህ መንገድ የምትለግሱት ምንዳው ወደ እናንተ በሙሉ ይሰጣል:: እናንተ ቅንጣት አትበደሉም::"},{"id":61,"translation":"61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ዕርቅ ቢያዘነብሉ አንተም ወደ እርቁ ተዘንበልና በአላህ ላይ ብቻ ተመካ:: እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን አዋቂው ነውና።"},{"id":62,"translation":"62. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሊያታልሉህ ቢፈልጉ አላህ በቂህ ነው:: እርሱ ያ በእርዳታውና በምዕምናን ያበረታህ ነውና::"},{"id":63,"translation":"63. በልቦቻቸውም መካከል ያስማማ ነው፡፡ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በምድር ያለውን ሁሉ ሀብት ብትለገስ ኖሮ እንኳን በልቦቻቸው መካከል ባላስማማህ ነበር:: ግን አላህ በመካከላቸው አስማማ:: እርሱ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":64,"translation":"64. አንተ ነብይ ሆይ! ለሁሉ ነገር በቂህ አላህ ነው:: ለተከተሉህም ምዕምናን በቂያቸው አላህ ነው::"},{"id":65,"translation":"65. አንተ ነብይ ሆይ! አማኞችን ጠላቶቻቸውን በመዋጋት ላይ አደፋፍራቸው:: ከናንተ ውስጥ ሃያ ታጋሾች ቢኖሩ ሁለት መቶን ያሸንፋሉ:: ከናንተም መካከል መቶ ሰዎች ቢኖሩ ከእነዚያ ከካዱት ሕዝቦች መካከል አንድ ሺሕን ያሸንፋሉ:: ምክንያቱም እነርሱ የማይገነዘቡ ህዝቦች ናቸዉና::"},{"id":66,"translation":"66. አሁን አላህ ከናንተ ላይ አቀለለላችሁ:: በእናንተ ውስጥም ድክመት መኖሩን አወቀ:: ስለዚህ ከናንተ መካካል መቶ ታጋሾች ቢኖሩ ሁለት መቶን ያሸንፋሉ:: ከናንተም አንድ ሺህ ቢኖሩ በአላህ ፍቃድ ሁለት ሺዎችን ያሸንፋሉ:: አላህ ከታጋሾቹ ጋር ነዉና::"},{"id":67,"translation":"67. ለነብይ በምድር ላይ ጠላቶቹን እስኪያደክም ድረስ ለእርሱ ምረኮኞች ሊኖሩት አይገባም:: (አማኞች ሆይ!) የቅርቢቱን ዓለም ጠፊ ጥቅም ትፈልጋላችሁ:: አላህ መጨረሻይቱን ይሻል:: አላህም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::"},{"id":68,"translation":"68. ከአላህ ያለፈ ውሳኔ ባልነበረ ኖሮ በወሰዳችሁት ቤዛ ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር::"},{"id":69,"translation":"69. (አማኞች ሆይ!) ያ! ከጠላት የማረካችሁትን ሀብት የተፈቀደና መልካም ሲሆን ብሉ:: አላህንም ፍሩ:: አላህም መሓሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":70,"translation":"70. አንተ ነብይ ሆይ! ከምርኮኞች መካከል በእጆቻችሁ ላሉት «አላህ በልቦቻቸው ውስጥ በጎን ነገር (እምነትን) ቢያውቅ ከተወሰደባችሁ የተሻለን ይሰጣችኋል:: ለእናንተም ይምራችኋል:: አላህም መሓሪና አዛኝ ነውና።» በላቸው።"},{"id":71,"translation":"71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሊክዱህ ቢፈልጉ ከዚህ በፊት አላህን በእርግጥ ከድተዋል:: እናም ከእነርሱ አስመችቶሃል:: አላህም ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::"},{"id":72,"translation":"72. እነዚያ በአላህ አምነው ለእርሱም ሲሉ ከሀገራቸው የተሰደዱ በአላህ መንገድ ላይም በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የታገሉ እና እነዚያም ስደተኞቹን ያስጠጉና የረዱ ሰዎች እነዚያ ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው:: እነዚያ አምነውም ያልተሰደዱ ሰዎች ደግሞ ለአላህ ብለው እስከሚሰደዱ ድረስ ከእነርሱ ምንም ዝምድና የላችሁም:: በሃይማኖት እርዳታን ቢፈልጉባችሁ በእናንተና በእነርሱ መካከል ቃል ኪዳን ባላችሁ ሕዝቦች ላይ ካልሆነ በስተቀር በእናንተ ላይ እነርሱን መርዳት አለባችሁ:: አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::"},{"id":73,"translation":"73. እነዚያም በአላህ የካዱ ሰዎች ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው:: (ከምዕምናን ጋር መረዳዳትን ከከሓዲያን መቆራረጥን) ባትሠሩት በምድር ላይ ሁከትና ታላቅ ጥፋት ይሆናል::"},{"id":74,"translation":"74. እነዚያ አምነው ለእርሱም ሲሉ የተሰደዱት፤ በአላህ መንገድ ላይም የታገሉ እና እነዚያም ያስጠጉና የረዱ እነዚያ ትክክለኛ አማኞች እነርሱው ናቸው:: ለእነርሱም ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አለላቸው::"},{"id":75,"translation":"75. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እነዚያ በኋላ ያመኑና ከሀገራቸው የተሰደዱ ከናንተም ጋር ሆነው የታገሉ እነዚያ ከናንተው ናቸው:: የዝምድናዎች ባለቤቶች በአላህ መጽሐፍ ከፊሎቻቸው ከከፊሉ ለመውረስ የተገቡ ናቸው። አላህ ሁሉን ነገር አዋቂ ነውና::"}]},{"id":9,"verses":[{"id":1,"translation":"1.(ሙስሊሞች ሆይ! ይህ) ከአላህና ከመልዕክተኛው ወደ እነዚያ ቃል ኪዳን ወደ ተጋባችኋቸው አጋሪዎች የሚደርስ የውል መሻሪያ መልዕክት ነው::"},{"id":2,"translation":"2. (ከሓዲያን ሆይ!) በምድር ላይ አራት ወሮችን ጸጥተኛ ስትሆኑ ተንቀሳቀሱ:: እናንተ ከአላህ ቅጣት የማታመልጡ መሆናችሁንና አላህ ከሓዲያንን አዋራጅ መሆኑንም እወቁ፡፡"},{"id":3,"translation":"3. (ይህ) ከአላህና ከመልዕክተኛው በታላቁ ሐጅ ቀን የወጣ አላህ እና መልዕክተኛው ከአጋሪዎቹ ንጹህ መሆናቸውን የሚገልፅ አዋጅ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከክህደት ብትጸጸቱ እርሱ ለእናንተ በላጭ ነው:: ከእምነት ብትሸሹ ግን እናንተ አላህን የማታቅቱት መሆናችሁን እወቁ በማለት ወደ ሰዎች የሚደርስ ማስታወቂያ ነው:: እነዚያን በአላህ የካዱትን ሰዎች በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው::"},{"id":4,"translation":"4. እነዚያ ከአጋሪዎቹ መካከል እነዚያ ቃል ኪዳን የተጋባችሁላቸውና ከዚያ ምንም ያላጎደሉባችሁ፤ በእናንተ ላይ ለማጥቃት አንድንም ያልተባበሩባችሁ ቃል ኪዳናቸውን እስከ ጊዜያቸው መጨረሻ ድረስ ሙሉላቸው:: አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና::"},{"id":5,"translation":"5. የተከበሩት ወሮች ባለቁ ጊዜ አጋሪዎቹን ባገኛችሁባቸው ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው:: ያዟቸዉም:: ክበቧቸዉም:: እነርሱንም ለመጠባበቅ ስትሉ በየኬላው ላይ ተቀመጡ:: ሆኖም ቢጸጸቱ፤ ሶላትን በደንቡ ቢሰግዱና ግዴታ የሆነባቸውን የዘካ ምጽዋትን በትክክል ከሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":6,"translation":"6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአጋሪዎች መካከል አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅህ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው:: ከዚያ ወደ ሰላም ማግኛው ስፍራ አድርሰው:: ይህም የሆነው እነርሱ የማያውቁ ህዝቦች በመሆናቸው ነው ::"},{"id":7,"translation":"7. ለአጋሪዎች ከአላህና ከመልዕክተኛው ዘንድ የሰላም ቃል ኪዳን እንዴት ይኖራቸዋል? እነዚያ በተከበረው መስጊድ ዘንድ ቃል ኪዳን የገባችሁላቸው ሰዎች ብቻ ሲቀሩ:: እነዚያማ በቃል ኪዳናቸው ለእናንተ ቀጥ እስካሉላችሁ ድረስ ለእርሱም በቃላችሁ ቀጥ በሉላቸው:: አላህ ጥንቁቆችን ሁሉ ይወዳልና::"},{"id":8,"translation":"8. በእናንተ ላይ ቢያይሉ ዝምድናንና ቃልኪዳንን የማይጠብቁ ሰዎች ሲሆኑ እንዴት ከአላህና ከመልዕክተኛው ዘንድ ቃልኪዳን ይኖራቸዋል? በአፎቻቸው ይሸነግሏችኋል:: ልቦቻቸው ግን እምቢ ይላሉ:: አብዛኞቻቸዉም አመጸኞች ናቸው::"},{"id":9,"translation":"9. በአላህ አናቅጽ ጥቂትን ዋጋ ገዙ:: እናም ከመንገዱም ሰዎችን አገዱ:: እነርሱ ይሰሩት የነበሩት ሥራም እጅግ በጣም ከፋ::"},{"id":10,"translation":"10. በትክክለኛ አማኞች ላይ ዝምድናንም ሆነ ቃል ኪዳንን አይጠብቁም:: ወሰን አላፊዎች ማለት እነርሱው ናቸው::"},{"id":11,"translation":"11. (ሙስሊሞች ሆይ!) ቢጸጸቱ፤ ሶላትንም ደንቡን አሟልተው ቢሰገዱና ግድ የሆነባቸውንም ዘካን በትክክል ቢሰጡ የእምነት ወንድሞቻችሁ ናቸው:: ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን እናብራራለን::"},{"id":12,"translation":"12. ከቃልኪዳናቸው በኋላ መሀላዎቻቸውን ካፈረሱና ሃይማኖታችሁን ካንቋሸሹ የክህደት መሪዎች ከክህደት ተግባራቸው ይከለከሉ ዘንድ ተዋጓቸው:: እነርሱ ምንም ቃልኪዳን የላቸዉምና::"},{"id":13,"translation":"13. እነዚያ መሀላዎቻቸውን ያፈረሱትን፤ መልዕክተኛውንም ከሀገር ለማውጣት ያሰቡትን ህዝቦች እነርሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ጦርነት የጀመሯችሁን ህዝቦች ሲሆኑ ለምን አትወጓቸዉም? ትፈሯቸዋላችሁን? ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ አላህን ይበልጥ ልትፈሩት የተገባው ነው::"},{"id":14,"translation":"14. (ሙስሊሞች ሆይ!) ተጋደሏቸው:: አላህ በእጆቻችሁ ያሰቃያቸዋል:: ያዋርዳቸዋልም:: በእነርሱም ላይ ይረዳችኋል:: የአማኝ ህዝቦችን ልቦችንም ያሽራል::"},{"id":15,"translation":"15. የልቦቻቸውንም ቁጭት ያስወግዳል:: አላህ ከሚፈልገው ሰው ላይ ጸጸትን ይቀበላል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":16,"translation":"16. አላህ ከመካከላችሁ በትክክል ለአላህ መስዋዕት የሚከፍሉትንና (የታገሉትንና) ከአላህ፣ ከመልዕክተኛውና ከትክክለኛ አማኞች በስተቀር አማካሪ ያልያዙትን ክፍሎች ለይቶ ሳያውቅ (ሳይገልጽ) የምትተዉ መሰላችሁን? አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ዉስጠ አዋቂ ነው::"},{"id":17,"translation":"17. አጋሪዎች በራሳቸው ላይ በክህደት የሚመሰክሩ ሲሆኑ የአላህን መስጊዶች ሊንከባከቡ አይገባቸዉም:: እነዚያ ሥራዎቻቸው የተበላሹና በአኼራም በእሳት ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::"},{"id":18,"translation":"18. የአላህን መስጊዶች የሚንከባከቡ ሰዎች በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመኑ፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው የሚሰግዱ፤ ግዴታ ምጽዋትን በትክክል የሚሰጡ፤ ከአላህ ሌላ ምንንም ያልፈሩ ሰዎች ብቻ ናቸው:: እንዲህ ያሉት ሰዎች ቀናዉን መስመር ከያዙት መሆናቸው ይከጀላልና::"},{"id":19,"translation":"19. ሰዎችን ማጠጣትንና የተከበረውን መስጊድ መንከባከብን፤ በአላህና በመጨረሻው ቀን እንዳመነና በአላህ መንገድም እንደታገለ ሰው እምነትና ትግል አደረጋችሁትን? በአላህ ዘንድ ፈጽሞ ሁለቱ ተግባሮች አይስተካከሉም:: አላህ በዳይ ህዝቦችን ሁሉ ወደ ቀጥተኛው መንገድ አይመራምና::"},{"id":20,"translation":"20. እነዚያ በአላህ ያመኑት ከየአገሮቻቸዉም የተሰደዱት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸዉም በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት አላህ ዘንድ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው:: ፍላጎታቸውን ያገኙ ማለትም እነርሱው ናቸው::"},{"id":21,"translation":"21. ጌታቸው ከእርሱ በሆነው እዝነትና ውዴታ፤ በውስጧ የማያቋርጥ መጠቀሚያ ባለባት ገነትም ያበስራቸዋል::"},{"id":22,"translation":"22. በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያበስራቸዋል:: አላህ እርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አለና::"},{"id":23,"translation":"23. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አባቶቻችሁንና ወንድሞቻችሁን ክህደትን ከእምነት አብልጠው ከወደዱ ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዟቸው:: ከናንተ መካከል እነርሱን ወዳጅ የሚያደርጓቸው ሁሉ በዳዮች ማለት እነርሱው ናቸው::"},{"id":24,"translation":"24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አባቶቻችሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁ፤ ወንድሞቻችሁ፤ ሚስቶቻችሁ ዘመዶቻችሁ፤ የሰበሰባችኋቸው ሀብቶች፤ መክሰሯን የምትፈሯት ንግድና የምትወዷቸው መኖሪያዎች በእናንተ ዘንድ ከአላህ፤ ከመልዕክተኛውና በእርሱ መንገድ ከመታገል ይበልጥ የተወደዱ ከሆኑ አላህ ጉዳዩን እስከሚያመጣ ድረስ ተጠባበቁ በላቸው:: አላህ አመጸኞች ህዝቦችን ሁሉ አይመራም::"},{"id":25,"translation":"25. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ በብዙ የጦር ሜዳዎች ላይ እገዛውን ለግሶላችኋል:: የሁነይንም ቀን ብዛታችሁ ባስደነቀቻችሁና ለእናንተም ብዛት ምንም ባልጠቀመቻችሁ ጊዜ ምድርም ከስፋቷ ጋር በጠበበቻችሁና ከዚያ ተሸናፊዎች ሆናችሁም በዞራችሁ ጊዜ ረዳችሁ::"},{"id":26,"translation":"26. ከዚያም አላህ እርጋታውን በመልዕክተኛውና በምዕመናኖች ላይ አወረደ:: ያላያችኋቸውንም ሰራዊት አወረደ:: እነዚያን የካዱትንም ሰዎች በመግደልና በመማረክ አሰቃየ:: ይህም የከሓዲያን ፍዳ ነው::"},{"id":27,"translation":"27. ከዚያም ከዚህ በኋላ አላህ ከሚፈልገው ሰው ላይ ጸጸትን ይቀበላል:: አላህ እጅግ መሀሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":28,"translation":"28. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው:: እናም ከዚህ ዓመታቸው በኋላ ወደ ተከበረው መስጊድ እንዳይቀርቡ። ድህነትንም ብትፈሩ አላህ ቢፈልግ ከችሮታው በእርግጥ ያከብራችኋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።"},{"id":29,"translation":"29. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከእነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡ ሰዎች መካከል እነዚያን በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑትን ክፍሎች አላህና መልዕክተኛው እርም ያደረጉትንም እርም የማያደርጉትን፤ እውነተኛውንም ሃይማኖት የማይቀበሉትን የተዋረዱ ሆነው ግብርን በእጆቻቸው እስከሚሰጡ ድረስ ተዋጓቸው::"},{"id":30,"translation":"30. አይሁድ «ኡዘይር የአላህ ልጅ ነው።» አሉ:: ክርስቲያኖችም «አል-መሲህ የአላህ ልጅ ነው።» አሉ:: ይህ በአፎቻቸው የሚናገሩት ጸያፍ ቃላቸው ነው:: የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የካዱትን (ሰዎች) ቃል ያመሳስላሉ:: አላህ ያጥፋቸው:: ከእውነት እንዴት ያፈነግጣሉ?"},{"id":31,"translation":"31. አይሁድና ክርስቲያኖች ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንዱን አምላክ አላህን ብቻ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲሆኑ ሊቃውንቶቻቸውን፤ መነኮሳቶቻቸውንና የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ:: ከእርሱ በስተቀር ትክክለኛ አምላክ የለም:: አላህ ግን ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው::"},{"id":32,"translation":"32. ከሓዲያን የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ:: እርሱ (አላህ) ከሓዲያን ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጂ ሌላን አይሻም::"},{"id":33,"translation":"33. አላህ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ መልዕክተኛው ሙሓመድን በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ አድርጎ የላከው ብቸኛ አምላክ ነው።"},{"id":34,"translation":"34. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሊቃውንትና ከመነኮሳት ብዙዎቹ የሰዎችን ገንዘቦች በውሸትም ይበላሉ:: ከአላህም መንገድም ሰዎችን ያግዳሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም ወርቅንና ብርን የሚያደልቡትን በአላህም መንገድ ላይ የማያወጧቸውን ሰዎች በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው::"},{"id":35,"translation":"35. (በብሩና በወርቁ) ላይ በገሀነም እሳት ውስጥ በሚግሉበትና ግንባሮቻቸውም፣ ጎኖቻቸውም፣ ጀርቦቻቸውም በእርሱ በሚተኮሱበት ቀን አሳማሚ በሆነ ቅጣት አብስራቸው:: «ይህ ለነፍሶቻችሁ ያደለባችሁት ነው:: ታደልቡት የነበራችሁትንም ቅመሱ።» ይባላሉ::"},{"id":36,"translation":"36. የወራት ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን አስራ ሁለት ወር ብቻ ነው:: ከእነርሱም መካከል አራቱ የተከበሩ ወሮች ናቸው:: ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው:: በእነርሱ ውስጥም (ክብሮቻቸውን በመጣስ) ነፍሶቻችሁን አትበድሉ:: አጋሪዎችንም በአንድ ላይ ሆነው እንደሚጋደሏችሁ በአንድ ላይ ሆናችሁ ተጋደሏቸው:: አላህ በእርዳታው እርሱኑ ከሚፈሩት ጋር መሆኑን እወቁ::"},{"id":37,"translation":"37. የአንዱን ወር ክብር ወደ ሌላው ማዘግየት በክህደት ላይ ክህደትን መጨመር ነው:: በዚህ ተግባር ላይ እነዚያ በአላህ የካዱት (ሰዎች) ይሳሳቱበታል:: በአንደኛው ዓመት የተፈቀደ ያደርጉታል:: በሌላው ዓመት ደግሞ ያወግዙታል:: ይህም አላህ ያከበራቸውን ወሮች ቁጥር ሊሞሉበትና አላህ እርም ያደረገውን ደግሞ የተፈቀደ ሊያደርጉበት ነው:: መጥፎ ሥራዎቻቸው ለእነርሱ ተዋበላቸው:: አላህ ከሓዲያን ህዝቦችን ወደ ቀናው መንገድ አይመራም::"},{"id":38,"translation":"38. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! «በአላህ መንገድ ለመታገል ዝመቱ።» በተባላችሁ ጊዜ ወደ ምድር የምትወዘፉት ለምንድን ነው? የቅርቢቱን ህይወት ከመጨረሻይቱ ህይወት ይበልጥ ወደዳችሁን? የቅርቢቱ ህይወት ጥቅም ከመጨረሻይቱ ህይወት አንፃር ጥቂት እንጂ ምንም አይደለም::"},{"id":39,"translation":"39. ( አማኞች ሆይ!) ለዘመቻ ባትወጡ አላህ አሳማሚ ቅጣት ይቀጣችኋል:: ከናንተ ሌላ የሆኑን ህዝቦችም ይለውጣል:: አላህን በምንም አትጎዱትምም:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::"},{"id":40,"translation":"40. (ሙስሊሞች ሆይ!) ነብዩ ሙሐመድን ባትረዱት እነዚያ በአላህ የካዱት ህዝቦች የሁለት ሰዎች ሁለተኛ ሆኖ ከመካ ባስወጡት ጊዜ አላህ ረድቶታል:: ሁለቱም በዋሻው ሳሉ ለጓደኛው «አትዘን አላህ ከእኛ ጋር ነውና» ባለ ጊዜ አላህ እርጋታውን በእርሱ ላይ አወረደ:: ባላያችኋቸዉም ሰራዊት አበረታው:: የእነዚያን በአላህ የካዱትን ሰዎች ቃል የበታች አደረገ:: የአላህ ቃል ግን የበላይ ነው:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":41,"translation":"41.(አማኞች ሆይ!) ቀላሎችም ከባዶችም ኾናችሁ ዝመቱ:: በአላህ መንገድ በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ ታገሉ :: ይህ ተግባር የምታውቁ ከሆናችሁ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው::"},{"id":42,"translation":"42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጠራህባቸው ነገር ቅርብ ጥቅምና መካከለኛ ጉዞ በሆነ ኖሮ በተከተሉህ ነበር:: ግን በእነርሱ ላይ መንገዲቱ ራቀችባቸው:: «በቻልንም ኖሮ ከናንተ ጋር በወጣን ነበር» ሲሉ በአላህ ይምላሉ:: እራሳቸውን ለጥፋት (በውሸት) ይዳርጋሉ :: አላህ እነርሱ ውሸታሞች መሆናቸውን ያውቃል::"},{"id":43,"translation":"43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) አላህ ይቅር ብሎሀል:: እነዚያ እውነተኞቹ እስከሚገለጹልህና ውሸታሞቹን ለይተህ እስከምታውቅ ድረስ ለእነርሱ ከዘመቻ እንዲቀሩ ለምን ፈቀድክላቸው?"},{"id":44,"translation":"44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው ከመታገላቸው ለመቅረት ፈቃድን አይጠይቁህም:: አላህም በትክክል የሚፈሩትን ሰዎች ሁሉ አዋቂ ነው::"},{"id":45,"translation":"45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ፈቃድ የሚጠይቁህ እነዚያ በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑት፤ ልቦቻቸው የተጠራጠሩት ሰዎች ብቻ ናቸው:: እነርሱም በጥርጣሬያቸው ውስጥ ይዋልላሉ::"},{"id":46,"translation":"46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ዘመቻ መውጣት ባሰቡ ኖሮ ለእርሱ ዝግጅትን ባሰናዱ ነበር:: ግን አላህ ለመውጣት እንቅስቃሴያቸውን ጠላውና አሰነፋቸው:: «ከተቀማጮቹ ጋር ተቀመጡ።» ተባሉም::"},{"id":47,"translation":"47. (አማኞች ሆይ!) ከናንተ ጋር በወጡ ኖሮ ጥፋትን እንጂ አይጨምሩላችሁም ነበር:: ሁከትንም የሚፈልጉላችሁ ሲሆኑ በመካከላችሁ ነገርን በማሳበቅ ይቻኮሉ ነበር:: በእናንተ ውስጥ ለእነርሱ አዳማጮች አሏቸው:: አላህም በዳዮችን አዋቂ ነው::"},{"id":48,"translation":"48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ ጠይዎች ሲኾኑ እውነቱ እስከመጣና የአላህም ትዕዛዝ እስከተገለጸ ድረስ ከዚህ በፊት ሁከትን በእርግጥ ፈለጉ፡፡ ነገሮችንም ሁሉ አገላበጡልህ፡፡"},{"id":49,"translation":"49. ከእነርሱም ውስጥ «ፍቀድልኝ አትሞክረኝ» የሚል ሰው አለ። (ሙስሊሞች) አስተውሉ! እነኝህ ሰዎች በመከራ ውስጥ ወደቁ:: ገሀነም ከሓዲያንን ከባቢ ናት::"},{"id":50,"translation":"50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መልካም ነገር ቢያገኝህ ያስከፋቸዋል:: መከራ ቢያገኝህ ግን «ፊቱንም ይህን ፈርተን የግል ጥንቃቄያችንን ይዘናል።» ይላሉ። ተደሳቾች ሆነዉም ይሸሻሉ::"},{"id":51,"translation":"51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ለእኛ የጻፈልን እንጂ ሌላ አይነካንም:: እርሱ ረዳታችን ነው:: ምዕምናን በአላህ ላይ ብቻ ይመኩ።» በላቸው::"},{"id":52,"translation":"52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእኛ ላይ ከሁለቱ መልካሞች አንደኛዋን እንጂ ሌላን ትጠባበቃላችሁን? እኛም አላህ ከእርሱ በሆነው ቅጣት ወይም በእጆቻችን የሚያጠፋችሁ መሆኑን በእናንተ ላይ እንጠባበቃለን:: ተጠባበቁ:: እኛም ከናንተው ጋር ተጠባባቂዎች ነንና።» በላቸው::"},{"id":53,"translation":"53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ወዳችሁም ሆነ ጠልታችሁ ለግሱ ከናንተ ተቀባይ የላችሁም:: እናንተ አመጸኞች ህዝቦች ናችሁና።» በላቸው::"},{"id":54,"translation":"54. ልግስናዎቻቸውን ከእነርሱ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ያደረገው በአላህና በመልዕክተኛው የካዱ፤ ሶላትንም ስልቹዎች ሆነው እንጂ የማይሰግዱ፤ እነርሱም ጠይዎች ሆነው እንጂ የማይሰጡ ከመሆናቸው በስተቀር ሌላ ነገር አልከለከላቸዉም::"},{"id":55,"translation":"55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው አይድነቁህ:: አላህ የሚሻው በቅርቢቱ ህይወት በእነርሱ (በገንዘቦቻቸውና በልጆቻቸው) ሊቀጣቸው ነፍሶቻቸዉም ከሓዲያን ሆነው ሊሞቱ ብቻ ነውና::"},{"id":56,"translation":"56. እነርሱም ከናንተ ጋር ለመሆናቸው በአላህ ይምላሉ:: እነርሱ ግን ከናንተ ጋር አይደሉም:: ይልቁንም እነርሱ አጋሪዎችን ያገኘው ነገር እንዳያገኛቸው የሚፈሩ ህዝቦች ናቸው::"},{"id":57,"translation":"57. (ሙስሊሞች ሆይ!) መጠጊያ ወይም መሸሸጊያ ዋሻዎችን ወይም መግቢያ ቀዳዳዎችን ባገኙ ኖሮ በፍጥነት ወደ እርሱ በሸሹ ነበር::"},{"id":58,"translation":"58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል በምጽዋቶች ክፍፍል ዙሪያ የሚዘልፉህ ሰዎች አሉ:: ከእርሷም የሚሹትን ያህል ቢሰጡ ይደሰታሉ:: ከእርሷ ምንም ካልተሰጣቸው ግን ይጠላሉ::"},{"id":59,"translation":"59. እነርሱም አላህና መልእክተኛው የሰጣቸውን በወደዱ፤ «አላህ በቂያችን ነው አላህ ከችሮታው በእርግጥ ይሰጠናል፣ መልክተኛውም (ይሰጠናል) እኛ ወደ አላህ ከጃዮች ነን።» ባሉ ኖሮ ለነርሱ በተሸላቸው ነበር::"},{"id":60,"translation":"60. ግዴታ ዘካን የሚከፈሉት ለድሆች፤ ለችግረኞች፤ በእርሷም ላይ ለሚሰሩ ሠራተኞች፤ ልቦቻቸው በኢስላም ለሚለማመዱት ወገኖች፤ ጫንቃዎችን (ባሪያዎች) ነጻ ለማውጣት፤ ባለ እዳ ለሆኑት፤ በአላህ መንገድም ለሚሰሩና (ስንቅ ላለቀበት) መንገደኛ ብቻ ነው:: ይህ ስርአት ከአላህ የተደነገገ ግዴታ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።"},{"id":61,"translation":"61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) ከአስመሳዮች መካከል ነብዩ ሙሐመድን የሚያስቸግሩና «እርሱ እኮ ወሬ ሰሚ ነው።» የሚሉ አሉ። «ለእናንተ የበጎ ወሬ ሰሚ ነው:: በአላህ ያምናል:: አማኞችንም ያምናቸዋል:: ከናንተ መካከል ለእነዚያ በአላህ ላመኑት ሰዎችም እዝነት ነው።» በላቸው:: እነዚያ የአላህን መልዕክተኛ የሚያስቸግሩ ሰዎች ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።"},{"id":62,"translation":"62. አላህንና መልዕክተኛውን ሊያስወድዱ ሲገባቸው እናንተን ሊያስወድዷችሁ ዘንድ በአላህ ይምሉላችኋል። ትክክለኛ አማኞች ከሆኑ (ግን አላህንና መልዕክተኛው ሊያስወድዱ ይገባቸዋል)::"},{"id":63,"translation":"63. አላህንና መልዕክተኛውን የሚከራከር ሰው ሁሉ በውስጡ ዘውታሪ ሲሆን የተዘጋጀችለት የገሀነም እሳት መሆኑን አያውቁምን? ይህ ደግሞ ታላቅ ውርደት ነው::"},{"id":64,"translation":"64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስመሳዮች በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ የሚነግራቸው ምዕራፍ በእነርሱ ላይ መወረዱን ዘወትር ይፈራሉ:: «ተሳለቁ:: አላህ የምትፈሩትን ነገር ሁሉ ገላጭ ነው።» በላቸው::"},{"id":65,"translation":"65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብትጠይቃቸው «እኛ የምንዘባርቅና የምንጫወት ሰዎች ብቻ ነበርን።» ይላሉ:: «በአላህ፤ በአናቅጹና በመልዕክተኛው ላይ ትቀልዱ ነበራችሁን?» በላቸው::"},{"id":66,"translation":"66. (አስመሳዮች ሆይ!) አታመካኙ ከእምነታችሁ በኋላ በእርግጥ ክዳችኋልና:: ከናንተ አንዷን ቡድን ብንምር የሌላዋን ቡድን አባላት ግን ኃጢአተኞች በመሆናቸው እንቀጣለን::"},{"id":67,"translation":"67. የወንድ አስመሳዮችና የሴት አስመሳዮች ከፊሎቻቸው ከከፊሉ ናቸው:: በመጥፎ ነገር ያዛሉ:: ከደግ ነገርም ይከለክላሉ:: እጆቻቸውን ከልግስና ይሰበስባሉ:: ለአላህ መታዘዝን ረሱ (ተዉ):: ስለዚህ እርሱም ተዋቸው:: አስመሳዮቹ አመጸኞች ማለት እነርሱው ናቸው::"},{"id":68,"translation":"68. የወንድ አስመሳዮችንና የሴት አስመሳዮችን እንዲሁም ከሓዲያንን የገሀነምን እሳት በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ አላህ ቃል ገብቶላቸዋል:: እርሷ በቂያቸው ናት:: አላህ ረግሟቸዋል:: ለእነርሱም ዘውታሪ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":69,"translation":"69. (አስመሳዮች ሆይ!) ተግባራችሁ ልክ እንደእነዚያ ከናንተ በፊት እንደነበሩት ህዝቦች ነው:: ከናንተ ይበልጥ በሃይል የበረቱ በገንዘብና በልጆችም ከናንተ ይበልጥ የበዙ ነበሩ:: በእድላቸው ተጠቀሙ:: እነዚያም ከእናንተ በፊት የነበሩት በዕድላቸው እንደተጠቀሙ በዕድላችሁ ተጠቀማችሁ፡፡ እንደዘባረቁትም ዘባረቃችሁ:: እነዚያ ስራዎቻቸው በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ተበላሸ:: ከሳሪዎቹም ማለት እነርሱው ናቸው::"},{"id":70,"translation":"70. የእነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት የኑህ፤ የዓድ፤ የሰሙድ፤ የኢብራሂም ህዝቦች፤ የመድየን ባለቤቶችና የተገልባጮቹም ከተሞች ታሪክ አልመጣላቸዉምን? መልዕክተኞቻቸው ግልጽ ተዓምራትን አመጡላቸው:: አላህ የሚበድላቸው አልነበረም:: ግን በራሳቸው ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ::"},{"id":71,"translation":"71. ወንድ አማኞችና ሴት አማኞች ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው:: በደግ ነገር ያዝዛሉ:: ከክፉም ነገር ይከለክላሉ:: ሶላትን ይሰግዳሉ:: ዘካን ይሰጣሉ:: አላህንና መልዕክተኛውን ይታዘዛሉ:: እነዚያን አላህ በእርግጥ ያዝንላቸዋል:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":72,"translation":"72. አላህ የወንድ ትክክለኛ አማኞችንና የሴት ትክክለኛ አማኞችን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በመኖሪያ ገነቶችም ውስጥ መልካም መኖሪያ ቤቶችን ቃል ገብቶላቸዋል:: ከአላህ የሆነው ውዴታ ደግሞ ከሁሉ የበለጠ ነው:: ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው::"},{"id":73,"translation":"73. አንተ ነብዩ ሆይ! ከሓዲያንንና አስመሳዮችን ታገል:: በእነርሱ ላይም ጨክን:: መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት:: መመለሻይቱም በጣም ከፋች::"},{"id":74,"translation":"74. ምንም ያላሉ ለመሆናቸው በአላህ ይምላሉ:: ግን የክህደትን ቃል በእርግጥ አሉ:: ከእስልምናቸዉም በኋላ ካዱ:: ያላገኙትንም ነገር አሰቡ:: አላህና መልዕክተኛው ከችሮታው ያከበራቸው መሆኑን እንጂ ሌላን አልጠሉም:: ቢጸጸቱም ለእነርሱ የተሻለ ይሆናል:: ቢሸሹም አላህ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም አሳማሚን ቅጣት ይቀጣቸዋል:: ለእነርሱም በምድር ውስጥ ምንም ወዳጅና ረዳት የላቸዉም::"},{"id":75,"translation":"75. ከእነርሱም መካከል አላህን «ከችሮታው ቢሰጠን በእርግጥ እንመጸውታለን::በእርግጥ ከመልካሞችም እንሆናለን።» ሲል ቃል የገባ አለ::"},{"id":76,"translation":"76. ከዚያም ከችሮታዉም በሰጣቸው ጊዜ ሰሰቱ:: እነርሱ ቃል ኪዳናቸውን የተው ሆነዉም ዞሩ::"},{"id":77,"translation":"77. ለአላህ ቃል የገቡትን በማፍረሳቸውና ይዋሹትም በነበሩት ውሸት ምክንያት እስከሚገናኙት ቀን ድረስ ንፍቅናን በልቦቻቻው አስከተላቸው::"},{"id":78,"translation":"78. (አስመሳዮችን) አላህ ምስጢራቸውንና ውይይታቸውን የሚያውቅ መሆኑንና አላህም ሩቅ ነገሮችን ሁሉ በጣም አዋቂ መሆኑን አያውቁምን?"},{"id":79,"translation":"79. እነዚያ ከምዕምናን በምጽዋቶች ፈቃደኛ የሆኑትን የችሎታቸውን ያክል እንጂ የማያገኙትን ሰዎች የሚያነውሩና በእነርሱ የሚሳለቁ ሰዎች ሁሉ አላህ ከእነርሱ ይሳለቅባቸዋል:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":80,"translation":"80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱ ምሕረትን ብትለምንላቸዉም ወይም ባትለምንላቸው ሁሉም እኩል ነው:: ለእነርሱ ሰባ ጊዜ ምህረትን ብትለምንላቸው እንኳን አላህ በፍጹም አይምራቸዉምና:: ምክንያቱም እነርሱ በአላህና በመልዕክተኛው ክደዋልና:: አላህ አመጸኞች ህዝቦችን አያቀናም::"},{"id":81,"translation":"81. እነዚያ ከዘመቻ የቀሩት ሰዎች ከአላህ መልዕክተኛ በኋላ ተገንጥለው በመቀመጣቸው ተደሰቱ:: በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው መታገልን ጠሉ:: ለሌሎችም «በሐሩር አትሂዱ» አሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የገሀነም እሳት ትኩሳት በጣም ከዚህ የበረታ ነው።» በላቸው:: እናም የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ ከዘመቻው አይቀሩም ነበር::"},{"id":82,"translation":"82. አስመሳዮች ጥቂት ጊዜን ብቻ ይሳቁ:: ይሠሩት በነበሩት እኩይ ተግባር ምክንያት ዋጋ ብዙ ጊዜ ያለቅሳሉና::"},{"id":83,"translation":"83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል ወደ ሆነችው ቡድን አላህ በሰላም ቢመልስህና ካንተ ጋር ዘመቻ ለመውጣት ቢያስፈቅዱህ «ከእኔ ጋር በፍጹም አትወጡም:: ከእኔም ጋር ጠላትን አትዋጉም:: እናንተ በመጀመሪያ ጊዜ መቀመጥን ወዳችኋልና:: ይልቁንም ከተቀማጮች ጋር ተቀመጡ።» በላቸው::"},{"id":84,"translation":"84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል በሞተ በአንዱም ሰው ላይ ቢሆን ፈጽሞ አትስገድ:: በመቃብሩም ላይ አትቁም:: እነርሱ በአላህና በመልዕክተኛው ክደዋል:: እነርሱ አመጸኞችም ሆነው ሞተዋልና::"},{"id":85,"translation":"85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው አይድነቁህ:: አላህ የሚፈልገው በቅርቢቱ ዓለም በገንዘቦቻቸውና በልጆቻቸው ሊቀጣቸውና ከሓዲያንም ሆነው ነፍሶቻቸው እንዲወጡ ሊያደርግ ብቻ ነውና::"},{"id":86,"translation":"86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ እመኑ:: ከመልዕክተኛው ጋር ሆናችሁ ታገሉ በማለት የቁርኣን ምዕራፍ በተወረደ ጊዜ ከእነርሱ የሰፊ ሀብት ባለቤቶች የሆኑት ሰዎች ለመቅረት ፈቃድ ይጠይቁሃል:: «ከተቀማጮቹ ጋር እንሁን ተወን» ይሉሃል::"},{"id":87,"translation":"87. በቤት ከሚቀሩት ወገኖች ጋር መሆናቸውን ወደዱ:: በልቦቻቸዉም ላይ (ዝገት) ታተመባቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያውቁም::"},{"id":88,"translation":"88. ግን መልዕክተኛውና ከእርሱ ጋር ያመኑት ሰዎች በገንዘቦቻቸዉም በነፍሶቻቸዉም ታገሉ:: እነዚያም መልካሞች ሁሉ ለእነርሱ ብቻ የተዘጋጁ ናቸው:: እነዚያም እነርሱ ምኞታቸውን ያገኙ ናቸው::"},{"id":89,"translation":"89. አላህ ለእነርሱ በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶችን በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ አዘጋጅቶላቸዋል:: ይህ ታላቅ ማግኜት (እድል) ነው::"},{"id":90,"translation":"90. ከአረብ ዘላኖች መካከል ይቅርታ ፈላጊዎቹ እንዲፈቀድላቸው መጡ:: እነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን ያስተባበሉት ግን ተቀመጡ:: እነዚያን በአላህ የካዱት ሰዎች አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል (ያገኛቸዋል)::"},{"id":91,"translation":"91. በደካሞች ላይ፤ በበሽተኞች ላይ፤ በእነዚያም ለስንቅና ለትጥቅ የሚያወጡት ገንዘብ በማያገኙት ላይ ለአላህና ለመልዕክተኛው ፍጹም ታዛዦች ከሆኑ ወደ ዘመቻ ባይወጡም ኃጢአት የለባቸዉም:: በበጎ አድራጊዎች ላይ ምንም የመወቀሻ መንገድ የለባቸዉም:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":92,"translation":"92. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በነዚያም መጓጓዣያ እንድትሰጣቸው ፈልገው ወደ አንተ በመጡ ጊዜ «እናንተን የምጭንበት (አጋሰስ) አላገኝም።» ያልካቸው ስትሆን የሚያወጡት ገንዘብ ባለማግኘታቸው ለማዘናቸው ዓይኖቻቸው እንባን እያፈሰሱ በዞሩት ላይ ምንም ወቀሳ የለባቸዉም::"},{"id":93,"translation":"93. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሚወቀሱት እነዚያ ባለጸጋዎች ሆነው ሳሉ ለመቅረት ፈቃድ በሚጠይቁህ ሰዎች ላይ ብቻ ናቸው:: ከቀሪዎቹ ጋር መሆናቸውን ወደዱ:: አላህ በልቦቻቸው ላይ አተመባቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያውቁም::"},{"id":94,"translation":"94. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነርሱ በተመለሳችሁ ጊዜ ምክንያቶቻቸውን ያቀርቡላችኋል:: «አታመካኙ እናንተን ፈጽሞ አናምንም:: አላህ ከወሬዎቻችሁ አስቀድሞ ነግሮናልና:: አላህና መልዕክተኛው ሥራችሁን ያያሉ:: ከዚያ ሩቅንና ቅርብን ሁሉ አዋቂ ወደ ሆነው አላህ ትመለሳላችሁ:: ወዲያዉም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል።» በላቸው::"},{"id":95,"translation":"95. (አማኞች ሆይ!) ከዘመቻ ወደ እነርሱ በተመለሳችሁ ጊዜ ጥፋታቸውን ይቅር እንድትሉሏቸው ለእናንተ በአላህ ይምላሉ:: እነርሱን ተዏቸው:: እነርሱ እርኩሶች ናቸውና:: ይሠሩትም በነበረው ኃጢአት መኖሪያቸው ገሀነም ነው::"},{"id":96,"translation":"96. እነርሱ ትወዱላቸው ዘንድ ለእናንተ ይምሉላችኋል:: እናንተ ብትወዱላቸውም አላህ ከአመጸኛ ህዝቦች አይወድም::"},{"id":97,"translation":"97. ዘላን አረቦች በክሕደትና በንፍቅና በጣም የበረቱ፤ አላህ በመልዕክተኛው ላይ ያወረደውን ህግጋት ባለማወቅም የተገቡ ናቸው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::"},{"id":98,"translation":"98. ከዘለኖች መካከል በአላህ መንገድ የሚያወጣውን ገንዘብ እዳ አድርጎ የሚይዝና በእናንተ ላይ የጊዜን መገለባበጥ የሚጠባበቅ ሰው አለ:: በእነርሱ ላይ ጥፋቱ ይዙርባቸው:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነው::"},{"id":99,"translation":"99. ከአረብ ዘላኖች መካከል በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሚሰጣቸውንም ምጽዋቶች አላህ ዘንድ መቃረቢያዎችና ወደ መልዕክተኛው ጸሎቶች መዳረሻ አድርጎ የሚይዝ ክፍል አለ:: አስተዉሉ! እርሷ ለእነርሱ በእርግጥ አቃራቢ ናት:: አላህ በችሮታው ውስጥ በገነቱ በእርግጥ ያስገባቸዋል:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና ::"},{"id":100,"translation":"100. ከስደተኞቹም ሆነ ከረዳቶቹ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎችና እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው ሰዎች አላህ የእነርሱን ተግባር ወዶላቸዋል:: እነርሱም ወደውለታል:: በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸዉም ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲሆኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል:: ይህ ታላቅ እድለኛነት ነው::"},{"id":101,"translation":"101. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዙሪያችሁም ካሉት የዐረብ ዘላኖች አስመሳዮች አሉ:: ከመዲና ሰዎችም በንፍቅና ላይ በማመጽ የዘወተሩ አሉ:: አታውቃቸዉም:: እኛ እናውቃቸዋለን:: ሁለት ጊዜ እንቀጣቸዋለን:: ከዚያ ወደ ታላቅ ቅጣት ይመለሳሉ::"},{"id":102,"translation":"102. ሌሎችም ኃጢአቶቻቸውን የተናዘዙ መልካም ሥራንና ሌላን መጥፎ ሥራ የቀላቀሉ አሉ:: አላህ ጸጸታቸውን ሊቀበል ይከጀላል:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":103,"translation":"103. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከገንዘቦቻቸው የምታጠራቸውና የምታፋፋቸውን ምጽዋት ያዝ:: ለነሱም ዱኣ አድርግላቸው፡፡ ዱኣእህ ለእነሱ እርጋታ ነውና አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡"},{"id":104,"translation":"104. አላህም እርሱ ከባሮቹ ንሰሃን የሚቀበልና ምጽዋቶችንም የሚወስድ፤ አላህ ብቸኛ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ መሆኑን አያውቁምን?"},{"id":105,"translation":"105. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሥሩ:: አላህ መልዕክተኛውና አማኞችም ሥራችሁን በእርግጥ ያያሉና:: ሩቁንና ቅርቡን ሁሉ አዋቂ ወደ ሆነው አላህ በእርግጥ ትመለሳላችሁ:: ትሰሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል።» በላቸው::"},{"id":106,"translation":"106. ሌሎችም የአላህን ውሳኔ ትዕዛዝ እንዲጠብቁ የተቆዩ ህዝቦች አሉ:: ይቀጣቸዋል ወይም ጸጸታቸውን ይቀበላቸዋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነዉና፡፡"},{"id":107,"translation":"107. እነዚያም አማኞችን ለመጉዳት ክህደትንም ለማበረታታት በአማኞችም መካከል ለመለያየት ከአሁን በፊት አላህንና መልዕክተኛውን የተዋጋውን ሰው ለመጠባበቅ መስጊዱን የሠሩት ሰዎች ከእነርሱ ናቸው:: «መልካምን እንጂ ሌላ አልሻንም።» ሲሉ በእርግጥ ይምላሉ:: አላህ ደግሞ ውሸታሞች መሆናቸውን በእርግጥ ይመሰክራል::"},{"id":108,"translation":"108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእርሱ ውስጥ በፍጹም አትስገድ:: ይልቁንም ከመጀመሪያ ቀን ይዞ በአላህ ፍራቻ ላይ የተመሠረተው (የቁባ ) መስጊድ በውስጡ ልትሰግዱበት የተገባው ነው:: በውስጡ መጥራራትን የሚወዱ ወንዶች አሉ:: አላህ ተጥራሪዎችን ይወዳል::"},{"id":109,"translation":"109. አላህን በመፍራትና ውዴታውን በመፈለግ ላይ ግንቡን የመሠረተ ሰው ወይስ ጎርፍ በሸረሸረው ለመናድ በተቃረበ ገደል አፋፍ ላይ ግንቡን የመሠረተውና እርሱንም ይዞት ወደ ገሀነም እሳት ውስጥ የወደቀው ይበልጣልን? አላህ በደለኛ ሕዝቦችን አይመራም::"},{"id":110,"translation":"110. ያ የካቡት ግንባቸው ልቦቻቸው በሞት ካልተቆራረጡ በስተቀር በልቦቻቸው ውስጥ የመጠራጠር ምክንያት ከመሆን አይወገድም:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::"},{"id":111,"translation":"111. አላህ ከትክክለኛ አማኞች ነፍሶቻቸውንና ገንዘቦቻቸውን ገነትን ለእነርሱ በማድረግ ገዛቸው:: በአላህ መንገድ ላይ ይጋደላሉ:: ይገድላሉም:: ይገደላሉም:: በተውራት፤ በኢንጂልና በቁርኣንም የተነገረውን ተስፋ በእርሱ ላይ አረጋገጠ:: ከአላህ የበለጠ በቃል ኪዳኑ የሚሞላ ማን ነው? (ትክክለኛ አማኞች ሆይ!) በዚያም በእርሱ በተሻሻጣችሁበት ሽያጫችሁ ተደሰቱ:: ይህ ታላቅ ዕድል ነውና::"},{"id":112,"translation":"112. እነርሱ ተጸፃቾች፤ ተገዢዎች፤ አመስጋኞች፤ ፆመኞች፤ (በሶላት) አጎንባሾች፤ በግንባር ተደፊዎች፤ በበጎ ሥራ አዛዦች፤ ከክፉ ከልካዮች እና የአላህንም ሕግጋት ጠባቂዎች ናቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ትክክለኛ አማኞችንም አብስር::"},{"id":113,"translation":"113. መልዕክተኛዉም ሆነ እነዚያ በእሱ ያመኑት ሰዎች ለአጋሪዎቹ የዝምድና ባለቤቶች ቢሆኑም እንኳ ከሓዲያን እነርሱ የእሳት ጓዶች መሆናቸው ከተገለጸላቸው በኋላ የአላህን ምሕረት ሊለምኑላቸው የሚገባ አልነበረም::"},{"id":114,"translation":"114. ኢብራሂምም ለአባቱ ምህረትን መለመኑ ቀድሞ ገብቶለት የነበረውን ቃል ለመሙላት እንጂ ለሌላ አልነበረም:: እናም የአላህ ጠላት መሆኑ በተገለጸለት ጊዜ ከእርሱ ራቀ:: (ተወው):: ኢብራሂም በእርግጥ አልቃሻ እና ታጋሽ ነበርና።"},{"id":115,"translation":"115. አላህ ህዝቦችን ካቀናቸው በኋላ የሚጠነቀቁትን ነገር እሥከሚገልጽላቸው ድረስ ሳያውቁ በሰሩት ጥፋት ጥፋተኛ የሚያደርግ ጌታ አይደለም:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነውና::"},{"id":116,"translation":"116. አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ ነው:: ህያው ያደርጋል:: ይገድላልም:: ለእናንተም ከእርሱ በስተቀር ጠባቂም ሆነ ወዳጅ የላችሁም::"},{"id":117,"translation":"117. በመልዕክተኛው በስደተኞችና በረዳቶች በእነዚህም በችግሩ ጊዜ (በተቡክ ዘመቻ) ከእነርሱ የከፊሎቹ ልቦች ለመቅረት ሊዘነበሉ ከተቃረቡ በኋላ በተከተሉት ላይ አላህ በእርግጥ ጸጸታቸውን ተቀበለ:: ከዚያ ከእነርሱ ንሰሃ መግባታቸውን ተቀበለ:: እርሱ(አላህ ) ለእነርሱ ሩህሩህና አዛኝ ነውና::"},{"id":118,"translation":"118. በእነዚያም ወደ ኋላ በቀሩት በሶስቱ ሰዎች ላይ ምድር ከስፋቷ ጋር በእነርሱ ላይ እስከምትጠብባቸው፤ ነፍሶቻቸዉም በእነርሱ ላይ እስከምትጠብባቸው፤ ከአላህም ወደ እርሱ ብቻ እንጂ ሌላ መጠጊያ አለመኖሩን እስከሚያረጋግጡ ድረስ በተቆዩት ላይ አላህ ጸጸትን ተቀበለ:: ከዚያም ይጸጸቱ ዘንድ ወደ ጸጸት መራቸው:: አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና::"},{"id":119,"translation":"119. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን በትክክል ፍሩ:: ከእውነተኞቹም ጋር ሁኑ::"},{"id":120,"translation":"120. የመዲና ሰዎችና በዙሪያቸው ያሉት የዘላን ዓረብ ህዝቦች ከአላህ መልዕክተኛ ጥሪ ወደ ኋላ ሊቀሩና ነፍሶቻቸውንም ከነፍሱ አብልጠው ሊወዱ አይገባቸዉም ነበር:: ይህም የሆነው ለእነርሱ መልካም ሥራ የሚጻፍላቸው ቢሆን እንጂ በአላህ መንገድ ላይ ጥምም ድካምም ርሀብም የማይነካቸው ከሓዲያንንም የሚያስቆጭን ስፍራ የማይረግጡ ከጠላትም የሚጎዳን ነገር (መግደል) የማያገኙ በመሆናቸው ነው:: አላህ የመልካም ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና::"},{"id":121,"translation":"121. ትንሽንም ትልቅንም ልግስና አይለግሱም ወንዝንም አያቋርጡም አላህ ይሠሩት ከነበረው የበለጠን ምንዳ ይመነዳቸው ዘንድ ለእነርሱ የሚጽፍላቸው ቢሆን እንጂ::"},{"id":122,"translation":"122. ምእምናንም (ከነቢዩ ጋር ካልኾነ) በሙሉ ሊወጡ አይገባም፡፡ ከእነሱ ውስጥ ከየክፍሉ አንዲት ጭፍራ ለምን አትወጣም፡፡ (ሌሎቹ) ሃይማኖትን እንዲማሩና ወገኖቻቸው ወደነርሱ በተመለሱ ጊዜ እንዲጠነቀቁ ይገስጹዋቸው ዘንድ (ለምን አይቀሩም)፡፡"},{"id":123,"translation":"123. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን በአቅራቢያችሁ ያሉትን ከሓዲያን ተዋጉ:: በናንተ ውስጥ ብርታትን ያግኙ:: አላህም ከሚጠነቀቁት ጋር መሆኑን እወቁ::"},{"id":124,"translation":"124. ምዕራፍ በተወረደ ጊዜ ከአስመሳዮች ውስጥ «ማንኛችሁ ነው ይህ ምዕራፍ እምነትን የጨመረለት?» የሚል ሰው አለ:: እነዚያ ያመኑት ሰዎች የሚደሰቱ ሲሆኑ እምነትን ጨመረላቸው::"},{"id":125,"translation":"125. እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ክፍሎች ግን በርክሰታቸው ላይ እርክሰትን ጨመረላቸው:: እነርሱም ከሓዲያን ሆነው ሞቱ::"},{"id":126,"translation":"126. በየዓመቱ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ እነርሱ የሚሞከሩ መሆናቸውን አያዩምን? ከዚያ አይጸጸቱምን?እነርሱም አይገሰጹምን?"},{"id":127,"translation":"127. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን የሚያወሳ ምዕራፍም በተወረደ ጊዜ «የሚያያችሁ (ሰው) አለን?» እያሉ ከፊሎቻቸው ወደ ከፊሉ ይመለከታሉ:: ከዚያ ተደብቀው ይሄዳሉ:: እነርሱ የማያውቁ ህዝቦች በመሆናቸው አላህ ልቦቻቸውን አዞረ::"},{"id":128,"translation":"128. (ሰዎች ሆይ!) ከጎሳችሁ ውስጥ የሆነ መቸገራችሁ በእርሱ ላይ ከባድ ጉዳይ የሆነበት፤ እናንተ እምነት እንዲኖራችሁ በጣም የሚጓጓና ለትክክለኛ አማኞችም ሩህሩህና አዛኝ የሆነ መልዕክተኛ (ሙሐመድ) መጣላችሁ::"},{"id":129,"translation":"129. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ቢያፈገፍጉ አላህ በቂዬ ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: በእርሱ ላይ ብቻ ተመካሁ:: እርሱም የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው።» በላቸው::"}]},{"id":10,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ እነዚህ ጥበብ ከተሞላው መፅሀፍ አንቀፆች ናቸው።"},{"id":2,"translation":"2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎችን (ከሓዲያንን) አስፈራራ፤ እነዚያን ያመኑትን ደግሞ ከጌታቸው ዘንድ መልካም ምንዳ ያላቸው መሆኑን አብስር» በማለት ከእነርሱ መካከል ወደ ሆነ አንድ ሰው ራዕይን ማውረዳችን ለሰዎች ድንቅ ሆነባቸውን? ከሓዲያን «ይህ (ሰው) ግልጽ ድግምተኛ ነው።» አሉ።"},{"id":3,"translation":"3. ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ ብቻ የፈጠራቸው አላህ ነው:: ከዚያም ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብር ሲሆን (ለሱ ክብር በምስማማ መልኩ) በዐርሹ ላይ ተደላደለ፡፡ ከእርሱ በጎ ፈቃድ በኋላ ቢሆን እንጂ አንድም አማላጅ የለም:: እነሆ ይህ አላህ ጌታችሁ ነው:: እናም በትክክል ተገዙት:: አትገሰጹምን?"},{"id":4,"translation":"4. (ሰዎች ሆይ!) የሁላችሁም መመለሻችሁ ወደ እርሱ ብቻ ነው:: ይህም የተረጋገጠ የአላህ ቃል ኪዳን ነው:: እርሱ መፍጠርን ይጀምራል:: ከዚያም እነዚያ ያመኑትንና መልካም የሠሩትን ሰዎች በትክክል ይመነዳ ዘንድ ፍጡራንን ከሞት በኋላ ህያው ያደርጋል:: እነዚያ የካዱት ክፍሎች ግን በክህደታቸው ምክንያት የፈላ ውሃ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":5,"translation":"5. እርሱ ያ ጸሐይን አንጸባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ፤ የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለጨረቃ የተለያዩ መስፈሪያ እርከኖችን የወሰነ ነው:: አላህ ይህንን በእውነት እንጂ በከንቱ አልፈጠረዉም:: ለሚያውቁ ሕዝቦችም አናቅጽን ያብራራል::"},{"id":6,"translation":"6. ሌሊትና ቀን በመተካካታቸው አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ በፈጠረው ሁሉ ለሚጠነቀቁ ሕዝቦች ታላላቅ ተአምራት አሉ::"},{"id":7,"translation":"7. እነዚያ ከኛ ጋር መገናኘታቸውን ተስፋ የማያደርጉ ቅርቢቱን ሕይወት የወደዱና በእርሷም የረኩ እነርሱ ከአናቅጻችን ዘንጊዎች የሆኑት።"},{"id":8,"translation":"8. እነዚያ ይሠሩት በነበሩት ኃጢአት ምክንያት መኖሪያቸው በእሳት ውስጥ ነው::"},{"id":9,"translation":"9. እነዚያ በአላህ ያመኑትና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ሰዎች ሁሉ ጌታቸው በእምነታቸው ምክንያት የገነትን መንገድ ይመራቸዋል:: ከሥሮቻቸው ወንዞች ይፈስሳሉ:: በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥም ዝንታለም ይኖራሉ::"},{"id":10,"translation":"10. በእርሷም ውስጥ ጸሎታቸው የሚሆነው «ጌታችን ሆይ! ጥራት ይገባህ።» ማለት ብቻ ነው:: በእርሷ ውስጥ መከባበሪያቸው ሰላም መባባል ነው:: የመጨረሻ ጸሎታቸዉም «ምስጋና ሁሉ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው።» ማለት ነው።"},{"id":11,"translation":"11. አላህ ለሰዎች ደግን ነገር ለማግኘት እንደ መቻኮላቸው የሚጠይቁትንም ክፉን ነገር ቢያቻኩልባቸው ኖሮ በዚያችው ጊዜያቸው እድሜያቸው በተፈጸመ ነበር:: እነዚያን መገናኘታችንን ተስፋ የማያደርጉትን ሰዎች በጥመታቸው ውስጥ እየዋለሉ እንተዋቸዋለን::"},{"id":12,"translation":"12. የሰውን ልጅ ጉዳት ባገኘው ጊዜ በጎኑ ላይ ተጋድሞ ወይም ተቀምጦ ወይም ቆሞ ይለምንና ጉዳቱን ከእሱ ላይ በገለጥንለት ጊዜ ላገኘው ጉዳት እንዳልተማጸንን ሆኖ ያልፋል:: ልክ እንደዚሁ ለድንበር አላፊዎች ሁሉ ይሠሩት የነበሩት መጥፎ ሥራ ተሸለመላቸው::"},{"id":13,"translation":"13. ከናንተ በፊት የነበሩትን የብዙ ክፍለ ዘመናት ሰዎች መልዕክተኞቻቸው በማስረጃዎች የመጡላቸው ሲሆኑ በበደሉና የማያምኑም በሆኑ ጊዜ አጠፋናቸው:: ልክ እንደዚሁ ተንኮለኞችን ህዝቦች እንቀጣለን::"},{"id":14,"translation":"14. ከዚያ እንዴት እንደምትሠሩ ልንመለከት ከእነርሱ በኋላ በምድር ላይ ምትኮች አደረግናችሁ::"},{"id":15,"translation":"15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አናቅጻችን ግልጽ ሆነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩት (የማይሹት) ሰዎች «ከዚህ ሌላ የሆነን ቁርኣን አምጣልን ወይም ለውጠው።» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ከራሴ በኩል ልለውጠው አይገባኝም:: ወደ እኔ የሚወረደውን እንጂ አልከተልም:: እኔ በጌታዬ ትዕዛዝ ላይ ባምጽ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራለሁ።» በላቸው::"},{"id":16,"translation":"16. (መልዕከተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ በሻ ኖሮ በእናንተ ላይ ባላነበብኩትና አላህ እርሱን ባላሳወቃችሁ ነበር:: በእናንተም ውስጥ ከእርሱ በፊት ምንም ሳልል ብዙን እድሜ በእርግጥ ኖሬያለሁ። አታውቁምን?» በላቸው።"},{"id":17,"translation":"17. በአላህ ላይ እብለትን ከቀጣጠፈ ወይ ከአናቅ ጹ መካከል (በአንዷ እንኳን) ካስተባበለ ይበልጥ በዳይ ማን ነው? እነሆ አመጸኞች አይድኑም::"},{"id":18,"translation":"18. አጋሪዎች ከአላህ ሌላ የማይጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውን ይገዛሉ:: «እነዚህ አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው።» ይላሉም። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ እናንተ ትነግሩታላችሁን?» በላቸው:: አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ:: ላቀም::"},{"id":19,"translation":"19. ሰዎች አንድ ህዝብ እንጂ ሌላ አልነበሩም:: ከዚያ ተለያዩ:: ከጌታህ ያለፈ ቃልም ባልነበረ ኖሮ በዚያ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው በቶሎ በተፈረደ ነበር::"},{"id":20,"translation":"20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ተዓምር ለምን አትወረድለትም?» ይላሉ:: «ሩቅ ነገር ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: እናንተም ተጠባበቁ እኔም ከናንተው ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ።» በላቸው።"},{"id":21,"translation":"21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰዎች ካገኛቸው ጉዳት በኋላ እዝነትን ምቾትን ባቀመስናቸው ጊዜ ወዲያውኑ ለእነርሱ በተዓምራቶቻችን በማላገጥ ተንኮል ይኖራቸዋል:: «አላህ ቅጣቱ ፈጣን ነው።» በላቸው። መልዕክተኞቻችን የምታሴሩትን ነገር ሁሉ በእርግጥ ይጽፋሉ።"},{"id":22,"translation":"22. (ሰዎች ሆይ!) አላህ ያ በየብስና በባሕር የሚያስኬዳችሁ ነው:: በመርከቦችም ውስጥ በሆናችሁና በእነርሱም በመልካም ነፋስ በእርሷ የተደሰቱ ሆነው መርከቦቹ በተንሻለሉ ጊዜ ሀይለኛ ነፋስ ትመጣባቸዋለች:: ከየስፍራዉም ማዕበል ይመጣባቸዋል:: እነርሱም ለጥፋት የተከበቡ መሆናቸውን ሲያረጋግጡ ያን ጊዜ አላህን «ከዚህች ጭንቀት ብታድነን ከአመስጋኞቹ እንሆናለን።» ሲሉ እምነታቸውን ለእርሱ ብቻ ፍጹም አድርገው ይለምኑታል::"},{"id":23,"translation":"23. በአዳናቸዉም ጊዜ እነርሱ ወዲያውኑ ያለ አግባብ በምድር ላይ ወሰን ያልፋሉ። እናንተ ሰዎች ሆይ ወሰን ማለፋችሁ ጥፋቱ በነፍሶቻችሁ ላይ ብቻ ነው:: እርሱ የቅርቢቱ ህይወት መጠቀሚያ ነው:: ከዚያ መመለሻችሁ ወደ እኛ ነው:: ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እንነግራችኋለን::"},{"id":24,"translation":"24. . የቅርቢቱ ህይወት ምሳሌ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ በእርሱም ሰውና እንስሳዎች ከሚበሉት የምድር በቃይ ተቀላቅሎበት እንደፋፋ ምድርም ውበትዋን በያዘችና ባጌጠች ጊዜ ባለቤቶችዋን በእርሷ ላይ እነርሱ ቻዮች መሆናቸውን ባሰቡ ጊዜ ትዕዛዛችን ሌሊት ወይም ቀን መጥቶባት ትላንት እንዳልነበረች የታጨደች እንዳደረግናት ብጤ ነው:: ልክ እንደዚሁ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ሁሉ አናቅጽን እናብራራለን::"},{"id":25,"translation":"25. አላህ (ሁል ጊዜም) ወደ ሰላም አገር ይጠራል:: የሚፈልገዉን ሰዉም ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል::"},{"id":26,"translation":"26. ለእነዚያ መልካም ለሠሩት ሰዎች መልካም ነገርና (ገነት) ሌላ ተጨማሪም አላቸው:: ፊቶቻቸውንም ጥቁረትና ውርደት አይሸፍናቸዉም:: እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው::"},{"id":27,"translation":"27. እነዚያ ኃጢአቶችን የሠሩት ደግሞ ኃጢአቲቱን የሚመጥን ቅጣት አለባቸው:: ውርደትም ትሸፍናቸዋለች :: እነርሱ ከአላህ ቅጣት ጠባቂ የላቸዉም:: ፊቶቻቸው በድቅድቅ ጨለማ ቁራጮች እንደ ተሸፈኑ ይሆናሉ:: እነዚያ የእሳት ሰዎች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘለዓለም ነዋሪዎች ናቸው::"},{"id":28,"translation":"28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማልክትንና አምላኪዎቻቸውን ሁሉ በአንድ የምንሰበስባቸውንና ከዚያም ለእነዚያ ላጋሩት «እናንተም ተጋሪዎቻችሁም ቦታችሁን ያዙ።» የምንልበትን ተጋሪዎቻቸዉም (እንዲህ) የሚሏቸው ሲሆኑ በመካከላቸው የምንለይበትን ቀን አስታውስ «ትገዙ የነበረው እኛን አልነበረም።"},{"id":29,"translation":"29. (ጣኦታቶቹ) «እኛን ለመገዛታችሁ ዘንጊዎች ለመሆናችን በኛና በእናንተ መካከል የአላህ መስካሪነት በቃ።» ይሏቸዋል::"},{"id":30,"translation":"30. በዚያ ቀን ነፍስ ሁሉ ያሳለፈችውን ሥራ ታውቃለች:: አጋሪዎች ወደ አላህ እውነተኛ ወደሆነው ጌታቸው ይመለሳሉ:: ያ በአላህ ላይ ይቀጣጥፋት የነበሩት ሁሉ ነገርም ይጠፋባቸዋል::"},{"id":31,"translation":"31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው? መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረላችሁ ማን ነው? ከሙትም ህያውን የሚያወጣ፤ ከህያዉም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው?» በላቸው:: «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል:: «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ? ታዲያ አትፈሩትምን?» በላቸው።"},{"id":32,"translation":"32. እውነተኛው ጌታችሁ አላህ ብቻ ነው:: ከእውነት በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ? ከእውነት እንዴት ትዞራላችሁ?"},{"id":33,"translation":"33. ልክ እንደዚሁ የጌታህ ቃል በእነዚያ ባመጹት ሰዎች ላይ ፈጽሞ የማያምኑ መሆናቸው ተረጋገጠ::"},{"id":34,"translation":"34. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከምታጋሯቸው ጣኦታት መካከል መፍጠርን የሚጀምር ከዚያ የሚመልስ አለን?» በላቸው። «አላህ ግን መፍጠርን ይጀምራል:: ከዚያ ይመልሰዋል:: ታዲያ ከእምነት እንዴት ትዘራላችሁ?» በላቸው::"},{"id":35,"translation":"35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከምታጋሯቸው ጣኦታት መካከልስ ወደ እውነት መንገድ የሚመራ አለን?» በላቸው:: «አላህ ግን ወደ እውነቱ ይመራል:: ወደ እውነት የሚመራው ጌታ ነውን ሊከተሉት የተገባው? ወይስ ካልተመራ በስተቀር የማይመራው? ለእናንተ ምን ( አስረጅ) አላችሁ? እንዴት በውሸት ትፈርዳላችሁ?» በላቸው::"},{"id":36,"translation":"36. አብዛኞቻቸው ጥርጣሬን እንጂ አይከተሉም:: ጥርጣሬ ደግሞ ከእውነት በፍጹም አያብቃቃም:: አላህ የሚሠሩትን ሁሉ አዋቂ ነው::"},{"id":37,"translation":"37. ይህም (ቁርኣን) ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባዉም:: ይልቁንም ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን መጽሐፍ የሚያረጋግጥና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርግጥ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው::"},{"id":38,"translation":"38. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእውነት ሙሐመድ ቀጣጠፈው» ይላሉን? ይህን የሚሉ ከሆነ «መሰሉን አንድ ምዕራፍ እንኳ እስቲ አምጡ:: ለዚህም ጉዳይ ከአላህ ሌላ የቻላችሁትን ሁሉ ረዳት ጥሩ:: እውነተኞች እንደሆናችሁ ለዚህ ተጋግዛችሁ አምጡ።» በላቸው::"},{"id":39,"translation":"39. ይልቁንም እውቀቱን ባላዳረሱትና ፍቹም ገና ባልመጣላቸው ነገር አስተባበሉ:: እንደዚሁ እነዚያ ከእነሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል፡፡ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የበዳዮች መጨረሻ እንዴት ይመስል እንደ ነበር በጥሞና ተመልከት::"},{"id":40,"translation":"40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመካከላቸው ወደፊት በቁርኣን የሚያምኑ አሉ:: ከእነርሱም መካከል በእርሱ የማያምኑ አሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ አጥፊዎቹን በጣም አዋቂ ነው::"},{"id":41,"translation":"41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ቢያስተባብሉህም ለእኔ የራሴ ሥራ አለኝ:: እናንተም የራሳችሁ ሥራ አላችሁ:: እናንተ እኔ ከምሠራው ተግባር ንጹህ ናችሁ (አትጠየቁም):: እኔም እናንተ ከምትሠሩት ነገር ንጹህ ነኝ (አልጠየቅም)።» በላቸው።"},{"id":42,"translation":"42. ከእነርሱ መካከል ወደ አንተ ንግግር የሚያዳምጡ የሚሰሙና የማያምኑ አሉ:: አንተ ደንቆሮዎችን የማያውቁ ቢሆኑም ታሰማለህን?::"},{"id":43,"translation":"43. ከእነርሱም መካከል ወደ አንተ የሚመለከቱ አሉ:: አንተ ልበ እውራንን የማያዩ ቢሆኑም ትመራለህን?"},{"id":44,"translation":"44. አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም:: ግን ሰዎች ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ::"},{"id":45,"translation":"45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያንን ከቀን አንዲትን ሰዓት እንጂ አንዳልቆዩ መስለው በመካከላቸው የሚተዋወቁ ሲሆኑ በምንሰበስባቸው ቀን የሚከሰተውን አስታውስ:: እነዚያ በአላህ መገናኘት ያስተባበሉት ሁሉ በእርግጥ ከሰሩ:: የተመሩም አልነበሩምና::"},{"id":46,"translation":"46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያንም የምናስፈራራባቸውን ነገር ውጤት ከፊሉን (በሕይወትህ ሳለህ) ብናሳይህ (መልካም ነው):: ወይም ሳናሳይህ ብንገድልህ (ጉዳዩ የእኔ ነው):: መመለሻቸው ወደ እኛ ነውና:: ከዚያ አላህ በሚሠሩት ሥራ ላይ ሁሉ አዋቂ ነው::"},{"id":47,"translation":"47. ለሕዝቦችም ሁሉ መልዕክተኛ አላቸው:: መልዕክተኛቸው በመጣ ጊዜ (ሲያስተባብሉት) በመካከላቸው በትክክል ይፈረዳል:: እነርሱም ፍጹም አይበደሉም::"},{"id":48,"translation":"48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እውነተኞች ከሆናችሁ የቅጣቱ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ::"},{"id":49,"translation":"49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለራሴ ጉዳትን ማድረስም ሆነ ጥቅምን ማስከበር አላህ ከሻው በስተቀር አልችልም:: ለህዝቦች ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸው:: ጊዜያቸው በደረሰ ወቅት አንዲትን ሰዓት እንኳን አይቆዩም:: አይቀደሙምም።» በላቸው::"},{"id":50,"translation":"50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እስቲ ንገሩኝ ቅጣቱ በሌሊት ወይም በቀን ቢመጣባችሁ አጋሪዎቹ የሚያስቸኩላቸው ነገር ምንድን ነው?» በላቸው::"},{"id":51,"translation":"51. «ከዚያም ቅጣቱ በወደቀ ጊዜ በእርሱ አመናችሁበትን? በእርግጥ በእርሱ የምትቻኮሉ የነበራችሁ ስትሆኑ አሁን ነው የምታምኑትን?» ይባላሉ።"},{"id":52,"translation":"52. ከዚያ ለእነዚያ ለበደሉት ሰዎች «ዘውታሪውን ቅጣት ቅመሱ። ትሠሩ የነበራችሁትን እኩይ ተግባር ዋጋ እንጂ ትመነዳላችሁን? (አትመነዱም)።» ይባላሉ::"},{"id":53,"translation":"53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «(ከሞት በኋላ መቀስቀስ) እውነት ነውን?» ሲሉ ይጠይቁሃል:: «አዎን! በጌታዬ እምላለሁ እርሱ እውነት ነው:: እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም።» በላቸው።"},{"id":54,"translation":"54. ለበደለች ነፍስ ሁሉ በምድር ላይ ያለው ሀብት ሁሉ የእርሷ ቢሆንላት በእርግጥ ቤዛ ባደረገችው ነበር:: ቅጣቱንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይደብቃሉ (ይገልጻሉ):: በመካከላቸዉም በትክክል ይፈረዳል:: እነርሱም ቅንጣት ያህል አይበደሉም::"},{"id":55,"translation":"55. አስተውሉ! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: አስተዉሉ! የአላህ የተስፋ ቃል እርግጥ ነው:: ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም::"},{"id":56,"translation":"56. እርሱ ሕያው ያደርጋል:: ይገድላልም:: ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::"},{"id":57,"translation":"57. ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ዘንድ ግሳጼ በደረቶች ውስጥ ላለው በሽታም ፍቱን መድሀኒት፤ ለአማኞችም ብርሃንና እዝነት የሆነ መልዕክት በእርግጥ መጣላችሁ።"},{"id":58,"translation":"58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በአላህ ችሮታና በእዝነቱ ተደሰቱ:: በዚህም ምክንያት ይደሰቱ:: እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት ሁሉ በላጭ ነው።» በላቸው::"},{"id":59,"translation":"59. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ከሲሳይ ለእናንተ ያወረደው ከእርሱም ከፊሉን እርም ከፊሉን የተፈቀደ ያደረጋችሁትን አያችሁን?» በላቸው:: «አላህ ይህንን ለእናንተ ፈቀደላችሁን? ወይስ በአላህ ላይ ትቀጣጥፋላችሁ?» በላቸው::"},{"id":60,"translation":"60. እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ሰዎች በትንሳኤ ቀን በአላህ ጥርጣሬያቸው ምንድን ነው? አይቀጡም ይመስላቸዋልን? አላህ በሰዎች ላይ ቅጣትን ባለማቻኮል የልግስና ባለቤት ነው:: ግን አብዛኛዎቹ አያመሰግኑትም::"},{"id":61,"translation":"61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በማንኛዉም ነገር ላይ አትሆንም፤ ከእርሱም ከቁርኣን ትንሽም አታነብም፤ ማንኛውንም ሥራ አንተም ሆንክ ሰዎቹ አትሠሩም፤ በገባችሁበት ጊዜ በናንተ ተግባር ላይ ተጠባባቂዎች ብንሆን እንጂ :: በምድርም ሆነ በሰማይ የብናኝ ክብደት ያክል እንኳን ከጌታህ እውቀት አይርቅም:: ከዚያም ያነሰም ሆነ የተለቀ ነገር በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈ ቢሆን እንጂ የለም::"},{"id":62,"translation":"62. አስተውሉ! የአላህ ወዳጆች ፍርሀት የለባቸዉም። አይተክዙምም።"},{"id":63,"translation":"63. እነርሱም እነዚያ ያመኑትና አላህን የሚፈሩት ናቸው::"},{"id":64,"translation":"64. ለእነርሱ በቅርቢቱ ህይወትም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ብስራት አለላቸው:: የአላህ ቃል አይለወጥም:: ይህ እርሱ ታላቅ እድል (ስኬታማነት) ነው::"},{"id":65,"translation":"65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ንግግራቸዉም አያሳዝንህ:: ኃይል በሙሉ የአላህ ብቻ ነውና:: እርሱም ሰሚውና ሁሉን አዋቂው ነው::"},{"id":66,"translation":"66. አስተውሉ! በሰማያት ያሉትና በምድርም ያሉት ሁሉ በእርግጥ የአላህ ናቸው፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ ተጋሪዎችን የሚጠሩ ምንን ይከተላሉ? ጥርጣሬን እንጂ ሌላ አይከተሉም፡፡ እነርሱም የሚዋሹ እንጂ አይደሉም፡፡"},{"id":67,"translation":"67. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት ጨለማ ቀንንም ልትሠሩበት ብርሃን ያደረገላችሁ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ህዝቦች ሁሉ በእርግጥ ብዙ ተአምራት አሉ::"},{"id":68,"translation":"68. «አላህ ልጅን ወለደ።» አሉ። ከሚሉት ሁሉ ጥራት ተገባው:: እርሱ በራሱ ተብቃቂ ነው:: በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: እናንተ ዘንድ በዚህ በምትሉት ምንም አስረጂ የላችሁም:: በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን?"},{"id":69,"translation":"69. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ሰዎች ፈጽሞ አይድኑም።» በላቸው"},{"id":70,"translation":"70. እነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ጥቂት ጊዜ ይጠቀሙና ከዚያም መመለሻቸው ወደ እኛ ነው:: ከዚያም ይክዱ በነበሩበት ምክንያት ብርቱን ቅጣት እናቀምሳቸዋለን::"},{"id":71,"translation":"71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የኑህንም ወሬ በእነርሱ ላይ አንብብላቸው:: ለህዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውሱ «ህዝቦቼ ሆይ! በእናንተ ውስጥ ብዙን ጊዜ መቆየቴ የአላህንም ተዓምራት ለእናንተ ማስታወሴ በእናንተ ላይ የከበደ ቢሆንባችሁም በአላህ ላይ ተጠግቻለሁ:: ነገራችሁንም ከምታጋሯቸው ጣኦታት ጋር ሆናችሁ እስቲ ቁረጡ:: ከዚያም ነገራችሁ በእናንተ ላይ ድብቅ አይሁን ግለጹት:: ከዚያም የሻችሁትን ወደ እኔ አድርሱ:: ጊዜም አትስጡኝ (ከምንም አልቆጥራችሁም)::"},{"id":72,"translation":"72. «ብትሸሹም (አትጎዱኝም::) ከምንዳ ምንንም አለመንኳችሁምና:: ምንዳዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለምና:: ከሙስሊሞች እንድሆንም ታዝዣለሁ።»"},{"id":73,"translation":"73. አስተባበሉት እርሱንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች በታንኳይቱ ውስጥ አዳንናቸው:: ለጠፉት ምትኮች አደረግናቸው:: እነዚያንም በአናቅጻችን ያስተባበሉትን አሰመጥን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተስፈራሩት ህዝቦች መጨረሻ እንዴት እንደ ነበር እስቲ ተመልከት::"},{"id":74,"translation":"74. ከዚያም ከእርሱ በኋላ መልዕክተኞችን ወደየ ህዝቦቻቸው ላክን:: በግልጽ ማስረጃዎችም መጡላቸው:: ከመላካቸው በፊት ባስተባበሉት ነገር የሚያምኑ አልሆኑም:: ልክ እንደዚሁ በወሰን አላፊዎች ልቦች ላይ እናትማለን::"},{"id":75,"translation":"75. ከዚያም ከእነርሱ በኋላ ሙሳንና ሃሩንን ወደ ፈርዖንና ወደ መማክርቱ በተአምራታችን ላክን:: ኮሩም:: ትእቢተኞች ህዝቦችም ነበሩ::"},{"id":76,"translation":"76. ከእኛም ዘንድ እውነቱ በመጣላቸው ጊዜ «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምት ነው።» አሉ።"},{"id":77,"translation":"77. ሙሳ አለ፡- «እውነቱን በመጣላችሁ ጊዜ ድግምተኞች የማይድኑ ሲኾኑ (እርሱ ድግምት ነው) ትላላችሁን?ይህ ድግምት ነውን?»"},{"id":78,"translation":"78. እነርሱም «አባቶቻችንን ካገኘንበት ሃይማኖት ልታዞሩንና በምድር ውስጥ ለእናንተም ኩራት ሹመት ልትኖራችሁ መጣህብን:: እኛ ለእናንተ በፍጹም አማኞች አይደለንም።» አሉ::"},{"id":79,"translation":"79. ፈርዖን፡- «አዋቂ ድግምተኛን ሁሉ አምጡልኝ።» አለ::"},{"id":80,"translation":"80. ድግምተኞቹ በመጡ ጊዜም ሙሳ ለእነርሱ፡- «እናንተ የምትጥሉትን ነገር ጣሉ።» አላቸው::"},{"id":81,"translation":"81. በጣሉም ጊዜ ሙሳ፡- «ያ በእርሱ የመጣችሁበት ነገር ድግምት ነው:: አላህ በእርግጥ ያፈርሰዋል:: አላህ የአጥፊዎችን ሥራ ፈጽሞ አያበጅምና።» አለ::"},{"id":82,"translation":"82. አላህም ከሓዲያን ቢጠሉም እውነትን በቃላቱ ያረጋግጣል::"},{"id":83,"translation":"83. ለሙሳም ከፈርዖንና ከሹማምንቶቻቸው ማሰቃየትን በመፍራት ከወገኖቹ ጥቂት ትውልዶች ብቻ እንጂ አላመኑለትም:: ፈርዖንም በምድር ላይ በእርግጥ ይኮራ ነበር። እርሱም በእርግጥ ወሰን ካለፉት ነበር።"},{"id":84,"translation":"84. ሙሳም፡- «ህዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በእርሱ ላይ ብቻ ተጠጉ:: ታዛዦች እንደ ሆናችሁም በአላህ ላይ ብቻ ተመኩ።» አለ::"},{"id":85,"translation":"85. አሉ፡- «በአላህ ላይ ተጠጋን:: ጌታችን ሆይ! ለበደለኞች ህዝቦች መፈተኛ አታድርገን::"},{"id":86,"translation":"86. «በእዝነትህም ከከሓዲያን ህዝቦች ግፍ አድነን።»"},{"id":87,"translation":"87. ወደ ሙሳና ወደ ወንድሙ፡ «ለህዝቦቻችሁ በግብጽ ውስጥ ቤቶችን ሥሩ:: ቤቶቻችሁንም መስገጃ አድርጉ:: ሶላትንም በደንቡ ስገዱ:: ምዕመናኖቹንም አብስር።» ስንል ላክን::"},{"id":88,"translation":"88. ሙሳም: «ጌታችን ሆይ! አንተ ለፈርዖንና ለሹሞቹ በቅርቢቱ ህይወት ጌጥን ብዙ ገንዘቦችንም በእርግጥ ሰጠህ:: ጌታችን ሆይ! ከመንገድህ ያሳስቱ ዘንድ ሰጠሃቸው:: ጌታችን ሆይ! ገንዘቦቻቸውን አጥፋ:: በልቦቻቸዉም ላይ አትም:: አሳማሚን ቅጣት አስከሚያዩ አያምኑምና።» አለ።"},{"id":89,"translation":"89. (አላህም) ፡- «ጸሎታችሁ ተሰምታለች:: ቀጥም በሉ:: የእነዚያን የማያውቁትን ሰዎች መንገድ አትከተሉ።» አላቸው::"},{"id":90,"translation":"90. የኢስራኢል ልጆችን ባህሩን አሳለፍናቸው:: ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው:: የመስመጥ አደጋ ባገኘውም ጊዜ «አመንኩ:: እነሆ ከዚያ የእሥራኤል ልጆች ካመኑበት አምላክ በስተቀር ሌላ የእውነት አምላክ የለም:: እኔም ከታዛዦቹ (ሙስሊሞች) አንዱ ነኝ።» አለ::"},{"id":91,"translation":"91. «ከአሁን በፊት በእርግጥ ያመጽክና ከአጥፊዎችም የነበርክ ስትሆን አሁን ታምናለህን?» ተባለ።"},{"id":92,"translation":"92. እናም ዛሬ ከኋላህ ለሚመጡ ትውልዶች ተዓምር ትሆን ዘንድ አካልህን (ከባሕሩ) እናወጣሀለን ከሰዎችም ብዙዎቹ ከተዐምሮቻችን በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው::"},{"id":93,"translation":"93. የኢስራኢልን ልጆችም ምስጉንን ስፍራ በእርግጥ አሰፈርናቸው:: ከመልካም ሲሳዮችም ሰጠናቸው:: እውቀትም እስከመጣላቸው ድረስ አልተለያዩም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በእርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው ይፈርዳል::"},{"id":94,"translation":"94. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)) ወደ አንተ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ከሆንክ እነዚያን ካንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ሰዎች ጠይቅ:: እውነቱ ከጌታህ ዘንድ መጥቶልሃል:: እናም ከተጠራጣሪዎች አትሁን::"},{"id":95,"translation":"95. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነዚያ የአላህን አናቅጽ ካስተባበሉት ሰዎች አትሁን:: ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና::"},{"id":96,"translation":"96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ የጌታህ ቃል የተረጋገጠባቸው ሰዎች አያምኑም::"},{"id":97,"translation":"97. ተዓምራት ሁሉ ቢመጣላቸዉም አሳማሚን ቅጣት እስከሚያዩ ድረስ(አያምኑም)::"},{"id":98,"translation":"98. ከነብዩ ዩኑስ በፊት ካለፉት ከተሞች ያመነችና እምነት የጠቀማት ከተማ ለምን አልኖረችም? ግን የነብዩ ዩኑስ ህዝቦች ባመኑ ጊዜ በቅርቢቱ ህይወት የውርደትን ቅጣት ከእነርሱ ላይ አነሳንላቸው:: እስከ ጊዜም ድረስ አጣቀምናቸው::"},{"id":99,"translation":"99. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በሻ ኖሮ በምድር ያሉት ሁሉ በአንድ የተሰበሰቡ ሆነው ባመኑ ነበር:: ታዲያ አንተ ሰዎችን አማኞች እንዲሆኑ ታስገድዳለህን?"},{"id":100,"translation":"100. ማንኛዋም ነፍስ በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ የምታምን አይደለችም:: ከእነዚያ በማያውቁት ላይ ርክሰትን ያደርጋል::"},{"id":101,"translation":"101. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉትን ተዓምራት ተመልከቱ።» በላቸው:: ሆኖም ተዓምራትና አስፈራሪዎች ለማያምኑ ህዝቦች ምንም አይጠቅሙም::"},{"id":102,"translation":"102. የእነዚያን ከእነርሱ በፊት ያለፉትን ህዝቦች ቀኖች ብጤ ያገኟቸውን አይነት ቀናትን እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተም ተጠባበቁ እኔም ከናንተው ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ።» በላቸው::"},{"id":103,"translation":"103. መልዕክተኞቻችንንና እነዚያን ያመኑትንም ከጭንቅ ሁሉ እናድናለን:: እንደዚሁም ምእምናንን (ከጭንቅ ሁሉ) እናድናለን፡፡ ይህ በእኛ ላይ ተረጋገጠ::"},{"id":104,"translation":"104. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! ከእኔ ሃይማኖት በመጠራጠር ውስጥ ከሆናችሁ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አልገዛም:: ይልቁንም ያንን የሚገድላችሁን አላህን ብቻ እገዛለሁ:: ከትክክለኛ አማኞች እንድሆንም ታዝዣለሁ።» በላቸው።"},{"id":105,"translation":"105. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ፊትህን ወደ ቀጥታው መንገድ ያዘነበልክ ስትሆን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ:: ከአጋሪዎቹም አትሁን::"},{"id":106,"translation":"106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከአላህ በስተቀር የማይጠቅምህንና የማይጎህዳን አትገዛ:: ይህን ብትሠራ ግን ያን ጊዜ ከበደለኞቹ ትሆናለህ (ተብያለሁ» በላቸው)::"},{"id":107,"translation":"107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ጉዳትን ቢያደርስብህ ከእርሱ ሌላ ለእርሱ ገላጭ የለዉም:: በጎ ነገርም ቢሻልህ ለችሮታው መላሽ ማንም የለም:: ከባሮቹ የሚሻውን በእርሱ ይለይበታል:: እርሱም መሓሪውና አዛኙ ነው::"},{"id":108,"translation":"108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እውነቱ ከጌታችሁ በእርግጥ መጣላችሁ:: በእርሱ የተመራም የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው:: የተሳሳተም የሚሳሳተው ጉዳቱ በራሱ ላይ ብቻ ነው:: እኔ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም።» በላቸው::"},{"id":109,"translation":"109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ አንተ የሚወረደውን ነገር ተከተል:: አላህ በእነርሱና ባንተ መካከል ባለው ጉዳይ ላይ እስከሚፈርድ ድረስ ታገሥ:: እርሱም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ፈራጅ ነውና::"}]},{"id":11,"verses":[{"id":1,"translation":"1.አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤. ይህ ቁርኣን አናቅጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ፤ ጥበበኛና ውስጠ አዋቂ ከሆነው (አምላክ) ዘንድ የተወረደ መጽሐፍ ነው::"},{"id":2,"translation":"2. መልዕክተኛው (እንዲህ በሚልበት ሰዎች ሆይ! ): «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ:: እኔ ለእናንተ ከእርሱ ዘንድ የተላኩ አስፈራሪና አብሳሪ ነኝ።»"},{"id":3,"translation":"3. (እንዲህም በሚልበት ሰዎች ሆይ! ): «ጌታችሁን ምህረት ለምኑት:: ከዚያ ወደ እርሱ ተመለሱ:: እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መልካምን መጥቀም ይጠቅማችኋል:: ለትሩፋት ባለቤት ሁሉ ችሮታውን (ምንዳዉን) ይሰጠዋል:: ብትሸሹም እኔ በእናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ::"},{"id":4,"translation":"4. «መመለሻችሁ ወደ አላህ ብቻ ነው። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።»"},{"id":5,"translation":"5. ሙስሊሞች ሆይ! አስተውሉ! እነርሱ ከእርሱ ከአላህ ይደበቁ ዘንድ ደረቶቻቸውን ያጥፋሉ:: ሙስሊሞች ሆይ! አስተውሉ! ልብሶቻቸውን በሚከናነቡ ጊዜ የሚደብቁትንም ሆነ የሚገልጹትን ሁሉ ያውቃል:: እርሱ በደረቶች ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነውና::"},{"id":6,"translation":"6. በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለና ማረፊያዋንም ሆነ መርጊያዋን የሚያውቅ ቢሆን እንጂ:: ሁሉም ነገር ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ነው::"},{"id":7,"translation":"7. አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ ነው:: ዐርሹም በውሃ ላይ ነበር:: የትኛችሁ ስራችሁ ያማረ መሆኑ ይፈትናችሁ ዘንድ ፈጠራችሁ:: «እናንተ ከሞት በኋላ በእርግጥ ተቀስቃሾች ናችሁ» ብትልም። እነዚያ የካዱት «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።» ይላሉ::"},{"id":8,"translation":"8. ቅጣቱንም ለተቆጠሩ ጥቂት ጊዜያቶች ብናቆይላቸው «ከመውረድ የሚከለክለው ምንድን ነው?» ይላሉ:: ሙስሊሞች ሆይ! አስተውሉ:: በሚመጣባቸው ቀን ከእነርሱ ላይ ተመላሽ አይደለም:: በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩትም ቅጣት በእነርሱ ላይ ይወርድባቸዋል::"},{"id":9,"translation":"9. ሰውንም ከችሮታችን ብናቀምሰውና ከዚያ ብንወስድበት እርሱ ተስፋ ቆራጭና ክህደተ ብርቱ ነው::"},{"id":10,"translation":"10. ካገኘችዉም ችግር በኋላ ጸጋዎቻችንን ብናቀምሰው «ችግሮች ከእኔ ላይ ተወገዱ።» ይላል:: አያመሰግንም:: እርሱ ተደሳችና ጉረኛ ነውና::"},{"id":11,"translation":"11. እነዚያ የታገሱና መልካም ሥራዎችንም የሰሩ ሁሉ እነዚያ ለእነርሱ ምህረትና ታላቅ ምንዳ አለላቸው::"},{"id":12,"translation":"12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርሱ ላይ (የሀብት) ድልብ ለምን አልተወረደም? ወይም ከእርሱ ጋር መልአክ ለምን አልመጣም?» ማለታቸውን በመፍራት ወደ አንተ ከሚወርደው ከፊሉን ልትተው በእርሱም ልብህ ጠባብ ሊሆን ይፈራልሃል:: አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ (ወኪል) ተጠባባቂ ነው::"},{"id":13,"translation":"13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም «ቁርኣንን ቀጣጠፈው» ይላሉን? «እውነተኞች እንደሆናችሁ ብጤው የሆኑን አስር የተቀጣጠፉ ምዕራፎች እስቲ አምጡ:: ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን ረዳት ጥሩ።» በላቸው።"},{"id":14,"translation":"14. ለእናንተ ምላሽ ካልሰጧችሁ «(ጣዖት አምላኪያን ሆይ!) የተወረደው በአላህ እውቀት ብቻ መሆኑንና ከእርሱ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም እወቁ:: እናም አትሰልሙምን?» በላቸው።"},{"id":15,"translation":"15. ቅርቢቱን ህይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሁሉ ሥራዎቻቸውን ምንዳዋን በእርሷ ውስጥ ወደ እነርሱ እንሞላላቸዋለን:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸዉም::"},{"id":16,"translation":"16. እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ከእሳት በስተቀር የሌላቸው ናቸው:: የሰሩትም ሥራ በእርሷ ውስጥ ተበላሸ:: በቅርቢቱ ዓለም ይሰሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው::"},{"id":17,"translation":"17. ከጌታው ዘንድ አስረጅ የደረሰውንና ከእርሱም የሆነ መስካሪ የሚከተለው ከቁርኣን በፊትም ለሙሳ መጽሐፍ መሪና እዝነት ሲሆን የመሰከረለት (ሰውና) የቅርቢቱን ህይወት እንደሚሻው (ሰው) ነውን? እነዚያ በእርሱ (ቁርኣን) ያምናሉ:: ከአህዛቦቹ በእርሱ የሚክድ ሰው ሁሉ መመለሻው እሳት ናት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእርሱም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን:: እሱ ከጌታህ ዘንድ የሆነ እውነት ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም::"},{"id":18,"translation":"18. በአላህ ላይ ውሸትን ከሚቀጣጥፍ ይበልጥ በዳይ ማነው? እነዚያ በጌታቸው ላይ ይቀረባሉ:: መስካሪዎቹም «እነዚህ በጌታቸው ላይ የዋሹት ናቸው።» ይላሉ:: «አስተዉሉ! የአላህ እርግማን በበዳዮች ላይ ብቻ ይሁን።» ይባላል።"},{"id":19,"translation":"19. እነርሱም እነዚያ ከአላህ መንገድ ሰዎችን የሚከለክሉ የአላህን መንገድ መጥመሟንም የሚሹት ናቸው:: እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከሓዲያን ናቸው።"},{"id":20,"translation":"20. እነዚያም በምድር ውስጥ ከአላህ የሚያመልጡ አልነበሩም:: ከአላህ ሌላ ለእነርሱ ረዳቶች አልነበሯቸዉም:: ለእነርሱ ቅጣቱ ይደራረብላቸዋል:: እውነትን መስማትን የሚችሉ አልነበሩም:: የሚያዩም አልነበሩም::"},{"id":21,"translation":"21. እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩና ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር የጠፋባቸው ናቸው::"},{"id":22,"translation":"22. እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም በጣም ከሳሪዎቹ ለመሆናቸው ጥርጥር የለዉም።"},{"id":23,"translation":"23. እነዚያ ያመኑትና በጎ ሥራዎችን የሠሩት ወደ ጌታቸዉም የተዋረዱት እነዚያ የገነት ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው::"},{"id":24,"translation":"24. የሁለቱ ክፍሎች ምሳሌ አይኑ የማያይ አይነ ስውር፤ ጆሮው የማይሰማ ደንቆሮ ሰውና አይኑ የሚያይ ጆሮው የሚሰማ ሰው ብጤ ነው:: ሁለቱ በምሳሌነት ይስተካከላሉን? አትገሰጹንም?"},{"id":25,"translation":"25. ኑሕን ወደ ህዝቦቹ ላክንና አላቸዉም: «እኔ ለእናንተ ግልጽ አስፈራሪ ነኝ።"},{"id":26,"translation":"26. «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ። እኔ ለእናንተ የአሳማሚን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁና።»"},{"id":27,"translation":"27. ከህዝቦቹም መካከል እነዚያ የካዱት መሪዎች «ብጤያችን ሰው ሆነህ እንጂ አናይህም:: እነዚያም እነርሱ ሐሳበ ጥሬዎች የሆኑት ወራዶቻችን እንጂ ሌላ ተከትሎህ አናይህም:: ለእናንተም በእኛ ላይ ምንም ብልጫን አናይም:: ከቶውንም ውሸታሞች መሆናችሁን እንጠረጥራችኋለን።» አሉ።"},{"id":28,"translation":"28. እርሱም አላቸው: «ህዝቦቼ ሆይ! እስቲ ንገሩኝ ከጌታዬ በግልጽ ማስረጃ ላይ ሆኜ ከእርሱም ዘንድ የሆነን ችሮታ ነብይነት ቢሰጠኝና በእናንተ ላይ ግን ይህች እውነታ ብትደበቅባችሁ እናንተ ለእርሷ ጠይዎች ስትሆኑ እርሷን በመቀበል እናስገድዳችኋለንን?"},{"id":29,"translation":"29. «ህዝቦቼ ሆይ! በእርሱ የተላክሁበትን በማድረስ ላይ ገንዘብን አልጠይቃችሁም:: ምንዳዬ ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለም:: እኔም እነዚያን በአላህ ያመኑትን ከአጠገቤ አባራሪ አይደለሁም:: እነርሱ ከጌታቸው ጋር የሚገናኙ ናቸውና:: ግን እኔም የምትሳሳቱ ህዝቦች ሆናችሁ አያችኋለሁ::"},{"id":30,"translation":"30. «ህዝቦቼ ሆይ! ባባርራቸው ከአላህ ቅጣት የሚያድነኝ ማን ነው? አትገሰጹምን?"},{"id":31,"translation":"31. «ለናንተም እኔ ዘንድ የአላህ ግምጃ ቤቶች አሉ:: ሩቅንም አውቃለሁ አልላችሁም:: እኔም መልአክ ነኝ አልላችሁም:: ለእነዚያም ዓይኖቻችሁ ለሚያዋርዷቸው አላህ ደግ ነገርን እምነትን አይሰጣቸዉም አልልም:: አላህ በነፍሶቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ ነገር አዋቂ ነው:: እኔ ያን ጊዜ ከበደለኞች እሆናለሁና።» አላቸው።"},{"id":32,"translation":"32. «ኑህ ሆይ! በእርግጥ ተከራከርከን:: እኛን መከራከርህንም አበዛህ:: ከእውነተኞቹም ከሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት አምጣው እስቲ።» አሉ።"},{"id":33,"translation":"33. አላቸውም: «እርሱን የሚያመጣባችሁ አላህ የፈለገ ከሆነ ብቻ ነው። እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም።"},{"id":34,"translation":"34. «እናንተም አላህ ሊያጠማችሁ ፈልጎ ከሆነ ልመክራችሁ ብፈልግም ምክሬ አይጠቅማችሁም:: እርሱ ጌታችሁ ነው:: ወደ እርሱም ብቻ ትመለሳላችሁ።» አላቸው።"},{"id":35,"translation":"35. ይልቁንም ቀጠፈው ይላሉን? (ሙሐመድ ሆይ) «ብቀጥፈው ኃጢአቴ ቅጣቱ በእኔ ላይ ነው:: እኔም ከምታጠፉት ጥፋት ሁሉ ንጹህ ነኝ።» በላቸው።"},{"id":36,"translation":"36. ወደ ኑህም (እንዲህ በሚል) ተወረደ: «እነሆ ከህዝቦችህ በእርግጥ ካመኑት በስተቀር ወደፊት ሌሎች አያምኑም:: ይሠሩትም በነበሩት ክህደት አትዘን።"},{"id":37,"translation":"37. «በጥበቃችንና በትዕዛዛችን ሆነህ መርከቢቱን ሥራ። በእነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታናግረኝ። እነርሱ በእርግጥ የሚሰምጡ ናቸውና።» አለው።"},{"id":38,"translation":"38. ከወገኖቹም መሪዎቹ በእርሱ አጠገብ ባለፉ ቁጥር በእርሱ ላይ እየተሳለቁበት መርከቢቱን ይሠራል። አላቸውም: «በእኛ ብትሳለቁ እኛም እንደተሳለቃችሁብን በእናንተ እንሳለቅባችኋለን።"},{"id":39,"translation":"39. «የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትን በእርሱም ላይ ዘውታሪ ቅጣት የሚሰፍርበትን ማንነት ወደ ፊት ታውቃላችሁ።» አላቸው።"},{"id":40,"translation":"40. ትዕዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ «በመርከቧ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት (ወንድና ሴት) ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን።» አልነው:: ከእርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም ነበር::"},{"id":41,"translation":"41. «‹መሄዷም መቆሟም በአላህ ስም ነው።› እያላችሁ በእርሷ ተሳፈሩ:: ጌታዬ መሓሪና አዛኝ ነውና።» አላቸው።"},{"id":42,"translation":"42. እርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ እነርሱን ይዛቸው የምትንሻለል ስትሆን (በአላህ ስም ተቀመጡባት።) ኑህም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ «ልጄ ሆይ! ከእኛ ጋር ተሳፈር። ከከሓዲያንም አትሁን።» ሲል ጠራው።"},{"id":43,"translation":"43. ልጁም «ከውሃው ወደሚጠብቀኝ ተራራ እጠጋለሁ።» አለ:: አባቱም «ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም:: እርሱ ብቻ ያዘነለት ካልሆነ በስተቀር።» አለው:: ማዕበሉም በመካከላቸው ጋረደ:: ልጁም ከሰማጮች ሆነ::"},{"id":44,"translation":"44. ተባለም «ምድር ሆይ! ዉሃሽን ዋጪ:: ሰማይ ሆይ! ዝናብሽን ያዢ።» ውሃዉም ሠረገ:: ቅጣቱም ተፈጸመ:: ጁዲይ በሚባለም ተራራ ላይ መርከቢቱ ተደላደለች:: «ለከሓዲያን ጥፋት ተገባቸው (ጥፉ)።» ተባለ።"},{"id":45,"translation":"45. ኑህም ጌታውን- «ጌታዬ ሆይ! ልጄ ከቤተሰቤ አንዱ ነው:: ቃል ኪዳንህም እውነት ነው:: አንተም ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ አዋቂ ነህ።» በማለት ጠየቀ (ተጣራ)::"},{"id":46,"translation":"46. አላህም «ኑህ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም:: እርሱ መልካም ያልሆነ ስራ ነው:: በእርሱ እውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ:: እኔ ከአላዋቂዎች እንዳትሆን እገስጽሃለሁ።» አለው::"},{"id":47,"translation":"47. «ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ለእኔ እውቀት የሌለኝን ነገር የምጠይቅህ ከመሆን እኔ ባንተ እጠበቃለሁ:: ለእኔም ባትምረኝና ባታዝንልኝ ከከሳሪዎቹ እሆናለሁ።» አለ።"},{"id":48,"translation":"48. «ኑህ ሆይ! ከእኛ በሆነ ሰላም ባንተ ላይና አንተም ጋር ባሉት ህዝቦች ላይ በሆኑ በረከቶችም የተጎናጸፍክ ሆነህ ወደ ምድር ውረድ:: ከነሱው ዘሮች የሆኑ ህዝቦችም በቅርቢቱ ዓለም በእርግጥ እናስመቻቸዋለን:: ከዚያም ከእኛ የሆነ አሳማሚ ቅጣት ይደርስባቸዋል።» ተባለ።"},{"id":49,"translation":"49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ዘገባ ከሩቁ ወሬዎች መካከል ወደ አንተ ያወረድነው ነው:: አንተም ሆንክ ህዝቦችህ ከዚህ በፊት የምታውቁት አልነበራችሁም:: ታገሥ ምስጉን የሆነችው ፍጻሜ ለሚጠነቀቁት ብቻ ናትና::"},{"id":50,"translation":"50. ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን:: አላቸው፡ «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: እናንተ ቀጣፊዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም::"},{"id":51,"translation":"51. «ህዝቦቼ ሆይ! በእርሱ (በማድረሴ) ላይም ምንዳን አልጠይቃችሁም:: ምንዳዬ በዚያ በፈጠረኝ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም:: አታውቁምን?"},{"id":52,"translation":"52. «ህዝቦቼ ሆይ! ጌታችሁን ምህረትን ለምኑት:: ከዚያ ወደ እርሱ ተጸጸቱ:: ዝናብን በእናንተ ላይ ተከታታይ አድርጎ ይልክላችኋልና:: ወደ ኃይላችሁም ሀይልን ይጨምርላችኋል:: አመጸኞችም ሆናችሁ አትሽሹ::»"},{"id":53,"translation":"53. እነርሱም አሉ፡- «ሁድ ሆይ! በአስረጂ አልመጣህልንም:: እኛም ላንተ ንግግር ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው አይደለንም:: እኛም ላንተ ትክክለኛ አማኞች አይደለንም።"},{"id":54,"translation":"54. «ከፊሎቹ አማልክቶቻችን በክፉ ነገር በዕብደት ለክፈውሃል እንጂ ሌላን አንልም።» አሉ:: እርሱም አላቸው: «እኔ አላህን አስመሰክራለሁ:: ከምታጋሩትም እኔ ንጹህ መሆኔን መስክሩ።"},{"id":55,"translation":"55. «ከእርሱ ሌላ አማልክትን ከምታጋሩት ንጹህ ነኝ። ሁላችሁም ሆናችሁ ተንኮልን ሥሩብኝ ከዚያ አታቆዩኝ።"},{"id":56,"translation":"56. «እኔ ጌታዬና ጌታችሁ በሆነው በአላህ ላይ ብቻ ተመካሁ:: በምድር ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም እርሱ አናትዋን የያዛት ብትሆን እንጂ:: ጌታዬ (ቃሉም ሥራዉም) በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነው።"},{"id":57,"translation":"57. «ብትዞሩም ወደ እናንተ የተላኩበትን ነገር በእርግጥ አድርሼላችኋለሁ:: ጌታዬም ሌላን ህዝብ ይተካል:: ምንም አትጎዱትም:: ጌታዬ በሁሉ ነገር ላይ ተጠባባቂ ነውና።» አላቸው::"},{"id":58,"translation":"58. ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ሁድንና እነዚያን ከእሱጋ ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን:: ከብርቱ ቅጣትም አዳናቸው::"},{"id":59,"translation":"59. ይህ ነገድ ዓድ ነው:: በጌታቸው ታዐምራት ካዱ:: መልዕክተኞቹንም አመጹ:: የኃያል ሞገደኛን ሁሉ ትዕዛዝም ተከተሉ::"},{"id":60,"translation":"60. በዚች በቅርቢቱ ዓለምም እርግማን እንዲከተላቸው ተደረጉ:: በትንሳኤም ቀን እንደዚሁ:: አስተውሉ! ዓዶች ጌታቸውን ካዱ። አስተውሉ! የሁድ ህዝቦች ለሆኑት ዓዶች ከእዝነት መራቅ ይገባቸው::"},{"id":61,"translation":"61. ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን። «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም:: እርሱ በምድር ፈጠራችሁ:: በውስጧ እንድታለሟትም አደረጋችሁ:: ምህረቱንም ለምኑት:: ከዚያም ወደ እርሱ ተመለሱ:: ጌታዬ ለሁሉም ቅርብና ለለመነው ተቀባይ ነውና።» አላቸው።"},{"id":62,"translation":"62. እነርሱም «ሷሊህ ሆይ! ከዚህ በፊት በእኛ ውስጥ መሪ ልትሆን በእርግጥ የምትከጀል የነበርክ ስትሆን:: አባቶቻችን የሚገዙትን ከመገዛት ትከለክለናለህን? እኛም ወደሱ ከምትጠራን ነገር በእርግጥ አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ነን።» አሉ።"},{"id":63,"translation":"63. ሷሊህም አለ: «ህዝቦቼ ሆይ! እስቲ ንገሩኝ ከጌታዬ በሆነ ማስረጃ ላይ ሆኜ ከእርሱም የሆነን ችሮታ ነብይነት ቢሰጠኝና ባልታዘዘው ከአላህ ቅጣት የሚያድነኝ ማነው? ከማጥፋትም በስተቀር ምንም አትጨምሩልኝም።"},{"id":64,"translation":"64. «ህዝቦቼ ሆይ! ይህች ለእናንተ ታዓምር ስትሆን የአላህ ግመል ናት:: ተዋትም በአላህ ምድር ውስጥ ትብላ:: በክፉም አትንኳት። ቅርብ የሆነ ቅጣት ያገኛችኋልና።» አለ።"},{"id":65,"translation":"65. ወግተው ገደሏትም ሷሊህም «በሀገራችሁም ሶስትን ቀናት ብቻ ተጠቀሙ ይህ የማይዋሽ ቀጠሮ ነው።» አላቸው::"},{"id":66,"translation":"66. እናም ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ሷሊህንና እነዚያን ከእሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው እዝነት አዳንን:: ከዚያም ቀን ውርደት አዳንናቸው:: ጌታህ ብርቱውና ሁሉን አሸናፊው ነውና::"},{"id":67,"translation":"67. እነዚያን የበደሉትንም ከባድ ጩኸት ያዛቸው:: በየቤቶቻቸዉም ውስጥ የተንበረከኩ ሙት በድን ሆነው አደሩ(አነጉ)::"},{"id":68,"translation":"68. በእርሷ ውስጥ እንዳልኖሩ ሆኑ:: አስተውሉ! ሠሙዶች ጌታቸውን በእርግጥ ካዱ:: አስተውሉ! ለሠሙዶች ከአላህ እዝነት መራቅ ተገባቸው::"},{"id":69,"translation":"69. መልዕክተኞቻችንም ወደ ኢብራሂም በልጅ መውለድ ብስራት መጡለትና ሰላም አሉት:: እሱም ሰላም አላቸው:: ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ::"},{"id":70,"translation":"70. እጆቻቸዉም ወደ ምግቡ የማይደርሱ መሆናቸውን ባየ ጊዜ ተግባራቸው እንግዳ ሆነበት:: ከእነርሱም ፍርሃት ተሰማው:: «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ህዝቦች ተልከናልና።» አሉት።"},{"id":71,"translation":"71. ሚስቱም ቁማ ነበርና ሳቀች:: እናም በኢስሓቅ አበሰርናት:: ከኢስሐቅም በኋላ በልጁ በየዕቁብ አበሰርናት::"},{"id":72,"translation":"72. እርሷም «ዋልኝ እኔ አሮጊት ይህም ባለቤቴ ሽማግሌ ሆኖ ሳለ እወልዳለሁን? ይህ በእርግጥ አስደናቂ ነገር ነው።» አለች።"},{"id":73,"translation":"73. «በአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን? :: የአላህ እዝነትና በረከት በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን:: እሱ ምስጉንና ለጋሽ ነውና።» አሉ።"},{"id":74,"translation":"74. ከኢብራሂም ፍራቻው በሄደለትና ብስራት በመጣችለት ጊዜ በሉጥ ህዝቦች ነገር ይከራከረን ጀመር::"},{"id":75,"translation":"75. ኢብራሂም በእርግጥ ታጋሽ፤ አልቃሻ (እጅግ የሚማፀን) እና መላሳ ነውና::"},{"id":76,"translation":"76. (እነርሱም አሉት): «ኢብራሂም ሆይ! ይህን ክርክር ተው:: እነሆ የጌታህ ትዕዛዝ በእርግጥ መጥቷል:: እነርሱም የማይመለስ ቅጣት የሚመጣባቸው ናቸው።»"},{"id":77,"translation":"77. መልዕክተኞቻችንም ወደ ሉጥ በመጡ ጊዜ በእነርሱ ምክንያት አዘነ:: ልቡም በእነርሱ ተጨነቀ:: «ይህ ብርቱ ቀን ነዉ።» አለም።"},{"id":78,"translation":"78. ህዝቦቹም ወደ እርሱ እየተጣደፉ መጡና ከዚህም በፊት መጥፎ ሥራዎችን ይሠሩ ነበር:: «ህዝቦቼ ሆይ! እነዚህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው:: ለእናንተ ይልቅ በጣም የጸዱ ናቸው:: አግቧቸው እናም አላህን ፍሩ:: በእንግዶቼም አታሳፍሩኝ። ከናንተ ውስጥ አንድ ቅን ሰው እንኳን የለምን?» አላቸው::"},{"id":79,"translation":"79. «ከሴቶች ልጆችህ እኛ ምንም ጉዳይ የሌለን መሆኑን በትክክል ታውቃለህ:: አንተም የምንሻውን በእርግጥ ታውቃለህ።» አሉት።"},{"id":80,"translation":"80. «በእናንተ ላይ ኃይል በኖረኝ ወይም ወደ ብርቱ ወገን ብጠጋ ኖሮ (የምሠራውን በሠራሁ ነበር)።» አላቸው።"},{"id":81,"translation":"81. «ሉጥ ሆይ! እኛ የጌታህ መልዕክተኞች ነን:: ህዝቦች ወደ አንተ በክፉ አይደርሱብህም:: ቤተሰብህንም ይዘህ ከሌሊቱ በከፊሉ ውስጥ ሂድ:: ከናንተም አንድም ወደ ኋላው አይገላመጥ:: ሚስትህ ብቻ ስትቀር:: እነሆ እርሷንማ እነርሱን የሚያገኛቸው ስቃይ ሁሉ ያገኛታልና:: ቀጠሯቸው ንጋቱ ላይ ነው:: ንጋቱ ቅርብ አይደለምን?» አሉት።"},{"id":82,"translation":"82. እናም ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ከተማይቱን ላይዋን ከታችዋ አድርገን ገለበጥናት:: ተከታታይም የሆነን የሸክላ ድንጋይ በእርሷ ላይ አዘነብንባት::"},{"id":83,"translation":"83. ከጌታህ ዘንድ ምልክት የተደረገባት ስትሆን (አዘነብናት)። እርሷም (መንደሯ) ከበደለኞቹ ህዝቦች ሩቅ አይደለችም::"},{"id":84,"translation":"84. ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን:: አላቸውም: «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም:: ስፍርንና ሚዛንን አታጉሉ:: እኔ በጸጋ ላይ ሆናችሁ አያችኋለሁ:: እኔም በእናንተ ላይ የከባቢን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ::"},{"id":85,"translation":"85. «ህዝቦቼ ሆይ! ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ:: ሰዎችን መብቶቻቸውን አታጓድሉባቸው:: በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ።"},{"id":86,"translation":"86. «አላህ ያስቀረላችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው:: ትክክለኛ አማኞች እንደ ሆናችሁ አላህ በሰጣችሁ ውደዱ። እኔም መካሪ እንጂ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም።»"},{"id":87,"translation":"87. «ሹዐይብ ሆይ! ስግደትህ አባቶቻችን የሚገዙትን ጣኦታት እንድንተው ወይም በገንዘቦቻችን የምንሻውን መሥራትን እንድንተው ታዝሃለችን? አንተ በእርግጥ ታጋሹ ቅኑው አንተ ነህና።» አሉት።"},{"id":88,"translation":"88. (እርሱም) አለ: «ህዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ እስቲ ከጌታዬ በሆነ አስረጅ ላይ ሆኜ ከእርሱም የሆነን መልካም ሲሳይ ቢሰጠኝ በቅጥፈት ልቀላቅለው ይገባልን? የከለከልኳችሁንም ነገር በመፈጸም ልለያችሁ አልሻም:: በተቻለኝ ያህል ማበጀትን እንጂ አልሻም:: ለደግ ሥራ መታደሌ በአላህ ፈቃድ ብቻ እንጂ በሌላ አይደለም:: በእርሱ ላይ ብቻ ተመካሁ:: ወደ እርሱም እመለሳለሁ።"},{"id":89,"translation":"89. «ወገኖቼ ሆይ! እኔን መከራከራችሁ የኑህን ህዝቦች ወይም የሁድን ህዝቦች ወይም የሷሊህን ህዝቦች ያገኛቸው ቅጣት ብጤ አይነት እንዲያገኛችሁ አይገፋፋችሁ:: የሉጥም ህዝቦች ከናንተ ሩቅ አይደሉም።"},{"id":90,"translation":"90. «ጌታችሁንም ምህረት ለምኑት ከዚያ ወደ እርሱ ተመለሱ። ጌታዬ አዛኝና ወዳድ ነውና።» አለ።"},{"id":91,"translation":"91. «ሹዐይብ ሆይ! ከምትለው ነገር ብዙውን አናውቀዉም (አይገባንም):: እኛም አንተን በኛ ውስጥ ደከማ ሆነህ እናይሃለን:: ጎሶችህም ባልኖሩ ኖሮ በወገርንህ ነበር:: አንተም በእኛ ላይ የተከበርክ አይደለህም።» አሉት::"},{"id":92,"translation":"92. (እርሱም) አለ: «ህዝቦቼ ሆይ? ጎሳዎቼ በእናንተ ላይ ከአላህ ይልቅ የከበሩ ናቸውን? አላህን ከኋላችሁ ወደ ጀርባ አደረጋችሁት:: ጌታዬ በምትሠሩት ሁሉ ከባቢ ነው።"},{"id":93,"translation":"93. «ህዝቦቼ ሆይ! በችሎታችሁ ልክ ሥሩ እኔ ሠሪ ነኝ። የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትንና እርሱ ውሸታም የሆነው ማን እንደ ሆነ ወደ ፊት ታውቃላችሁ:: ጠብቁም እኔም ከናንተ ጋር ተጠባባቂ ነኝና።» አለ።"},{"id":94,"translation":"94. ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ሹዐይብንና እነዚያን ከእርሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን:: እነዚያን የበደሉትንም (የጂብሪል) ጩኸት ያዘቻቸው። በየቤቶቻቸዉም ውስጥ ተንከፍርረው አደሩ::"},{"id":95,"translation":"95. በእርሷ ውስጥ እንዳልነበሩ ሆኑ:: አስተዉሉ! ሠሙድ ከአላህ እዝነት እንደራቀች መድየንም ትራቅ::"},{"id":96,"translation":"96. ሙሳንም በታዐምራቶቻችንና በግልጽ ብርሃን በእርግጥ ላክነው::"},{"id":97,"translation":"ወደ ፈርዖንና ወደስዎቹ ላክነው፡፡የፈርዖንን ነገር ህዝቦቹ ተከተሉ፡፡ የፈርዖን ነገር ቀጥተኛ አል ነበረም፡፡"},{"id":98,"translation":"በትንሳኤ ቀን ህዝቦቹን ይቀድማል፡፡ ከዚያም ወደ አሳት ያወርዳቸዋል፡፡ የሚገቡትም አገባብ ምንኛ ከፋ፡፡"},{"id":99,"translation":"99. በዚችም በቅርቢቱ ዓለም እርግማንን አስከተልናቸው:: በትንሳኤም ቀን እንደዚሁ። የተሰጡት ስጦታ ምንኛ ከፋ!"},{"id":100,"translation":"100. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ከላይ የተነገረው ከከተሞቹ ወሬዎች የተወሰነው ነው:: ባንተ ላይ እንተርከዋለን:: ከእርሷ ቋሚና እጭድም የሆነ አለ::"},{"id":101,"translation":"101. እኛም አልበደልናቸዉም:: ግን ነፍሶቻቸውን በደሉ:: የጌታህ ጉዳይ በመጣ ጊዜ እነዚያ ከአላህ ሌላ የሚገዟቸው አማልክቶቻቸው ሁሉ በምንም አላዳኗቸዉም:: ከማክሰርም በስተቀር ምንም አልጨመሩላቸዉም::"},{"id":102,"translation":"102. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ ቅጣት የከተሞችን ሰዎች በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ ልክ እንደዚህ ነው:: ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚና ብርቱ ነው::"},{"id":103,"translation":"103. በዚህ ውስጥ የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ለሚፈሩ ሁሉ መገሰጫ አለ:: ይህ የትንሳኤ ቀን ሰዎች በእርሱ የሚሰበሰቡበት ቀን ነው:: ይህ የሚጣዱት ቀን ነው::"},{"id":104,"translation":"104. ይህንን ቀን ለተቆጠረም (ለተወሰነ) ጊዜ እንጂ አናቆየዉም::"},{"id":105,"translation":"105. በሚመጣ ቀን ማንኛዉም ነፍስ በእርሱ ፈቃድ ቢሆን እንጂ አትናገርም:: ከእነርሱም መናጢም (እድለቢስ) እድለኛም አለ::"},{"id":106,"translation":"106. እነዚያ ያመጹትማ በእሳት ውስጥ ናቸው:: ለእነርሱ በእርሷ ውስጥ ማናፋትና መንሰቅሰቅ አላቸው::"},{"id":107,"translation":"107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ከፈለገው በስተቀር ሰማያትና ምድር እስከዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ በእሳት ውስጥ ይኖራሉ:: ጌታህ የሚፈልገውን ሠሪ ነውና::"},{"id":108,"translation":"108. እነዚያ እድለኞቹማ ጌታ ከሻው በስተቀር ሰማያትና ምድር እስከ ዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውታሪዎች ሆነው በገነት ውስጥ ይኖራሉ:: የማያቋርጥ ስጦታን ተሰጡ::"},{"id":109,"translation":"109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ከሓዲያን ከሚገዙት ጣኦት በመጠራጠር ውስጥ አትሁን:: አባቶቻቸው ከዚህ በፊት እንደሚገዙት እንጂ አይገዙም:: እኛም እነዚህን ፈንታቸውን የማይጓደል ሲሆን የምንሞላላቸው ነን::"},{"id":110,"translation":"110. ለሙሳም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው:: በእርሱም ተለያዩበት። ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በመካከላቸው አሁን ይፈረድ ነበር:: እነርሱም ከእርሱ ከቁርኣን አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ናቸው::"},{"id":111,"translation":"111. ሁሉንም ጌታህ ሥራዎቻቸውን ምንዳቸውን በእርግጥ ይሞላላቸዋል:: እርሱ በሚሠሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::"},{"id":112,"translation":"112. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደታዘዝከው ቀጥ በል። ካንተ ጋር ያመኑትም ቀጥ ይበሉ። ወሰንንም አትለፉ። እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::"},{"id":113,"translation":"113. ወደ እነዚያም ወደ በደሉት ህዝቦች አትዘንበሉ:: እሳት ትነካችኋለችና:: ከአላህ ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም ከዚያ አትረዱም::"},{"id":114,"translation":"114. ሶላትንም በቀን ጫፍና ጫፎች ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም:: መልካም ሥራዎች ኃጢአቶችን ያስወግዳሉና:: ይህ ለተገሳጮች ሁሉ ግሳጼ ነው::"},{"id":115,"translation":"115. ታገስ አላህ የበጎ ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና::"},{"id":116,"translation":"116. ከናንተ በፊት ከነበሩት ከክፍለ ዘመናት (ሰዎች) ውስጥ በምድር ላይ ከማበላሸት የሚከለክሉ የመልካም ሥራዎች ቅሪት ባለቤቶች ለምን አልነበሩም? ግን ከእነርሱ ያዳንናቸው ጥቂቶቹ ከለከሉና ዳኑ:: እነዚያም የበደሉት ሰዎች አልከለከሉም። በእርሱ የተቀማጠሉበትን ተድላ ተከተሉ አመጠኞችም ነበሩ::"},{"id":117,"translation":"117. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ከተሞችን ባለቤቶቻቸው መልካም ሠሪዎች ሆነው ሳሉ በመበደል የሚያጠፋቸው አልነበረም::"},{"id":118,"translation":"118. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በሻ ኖሮ ሰዎችን ሁሉ አንድ ህዝብ ባደረጋቸው ነበር። የተለያዩም ከመሆን አይወገዱም::"},{"id":119,"translation":"119. ጌታህ ያዘነለት ብቻ ሲቀር ከመለያየት አይወገዱም:: ለዚሁም ነው የፈጠራቸው:: የጌታህ ቃልም «ገሀነምን ከአጋንንትና ከሰዎች ከሁሉም በእርግጥ እሞላታለሁ።» በማለት ተፈጸመች::"},{"id":120,"translation":"120. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞቹም ዜናዎች ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናጸናበትን እንተርክልሀለን። በዚህችም ሱራ እውነቱ ነገር፣ ለምእምናን ግሳጼና ማስታወሻ መጥቶልሀል::"},{"id":121,"translation":"121. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያም ለማያምኑት (እንዲህ) በላቸው: «ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ሥሩ:: እኛ ሠሪዎች ነን።"},{"id":122,"translation":"122. «የራሳችሁን ውጤት ተጠባበቁ እኛ ተጠባባቂዎች ነንና።» በላቸው::"},{"id":123,"translation":"123. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሰማያትና በምድር ያለው ሚስጥር ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: ሁሉም ነገር ወደ እርሱ ብቻ ይመለሳል:: ስለዚህ እሱን ብቻ ተገዛው:: በእርሱም ላይ ብቻ ተመካ:: ጌታህም ከሚሰሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም::"}]},{"id":12,"verses":[{"id":1,"translation":"1.አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ እነዚህ አናቅጽ ግልጽና የተብራራ ከሆነው መጽሐፍ አናቅጽ ናቸው።"},{"id":2,"translation":"2. እኛ ይህንን ቁርኣንን ትረዱት ዘንድ በዐረበኛ ቋንቋ አወረድነው።"},{"id":3,"translation":"3.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህንን የቁርኣን ወደ አንተ በማውረዳችን እጅግ ውብና ማራኪ የሆነ ታሪክ እንተርክልሃለን:: ከዚህ በፊት አንተም ይህንን ታሪክ ከማያውቁት ነበርክ::"},{"id":4,"translation":"4. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነብዩ ዩሱፍ በልጅነቱ ለአባቱ «አባቴ ሆይ! እኔ አስራ አንድ ኮከቦችን፤ ጨረቃንና ጸሐይን ሲሰግዱልኝ በሕልሜ አየሁኝ።» ባለ ጊዜ የሆነውን ታሪክ ለህዝቦችህ አስታውስ።"},{"id":5,"translation":"5. አባቱም አለ: «ልጄ ሆይ! ይህን ህልምህን ለወንድሞችህ አትንገር። ባንተ ላይ ተንኮል እንዳያሴሩ። ምክንያቱም ሰይጣን ለሰው ልጅ ሁልጊዜም ግልጽ ጠላት ነውና።"},{"id":6,"translation":"6. «ጌታህ ልክ ይህን ህልም እንዳሳየህ ሁሉ ለነብይነትም ይመርጥሃል:: የንንግግሮችን ፍፃሜ ያስተምርሃል:: ጸጋውንም ቀደም ሲል ለአባቶችህ ለኢብራሂምና ለኢስሃቅ እንደሞላ ሁሉ ላንተና ለያዕቁብ ቤተሰቦችም ይሞላል:: ጌታህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።»"},{"id":7,"translation":"7. በዩሱፍና በወንድሞቹ ታሪክ ዉስጥ እውቀትን በመሻት ለሚጠይቁ ሁሉ እያሌ ተዓምራት አሉ::"},{"id":8,"translation":"8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) ባሉ ጊዜ: «እኛ በቁጥር ብዙዎች ሁነን እያለ ዩሱፍና ወንድሙ (ብንያም) ከአባታችን ዘንድ ከእኛ ይበልጥ ተወዳጆች ናቸው:: በእውነቱ አባታችን ግልጽ ስህተት ውስጥ ነው።"},{"id":9,"translation":"9. «ዩሱፍን ግደሉት ወይም እሩቅ ቦታ ጣሉት:: ይህን ካረጋችሁ የአባታችሁን ፊት ትኩረትና ውዴታ የራሳችሁ ብቻ ታደርጋላችሁ:: ከዚህ በኋላ ከኃጥያታችሁ በመመለስ መልካም ሰዎች ትሆናለችሁ።"},{"id":10,"translation":"10. ከእነሱ አንድ ተናጋሪ «ዩሱፍን አትግደሉ ግን በጉድጓድ አዘቅት ጨለማ ውስጥ ጣሉት፤ ከተጓዢዎች አንዱ ያነሳዋልና፡፡ ሠሪዎች ብትኾኑ (በዚሁ ተብቃቁ) አላቸው፡፡"},{"id":11,"translation":"11. አሉም: «አባታችን ሆይ! በዩሱፍ ጉዳይ እኛ ለእርሱ ቅን አሳቢዎች ሁነን ሳለ ለምን አታምነንም?"},{"id":12,"translation":"12. «እስቲ ይዝናና ይጫወት ዘንድ ነገ ከእኛ ጋር አብረህ ላከው::እኛም ለእርሱ ጠባቂዎች ነን።»"},{"id":13,"translation":"13. አባቱም «እርሱን መውሰዳችሁ ያሳዝነኛል። ዘንግታችሁት ተኩላ እንዳይበላዉም እፈራለሁ።» አለ።"},{"id":14,"translation":"14. እነርሱም «እኛ እንዲህ ጭፍሮች ሆነን ተኩላ ከበላውማ ከሳሪዎቹ እኛ ነን።» አሉ።"},{"id":15,"translation":"15. እርሱንም ወስደውት በጉድጓድ ወለል ላይ ሊጥሉት በወሰኑ ጊዜ «እነርሱ ሳያውቁ ይህን ጸያፍ ተግባራቸውን ወደ ፊት ትነግራቸዋለህ» የሚል መልዕክት ላክንለት።"},{"id":16,"translation":"16. አባታቸውንም በምሽት እያለቀሱ መጡት።"},{"id":17,"translation":"17. «አባታችን ሆይ! እኛ ለሩጫና ለውርወራ ልንሽቀዳደም ሄድን። ዩሱፍንም እቃችን ዘንድ ተውነው:: ወዲያዉም ተኩላ በላው:: አንተም እውነተኞች ብንሆንም የምታምነን አይደለህም።» አሉ።"},{"id":18,"translation":"18. በቀሚሱም ላይ የውሸትን ደም አመጡ:: አባታቸውም: «ይህ ትክክል አይደለም። ይልቁን ነፍሶቻችሁ ውሸት ነገርን ለናንተ ሸለሙላችሁ:: ስለዚህ መልካም ትዕግስት ማድረግ አለብኝ:: በምትሉትም ነገር ላይ መታገዣው አላህ ብቻ ነው።» አለ።"},{"id":19,"translation":"19. መንገደኞችም መጡ:: ውሃ ቀጂያቸውንም ላኩ:: አኮሌውንም ወደ ጉድጎዱ ሰደደ:: የምስራች:: «ይህ ልጅ ነው።» አለ:: ሸቀጥ አድርገዉም ደበቁት:: አላህ የሚሠሩትን ሁሉ አዋቂ ነው::"},{"id":20,"translation":"20. በርካሽ ዋጋና በሚቆጠሩ ዲርሃሞች ሸጡት:: በእርሱም ላይ ከቸልተኞቹ ነበሩ::"},{"id":21,"translation":"21. ያም ከምስር የገዛው ሰው ለሚስቱ «ይህ ልጅ መኖሪያውን አክብሪ ሊጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጅላልና።» አላት:: ልክ እንደዚሁ ለዩሱፍ ገዥ ልናደርገውና የሕልሞችንም ፍች ልናስተምረው በምድር ላይ አስመቸነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ አሸናፊ ነው። ግን አብዛኞቹ ሰዎች ይህን አያውቁም::"},{"id":22,"translation":"22. ጥንካሬውንም በደረሰ ጊዜ ጥበብንና ዕውቀትን ሰጠነው:: ልክ እንደዚህም መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን::"},{"id":23,"translation":"23. ያችም እርሱ በቤትዋ የነበረባት ሴት ከነፍሱ አባበለችው:: ደጃፎቹንም ዘጋችና «ይኸው ላንተ ተዘጋጂቼልሃለሁና ቶሎ በል» አለችው:: እሱም «ከዚህ ጸያፍ ተግባር በአላህ እጠበቃለሁ:: እርሱ የገዘኝ ጌታዬ ኑሮዬን ያሳመረልኝ ነውና አልከዳዉም:: እነሆ በደለኞች ሁሉ አይድኑምና» አላት።"},{"id":24,"translation":"24. በእርሱም በእርግጥ አሰበች፡፡ በእርሷም አሰበ ፡፡የጌታውን ማስረጃ ባላዬ ኖሮ (በእርሷም ባሰበ ነበር) ፡፡ልክ እንደዚሁ መጥፎ ነገርንና ኃጢአትን ከእርሱ ላይ ልንመልስለት አስረጃችንን አሳየነው ፡፡እርሱ ከተጠበቁት ባሮቻችን አንዱ ነዉና ፡፡"},{"id":25,"translation":"25. እርሱና እርሷ በሩን ተሸቀዳደሙና ቀሚሱን ከኋላው ቀደደችው። ባለቤትዋን እበሩ አጠገብ አገኙት:: እርሷም ቀደም ብላ «በባለቤትህ መጥፎን ያሰበ ሰው ቅጣቱ መታሰር ወይም አሳማሚ ስቃይ እንጂ ሌላ አይደለም።» አለችው።"},{"id":26,"translation":"26. ዩሱፍም «እርሷ ናት ከነፍሴ ያባበለችኝ።» አለ:: ከቤተሰቦቿም አንድ መስካሪ (እንዲህ) መሰከረ: «ቀሚሱ ከበስተፊት ተቀዶ ከሆነ እርሷ እውነት ተናገረች:: እርሱ ከውሸታሞቹ አንዱ ነው።"},{"id":27,"translation":"27. «ቀሚሱም ከበስተኋላው ተቀዶ እንደሆነ ዋሸች:: እርሱም ከእውነተኞቹ ነው።»"},{"id":28,"translation":"28. ቀሚሱንም ከበስተኋላ ተቀዶ ባየ ጊዜ አለ: «እርሱ የተናገርሽው ከተንኮላችሁ ነው። የእንናንተ የሴቶች ተንኮል በእርግጥ ብርቱ ነው።"},{"id":29,"translation":"29. «ዩሱፍ ሆይ! አንተም ከዚህ ወሬ ተከልከል:: አንቺም ለኃጢአትሽ ማርታን ለምኝ። አንቺ ከስሕተተኞቹ ሆነሻልና።» አለ::"},{"id":30,"translation":"30. በከተማው ያሉ ሴቶችም «የዐዚዝ ሚስት ሰራተኛዋን ከነፍሱ ታባብለዋለች:: በእውነቱ ፍቅሩ ልቧን መቷታል:: እኛ በግልጽ ስሕተት ውስጥ ሆና በእርግጥ እናያታለን።» አሉ።"},{"id":31,"translation":"31. እርሷም ሐሜታቸውን በሰማች ጊዜ ወደነሱ ላከችባቸው:: ግብዣንም ለእነርሱ አዘጋጀችላቸው:: ለያንዳንዳቸዉም ቢላዋን ሰጠችና «በእነርሱም ላይ ውጣ።» አለችው:: እነርሱም በተመለከቱት ጊዜ በጣም አደነቁት:: እጆቻቸዉንም ቆረጡ። «ለአላህ ጥራት ይገባው:: ይህ ሰው አይደለም:: ይህ የተከበረ መልአክ እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ።"},{"id":32,"translation":"32. በዚህ ጊዜ «ይህ እኮ ነው ያ በእርሱ ፍቅር ያማችሁኝ ሰው:: በእርግጥም ከነፍሱ አባባልኩት ግና እርሱ እንቢ አለ:: ወደፊትም የማዘውን ነገር ባይሠራ በእርግጥ ይታሰራል ከወራዶቹም ይሆናል።» አለች።"},{"id":33,"translation":"33. «ጌታዬ ሆይ! ወደ እርሱ ከሚጠሩኝ ነገር (ከዝሙት) ይልቅ መታሰር ለእኔ የተወደደ ነው:: ተንኮላቸውንም ከእኔ ላይ ባትመልስልኝ ወደ እነርሱ እዘነበላለሁ:: ከስሕተተኞቹም እሆናለሁ።» አለ።"},{"id":34,"translation":"34. ጌታዉም ጸሎቱን ተቀበለው፤ ተንኮላቸውንም ከእርሱ መለሰለት:: እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና።"},{"id":35,"translation":"35. ከዚያም ማስረጃዎችን ካዩ በኋላ እስከ ጊዜ ድረስ እንዲያስሩት ለእነርሱ ታያቸው::"},{"id":36,"translation":"36. ከእሱም ጋር ሁለት ወጣቶች እስር ቤቱ ገቡ:: አንደኛቸው «እኔ በሕልሜ የወይን ጠጅን ስጠምቅ አየሁ።» አለ:: ሌላው ደግሞ «እኔ በራሴ ላይ ቂጣን ተሸክሜ ከእሱ በራሪ አሞራ ስትበላ አየሁ ፍችውን ንገረን እኛ ከአሳማሪዎች ሁነህ እናይሃለንና።» አሉት።"},{"id":37,"translation":"37. ዩሱፍም አለ: «ማንኛዉም የምትሰጡት ምግብ ለእናንተ ከመምጣቱ በፊት ፍችውን የምነግራችሁ ቢሆን እንጂ አይመጣላችሁም:: ይህ ጉዳይ ጌታዬ ካሳወቀኝ ነገር ነው:: እኔም በአላህ የማያምኑትንና በመጨረሻይቱ ዓለም ከሓዲያን የሆኑ ሕዝቦችን ሃይማኖት ትቻለሁ::"},{"id":38,"translation":"38. «የአባቶቼንም የኢብራሂምን፤ የኢስሐቅንና የያዕቁብን ሃይማኖት ተከትያለሁ:: ለእኛ በአላህ ምንንም ማጋራት አይገባንም:: ያ አለማጋራት በእኛ ላይና በሰዎች ላይ የአላህ ችሮታ ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም::"},{"id":39,"translation":"39. «የእስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! የተለያዩ አምላኮች ይሻላሉን ወይስ አሸናፊውና አንዱ አላህ?"},{"id":40,"translation":"40. «ከእርሱ ሌላ እናንተና አባቶቻችሁ አማልክት ብላችሁ የጠራችኋቸውን ስሞች እንጂ አትገዙም። አላህ በእርሷ ምንም አስረጂ አላወረደም። ፍርዱ የአላህ እንጂ ሌላ አይደለም:: እርሱን እንጂ ሌላን እንዳትገዙም አዟል:: ይህ ትክክለኛው ሃይማኖት ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::"},{"id":41,"translation":"41. «የአስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! አንደኛችሁማ ንጉሡን ጠጅ ያጠጣል። ሌላውም ይሰቀላል:: ከራሱም በራሪ አሞራ ትበላለች:: ያ ፍቹን የምትጠይቁት ነገር ተፈጸመ።» አላቸው።"},{"id":42,"translation":"42. ለዚያም ከሁለቱ እርሱ የሚድን መሆኑን ለተጠራጠረው እጌታህ ዘንድ አስታውሰኝ አለው፡፡ ጌታውንም ከማስታወስ ሰይጣን አስረሳው፡፡ ለጥቂት ዓመታትም በወህኒ ቤቱ ውስጥ ቆየ፡፡"},{"id":43,"translation":"43. ንጉሡም «እኔ ሰባት የሰቡ ላሞችን ሰባት የከሱ ላሞች ሲበሉዋቸው፤ ሰባት ለምለም ዘለላዎችም ሌሎች ሰባት ደረቆችን ስብርብር ሲያደርጉ በሕልሜ አየሁ:: እናንተ ታላላቅ ሰዎች ሆይ! ሕልም መፍታት የምታውቁ ከሆናችሁ ሕልሜን ፍቱልኝ።» አላቸው።"},{"id":44,"translation":"44. «ሕልሞችህ ቅዠቶች ናቸው:: እኛም የሕልሞችን ፍች አዋቂዎች አይደለንም።» አሉት።"},{"id":45,"translation":"45. ያም ከሁለቱ መካከል የዳነውና ከብዙ ጊዜ በኋላ ዩሱፍን ያስታወሰው ሰው «እኔ ፍቹን እነግራችኋለሁና ላኩኝ።» አለ።"},{"id":46,"translation":"46. «አንተ እውነተኛው ዩሱፍ ሆይ! ሰባትን የሰቡ ላሞች ሰባት ከሲታዎች ላሞች ሲበሏቸው፤ ሰባትን ለምለም ዘለላዎችም ሌሎች ሰባት ደረቆች በእነርሱ ላይ ስብርብር ሲያደርጉ ያየን ሰው ሕልም ፍች እስቲ ተችልን:: ያውቁ ዘንድ ወደ ሰዎቹ ልመለስ እከጅላለሁና።» አለው።"},{"id":47,"translation":"47. እርሱም አለ: «ሰባትን የተከታተሉ ዓመታት ትዘራላችሁ ያጨዳችሁትንም ሁሉ ከምትበሉት ጥቂት በስተቀር በዘለላው ውስጥ ተውት።"},{"id":48,"translation":"48. «ከዚያም ከነዚያ በኋላ ካደለባችሁት ጥቂት ሲቀር ለእነርሱ ያደለባችሁትን ሁሉ የሚበሉ ሰባት የችግር ዓመታት ይመጣሉ።"},{"id":49,"translation":"49. «ከዚያ ከእነዚያ በኋላ ሰዎቹ በእርሱ ዝናብ የሚያገኙበትና በእርሱም ወይንን የሚጨምቁበት ዓመት ይመጣል።»"},{"id":50,"translation":"50. ንጉሡም «እርሱን አምጡልኝ።» አለ። መልእክተኛዉም ወደ ዩሱፍ በመጣ ጊዜ ዩሱፍ: «ወደ ጌታህ ተመለስና የእነዚያን እጆቻቸውን የቆረጡትን ሴቶች ሁኔታ ጠይቀው ጌታዬ ተንኮላቸውን አዋቂ ነውና።» አለው።"},{"id":51,"translation":"51. ንጉሡም «ዩሱፍን ከነፍሱ ባባበላችሁት ጊዜ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው። «ለአላህ ጥራት ይገባው በእርሱ ላይ ምንም መጥፎን ነገር አላወቅንም (አላየንም)።» አሉት። የዐዚዝ ሚስትም አለች: «አሁን እውነቱ ተገለጸ እኔ አባበልኩት እርሱም ከእውነተኞቹ ነው።"},{"id":52,"translation":"52. «ይህ ጌታዬ ሩቅ ሆኖ ሳለ ያልከዳሁት መሆኔንና አላህም የከዳተኞችን ተንኮል የማያቃና መሆኑን እንዲያውቅ ነው።»"},{"id":53,"translation":"53. «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም:: ነፍስ ሁሉ ጌታዬ ያዘነላት (የጠበቃት) ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና:: ጌታዬ በጣም መሐሪና አዛኝ ነው።»"},{"id":54,"translation":"54. ንጉሡም «እርሱን አምጡልኝ ለራሴ የግሌ አደርገዋለሁና።» አለ። ባናገረዉም ጊዜ «አንተ ዛሬ እኛ ዘንድ ባለሟልና ታማኝ ነህ።» አለው።"},{"id":55,"translation":"55. «በምድር ግምጃ ቤቶች ላይ ሹም አድርገኝ እኔ ጠባቂ አዋቂ ነኝና።» አለ።"},{"id":56,"translation":"56. እንደዚሁም ለዩሱፍ በምድር ላይ ከእርሷ በፈለገው ስፍራ የሚሰፍር ሲሆን አስመቸነው:: በችሮታችን የምንሻውን ሰው እንለያለን። የበጎ ሠሪዎችንም ዋጋ አናጠፋም።"},{"id":57,"translation":"57. የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ለእነዚያ ላመኑትና ይጠነቀቁ ለነበሩት የበለጠ ነው::"},{"id":58,"translation":"58. የዩሱፍ ወንድሞችም መጡ በእርሱም ላይ ገቡ:: እነርሱም እርሱን የሳቱት ሲሆኑ አወቃቸው::"},{"id":59,"translation":"59. ጉዳያቸውን ፈጽሞ ስንቃቸውንም ባዘጋጀላቸው ጊዜ አለ: «ከአባታችሁ በኩል የሆነውን ወንድማችሁን አምጡልኝ እኔ ከአስተናጋጆች ሁሉ በላጭ ስሆን ስፍርን የምሞላ መሆኔን አታዩምን?"},{"id":60,"translation":"60. «እርሱንም ባታመጡልኝ። እኔ ዘንድ ለእናንተ ስፍር የላችሁም:: አትቀርቡኝምም።» አለ"},{"id":61,"translation":"61. «ስለ እርሱ አባቱን በጥብቅ እንጠይቃለን፤ እኛም ይህንን በእርግጥ ሰሪዎች ነን።» አሉት።"},{"id":62,"translation":"62. ለአሽከሮቹም፡- «ወደ ቤተሰቦቻቸው በተመለሱ ጊዜ ሸቀጣቸውን (ገንዘባቸውን) ያውቋት ዘንድ በየጓዞቻቸው ውስጥ አድርጉላቸው ሊመለሱ ይከጀላልና።» አላቸው።"},{"id":63,"translation":"63. ወደ አባታቸዉም በተመለሱ ጊዜ፡- «አባታችን ሆይ! (ወንድማችንን እስከምንወስድ) ስፍር ከኛ ተከልክሏል። ስለዚህ ወንድማችንን ከእኛ ጋር ላከው፤ ይሰፈርልናልና እኛም ለእርሱ ጠባቂዎች ነን።» አሉ::"},{"id":64,"translation":"64. «ከአሁን በፊት በወንድሙ ላይ እንዳመንኳችሁ እንጂ በእርሱ ላይ አምናችኋለሁን? አላህም በጠባቂነት ከሁሉ የበለጠ ነው:: እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው።» አላቸው።"},{"id":65,"translation":"65. እቃቸውንም በከፈቱ ጊዜ ሸቀጣቸውን ወደ እነርሱ ተመልሶ አገኙት። «አባታችን ሆይ! ምን እንፈልጋለን? ይህች ሸቀጣችን ናት ወደ እኛ ተመልሳልናለች እንረዳባታለን:: ለቤተሰቦቻችንም እንሸምታለን። ወንድማችንንም እንጠብቃለን:: የአንድ ግመልን ጭነትም እንጨምራለን:: ይህ በንጉሱ ላይ ቀላል ስፍር ነው።» አሉ።"},{"id":66,"translation":"66. «ካልተከበባችሁ በስተቀር እርሱን በእርግጥ የምታመጡልኝ ለመሆናችሁ ከአላህ የሆነን ቃልኪዳን (መተማመኛ) እስከምትሰጡኝ ድረስ ከናንተ ጋር ፈጽሞ አልከዉም።» አላቸው። መተማመኛቸውንም በሰጡ ጊዜ «አላህ በምንለው ሁሉ ላይ ዋስ ነው።» አላቸው።"},{"id":67,"translation":"67. አለም፡- «ልጆቼ ሆይ! በአንድ በር አትግቡ:: ግን በተለያዩ በሮች ግቡ:: ከአላህም ፍርድ በምንም አልጠቅማችሁም (አልመልስላችሁም)። ፍርዱ የአላህ እንጂ የሌላ አይደለም:: በእርሱ ላይ ብቻ ተመካሁ:: ተመኪዎችም ሁሉ በእርሱ ላይ ብቻ ይመኩ።»"},{"id":68,"translation":"68. አባታቸው ካዘዛቸው ስፍራ በገቡ ጊዜ ከአላህ ፍርድ ምንም ነገር ከእነርሱ የሚከለክልላቸው አልነበረም:: ግን በየዕቁብ ነፍስ ውስጥ የነበረች ጉዳይ ናት:: ፈጸማት። እርሱም ስላሳወቅነው የእውቀት ባለቤት ነው። ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::"},{"id":69,"translation":"69. በዩሱፍ ላይ በገቡ ጊዜም ወንድሙን ወደ እርሱ አስጠጋውና «እነሆ እኔ ወንድምህ ነኝ:: ይሰሩት በነበሩትም ሁሉ አትበሳጭ።» አለው።"},{"id":70,"translation":"70. እቃቸውን ባዘጋጀላቸው ጊዜ ዋንጫይቱን በወንድሙ እቃ ውስጥ አደረገና ከዚያ «እናንተ ባለ ግመሎች ሆይ! እናንተ በእርግጥ ሌቦች ናችሁ።» ሲል ጠሪ ተጣራ።"},{"id":71,"translation":"71. ወደ እነርሱ ዞረዉም: «ምንድን ጠፋችሁ?» አሉ።"},{"id":72,"translation":"72. «የንጉሱ መስፈሪያ ጠፍቶናል እርሱንም ላመጣ ሰው የአንድ ግመል ጭነት አለው። እኔም በእርሱ ተያዥ ነኝ።» አለ።"},{"id":73,"translation":"73. «በአላህ እንምላለን! በምድር ላይ ለማጥፋት እንዳልመጣን በእርግጥ አውቃችኋል ሌቦችም አልነበርንም።» አሉ።"},{"id":74,"translation":"74. «ውሸታሞች ብትሆኑስ ቅጣቱ ምንድን ነው?» አሏቸው።"},{"id":75,"translation":"75. «ቅጣቱ በየዕቁብ ሕግ እቃው በጓዙ ውስጥ የተገኘበት ሰው ራሱ ባሪያ ተደርጎ መውሰድ ነው። እርሱም ቅጣቱ ነው:: ልክ እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን።» አሉ።"},{"id":76,"translation":"76. ምርመራውን ከወንድሙ እቃ በፊትም በእቃዎቻቸው ጀመረ:: ከዚያ ዋንጫይቱን ከወንድሙ እቃ ውስጥ አወጣት። ልክ እንደዚሁ ለዩሱፍ ብልሃትን አስተማርነው:: አላህ ባልሻ ኖሮ በንጉሱ ሕግ ወንድሙን ሊይዝ አይገባዉም ነበር:: የምንሻውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን። ከእውቀት ባለቤቶች ሁሉ በላይም አዋቂ አለ::"},{"id":77,"translation":"77. «እርሱ ቢሰርቅ ከአሁን በፊት የእርሱው ወንድም በእርግጥ ሰርቋል።» አሉ። ዩሱፍም ይህችን (አስቀያሚ ንግግር) በነፍሱ ውስጥ ደበቃት:: ለእነርሱም አልገለጣትም። በልቡ «እናንተ ሥራችሁ የከፋ ነው:: አላህ የምትሉትን ሁሉ ይበልጥ አዋቂ ነው።» አለ።"},{"id":78,"translation":"78. «አንተ የተከበርከው ሆይ! ለእርሱ በእርግጥ ታላቅ ሽማግሌ አባት አለው:: ስለዚህ በእርሱ ስፍራ አንደኛችንን ያዝ:: እኛ ከመልካም ሠሪዎች ሆነህ እናይሃለንና።» አሉት።"},{"id":79,"translation":"79. «ዕቃችንን እርሱ ዘንድ ያገኘንበትን ሰው እንጂ ሌላን ከመያዝ በአላህ እንጠበቃለን:: እኛ ያን ባደረግን ጊዜ በእርግጥ በዳዮች ነን።» አለ።"},{"id":80,"translation":"80. ከእርሱም ተስፋን በቆረጡ ጊዜ የሚመካከሩ ሆነው ገለል አሉ:: ታላቃቸውም አለ: «አባታችሁ በእናንተ ላይ ከአላህ የሆነን መተማመኛ ቃል ኪዳን በእርግጥ የያዘባችሁ መሆኑንና ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ ለእኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለእኔ እስከሚፈርድልኝ ድረስ የምስርን (የግብጽን) ምድር አልለይም:: እርሱ ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው።"},{"id":81,"translation":"81. «ወደ አባታችሁ ተመለሱ:: በሉትም: ‹አባታችን ሆይ ልጅህ ሰረቀ፤ ባወቅነዉም ነገር እንጂ አልመሰከርንም:: ሩቁንም ነገር ምስጢሩን አዋቂዎች አልነበርንም።"},{"id":82,"translation":"82. «‹ያችንም በውስጧ የነበርንባትን ከተማ ያችንም በውስጧ የመጣነውን ባለ ግመል ጓድ ጠይቅ እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን።›»"},{"id":83,"translation":"83. ያዕቁብም፡- «አይደለም። ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርን ለእናንተ ሸለሙላቸሁና ሠራችሁት እንጂ:: እናም መልካም ትዕግስት ማድረግ አለብኝ:: እነርሱን ሁሉንም የተሰበሰቡ ሆነው አላህ ሊያመጣልኝ ይከጀላል:: እነሆ እርሱ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።» አላቸው።"},{"id":84,"translation":"84. ከነርሱም ዞር አለና፡- «በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ:: ዓይኖቹም ከሐዘን የተነሳ ነጡ:: እርሱም በትካዜ የተሞላ ነው።"},{"id":85,"translation":"85. እነርሱም፡- «በአላህ እንምላለን! ለጥፋት የቀረብክ እስከምትሆን ወይም ከጠፊዎቹ እስከምትሆን ድረስ ዩሱፍን ከማውሳት አትወገድም።» አሉ።"},{"id":86,"translation":"86. «ጭንቀቴንና ሐዘኔን የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው። ከአላህ በኩል የማታውቁትን ነገር እኔ አውቃለሁና።» አላቸው።"},{"id":87,"translation":"87. «ልጆቼ ሆይ! ሂዱ ከዩሱፍና ከወንድሙም ወሬ ተመራመሩ:: ከአላህም እዝነት ተስፋ አትቁረጡ:: እነሆ ከአላህ እዝነት ከሓዲያን ህዝቦች እንጂ ማንም ተስፋ አይቆርጥም።» አለ።"},{"id":88,"translation":"88. በእርሱም ላይ በገቡ ጊዜ: «አንተ የተከበርከው ሆይ! እኛንም ቤተሰቦቻችንንም ጉዳት ደረሰብን። እርካሽ ሸቀጥም ይዘን መጥተናል:: ስፍርንም ለእኛ ሙላልን:: በእኛም ላይ መጽውት:: አላህ መጽዋቾችን ይመነዳልና።» አሉት።"},{"id":89,"translation":"89. «እናንተ የማታውቁ በነበራችሁ ጊዜ በዩሱፍና በወንድሙ ላይ የሠራችሁትን ግፍ አወቃችሁን?» አላቸው።"},{"id":90,"translation":"90. «አንተ በእርግጥ አንተ ዩሱፍ ነህን?» አሉት። «አዎ እኔ በትክክል ዩሱፍ ነኝ:: ይህም ወንድሜ ነው:: አላህ በእኛ ላይ በእርግጥ ለገሰልን:: እነሆ የሚጠነቀቅና የሚታገስ ሰው አላህ ይክሰዋል:: አላህ የበጎ አድራጊዎችን ዋጋ አያጠፋምና።» አለ።"},{"id":91,"translation":"91. «በአላህ እንምላለን! አላህ በእኛ ላይ በእርግጥ አበለጠህ፤ እኛም በእርግጥ አጥፊዎች ነበርን።» አሉ::"},{"id":92,"translation":"92. እርሱም አላቸው: «ዛሬ በእናንተ ላይ ምንም ወቀሳ የለባችሁም። አላህ ለእናንተ ይምራል። እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነውና።»"},{"id":93,"translation":"93. «ይህንን ቀሚሴን ይዛችሁ ሂዱ:: በአባቴ ፊትም ጣሉት:: የሚያይ ሆኖ ይመጣልና:: ቤተሰቦቻችሁንም በሙሉ ሰብስባችሁ አምጡልኝ።» አላቸው።"},{"id":94,"translation":"94. ግመል ጫኞችም ከግብጽ በወጡ ጊዜ አባታቸው «እኔ የዩሱፍን ሽታ በእርግጥ አገኛለሁ:: ባታቄሉኝ ኖሮ ታምኑኝ ነበር።» አለ።"},{"id":95,"translation":"95. «በአላህ እንምላለን! አንተ በእርግጥ እስካሁንም በዚያው በቀድሞው ስህተትህ ውስጥ ነህ።» አሉት።"},{"id":96,"translation":"96. አብሳሪዉም በመጣ ጊዜ ቀሚሱን በፊቱ ላይ ጣለው፤ ወዲያዉም የሚያይ ሆነ:: «እኔ ለእናንተ ከአላህ በኩል የማታውቁትን አውቃለሁ አላልኳችሁም ነበርን?» አላቸው።"},{"id":97,"translation":"97. «አባታችን ሆይ! ለኃጢያቶቻችን ምሕረትን ለምንልን:: እኛ ጥፋተኞች ነበርንና።» አሉ::"},{"id":98,"translation":"98. «ወደ ፊት ለእናንተ ጌታዬን ምሕረትን እለምንላችኋለሁ:: እነሆ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና።» አላቸው።"},{"id":99,"translation":"99. በዩሱፍ ላይም በገቡ ጊዜ ወላጆቹን ወደ እርሱ አስጠጋቸው፤ «በአላህም ፈቃድ ጥብቆች ስትሆኑ ሚስርን (ግብጽ) ግቡ።» አላቸው::"},{"id":100,"translation":"100. ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው ለርሱም ሰጋጆች ሆነው ወረዱለት። «አባቴም ሆይ! ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው፡፡ ጌታዬ በእርግጥ እውነት አደረጋት፡፡ ከወህኒ ቤትም ባወጣኝና ሰይጣንም በእኔና በወንድሞቼ መካከል ካበላሸ በኋላ እናንተን ከገጠር ባመጣችሁ ጊዜ በእርግጥ ለእኔ መልካም ዋለልኝ:: ጌታዬ ለሚሻው ነገር እዝነቱ ረቂቅ ነው:: እነሆ እርሱ አዋቂውና ጥበበኛው ነው።» አለ።"},{"id":101,"translation":"101. «ጌታዬ ሆይ! ከንግስና በእርግጥ ሰጠኸኝ:: ከህልሞችም ፍች አስተማርከኝ:: የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቴ ነህ:: ሙስሊም ሆኜ ግደለኝ:: ወደ መልካም ሰሪዎችም አስጠጋኝ።» አለ።"},{"id":102,"translation":"102. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ወደ አንተ የምናወርደው ሲሆን ከሩቅ ወሬዎች ነው:: አንተም እነርሱ በዩሱፍ ላይ የሚያሴሩ ሆነው ነገራቸውን በቆረጡ ጊዜ እነርሱ ዘንድ አብረህ አልነበርክም::"},{"id":103,"translation":"103. አብዛኛዎቹ ሰዎች ለማመናቸው ብትጓጓም የሚያምኑ አይደሉም::"},{"id":104,"translation":"104. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በቁርኣን ላይ ምንም ዋጋን አትጠይቃቸዉም:: እርሱ ለዓለማት ግሳጼ እንጂ ሌላ አይደለም::"},{"id":105,"translation":"105. በሰማያትና በምድር ካለችው ምልክት ብዙይቱ እነርሱ ከእርሷ ዘንጊዎች ሆነው በእርሷ ላይ ያልፋሉ::"},{"id":106,"translation":"106. አብዛኞቻቸዉም እነርሱ አጋሪዎች ሆነው እንጂ በአላህ አያምኑም::"},{"id":107,"translation":"107. ከአላህ ቅጣት ሽፋኝ አደጋ የምትመጣባቸው ወይም ሰዓቲቱ እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ በድንገት የምትመጣባቸው መሆኑዋን አይፈሩምን?"},{"id":108,"translation":"108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ይህ መንገዴ ነው:: ወደ አላህ እጠራለሁ:: እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን:: ጥራትም ለአላህ ብቻ ይገባው:: እኔም ከአጋሪዎች አይደለሁም።» በል::"},{"id":109,"translation":"109. ካንተ በፊትም ከከተሞች ሰዎች ወደነርሱ ራዕይ የምናወርድላቸው የሆኑን ወንዶችን እንጂ አላክንም:: በምድር ላይ አይሄዱምና የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደሆነ አይመለከቱምን? የአኺራ ደስታ ለተጠነቀቁት ሰዎች ሁሉ በእርግጥ የተሻለች ናት:: አታውቁምን?"},{"id":110,"translation":"110. መልዕክተኞች ተስፋ በቆረጡና እነርሱ በእርግጥ የተዋሹ መሆናቸውን በተጠራጠሩ ጊዜ እርዳታችን መጣላቸው:: ከዚያ እኛ የምንፈልገው ሰው እንዲድን ተደረገ:: ቅጣታችንም ከአመፀኞቹ ህዝቦች ላይ አይመለስም::"},{"id":111,"translation":"111. በታሪካቸው ውስጥ ለአዕምሮ ባለቤቶች ሁሉ በእርግጥ መገሰጫ ነበረ:: ይህ ቁርኣን የሚቀጣጥፍ ወሬ አይደለም:: ይልቁንም ያንን በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ፤ ሁሉን ጉዳዮች ገላጭና ለሚያምኑ ህዝቦችም ሁሉ መሪ፤ ችሮታ ነው::"}]},{"id":13,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አሊፍ ፤ላም ፤ሚይም፤ ራ፤ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ አናቅጽ ከመጽሐፉ አናቅጽ ናቸው:: ያም ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው እውነት ነው:: ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያምኑም::"},{"id":2,"translation":"2. አላህ ያ ሰማያትን የምታይዋት ቋሚዎች ሳይኖራት በችሎታው ከፍ ያረጋት፤ ከዚያ በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ፤ ጸሐይንና ጨረቃንም የገራ ነው:: ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ:: ነገሩን ሁሉ ያስተናብራል:: ከጌታችሁ ጋር መገናኘትን ታረጋግጡ ዘንድ ተዓምራትን ይዘረዝራል::"},{"id":3,"translation":"3. እርሱ (አላህ)ያ ምድርን የዘረጋ፤ በእርሷም ውስጥ ተራራዎችንና ወንዞችን ያደረገ:: በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ዓይነቶችን ያደረገ ነው:: ሌሊትን በቀን ይሸፍናል:: በዚህም ውስጥ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ሁሉ ብዙ ምልክቶች አሉ::"},{"id":4,"translation":"4. በምድርም ውስጥ የተጎራበቱ ቁርጥራጮች አሉ:: የወይኖች አትክልቶችም፤ አዝርዕቶችም መንታዎችና መንታዎች ያልሆኑ ዘንባባዎችም አሉ:: በአንድ ውሃ ይጠጣሉ:: በጣዕም ግን ይለያያሉ ከፊልዋንም በከፊሉ ላይ በሚበላው ሰብል እናበልጣለን:: በዚህም ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች ሁሉ ብዙ ተአምራት አለበት::"},{"id":5,"translation":"5. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብትደነቅም አፈር በሆንን ጊዜ እኛ አዲስ ፍጥረት እንሆናለን? ማለታቸው በጣም የሚደንቅ ነው:: እነዚህ እነዚያ ሰዎች ማለት እነዚያ በጌታቸው የካዱት ሰዎች ናቸው:: እነዚህም እንዛዝላዎች በአንገቶቻቸው ላይ ያሉባቸው ናቸው:: እነዚህም የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው::"},{"id":6,"translation":"6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ በፊት የመሰሎቻቸው ቅጣቶች በእርግጥ ያለፉ ሲሆኑ ከመልካሙ በፊት በመጥፎ ያስቸኩሉሃል! ጌታህም ለሰዎች ሁሉ ከመበደላቸው ጋር በእርግጥ የምህረት ባለቤት ነው:: ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ብርቱም ነው::"},{"id":7,"translation":"7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች «በእርሱ ላይ ከጌታው ተአምር ለምን አልተወረደለትም?» ይላሉ:: አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ፤ ለሕዝብም ሁሉ መሪ አለላቸው።"},{"id":8,"translation":"8. አላህ ሴት ሁሉ የምታረግዘውን ጽንስ ሁሉ ጠንቅቆ ያውቃል:: ማሕጸኖች የሚያጎድሉትንም ሆነ የሚጨምሩትን ያውቃል:: ነገሩ ሁሉ እርሱ ዘንድ በልክ የተወሰነ ነውና::"},{"id":9,"translation":"9. ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ የሆነ ታላቅና የላቀ ጌታ ነው::"},{"id":10,"translation":"10. ከናንተ ውስጥ ቃሉን ዝቅ ያደረገ፤ በእርሱ የጮኸም፤ እርሱ በሌሊት ተደባቂም በቀን ተገልፆ ሂያጅም የሆነ ሁሉ (እርሱ አላህ ዘንድ) እኩል ነው (አላህ ያውቀዋል)።"},{"id":11,"translation":"11. ለእርሱ ለሰው በስተፊቱም ከኋላዉም በአላህ ትዕዛዝ ከክፉ የሚጠብቁት ተተካኪዎች መላዕክት አሉት:: አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን (ጸጋ) በነፍሶቻቸው ያለውን (ሁኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም:: አላህም በሰዎች ላይ ክፉን በሻ ጊዜ ለእርሱ መመለስ የለዉም:: ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም ተከላካይ የላቸዉም::"},{"id":12,"translation":"12. እርሱ ያ የምትፈሩና የምትከጅሉም ስትሆኑ ብልጭታን የሚያሳያችሁ ከባዶች ደመናዎችንም የሚያስገኝ ነው::"},{"id":13,"translation":"13. ነጎድጓድም አላህን በማመስገን ያጠራል:: መላዕክትም እርሱን ከመፍራት ያጠሩታል፤ መብረቆችም ይልካል። እነርሱም (ከሓዲያን) በአላህ የሚከራከሩ ሲሆኑ በእርሷ የሚሻውን ሰው ይመታል:: እርሱም ሀይለ ብርቱ ነው::"},{"id":14,"translation":"14. ለእርሱ(አላህ) የእውነት ጥሪ አለው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ የሚገዟቸው ጣዖታት ምሳሌው ወደ አፉ ይደርስ ዘንድ ወደ ውሃ መዳፎቹን በሩቅ ሆኖ እንደሚዘረጋና እንደማይደርስባት ሰው እንጂ ለእነርሱ በምንም አይመልሱላቸዉም:: እርሱም ወደ አፉ ደራሽ አይደለም:: የከሓዲያን ጥሪ በከንቱ ልፋት እንጂ ሌላ አይደለም።"},{"id":15,"translation":"15. በሰማያትና በምድር ያሉት ሁሉ በዉድም ሆነ በግድ ለአላህ ይሰግዳሉ:: ጥላዎቻቸዉም በጧቶችና በማታዎች ይሰግዳሉ:: (1)","footnotes":"(1) እዚህ አንድ ሱጁድ ይደረጋል። የቁርኣን ንባብ ሱጁድ (ሱጁዱትላዋህ) ይባላል። በቁርኣን ውስጥ 15 ቦታዎች ይገኛል።"},{"id":16,"translation":"16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው?» በላቸው:: «አላህ ነው።» በልም። «ለነፍሶቻቸው ጥቅምንም ጉዳትን የማይችሉን ረዳቶች ከእርሱ ሌላ ያዛችሁን?» በላቸው። «እውርና የሚያይ ይስተካከላሉን? ወይስ ጨለማዎችና ብርሃን ይስተካከላሉን? ወይስ ለአላህ እንደ እርሱ አፈጣጠር የፈጠሩን ተጋሪዎች አረጉለትና ፍጥረቱ በእነርሱ ላይ ተመሳሰለባቸውን?» በልም። «አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው:: እርሱም ብቸኛውና ሁሉን አሸናፊው ነው።» በል።"},{"id":17,"translation":"17. ከሰማይ ውሃን አወረደ:: ሸለቆዎቹም በየመጠናቸው ፈሰሱ:: ጎርፉም አስፋሪውን የውሃ አረፋ ተሸከመ:: ለጌጥ ወይም ለዕቃ ፍላጎት በእርሱ ላይ እሳት የሚያነዱበትም ማዕድን ብጤው የሆነ ኮረፋት አለው:: ልክ እንደዚሁ አላህ ለእውነትና ለውሸት ምሳሌን ያደርጋል:: የውሃ አረፋዉም ግብስብስ ሆኖ ይጠፋል:: ለሰዎች የሚጠቅመውማ በምድር ላይ ይቆያል:: ልክ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ይገልጻል::"},{"id":18,"translation":"18. ለእነዚያ ለጌታቸው ለታዘዙት ሰዎች መልካም ነገር ገነት አለላቸው:: እነዚያም ለእርሱ ያልታዘዙት ለእነርሱ በምድር ያለው ሁሉ ከእርሱም ጋር ብጤው ቢኖራቸው ኖሮ በእርሱ በተበዡበት ነበር:: እነዚያ ለእነርሱ ክፉ ምርመራ አለባቸው:: መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት:: ፍራሻቸዉም ገሀነም ከፋች!"},{"id":19,"translation":"19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው ሁሉ እውነት መሆኑን የሚያውቅ ሰው ልክ እንደዚያ እርሱ እውር እንደ ሆነው ሰው ነውን? የሚገሠጹት የአእምሮ ባለቤቶች ብቻ ናቸው::"},{"id":20,"translation":"20. እነዚያ የአላህን ቃል ኪዳን የሚሞሉ የጠበቀውንም ኪዳን የማያፈርሱ ናቸው::"},{"id":21,"translation":"21. እነዚያም አላህ እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቀጥሉ፤ ጌታቸውንም የሚያከብሩ፤ መጥፎንም ቁጥጥር የሚፈሩ ናቸው::"},{"id":22,"translation":"22. እነዚያም የጌታቸውን ውዴታ ለመፈለግ የታገሱ ሶላትንም አዘውትረው የሰገዱ ሰዎች እኛ ከሰጠናቸው ሲሳይም በምስጢርም ሆነ በግልጽ የመጸወቱ ክፉውንም በበጎ የሚገፈትሩ ናቸው:: እነዚያ ለእነርሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለችላቸው::"},{"id":23,"translation":"23. እርሷም የመኖሪያ ገነቶች ናት:: ይገቡባታል:: ከአባቶቻቸዉም ከሚስቶቻቸዉም ከዝርያቸዉም መልካም የሠራ ሰው ሁሉ ይገባባታል። መላዕክትም በእነርሱ ላይ ከየደጃፉ ሁሉ ይገባሉ።"},{"id":24,"translation":"24. «ሰላም ለእናንተ ይሁን:: ይህ ምንዳ በመታገሳችሁ የተሰጣችሁ ነው:: የመጨረሻይቱም ሀገር ምን ታምር!» ይሏቸዋል::"},{"id":25,"translation":"25. እነዚያ የአላህን ቃል ኪዳን ከጠበቀ በኋላ የሚያፈርሱ፤ አላህም እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ፤ በምድርም ላይ የሚያበላሹ እነዚያ ለእነርሱ እርግማን አለባቸው:: ለእነርሱም መጥፎ ሀገር ገሀነም አለላቸው::"},{"id":26,"translation":"26. አላህ ለሚሻው ሁሉ ሲሳይን ያሰፋል:: ለሚሻውም ያጠባል:: ከሓዲያን በቅርቢቱም ሕይወት ተደሰቱ:: የቅርቢቱም ሕይወት ከመጨረሻይቱ አንጻር ትንሽ መጠቀሚያ እንጂ ምንም አይደለችም::"},{"id":27,"translation":"27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ የካዱት ሰዎች «በእርሱ ላይ ከጌታው ተዓምር ለምን አልተወረደልትም?» ይላሉ:: «አላህ የሚሻውን ሰው ያጠማል:: የተመለሰንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል።» በላቸው::"},{"id":28,"translation":"28. እነርሱም እነዚያ በአላህ ያመኑ ልቦቻቸዉም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው:: አስተውሉ:: አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ::"},{"id":29,"translation":"29. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካም ስራዎችን የሠሩት ለእነርሱ ደግ ኑሮና መልካም መመለሻ አለላቸው::"},{"id":30,"translation":"30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ ከበፊትዋ ብዙ ሕዝቦች በእርግጥ ያለፉ ወደ ሆነችው ሕዝብ እነርሱ በአር-ረህማን የሚክዱ ሲሆኑ ያንን ወደ አንተ ያወረድነውን ቁርኣን በእነርሱ ላይ ታነብላቸው ዘንድ ላክንህ:: «እርሱ አር-ረህማን ጌታዬ ነው:: ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: በእርሱ ላይ ተመካሁ። መመለሻዬም ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው::"},{"id":31,"translation":"31. ቁርኣንም በእርሱ ተራራዎች የሚነዱበት፤ ወይም በእርሱ ምድር የሚቆራረጥበት፤ ወይም በእርሱ ሙታን እንዲናገሩ የሚደረጉበት ቢሆን ኖሮ (ይሀው ቁርአን በሆነ ነበር።) በእውነቱ ነገሩ ሁሉ የአላህ ነው:: እነዚያ በአላህ ያመኑት ሰዎች እነሆ አላህ በሻ ኖሮ ሰዎችን በመላ በእርግጥ ወደ ቀናው መንገድ ይመራቸው እንደ ነበረ አያውቁምን? እነዚያን የካዱት በሥራቸው ምክንያት አጥፊ አደጋ የምታገኛቸው ከመሆን ወይም የአላህ ቀጠሮ እስኪ መጣ በሀገራቸው አቅራቢያ አንተ የምትሰፍርባቸው ከመሆን አይወገዱም:: አላህ ቀጠሮውን አያፈርስምና::"},{"id":32,"translation":"32. ካንተ በፊት የነበሩትም መልዕክተኞች በእርግጥ ተላግጦባቸው ነበር:: እናም ለእነዚያም ለካዱት ጊዜን ሰጠኋቸው:: ከዚያም በቅጣት ያዝኳቸው:: ቅጣቴ እንዴት ነበር (ምን ያህል የከፋ ነበር።)"},{"id":33,"translation":"33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስ ሁሉ በሰራችው ሥራ ላይ ተጠባባቂ የሆነው አላህም እንደዚህ እንዳልሆነው ጣዖት ብጤ ነውን? ለአላህ ተጋሪዎችን አደረጉ። «ጥሯቸው:: አላህን በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታለችሁን? ወይስ ከቃል በቀጥታ ፍቺ በሌለው ከንቱ ቃል ተጋሪዎቹ በማለት ትጠሯቸዋላችሁን?» በላቸው። በእውነቱ ለእነዚያ ለካዱት ተንኮላቸው ተሸለመላቸው። ከእውነቱ መንገድም ታገዱ። አላህ ያጠመመውንም ምንም አቅኚ የለዉም።"},{"id":34,"translation":"34. ለእነርሱ በቅርቢቱ ሕይወት ቅጣት አለባቸው:: የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት በጣም የበረታ ነው:: ለእነርሱ ከአላህ ቅጣት ምንም ጠባቂ የላቸዉም::"},{"id":35,"translation":"35. ያች ጥንቁቆች የተሰጧት ገነት ምጣኔዋ (ምሳሌዋ) እንደሚነገራችሁ ነው:: ከሥርዋ ወንዞች ይፈሳሉ:: ምግቧ ሁል ጊዜም የማያቋረጥ ነው:: ጥላዋም እንደዚሁ። ይህች ገነት የእነዚያ የተጠነቀቁት መጨረሻ ናት:: የከሓዲያን መጨረሻ ግን እሳት ናት::"},{"id":36,"translation":"36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም መጽሐፉን የሰጠናቸውን ወደ አንተ በተወረደው ይደሰታሉ:: ከአህዛብም ከፊሉን የሚክዱ ሰዎች አሉ። «እኔ የታዘዝኩት አላህን ብቻ እንድገዛና በእርሱም እንዳላጋራ ነው። ወደ እርሱ እጠራለሁ:: መመለሻዬም ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው።"},{"id":37,"translation":"37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትህ ሲሆን አወረድነው:: እውቀቱ ከመጣልህም በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን ብትከተል ከአላህ ቅጣት ወዳጅም ሆነ ጠባቂ ምንም የለህም::37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትህ ሲሆን አወረድነው:: እውቀቱ ከመጣልህም በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን ብትከተል ከአላህ ቅጣት ወዳጅም ሆነ ጠባቂ ምንም የለህም::"},{"id":38,"translation":"38. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ብዙ መልዕክተኞችን በእርግጥ ልከናል:: ለእነርሱም ሚስቶችንና ልጆችን አድርገናል:: ማንኛዉም መልዕክተኛ በአላህ ፈቃድ እንጂ ተዓምር ሊያመጣ አይገባዉም:: ለየጊዜው ሁሉ ጽሑፍ አለው::"},{"id":39,"translation":"39. አላህ የሚፈልገውን ያብሳል:: የሚሻውን ያጸድቃል:: የመጽሐፉ ዋና መሠረትም እርሱ ዘንድ ብቻ ነው::"},{"id":40,"translation":"40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያን ያስፈራራናቸውን ቅጣት ከፊሉን በሕይወት እያለህ ብናሳይህ መልካም ነው:: ወይም ሳናሳይህ ብንገድልህ ወቀሳ የለብህም:: ባንተ ላይ ያለብህ መልዕክትህን ማድረስ ብቻ ነው:: ምርመራው ግን በእኛ ላይ ነው::"},{"id":41,"translation":"41. እኛ ምድርን ከጫፎችዋ የምናጎድላት ሆነን የምናመጣባት መሆናችንን አላወቁምን? አላህም ይፈርዳል:: ለፍርዱም በይግባኝ ገልባጭ የለዉም:: እርሱም ምርመራው ፈጣን ነው::"},{"id":42,"translation":"42. እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት ሰዎች መከሩ (አሴሩ):: አዘንግቶም የመያዙ ዘዴ በሙሉ የአላህ ብቻ ነው:: አላህ ነፍስ ሁሉ የምትሰራውን ያውቃል:: ከሓዲያን የመጨረሻይቱ አገር ለማን እንደምትሆን ወደፊት ያውቃሉ::"},{"id":43,"translation":"43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያም በአላህ የካዱ ሰዎች መልእክተኛ አይደለህም።» ይላሉ። «በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአላህና እርሱ ዘንድ የመጽሐፉ እውቀት ባለው ሰው በቃ።» በላቸው።"}]},{"id":14,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ቁርኣን ሰዎችን በጌታቸው ፈቃድ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አሸናፊ፤ ምስጉን ወደ ሆነው ጌታ መንገድ ታወጣ ዘንድ ወደ አንተ ያወረድነው መጽሐፍ ነው::"},{"id":2,"translation":"2. ወደ እዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ወደ ሆነው ጌታ ወደ አላህ መንገድ (ታወጣ ዘንድ ):: ለከሓዲያን ሁሉ ከብርቱ ቅጣት ወዮላቸው::"},{"id":3,"translation":"3. እነዚያ የቅርቢቱን ህይወት ከመጨረሻይቱ ህይወት ይበልጥ የሚወዱና ከአላህ መንገድ ሰዎችን የሚያግዱ፤ መጥመሟንም (ደካማ ጎኗን) የሚፈልጓት ናቸው:: እነዚያ በሩቅ ስህተት ውስጥ ናቸው::"},{"id":4,"translation":"4. ከመልዕክተኞች ማንኛውንም ለእነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ በወገኖቹ ቋንቋ እንጂ በሌላ አልላክንም:: አላህ የሚፈልገውንም ያጠምማል:: የሚፈልገውንም ያቀናል:: እርሱ ሁሉን አሸናፊውና ጥበበኛው ነውና::"},{"id":5,"translation":"5. ሙሳን ወገኖችህን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አውጣ:: የአላህንም ቀናት አስገንዝባቸው በማለት በተዓምራታችን አጠናክረን በእርግጥ ላክነው:: በዚህ ውስጥ በብዙ ታጋሽና በብዙ አመስጋኝ ለሆኑት ሁሉ በእርግጥ ብዙ ተዓምራት አሉበት::"},{"id":6,"translation":"6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳም ለህዝቦቹ «ከፈርዖን ቤተሰቦች መጥፎን ቅጣት የሚያቀምሷችሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁን የሚያርዱና ሴቶቻችሁንም የሚተው ሲሆን በአዳናችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለላችሁን የአላህን ጸጋ አስታውሱ:: በዚሃችሁ ከጌታችሁ የሆነ ታላቅ ፈተና አለበት።» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ::"},{"id":7,"translation":"7. ጌታችሁም፦ «ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ:: ብትክዱም እቀጣችኋለሁ:: ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነው።» በማለት ባስታወቀ ጊዜ (የሆነዉን አስታውሱ)::"},{"id":8,"translation":"8. ሙሳ፡- «እናንተም በምድር ያለዉም ሁሉ በመላ ብትክዱ አላህ ተብቃቂና ምስጉን ነው።» አለ።"},{"id":9,"translation":"9. (ሙስሊሞች ሆይ!) የእነዚያ ከእናንተ በፊት የነበሩት የኑህ ህዝቦች፤ የዓድ፣ የሠሙድም የእነዚያም ከእነርሱ በኋላ የነበሩት ከአላህ በስተቀር ሌላ የማያውቃቸው ህዝቦች ወሬ (ታሪክ) አልመጣላችሁምን? መልዕክተኞቻቸው በማስረጃዎች መጡላቸውና እጆቻቸውን በቁጭት ሊነክሱ ወደ አፎቻቸው መለሱ: «በተላካችሁበት ነገር ካድን እኛም ወደ እርሱ ከምትጠሩን ነገር አወላዋይ በሆነ ጥርጣሬ ውስጥ ነን።» አሉ።"},{"id":10,"translation":"10. መልዕክተኞቻቸው «ከኃጢአቶቻችሁ እንዲሚራችሁ ወደ ተወሰነ ጊዜም ያለ ቅጣት እንዲያቆያችሁ የሚጠራችሁ ሲሆን ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ በሆነው አላህ በመኖሩ ጥርጣሬ አለን?» አሏቸው:: ህዝቦቹም፡ «እናንተ ብጤያችን ሰው እንጂ (ሌላ ፍጡር) አይደላችሁም:: አባቶቻችን ይገዙት ከነበሩት ልትከለክሉን ትሻላችሁን? ግልጽን አስረጅ ካመጣችሁት ሌላ እስቲ አምጡልን።» አሉ::"},{"id":11,"translation":"11. መልዕክተኞቻቸውም ለእነርሱ አሉ: «እኛ ብጤያችሁ ሰዎች እንጂ ሌላ አይደለንም:: ግን አላህ ከባሮቹ መካከል በሚሻው ሰው ላይ ይለግሳል:: እኛም በአላህ ፈቃድ እንጂ ማስረጃን ልናመጣላችሁ አይገባንም:: በአላህ ላይ ብቻ ምእመናን ይጠጉ (ይመኩ)።"},{"id":12,"translation":"12. «መንገዳችንን በእርግጥ የመራን ሲሆን በአላህ ላይ የማንመካበት ምን አለን? በማሰቃየታችሁም ላይ እንታገሳለን:: በአላህ ላይ ብቻ ተመኪዎች ሁሉ ይመኩ።» (አሉ)"},{"id":13,"translation":"13. እነዚያ በአላህ የካዱት ለመልእክተኞቻቸው: «ከምድራችን በእርግጥ እናወጣችኋለን ወይም ወደ ሃይማኖታችን ትመለሳላችሁ።» አሉ:: ወደ እነርሱም ጌታቸው እንዲህ ሲል ላከ: «(ከሓዲያን) በዳዮችን እናጠፋለን።"},{"id":14,"translation":"14. «ከእነርሱ በኋላም በምድሪቱ በእርግጥ እናስቀምጣችኋለን:: ይህ በፊቴ መቆሙን ለሚፈራና ዛቻዬን ለሚፈራ ነው።»"},{"id":15,"translation":"15. እርዳታንም ከአላህ ፈለጉ፤ ተረዱም። ጨካኝ ሞገደኛ የሆነም ሁሉ አፈረ።"},{"id":16,"translation":"16. ከስተፊቱ ገሀነም አለበት:: እዥ ከሆነም ውሃ ይጋታል::"},{"id":17,"translation":"17. ይጎነጨዋል፤ ሊውጠዉም አይቀርብም:: ሞትም ከየስፍራው ሁሉ ይመጣበታል:: እርሱም የሚሞት አይደለም:: ከበስተፊቱም ከባድ ቅጣት አለ::"},{"id":18,"translation":"18. የእነዚያ በጌታቸው የካዱት ሰዎች መልካም ሥራዎቻቸው ምሳሌ በነፋሻ ቀን ነፋስ እንደ በረታችበት አመድ ነው:: በሠሩት ሥራ በምንም ላይ ሊጠቀሙ አይችሉም። ይህ እርሱ ሩቅ ጥፋት ነው::"},{"id":19,"translation":"19. (የሰው ልጅ ሆይ!) አላህ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ መሆኑን አታይምን? ቢሻ ያጠፋችኋል:: አዲስ ፍጡርንም ያመጣል::"},{"id":20,"translation":"20. ይህም እናንተን አጥፍቶ አዲስ ፍጥረትን ማምጣት በአላህ ላይ አስቸጋሪ ጉዳይ አይደለም::"},{"id":21,"translation":"21. የተሰበሰቡ ሆነው ለአላህ ይገለጻሉ። ሐሳበ ደካማዎቹም ተከታዮች ለእነዚያ ለኮሩት «እኛ ለእናንተ ተከታዮች ነበርን እናንተ ከአላህ ቅጣት ከእኛ ላይ አንዳችን ነገር ተከላካዮች ናችሁን?» ይሏቸዋል። አስከታዮቹም። «አላህ ባቀናን ኖሮ በመራናችሁ ነበር።» ይሏቸዋል:: «ብንበሳጭ ወይም ብንታገሥም በእኛ ላይ ሁሉም እኩል ነው:: ለእኛ ምንም መጠጊያ የለንም።» ይላሉ።"},{"id":22,"translation":"22. ነገሩም በተፈጸመ ጊዜ ሰይጣን ይላቸዋል: «አላህ እውነተኛውን ቃል ኪዳን ገባላችሁ እኔም ቃል ኪዳንም ገባሁላችሁ:: አፈረስኩባችሁም:: ለእኔም በእናንተ ላይ ምንም ሥልጣን አልነበረኝም:: ግና ጠራኋችሁና ታዘዛችሁኝ:: ስለዚህ አትውቀሱኝ ነፍሶቻችሁንም ውቀሱ:: እኔ የምረዳችሁ አይደለሁም እናንተም የምትረዱኝ አይደላችሁም። እኔ ከአሁን በፊት ለአላህ ተጋሪ በአደረጋችሁት ነገር ሁሉ ካድኩ በዳዮቹ ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።»"},{"id":23,"translation":"23. እነዚያ በትክክል ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ሁሉ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በጌታቸው ፈቃድ እንዲገቡ ይደረጋሉ:: በውስጣቸው መከባበሪያቸው ሰላምታቸው «ሰላም ለእናንተ ይሁን መባባል» ነው።"},{"id":24,"translation":"24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ መልካምን ቃል ሥሯ በምድር ውስጥ የተደላደለች ቅርንጫፏም ወደ ሰማይ የረዘመች እንደሆነች መልካም ዛፍ አድርጎ ምሳሌን እንዴት እንደገለጸ አላየህምን?"},{"id":25,"translation":"25. ፍሬዋን (ምግቧን) በጌታዋ ፈቃድ በየጊዜው ትሰጣለች:: አላህም ለሰዎች ይገሰጹ ዘንድ ምሳሌዎችን ይገልጻል::"},{"id":26,"translation":"26. የመጥፎ ቃል ምሳሌ ከምድር በላይ የተገረሰሰች ለእርሷ ምንም መደላደል የሌላት እንደ ሆነች መጥፎ ዛፍ ነው::"},{"id":27,"translation":"27. አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትን በቅርቢቱም ህይወት ሆነ በመጨረሻይቱም በመቃብር በተረጋገጠው ቃል (በሸሀዳ) ላይ ያደርጋቸዋል (ያጸናቸዋል):: ከሓዲያንንም አላህ ያሳስታቸዋል፤ አላህም የሚሻውን ይሰራልና::"},{"id":28,"translation":"28. ወደ እነዚያ የአላህን ጸጋ በክህደት ወደ ለወጡትና ህዝቦቻቸውን በጥፋት ሀገር ወዳሰፈሩት (ወደ ቁረይሾች) አላየህምን? (አልተመለከትክምን?)"},{"id":29,"translation":"29. ሀገሪቱም የሚገቡባት ስትሆን ገሀነም ናት:: መርጊያነቷ ምንኛ ትከፋ!"},{"id":30,"translation":"30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለአላህ ከመንገዱ ያሳስቱ ዘንድ ባላንጣዎችን አደረጉለት:: (ሙሐመድ ሆይ!) «ጥቂትን ተጠቀሙ መመለሻችሁም ወደ እሳት ነው።» በላቸው።"},{"id":31,"translation":"31. መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ለእነዚያ ላመኑት ባሮቼ ሽያጭና ወዳጅነት የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ሶላትን በደንቡ እንዲሰግዱ፤ ከሰጠናቸውም ሲሳይ በሚስጢርም ሆነ በግልጽ እንዲለግሱም ንገራቸው።"},{"id":32,"translation":"32. አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ከሰማይ ዳመናም ውሃን ያወረደ፤ በእርሱም ከፍሬዎች ሁሉ ለእናንተ ሲሳይን ያወጣላችሁ፤ መርከቦችንም በፈቃዱ በባህር ላይ ይንሳፈፉ ዘንድ ለእናንተ ያገራ፤ ወንዞችንም ለናንተ ያገራ ነው።"},{"id":33,"translation":"33. ጸሓይንና ጨረቃንም ዘወትር ሒያጆች ሲሆኑ ለእናንተ የገራ፤ ሌሊትንና ቀንንም ለእናንተ የገራላችሁ ነው::"},{"id":34,"translation":"34. ከለመናችሁትም ሁሉ የሰጣችሁ ነው:: የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ እንኳ አትዘልቁትም:: ሰው በጣም በደለኛና ከሓዲ ነው::"},{"id":35,"translation":"35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም ባለ ጊዜ አስታውስ: «ጌታዬ ሆይ! ይህንን ሀገር መካን ጸጥተኛ አድርገው:: እኔንና ልጆቼንም ጣኦታትን ከመገዛት አርቀን።"},{"id":36,"translation":"36. «ጌታዬ ሆይ! እነርሱ (ጣኦታቱ) ከሰዎች ብዙዎችን አሳስተዋልና:: የተከተለኝም ሰው እርሱ ከእኔ ነው:: ትዕዛዜን የጣሰ ሰው ግን አንተ መሓሪና አዛኝ ነህ።"},{"id":37,"translation":"37. «ጌታችን ሆይ! እኔ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤትህ በካዕባ አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ:: ጌታችን ሆይ! ሶላትን ደንቡን ጠብቀው ይሰግዱ ዘንድ አስቀመጥኳቸው:: ከሰዎችም ልቦችን ወደ እነርሱ የሚናፍቁ አድርግ:: ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍሬዎች ስጣቸው::"},{"id":38,"translation":"38. «ጌታችን ሆይ! አንተ የምንደብቀውንም የምንገልጸውንም ሁሉ በእርግጥ ታውቃለህ:: በአላህ ላይ በምድርም በሰማይም ምንም ነገር አይደበቅም::"},{"id":39,"translation":"39. «ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ ኢስማኢልንና ኢስሐቅን ለሰጠኝ አላህ ምስጋና ሁሉ ይገባው። ጌታዬ ልመናን ሰሚ ነውና::"},{"id":40,"translation":"40. «ጌታዬ ሆይ! ሶላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ:: ከዘሮቼም አድርግ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ።"},{"id":41,"translation":"41. «ጌታችን ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ለአማኞችም ሁሉ ምርመራ በሚደረግበት ቀን ማረን።»"},{"id":42,"translation":"42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ። የሚያቆያቸው ዓይኖች እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው::"},{"id":43,"translation":"43. ወደ ጠሪው መልአክ ቸኳዮች ራሶቻቸውንም አንጋጣጮች ሆነው ዓይኖቻቸው ይፈጣሉ። ዓይኖቻቸው ወደ እነርሱ አይመለሱም:: ልቦቻቸው ባዶዎች ናቸው::"},{"id":44,"translation":"44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰዎችንም ቅጣቱ የሚመጣባቸውን ቀን አስፈራራቸው:: እነዚያም የበደሉትማ «ጌታችን ሆይ! እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አቆየን:: ጥሪህንም እንቀበላለንና መልዕክተኞቹንም እንከተላለንና።» ይላሉ። ይባላሉም: «ከአሁን በፊት በምድረ ዓለም ለእናንተ ምንም መወገድ የላችሁም በማለት የማላችሁ አልነበራችሁምን?"},{"id":45,"translation":"45. «በእነዚያም ነፍሶቻቸውን በበደሉት ሰዎች መኖሪያ ውስጥ ተቀመጣችሁ:: በእነርሱም እንዴት እንደሠራንባቸው ለእናንተም ተገለጸላችሁ፤ ለእናንተ ምሳሌዎችንም ገለጽንላችሁ።»"},{"id":46,"translation":"46. በነብዩ ላይ ሴራቸውንም በእርግጥ አሴሩ:: ሴራቸዉም ቅጣቱ አላህ ዘንድ ነው:: ሴራቸዉም ኮረብታዎች በእርሱ የሚወገዱበት አልነበረም::"},{"id":47,"translation":"47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህንም ለመልዕክተኞቹ የገባላቸውን ቃል ኪዳኑን አፍራሽ አድርገህ አታስብ:: አላህ ሁሉን አሸናፊና የመበቀል ባለቤት ነው::"},{"id":48,"translation":"48. ምድር በሌላ ምድር የምትለወጥበትን ሰማያትም እንደዚሁ በሌላ ሰማያት የሚለወጥበትን እና አንድ ብቸኛና አሸናፊ ለሆነው አላህ ፍጡራን ሁሉ የሚገለጹበትን ቀን የሚሆነውን አስታውስ::"},{"id":49,"translation":"49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አመጸኞችንም በዚያ ቀን በሰንሰለቶች ተቆራኝተው ታያቸዋለህ::"},{"id":50,"translation":"50. ቀሚሶቻቸው ከካትራሜ የተሰሩ ናቸው:: ፊቶቻቸውንም እሳት ትሸፍናቸዋለች::"},{"id":51,"translation":"51. አላህ ይህንን ያደረገው ነፍስ ሁሉ የሠራችውን ትመነዳ ዘንድ ነው:: አላህ ምርመራው ፈጣን ነው::"},{"id":52,"translation":"52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገሳጭና መድረስ ያለበት ነው:: ሊመከሩበት በእርሱም ሊስፈራሩበት፤ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መሆኑን ሊያውቁበት፤ የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰጹበት የተወረደ ነው::"}]},{"id":15,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ እነዚህ አናቅጽ ከመጽሐፍ አናቅጽና ገላጭ ከሆነው ቁርኣን ናቸው።"},{"id":2,"translation":"2.እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች በትንሳኤ ቀን ሙስሊሞች በሆኑ ኖሮ ብለው በብዛት ይመኛሉ::"},{"id":3,"translation":"3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ተዋቸው:: ይብሉ ይጠቀሙም:: ተስፋም ያዘናጋቸው:: በእርግጥም መጥፎ ፍጻሜያቸውን ያውቃሉ::"},{"id":4,"translation":"4. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ማንኛይቱንም ከተማ ለእርሷ የተወሰነ መጽሐፍ ጊዜያት ያላት ሆና እንጂ አላጠፋንም::"},{"id":5,"translation":"5. ማንኛይቱም ሕዝብ የመጥፊያ ጊዜዋን በምንም ዘዴ አትቀድምም:: ከእርሱም በማንም ሀይል አትዘገይምም::"},{"id":6,"translation":"6. እነዚያ የመካ ከሓዲያን አሉ: «አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ እብድ ነህ።"},{"id":7,"translation":"7. «ከእውነተኞቹ እንደ ሆንክ መስካሪ መላዕክት ለምን አታመጣልንም?» አሉ።"},{"id":8,"translation":"8. መላእክትን ደግሞ በእውነት በቅጣት እንጂ አናወርድም:: ያን ጊዜም የሚቆዩ ጊዜ የሚሰጣቸው አይደሉም::"},{"id":9,"translation":"9. እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው:: እኛም ጠባቂዎቹ ነን::"},{"id":10,"translation":"10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተም በፊት በነበሩት በመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ውስጥ መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል:"},{"id":11,"translation":"11. ማንኛዉም መልዕክተኛ በእርሱ የሚያላግጡበት ሆነው እንጂ አይመጣላቸዉም ነበር::"},{"id":12,"translation":"12. ልክ እንደዚሁ ማስተባበልን በአመጸኞች ልቦች ውስጥ እናስገባዋለን::"},{"id":13,"translation":"13. በእርሱ አያምኑበትም፤ የቀድሞዎቹም ድርጊት በእርግጥ አልፋለች (እንደጠፉ ይጠፋሉ)::"},{"id":14,"translation":"14. በእነርሱም ላይ ከሰማይ ደጃፍን በከፈትንላቸውና በእርሱ ሲወጡ ቢውሉም"},{"id":15,"translation":"15. «የተዘጉ ዓይኖቻችን ተጭበርብረው ነው:: እንዲያዉም እኛ የተደገመብን ሰዎች ነን።» ባሉ ነበር።"},{"id":16,"translation":"16. በሰማይም ላይ ከዋክብቶችን በእርግጥ አድርገናል (ፈጥረናል):: ለተመልካቾችም በከዋክብት አጊጠናታል::"},{"id":17,"translation":"17. ከተባረረ ሰይጣንም ሁሉ ጠብቀናታል::"},{"id":18,"translation":"18. ግን ወሬ መስማትን የሚሰርቅ ወዲያውኑ አብሪ ችቦ ይከተለዋል:: (ያቃጥለዋል)::"},{"id":19,"translation":"19. ምድርንም ዘረጋናት:: በውስጧም ኮረብታዎችን ጣልንባት:: በውስጧም የተለካን በቃይ ሁሉ አበቀልንባት::"},{"id":20,"translation":"20.(ሰዎች ሆይ!) በእርሷ ውስጥ ለእናንተ ልዩ ልዩ መኖሪያዎችንና ለእርሱ መጋቢዎቹ ያልሆናችሁትንም እንስሳትን አደረግንላችሁ::"},{"id":21,"translation":"21. መጋዘኖቹም መክፈቻቸው እኛው ዘንድ ያልሆነ ምንም ነገር የለም:: በተወሰነም ልክ እንጂ አናወርደዉም::"},{"id":22,"translation":"22. ንፋስን ደመናን ተሸካሚዎች አድርገን ላክን:: ከሰማይም ከደመና ዝናብን አወረድን:: እርሱንም አጠጣናችሁ:: እናንተ ለእርሱ አድላቢዎች (አከማቾች) አይደላችሁም::"},{"id":23,"translation":"23. እኛ ሕያው የምናደርግና የምንገድል እኛው ብቻ ነን:: እኛው ፍጡርን ሁሉ የምንወርስ ቀሪ ነን::"},{"id":24,"translation":"24. ከናንተም ተቀዳሚዎቹን በእርግጥ አውቀናል:: ወደ ኋላ ቀሪዎቹንም በእርግጥ አውቀናል::"},{"id":25,"translation":"25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)ጌታህ ይሰበስባቸዋል:: እርሱ ጥበበኛና ሁሉን አዋቂ ነውና::"},{"id":26,"translation":"26. ሰውንም ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጥቁር ጭቃ በእርግጥ ፈጠርነው::"},{"id":27,"translation":"27. ጃንን ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው::"},{"id":28,"translation":"28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ለመላዕክት ባለ ጊዜ (የሆነውን አስታውስ): «እኔ ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጭቃ እፈጥራለሁ።"},{"id":29,"translation":"29. «ፍጥረቱን ባስተካከልኩትና በውስጡ ከመንፈሴ በነፋሁበትም ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ሆናችሁ ውደቁ።»"},{"id":30,"translation":"30. መላዓክትም ሁሉም ተሰብስበው ሰገዱ::"},{"id":31,"translation":"31. ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር:: እርሱማ ከሰጋጆቹ ጋር ከመሆን እንቢ አለ።"},{"id":32,"translation":"32. አላህም፡ «ዲያብሎስ ሆይ! ከሰጋጆቹ ጋር የማትሆን ላንተ ምን ምክንያት አለህ?» አለው።"},{"id":33,"translation":"33. «ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከግም ጭቃ ለፈጠርከው ሰው ልሰግድ አይገባኝም።» አለ።"},{"id":34,"translation":"34. አላህም አለው: «ከእርሷም ውጣ አንተ የተባረርክ እርጉም ነህና።"},{"id":35,"translation":"35. «ባንተ ላይም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ እርግማን አለብህ።» አለው።"},{"id":36,"translation":"36. «ጌታዬ ሆይ! እንግዲያውስ እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ።» አለ።"},{"id":37,"translation":"37. አላህም አለ፡- «አንተ ከሚቆዩት ነህ።"},{"id":38,"translation":"38. «እስከታወቀው ቀን ድረስ።»"},{"id":39,"translation":"39. ዲያብሎስም አለ፡- «ጌታዬ ሆይ! እኔን በማጥመምህ ይሁንብኝ ለእነርሱ በምድር ላይ ኃጢአትን እሸልምላቸዋለሁ። ሁላቸውንም አጠማቸዋለሁ።"},{"id":40,"translation":"40. «ከእነርሱ ፍጹሞቹ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ።»"},{"id":41,"translation":"41. አላህም አለ፡- «ይህ በእኔ ላይ መጠበቁ የተገባ ቀጥተኛ መንገድ ነው።"},{"id":42,"translation":"42. «እነሆ ባሮቼ! በእነርሱ ላይ አንተ ስልጣን የለህም። ከጠማሞች የተከተለህ ሰው ብቻ ሲቀር።"},{"id":43,"translation":"43. «ገሀነምም ለእርሱና ለተከተሉት ለሁሉም በእርግጥ ቀጠሯቸው ናት።"},{"id":44,"translation":"44. «ለእርሷ ሰባት በሮች (ደጃፎች ) አሏት። ለየበሮቹም ሁሉ ከሰይጣናት ቡድኖች የተከፋፈለ ድርሻ አለ።»"},{"id":45,"translation":"45. እነዚያ ከኃጢአት የተጠነቀቁት በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው::"},{"id":46,"translation":"46. «ጸጥተኞች ሆናችሁ በሰላም ግቧት።» ይባላሉ።"},{"id":47,"translation":"47. በአልጋዎችም ላይ ፊት ለፊት የሚተያዩ ወንድማማቾች ሆነው በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ቂም ሁሉ እናስወግዳለን::"},{"id":48,"translation":"48. በእርሷም ውስጥ ምንም ድካም አይነካቸዉም፤ እነርሱም ከእርሷ ለምንጊዜም የሚወጡ አይደሉም::"},{"id":49,"translation":"49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መሃሪና አዛኝ እኔው ብቻ መሆኔን ለባሮቼ ንገር::"},{"id":50,"translation":"50. ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መሆኑንም ንገራቸው።"},{"id":51,"translation":"51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከኢብራሂም እንግዶችም ወሬ ንገራቸው::"},{"id":52,"translation":"52. በእርሱ ላይ በገቡና ሰላም ባሉት ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: እርሱም፡- «እኛ ከናንተ ፈሪዎች ነን።» አላቸው።"},{"id":53,"translation":"53. «አትፍራ እኛ አዋቂ በሆነ ወንድ ልጅ እናበስርሃለን።» አሉት።"},{"id":54,"translation":"54. «እርጅና የደረሰብኝ ከመሆኔ ጋር አበሰራችሁኝን? በምን ታበስሩኛላችሁ?» አለ።"},{"id":55,"translation":"55. «በእውነት አበሰርንህ ከተስፋ ቆራጮችም አትሁን።» አሉ።"},{"id":56,"translation":"56. «ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነው?» አለ።"},{"id":57,"translation":"57. «እናንተ መልዕክተኞች ሆይ! ኧረ ለመሆኑ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አለ።"},{"id":58,"translation":"58. አሉም: «እኛ አመፀኞች ወደ ሆኑ ሕዝቦች ተልከናል።"},{"id":59,"translation":"59. «የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱን እኛ ሁላቸውንም በእርግጥ የምናድናቸው ነን።"},{"id":60,"translation":"60. «ሚስቱ ብቻ ስትቀር።» (አሉ) እርሷንማ በቅጣቱ ውስጥ ከሚቀሩት ሰዎች መሆኗን ወስነናል።"},{"id":61,"translation":"61. መልዕክተኞቹም የሉጥን ቤተሰቦች በመጡባቸው ጊዜ።"},{"id":62,"translation":"62. ሉጥ «እናንተ የተሳሳታችሁ ሕዝቦች ናችሁ።» አላቸው።"},{"id":63,"translation":"63. አሉም: «አይደለም:: እኛ ህዝቦችህ በእሱ ይጠራጠሩበት በነበሩት ቅጣት መጣንልህ።"},{"id":64,"translation":"64. «እውነትንም ይዘን መጣንልህ:: እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን።"},{"id":65,"translation":"65. «ከቤተሰብህ ጋር በሌሊቱ ከፊል (አጋማሽ) ላይ ሂድ:: በኋላቸዉም ተከተል:: ከናንተም አንድም ሰው ወደ ኋላው አይገላመጥ:: ወደ ታዘዛችሁበትም ስፍራ እለፉ።» አሉት::"},{"id":66,"translation":"66. ወደ እርሱም ያንን ትዕዛዝ አወረድን :: እርሱም የእነዚህ ሕዝቦች መጨረሻ ያነጉ ሲሆኑ ስራቸው መቆረጥ ነው::"},{"id":67,"translation":"67. የከተማይቱም ሰዎች የሚበሳሰሩ ሆነው መጡ::"},{"id":68,"translation":"68. ሉጥም አለ፡- «እነዚህ እንግዶቼ ናቸውና አታጋልጡኝ።"},{"id":69,"translation":"69. «አላህንም ፍሩ አታሳፍሩኝም።»"},{"id":70,"translation":"70. «ከዓለማት ማንንም እንዳታስተናግድ አልከለከልንህምን?» አሉት።"},{"id":71,"translation":"71. ሉጥም፡- «እነዚህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው። የምትፈጽሙ ከሆናችሁ አግቧቸው።» አለ።"},{"id":72,"translation":"72. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዕድሜህ እንምላለን እነርሱ በእርግጥ በስካራቸው ውስጥ ይዋልላሉ::"},{"id":73,"translation":"73. ጩኸቲቱም ጸሐይ የወጣችባቸው ሲሆኑ ያዘቻቸው::"},{"id":74,"translation":"74. ላይዋንም ከታችዋ አደረግን:: በእነርሱም ላይ የሸክላ ድንጋዮችን አዘነብንባቸው::"},{"id":75,"translation":"75. በዚህ ውስጥ ለተመልካቾች በእርግጥ ብዙ መገሰጫዎች አሉበት::"},{"id":76,"translation":"76. እርሷም ከተማይቱ በቀጥታ መንገድ ላይ ናት::"},{"id":77,"translation":"77. በዚህ ውስጥ በእርግጥ ለአማኞች መገሰጫ አለ::"},{"id":78,"translation":"78. እነሆ የአይካ ሰዎችም በእርግጥ በዳዮች ነበሩ::"},{"id":79,"translation":"79. ከእነርሱም ተበቀልን ሁለቱም የሉጥና የአይከት ሕዝቦች ከተሞች በእርግጥ በግልጽ መንገድ ላይ ናቸው::"},{"id":80,"translation":"80. የሒጅር ሰዎች መልዕክተኞቹን በእርግጥ አስተባበሉ::"},{"id":81,"translation":"81. ተዓምራታችንን ሰጠናቸው ከርሷም ዘንጊዎች ነበሩ::"},{"id":82,"translation":"82. ከኮረብታዎችም ቤቶችን ጸጥተኞች ሆነው ይጠርቡ ነበር::"},{"id":83,"translation":"83. ያነጉ ሲሆኑ ጩኸት ያዘቻቸው (ወደሙ)።"},{"id":84,"translation":"84. ይሠሩት የነበሩትም ምንም አልጠቀማቸዉም::"},{"id":85,"translation":"85. ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በእውነት እንጂ በላግጣ አልፈጠርንም:: ሰዓቲቱም በእርግጥ መጪ ናት:: መልካምን ይቅርታ አድርግላቸው::"},{"id":86,"translation":"86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ እርሱ ያልነበረን ነገር ሁሉ ፈጣሪው፤ አዋቂው ነው።"},{"id":87,"translation":"87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሚደጋገሙ የሆኑን ባለ ሰባት አንቀጽንና ታላቁንም ቁርኣን በሙሉ በእርግጥ ሰጠንህ::"},{"id":88,"translation":"88. ከእነርሱ ከከሓዲያን ብዙዎችን ወገኖች በእርሱ ወደ አጣቀምንበት ጸጋ ዓይኖችህን አትዘርጋ፤ በእነርሱም ላይ ባያምኑ አትዘን፤ ክንፍህንም ለአማኞች አለዝብ።"},{"id":89,"translation":"89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ግልጽ አስፈራሪ እኔ ነኝ።» በል።"},{"id":90,"translation":"90. (ሰዎችን ለማገድ የመካን በሮች) በተከፋፈሉት ላይ እንደ አወረድነው (ቅጣት አስፈራሪያችሁ ነኝ በል)::"},{"id":91,"translation":"91. እነርሱም እነዚያ ቁርኣንን ክፍልፍሎች ያደረጉ ናቸው::"},{"id":92,"translation":"92. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጌታህ እንምላለን ሁላቸውንም እንጠይቃቸዋለን::"},{"id":93,"translation":"93. ይሠሩት ከነበሩት ነገር ሁሉ"},{"id":94,"translation":"94. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለጽ:: አጋሪዎችንም ተዋቸው::"},{"id":95,"translation":"95. ተሳላቂዎችንም ሁሉ እኛ በቅተንሃል::"},{"id":96,"translation":"96. እነርሱም እነዚያ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን ያደረጉ ናቸው:: በእርግጥም ፍጻሜያቸውን ወደፊት ያውቃሉ::"},{"id":97,"translation":"97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መሆኑን እናውቃለን::"},{"id":98,"translation":"98. ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው:: ከሰጋጆቹም ሁን::"},{"id":99,"translation":"99. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውነቱም ነገር (ሞት) እስኪመጣልህ ድረስ ጌታህን ተገዛ::"}]},{"id":16,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (ከሓዲያን ሆይ!)፤ የአላህ ትዕዛዝ መጣ ስለዚህ አታጣድፉት:: አላህ ከማይገባው ሁሉ ጠራ:: ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ::"},{"id":2,"translation":"2. ከባሮቹ መካከል በሚሻው ሰው ላይ መላዕክትን ከራዕይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል:: «ከሓዲያንን በቅጣት አስጠንቅቁ:: እነሆ ከእኔ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: ፍሩኝም።» ማለትን አስታውቁ በማለት ያወርዳል።"},{"id":3,"translation":"3. ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ:: ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ :: ከፍም አለ::"},{"id":4,"translation":"4.ሰውን ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው:: ከዚያም እርሱ ወዲያውኑ ትንሣኤን በመካድ ግልጽ ተከራካሪ ይሆናል::"},{"id":5,"translation":"5. (ሰዎች ሆይ!) ግመልን፤ ከብትን፤ ፍየልንም፤ በእርሷ ብርድ መከላከያ ሙቀትና ሌሎች ጥቅሞችም ያሉባት ስትሆን ለእናንተ ፈጠረላችሁ:: ከእርሷም ትበላላችሁ (ትመገባላችሁ)::"},{"id":6,"translation":"6. በእርሷም ወደ ማረፊያዋ በምትመልሷት ጊዜና ጧት ወደ ግጦሽ ቦታዋ በምታሰማሯት ወቅት ለእናንተ ውበት አለላችሁ።"},{"id":7,"translation":"7. ጓዞቻችሁንም ነፍሶቻችሁን በማስቸገር እንጂ ወደ ማትደርሱበት አገር ትሸከማለች:: ጌታችሁ በእርግጥ ሩህሩህ እና አዛኝ ነውና::"},{"id":8,"translation":"8. ፈረሶችን፤ በቅሎዎችንና አህዮችን ልትጋልቧቸውና ልታጌጡባቸው ፈጠረላችሁ:: የማታውቁትን ድንቅ ነገርም ወደ ፊት ይፈጥራል::"},{"id":9,"translation":"9. በአላህም ላይ በችሮታው ቀጥተኛውን መንገድ መግለጽ አለበት:: ከእርሷም ጠማማ አለ:: በሻም ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር::"},{"id":10,"translation":"10. እርሱ ያ ከሰማይ ውሃን ያወረደ ነው:: ከእርሱም ለእናንተ መጠጥ አለላችሁ:: ከእርሱም እንስሳዎችን በእርሱ ውስጥ የምታሰማሩበት ዛፍ ይበቅልበታል::"},{"id":11,"translation":"11. በእርሱ አዝመራን፣ የዘይት ወይራን፣ ዘምባባዎችን፣ ወይኖችንና ከፍሬዎችም ሁሉ ያበቅልላችኋል:: በዚህ ክስተት ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ሁሉ በእርግጥ ትልቅ ተዓምር አለ።"},{"id":12,"translation":"12. ለእናንተ ሌሊትንና ቀንን ጸሐይንና ጨረቃንም ገራላችሁ:: ከዋክብትም በሙሉ በፈቃዱ ብቻ የተገሩ ናቸው:: በዚህ ክስተት ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች ሁሉ በእርግጥ አያሌ ተዓምራት አሉ::"},{"id":13,"translation":"13. በምድርም ላይ መልኮቹ የተለያዩ ሆኖ የፈጠረላችሁን ሁሉ ገራላችሁ:: በዚህ ውስጥ ለሚገሠጹ ሕዝቦች ሁሉ ግልጽ ተዐምር አለ::"},{"id":14,"translation":"14. እርሱ ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ስጋን ልትበሉና ከእርሱም የምትለብሱትን ጌጣጌጥ ታወጡ ዘንድ የገራ ነው:: መርከቦችንም በውስጡ ውሃውን ቀዳጆች ሆነው ሲንሻለሉ ታያለህ:: ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑም ገራላችሁ::"},{"id":15,"translation":"15. በምድር ውስጥ በናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለባት። ትመሩም ዘንድ ጅረቶችንና መንገዶችን አደረገ።"},{"id":16,"translation":"16. ምልክቶችንም አደረገ:: በከዋክብትም እነርሱ ይመራሉ::"},{"id":17,"translation":"17. (ሰዎች ሆይ!) የሚፈጥር ልክ እንደማይፈጥር ነውን? አትገሠጹምን?"},{"id":18,"translation":"18. የአላህን ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":19,"translation":"19. አላህ የምትደብቁትንና የምትገልጹትንም ሁሉ ያውቃል::"},{"id":20,"translation":"20. እነዚያም ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው አማልክት ሁሉ ምንንም አይፈጥሩም:: እንዲያዉም እነርሱ ራሳቸው ይፈጠራሉ::"},{"id":21,"translation":"21. እነርሱ ሕያው ያልሆኑ ሙታን ናቸው:: እራሳቸው እንኳን መቼ እንደሚቀሰቀሱ አያውቁም::"},{"id":22,"translation":"22. አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ልቦቻቸው ከሓዲያን ናቸው:: እነርሱም የኮሩ ናቸው::"},{"id":23,"translation":"23. አላህ የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ የሚያውቅ ለመሆኑ ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ የለበትም:: እርሱ ኩሩዎችን አይወድም::"},{"id":24,"translation":"24. ጌታችሁ በሙሐመድ ላይ ምን አወረደ በተባሉ ጊዜም: «የመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ተረቶችን ነው።» ይላሉ።"},{"id":25,"translation":"25. ይህንን የሚሉት በትንሣኤ ቀን ኃጢአቶቻቸውን በሙሉና ከነዚያም ያለ ዕውቀት ሆነው ከሚያጣምሟቸው ሰዎች ኃጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው:: ንቁ የሚሸከሙት ኃጢአት ምንኛ ከፋ!"},{"id":26,"translation":"26. እነዚያ ከእነርሱ (ከቁረይሾች) በፊት የነበሩት ከሓዲያን አሴሩ:: ከዚያም አላህ ሕንጻዎቻቸውን ከመሠረቶቻቸው አፈረሰ:: እናም ጣሪያው በላያቸው ላይ ወደቀባቸው:: ቅጣቱም ከማያውቁት ስፍራ መጣባቸው::"},{"id":27,"translation":"27. ከዚያም በትንሣኤ ቀን ያዋርዳቸዋል:: «እነዚያም በእነርሱ ጉዳይ ትከራከሩኝ የነበራችሁት ተጋሪዎቼ የት ናቸው?» ይላቸዋል። እነዚያ እውቀትን የተሰጡት ክፍሎች «ዛሬ ሐፍረቱና ቅጣቱ በከሓዲያን ላይ ነው።» ይላሉ።"},{"id":28,"translation":"28. እነዚያ ነፍሶቻችውን በዳይ ሆነው መላዕክት የሚገድሏቸው «ከክፉ ሥራ ምንም ነገር የምንሠራም አልነበርንም» ሲሉ ታዛዥነታቸውን ይገልፃሉ:: «በእውነት አላህ ትሠሩት የነበራችሁትን ነገር አዋቂ ነው።» ይባላሉ።"},{"id":29,"translation":"29. «የገሀነምንም ደጃፎች በውስጧ ዘውታሪዎች ስትሆኑ ግቡ።» ይባላሉ:: የኩሩ ሰዎች ሁሉ መኖሪያ የሆነችው ገሀነምም በእርግጥ ከፋች!"},{"id":30,"translation":"30. ለእነዚያም ለተጠነቀቁት ሰዎች «ጌታችሁ ምንን ነገር አወረደ?» ተባሉ:: «መልካምን ነገር አወረደ» አሉ:: ለእነዚያ ደግ ለሠሩት ህዝቦች ሁሉ በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ኑሮ አለላቸው:: የመጨረሻይቱም አገር በእርግጥ በላጭ ናት:: የጥንቁቆቹም አገር ገነት ምን ታምር!"},{"id":31,"translation":"31. እርሷም የሚገቧትና በሥርዋ ወንዞች የሚፈሱባት ስትሆን የመኖሪያ አትክልቶች (ጀነት) ናት:: ለእነርሱም በውስጧ የሚሹት ነገር ሁሉ አለላቸው:: ልክ እንደዚሁም አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል::"},{"id":32,"translation":"32. እነዚያ ጥሩ ሆነው መላዕክት «ሰላም ለእናንተ ይሁን\" እያሉ የሚገድሏቸው \"ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ምክንያትም ወደ ገነት ግቡ።» ይባላሉ።"},{"id":33,"translation":"33. ከሓዲያን የመላዕክትን ወደ እነርሱ መምጣት ወይም የጌታህ ትዕዛዝ መምጣቱን እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? ከእነርሱ በፊት የነበሩትም ልክ እንደዚህ ሠርተዋል:: አላህም አልበደላቸዉም:: ግን እነርሱ ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ::"},{"id":34,"translation":"34. እናም የሠሯቸዉም ኃጢአቶች ቅጣት አገኛቸው:: ይሳለቁበት የነበሩት ነገር ሁሉ በእነርሱ ላይ ወረደባቸው::"},{"id":35,"translation":"35. እነዚያም ጣዖታትን በአላህ ያጋሩ ህዝቦች «አላህ በሻ ኖሮ ከእርሱ ሌላ እኛም ሆንን አባቶቻችን ምንንም ባልተገዛን ነበር:: ያለ እርሱም ትዕዛዝ ምንንም እርም ባላደረግን ነበር።» አሉ:: እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት ህዝቦች ልክ እንደዚሁ ሠሩ:: በመልዕክተኞቹም ላይ ግልጽ ማድረስ ብቻ እንጂ ሌላ የለባቸዉም::"},{"id":36,"translation":"36. በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣዖትን ራቁ በማለት የሚያስተምር መልዕክተኛን ልከናል:: ከእነርሱም ውስጥ አላህ ያቀናው አለ:: ከእነርሱም ውስጥ በእርሱ ላይ ጥመት የተረጋገጠበት አለ:: እናም በምድር ላይ ሂዱ:: የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበር ተመልከቱ::"},{"id":37,"translation":"37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመቅናታቸው ላይ ብትጓጓ (ምንም ልታደርግ አትችልም):: ምክንያቱም አላህ የሚያጠመውን አያቀናዉምና:: ለእነርሱም ከረዳቶች ምንም የላቸዉም::"},{"id":38,"translation":"38. ጥብቅ መሐሎቻቸውንም «አላህ የሚሞትን ሰው አያስነሳም።» ሲሉ በአላህ ስም ማሉ:: አባባላቸው ሐሰት ነው። ያስነሳቸዋል:: በእርሱ ላይ ቃል ኪዳን ገብቷል:: አረጋግጧልም:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::"},{"id":39,"translation":"39. የሚቀሰቅሳቸዉም ለእነርሱ ያንን የሚለያዩበትን ሊገልጽላቸውና እነዚያ የካዱትም እነርሱ ውሸታሞች የነበሩ መሆናቸውን እንዲያውቁ ነው::"},{"id":40,"translation":"40. ለማንኛዉም ነገር መሆኑን በፈለግን ጊዜ ቃላችን ለእርሱ \"ሁን\" ማለት ብቻ ነው:: ወዲያዉም ይሆናል::"},{"id":41,"translation":"41. እነዚያም ከተበደሉ በኋላ በአላህ መንገድ ላይ የተሰደዱ በቅርቢቱ ዓለም መልካሚቱን አገር (መዲናን) እናሰፍራቸዋለን:: የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ታላቅ ነው:: (ከሓዲያን) ቢያውቁ ኖሮ (በተከተሏቸው ነበር)::"},{"id":42,"translation":"42. እነርሱ እነዚያ የታገሡና በጌታቸዉም ላይ የሚጠጉ ናቸው::"},{"id":43,"translation":"43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተም በፊት ወደ እነርሱ ወሕይን የምናወርድላቸውን ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም:: (ሰዎች ሆይ! ) የማታውቁም ከሆናችሁ የዕውቀትን ባለቤቶችን ጠይቁ::"},{"id":44,"translation":"44. በግልጽ ማስረጃዎችና በመጽሐፍ ላክናቸው። ለሰዎችም ወደ እነርሱ የተወረደላቸውን ፍች ትገልጽላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ ወደ አንተ ቁርኣንን አወረድን::"},{"id":45,"translation":"45. እነዚያን መጥፎዎችን የዶለቱ ሰዎች አላህ በእነርሱ ምድርን የሚያስዉጣቸው ወይም ከማያውቁት ሥፍራ ቅጣት የሚመጣባቸው መሆኑን ተማመኑን? አይፈሩምን?"},{"id":46,"translation":"46. ወይም ከአገር ወደ አገር በሚዛወሩበት ጊዜ በእንቅስቃሴ ላይ እያሉ የሚይዛቸው መሆኑን አይፈሩምን? እነርሱም አሸናፊዎች አይደሉም::"},{"id":47,"translation":"47. ወይም ቀስ በቀስ በማጉደል ላይ የሚይዛቸው መሆኑን ተማመኑን? አይፈሩምን? ጌታችሁም ሩሕሩህና አዛኝ ነው::"},{"id":48,"translation":"48. ወደዚያ ከማንኛዉም ነገር አላህ ወደ ፈጠረው ጥላዎቹ እነርሱም የተዋረዱ ሲሆኑ ለአላህ ሰጋጆች ሆነው ከቀኝ እና ከግራዎች ወደ ሚዛወሩት አላዩምን?"},{"id":49,"translation":"49. በሰማያትና በምድር ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ መላዕክትም ለአላህ ብቻ ይሰግዳሉ:: እነርሱም አይኮሩም::"},{"id":50,"translation":"50. ጌታቸውን ከበላያቸው ሲሆን ይፈሩታል:: የታዘዙትንም ሁሉ ይሰራሉ (ይፈጽማሉ):: {1}","footnotes":"{1} አዚህ የንባብ ሱጁድ (ሱጁድ አትላዋ) ይደረጋል።"},{"id":51,"translation":"51. አላህም አለ: «ሁለት አማልክት አትያዙ እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እኔን ብቻ ፍሩኝ።»"},{"id":52,"translation":"52. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: አምልኮም ዘወትር ለርሱ ብቻ ነው:: ከአላህ ሌላ ያለን ትፈራላችሁን?"},{"id":53,"translation":"53. ማንኛዉም በናንተ ላይ ያለው ጸጋ ከአላህ ብቻ ነው። ከዚያም ችግር በደረሰባችሁ ጊዜ ወደ እርሱ ብቻ ትጮሀላችሁ።"},{"id":54,"translation":"54. ከዚያም ከናንተ ላይ ችግርን ባነሳላችሁ ጊዜ ከናንተ የሆኑ ቡድኖች ወዲያውኑ በጌታችሁ ጣዖትን ያጋራሉ::"},{"id":55,"translation":"55. የሚያጋሩትም በሰጠናቸው ሊክዱ ነው:: ተጠቀሙም ወደፊትም የሚደርስባቸውን ታውቃላችሁ::"},{"id":56,"translation":"56. ለማያውቁት ጣዖታትም ከሰጠናቸው ሲሳይ ድርሻን ያደርጋሉ:: በአላህ እምላለሁ ትቀጣጥፉት ከነበራችሁት ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ::"},{"id":57,"translation":"57. ለአላህ ሴቶች ልጆችን ያደርጋሉ። ጥራት ይገባው። ለእነርሱ ግን የሚፈልጉትን ያደርጋሉ።"},{"id":58,"translation":"58. ከመሀከላቸው አንዱ በሴት ልጅ (መወለድ) በተበሰረ ጊዜ እርሱ የተቆጨ ሆኖ ፊቱ ጠቁሮ ቅስሙ ይሰበራል።"},{"id":59,"translation":"59. ከተበሰረበት ነገር መጥፎነት በውርደት ላይ ሆኖም ቢሆን ይያዘውን? ወይስ በአፈር ውስጥ ይደብቀውን? በማለት እያምታታ ከሰዎች ይደበቃል:: የሚፈርዱት ፍርድ ምንኛ ከፋ!"},{"id":60,"translation":"60. ለእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም ለማያምኑት ሰዎች ሁሉ መጥፎ መገለጫ አላቸው:: ለአላህ ግን ታላቅ መገለጫ አለው:: እርሱም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::"},{"id":61,"translation":"61. አላህም ሰዎችን በበደላቸው ሁሉ በቀጣቸው ኖሮ በምድር ላይ ከተንቀሳቃሽ ምንንም ባላስቀረ ነበር:: ግን እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ያቆያቸዋል:: ጊዜያቸዉም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይዘገዩም፤ አይቀድሙም።"},{"id":62,"translation":"62. ለአላህም የሚጠሉትን ነገር ያደርጋሉ:: ለእነርሱም መልካሚቱ (ሀገር) እንዳለቻቸው በምላሶቻቸው ውሸትን ይናገራሉ:: ለእነርሱም እሳት ያለቻቸው መሆናቸውና እነርሱም ወደ እርሷ በቅድሚያ የሚነዱ መሆናቸው ጥርጥር የለበትም::"},{"id":63,"translation":"63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ እንምላለን ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ ብዙ መልዕክተኞችን ልከናል:: ሰይጣንም ለእነርሱ ስራዎቻቸውን ሸለመላቸው:: ረዳታቸው ዛሬም እርሱ ነው:: ለእነርሱም ኋላ አሳማሚ ቅጣት አላቸው::"},{"id":64,"translation":"64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን በእርሱ የተለያዩበትን ለእነርሱ ልታብራራላቸውና ለሚያምኑትም ህዝቦች መሪና እዝነት ሊሆን እንጂ ባንተ ላይ መፅሀፉን አላወረድንም።"},{"id":65,"translation":"65. አላህ ከሰማይ ውሃን አወረደ:: በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው አደረገ:: በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ህዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለ::"},{"id":66,"translation":"66. (ሰዎች ሆይ!) ለእናንተ በግመል በከብት በፍየል አፈጣጠር አያሌ ምክር ሰጪ ትምህርት አለላችሁ:: በሆዶች ውስጥ ካለው ከፈርስና ከደም መካከል ጥሩ ወተትን ለጠጪዎች ጣፋጭ ሲሆን እናጠጣችኋለን::"},{"id":67,"translation":"67. ከዘንባባዎች ከወይኖችም ፍሬዎች እንመግባችኋለን፤ ከእርሱ ጠጅንና መልካም ምግብንም ትሰራላችሁ (ታዘጋጃላችሁ):: በዚህም ውስጥ ለሚያስቡ ህዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለ::"},{"id":68,"translation":"68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል (አስታወቀ) አስተማረ፡ «ከተራራዎች ከዛፍና ሰዎች ከሚሠሩት ቀፎ ቤቶችን ያዢ::"},{"id":69,"translation":"69. «ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ የጌታሽንም መንገዶች ለአንቺ የተገሩ ሲሆኑ ግቢ።» ከሆዶቿ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል:: በእርሱ ውስጥ ለሰዎች ፍቱን መድሀኒት አለበት። በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ተዓምር አለበት::"},{"id":70,"translation":"70. አላህም ፈጠራችሁ ከዚያ ይገድላችኋል:: ከናንተም መካከል ከእውቀት በኋላ ምንንም ነገር የማያውቅ ወደሚሆንበት የጃጀ እድሜ የሚመለስም ሰው አለ:: አላህ ሁሉን አዋቂ፤ በሁሉም ነገር ላይ ቻይም ነው።"},{"id":71,"translation":"71. አላህ ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በሲሳይ አበለጠ:: እነዚያም በላጭ የተደረጉት ሲሳያቸውን እጆቻቸው በያዟቸው ባሮች ላይ እነርሱ በእርሱ ይስተካከሉ ዘንድ መላሾች አይደሉም:: ታዲያ በአላህ ጸጋ ለእርሱ ተጋሪ በማድረግ ይክዳሉን?"},{"id":72,"translation":"72. አላህ ከነፍሶቻችሁ (ከጎሳዎቻችሁ) ለእናንተ ሚስቶችን አደረገ (የትዳር አጋሮችን ፈጠረ)፤ ለእናንተም ከሚስቶቻችሁ ወንዶች ልጆችን የልጅ ልጆችንም አደረገላችሁ:: ከመልካሞችም ጸጋዎች ሰጣችሁ:: ታዲያ በውሸት በጣኦት አምነው በአላህ ጸጋ ይክዳሉን?"},{"id":73,"translation":"73. ከአላህም ሌላ ከሰማያትና ከምድር ምንንም ሲሳይ የማይሰጧቸውንና ምንንም የማይችሉትን እነርሱ ያመልካሉን::"},{"id":74,"translation":"74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለአላህ አምሳያዎችን አታድርጉ:: አላህ ያውቃል፤ እናንተ ግን አታውቁም::"},{"id":75,"translation":"75. በምንም ላይ የማይችል ሆኖ በይዞታ (አለቃ ያለበት) የሆነውን ባሪያና መልካም ሲሳይን ሰጥተነው እርሱም ከእርሱ ከሰጠነው በሚስጥርና በግልጽ የሚለግሰውን ነፃ ሰው አላህ ለጣኦትና ለእርሱ ምሳሌ አደረገ:: ሁለቱ ይስተካከላሉን? ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይሁን:: በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም::"},{"id":76,"translation":"76. አላህ ሁለትን ወንዶች (ለከሓዲያንና ለአማኞች) ምሳሌ አደረገ:: አንደኛቸው በምንም ነገር ላይ የማይችል ዲዳ ነው:: እርሱም በጌታው ላይ ሸክም ነው:: ወደ የትም ቢያዞረው ደግ ነገር አያመጣም:: እርሱና ያ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ሆኖ በማስተካከል (ፍትህ) የሚያዘው ሰው ይስተካከላሉን?"},{"id":77,"translation":"77. በሰማያትና በምድር ያለው ሩቅ ምስጢር የአላህ ብቻ ነው:: የሰዓቲቱም ነገር መምጣቷ እንደ ዓይን ቅጽበት እንጂ አይደለም:: ወይም ይበልጥ የቀረበ ነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::"},{"id":78,"translation":"78. አላህ ከእናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ:: ታመሰግኑ ዘንድም ለእናንተ መስሚያንና ማያዎችን ልቦችንም አደረገላችሁ (ፈጠረላችሁ)::"},{"id":79,"translation":"79. ወደ በራሪዎችም በሰማይ አየር ውስጥ ለመብረር የተገሩ ሲሆኑ ከመውደቅ አላህ እንጂ ሌላ የማይዛቸው መሆናቸውን አይመለከቱምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተዓምራት አሉ::"},{"id":80,"translation":"80. አላህም ከቤቶቻችሁ ለእናንተ መርጊያን (ማረፊያን) አደረገላችሁ (ፈጠረላችሁ):: ከእንስሳዎችም ቆዳዎችን በጉዟችሁ ቀንም ሆነ በመቀመጫችሁ ቀን የምታቀሏቸውን ቤቶች (ዳሶች) ለእናንተ ፈጠረላችሁ:: ከበጓ ሱፎች፣ ከግመሏም ጠጉሮች፣ ከፍየሏም ጠጉሮች የቤት እቃዎችን እስከ ጊዜም ድረስ መጠቃቀሚያን አደረገላችሁ።"},{"id":81,"translation":"81. አላህ ከፈጠረው ነገር ለእናንተ ጥላዎችን ፈጠረላችሁ:: ከጋራዎችም መከለያዎችን ፈጠረላችሁ:: ሐሩርንም ብርድንም የሚጠብቋችሁን ልብሶች፤ የጦራችሁንም አደጋ የሚጠብቋችሁን ጥሩሮች ፈጠረላችሁ:: ልክ እንደዚሁ ትሰልሙ ዘንድ ጸጋውን በእናንተ ላይ ይሞላል::"},{"id":82,"translation":"82. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከኢስላም ቢሸሹም ባንተ ላይ ያለብህ ግልጽ ማድረስ ብቻ ነው::"},{"id":83,"translation":"83. የአላህን ጸጋ ያውቃሉ:: ሆኖም ከዚያ ይክዷታል:: አብዛኞቻቸዉም ከሓዲያን ናቸው::"},{"id":84,"translation":"84. ከየህዝቡም ሁሉ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን ቀን አስታውስ:: ከዚያ ለእነዚያ ለካዱት ንግግር አይፈቀድላቸዉም:: እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም::"},{"id":85,"translation":"85. እነዚያ የበደሉ ሰዎች ቅጣትን ባዩ ጊዜ ለእነርሱ አይቃለልላቸዉም:: ጊዜም አይሰጣቸዉም::"},{"id":86,"translation":"86. እነዚያ በአላህ ያጋሩት ሰዎች ተጋሪዎቻቸውን ባዩ ጊዜ «ጌታችን ሆይ! እነዚህ ካንተ ሌላ እናመልካቸው የነበሩ ተጋሪዎቻችን ናቸው።» ይላሉ። አማልክቶችም «ውሸታሞች ናችሁ።» በማለት ቃሉን ወደ እነርሱው መልሰው ይወረውራሉ።"},{"id":87,"translation":"87. አጋሪዎቹ በዚያ ቀንም ታዛዥነታቸውን ወደ አላህ ያቀርባሉ:: ይቀጣጥፉት የነበሩትም ሁሉ ከእነርሱ ይጠፋባቸዋል::"},{"id":88,"translation":"88. እነዚያ በአላህ የካዱና ከአላህ መንገድ የከለከሉ ያጠፉ በነበሩት ምክንያት ቅጣትን በቅጣት ላይ ጨመርንባቸው::"},{"id":89,"translation":"89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በየህዝቡ ሁሉ ውስጥ ከጎሳቸው በራሳቸው ላይ መስካሪን የምንቀሰቅስበትንና አንተንም በእነዚህ ሕዝቦች ላይ መስካሪ አድርገን የምናመጣብህን ቀን አስታውስ:: መጽሐፉንም ለሁሉም ነገር አብራሪ፤ መመሪያ፣ እዝነትና ለሙስሊሞች አብሳሪ ሆኖ ባንተ ላይ አወረድነው::"},{"id":90,"translation":"90. አላህ በማስተካከል (በፍትህ) ፤ በማሳመር (በመልካም ሥራ) እና ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል። ከአስከፊ (ጸያፍ ነገር) ከማመንዘር፤ ከሚጠላ ነገር ሁሉ ከመበደልም ይከለክላል:: ትገነዘቡ ዘንድ ይገሥጻችኋል::"},{"id":91,"translation":"91. (ሙስሊሞች ሆይ!) ቃል ኪዳን በገባችሁ ጊዜ በአላህ ቃል ኪዳን ሙሉ:: መሓሎቻችሁንም ከአጠነከራችኋት በኋላና አላህን በእናንተ ላይ መስካሪ ያደረጋችሁ ስትሆኑ አታፍርሱ:: አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃልና::"},{"id":92,"translation":"92. ቃል ኪዳናችሁን በማፍረስ አንዲቱ ሕዝብ ከሌላይቱ ሕዝብ የበዛች ለመሆንዋ በመካከላችሁ መሓሎቻችሁን ለክዳት መግቢያ አድርጋችሁ የምትይዙ ስትሆኑ እንደዚያች ፈትሏን ከጠነከረ በኋላ ትርትሮች አድርጋ እንዳፈረሰችው ሴት አትሁኑ:: አላህ በእርሱ ይሞክራችኋል፤ በትንሣኤ ቀንም ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር በእርግጥ ያብራራላችኋል::"},{"id":93,"translation":"93. አላህ በፈለገ ኖሮ አንዲት ሕዝብ ባደረጋችሁ ነበር:: ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያጠማል:: የሚሻውን ሰው ያቀናል:: ትሠሩት ከነበራችሁት ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ::"},{"id":94,"translation":"94. ጫማዎች ከተደላደሉ በኋላ እንዳያንዳልጡ ከአላህ መንገድ በመከልከላችሁ ምክንያት ቅጣትንም እንዳትቀምሱ መሓሎቻችሁን በመካከላችሁ ለክዳት መግቢያ አታድርጉት:: ለእናንተም ያን ጊዜ ታላቅ ቅጣት አላችሁ::"},{"id":95,"translation":"95. በአላህ ቃል ኪዳን ጥቂትን ዋጋ አትግዙ። የምታውቁ ብትሆኑ አላህ ዘንድ ያለው ምንዳ እርሱ ለእናንተ በላጭ ነውና::"},{"id":96,"translation":"96. እናንተ ዘንድ ያለው ሁሉ ያልቃል:: አላህ ዘንድ ያለው ግን ለዘለዓለም ቀሪ ነው (አያልቅም):: እነዚያንም የታገሡትን ይሠሩት በነበሩት በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን::"},{"id":97,"translation":"97. ከወንድም ይሁን ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሠራ ሁሉ መልካም ኑሮን እናኖረዋለን:: ይሠሩት ከነበሩት ነገር በመልካሙም ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን::"},{"id":98,"translation":"98. ቁርኣንንም ለማንበብ ባሰብክ ጊዜ እርጉም ከሆነው ሰይጣን በአላህ ተጠበቅ::"},{"id":99,"translation":"99. እርሱ በእነዚያ በትክክል ባመኑትና በጌታቸው ላይ በሚጠጉት ላይ ለእርሱ ሥልጣን የለዉምና::"},{"id":100,"translation":"100. ሥልጣኑ በእነዚያ በሚታዘዙት ላይና በእነዚያም እነርሱ በእርሱ ምክንያት አጋሪዎች በሆኑት ላይ ብቻ ነው::"},{"id":101,"translation":"101. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአንቀጽም ስፍራ ሌላ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ነገር አዋቂ ነው:: «አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም።» ይላሉ:: በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም::"},{"id":102,"translation":"102. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ያመኑትን ሰዎች ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር ቁርኣንን ጂብሪል እውነተኛ ሲሆን ከጌታህ አወረደው።» በላቸው::"},{"id":103,"translation":"103. እነርሱም «እርሱን ቁርኣንን የሚያስተምረው ሰው ብቻ ነው።» ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን:: የዚያ ወደ እርሱ የሚያስጠጉበት ሰው ቋንቋ ዐረበኛ ያልሆነ ዐጀምኛ ነው:: ይህ ቁርኣን ግን በግልጽ በዐረብኛ ቋንቋ የተነገረ ነው::"},{"id":104,"translation":"104. እነዚያን በአላህ አናቅጽ የማያምኑትን አላህ አይመራቸዉም:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":105,"translation":"105. ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አናቅጽ የማያምኑት ብቻ ናቸው:: እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው::"},{"id":106,"translation":"106. ከእምነቱ በኋላ በአላህ የካደ ሰው ብርቱ ቅጣት አለው። ልቡ በእምነት የረካ ሆኖ በክሕደት ቃል ለመናገር የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር:: ግን ልባቸውን በክሕደት የከፈቱ ሰዎች ከአላህ ቁጣ አለባቸው:: ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው::"},{"id":107,"translation":"107. ይህ ቅጣት እነርሱ ቅርቢቱን ሕይወት ከመጨረሻይቱ በመምረጣቸው ምክንያትና አላህም ከሓዲያንን ሕዝቦች የማያቀና በመሆኑ ነው::"},{"id":108,"translation":"108. እነዚያ እነርሱ በልቦቻቸው፤ በዓይኖቻቸውና በጆሮቻቸዉም ላይ አላህ ያተመባቸው ናቸው:: እነዚያም ዝንጉዎቹ እነርሱ ብቻ ናቸው::"},{"id":109,"translation":"109. እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ከሳሪዎቹ እነርሱ ለመሆናቸው ጥርጥር የለም::"},{"id":110,"translation":"110. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያም ጌታህ ለእነዚያ ከተፈተኑ በኋላ ለተሰደዱት ከዚያም ለታገሉትና ለታገሡት ሁሉ ጌታህም ከፈተናዋ በኋላ በእርግጥ መሐሪና አዛኝ ነው።"},{"id":111,"translation":"111. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስ ሁሉ ከራሷ ላይ የምትከራከር ሆና የምትመጣበትን ነፍስም ሁሉ የሠራችውን ዋጋ የምትቀበልበትን ቀን (አስታውስ):: እነርሱም ፈጹሞ አይበደሉም::"},{"id":112,"translation":"112. አላህ ጸጥተኛ የረካች ሲሳይዋ ሰፊ ሆኖ ከየስፍራው ይመጣላት የነበረችውንና ከዚያም በአላህ ጸጋዎች የካደችውን አላህም ይሠሩት በነበሩት ኃጢአት የረሀብንና የፍርሀትን ቅጣቶች ያቀመሳትን ከተማ ምሳሌ አደረገ::"},{"id":113,"translation":"113. ከእነርሱም ውስጥ የሆነ መልዕክተኛም በእርግጥ መጣላቸው:: አስተባበሉትም እነርሱም በዳዬች ሆነው ቅጣቱ ያዛቸው::"},{"id":114,"translation":"114. አላህም ከሰጣችሁ ሲሳይ የተፈቀደና ንጹሕ ሲሆን ብሉ:: የአላህንም ጸጋ እርሱን የምትገዙት ከሆናችሁ አመስግኑት::"},{"id":115,"translation":"115. በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማን ሥጋ፣ ያንንም በሚታረድ ጊዜ በእርሱ ላይ ከአላህ ስም ሌላ የተወሳበትን ብቻ ነው:: አመጸኛና ወሰን አላፊም ሳይሆን ከእነዚህ አንዱን ለመብላት የተገደደ ሰው ይፈቀድለታል:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":116,"translation":"116. (ሰዎች ሆይ) በአላህ ላይ ውሸትን ልትቀጣጥፉ ምላሶቻችሁ በሚመጥኑት ውሸት «ይህ የተፈቀደ ነው፤ ይህ ደግሞ እርም ነው» አትበሉ:: እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ክፍሎች በፍጹም አይድኑም::"},{"id":117,"translation":"117. ጥቂት መጣቀም ብቻ አለላቸው:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":118,"translation":"118. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነዚያ አይሁድ በሆኑት ሰዎች ላይ ከአሁን በፊት ባንተ ላይ የተረክነውን ነገር እርም አድርገንባቸዋል:: እኛም አልበደልናቸዉም:: ግን ራሳቸው ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበሩ::"},{"id":119,"translation":"119. ከዚያም ጌታህ ለእነዚያ በስህተት መጥፎን ለሠሩትና ከዚያም ከዚህ በኋላ ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪና አዛኝ ነው::"},{"id":120,"translation":"120. ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ፤ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ ህዝብ ነበር:: ከአጋሪዎችም አልነበረም::"},{"id":121,"translation":"121. ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ነበር:: መረጠው:: ወደ ቀጥተኛዉም መንገድ መራው::"},{"id":122,"translation":"122. በቅርቢቱም ዓለም በጎ ነገርን ሰጠነው:: እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም በእርግጥ ከመልካሞቹ ነው::"},{"id":123,"translation":"123. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያም የኢብራሂምን ሃይማኖት ቀጥተኛ ሲሆን ተከተል:: ከአጋሪዎቹም አልነበረም ማለትን ወደ አንተ አወረድን::"},{"id":124,"translation":"124. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በቅዳሜ ቀን መስራት ክልክል የተደረገው በእነዚያ በእርሱ በተለያዩበት ሰዎች ላይ ብቻ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም በትንሳኤ ቀን ይለያዩበት በነበሩት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ ይፈርዳል::"},{"id":125,"translation":"125. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ በለዘብተኛ ቃልም ሰዎችን ጥራ:: በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው ዘዴ ተከራከራቸው:: ጌታህ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው አዋቂ ነው:: እንደዚሁም እርሱ ቅን የሆኑትን ሰዎች አዋቂ ነው::"},{"id":126,"translation":"126. (ሙስሊሞች ሆይ!) ብትበቀሉም በእርሱ በተቀጣችሁበት ብጤ ተበቀሉ:: ብትታገሱ ግን እርሱ ለታጋሾች በእርግጥ በላጭ ነው::"},{"id":127,"translation":"127. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ታገስ:: መታገስህ በአላህ ማስቻል ብቻ እንጂ አይደለም:: በእነርሱም ላይ ባያምኑ አትተክዝ:: ባንተ ላይ በሚመክሩት ተንኮልም በጭንቀት ውስጥ አትሁን::"},{"id":128,"translation":"128. አላህ ከእነዚያ እነርሱ ከሚፈሩትና ከእነዚያም እነርሱ ከመልካም ሠሪ ከሆኑት ሰዎች ጋር ነው::"}]},{"id":17,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ጥራት ለዚያ ባሪያውን (ሙሐመድን) ከተከበረው የሐረም መስጊድ ወደ እዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ሩቁ (አል አቅሷ) መስጊድ በሌሊት ለወሰደው አምላክ ለአላህ ይሁን:: ይህን ያደረግን ተዓምራታችንን ልናሳየው ነው:: እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚዉና ተመልካቹ ነው::"},{"id":2,"translation":"2. ለሙሳም (ተውራት የተባለውን) መጽሐፍ ሰጠነውና ለኢስራኢል ልጆች መሪ አደረግነው:: ከእኔ ሌላ ወኪል (መጠጊያ) አድርጋችሁ ማንንም አታድርጉ“ስንልም አዘዝናቸው::"},{"id":3,"translation":"3. «ከኑህ ጋር (በመርከቧ ላይ) የጫንናቸው (አማኝ )ዝርዮች ሆይ! (አላህን ተገዙ)፤ ኑህ በእርግጥ አምላኩን በብዛት አመስጋኝ ባሪያ ነበርና» አልናቸው።"},{"id":4,"translation":"4. ለኢስራኢል ልጆችም፡ “በምድር ላይ ሁለት ጊዜ ጥፋት ትፈጽማላችሁ:: አለቅጥም አምባገነን ትሆናላችሁ::” ስንል በመጽሐፉ ውስጥ ገለጽን::"},{"id":5,"translation":"5. ከሁለቱ የመጀመሪያው ጥፋት መፈጸሚያ ወቅቱ በደረሰ ጊዜ የበረታ ኃይል ያላቸውን ባሮቻችንን በእናነተ ላይ ላክንባችሁ:: እነርሱም ቤቶችን ሁሉ በረበሩ:: ይህ መፈጸሙ የማይቀር ውሳኔ ነበር::"},{"id":6,"translation":"6. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ከዚያም በኋላ በእነርሱ ላይ የድል አድራጊነትን እድል ሰጠናችሁ:: ገንዘብንና ወንዶች ልጆችንም ለገስናችሁ:: በሰው ኃይልም ብዙ አደረግናችሁ::"},{"id":7,"translation":"7. መልካምን ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ:: መጥፎንም ብትሠሩ በነፍሶቻችሁ ላይ ነው:: የኋለኛይቱ ጥፋት ቀጠሮ በደረሰ ጊዜ ፊቶቻችሁን ሊያስከፉ፤ መስጊዱንም በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡቡት ሊገቡ፤ ያሸነፉትንም ሁሉ ፈጽመው ማጥፋትን እንዲያጠፉ እንልካቸዋለን::"},{"id":8,"translation":"8. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ! በመጽሐፉም አልን ብትጸጸቱ) «ጌታችሁ ሊያዝንላችሁ ይከጀላል:: ወደ ማጥፋት እንደገና ብትመለሱም እኛም ወደ ቅጣቱ እንመለሳለን:: ገሀነምንም ለከሓዲያን ሁሉ ማሰሪያ አድርገናል።»"},{"id":9,"translation":"9. ይህ ቁርኣን ወደዚያች በሁሉ ነገር ቀጥተኛ ወደ ሆነችው መንገድ ይመራል:: እነዚያንም በጎ የሚሠሩትንም አማኞች ለእነርሱ ታላቅ ምንዳ ያላቸው መሆኑን ያበስራል::"},{"id":10,"translation":"10. እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅተንላቸዋል::"},{"id":11,"translation":"11. ሰው መልካምን ነገር እንደሚለምን ሁሉ መጥፎንም ነገር ይለምናል:: ሰዉም ቸኳይ ነውና::"},{"id":12,"translation":"12. ሌሊትንና ቀንን ለችሎታችን ምልክቶች አደረግን:: የሌሊትን ምልክትም አበስን:: የቀንን ምልክትም የምታሳይ አደረግን:: ይህም የሆነበት ከአላህ ትርፍን ልትፈልጉበትና የዓመታትንም ቁጥርና ሒሳብን ታውቁበት ዘንድ ነው:: ነገሩንም ሁሉ ለያይተን ዘረዘርነው::"},{"id":13,"translation":"13. ሰውን ሁሉ በራሪውን (ሥራውን) በአንገቱ ላይ አስያዝነው:: ለእርሱም በትንሣኤ ቀን የተዘረጋ ሆኖ የሚያገኘው የሆነን መጽሐፍ እናወጣለታለን::"},{"id":14,"translation":"14. (ከዚያም) «መጽሐፍህን አንብብ:: ዛሬ ባንተ ላይ ተቆጣጣሪነት በነፍስህ ብቻ በቃ።» ይባላል።"},{"id":15,"translation":"15. በቀናው መንገድ የተመራ ሁሉ የሚመራው ለእራሱ ብቻ ነው:: ከቀናው መንገድ የተሳሳተም የመሳሳቱ ጉዳት በእርሱ ላይ ብቻ ነው:: ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም:: መልዕክተኛንም እስከምንልክ ድረስ ማንንም የምንቀጣ አይደለንም።"},{"id":16,"translation":"16. ማንኛዋንም ከተማ ለማጥፋት በፈለግን ጊዜ ባለ ጸጋዎችዋን እናዛቸዋለን:: በውስጧም ያምፃሉ:: በእርሷም ላይ የቅጣት ቃሉ ይፈጸምባታል:: ከዚያም ማውደምን እናወድማታለን::"},{"id":17,"translation":"17. ከኑሕም በኋላ ከየክፍለ ዘመናት ሰዎች ያጠፋናቸው ብዙዎች ናቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የባሮቹንም ኃጢአቶች ውስጠ አዋቂ ተመልካች መሆን በጌታህ ብቻ በቃ::"},{"id":18,"translation":"18. ጊዜያዊቱን ዓለም (በሥራው) የሚፈልግ ሁሉ ለእርሱ ከእርሷ ውስጥ የፈለግነውን ጸጋ ብቻ ለምንፈልገውም ብቻ እናስቸኩልለታለን:: ከዚያም ለእርሱ ገሀነምን መኖሪያ አድርገንለታል:: ተወቃሽና ከአላህ እዝነት የተባረረ ሆኖ ይገባባታል።"},{"id":19,"translation":"19. የመጨረሻይቱን ዓለም የፈለገ እና እርሱ አማኝ ሆኖ ለእርሷ ተገቢ የሆነን ሥራ የሠራ ደግሞ እነዚህ ሥራቸው የተመሰገነ ይሆናል::"},{"id":20,"translation":"20. ሁሉንም እነዚህንም እነዚያንም ከጌታህ ስጦታ በዚህ ዓለም እንጨምርላቸዋለን:: የጌታህም ስጦታ በዚች ዓለም ክልክል አይደለም::"},{"id":21,"translation":"21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ እንዴት እንዳስበለጥን ተመልከት:: የመጨረሻይቱም ሀገር በማዕረጎች በጣም የከበረችና በመብለጥም የላቀች ናት::"},{"id":22,"translation":"22. (የሰው ልጅ ሆይ!) ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ አታድርግ:: የተወቀስክ፤ ረዳት የሌለህ ትሆናለህና::"},{"id":23,"translation":"23. (የሰው ልጅ ሆይ!) ጌታህ እንዲህ ሲል አዘዘ:: እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ ለወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፤ ባንተ ዘንድ ሆነው ከወላጆችህ አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ «ኡፍ!» እንኳን አትበላቸው:: አትገላምጣቸዉም:: ለእነርሱም መልካምን ቃል ብቻ ተናገራቸው::"},{"id":24,"translation":"24. (ልጅ ሆይ!) ለሁለቱም የመተናነስ ክንፍን ዝቅ አድርግላቸው። «ጌታዬ ሆይ! በሕጻንነቴ በርህራሄ እንዳሳደጉኝ ሁሉ ለእነርሱም እዘንላቸው።» በልም።"},{"id":25,"translation":"25. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ ይበልጥ አዋቂ ነው:: ታዛዦችም ብትሆኑ ወይም ብታጠፉ እርሱ ለተመላሾች ሁሉ መሓሪ ነው::"},{"id":26,"translation":"26. (የሰው ልጅ ሆይ!) ለዝምድና ባለቤት ሁሉ ተገቢ መብቱን ስጥ:: ለምስኪንና ለመንገደኛም እንዲሁ መብቱን ስጥ:: (በሁሉም ነገር ላይ) ማባከንንም አታባክን::"},{"id":27,"translation":"27. አባካኞች የሰይጣናት ወንድሞች ናቸውና:: ሰይጣንም ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው::"},{"id":28,"translation":"28. ከጌታህም የምትከጅላትን ጸጋ ለማምጣት በማሰብ ከእነርሱ ብትዞር ለእነርሱ ልዝብን ቃል ተናገራቸው::"},{"id":29,"translation":"29. እጅህን ወደ አንገትህ ታጥፋ የታሠረች አታድርግ:: መዘርጋትንም ሁሉ አትዘርጋት:: የተወቀስክና የተቆጨህ ትሆናለህና::"},{"id":30,"translation":"30. ጌታህ ሲሳይን ለሚፈልገው ሁሉ ያሰፋል። ለሚፈልገውም ያጠባል። እርሱ በባሮቹ ሁኔታ ውስጠ አዋቂና ተመልካች ነውና።"},{"id":31,"translation":"31. (ሰዎች ሆይ!) ልጆቻችሁንም ድህነትን በመፍራት አትግደሉ:: እኛ እንመግባቸዋለን:: እናንተንም እንመግባችኃለን:: እነርሱን መግደል ታላቅ ኃጢአት ነውና::"},{"id":32,"translation":"32. (ሰዎች ሆይ!) ዝሙትንም አትቅረቡ:: እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና:: መንገድነቱም ከፋ!"},{"id":33,"translation":"33. (ሰዎች ሆይ!) ያቺንም አላህ ያከበራትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ:: የተበደለ ሆኖ ለተገደለም ሰው ዘመዱ በገዳዩ ላይ ስልጣንን አድርገንለታል:: በመግደል ወሰንን አይለፍ:: እርሱ እገዛ ያለው ነውና::"},{"id":34,"translation":"34. (ሰዎች ሆይ!) የየቲምንም ገንዘብ የብርታቱን ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በሆነች ሁኔታ እንጂ አትቅረቡ:: በቃል ኪዳናችሁም ሙሉ:: ቃል ኪዳን የሚጠየቁበት ጉዳይ ነውና::"},{"id":35,"translation":"35. (ሰዎች ሆይ!) በሰፈራችሁም ጊዜ ስፍርን ሙሉ:: በትክክለኛው ሚዛንም መዝኑ:: ይህ መልካም ነገር ነው:: መጨረሻዉም ያማረ ነው::"},{"id":36,"translation":"36. (የሰው ልጅ ሆይ!) ላንተ በእርሱ እውቀት የሌለህንም ነገር አትከተል:: መስሚያ፤ ማያ፤ ማሰቢያም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና::"},{"id":37,"translation":"37. (የሰው ልጅ ሆይ!) በምድር ላይ የተንበጣረርክ ሆነህም አትሂድ:: አንተ ፈጽሞ ምድርን አትሰረጉድምና:: በርዝመትም ፈጽሞ ጋራዎችን አትደርስምና::"},{"id":38,"translation":"38. (የሰው ልጅ ሆይ!) ይህ ሁሉ ክፋቱ ከጌታህ ዘንድ የተጠላ ነው።"},{"id":39,"translation":"39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ጌታህ ከጥበብ ወደ አንተ ካወረደው ነገር ነው:: ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ አታድርግ:: የተወቀስክ፤ የተባረርክ ሆነህ በገሀነም ውስጥ ትጣላለህና::"},{"id":40,"translation":"40. (ጣኦታዊያን ሆይ!) ጌታችሁ በወንዶች ልጆች መረጣችሁና ከመላዕክት ሴቶችን ልጆች ለራሱ ያዘን? እናንተ ከባድ ቃልን በእርግጥ ትናገራላችሁ::"},{"id":41,"translation":"41. ይገሰጹ ዘንድ በዚህ ቁርኣን ውስጥ ደጋግመን በእርግጥ ገለጽን:: ለእነርሱ ግን ከትክክለኛው መንገድ መበርገግን እንጂ ሌላን አይጨምርላቸዉም::"},{"id":42,"translation":"42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነርሱ እንደሚሉት ከእርሱ ጋር ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ ያን ጊዜ ወደ ዐርሹ ባለቤት መንገድን በፈለጉ ነበር።» በላቸው።"},{"id":43,"translation":"43. ጥራት ይገባው:: አላህ እነርሱ ከሚሉት ነገር ሁሉ ከፍ ያለን ልቅና ላቀ::"},{"id":44,"translation":"44. ሰባቱ ሰማያትና ምድር እንዲሁም በውስጣቸውም ያለው ሁሉ እርሱን ያጠራሉ:: ከነገሩ ሁሉ እሱን ከማመስገን ጋር የሚያጠራው እንጂ አንድም የለም:: ማጥራታቸውን ግን አታውቁትም:: እርሱ ታጋሽና መሓሪ ነው::"},{"id":45,"translation":"45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንን ባነበብክ ጊዜ ባንተና በእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም በማያምኑት ሰዎች መካከል የሚሸሸግን ግርዶሽ አድርገናል::"},{"id":46,"translation":"46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዳያውቁትም በልቦቻቸው ላይ ሽፋንን፤ በጆሮቻቸዉም ውስጥ ድንቁርናን አደረግን:: ጌታህንም ብቻውን ሆኖ በቁርኣን ባወሳሀው ጊዜ የሚሸሹ ሆነው በጀርባዎቻቸዉ ላይ ይዞራሉ::"},{"id":47,"translation":"47. እኛ ወደ አንተ በሚያዳምጡ፤ በሚንሾካሸኩ፤ በዳዮችም እርስ በእርሳቸው «የተደገመበትን ሰው እንጂ አትከተሉም።» በሚሉ ጊዜ የሚያዳምጡበትን ምክንያት አዋቂ ነን።"},{"id":48,"translation":"48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ላንተ ምሳሌዎችን እንዴት እንዳደረጉልህና ከዚያም እንዴት እንደ ተሳሳቱ ተመልከት:: ወደ እውነቱ ለመድረስ ትክክለኛውን መንገድ መከተል አይችሉም።"},{"id":49,"translation":"49. አሉም፡- «አጥንቶችና ብስብሶች በሆን ጊዜ እኛ እንዴት እንደገና አዲስ ፍጥረት ሆነን በእርግጥ ተቀስቃሾች እንሆናለን?»"},{"id":50,"translation":"50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በላቸው: «ድንጋዮች ወይም ብረትም ሁኑ፤"},{"id":51,"translation":"51. ወይም በልቦቻቸሁ ውስጥ የሚተልቅን ፍጥረትም ሁኑ (መቀስቀሳችሁ አይቀርም።)» «የሚመልሰንም ማነው?» ይላሉም። «ያ በመጀመሪያ ጊዜ የፈጠራችሁ ነው።» በላቸው:: ወደ አንተም ራሶቻቸውን ይነቀንቃሉ። «እርሱም መቼ ነው?» ይላሉም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በላቸው: «እርሱ በቅርብ ቀን ሊሆን ይችላል።"},{"id":52,"translation":"52. «እርሱም የሚጠራችሁንና አላህን አመስጋኞቹ ሆናችሁ ጥሪውን የምትቀበሉበት፤ ጥቂትን ቀናት እንጂ ያልቆያችሁ መሆናችሁን የምትጠራጠሩበት ቀን ነው።» በላቸው::"},{"id":53,"translation":"53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለባሮቼም ንገራቸው:: መልካም የሆነችውን ቃል ብቻ ይናገሩ:: ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና:: ሰይጣን ለሰው ልጆች ግልጽ ጠላት ነውና::"},{"id":54,"translation":"54. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁ በእናንተ ሁኔታ አዋቂ ነው:: ቢፈልግ ያዝንላችኋል፤ ቢፈልግም ይቀጣችኃል። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱ ላይ ሀላፊ ሆነህ አላክንህም:: አታስገድዳቸዉም::"},{"id":55,"translation":"55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ አዋቂ ነው:: ከፊሉን ነብያት በከፊሉ ላይ አብልጠናል:: ዳውድንም ዘቡርን ሰጥተነዋል::"},{"id":56,"translation":"56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በለቸው (ጣዖታዊያን ሆይ!) « እነዚያን ከእርሱ ሌላ አማልዕክት የምትሏቸውን እስቲ ጥሯቸው:: ከናንተም ላይ ጉዳትን ማስወገድን ወደ ሌላ ማዞርንም አይችሉም።»።"},{"id":57,"translation":"57. እነዚያ እነርሱ የሚገዟቸው ማንኛቸዉም (ወደ አላህ) በጣም ቀራቢያቸው እንኳን ለራሳቸው ወደ ጌታቸው መቃረቢያን ሥራ ይፈልጋሉ:: እዝነቱንም ይከጅላሉ:: ቅጣቱንም ይፈራሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ ቅጣት የሚፈራ ነውና::"},{"id":58,"translation":"58. አንዲትም ከተማ የለችም እኛ ከትንሳኤ ቀን በፊት አጥፊዎችዋ ወይም ብርቱን ቅጣት ቀጭዎችዋ ብንሆን እንጂ:: ይህም በመጽሐፍ የተጻፈ ነው::"},{"id":59,"translation":"59. ተዓምራትን ከመላክ የቀድሞዎቹ ሰዎች በእርሷ ማስተባበልና መጥፋት እንጂ ሌላ አልከለከለንም። ለሠሙድም ግመልን ግልጽ ተዓምር ሆና ሰጠናቸው:: በእርሷም በደሉ፤ ተዓምራትንም ለማስፈራራት እንጂ አንልክም::"},{"id":60,"translation":"60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ላንተም ጌታህ በእውቀቱ ሰዎችን ያካበበ መሆኑን በነገርንህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: በሌሊቱ ጉዞ በዓይንህ ያሳየንህም ትርኢት ለሰዎች ፈተና እንጂ አላደረግነዉም:: በቁርኣንም የተረገመችውን ዛፍ እንደዚሁ ፈተና እንጂ አላደረግንም፤ እናስፈራራቸዋለንም፤ ትልቅንም ጥመት እንጂ አይጨምርላቸዉም::"},{"id":61,"translation":"61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመላዕክትም «ለአደም ስገዱ» ባልናቸው ጊዜ የነበረውን ሁኔታ አስታውስ:: ወዲያዉም ሰገዱ ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር «ከጭቃ ለፈጠርከው ሰው እሰግዳለሁን?» አለ።"},{"id":62,"translation":"62. «እስቲ ንገረኝ ይህ ያ በእኔ ላይ ያበለጥከው ነውን? እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ብታቆየኝ ዘሮቹን ጥቂቶች ሲቀሩ ወደ ስህተት በእርግጥ እስባቸዋለሁ።» አለ።"},{"id":63,"translation":"63. አላህም አለው: «ሂድ ከእነርሱም የተከተለህ ገሀነም የተሟላች ቅጣት ስትሆን ፍዳችሁ ናት።"},{"id":64,"translation":"64. «ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ ገፋፋ:: በእነርሱም ላይ በፈረሰኞችህ በእግረኞችህም ሆነህ ለልብ (አውጅ)። በገንዘቦቻቸዉም በልጆቻቸዉም ተጋራቸው:: የተስፋ ቃልም ግባላቸው።» ሰይጣንም ማታለልን እንጂ ተስፋ ቃልን አይገባላቸዉም::"},{"id":65,"translation":"65. ንጹህ ባሮቼ ግን በእነርሱ ላይ ፈጽሞ ላንተ ስልጣን የለህም:: ዋስም በጌታህ በቃ።"},{"id":66,"translation":"66. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁ ያ ከችሮታው ትፈልጉ ዘንድ መርከቦችን በባህር ላይ ለእናንተ የሚነዳላችሁ ነው:: እነሆ እርሱ ለእናንተ አዛኝ ነውና::"},{"id":67,"translation":"67. በባህሩ ውስጥ ሆናችሁ ጉዳት በደረሰባችሁ ጊዜ የምትጠሯቸው አማልክት ሁሉ ይጠፉባችሁና እርሱ አላህ ብቻ ይቀራል። ወደ የብስም በማድረስ ባዳናችሁ ጊዜ እምነትን ትተዋላችሁ:: ሰው ሲባል በጣም ከሓዲ ነውና::"},{"id":68,"translation":"68. (ሰዎች ሆይ!) የየብሱን በኩል ምድርን በናንተ መገልበጡን ወይም ጠጠርን የያዘ ንፋስን በእናንተ ላይ መላኩን ከዚያም ለእናንተ ጠባቂ አለማግኘታችሁን አትፈሩምን?"},{"id":69,"translation":"69. ወይስ ሌላ ጊዜ ወደ እርሱ (ወደ ባህር) የሚመልሳችሁ ወዲያውኑም በእናንተ ላይ ብርቱን ነፋስ የሚልክ፤ በክህደታችሁም ምክንያት የሚያሰምጣችሁ መሆኑን ከዚያም በእኛ ላይ በእርሱ ተከታይነት (ረዳትን) ለእናንተ የማታገኙ መሆናቸሁን አትፈሩምን?"},{"id":70,"translation":"70. የአደምን ልጆች በእርግጥ ከሌላው ፍጡር አከበርናቸው:: በየብስና በባህርም አሳፈርናቸው:: ከመልካሞችም ሲሳዮችም ሰጠናቸው፤ ከፈጠርናቸው ፍጡራንም በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው::"},{"id":71,"translation":"71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰዎችን ሁሉ በመሪያቸው የምንጠራበትን ቀን አስታውስ። ያ መጽሐፉንም በቀኙ የተሰጠ ሰው እነዚያ መጽሐፋቸውን ያነባሉ፤ በተምር ፍሬ ስንጥቅ ላይ ያለውን ክር ያክል እንኳን አይበደሉም::"},{"id":72,"translation":"72. በዚህች ዓለም ልበ እውር የሆነ ሰው ሁሉ እርሱ በመጨረሻይቱም ዓለም እውር ነው:: መንገድንም በጣም የተሳሳተ ነው::"},{"id":73,"translation":"73. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነሆ ከዚያም ወደ አንተ ካወረድነው ሌላን በእኛ ላይ ትዋሽ ዘንድ ሊፈትኑህ በእርግጥ ተቃረቡ፤ ያን ጊዜም ወዳጅ አድርገው በያዙህ ነበር::"},{"id":74,"translation":"74.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባላረጋጋንህም ኖሮ ወደ እነርሱ ጥቂትን ዝንባሌ ልትዘነበል በእርግጥ በተቃረብክ ነበር::"},{"id":75,"translation":"75. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያን ጊዜ የሕይወትን ሆነ የሞትን ድርብ ቅጣት እናቀምስህ ነበር:: ከዚያም ላንተ በእኛ ላይ ረዳትን አታገኝም ነበር::"},{"id":76,"translation":"76. ከምድሪቱ (ከዓረብ) ምድር ከእርሷ ያወጡህ ዘንድ ሊያሸብሩህ በእርግጥ ተቃረቡ:: ያን ጊዜም ካንተ በኋላ ጥቂትን ጊዜ እንጂ አይቆዩም ነበር::"},{"id":77,"translation":"77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞቻችን ካንተ በፊት በእርግጥ እንደ ላክናቸው ሰዎች ልማድ ብጤ ይጠፋ ነበር፤ ለልማዳችንም መለወጥን አታገኝም (አይለወጥም)።"},{"id":78,"translation":"78. ሶላትን ከጸሐይ መዘንበል እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ:: የጎህንም ሶላት ስገድ:: የጎህ ሶላት መላዕክት የሚገኙበት ነውና::"},{"id":79,"translation":"79. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሌሊት ላንተ ተጨማሪ የሆነችን ሶላት በቁርኣን ስገድ:: ጌታህ ምስጉን በሆነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃልና::"},{"id":80,"translation":"80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በልም: «ጌታዬ ሆይ! የተወደደን መግባት አስገባኝ፤ የተወደደንም መውጣት አስወጣኝ:: ለእኔም ካንተ ዘንድ የተረዳን ስልጣን አድርግልኝ።»"},{"id":81,"translation":"81. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና።» በል።"},{"id":82,"translation":"82. ከቁርኣን ለአማኞች መድሓኒትና እዝነት የሆነን እናወርዳለን በዳዮችንም ኪሳራን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸዉም::"},{"id":83,"translation":"83. በሰዉም ላይ ጸጋችንን በለገስን ጊዜ ከምስጋና ይዞራል ጎኑንም ከእውነት ያርቃል:: ችግርም በነካው ጊዜ ተስፋ ቆራጭ ይሆናል::"},{"id":84,"translation":"84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁሉም በሚመስለው መንገድ ላይ ይሠራል:: ጌታችሁም እርሱ መንገዱ ቀጥተኛ የሆነውን አዋቂ ነው።» በላቸው።"},{"id":85,"translation":"85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን ከሩህ ይጠይቁሃል። «ሩህ ከጌታዬ ነገር ነው:: ከእውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም።» በላቸው::"},{"id":86,"translation":"86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብንሻ ያንን ወደ አንተ ያወረድነውን በእርግጥ እንወስድብሃለን:: ከዚያም ላንተ በእኛ ላይ በእርሱ ለማስመለስ ተያዢን አታገኝም::"},{"id":87,"translation":"87. ግን ከጌታህ በሆነው እዝነት ጠበቅነው:: ችሮታው ባንተ ላይ ታላቅ ነውና::"},{"id":88,"translation":"88. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎችና ጋኔኖች የዚህን ቁርኣን ቢጤ በማምጣት ላይ ቢሰበሰቡና ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳት ቢሆኑም እንኳ ብጤውን አያመጡም።» በላቸው።"},{"id":89,"translation":"89. በዚህም ቁርኣን ውስጥ ከምሳሌው ሁሉ ለሰዎች በእርግጥ መላልሰን አብራራን:: አብዛኞቹም ሰዎች ክህደትን እንጂ ሌላን እምቢ አሉ::"},{"id":90,"translation":"90. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አሉም: «ለእኛ ከምድር ምንጭን እስከምታፈልቅልን ድረስ ላንተ አናምንም።"},{"id":91,"translation":"91. «ወይም ከዘንባባዎችና ከወይን የሆነች አትክልት ላንተ እስከምትኖርህና በመካከሏም ጅረቶችን በብዛት እስከምታንቧቧ ድረስ"},{"id":92,"translation":"92. «ወይም እንደምትለው ከሰማይ ቁራጮችን በእኛ ላይ እስከምታወርድ ወይም አላህንና መላዕክትን በግልጽ እስከምታመጣ ድረስ"},{"id":93,"translation":"93 «ወይም ከወርቅ የሆነ ቤት ላንተ እስከሚኖርህ ወይም በሰማይ እስከምትወጣ፤ ለመውጣትህም በእኛ ላይ የምናነበው የሆነን መጽሐፍ እስከምታወርድልን ድረስ ፈጽሞ አናምንልህም።» አሉ:: «ጌታዬ ጥራት ይገባው:: እኔ መልዕክተኛ (የሆንኩ) ሰው እንጂ ሌላ ነገር ነኝ እንዴ?!» በላቸው::"},{"id":94,"translation":"94. ሰዎችን መሪ ቁርኣን በመጣላቸው ጊዜ በሱ ከማመን «አላህ ሰውን መልዕክተኛ አድርጎ ላከን?» ማለታቸው ብቻ እንጂ ሌላ አልከለከላቸዉም።"},{"id":95,"translation":"95. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በምድር ላይ ተረጋግተው የሚጓዙ መላእክት ቢኖሩ ኑሮ ከሰማይ የመልአክ መልዕክተኛ እናወርድላቸው እንደነበር ንገራቸው።"},{"id":96,"translation":"96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእኔና በእናንተ መካከል ላለን ልዩነት መስካሪ በአላህ በቃ:: ምክኒያቱም እርሱ ባሮቹን ጠንቅቆ አዋቂና ተመልካች ነውና።» በላቸው።"},{"id":97,"translation":"97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያቀናው በእርግጥም የተቀና ማለት እርሱው ነው:: እርሱ ያጠመማቸውን ግን ከቅጣቱ የሚያድናቸው ማንም ወዳጅ አታገኝላቸዉም:: የትንሳኤ ቀንም እውር፤ ዲዳና፤ ደንቆሮ አድርገን በፊቶቻቸው እየተጎተቱ እንሰበስባቸዋለን:: መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት:: ሀይሏ በደከመ ጊዜም ግለትን እንጨምርላቸዋለን::"},{"id":98,"translation":"98. ይህ ቅጣት የሚጠብቃቸው ቅጣታቸው ነው:: ምክንያቱም በመልዕክተኞቻችን ክደው «የበሰበሰ አጥንት ከሆንና (ወደ አቧራነት) ከተቀየርን በኋላ እንደ አዲስ እንቀሰቀሳለን?» በማለታቸውም ነው።"},{"id":99,"translation":"99. ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ አላህ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ መሆኑን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበትንም ጊዜ ለሞትም ለትንሳኤም ለእነርሱ የወሰነ መሆኑን አላወቁምን? በደለኞችም ከክህደት በስተቀር እምቢ አሉ::"},{"id":100,"translation":"100. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የጌታዬን የችሮታ መካዚኖች ብትይዙ ኖሮ ያን ጊዜ በማውጣታችሁ ማለቋን በመፍራት በጨበጣችሁ ነበር:: ሰው በጣም ንፉግ ነውና።» በላቸው።"},{"id":101,"translation":"101. ለሙሳ ግልጽ የሆኑን ዘጠኝ ተዓምራት በእርግጥ ሰጠነው:: በመጣቸዉም ጊዜ የኢስራኢልን ልጆች ከፈርዖን እንዲለቀቁ ጠይቅ አልነው:: ፈርዖንም፡- «ሙሳ ሆይ! እኔ የተደገመብህ መሆንህን በእርግጥ እጠረጥርሃለሁ።» አለው።"},{"id":102,"translation":"102. ሙሳም፡- «እነዚህን ተዓምራት መግሰጫዎች ሲሆኑ የሰማያትና የምድር ጌታ እንጂ ሌላ እንዳላወረዳቸው በእርግጥ አውቀሀል:: እኔም ፈርዖን ሆይ! የምትጠፋ መሆንህን በእርግጥ እጠረጥርሃለሁ።» አለው።"},{"id":103,"translation":"103. ከምድርም ሊያባርራቸው አሰበ:: እርሱንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ሁሉንም አሰመጥናቸው::"},{"id":104,"translation":"104. ከእርሱም በኋላ ለኢስራኢል ልጆች «ምድሪቱን ተቀመጡባት:: የኋለኛይቱም ሰዓት ቀጠሮ በመጣ ጊዜ እናንተን የተከማቻችሁ ስትሆኑ እናመጣችኋለን።» አልናቸው።"},{"id":105,"translation":"105. ቁርኣንን በእውነትም አወረድነው:: በእውነትም ወረደ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተንም አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን እንጂ አልላክንህም::"},{"id":106,"translation":"106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንንም በሰዎች ላይ ሁነህ በዝግታ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው:: ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው::"},{"id":107,"translation":"107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርሱ እመኑ ወይም አትመኑ።» በላቸው:: እነዚያ ከእርሱ በፊት እውቀትን የተሰጡት በእነርሱ ላይ በተነበበ ጊዜ ሰጋጆች ሆነው በሸንጎበቶቻቸው ላይ ይወድቃሉ::"},{"id":108,"translation":"108. ይላሉም: «ጌታችን ጥራት ይገባው። እነሆ የጌታችን ተስፋ ተፈጻሚ ነው።» ይላሉ።"},{"id":109,"translation":"109. እያለቀሱም በአሸንጎበቶቻቸው (በአገጮቻቸው) ላይ ይወድቃሉ:: አላህም ፍርሃትን ይጨምርላቸዋል::{1}","footnotes":"{1} አዚህ የንባብ ሱጁድ (ሱጁድትላዋ) ይደረጋል።"},{"id":110,"translation":"110. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህን ጥሩ ወይም አር-ረህማንን ጥሩ:: ማንኛውንም ስም ብትጠሩ መልካም ነው:: ለእርሱ ብዙ መልካም ስሞች አሉትና።» በላቸው። በስግደትህም ስታነብ በጣም ድምጽህን አትጩህ:: በእርሷም በጣም ድምጽህን ዝቅ አታድርግ:: በሁለቱ መካከል የሆነ መንገድን ፈልግ::"},{"id":111,"translation":"111. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ምስጋና ሁሉ ለዚያ ልጅን ላልያዘው ለእርሱም በንግስናው ተጋሪ ለሌለው ለእርሱም ከውርደት የሚያድነው ወዳጅ ለሌለው ለአላህ ብቻ ይገባው።» በል። እርሱን ማክበርንም አክብረው።"}]},{"id":18,"verses":[{"id":1,"translation":"1-ምስጋና ሁሉ ለዚያ መጽሐፉን በውስጡ ቅንጣት መጣመምን ሳያደርግ በባሪያው (በሙሐመድ) ላይ ላወረደው ለአላህ ብቻ ይገባው::"},{"id":2,"translation":"2. ቀጥተኛ ሲሆን ከርሱ ዘንድ የሆነን ብርቱን ቅጣት ሊያስፈራራበት፤ እነዚያንም በጎ ሰሪዎችን ለእነርሱ መልካም ምንዳ ያላቸው መሆኑን ሊያበስርበት (አወረደው)።"},{"id":3,"translation":"3. በውስጡም ዘለዓለም የሚቆዩ መሆናቸውን ሊያበስርበት አወረደው።"},{"id":4,"translation":"4. እነዚያንም «አላህ ልጅን ይዟል።» ያሉትን ሊያስፈራራበት (ቁርኣንን አወረደው።)"},{"id":5,"translation":"5.ለእነርሱም ሆነ ለአባቶቻቸው ስለ አላህ ልጅ መኖር ምንም እውቀት የላቸዉም:: ከአፎቻቸው የሚወጣው ቃል ምን አከበደው! ውሸትን እንጂ ሌላን አይናገሩም::"},{"id":6,"translation":"6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚህም ንግግር በቁርኣን ካላመኑ በፈለጎቻቸው ላይ በቁጭት ነፍስህን አጥፊ ልትሆን ይፈራልሀል::"},{"id":7,"translation":"7.እኛ ማንኛቸው ሥራው ያማረ መሆኑን ልንፈትናቸው በምድር ላይ ያለን ሁሉ የእርሷ ጌጥ አደረግን::"},{"id":8,"translation":"8. እኛ በእርሷ ላይ ያለውን ሁሉ በመጨረሻ ቡቃያ የሌለበት ምልጥ አፈር አድራጊዎች ነን::"},{"id":9,"translation":"9-(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዋሻውና የሰሌዳው ባለቤቶች ከተዓምራታችን ሲሆኑ ግሩም መሆናቸውን አሰብክን?"},{"id":10,"translation":"10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወጣቶቹ ወደ ዋሻው በተጠጉና: «ጌታችን ሆይ! ካንተ ዘንድ እዝነትን ስጠን:: ለእኛም ከነገራችን ቅንን ነገር አዘጋጅልን።» ባሉ ጊዜ (የሆነውን ታሪክ አስታውስ።)"},{"id":11,"translation":"11. በዋሻዉም ውስጥ የተቆጠሩን ዓመታት በጆሮዎቻቸው ላይ መታንባቸው (አስተኛናቸው)::"},{"id":12,"translation":"12.ከዚያም ከሁለቱ ክፍሎች ለቆዩት ጊዜ ልክ ያረጋገጠው ማንኛው መሆኑን ልናውቅ ከተኙበት አስነሳናቸው::"},{"id":13,"translation":"13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ወሬያቸውን ባንተ ላይ በእውነት እንተርክልሃለን:: እነርሱ በጌታቸው በትክክል ያመኑ ወጣቶች ናቸው:: ወደ ቀናው መንገድ መመራትንም ጨመርንላቸው::"},{"id":14,"translation":"14. በንጉሳቸው ፊት በቆሙና እንዲህም ባሉ ጊዜ ልቦቻቸውን በእምነት አጠነከርን: «ጌታችን የሰማያትና የምድር ጌታ ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክን አንገዛም:: ከእሱ ሌላን ብናመልክማ ወሰን ያለፈን ንግግር በእርግጥ ተናገርን።"},{"id":15,"translation":"15. «እነዚህ ህዝቦቻችን ከእርሱ ሌላ አማልክትን ያዙ:: እውነተኞች ከሆኑ በእነርሱ ላይ ግልጽ ማስረጃን ለምን አያመጡም? በአላህ ላይ ውሸትን ከሚቀጣጥፍ ይበልጥ በዳይ ማን ነው?» አሉ።"},{"id":16,"translation":"16. «እነርሱንና ያንን ከአላህ ሌላ የሚገዙትን በተለያችሁ ጊዜ ወደ ዋሻው ተጠጉ። ጌታችሁ ለእናንተ ከችሮታው ይዘረጋላችኋልና፤ ከነገራችሁም ለእናንተ መጠቃቀሚያ ያዘጋጅላችኋልና።» (ተባባሉ)።"},{"id":17,"translation":"17.ጸሐይዋ በወጣች ጊዜ ከዋሻቸው ወደ ቀኝ ጎን ስታዘነብል ታያታለህ:: በገባችም ጊዜ ከሰፊው ዋሻ ውስጥ እያሉ በግራ በኩል ትተዋቸዋለች:: ይህ ከአላህ ተዓምራት አንዱ ነው:: አላህ ያቀናው በእርግጥም የተቀናው እርሱ ብቻ ነው:: እርሱ ያጠመመውን ደግሞ ቅኑን መንገድ የሚመራው ረዳት ማንንም አታገኝለትም::"},{"id":18,"translation":"18. እነርሱ በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ እያሉ የነቁ ይመስሉሃል:: ወደቀኝና ወደ ግራ ጎናቸው እናገላብጣቸዋለን:: ውሻቸዉም በዋሻቸው በር ላይ የፊት እግሩን ዘርግቷል:: ብታያቸው ኖሮ ከእነርሱ በእርግጥ የምትሸሽ ኾነህ በዞርክ ነበር:: በፍርሀትም በተሞላህ ነበር::"},{"id":19,"translation":"19. ልክ እንዳስተኛናቸውም ሁሉ በመካከላቸው እንዲጠያየቁም ቀሰቀስናቸው:: ከእነርሱ አንድ ተናጋሪ «ምን ያህል ቆያችሁ አለ?» ሌሎቹም «አንድን ቀን ወይም የቀንን ከፊል ቆየን።» አሉ። ተባባሉም: «ጌታችሁ የቆያችሁትን ጊዜ ልክ አዋቂ ነው:: ከዚህም ገንዘባችሁ ጋር አንዳችሁን ወደ ከተማይቱ ላኩ:: ከምግብ የትኛዋ ንጹህ መሆኗንም ይመልከት:: (ከንጹሑ) ምግብን ያምጣላችሁ:: ቀስም ይበል:: በእናንተም አንድንም ሰው አያሳውቅ።"},{"id":20,"translation":"20. «እነርሱ በእናንተ ላይ ቢዘልቁ ይቀጠቅጧችኋል:: ወይም ወደ ሃይማኖታቸው ይመልሷችኋል፤ ያን ጊዜም በፍጹም ፍላጎታችሁን አታገኙም።» ተባባሉ።"},{"id":21,"translation":"21. ልክ እንደዚሁም የአላህ ቀጠሮ እርግጠኛ መሆኑን ሰዓቲቱም በእርሷ ጥርጣሬ የሌለ መሆኑን ያውቁ ዘንድ በእነርሱ ላይ ሰዎችን አሳወቅን:: አማኞቹና ከሓዲያን ነገራቸውን በመካከላቸው ሲከራከሩ የሆነውን አስታውስ:: ከሓዲያን «በእነርሱ ላይ ግንብን ገንቡ።» አሉ:: ጌታቸው ለእነርሱ ይበልጥ አዋቂ ነው:: እነዚያ በነገራቸው ላይ ያሸነፉት ግን «በእነርሱ ላይ በእርግጥ መስጊድን እንሰራለን።» አሉ።"},{"id":22,"translation":"22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ስለ እነርሱ የተወሰኑ ቡድኖች በጥርጣሬ) «ሶስት ናቸው አራተኛው ውሻቸው ነው።» ይላሉ:: (ሌሎች ቡድኖች) «አምስት ናቸው ስድስተኛው ውሻቸው ነው።» ይላሉ። በሩቅ ወርዋሪዎች ሆነው (ባላወቁት አለም) ሲገምቱ። (ሶስተኛው ቡድን ደግሞ) «ሰባት ናቸው ስምንተኛቸው ውሻቸው ነዉ።» ይላሉ:: «ጌታዬ ብቻ ቁጥራቸውን አዋቂ ነው:: ጥቂት ሰው እንጂ አያውቃቸዉም።» በላቸው:: እናም በእነርሱ ነገር ግልጽን ክርክር እንጂ ጠልቀህ አትከራከር:: በእነርሱም ጉዳይ ከመጽሐፉ ሰዎች አንድንም አትጠይቅ::"},{"id":23,"translation":"23 ለማንኛዉም ነገር «እኔ ይህንን ነገ ሠሪ ነኝ።» አትበል።"},{"id":24,"translation":"24. «አላህ ቢሻ እሠራዋለሁ።» ብትል እንጂ። በረሳህ ጊዜም ጌታህን አውሳ። «ጌታዬም ከዚህ ይበልጥ ለቀጥታ የቀረበን ሊመራኝ ይከጀላል» በላቸው።"},{"id":25,"translation":"25. በዋሻቸዉም ውስጥ ሶስት መቶ ዓመታትን ቆዩ:: ዘጠኝ አመታትንም ጨመሩ::"},{"id":26,"translation":"26.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ብቻ የቆዩትን ልክ በትክክል አዋቂ ነው። የሰማያትና የምድር ሚስጢር የእሱ ብቻ ነዉ። እርሱ (አላህ) ሁሉን ተመልካች ሁሉን ሰሚ መሆኑ ይግረምህ። ለእነርሱ ከእርሱ በስተቀር ምንም ወዳጅ የላቸዉም:: በፍርዱም አንድንም አያጋራም።» በላቸው።"},{"id":27,"translation":"27.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ መጽሀፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ:: ለቃሎቹ ለዋጭ የላቸዉም:: ከርሱም በስተቀር መጠጊያን በፍጹም አታገኝም።"},{"id":28,"translation":"28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስህንም ከእነዚያ ጌታቸውን ፊቱን የሚሹ ሆነው በጥዋትና በማታ ከሚገዙት ጋር አስታግስ:: የቅርቢቱንም ህይወት ሽልማት የምትሻ ሆነህ አይኖችህ ከእነርሱ ወደ ሌላ አይለፉ:: ያ ልቡን እኛን ከማስታወስ ያዘነጋነውንና የግል ፍላጎቱን የተከተለውን ነገሩ ሁሉ ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው አትታዘዝ።"},{"id":29,"translation":"29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እውነቱ ሁሉ ከጌታችሁ ነው:: ስለዚህ የፈለገም ሰው በእውነቱ ይመን:: የፈለገም ሰው ይካድ።» በላቸው:: እኛ ለበደለኛ ከሓዲያን አጥሯ በእነርሱ ላይ የከበበ የሆነችውን እሳት አዘጋጅተናል:: ከጥም ለመዳን እርዳታን ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ ይረዳሉ:: መጠጡም ከፋ፤ መደገፊያይቱም ምንኛ አስከፋች!"},{"id":30,"translation":"30. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ እኛ ሥራ ያሳመረን ምንዳ አናጠፋም።"},{"id":31,"translation":"31.እነዚያ ለእነርሱ የመኖሪያ ገነቶች ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው አሏቸው:: በእርሷ ውስጥ ከወርቅ የሆኑን አምባሮች ይሸለማሉ:: ከቀጭን ሀርና ከወፍራም ሀርም አረንጓዴ ልብሶችን ይለብሳሉ:: በውስጧ በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ የተደገፉ ሆነው ይቀመጣሉ:: እነዚህ ሰዎች ምንዳቸው ምን ያምር! መኖሪያቸው ገነትም ምንኛ አማረች!"},{"id":32,"translation":"32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለከሓዲያን የሁለትን ሰዎችን ምሳሌ ግለጽላቸው:: ለአንደኛው ከሓዲ ሁለት የወይን አትክልቶች አደረግንለት። በዘንባባም ከበብናቸው። በመካከላቸውም አዝመራን አደረግን።"},{"id":33,"translation":"33. ሁለቱም አትክልቶች ሰብላቸውን ሰጡ፤ ከርሱም ምንም አላጎደሉም። በመካከላቸዉም ወንዝን አፈሰስን።"},{"id":34,"translation":"34.ለእርሱ ከአትክልቶቹ ሌላ ፍሬያማ ሀብት ነበረው:: ለአማኙ ጓደኛዉም የሚወዳደረው ሲሆን «እኔ ካንተ በገንዘብ ይበልጥ የበዛሁ በወገንም ይበልጥ የበረታሁ ነኝ።» አለው።"},{"id":35,"translation":"35. እርሱም ነፍሱንም በዳይ ሆኖ ወደ አትክልቱ ገባ። (እንዲህም) አለ: «ይህች አትክልት መቸም ትጠፋለች ብዬ አልጠረጥርም።"},{"id":36,"translation":"36. «ሰዓቲቱንም ትከሰታለች ብዬ አልጠረጥርም፤ እንደምትለው ወደ ጌታዬም ብመለስ ከእርሷ የበለጠን መመለሻ በእርግጥ አገኛለሁ።» አለው።"},{"id":37,"translation":"37. አማኙ ጓደኛውም ለእርሱ የሚመላለሰው ሲሆን (እንዲህ) አለው: «በዚያ ከአፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ በፈጠረህ ከዚያም ሰው ባደረገህ ሃያል አምላክ ካድክን?"},{"id":38,"translation":"38. «እኔ ግን አላህ ጌታዬ ነው እላለሁ። በጌታዬም አንድንም አላጋራም።"},{"id":39,"translation":"39. «እኔን በገንዘብም ሆነ በልጅ ካንተ በጣም ያነስኩ ሆኜ ብታየኝም ወደ አትክልትህ በገባህ ጊዜ ‹አላህ የሻው ሆኗል። በአላህ ቢሆን እንጂ ብልሃትም የለም› አትልም ኖሯልን?"},{"id":40,"translation":"40. «ጌታዬ ከአትክልትህ የበለጠን ሊሰጠኝ በአትክልትህ ላይ ደግሞ በሰማይ መብረቆችን ሊልክባትና የምታንዳልጥ ምልጥ ምድር ልትሆንም ይቻላል።"},{"id":41,"translation":"41. «ወይም ውሀው ሰራጊ ሊሆንብህ ይችላል። ያን ጊዜ እርሱን መፈለጉን ፈጽሞ አትችልም።» አለው።"},{"id":42,"translation":"42. ሀብቱም ተጠፋ:: እርሷ በዳሶችዋ ላይ የወደቀች ሆና በእርሷ ባወጣው ገንዘብ ላይ የተጸጸተ መዳፎቹን የሚያገላብጥና «ወይ ጸጸቴ! በጌታዬ አንድንም ባላጋራሁ።» የሚል ሆነ።"},{"id":43,"translation":"43.እርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዱት ቡድኖች አልነበሩትም:: ተረጂም አልነበረም::"},{"id":44,"translation":"44.እዚያ ዘንድ በትንሳኤ ቀን ስልጣኑ እውነተኛ ለሆነው ለአላህ ብቻ ነው:: እርሱ በመመንዳት የበለጠ ፍጻሜንም በማሳመር የበለጠ ነው::"},{"id":45,"translation":"45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱም የቅርቢቱን ህይወት ምሳሌ አውሳላቸው:: እርሷ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ በእርሱም የምድር ቡቃያ እንደተቀላቀለበት፤ ከተዋበ በኋላም ደርቆ ንፋሶች የሚያበኑት ደቃቅ እንደሆነ ብጤ ናት:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው::"},{"id":46,"translation":"46. ገንዘብና ልጆች የቅርቢቱ ህይወት ጌጦች ብቻ ናቸው:: መልካም ቀሪ ሥራዎች ግን በጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸው:: በተስፋም በላጭ ናቸው::"},{"id":47,"translation":"47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተራራዎችን የምናስኬድበትን ቀን አስታውስ:: ምድርንም ግልጽ ሆና ታያታለህ:: እንሰበስባቸዋለንም:: ከእነርሱ አንድንም አንተዉም::"},{"id":48,"translation":"48. የተሰለፉ ሆነው በጌታህ ላይ ይቀርባሉ:: ይባላሉም «በመጀመሪያ ጊዜ እንደፈጠርናችሁ በእርግጥ ወደ እኛ መጣችሁ:: በእውነቱ ለእናንተ የመቀስቀሻ ጊዜን አናደርግም መስሏችሁ ነበር።»"},{"id":49,"translation":"49 ለሰው ሁሉ መጽሐፉ ይቀርባል:: ወዲያዉም ከሓዲያንን በውስጡ ካለው ነገር ፈሪዎች ሆነው ታያቸዋለህ። «ዋ ጥፋታችን! ይህ መጽሐፍ ከሥራ ትንሽንም ትልቅንም የቆጠራት ቢሆን እንጂ የማይተወው ምን አለው?» ይላሉ:: የሠሩትንም ነገር ሁሉ ቅርብ ሆኖ ያገኙታል:: ጌታህም አንድንም አይበድልም::"},{"id":50,"translation":"50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመላዕክት «ለአደም ስገዱ።» ባልናቸው ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: ወዲያዉም ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር ሁሉም ሰገዱ:: ከአጋንንት ጎሳ ነበርና:: ከጌታዉም ትዕዛዝ ወጣ:: እርሱንና ዘሮቹን እነርሱም ለእናንተ ጠላቶች ሲሆኑ ከኔ ሌላ ረዳቶች ታደርጋላችሁን? ለበዳዮች ልዋጭነቱ ከፋ::"},{"id":51,"translation":"51.የሰማያትና የምድርም አፈጣጠር አላሰየኋቸዉም:: የነፍሶቻቸውንም አፈጣጠር እንደዚሁ አሳሳቾችንም ረዳቶች አድርጌ የምይዝ አይደለሁም::"},{"id":52,"translation":"52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያንም አምላክ የምትሏቸውን ተጋሪዎቼን ጥሩ።» የሚልበትን ቀን አስታውስ:: ይጠሯቸዋልም። ግን አይመልሱላቸዉም:: በመካከላቸዉም መጥፊያን ስፍራ ገሀነምንም አደረግን።"},{"id":53,"translation":"53. ከሓዲያንም እሳትን ያያሉ፤ እነርሱም በውስጧ ወዳቂዎች መሆናቸውን ያረጋግጣሉ:: ከእርሷም መሸሻን አያገኙም።"},{"id":54,"translation":"54. በዚህም ቁርኣን ውስጥ ከየምሳሌው ሁሉ ለሰዎች መላልሰን ገለጽን፤ ሰዉም ከነገሩ ሁሉ ይበልጥ ክርክረ ብዙ ነው::"},{"id":55,"translation":"55.ሰዎችንም መመሪያ በመጣላችሁ ጊዜ ከማመንና ጌታቸውንም ምህረትን ከመለመን የከለከላቸው የመጀመሪያዎቹ ህዝቦች ልማድ መጥፋት ልትመጣባቸው ወይም ቅጣቱ በየዓይነቱ ሊመጣባቸው መጠባበቅ ብቻ እንጂ ሌላ አይደለም::"},{"id":56,"translation":"56. መልዕክተኞችንም አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች ሆነው እንጂ አንልክም:: እነዚያ የካዱትም በውሸት እውነቱን በእሱ ሊያበላሹ ይከራከራሉ:: አንቀፆቼንና በእርሱ የተስፈራሩበትንም ነገር ማላገጫ አድርገው ያዙ::"},{"id":57,"translation":"57.በጌታዉም አናቅጽ ከተገሰጸና ከእርሷም ከዞረ፤ ሁለት እጆቹም ያስቀደሙትን ነገር ከረሳቸዉም ይበልጥ በዳይ ማን ነው? እኛ በልቦቻቸው ላይ እንዳያውቁት ሽፋኖችን፤ በጆሮዎቻቸዉም ውስጥ ድንቁርናን አደረግን። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ መመራትም ብትጠራቸው ያን ጊዜ ፈጽሞ አይመሩም::"},{"id":58,"translation":"58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም በጣም መሀሪው የእዝነት ባለቤት ነው:: በሠሩት ሥራ ቢይዛቸው ኖሮ ቅጣቱን ለእነርሱ ባስቸኮለባቸው ነበር:: ግን ለእነርሱ ከእርሱ ሌላ መጠጊያን ፈጽሞ የማያገኙበት ቀጠሮ አላቸው::"},{"id":59,"translation":"59.እነዚህ ከተሞችም በበደሉ ጊዜ አጠፋናቸው፤ ለመጥፊያቸዉም የተወሰነ ጊዜ አደረግን::"},{"id":60,"translation":"60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳ ለወጣቱ «የሁለቱን ባህሮች መገናኛ እስከምደርስ ወይም ብዙን ጊዜ እስከምሄድ ድረስ ከመጓዝ አልወገድም።» ያለውን (አስታውስ)።"},{"id":61,"translation":"61. የሁለቱን ባህር መገናኛ በደረሱም ጊዜ ዓሳቸውን ረሱ፤ ዓሳውም መንገዱን በባህር ውስጥ ቀዳዳ አድርጎ ያዘ።"},{"id":62,"translation":"62. ባለፉም ጊዜ ለወጣቱ «ምሳችንን ስጠን ከዚህ ጉዟችን በእርግጥ ድካምን አግኝተናልና።» አለ።"},{"id":63,"translation":"63. «አየህን? ወደ ቋጥኟ በተጠጋን ጊዜ እኔ ዐሳውን ረሳሁ፤ ሰይጣን እንጂ ሌላ አላስረሳኝም፤ በባህሩም ውስጥ መንገዱን አስደናቂ መንገድ አድርጎ ያዘ።» አለ።"},{"id":64,"translation":"64. ሙሳም «ይህ እኮ እንፈልገው የነበረው ነው።» አለው። ከዚያ በኮቴዎቻቸው (ዱካቸው) ላይ እየተከተሉ ተመለሱ።"},{"id":65,"translation":"65.ከባሮቻችንም ከእኛ ዘንድ ችሮታን የሰጠነውን ከኛም ዘንድ እውቀትን ያስተማርነውን አንድን ባሪያችንን አገኙ::"},{"id":66,"translation":"66. ሙሳ «ለእርሱ ከተማርከው ነገር ቀጥተኛን እውቀት ታስተምረኝ ዘንድ ልከተልህ?» አለው።"},{"id":67,"translation":"67. ባሪያዉም አለ: «አንተ ከእኔ ጋር መታገስን በጭራሽ አትችልም።"},{"id":68,"translation":"68. «በእውቀት ባልደረስክበት ነገር ላይስ እንዴት ትታገሳለህ?»"},{"id":69,"translation":"69. ሙሳም «አላህ የፈለገ እንደሆነ ታጋሽና ላንተ ትዕዛዝን የማልጥስ ሆኜ ታገኘኛለህ።» አለው።"},{"id":70,"translation":"70. «ብትከተለኝም ላንተ ከእርሱ ማውሳትን እስከምጀምርልህ ድረስ ከምንም ነገር እንዳትጠይቀኝ።» አለው።"},{"id":71,"translation":"71. ሄዱም:: በመርከቢቱም በተሳፈሩ ጊዜ መርከቢቱን ቀደዳት። «ባለቤቶችዋን ልታሰምጥ ቀደድካትን? ትልቅን ጥፋት በእርግጥ ሠራህ።» አለው።"},{"id":72,"translation":"72. «አንተ ከእኔ ጋር ትዕግስትን ፈጽሞ አትችልም አላልኩምን?» አለ።"},{"id":73,"translation":"73. «በረሳሁት ነገር አትያዝብኝ:: ከነገሬም ችግርን አታሸክመኝ።» አለው።"},{"id":74,"translation":"74. ወርደው ተጓዙም ወጣቱንም ልጅ ባገኘውና በገደለው ጊዜ «ነፍስን ያልገደለችን ንጹህን ነፍስ ገደልክን? በእርግጥ መጥፎን ነገር ሰራህ።» አለው።"},{"id":75,"translation":"75. «አንተ ከእኔ ጋር ትዕግስትን ፈጽሞ አትችልም አላልኩህምን?» አለ።"},{"id":76,"translation":"76. «ከአሁኒቱ በኋላ ከምንም ነገር ብጠይቅህ አትጎዳኘኝ:: ከእኔ የይቅርታን መጨረሻ በእርግጥ ደርሰሃል።» አለው።"},{"id":77,"translation":"77. ሄዱም። ወደ አንዲት ከተማ ሰዎች ዘንድ ደረሱ ከነዋሪዎች ምግብን ጠየቁ:: (እንደ እንግዳ) ማስተናገዳቸዉንም እምቢ አሉ:: በእርሷም ውስጥ ለመውደቅ የተቃረበን የቤት ግድግዳ አገኙ:: አቆመው:: ሙሳም «ብትፈልግ ኖሮ በእርሱ ላይ ዋጋን በተቀበልክ ነበር።» አለው።"},{"id":78,"translation":"78. አለም: «ይህ በእኔና ባንተ መካከል መለያያችን ነው። በእርሱ ላይ መታገስን ያልቻለክበትን ፍቺ እነግርሃለሁ።"},{"id":79,"translation":"79. «መርከቢቱማ በባህር ውስጥ ለሚሠሩ ምስኪኖች ነበረች:: ከኋላቸው መርከብን ሁሉ በቅሚያ የሚወስድ ክፉ ንጉስ ነበረና እንዳይቀማቸው ላስነውራት ፈልጌ ነው።"},{"id":80,"translation":"80. «ያ ወጣቱም ልጅ ወላጆቹ አማኞች ነበሩ:: ቢያድግ በትዕቢትና በክህደት ወላጆቹን የሚያስገድዳቸው መሆኑን ፈራን።"},{"id":81,"translation":"81. «ጌታቸው በንጹሕነት ከእርሱ በላጭን፤ በእዝነትም ከእርሱ በጣም ቀራቢን ልጅ ሊለውጥላቸው ፈለግን።"},{"id":82,"translation":"82. «ግድግዳዉም በከተማይቱ ውስጥ የነበሩ የሁለት የቲሞች ወጣቶች ነበር:: በስሩም ለእነርሱ የሆነ የተቀበረ ድልብ ነበረና አባታቸዉም መልካም ሰው ነበር:: ጌታህም ለአካለ መጠን እንዲደርሱና ከጌታህ ችሮታ ድልባቸውን እንዲያወጡ ፈቀደ:: በፈቃዴም አልሠራሁትም:: ይህ ያ በእርሱ ላይ መታገስን ያልቻልከው ነገር ፍቹ ነው።» አለው።"},{"id":83,"translation":"83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለ ዙልቀርነይንም ይጠይቁሀል:: «በእናንተ ላይ ከእርሱ ወሬን (ማስታወሻን) አነባለሁ።» በላቸው።"},{"id":84,"translation":"84.እኛ እርሱን በምድር ላይ አስመቸነው:: በነገሩም ሁሉ መዳረሻ መንገድን ሰጠነው::"},{"id":85,"translation":"85. መንገድንም (ወደ ምዕራብ) ተከተለ::"},{"id":86,"translation":"86. ወደ ጸሐይ መግቢያም በደረሰ ጊዜ ጥቁር ጭቃማ ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ አገኛት:: በአጠገቧም ህዝቦችን አገኘ:: «ዙልቀርነይን ሆይ! ወይም በመግደል ትቀጣለህ፤ ወይም በእነርሱ መልካም ነገርን ትሠራለህ።» አልነው።"},{"id":87,"translation":"87. (እርሱም) አለ: «የበደለውንማ ወደፊት እንቀጣዋለን ከዚያ ወደ ጌታው ይመለሳል:: ብርቱንም ቅጣት ይቀጣዋል።"},{"id":88,"translation":"88. «ያመነና መልካምን ሥራ የሰራ ለእርሱ ከምንዳ በኩል መልካሚቱ ገነት አለችው:: ለእርሱም ከትዕዛዛችን ገርን ነገር እናዘዋለን።» አለ።"},{"id":89,"translation":"89-. ከዚያ መንገድን (ወደ ምስራቅ) ቀጠለ::"},{"id":90,"translation":"90.ወደ ጸሐይ መውጫ በደረሰም ጊዜ ለእነርሱ ከበታቹ መከለያን ባላደረግንላቸው ህዝቦች ላይ ስትወጣ አገኛት::"},{"id":91,"translation":"91.ነገሩ ልክ እንደዚሁ ነው:: እርሱም ዘንድ ባለው ነገር ሁሉ በእርግጥ በእውቀት ከበብን::"},{"id":92,"translation":"92. ከዚያ (ወደ ሰሜን አቅጣጫ) መንገድን ቀጠለ::"},{"id":93,"translation":"93.በሁለቱ ጋራዎችም መካከል በደረሰ ጊዜ በአቅራቢያቸው ንግግርን ለማወቅ የማይቃረቡ ህዝቦችን አገኘ::"},{"id":94,"translation":"94. «ዙልቀርነይን ሆይ! የዕጁጅና መዕጁጅ በምድር ላይ አበላሾች ናቸው። ግብር እናድርግልህና በእኛና በእነርሱ መካከል ግድብን ታደርግልን?» አሉ።"},{"id":95,"translation":"95. (እርሱም) አለ: «ጌታዬ ያስመቸብኝ ሀብት ከናንተ ግብር በላጭ ነው:: እናም በጉልበት ብቻ እገዙኝ:: በእናንተና በእነርሱ መካከል ብርቱን ግድብ አደርጋለሁና።"},{"id":96,"translation":"96. «የብረትን ታላላቅ ቁራጮች ስጡኝ።» አላቸው:: በሁለቱ ኮረብታዎች ጫፍ መካከልም ባስተካከለ ጊዜ «አናፉ» አላቸው። ብረቱን እሳትም ባደረገው ጊዜም: «የቀለጠውን ነሀስ ስጡኝ በእርሱ ላይ አፈስበታለሁና።» አላቸው።"},{"id":97,"translation":"97. የእጁጅና መእጁጅ ይህን መከላከያ ሊወጡት አልቻሉም:: ለእርሱ መሸንቆሩንም እንኳን አልቻሉም።"},{"id":98,"translation":"98. «ይህ ግድብ ከጌታዬ ችሮታዎች ነው:: የጌታዬ ቀጠሮ በመጣ ጊዜ እንኩትኩት ያደርገዋል:: የጌታዬም ቀጠሮ የተረጋገጠ ነው።» አለ።"},{"id":99,"translation":"99. በዚያን ቀን ከፊላቸውን በከፊሉ የሚቀላቀሉ አድርገን እንተዋቸዋለን:: በቀንዱም ይነፋል:: መሰብሰብንም እንሰበስባቸዋለን::"},{"id":100,"translation":"100. ገሀነምንም በዚያ ቀን ለከሓዲያን በጣም ማቅረብን እናቀርባታለን::"},{"id":101,"translation":"101.ለእነዚያ አይኖቻቸው ከግሳጼዬ በሽፋን ውስጥ ለነበሩትና መስማትንም የማይችሉ ለነበሩት እናቀርባታለን::"},{"id":102,"translation":"102. እነዚያ በእኔ የካዱት ባሮቼን ከኔ ሌላ አማልክት አድርገው መያዛቸውን የማያስቆጣኝ አድርገው አሰቡን? እኛ ገሀነምን ለከሓዲያን መስተንግዶ አዘጋጅተናል::"},{"id":103,"translation":"103. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በላቸው: «በሥራዎች በጣም ከሳሪዎቹን እንንገራችሁን?"},{"id":104,"translation":"104. «እነዚያ እነርሱ ሥራን የሚያሳምሩ የሚመስላቸው ሲሆኑ በቅርቢቱ ህይወት ሥራቸው የጠፋባቸው ናቸው።»"},{"id":105,"translation":"105. እነዚያ እነርሱ በጌታቸው ተዓምራትና መገናኘት የካዱ ናቸው። ሥራዎቻቸዉም ተበላሸ:: ለእነርሱም በትንሳኤ ቀን ሚዛንን አናቆምላቸዉም::"},{"id":106,"translation":"106. ነገሩ ይህ ነው:: በክህደታቸው፣ አንቀፆቼንና መልዕክተኞቼንም መሳለቂያ አድርገው በመያዛቸው ፍዳቸው ገሀነም ነው::"},{"id":107,"translation":"107. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ፊርደውስ የተባለው የገነት ክፍል ለእነርሱ መስፈሪያ ናቸው::"},{"id":108,"translation":"108. በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች፤ ከእርሷም መዛወርን የማይፈልጉ ሲሆኑ መስፈሪያቸው ነው።"},{"id":109,"translation":"109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ባህሩ ለጌታዬ ቃላት መጻፊያ ቀለሞችን ቢሆን ኖሮ ብጤውን ጭማሪ ብናመጣም እንኳ የጌታዬ ቃላት ከማለቋ በፊት ባህሩ ባለቀ ነበር።» በላቸው።"},{"id":110,"translation":"110. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ መሰላችሁ ሰው ነኝ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው የሚል መልዕክት ወደ እኔ የሚወረድልኝ:: እናም ከጌታው ጋር መገናኘት የሚፈልግ ሰው ሁሉ መልካም ሥራን ይሥራ:: በጌታዉም መገዛት ላይ አንድንም አያጋራ።» በላቸው።"}]},{"id":19,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ካፍ፤ ሃ፤ ያ፤ ዐይን፤ ሷድ፤"},{"id":2,"translation":"2. ይህ ጌታህ ባርያውን ዘከሪያን በችሮታው ያወሳበት ነው::"},{"id":3,"translation":"3. ጌታውን የሚስጢርን ጥሪ በተጣራ ጊዜ የሆነውን አስታውስ::"},{"id":4,"translation":"4. (እንዲህም) አለ: «ጌታዬ ሆይ! እኔ አጥንቴም ደከመ:: ራሴም በሽበት ተንቀለቀለ። ጌታዬ ሆይ! አንተንም በመለመኔ፤ ምንጊዜም ዕድለ ቢስ እልሆንኩም።"},{"id":5,"translation":"5. «እኔም ከበኋላዬ (ከሞትኩ በኋላ) ዘመዶቼን (ከእምነት እንዳይወጡ) ፈራሁ:: ሚስቴም መካን ነበረች:: ስለዚህ ካንተ ዘንድ ለእኔ ልጅን ስጠኝ::"},{"id":6,"translation":"6. «የሚወርሰኝ ከየዕቁብ ቤተሰቦችም የእምነትን ሃላፊነት የሚወርስን ልጅ ስጠኝ:: ጌታዬ ሆይ! ተወዳጅም አድርገው።» አለ።"},{"id":7,"translation":"7. «ዘከሪያ ሆይ! እኛ ስሙ የሕያ በሆነና ከዚያ በፊት ሞክሼን ባላደረግንለት ወንድ ልጅ እናበስርሃለን።» አለው።"},{"id":8,"translation":"8. «ጌታዬ ሆይ! ሚስቴ መካን እኔም ከእርጅና የተነሳ ድርቀትን የደረስኩ ስሆን እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለ።"},{"id":9,"translation":"9. (ጅብሪልም) አለ: «ነገሩ ልክ እንደዚሁ ነው። ጌታህ ‹ከዚህ በፊት ምንም ያልነበርከውን የፈጠርኩህ ስሆን እርሱ በእኔ ላይ ቀላል ነው።› ብሏል።»"},{"id":10,"translation":"10. እርሱም «ጌታዬ ሆይ! እንግዲያውስ ምልክት አድርግልኝ።» አለ። «ምልክትህ (ጤናማ ሆነህ ሳለህ) ሶስት ሌሊት ከነቀናቸው ሰዎችን ማነጋገር አለመቻልህ ነው።» አለው።"},{"id":11,"translation":"11. እርሱም ከምኩራቡ ወደ ህዝቦቹ ወጣ:: ጧትና ማታ ጌታችሁን አውሱ አጥሩትም በማለትም ወደ እነርሱ ጠቀሰ።"},{"id":12,"translation":"12. «የሕያ ሆይ! መጽሐፉን በጥብቅ ያዝ።» አልነው:: ጥበብንም በሕጻንነቱ ሰጠነው።"},{"id":13,"translation":"13. ከእኛም የሆነን ርህራሄና ንጽህናንም (ሰጠነው):: ጥንቁቅም ነበር::"},{"id":14,"translation":"14. ለወላጆቹም በጎ ሠሪ ነበር:: ትዕቢተኛና አመጸኛም አልነበረም::"},{"id":15,"translation":"15. በተወለደበት ቀንና በሚሞትበት ቀን ህያው ሆኖ በሚነሳበትም ቀን ሰላም በእሱ ላይ ይሁን ::"},{"id":16,"translation":"16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መርየም ከቤተሰቧ ወደ ምስራቃዊ ስፍራ በተለየች ጊዜ የሆነውን ታሪኳን በመጽሐፉ ውስጥ አውሳ::"},{"id":17,"translation":"17. ከእነርሱም መጋረጃን አደረገች:: መንፈሳችንንም (መልዐኩ ጂብሪልን) ወደ እርሷ ላክን:: ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት::"},{"id":18,"translation":"18. «ካንተ በአር-ረህማን እጠበቃለሁ። ጌታህን ፈሪ ከሆንክ (አትቅረበኝ)።» አለች።"},{"id":19,"translation":"19. «እኔ ንጹሕ የሆነን ልጅ ላንቺ ልሰጥ የመጣሁ የጌታሽ መልዕክተኛ ነኝ።» አላት።"},{"id":20,"translation":"20. «በጋብቻ አንድም ሰው ያልነካኝ ሆኜ አመንዝራ ዝሙትኛ ሳልሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል!» አለች።"},{"id":21,"translation":"21. (መልአኩም) «ነገሩ ልክ እንደዚሁ ነው የሚፈጸመው። ጌታሽ ‹እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው:: ለሰዎችም ተዓምር ከእኛም ችሮታ ልናደርገው ይህንን ሰራን፤ ነገሩ የተወሰነም ነው።› ብሏል።» አለ።"},{"id":22,"translation":"22. ወዲያውኑም አረገዘችው:: እርሱንም በሆድዋ ይዛው ወደ ሩቅ ስፍራ ገለል አለች::"},{"id":23,"translation":"23. ምጡ ወደ ዘንባባይቱ ግንድ አስጠጋት:: እርሷም «ወይኔ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩና የተረሳሁ በሆንኩ።» አለች።"},{"id":24,"translation":"24. ከበታቿም እንዲህ ሲል ጠራት: «አትዘኝ። ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓልና።"},{"id":25,"translation":"25. «የዘምባባይቱን ግንድ ወደ አንቺ ወዝውዢው:: በአንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ያረግፍልሻልና።"},{"id":26,"translation":"26. «ብይ፤ ጠጭም። ተደሰችም ከሰዎች አንድንም ብታይ እኔ ለአዛኙ አምላክ ዝምታን ተስያለሁ:: እናም ዛሬ ማንንም ሰው በፍጹም አላነጋግርም በይ።» አላት።"},{"id":27,"translation":"27. እርሱን ተሸክማው ወደ ዘመዶቿ መጣች (እንዲህም) አሏት: «መርየም ሆይ! ከባድ ነገርን በእርግጥ ፈጸምሽ።"},{"id":28,"translation":"28. «አንቺ የሃሩን እህት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም:: እናትሽም አመንዝራ ዝሙተኛ አልነበረችም።» አሏት።"},{"id":29,"translation":"29. እርሷም ወደ ህፃኑ አመለከተች:: እነርሱም «በአንቀልባ ያለን ህፃን እንዴት እናናግራለን?» አሉ።"},{"id":30,"translation":"30. ህፃኑም አለ: «እኔ የአላህ አገልጋይ ነኝ፤ መጽሐፍን ሰጥቶኛል። ነብይም አድርጎኛል።"},{"id":31,"translation":"31. «በየትም ስፍራ ብሆን የተባረኩኝ አድርጎኛል። በህይወትም እስካለሁ ሶላትንና ዘካን አዞኛል።"},{"id":32,"translation":"32. «ለእናቴም ታዛዥ አድርጎኛል:: ትዕቢተኛ እድለቢስ አላደረገኝም።"},{"id":33,"translation":"33. «በተወለድሁበት ቀን በምሞትበት ቀንና ሕያው ሆኜ በምቀሰቀስበትም ቀን ሰላም በእኔ ላይ ይስፈን።» አለ።"},{"id":34,"translation":"34. የመርየም ልጅ ዒሳ ይሀው ነው፤ ያ በእርሱ የሚጠራጠሩበት እውነተኛ ቃል ይህ ነው።"},{"id":35,"translation":"35. ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባዉም:: ከጉድለት ሁሉ ጠራ:: አንድን ነገር በወሰነ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ሁን» ብቻ ነው:: ወዲያዉም ይሆናል።"},{"id":36,"translation":"36. ዒሳ ለህዝቦቹ «አላህ የእኔም ጌታዬ የእናንተም ጌታችሁ ነውና ተገዙት:: ይህ ቀጥተኛው መንገድ ነው።» አለ።"},{"id":37,"translation":"37. ከመካከላቸዉም አንጃዎች በእርሱ ነገር ላይ ተለያዩ:: ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከታላቁ ቀን መጋፈጥ ክስተት ወዮላቸው::"},{"id":38,"translation":"38. ወደ እኛ በሚመጡ ቀን ምን ያህል ሰሚ ምን ያህል ተመልካች አደረጋቸው:: ግን አመጸኞች በዳዮች ዛሬ በዚህች ዓለም በግልጽ ስህተትና ጥመት ውስጥ ናቸው::"},{"id":39,"translation":"39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሚፈረድበት ጊዜ የቁጭትን ቀን አስፈራራቸው እነርሱ አሁን በመዘንጋት ላይ ናቸው:: እነርሱ አያምኑምና::"},{"id":40,"translation":"40. ምድርንና በእርሷም ላይ ያለውን ፍጡር ሁሉ እኛ እንወርሳለን:: ወደ እኛም ይመለሳሉ::"},{"id":41,"translation":"41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ኢብራሂምን አውሳ:: እርሱም በጣም እውነተኛ ነብይ ነበርና::"},{"id":42,"translation":"42. ለአባቱ (እንዲህ) ባለው ጊዜ የሆነውን አስታውስ: «አባቴ ሆይ! የማይሰማንና የማያይን ላንተም ምንንም የማይጠቅምህን (የማይፈይድህን) ጣዖት ለምን ታመልካለህን?"},{"id":43,"translation":"43. «አባቴ ሆይ! እኔ አንተ ያልደረሰህን እውቀት መጥቶልኛልና ተከተለኝ:: ቀጥተኛውን መንገድ እመራሃለሁና።"},{"id":44,"translation":"44. «አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አትገዛ \\አታምልክ\\:: ሰይጣን ለአር-ረህማን አመጸኛ ነውና።"},{"id":45,"translation":"45. «አባቴ ሆይ! እኔ የአር-ረህማን ቅጣት ሊያገኝህ እና ከዚያ የሰይጣን ጓደኛ ልትሆን እፈራለሁ::»"},{"id":46,"translation":"46. አባቱም «ኢብራሂም ሆይ! አንተ አምላኮቼን ትተህ የምትዞር ነህን? ከዚህ ተግባርህ ባትከለከል በእርግጥ እወግርሃለሁ:: ረዥም ጊዜንም ተወኝ።» አለ።"},{"id":47,"translation":"47. ኢብራሂምም አለ: «ደህና ሁን (ሰላም ላንተ ይሁን):: ከጌታዬ ምህረትን እለምንልሃለሁ:: እርሱ ለእኔ በጣም ሩህሩህ ነውና።"},{"id":48,"translation":"48. «እናንተንና ከአላህ ሌላ የምትገዙትን ሁሉ እርቃለሁ:: ጌታዬንም ብቻ እገዛለሁ፤ ጌታዬን በመገዛት የማፍር አለመሆኔን እከጅላለሁ (ተስፋ አደርጋለሁ)።» አለ።"},{"id":49,"translation":"49. እነርሱንና ከአላህ ሌላ የሚገዙትን በራቀ ጊዜ ኢስሐቅንና የዕቁብን ሰጠነው:: ሁለቱንም ነብይ አደረግናቸው::"},{"id":50,"translation":"50. ለእነርሱም ከችሮታችን ሰጠናቸው:: ለእነርሱም ከፍ ያለ ምስጉን ዝናን አደረግንላቸው::"},{"id":51,"translation":"51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ሙሳን አውሳ:: እርሱ ምርጥ ነበርና:: መልዕክተኛ ነብይም ነበርና::"},{"id":52,"translation":"52. ከጡር ጋራ በስተቀኝ ጎን በኩልም ጠራነው። በሚስጥር ያነጋገርነውም ስንሆን አቀረብነው።"},{"id":53,"translation":"53. ከእዝነታችንም (ከችሮታችንም) ወንድሙን ሃሩንን ነብይ አደረግንለት።"},{"id":54,"translation":"54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ኢስማዒልንም አውሳ:: እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበርና። መልዕክተኛ ነብይም ነበር።"},{"id":55,"translation":"55. ቤተሰቦቹንም በሶላትና በዘካ ያዝ ነበር:: በጌታዉም ዘንድ ተወዳጅ ነበር::"},{"id":56,"translation":"56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ኢድሪስንም አውሳ:: እርሱ እውነተኛ ነብይ ነበርና::"},{"id":57,"translation":"57. (ኢድሪስን) ወደ ከፍተኛም ስፍራ አነሳነው::"},{"id":58,"translation":"58. እነዚህ (አሥሩ) እነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ችሮታውን የለገሰላቸው ከነብያት ከአዳም ዘር ከኑሕ ጋር በመርከቢቱ ላይ ከጫንናቸዉም ዘሮች ከኢብራሂምና ከኢስራኢልም ዘሮች ከመራናቸውና ከመረጥናቸዉም የሆኑት የአር-ረህማን አናቅጽ በእነርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ ሰጋጆችና አልቃሾች ሆነው ወደ መሬት የሚወድቁ (የሚደፉ) ናቸው። {1}","footnotes":"{1} እዚህ ሱጁዱ ትላዋ ይደረጋል።"},{"id":59,"translation":"59. ከእነርሱም በኋላ ሶላትን ያጎደሉ ከንቱ ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ትውልዶች ተተኩ:: «ገይ» የሚባልን የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ::"},{"id":60,"translation":"60. ግና ከእነርሱ የተጸጸቱ በአላህ ያመኑ በጎንም ስራ የሰሩ ሰዎች ወደ ገነት ይገባሉ:: አንዳችንም አይበደሉም::"},{"id":61,"translation":"61. የመኖሪያን ገነቶች ያችን አር-ረህማን ለባሮቹ በሩቅ ሆነው ሳሉ ተስፋ ቃል የገባላቸውን ይገባሉ:: እርሱ ተስፋው ሁልጊዜም ተፈጻሚ ነውና::"},{"id":62,"translation":"62. በእርሷ ሰላምን እንጂ ውድቅን ነገር አይሰሙም:: ለእነርሱም በእርሷ ውስጥ ጧትም ማታም ሲሳያቸው አላቸው::"},{"id":63,"translation":"63. ይህ ያቺ ከባሮቻችን ጥንቁቆች ለሆኑት ሁሉ የምናወርሳት ገነት ናት::"},{"id":64,"translation":"64. (ጂብሪልም ለነቢዩ) «በጌታህ ትእዛዝ እንጂ አንወርድም:: በፊታችን፤ በኋላችንና በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: ጌታህም ረሺ አይደለም።» አለ።"},{"id":65,"translation":"65. እርሱ የሰማያትና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው:: እርሱን በመገዛትም ላይ ታገሥ:: ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን?"},{"id":66,"translation":"66. ሰው «በሞትኩ ጊዜ ወደ ፊት ህያው ሆኜ ከመቃብር እወጣለሁን?» ይላል።"},{"id":67,"translation":"67. ሰው ከዚህ በፊት ምንም ነገር ያልነበረ ሲሆን የፈጠርነው መሆኑን አያስታውስምን?"},{"id":68,"translation":"68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጌታህ እንምላለን ሰይጣናት ጋር በእርግጥ እንሰበስባቸዋለን:: ከዚያም በገሀነም ዙሪያ የተንበረከኩ ሆነው እናቀርባቸዋለን::"},{"id":69,"translation":"69. ከዚያም ከየቡድኖቹ ሁሉ ከእነርሱ ያንን በአር-ረህማን ላይ በድፍረት በጣም ብርቱ የሆነውን መዘን እናወጣለን::"},{"id":70,"translation":"70. ከዚያም እነዚያን በእርሷ ለመቃጠል ይበልጥ ተገቢ የሆኑትን ሰዎች እናውቃለን::"},{"id":71,"translation":"71. (ሰዎች ሆይ!) ከናንተ መካከል ወደ ገሀነም የማይወርድ አንድም የለም:: መውረዱም ጌታህ የፈረደው ግዴታና አይቀሬ ዉሳኔ ነው:: {1}","footnotes":"{1} ይህ ጀሀነም መውረድ ትርጉሙ ሙስሊሞች በርሷ ላይ በተዘረገው ሲራጥ በተባለ በጣም ቀጭን ድልድይ ላይ ያልፋሉ ማለት ነው፣ ሰው ያለ ጥፋት ገሀነም የማይገባ መሆኑ የተወቀ ነው [ተፍሲር ኢብኑጀሪር አጥጠበሪ]"},{"id":72,"translation":"72. ከዚያም እነዚያን አላህን የፈሩትን ብቻ እናድናለን:: አመጸኞችን ደግሞ የተንበረከኩ ሆነው በውስጧ እንተዋቸዋለን::"},{"id":73,"translation":"73. በእነርሱም ላይ አናቅጻችን ግልጽ ማስረጃዎች ሆነው በተነበቡላቸው ጊዜ እነዚያ የካዱት ለእነዚያ ላመኑት «ከሁለቱ ክፍሎች መኖሪያው የበለጠውና ሸንጎዉም ይበልጥ የሚያምረው ማንኛው ነው?» ይላሉ።"},{"id":74,"translation":"74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች እነርሱ በእይታ በጣም ያማሩትን ብዙዎችን አጥፍተናል::"},{"id":75,"translation":"75. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በስህተት ውስጥ የሆነውን አዛኙ አምላክ ለእርሱ ጥመትን ይጨምርለት (ማዘግየትን ያዘግየው::) የሚዛትባቸውንም ቅጣትን ወይም ሰዓቲቱን ባዩ ጊዜ እርሱ ስፍራው መጥፎና ሰራዊቱ ደካማ ማን እንደሆነ በእርግጥ ያውቃሉ።» በላቸው::"},{"id":76,"translation":"76. እነዚያንም የቀኑትን ሰዎች አላህ ቅንነትን ይጨምርላቸዋል:: መልካም ቀሪ ስራዎች በጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸው:: በመመለሻነትም የተሻሉ ናቸው::"},{"id":77,"translation":"77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን በአናቅጻችን የካደውንና «በትንሣኤ ቀን ገንዘብም ሆነ ልጅ በእርግጥ እሰጣለሁ» ያለውን አየህን?"},{"id":78,"translation":"78. ሩቁን ምስጢር አወቀን ? ወይስ አዛኙ አምላክ ዘንድ ቃል ኪዳንን ያዘ?"},{"id":79,"translation":"79. ከዚህ አቋሙ ይታቀብ:: አይሰጠዉም:: የሚለውን ሁሉ በእርግጥ እንጽፋለን:: ለእርሱም ከቅጣት ጭማሬን እንጨምርለታለን::"},{"id":80,"translation":"80. አለኝ የሚለውንም ሁሉ እንወርሰዋለን ወደ እኛም ብቻውን ሆኖ ይመጣል::"},{"id":81,"translation":"81. ከአላህ ሌላ አማልክትን ለእነርሱ መከበሪያ አማላጅ እንዲሆኗቸው ያዙ::"},{"id":82,"translation":"82. ከዚህ ተግባራቸው ይከልከሉ (ይታቀቡ):: መገዛታቸውን በእርግጥ ወደፊት ይከዷቸዋል:: በእነርሱም ላይ ተቃራኒ (ባላጋራ) ይሆኑባቸዋል::"},{"id":83,"translation":"83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰይጣናትን በከሓዲያን ላይ በመጥፎ ሥራ የሚገፋፏቸው ሲሆኑ የላክንባቸው መሆናችንን አላየህምን::"},{"id":84,"translation":"84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱም መቀጣት ላይ አትቸኩል:: ለእነርሱ ቀንን እንቆጥርላቸዋለንና::"},{"id":85,"translation":"85. ትክክለኛ አማኞችን የተከበሩ ቡድኖች ሆነው ወደ አዛኙ አምላክ የምንሰበሰብበትንና:"},{"id":86,"translation":"86. ከሓዲያንን የተጠሙ ሆነው ወደገሀነም የምንነዳበትን ቀን አስታውስ።"},{"id":87,"translation":"87. አዛኙ አምላክ ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ቢሆን እንጂ ሌሎች ማማለድን አይችሉም::"},{"id":88,"translation":"88. አጋሪዎች «አዛኙ አምላክ አላህ ልጅ ወለደ።» አሉ።"},{"id":89,"translation":"89.(አጋሪዎች ሆይ!) እጅግ ከባድና መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ::"},{"id":90,"translation":"90. ከዚህ ንግግራቸው ሰማያት ሊቀደዱ፤ ምድርም ልትሰነጠቅ፤ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ::"},{"id":91,"translation":"91. ይህም ለአዛኙ አምላክ ልጅ አለው ስላሉ ነው::"},{"id":92,"translation":"92. አዛኙ ጌታ ልጅን መያዝ አይገባዉም::"},{"id":93,"translation":"93. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ በትንሣኤ ቀን (ለአር-ረህማን) ለአዛኙ ጌታ ባሪያ ሆነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም::"},{"id":94,"translation":"94. አላህ በእርግጥ በዕውቀቱ ከቧቸዋል:: መቁጠርንም ቆጥሯቸዋል::"},{"id":95,"translation":"95. ሁሉም በትንሳኤ ቀን ለየብቻ ሆነው ወደ እርሱ መጪዎች ናቸው::"},{"id":96,"translation":"96. እነዚያ በአላህ ያመኑና በጎ ስራዎችን የሰሩ ሁሉ አር-ረህማን ለእነርሱ ውዴታን ይሰጣቸዋል::"},{"id":97,"translation":"97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በምላስህም ቁርኣንን ያገራነው በእርሱ ጥንቁቆችን ልታበስርበትና በእርሱ ተከራካሪ ሕዝቦችን ልታስፈራራበት ዘንድ ነው::"},{"id":98,"translation":"98. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙ ትውልዶችን አጥፍተናል:: ከእነርሱ አንድን እንኳ ታያለህን? ወይንስ ለእነርሱ ሹክሹክታን ትሰማለህን? (አታይም፣ አጸማምም)።"}]},{"id":20,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ጧሃ፤"},{"id":2,"translation":"2.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንን አንድትቸገር ባንተ ላይ አላወረድንም::"},{"id":3,"translation":"3. አላህን ለሚፈራ ሁሉ መገሠጫ ይሆን ዘንድ እንጂ"},{"id":4,"translation":"4. ቁርኣን ምድርንና የላይኛዎቹን (የተከበሩ) ሰማያትን ከፈጠረ አምላክ ተወረደ::"},{"id":5,"translation":"5.እርሱ አዛኙ ጌታ (አር-ረህማን) በዐርሹ ላይ ከፍ አለ::"},{"id":6,"translation":"6. በሰማያት፤በምድርና በመካከላቸዉም ያለው ከአፈር በታችም ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው::"},{"id":7,"translation":"7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በንግግር ብትጮህ (አላህ ከጩኸቱ የተብቃቃ ነው።) እርሱ ምስጢርን ከዚያም በጣም የተደበቀንም ያውቃልና::"},{"id":8,"translation":"8.አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ለእርሱ መልካሞች የሆኑ አያሌ ስሞች አሉት::"},{"id":9,"translation":"9.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሙሳ ወሬ (ታሪክ) መጥቶሃልን (ደርሶሃልን)?"},{"id":10,"translation":"10. እሳትን ባየና ለቤተሰቦቹ «(እዚህ) ቆዩ:: እኔ እሳትን አየሁ፤ ከእርሷ ችቦን ላመጣላችሁ ወይም እሳቲቱ ዘንድ መሪን ላገኝ እከጅላለሁ።» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ::"},{"id":11,"translation":"11. እናም ወደ እርሷ በመጣ ጊዜ (እንዲህ) በማለት ተጠራ: «ሙሳ ሆይ!"},{"id":12,"translation":"12. «እኔ ጌታህ ነኝ። ጫማዎችህን አውልቅ፤ አንተ በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ ነህና።"},{"id":13,"translation":"13. «እኔም መረጥኩህ ስለ ሆነም የሚወረድልህን ነገር በደንብ አዳምጥ።"},{"id":14,"translation":"14. «እኔ አላህ ነኝ። ያለ እኔ ትክክለኛ አምላክ የለምና እኔን ብቻ ተገዛኝ:: ሶላትንም እኔን ለማውሳት በአግባቡ ስገድ።"},{"id":15,"translation":"15. «ነፍስ ሁሉ በምትሰራው ነገር ትመነዳ ዘንድ ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት። የትንሳኤውን ወሬ ልደብቃት እቀርባለሁ።"},{"id":16,"translation":"16. (ሙሳ ሆይ!) «በእርሷ የማያምንና ዝንባሌውን የሚከተል ሰው ሁሉ ከእርሷ አያግድህ ትጠፋለህና።"},{"id":17,"translation":"17. (ሙሳ ሆይ!) «ይህችም በቀኝ እጅህ ያለችው ምንድን ናት?» (ተባለ)።"},{"id":18,"translation":"18. «እርሷ በትሬ ናት:: በእርሷም እደገፍባታለሁ:: በእርሷም ለፍየሎቼ ቅጠልን አረግፍባታለሁ:: በእርሷ ሌሎች ጉዳዮችም አሉኝ።» አለ።"},{"id":19,"translation":"19. አላህም «ሙሳ ሆይ! እስቲ ጣላት።» አለው።"},{"id":20,"translation":"20.ሙሳም ጣላትና፤ ወዲያዉም እርሷ የምትሮጥ እባብ ሆነች::"},{"id":21,"translation":"21.አላህም አለው: «ሙሳ ሆይ! ያዛት አትፍራም ወደ መጀመሪያ ጠባይዋ እንመልሳታለን።"},{"id":22,"translation":"22. «እጅህንም ወደ ብብትህ አስገባ:: ሌላ ተዓምር ስትሆን ያለ ምንም ችግር ነጭ ሆና ትወጣለችና::"},{"id":23,"translation":"23. (ሙሳ ሆይ!) «ከተዓምራቶቻችን ታላቋን እናሳይህ ዘንድ ይህን ፈጸምን::"},{"id":24,"translation":"24. (ሙሳ ሆይ!) «ወደ ፈርዖን ሂድ:: እርሱ ወሰን (ድንበር) አልፏልና።»"},{"id":25,"translation":"25. ሙሳም አለ: «ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ።"},{"id":26,"translation":"26. «ጉዳዬንም አግራልኝ።"},{"id":27,"translation":"27. «የምላሴን መኮላተፍም አስወግድልኝ።"},{"id":28,"translation":"28. «ንግግሬን ይረዱ ዘንድ።"},{"id":29,"translation":"29. «ከቤተሰቦቼም ለእኔ ረዳትን አድርግልኝ።"},{"id":30,"translation":"30. «ወንድሜን ሃሩንን"},{"id":31,"translation":"31. «ኃይሌንም በእርሱ አበርታልኝ::"},{"id":32,"translation":"32. «በነገሬም አጋራው።"},{"id":33,"translation":"33. «በብዛት እንድናጠራህና"},{"id":34,"translation":"34. «በብዛት እንድናወሳህ"},{"id":35,"translation":"35. «አንተ በእኛ ነገር አዋቂ ነህና።»"},{"id":36,"translation":"36. አላህም አለ: «ሙሳ ሆይ! ልመናህ በእርግጥ ተቀባይነትን አገኝቷል።"},{"id":37,"translation":"37. «ሙሳ ሆይ! በሌላም ጊዜ ባንተ ላይ በእርግጥ ውለታን ውለናል::"},{"id":38,"translation":"38. «ለእናትህ በራእይ ባሳወቅን ጊዜ ነው።"},{"id":39,"translation":"39. «‹ሕፃኑን በሳጥኑ ውስጥ አስገቢው እርሱንም (ሳጥኑን) በባህር ላይ ጣይው፤ ባህሩም በዳርቻው ይጥለዋል (ይተፋዋል):: ለእኔም ለእርሱም ጠላት የሆነ ሰው ይይዘዋልና› በማለት (ባሳወቅን ጊዜ ለገስንልህ)። ልትወደድና በዐይኔ እይታ (በእኔም ጥበቃ) ታድግ ዘንድ ባንተ ላይም ከእኔ የሆነ መወደድን ጣልኩብህ::"},{"id":40,"translation":"40. «እህትህ በምትሄድና ‹የሚያሳድገውን ሰው ላመላክታችሁን?› ባለች ጊዜ (መወደድን ጣልኩብህ):: ወደ እናትህም ዓይኗ እንዲረጋና እርሷ እንዳታዝንም መለስንህ:: ነፍስንም ገደልክ ከጭንቅም አዳንንህ:: ፈተናዎችንም ፈተንህ:: በመድየን ቤተሰቦችም ውስጥ ብዙ ዓመታትን ተቀመጥክ:: ከዚያ ሙሳ ሆይ! በተወሰነ ጊዜ ላይ መጣህ::"},{"id":41,"translation":"41. «ለራሴም ለመልዕክተኝነት መረጥኩህ::"},{"id":42,"translation":"42. «አንተና ወንድምህ በተዓምራቴ ሆናችሁ ሂዱ:: እኔንም ከማውሳትም አትቦዝኑ::"},{"id":43,"translation":"43. «ወደ ፈርዖን ሂዱ:: እርሱ ወሰን አልፏልና::"},{"id":44,"translation":"44. «እርሱ ምን አልባትም ይገሰጥ ወይም ይፈራ ዘንድ:: ለእርሱ ለስላሳን ቃል ተናገሩት።»"},{"id":45,"translation":"45. «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ክፋት በመስራት መቸኮሉን ወይም ኩራትን መጨመሩን እንፈራለን።» አሉ።"},{"id":46,"translation":"46. አላህም አለ: «እኔ በእርግጥ ከናንተ ጋር ነኝና አትፍሩ:: የሚለውንም ሁሉ እሰማለሁ። የሚፈጸመዉንም አያለሁም።"},{"id":47,"translation":"47. እናም ወደ እርሱም ሂዱና (እንዲህ) በሉት: ‹እኛ የጌታህ መልዕክተኞች ነንና የኢስራኢልን ልጆች ሁሉ ከእኛ ጋር ልቀቅ። አታሰቃያቸዉም:: ከጌታህ በሆነው ተዓምር በእርግጥ መጥተንሃልና:: ሰላምም ቀጥታን በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን።"},{"id":48,"translation":"48. «‹እነሆ የአላህ ቅጣት እውነትን ባስተባበለና እምቢ ባለ ሰው ላይ እንደሆነ በእርግጥ አያሌ መልዕክት ተወረደልን።› በሉት።»"},{"id":49,"translation":"49. ፈርዖንም «ሙሳ ሆይ! ጌታችሁ ማነው?» አለ።"},{"id":50,"translation":"50. «ጌታችን ያ ለፍጥረቱ ሁሉ የሚያስፈልገውን ቅርጹንና ባህሪውን የሰጠው ከዚያም ሁሉንም ለተፈጠረለት የመራው ነው።» አለው።"},{"id":51,"translation":"51. ፈርዖንም «የመጀመሪያይቱ ዘመናት ህዝቦች ሁኔታስ ምንድን ነው?» አለ::"},{"id":52,"translation":"52. ሙሳም «የዚህ ዕውቀት እጌታዬ ዘንድ በመጽሐፍ የተመዘገበ ነው:: ጌታዬ አይሳሳትም አይረሳምም።» አለው።"},{"id":53,"translation":"53. ያ ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ ያደረገላችሁ በእርሷም ውስጥ ለእናንተ መንገድን ያገራላችሁ ውሃንም ከሰማይ ያወረደላችሁ ነው። በእርሱም ከተለያየ በቃይ ዓይነቶችን አወጣንላችሁ።"},{"id":54,"translation":"54. ለራሳችሁ ብሉ:: እንስሳዎቻችሁንም አግጡ:: (ባዮች ሆነን አወጣንላችሁ።) በዚህ ውስጥ ለአእምሮ ባለቤቶች ሁሉ በእርግጥ ተዐምራት አለበት።"},{"id":55,"translation":"55. (ሰዎች ሆይ!) ከእርሷ (ከምድር) ፈጠርናችሁ:: ወደ እርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን:: ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን::"},{"id":56,"translation":"56.ተዓምራቶቻችንንም ሁሏንም ለፈርዖን በእርግጥ አሳየነው:: አስተባበለም:: እምቢም አለ::"},{"id":57,"translation":"57. አለም: «ሙሳ ሆይ! ከምድራችን በድግምትህ ልታወጣን መጣህብን?"},{"id":58,"translation":"58. «መሰሉንም ድግምት እናመጣብሃለን:: በእኛና ባንተም መካከል እኛም አንተም የማንጥሰው የሆነ ቀጠሮን በመካከለኛ ስፍራ አድርግልን።» አለ::"},{"id":59,"translation":"59.ሙሳም: «ቀጠሯችሁ ያ የማጌጫው የበአሉ ቀን ነው። ሰዎችም ረፋድ ላይ እንዲሰበሰቡ ይሁን።» አለ።"},{"id":60,"translation":"60. ፈርዖንም ዞረ:: ተንኮሉን ሰበሰበ:: ከዚያ መጣ::"},{"id":61,"translation":"61.ሙሳም ለእነርሱ: «ወዮላችሁ በአላህ ላይ ውሸትን አትቅጠፉ:: በቅጣት ያጠፋችኋልና:: የቀጠፈም ሰው በእርግጥ አፈረ።» አላቸው።"},{"id":62,"translation":"62. (ድግምተኞቹ) በመካከላቸውም ነገራቸውን ተጨቃጨቁ፡፡ ውይይትንም ደበቁ፡፡"},{"id":63,"translation":"63. አሉም: «እነዚህ በእርግጥ ደጋሚዎች ናቸው:: ከምድራችሁ በድግምታቸው ሊያወጧችሁ በላጪቱንም መንገዳችሁን ሊያስወግዱባችሁ ይሻሉ።"},{"id":64,"translation":"64. «ተንኮላችሁንም አጠንክሩ:: ከዚያም ተሰልፋችሁ ኑ:: ዛሬ ያሸነፈም ሰው ምኞቱን አገኘ።» ተባባሉ።"},{"id":65,"translation":"65. «ሙሳ ሆይ! በመጀመሪያ ትጥላለህ ወይስ እኛ እንጣል? (ምረጥ)» አሉ።"},{"id":66,"translation":"66. ሙሳም «እናንተ በመጀመሪያ ጣሉ።» አላቸው። ጣሉም:: ወዲያዉም ገመዶቻቸውና ዘንጎቻቸው ከድግምታቸው የተነሳ የሚሮጡ እባቦች ሆነው (መስለው) ወደ እርሱ ተመሰሉበት።"},{"id":67,"translation":"67.ሙሳም በውስጡ ፍርሃት አደረበት::"},{"id":68,"translation":"68. አልነውም: «አትፍራ። የበላዩ አንተ ነህና።"},{"id":69,"translation":"69. «በቀኝ እጅህ ያለችውን ብትር ጣል:: ያንን የሰሩትን ሁሉ ትውጣለችና። ያ የሰሩት ሁሉ የድግምተኛ ተንኮል ብቻ ነውና:: ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናዉም::»"},{"id":70,"translation":"70. ድግምተኞቹም ሱጁድ ወረዱ: «በሃሩንና በሙሳ ጌታ አመንን።» አሉ::"},{"id":71,"translation":"71. (ፈርዖንም) «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁለትን! እርሱ በእርግጥ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ መሪያችሁ ነው:: እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን (በማናጋት) ግራንና ቀኝን በማፈራረቅ እቆራርጣችኋለሁ:: በዘምባባም ግንዶች ላይ እሰቅላችኋለሁ:: የማንኛችን ቅጣት በጣም ብርቱና የሚቆይ መሆኑን በዚያ ጊዜ ታውቃላችሁ።» አላቸው።"},{"id":72,"translation":"72. አሉትም: «ከመጡልን ተዓምራትና ከዚያ ከፈጠረን አምላክ ፈጽሞ አናስበልጥህም:: እናም የምትፈርደውን ፍረድ:: የምትፈርደው በዚህች በአነስተኛይቱ ህይወት ብቻ ላይ ነውና።"},{"id":73,"translation":"73. «ኃጢአቶቻችንንና ከድግምትም እንድንፈጽመው ያስገደድከንን ይምረን ዘንድ እኛ በጌታችን አምነናል:: አላህ በጣም በላጭ ነው:: ቅጣቱም ሆነ ምንዳው በጣም የሚዘወትር ነው።» አሉ።"},{"id":74,"translation":"74. ከሃዲ ሆኖ ወደ ጌታው የሚመጣ (የሚሞት) ሰው ሁሉ ለእርሱ ገሀነም አለችለት:: በውስጧም አይሞትም ህያዉም አይሆንም::"},{"id":75,"translation":"75.እነዚያ በጎ ስራዎችን የሰሩና አማኝ ሆነው ወደ ጌታቸው የመጡ ሰዎች ደግሞ እነዚያ ለእነርሱ ከፍተኛ ደረጃዎች አሏቸው::"},{"id":76,"translation":"76.ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ አሏቸው:: ይህም አይነቱ ክፍያ ለተጥራራ ሁሉ ምንዳው ነው::"},{"id":77,"translation":"77. ወደ ሙሳም «ባሮቼን ይዘህ በሌሊት ሂድ:: ለእነርሱም በባህር ውስጥ ደረቅ መንገድን አድርግላቸው:: ፈርዖን ያገኘኛል ብለህ አትፍራ:: ከመስመጥም አትጨነቅ።» ስንል በእርግጥ ላክንበት።"},{"id":78,"translation":"78. ፈርዖን ከሰራዊቱ ጋር ሆኖ ተከተላቸው:: ከባህሩም የሚሸፍን ነገር ሸፈናቸው።"},{"id":79,"translation":"79.ፈርዖንም ህዝቦቹን አሳሳታቸው:: ቅኑንም መንገድ አልመራቸዉም::"},{"id":80,"translation":"80. የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ከጠላታችሁ በእርግጥ አዳንናችሁ:: በጡር ተራራም ቀኝ ጎን ላይ ቀጠሮ አደረግንላችሁ። በእናንተም ላይ መናንና ሰልዋን (ድርጭት) አወረድንላችሁ።"},{"id":81,"translation":"81. ከሰጠናችሁ ሲሳይ ከመልካሙ ብሉ:: በእርሱም ወሰንን አትለፉ:: ቁጣዬ በእናንተ ላይ ይወርድባችኋልና:: ቁጣዬ የሚወርድበት ሁሉ በእርግጥ ይጠፋል::"},{"id":82,"translation":"82.እኔም ለተጸጸተ ላመነም መልካምንም ለሰራ ከዚያ ለተመራ ሁሉ በእርግጥ መሓሪ ነኝ::"},{"id":83,"translation":"83. «ሙሳ ሆይ! ከህዝቦችህ ምን አስቸኮለህ?» ተባለ::"},{"id":84,"translation":"84. «እነርሱ እነዚህ በዱካዬ ላይ ያሉ ናቸው:: ጌታዬ ሆይ! ትወድልኝ ዘንድ ወደ አንተ ቸኮልኩ።» አለ።"},{"id":85,"translation":"85.(አላህም) «እኛም ካንተ በኋላ ሰዎችህን በእርግጥ ፈተንን:: ሳምራዊዉም አሳሳታቸው።» አለው::"},{"id":86,"translation":"86. ሙሳም ወደ ሰዎች የተቆጣና ያዘነ ሆኖ ተመለሰ:: «ህዝቦቼ ሆይ! ጌታችሁ መልካም ተስፋን አልቀጠራችሁምን? ቀጠሮው በእናንተ ላይ ረዘመባችሁን? ወይስ በእናንተ ላይ ከጌታችሁ ቅጣት ሊወርድባችሁ ፈለጋችሁና ቃል ኪዳኔን አፈረሳችሁ?» አላቸው::"},{"id":87,"translation":"87. «ቀጠሮህን በፈቃዳችን አልጣስንም:: ግን እኛ ከህዝቦች ጌጥ ሸክሞችን ተጫን:: በእሳት ላይ ጣልናትም:: ሳምራዊዉም እንደዚሁ አብሮን ጣለ።» አሉት።"},{"id":88,"translation":"88. ለእነርሱም የመጓጎር ባህሪ ያለውን ጥጃን (መሰል) አካልን አወጣላቸው። «ተከታዮቹ ሆይ! ይህ የእናንተም ሆነ የሙሳ አምላክ ነው:: ግን ረሳው እንጂ።» አሉ።"},{"id":89,"translation":"89.ወደ እነርሱ ንግግርን የማይመልስ ለእነርሱም ጉዳትንና ጥቅምን የማይችል መሆኑን አያዩምን?"},{"id":90,"translation":"90-.ከዚያ በፊት ሀሩንም በእርግጥ አላቸው: «ህዝቦቼ ሆይ! ይህ በእርሱ የተሞከራችሁበት ብቻ ነው:: ጌታችሁም አር-ረህማን ነው:: ተከተሉኝም፤ ትእዛዜንም ስሙ።»"},{"id":91,"translation":"91. «ሙሳ ወደ እኛ እስከሚመለስ በእርሱ መገዛት ላይ ከመቆየት ፈጽሞ አንወገድም።» አሉ።"},{"id":92,"translation":"92- ሙሳም አለ፡- «ሃሩን ሆይ! ተሳስተው ባየሃቸው ጊዜ ምን ከለከለህ?"},{"id":93,"translation":"93. «እኔን ከመከተል? ትእዛዜን ጣስክን?» አለ።"},{"id":94,"translation":"94. «ሃሩን የእናቴ ልጅ ሆይ! ፂሜንም ሆነ ራሴን አትያዝ:: እኔ ‹በኢስራኢል ልጆች መካከል ለያየህ ቃሌንም አልጠበክም› ማለትህን ፈራሁና ነው።» አለው።"},{"id":95,"translation":"95. ሙሳም «ሳምራዊው ሆይ! ነገርህ ምንድን ነው?» አለ።"},{"id":96,"translation":"96. ሳምራዊውም: «እነርሱ ያላዩትን ነገር አየሁ:: ከመልዕክተኛው ፈረስ ኮቴ ዱካም ጭብጥ አፈርን ዘገንኩ:: በቅርጹ ላይ ጣልኳትም:: ልክ እንደዚሁ ነፍሴ ሸለመችልኝ።» አለ።"},{"id":97,"translation":"97. ሙሳም ለሳምራዊው አለው: «ሂድ። በህይወትህ ላየኸው ሰው ሁሉ ‹መነካካት የለም› እያልክ ኑር:: ላንተም ፈጽሞ የማትቀር ቀጠሮ አለህ:: ወደ እዚያዉም በእርሱ ላይ ተገዢው ሆነህ ወደ ቆየህበት አምላክህ ተመልከት:: በእርግጥ እናቃጥለዋለን:: ከዚያም በባህሩ ውስጥ እንበትነዋለን::»"},{"id":98,"translation":"98.(ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁም ያ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ የሆነው አላህ ብቻ ነው:: እውቀቱ ሁሉን ነገር አዳረሰ::"},{"id":99,"translation":"99. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ በእርግጥ ካለፉት ወሬዎች ባንተ ላይ እንተርካለን፤ ከእኛም ዘንድ ቁርኣንን በእርግጥ ሰጠንህ::"},{"id":100,"translation":"100.ከእርሱ ያፈገፈገ ሰው እርሱ በትንሳኤ ቀን ከባድን ቅጣት ይሸከማል::"},{"id":101,"translation":"101.በእርሱ ውስጥ ዘውታሪዎች ሆነው ይሸከማሉ:: በትንሳኤ ቀን ለእነርሱ እጣ ፈንታ የሆነው ሸክም ከፋ!"},{"id":102,"translation":"102. በቀንዱ በሚነፋ ቀን ሸክማቸው ከፋ:: ከሓዲያን በዚያ ቀን ዓይኖቻቸው ሰማያዊዎች ሆነው እንሰበስባቸዋለን::"},{"id":103,"translation":"103. «አስርን (ቀን) እንጂ አልቆያችሁም።» በመባባል በመካከላቸው ይንሾካሾካሉ::"},{"id":104,"translation":"104. በሃሳብ ቀጥተኛቸው «አንድን ቀን እንጂ አልቆያችሁም።» በሚል ጊዜ የሚሉትን ነገር እኛ አዋቂዎች ነን።"},{"id":105,"translation":"105. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጋራዎች ይጠይቁሃልና (እንዲህ) በላቸው: «ጌታዬ መበተንን ይበትናቸዋል።"},{"id":106,"translation":"106. «ትክክል ሜዳም ሆና ይተዋታል።"},{"id":107,"translation":"107. «በእርሷ ዝቅታና ከፍታን ፈጽሞ አታይም።»"},{"id":108,"translation":"108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚያ ቀን ለመሰብሰብ ጠሪውን ምንም እንከን የሌለውን ተጣሪ ይከተላሉ:: ድምፆችም ሁሉ ለአር-ረህማን ጸጥ ይላሉ:: ስለዚህ (የኮቴ) ሹክሹክታን እንጂ አትሰማም።"},{"id":109,"translation":"109.በዚያ ቀን ለእርሱ አር-ረህማን የፈቀደለትንና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ብቻ ቢሆን እንጂ ምልጃ አንድንም አትጠቅምም::"},{"id":110,"translation":"110. በስተፊታቸው ያለውንም ሆነ በስተኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል:: በእርሱ ላይ ግን ማንም በእውቀቱ አያካብብም::"},{"id":111,"translation":"111. ፊቶችም ሁሉ ህያውና የሁሉ አስተናባሪ ለሆነው አላህ ተዋረዱ:: በደልንም የተሸከመ በእርግጥ ከሰረ::"},{"id":112,"translation":"112. አማኝ ሆኖ መልካም ስራዎችን የሰራ በደልንም ሆነ መጉደልን አይፈራም::"},{"id":113,"translation":"113.ልክ እንደዚሁም ዐረብኛ ቁርኣን ሆኖ አወረድነው:: አላህን ይፈሩ ዘንድ ወይም ለእነርሱ ግሣጼን ያድስላቸው ዘንድ ከዛቻ ደጋግመን በውስጡ ገለጽን::"},{"id":114,"translation":"114. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውነተኛው ንጉስ አላህ ከሓዲያን ከሚሉት ነገር ሁሉ ላቀ:: ወደ አንተ መወረዱም ከመፈጸሙ በፊት ቁርኣንን በማንበብ አትቸኩል:: «ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ጨምርልኝ።» በልም።"},{"id":115,"translation":"115. ወደ አደምም ከዚህ በፊት ቃል ኪዳንን በእርግጥ አወረድንና ረሳ:: ለእርሱም ቆራጥነትን አላገኘንለትም::"},{"id":116,"translation":"116.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ።» ባልን ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: እነርሱም ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር ሰገዱ:: እሱማ እምቢ አለ::"},{"id":117,"translation":"117.ከዚያም አልን: «አደም ሆይ! ይህ ላንተም ለሚስትህም በእርግጥ ጠላት ነው:: ስለዚህ ከገነት አያውጣችሁ፤ ትለፋለህና::"},{"id":118,"translation":"118.(አደም ሆይ!) «ላንተ በእርሷ ውስጥ አለመራብና አለመታረዝ አለህ::"},{"id":119,"translation":"119. «አንተም ከእርሷ ውስጥ አትጠማም:: በጸሐይም አትተኮስም።»"},{"id":120,"translation":"120. ሰይጣን ወደ እርሱ (አደም) « አደም ሆይ! በመዘውተሪያ ዛፍ በማይጠፋ ንግስናም ላይ ላመላክትህን?» በማለት ጎተጎተ።"},{"id":121,"translation":"121.ከእርሷም በሉ:: ለእነርሱም ሀፍረተ ገላቸው ተገለጸች:: ከገነትም ቅጠል በላያቸው ላይ ይለጥፉ ጀመር:: አደምም የጌታውን ትእዛዝ ረስቶ ጣሰ:: ተሳሳተም::"},{"id":122,"translation":"122. ከዚያም ጌታው መረጠው:: ከእርሱም ጸጸቱን ተቀበለው:: መራዉም::"},{"id":123,"translation":"123.አላህም አላቸው፡- «ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲሆን (አደምና ሐዋ) ሁላችሁም ከእርሷ ውረዱ:: ከእኔ የሆነ መመሪያ ቢመጣላችሁ መመሪያየን የተከተለ ሁሉ አይሳሳትም:: አይቸገርምም::"},{"id":124,"translation":"124. «ከግሳጼዬ የዞረ ግን በዚህች ዓለም ጠባብ ኑሮ አለው:: በትንሳኤ ቀንም ዕውር ሆኖ እንቀሰቅሰዋለን::»"},{"id":125,"translation":"125. «ጌታዬ ሆይ! ለምን ዕውር አድርገህ አስነሳኸኝ:: በእርግጥ የማይ የነበርኩ ስሆን» አለ።"},{"id":126,"translation":"126. «ነገሩ ልክ እንደዚሁ ነው:: ተዓምራቶቻችን መጡልህና ተውካቸውም:: ልክ እንደዚሁም ዛሬ ትተዋለህ።» ይለዋል።"},{"id":127,"translation":"127.እንደዚሁም ያጋራንና በጌታው አናቅጽ ያላመነን እንቀጣዋለን:: የመጨረሻይቱ ዓለም ቅጣት በጣም ብርቱና ለሁልጊዜም ዘውታሪ ነው::"},{"id":128,"translation":"128. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ቁረይሾች) ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙዎችን ያጠፋን መሆናችን በመኖሪያዎቻቸው የሚሄዱ ሆነው ሳሉ ለእነርሱ አልተገለጸላቸዉምን? በዚህ ውስጥ ለአእምሮ ባለቤቶች በእርግጥ መልዕክቶች አሉበት::"},{"id":129,"translation":"129.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ያለፈች ቃልና የተወሰነ ጊዜ ባልነበረ ኖሮ ቅጣቱ አሁኑኑ የሚይዛቸው ይሆን ነበር::"},{"id":130,"translation":"130. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) በሚሉትም ሁሉ ላይ ታገሥ፤ ጌታህንም ጸሐይ ከመውጣቷ በፊትና ከመግባቷም በፊት የምታመሰግን ሆነህ አጥራው:: ከሌሊት ሰዓቶችም በቀን ጫፎችም አጥራው:: በሚሰጥህ ምንዳ ልትወድ ይከጀላልና::"},{"id":131,"translation":"131.ዐይኖችህን ከሰዎች የተወሰኑ ክፍሎችን ልንፈትናቸው ወደ አጣቀምንበት ወደ ቅርቢቱ ህይወት ጌጦች አትዘርጋ:: የጌታህ ሲሳይ በጣም በላጭና ዘውታሪ ነው።"},{"id":132,"translation":"132.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቤተሰብህንም በሶላት ላይ እዘዝ:: አንተም በእርሷ ላይ ዘውትር:: ሲሳይን አንጠይቅህም:: እኛ እንሰጥሃለን:: መልካሚቱ መጨረሻ ለጥንቁቆቹ ናት::"},{"id":133,"translation":"133. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተከራካሪዎችህ «ከጌታው በሆነ ተዓምር አይመጣምን?» አሉ:: በመጀመሪያዎቹ ጹሁፎች ውስጥ ያለችው ማስረጃ አልመጣቻቸዉምን?"},{"id":134,"translation":"134. እኛም (ከሙሐመድ መላክ) በፊት በቅጣት ባጠፋናቸው ኖሮ «ጌታችን ሆይ! ከመዋረዳችንና ከማፈራችን በፊት አናቅጽህን እንከተል ዘንድ ወደኛ መልዕክተኛን አትልክልንም ነበርን?» ባሉ ነበር::"},{"id":135,"translation":"135. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁሉም ተጠባባቂ ነው:: ተጠባበቁም የቀጥታዉም መንገድ ባለቤቶች እነማን እንደ ሆኑ እነማንም እንደ ተመሩ ወደፊት ታውቃላችሁ።» በላቸው::"}]},{"id":21,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ለሰዎች እነርሱ በዝንጋታ ውስጥ መሰናዳትን የተዉ ሆነው ሳሉ ምርመራቸው ቀረበ::"},{"id":2,"translation":"2. ከጌታቸው አዲስ የተወረደ ቁርኣን አይመጣላቸዉም:: እነርሱ የሚያላግጡበት ሆነው ፤ የሚያዳምጡት ቢሆኑ እንጂ::"},{"id":3,"translation":"3.ልቦቻቸው ዝንጉዎች ሆነው። እነዚያም የበደሉት ሰዎች መንሾካሾክን ደበቁ:: «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ ነውን? እናንተም የምታዩ ስትሆኑ ድግምትን ለመቀበል ትመጣላችሁን?» አሉ።"},{"id":4,"translation":"4. (ሙሐመድም) «ጌታዬ ቃልን ሁሉ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለ ሲሆን ያውቃል:: እርሱም ሰሚና አዋቂ ነው።» አለ።"},{"id":5,"translation":"5. በእውነቱ «ቁርኣኑ የሕልሞች ቅዠቶች ነው። ይልቁንም ቀጠፈው፤ እንዲያዉም እርሱ ቅኔን ገጣሚ ነው:: የቀድሞዎቹም እንደ ተላኩ ሁሉ መልዕክተኛ ከሆነ በተዓምር ይምጣብን።» አሉ።"},{"id":6,"translation":"6. ከእነርሱ በፊት ያጠፋናት ከተማ አላመነችም:: ታዲያ እነርሱ ያምናሉን?"},{"id":7,"translation":"7.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአንተም በፊት ወደእነሱ የምናወርድላቸው የኾነን ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም፡፡ የማታውቁ ከሆናችሁ የመጽሐፉን ባለቤቶች ጠይቁ::"},{"id":8,"translation":"8.ምግብን የማይበላ አካልም አላደረግናቸዉም:: ዘውታሪዎችም አልነበሩም::"},{"id":9,"translation":"9.ከዚያ ቀጠሮን ሞላንላቸውና እነርሱንና የምንሻውን ሰው አዳንናቸዉም:: ወሰን አላፊዎችንም አጠፋን::"},{"id":10,"translation":"10. (ሙስሊሞች ሆይ!) ክብራችሁ በውስጡ ያለበትን መጽሐፍ ወደእናንተ በእርግጥ አወረድን፡፡ አታውቁምን?"},{"id":11,"translation":"11. በዳይም ከነበረች ከተማ ያጠፋናትና ከኋላዋም ሌሎችን ህዝቦች ያስገኘነው ብዙ ናት::"},{"id":12,"translation":"12. ቅጣታችንም በተሰማቸው ጊዜ እነርሱ ወዲያውኑ ከርሷ ለመሸሽ ይገሰግሳሉ።"},{"id":13,"translation":"13. «አትገስግሱ፤ ትጠየቁም ይሆናልና በእርሱ ወደ ተቀማጠላችሁበት ጸጋ ወደ መኖሪያዎቻችሁም ተመለሱ።» ይባላሉ።"},{"id":14,"translation":"14. «ዋ ጥፋታችን! እኛ በእርግጥ በዳዮች ነበርን።» ይላሉ።"},{"id":15,"translation":"15.የታጨዱ ሬሳዎችም እስካደረግናቸው ድረስ ይህቺ ጥሪያቸው ከመሆን አልተወገደችም::"},{"id":16,"translation":"16. ሰማይንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ሆነን አልፈጠርንም::"},{"id":17,"translation":"17.መጫዎቻን (ሚስትንና ልጅን) ልንይዝ በሻን ኖሮ ከኛ ዘንድ በያዝነው ነበር፤ ግን ሰሪዎች አይደለንም።"},{"id":18,"translation":"18. በእርግጥ እውነትን በውሸት ላይ እንጥላለን:: አንጎሉን ያፈርሰዋልም:: ወዲያዉም እርሱ ጠፊ ነው:: ለእናንተም ከዚያ (ሚስትና ልጅ) አለው በማለት ከምትመጥኑት ነገር ብርቱ ቅጣት አላችሁ:: (ወዮላችሁ)።"},{"id":19,"translation":"19. በሰማያትና በምድር ዉስጥ ያለው ሁሉም የእርሱ ብቻ ነው:: እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም:: አይሰለቹምም።"},{"id":20,"translation":"20. በበሌሊትና በቀንም ያጠሩታል:: አይታክቱም።"},{"id":21,"translation":"21. ይልቁንም ከምድር የሆኑን ሙታንን የሚያስነሱ አማልክትን ያዙን? የለም።"},{"id":22,"translation":"22.በሰማያትና በምድር ውስጥ ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ ሁለቱም በተበላሹ ነበር:: የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ::"},{"id":23,"translation":"23. አላህ ከሚሰራው ሁሉ አይጠየቅም:: እነርሱ (ፍጥረቶቹ) ግን ይጠየቃሉ::"},{"id":24,"translation":"24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም ከርሱ ሌላ አማልክትን ያዙን? «አስረጃችሁን አምጡ:: ይህ ቁርኣን እኔ ዘንድ ያለው ህዝብ መገሰጫ፤ ከኔ በፊትም የነበሩት ህዝቦች መገሠጫ ነው።» በላቸው:: እንዲያዉም አብዛኞቻቸው እውነቱን አያውቁም:: ስለዚህ እነርሱ እንቢተኞች ናቸው::"},{"id":25,"translation":"25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጂ ከመልዕክተኛ አንድንም አላክንም::"},{"id":26,"translation":"26. «አር-ረሕማንም ከመላእክት መካከል ልጅን ያዘ።» አሉ። ጥራት ተገባው። አይደለም መላእክት የተከበሩ ባሮች ብቻ ናቸው።"},{"id":27,"translation":"27. በንግግር አይቀድሙትም፤ ያዘዘውንም ይፈጽማሉ።"},{"id":28,"translation":"28.በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል:: ለወደደውም እንጂ ለሌላው አያማልዱም:: እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው::"},{"id":29,"translation":"29. ከእነርሱም «እኔ ከእርሱ ሌላ አምላክ ነኝ።» የሚል ያንን ገሀነምን እንመነዳዋለን፤ በዳዮችን እንደዚሁ እንመነዳለን።"},{"id":30,"translation":"30. እነዚያም በአላህ የካዱ ሰዎች ሰማያትና ምድር የተጣበቁ የነበሩና የለያየናቸው መሆናችንን አያውቁምን? ህያው የሆነንም ነገር ሁሉ ከውሃ ፈጠርን። አያምኑምን?"},{"id":31,"translation":"31. በምድርም ውስጥ በእነርሱ እንዳታረገርግ ጋራዎችን አደረግን። ይመሩም ዘንድ በእርሷ ውስጥ ሰፋፊ መንገዶችን አደረግን።"},{"id":32,"translation":"32. ሰማይንም ከመውደቅ የተጠበቀ ጣራ አደረግን:: እነርሱ ግን ከተዓምራቱ ዘንጊዎች ናቸው::"},{"id":33,"translation":"33.እርሱም ሌሊትንና ቀንን ጸሐይንና ጨረቃንም የፈጠረ ነው:: ሁሉም በየ ምህዋራቸው (ፈለካቸው) ውስጥ ይዋኛሉ::"},{"id":34,"translation":"34. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረግንም:: ታዲያ ብትሞት እነርሱ ዘውታሪዎች ናቸውን?"},{"id":35,"translation":"35.(ሰዎች ሆይ!) ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት:: ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን:: ወደ እኛም ትመለሳላችሁ::"},{"id":36,"translation":"36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ የካዱት ሰዎች ባዩህ ጊዜ መሳለቂያ አድርገው እንጂ አይዙህም። እነርሱ በአር-ረህማን መወሳት እነርሱ ከሓዲያን ሲሆኑ: «ያ አማልክቶቻችሁን በክፉ የሚያነሳቸው ይህ ነውን?» ይላሉ።"},{"id":37,"translation":"37. ሰው ቸኳይ ሆኖ ተፈጠረ:: ታዓምራቶቼን በእርግጥ አሳያችኋለሁና አታቻኩሉኝ::"},{"id":38,"translation":"38. «እውነተኞች ከሆናቸሁ ይህ ቀጠሮም መቼ ነው?» ይላሉ።"},{"id":39,"translation":"39.እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች ከፊቶቻቸውና ከጀርቦቻቸው ላይ እሳትን የማይከለክሉበትን እነርሱም የማይረዳዱበትን ጊዜ ቢያውቁ ኖሮ ይህንን አይሉም ነበር::"},{"id":40,"translation":"40. ይልቁንም ሰዓቲቱ በድንገት ትመጣቸዋለች:: ታስደነግጣቸዋለችም:: መመለሷንም አይችሉም:: እነርሱም የሚቆይላቸው አይደሉም።"},{"id":41,"translation":"41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም የነበሩት መልዕክተኞች በእርግጥ ተቀለደባቸው፤ በእነዚያ ከእነርሱ ይቀልዱ በነበሩት ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት ሰፈረባቸው።"},{"id":42,"translation":"42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከአር-ረህማን ቅጣት በሌሊትና በቀን የሚጠብቃችሁ ማነው?» በላቸው:: በእውነቱ እነርሱ ከጌታቸው ግሠጼ ከቁርኣን ዘንጊዎች ናቸው::"},{"id":43,"translation":"43.ለእነርሱ ከእኛ ሌላ የምትከላከልላቸው አማልዕክት አለቻቸውን? ነፍሶቻቸውን መርዳትን አይችሉም:: እነርሱም (ከሓዲያኑ) ከእኛ አይጠብቁም።"},{"id":44,"translation":"44.በእውነትም እነዚህንና አባቶቻቸውን በእነርሱ ላይ ዕድሜ እስከ ረዘመባቸው ድረስ አጣቀምናቸው:: ተታለሉም። እኛ ምድርን ከጫፎቿ የምናጎድላት ሆነን ስንመጣባት አያዩምን? እነርሱ አሸናፊዎች ናቸውን?"},{"id":45,"translation":"45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የማስፈራራችሁ በተወረድልኝ ብቻ ነው። ግን ደንቆሮዎች በሚስፈራሩበት ጊዜ ጥሪን አይሰሙም።» በላቸው።"},{"id":46,"translation":"46. ከጌታህ ቅጣትም ወላፈን ብትነካቸው «ዋ ጥፋታችን! እኛ በዳዮች ነበርን።» ይላሉ።"},{"id":47,"translation":"47.በትንሳኤ ቀን ትክክለኛ ሚዛኖችን እናቆማለን:: ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም:: ስራው የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ቢሆንም እርሷን እናመጣታለን:: ተቆጣጣሪነትም በእኛ በቃ::"},{"id":48,"translation":"48. ለሙሳና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንን ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ ሰጠናቸው::"},{"id":49,"translation":"49. ለእነዚያ ጌታቸውን በሩቅ ለሚፈሩት እነርሱም ከሰዓቲቱ ተጨናቂዎች ለሆኑት መገሰጫን ሰጠን::"},{"id":50,"translation":"50.ይህም (ቁርኣን) ያወረድነው የኾነ ብሩክ መገሰጫ ነው፡ ታዲያ እናንተ ለእርሱ ከሓዲያን ናችሁን?"},{"id":51,"translation":"51. ለኢብራሂምም ከዚያ በፊት ቅን መንገዱን በእርግጥ ሰጠነው:: እኛም በእርሱ ተገቢነት አዋቂዎች ነበርን::"},{"id":52,"translation":"52. ለአባቱና ለህዝቦቹ፡- «ይህቺ ቅርጻ ቅርጽ ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የሆናችኃት ምንድን ናት?» ባለ ጊዜ መራነው።"},{"id":53,"translation":"53. «አባቶቻችንን ለእርሷ ተገዢዎች ሆነው አገኘን።» አሉት።"},{"id":54,"translation":"54. «እናንተም አባቶቻችሁም በእርግጥ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበራችሁ።» አላቸው።"},{"id":55,"translation":"55. «በምሩ መጣህልን? ወይንስ አንተ ከሚቀልዱት ነህ?» አሉት።"},{"id":56,"translation":"56. (እርሱም) አለ: «አይደለም። ጌታችሁ የሰማያትና የምድር ጌታ ያ የፈጠራቸው ነው:: እኔም በይሃችሁ ላይ ከመስካሪዎች ነኝ።"},{"id":57,"translation":"57. «በአላህ እምላለሁ ዟሪዎች ሆናችሁ ከሄዳችሁ በኋላ ጣዖቶቻችሁን ተንኮል እሰራባቸዋለሁ።» አለ።"},{"id":58,"translation":"58. ዘወር ሲሉም ስብርብሮች አደረጋቸው:: ለእነርሱ የሆነ አንድ ትልቅ ጣዖት ብቻ ሲቀር :: ወደ እርሱ ይመለሱ ዘንድ እርሱን ብቻ ተወው።"},{"id":59,"translation":"59. «በአማልክቶቻችን ይህንን የሰራ ማነው? እርሱ በእርግጥ ከበደለኞች ነው።» አሉ።"},{"id":60,"translation":"60. «ኢብራሂም የሚባል ጎበዝ (ወጣት) በመጥፎ ሲያነሳቸው ሰምተናል።» ተባባሉ።"},{"id":61,"translation":"61. «ይመሰክሩበት ዘንድ በሰዎች ዓይን ፊት ላይ አምጡት።» አሉ።"},{"id":62,"translation":"62. «ኢብራሂም ሆይ! በአማልክቶቻችን ይህንን የሰራህ አንተ ነህን?» አሉት።"},{"id":63,"translation":"63. «አይደለም:: ይህ ትልቃቸው ሰራው፤ ይናገሩም እንደ ሆነ ጠይቋቸው።» አለ።"},{"id":64,"translation":"64. ወደ ነፍሶቻቸዉም ተመለሱ: «እናንተ በመጠየቃችሁ በዳዮቹ እናንተው ናችሁ።» ተባባሉም።"},{"id":65,"translation":"65. ከዚያም በራሶቻቸው ላይ ተገለበጡና «እነዚህ የሚናገሩ አለመሆናቸውን በእርግጥ አውቀሃል።» አሉ።"},{"id":66,"translation":"66.ኢብራሂምም አላቸው: «ታዲያ ለእናንተ ብታመልኳቸው ምንም የማይጠቅማችሁንና ባታመልኳቸዉም በምንም ነገር የማይጎዳችሁን ጣዖታትን ከአላህ ሌላ ትገዛላችሁን?"},{"id":67,"translation":"67. «ኡፍ! ለእናንተም ሆነ ከአላህ ሌላ ለምትገዙት ጣዖታት። አታስተውሉምን?» አለ።"},{"id":68,"translation":"68. «ሰሪዎች (ተቆርቋሪዎች) እንደ ሆናችሁ ኢብራሂምን በእሳት አቃጥሉት አማልክቶቻችሁንም እርዱ።» አሉ:: (በእሳት ላይ ጣሉትም።)"},{"id":69,"translation":"69. «እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛና ሰላም ሁኚ።» አልን።"},{"id":70,"translation":"70. በእርሱም ተንኮልን አሰቡ። በጣም ከሳሪዎች አደረግናቸው።"},{"id":71,"translation":"71. እርሱንና ሉጥንም ወደዚያች በውስጡ ለዓለማት በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር በመውሰድ አዳንናቸው::"},{"id":72,"translation":"72.ለእርሱም ኢስሐቅን ያዕቆብንም ተጨማሪ አድርገን ሰጠነው:: ሁሉንም መልካሞች አደረግን::"},{"id":73,"translation":"73. በትእዛዛችንም ወደ በጎ ስራ የሚመሩ መሪዎች አደረግናቸው:: ወደነሱም መልካም ስራዎችን መስራትን፤ ሶላትንም መስገድን ዘካንም መስጠትን አወረድን:: ለእኛም ተገዢዎች ነበሩ::"},{"id":74,"translation":"74. ሉጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው:: ከዚያችም መጥፎ ስራዎችን ትሰራ ከነበረችው ከተማ አዳንነው:: እነርሱ ክፉ ሰዎች አመጸኞች ነበሩና::"},{"id":75,"translation":"75. በችሮታችንም ውስጥ አስገባነው:: እርሱ ከመልካሞች አንዱ ነውና::"},{"id":76,"translation":"76.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኑሕንም ከዚያ በፊት ጌታውን በጠራ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፤ እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳን::"},{"id":77,"translation":"77.ከእነዚያም በታዓምራቶቻችን ከአስተባበሉት ህዝቦች ተንኮል ጠበቅነው:: እነርሱ ክፉ ህዝቦች አመጸኞች ነበሩና ሁሉንም አሰመጥናቸዉም::"},{"id":78,"translation":"78.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ ! ) ዳውድንና ሱለይማንንም በአዝመራው ነገር በሚፈርዱ ጊዜ የህዝቦቸ ፍየሎች ሌሊት በእርሱ ውስጥ በተሰማሩ ጊዜ አስታውስ:: ፍርዳቸውንም አዋቂዎች ነበርን::"},{"id":79,"translation":"79. ለሱለይማንም ትክክለኛይቱን ፍርድ አሳወቅነው:: ለሁሉም ጥበብንና እውቀትን ሰጠን:: ተራራዎችን ከዳውድ ጋር የሚያወድሱ ሲሆን ገራን፤ አእዋፍንም እንደዚሁ ገራን ሰሪዎችም ነበርን።"},{"id":80,"translation":"80.የብረት ልብስንም ስራ ለእናንተ ከጦራችሁ ትጠብቃችሁ ዘንድ አስተማርነው:: እናንተ አመስጋኞች ናችሁን?"},{"id":81,"translation":"81. ለሱለይማንም ነፋስን በኃይል የምትነፍስ በትእዛዙ ወደዚያች በእርሷ ውስጥ በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር (ወደ ሻም) የምትነፍስ ስትሆን (ገራንለት) በነገሩ ሁሉም አዋቂዎች ነበርን::"},{"id":82,"translation":"82.ከሰይጣናትም ለእርሱ (ሉልን ለማውጣት) የሚጠልሙንና ከዚያ ሌላ ያለን ስራ የሚሰሩን ገራንለት፤ ለእነርሱም ተጠባባቂዎች ነበርን::"},{"id":83,"translation":"83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አዩብንም ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ:: አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ።» ሲል በተጣራ ጊዜ የሆነውን አስታውስ።"},{"id":84,"translation":"84. ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፤ ከጉዳትም በእርሱ ላይ የነበረውን ሁሉ አስወገድን:: ቤተሰቦቹንም ከእነርሱም ጋር መሰላቸውን ከእኛ ዘንድ ለችሮታና ለተገዢዎች ለማስገንዘብ ሰጠነው::"},{"id":85,"translation":"85. ኢስማዒልንም፤ ኢድሪስንም፤ ዙልኪፍልንም፤ አስታውስ:: ሁሉም ከታጋሾች ናቸው::"},{"id":86,"translation":"86. በችሮታችንም ውስጥ አስገባናቸው:: እነርሱ ከመልካሞቹ ናቸውና::"},{"id":87,"translation":"87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በሄደ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መሆናችንን ጠረጠረ:: ዓሳም ዋጠው:: በጨለማዎችም ውስጥ ሆኖ «ካንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም ጥራት ይገባህ:: እኔ በእርግጥ ከበዳዮች ነበርኩ።» በማለት ተጣራ።"},{"id":88,"translation":"88. ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው:: ከጭንቅም አዳነው:: ልክ እንደዚሁም ምዕምናንን እናድናለን::"},{"id":89,"translation":"89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ዘከሪያንም «ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ:: አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ።» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ አስታውስ።"},{"id":90,"translation":"90. ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው:: ለእርሱም የህያን ሰጠነው:: ለእርሱም ሚስቱን አበጀንለት:: እነርሱ በበጎ ስራዎች የሚቻኮሉ ከጃዮችና ፈሪዎች ሆነው የሚለምኑንም ነበሩ:: ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ::"},{"id":91,"translation":"91.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያችንም ብልቷን (ከዝሙት) የጠበቀችውንና በእርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን የነፋንባትን እርሷንም ሆነ ልጇን ለዓለማት ተዓምር ያደረግናትን መርየምን አስታውስ::"},{"id":92,"translation":"92. እነዚህ ህግጋት አንድ መንገድ ሲሆኑ በእርግጥ የሃይማኖታችሁ ህግጋት ናቸው:: እኔም ጌታችሁ ነኝና ተገዙኝ::"},{"id":93,"translation":"93.በሃይማኖታቸዉም ነገር በመካከላቸው ተለያዩ:: ሁሉም ወደ እኛ ተመላሾች ናቸው::"},{"id":94,"translation":"94. እርሱ ያመነ ሆኖ ከበጎ ስራዎች ማንኛውንም የሚሰራም ምንዳውን አይነፍግም፤ እኛም ለእርሱ መዝጋቢዎች ነን::"},{"id":95,"translation":"95. ባጠፋናትም ከተማ ላይ ዘበት ነው፤ (ወደ ዱኒያ) አይመለሱምና።"},{"id":96,"translation":"96.የዕጁጅና መዕጁጅም እነርሱ ከየሸንተረሩ የሚንደረደሩ ሲሆኑ ግድባቸው በተከፈተች ጊዜ ፤"},{"id":97,"translation":"97. እውነተኛዉም ቀጠሮ በቀረበ ጊዜ ያንን ጊዜ እነሆ የእነዚያ ከሀዲያን ዓይኖች ይፈጥጣሉ:: «ዋ ጥፍታችን! ከዚያ ቀን በእርግጥ በዝንጋቴ ላይ ነበርን:: በእውነትም በዳዮች ነበርን።» ይላሉ።"},{"id":98,"translation":"98. (ከሓዲያን ሆይ!) እናንተና ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣዖታት የገሀነም ማገዶዎች ናችሁ:: እናንተ ለእርሷ ወራጆች ናችሁ::"},{"id":99,"translation":"99.እነዚህ ጣዖታት አማልክት በነበሩ ኖሮ ገሀነምን አይገቧትም ነበር:: ግን ሁሉም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::"},{"id":100,"translation":"100.እነርሱ በእርሷ ውስጥ ይንሰቀሰቃሉ:: እነርሱም በውስጧ ምንንም አይሰሙም::"},{"id":101,"translation":"101. እነዚያ ከእኛ መልካሟ ቃል ለእነርሱ ያለፈችላቸው እነዚያ ከእርሷ የተራቁ ናቸው::"},{"id":102,"translation":"102. ድምጿንም አይሰሙም:: እነርሱም ነፍሶቻቸው በሚሹት ነገር ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::"},{"id":103,"translation":"103. ታላቁ ድንጋጤ አያስተክዛቸዉም:: መላእክትም «ይህ ያ ! ትቀጠሩት የነበራችሁት ቀናችሁ ነው።» እያሉ ይቀበሏቸዋል።"},{"id":104,"translation":"104. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመጽሐፎች ገፆች እንደሚጠቀለሉ ሁሉ ሰማይን የምንጠቀልልበትን ቀን አስታውስ:: የመጀመሪያን ፍጥረት እንደ ጀመርን እንመልሰዋለን:: ይህን መፈጸሙ የማይቀር ቀጠሮን ቀጠርን:: እኛ የቀጠርነውን ሰሪዎች ነን::"},{"id":105,"translation":"105. ምድርንም መልካሞቹ ባሮቼ ይወርሷታል ማለትን ከመጽሐፉ (ከተጠበቀው ሰሌዳ) በኋላ በመጽሐፎች በእርግጥ ጽፈናል::"},{"id":106,"translation":"106.በዚህ ቁርኣን ውስጥ ያሉት ህግጋት ለአላህ ተገዢ ህዝቦች ሁሉ በቂ ናቸው።"},{"id":107,"translation":"107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማት እዝነት አድርገን እንጂ አልላክንህም::"},{"id":108,"translation":"108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያ ወደ እኔ የሚወርደው መልዕክት ‹አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው።› የሚል ነው:: ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን?» በላቸው።"},{"id":109,"translation":"109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እምቢ ቢሉም (እንዲህ) በላቸው: «የታዘዝኩትን በእኩልነት አሳውቂያችኋለሁ:: የምትስፈራሩበትም ነገር ቅርብ ወይም ሩቅ መሆኑን አላውቅም።"},{"id":110,"translation":"110. «እርሱ ከንግግር ጩኸቱን ያውቃል:: የምትደብቁትንም ሁሉ ያውቃል::"},{"id":111,"translation":"111. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እርሱም ቅጣትን ማቆየት ምናልባት ለእናንተ ፈተናና እስከ ጊዜው መጣቀሚያ እንደ ሆነም አላውቅም።» በላቸው::"},{"id":112,"translation":"112. «ጌታዬ ሆይ! በእውነት ፍረድ:: ጌታችንም እጅግ በጣም ሩህሩህን በምትሉት ነገር ላይ መታገዣ ነው።» አለ::"}]},{"id":22,"verses":[{"id":1,"translation":"1.እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን (አላህን) ፍሩ:: የሰዓቲቱ እንቅጥቃጤ በጣም ከባድ ነገር ነውና::"},{"id":2,"translation":"2. በምታዩዋት ቀን ሁኔታው አጥቢ ሁሉ ያጠባችውን ልጅ ትዘነጋዋለች። እርጉዝ ሴት ሁሉ እርጉዝዋን ትጨነግፋለች:: ሰዎቹንም በድንጋጤ ብርታት የሰከሩ መስለው ታያቸዋለህ:: እነርሱ ከመጠጥ የሰከሩ ሁው ሳይሆን ግን የአላህ ቅጣት ብርቱ ስለሆነ ነው።"},{"id":3,"translation":"3. ከሰዎች መካከል ያለ ምንም ዕውቀት በአላህ ነገር የሚከራከር፤ ሞገደኛ ሰይጣንንም የሚከተል ሰው አለ::"},{"id":4,"translation":"4. እነሆ የተከተለውን ሰው እርሱ ያጠመዋል:: ወደ አቃጣይ እሳት ስቃይም ይመራዋል ማለት በእርሱ ላይ ተጽፏል:: (ተወስኖባቸዋል)"},{"id":5,"translation":"5. ሰዎች ሆይ! ከሞት በኋላ ከመቀስቀስ በመጠራጠር ጉዳይ እንደ ሆናችሁ የመጀመሪያውን (አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ። እኛም) ከአፈር ፈጠርናችሁ:: ከዚያ ከፍትወት ጠብታ፤ ከዚያም ከረጋ ደም፤ ከዚያም ከቁራጭ ስጋ ፍጥረትዋ ሙሉ ከሆነችና ሙሉ ካልሆነች (ችሎታችንን) ለእናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ። የምንሻውንም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ በማህጸን ውስጥ እናረጋዋለን። ከዚያም ህፃን ሆናችሁ እናወጣችኋለን:: ከዚያም ሙሉ ጥንካሪያችሁን ትደርሱ ዘንድ (እናሳድጋችኋለን):: ከናንተም መካከል በወጣትነቱ የሚሞት ሰው አለ:: ከናንተም መካከል ከዕውቀት በኋላ ምንንም ላያውቅ ወደ ጃጀ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አለ:: ምድርንም ደረቅ ሆና ታያታለህ:: በእርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ ትላወሳለች \\ትነቃነቃለች\\:: ትነፋለችም:: ውበት ካለው የእጽዋት አይነት ሁሉ ታበቅላለችም።"},{"id":6,"translation":"6. ይህ ሁሉ አላህ ፍፁም እውነት፤ እርሱም ሙታንን ህያው የሚያደርግ፤ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ በመሆኑ ነው።"},{"id":7,"translation":"7. የሰዓቲቱም መከሰት ፈጽሞ ጥርጣሬ የሌለበት በመሆኑና አላህ በመቃብሮች ውስጥ ያለን ሁሉ የሚቀሰቅስ በመሆኑም ነው።"},{"id":8,"translation":"8. ከሰዎች መካከል ያለ ምንም ዕውቀት ያለ አንዳች ማስረጃም ያለ አብራሪ መጽሐፍም ጎኑን ያጠፈ ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስት በአላህ ነገር የሚከራከር ሰው አለ::"},{"id":9,"translation":"9. ጎኑን ያጠፈ ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስት (ይከራከራል)። በቅርቢቱ ዓለም ለርሱ ውርደት አለው:: በትንሳኤ ቀንም አቃጣይን (የእሳት) ቅጣት እናቀምሰዋለን::"},{"id":10,"translation":"10. «ይህ እጆችህ ባስቀደሙት ኃጢአት ነው፣ አላህም ለባሮቹ ፈጽሞ በዳይ አይደለም።» (ይባላል።)"},{"id":11,"translation":"11. ከሰዎችም መካከል በሃይማኖት ጫፍ ላይ ሆኖ አላህን የሚገዛ ሰው አለ:: እናም መልካም ነገር ካገኘው በእምነቱ ላይ ይረጋል:: መከራ ካገኘው ግን በፊቱ ላይ ይገለበጣል (ይክዳል):: ይህ አይነቱ ሰው የቅርቢቱን ዓለምም ሆነ የመጨረሻይቱን ዓለም ከሰረ:: ይህ ነው ግልጽ ኪሳራ ማለት።"},{"id":12,"translation":"12. ከአላህ ሌላ የማይጎዳውንና የማይጠቅመውን ይገዛል:: ይህ እርሱ ከእውነት የራቀ ስህተት ነው::"},{"id":13,"translation":"13. ያንን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ወደ እሱ የሚቀርብን ይገዛል:: ረዳቱ ምንኛ ከፋ! ወዳጁም ምንኛ ከፋ!"},{"id":14,"translation":"14. አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትንና መልካም ስራዎችን የሰሩትን ሰዎች በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያስገባቸዋል:: አላህም የሚሻውን ነገር ሁሉ በእርግጥ ይሰራልና።"},{"id":15,"translation":"15. አላህ (መልዕክተኛውን) ሙሐመድን በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም አይረዳዉም ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ ገመድን ወደ ሰማይ ይዘርጋና ከዚያ (ትንፋሹ እስኪቆረጥ) ይታነቅ:: ይህ ተግባሩ ተንኮሉ የሚያስቆጨውን ነገር ያስወግደለት እንደሆነም ይመልከት።"},{"id":16,"translation":"16. ልክ እንደዚሁ (ቁርኣንን) የተብራሩ አናቅጽ አድርገን አወረድነው:: አላህ የሚሻውን ሁሉ ይመራልና።"},{"id":17,"translation":"17. እነዚያ በአላህ ያመኑ እነዚያ አይሁዳውያን፤ እነዚያ ምንም እምነት የሌላቸው ሳቢያኖች፤ ክርስቲያኖችም፤ መጁሶችም እነዚያም (ጣዖታትን በአላህ) ያጋሩ ሁሉ አላህ በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ በእርግጥ አዋቂ ነውና::"},{"id":18,"translation":"18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ጸሐይና፤ ጨረቃም፤ ከዋክብትም፤ ተራሮችም፤ ዛፎችም፤ ተንቀሳቃሾችም ፍጡራንና ከሰዎች ብዙዎችም ለእርሱ የሚሰግዱለት መሆኑን አታውቅምን? ብዙዉም በእርሱ ላይ የአላህ ቅጣት ተረጋገጠበት:: አላህ የሚያዋርደው ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለዉም:: አላህ የሻውን ይሰራልና:: {1}","footnotes":"{1} እዚህ የንባብ ሱጁድ (ሱጁዱ ትላዋ) ይደረጋል።"},{"id":19,"translation":"19. እነዚህ በጌታቸው ጉዳይ የተከራከሩ ሁለት ባላጋራዎች ናቸው:: እነዚያ በአላህ የካዱት የእሳት ልብሶች ተለክተውላቸዋል፤ እንዲቀልጥ ከራሶቻቸው ላይ የፈላ ውሃ ይምቧቧባቸዋል።"},{"id":20,"translation":"20. በሆዶቻቸው ውስጥ ያለውና ቆዳዎቻቸው በእርሱ ይቀለጣል::"},{"id":21,"translation":"21. ለእነርሱም (መቅጫ) ከብረት የሆኑ መዶሻዎች አሉ::"},{"id":22,"translation":"22. ከጭንቀት ብርታት የተነሳ ከእርሷ ለመውጣት በፈለጉ ቁጥር በእርሷ ውስጥ እንዲመለሱ ይደረጋሉ። «ያን በጣም የሚያቃጥለውን ቅጣት ቅመሱ።» (ይባላሉ።)"},{"id":23,"translation":"23. አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትንና መልካም ስራዎችን የሰሩትን ሰዎች በስሮቻቸው ጅረት ወንዞች በሚፈሱባቸው ገነቶች ያስገባቸዋል:: በእርሷ ውስጥ የወርቅ አንባሮችና ሉልን ይሸለማሉ:: በእርሷ ውስጥ ልብሶቻቸዉም ከሐር የተሰሩ ናቸው::"},{"id":24,"translation":"24. ወደ መልካም ንግግር ተመሩ፣ ወደ ምስጉን መንገድም ተመሩ።"},{"id":25,"translation":"25. እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎችን ከአላህ መንገድና ከዚያም በውስጡ ነዋሪ ለሆኑትም ሆነ ከሩቅ ለሚመጡት (ሰዎች) እኩል ካደረግነው ከተከበረው መስጊድ የሚከለክሉ ሁሉ (አሳማሚ ቅጣት እንቀጣቸዋልን::) በእርሱም ውስጥ ከትክክለኛ መንገድ በመዘንበል ራሱን በዳይ ሆኖ (ማንኛውንም ነገር) የሚያስብ ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን::"},{"id":26,"translation":"26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለኢብራሂም የቤቱን የከዕባን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት (እንዲህ) ባልነውም ጊዜ (የሆነውን አስታውስ): «በኔ ምንንም አታጋራ:: ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት (ለኢባዳ) ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸዉም ለሚደፉት (ሩኩዕና ሱጁድ ለሚያደርጉት) ንጹህ አድርግላቸው።"},{"id":27,"translation":"27. «ኢብራሂም ሆይ! በሰዎች መካከል የሐጅን ትእዛዝ አሰማ:: እግረኞችና ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎች ሁሉ ላይም ሆነዉም ይመጡልሃልና።"},{"id":28,"translation":"28. «ለእነርሱ የሆኑ ጥቅሞችን ያገኙ ዘንድና በእነዚያ በታወቁ ቀናትም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ ይመጡልሃል:: ከእርሷም ብሉ:: ችግረኛ ድሀንም አብሉ።"},{"id":29,"translation":"29. «ከዚያም (እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን) ትርፍ አካላቸውንና እድፋቸውን ያስወግዱ:: ስለቶቻቸውንም በትክክል ይሙሉ:: በጥንታዊዉም ቤት በካዕባ ዙሪያ ይዙሩ።» አልን።"},{"id":30,"translation":"30. ይሀው ነው። የአላህንም ህግጋት የሚያከብር ሁሉ እርሱ እጌታው ዘንድ ለእርሱ በጣም የተሻለ መልካም ነው:: የቤት እንስሳትም በእናንተ ላይ እርም መሆኑ ከሚነበብላችሁ በስተቀር ለእናንተ ተፈቅዳላችኋለች:: ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ:: ሐሰትንም ቃል ራቁ::"},{"id":31,"translation":"31. ለአላህ ታዛዦች፤ በእርሱ የማታጋሩና ወደ ቀጥተኞች መንገድ የተዘነበላችሁ ሁኑ:: በአላህ የሚያጋራ ሁሉ ከሰማይ እንደ ወደቀና በራሪ እንደምትነጥቀው ወይም ንፋስ በሩቅ ስፍራ እንደምትጥለው ነው::"},{"id":32,"translation":"32. (ነገሩ) ይህ ነው። የአላህን ሃይማኖታዊ ምልክቶች የሚያከብር ሁሉ ይህ ድርጊቱ አላህን ከሚፈሩ ልቦች የሚፈጸም ጥንቃቄ ነው።"},{"id":33,"translation":"33. ለእናንተ በእርሷ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ጥቅሞች አሏችሁ:: ከዚያም የ(ኡዱሂያ)ማረጃ ስፍራ እጥንታዊው ቤት አጠገብ ነው::"},{"id":34,"translation":"34. ከቤት እንስሳት በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ብቻ ያወሱ ዘንድ ለህዝቦች ሁሉ (ወደ አላህ) መስዋዕት ማቅረብን ሀይማኖታዊ ሥርአቶችን ደነገግን:: አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እርሱንም ብቻ ታዘዙ:: ለአላህ ተዋራጆችንም በመልካም ነገር አብስራቸው::"},{"id":35,"translation":"35. እነዚያን አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚጨነቁትን (የሚፈሩትን)፤ በደረሰባቸዉም መከራ ላይ ታጋሾችን፤ ሰላትንም አስተካክለው ሰጋጆችን፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ የሚለግሱትን በገነት አብስር::"},{"id":36,"translation":"36. ግመሎችንም ለእናንተ ከአላህ ሃይማኖት ምልክቶች አደረግናቸው:: በእነርሱ ለእናንተ ብዙ መልካም ጥቅሞች አሏችሁ:: በእርሷም ላይ ስታርዷት በሦስት እግሮቿ ቆማ የተሰለፈች ሆና የአላህን ስም አውሱ:: ጎኖቻቸዉም በወደቁ ጊዜ ከእርሷ ብሉ:: በግልጽ ለማኝንም ለልመና የሚያገዳድምንም አብሉ:: ልክ እንደዚሁ ታመሰግኑ ዘንድ ለእናንተ ገራናት::"},{"id":37,"translation":"37. አላህን ስጋዎቿም ሆኑ ደሞቿ ፈጽሞ አይደርሰዉም:: ግን ከእናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርሰዋል:: እንደዚሁ አላህን በመራችሁ ላይ ልታከብሩት ለእናንተ ገራት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጎ ሰሪዎችንም አብስር::"},{"id":38,"translation":"38. አላህ ከእነዚያ በእርሱ ካመኑት ላይ ይከላከልላቸዋል። አላህ ከዳተኛንና ውለታ ቢስን ሁሉ አይወድምና።"},{"id":39,"translation":"39. ለእነዚያ በከሓዲያን ለሚገደሉት ትክክለኛ አማኞች የተበደሉ በመሆናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው:: አላህ እነርሱን በመርዳት ላይ በእርግጥ ቻይ ነውና::"},{"id":40,"translation":"40. ለእነዚያ «ጌታችን አላህ ነው።» ከማለታቸው በስተቀር ያለ አግባብ ከየቀያቸው የተባረሩ ለሆኑት ከራሳቸው ላይ መከላከል ተፈቀደ:: አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ ባልነበረ ኖሮ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችና በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም በተፈረሱ ነበር:: አላህም ሃይማኖቱን የሚረዳውን ሁሉ በእርግጥ ይረዳዋል:: አላህ ብርቱና ሁሉን አሸናፊ ነውና::"},{"id":41,"translation":"41. እነርሱ ማለት እነዚያ በምድር ላይ ብናስመቻቸው (የበላይነትን ሰጥተን ባጎናጸፍናቸው ኖሮ) ሶላትን እንደሚገባ የሚያስተካክሉ፤ ዘካንም የሚሰጡ፤ በደግ ነገርም የሚያዝዙ፤ ከመጥፎ ነገርም የሚከለከሉ ናቸው:: የነገሮች ሁሉ መጨረሻ ወደ አላህ ብቻ ነው::"},{"id":42,"translation":"42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ከእነርሱ በፊት የኑሕ ህዝቦች፣ የዓድና የሰሙድም በእርግጥ አስተባብለዋል።"},{"id":43,"translation":"43. የኢብራሂምም ህዝቦች የሉጥም ህዝቦች እንደዚሁ አስተባብለዋል፤"},{"id":44,"translation":"44. የመድየንም ሰዎች እንዲሁ አስተባብለዋል:: ሙሳም ተስተባብሏል:: ለከሓዲያንም ጊዜን ሰጠኋቸው:: ከዚያ ያዝኳቸው። ጥላቻዬም እንዴት ነበረ (ተመልከቱ)።"},{"id":45,"translation":"45. ከከተሞች መካከል በደለኛ ሆነው ያጠፋናቸው እና በጣሪያዎቻቸው ላይ ወዳቂ የሆኑ ብዙ ናቸው:: ከተራቆተም የውሃ ጉድጓድ ከተገነባም ህንፃ ያጠፋነው ብዙ ነው::"},{"id":46,"translation":"46. ለእነርሱም የሚያውቁባቸው ልቦች፤ ወይም የሚሰሙባቸው ጆሮዎች ይኖሯቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን? እነሆ ዓይኖች አይታወሩም:: እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ናቸው የሚታወሩት።"},{"id":47,"translation":"47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) አላህ ቀጠሮውን በፍጹም የማይጥስ ሲሆን ቅጣትን እንድታመጣ ያቻኩሉሃል (ያጣድፉሃል):: በጌታህ ዘንድ አንዱ ቀን ከምትቆጥሩት ቀን እንደ አንድ ሺህ ዓመት የሚመጥን ነው::"},{"id":48,"translation":"48. ከከተማ በዳይ ሆና ጊዜ የሰጠኋትና ከዚያ የያዝኳት የቀጣኋት ብዙ ናት:: የመጨረሻው መመለሻም ወደ እኔ ብቻ ነው::"},{"id":49,"translation":"49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ለእናንተ ግልጽ አስፈራሪ ብቻ ነኝ።» በላቸው።"},{"id":50,"translation":"50. እነዚያም በትክክል ያመኑና መልካም ስራዎችን የሰሩ ለእነርሱ ምህረትና ያማረ ሲሳይ አላቸው::"},{"id":51,"translation":"51. እነዚያ ከአላህ የሚያመልጡ መስሏቸው ተዓምራታችንን በመንቀፍ የተጉ ሁሉ እነርሱ የእሳት ጓዶች ናቸው።"},{"id":52,"translation":"52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት አንድንም መልዕክተኛ ወይም ነብይ አላክንም ባነበበ ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ውስጥ የማጥመሚያን ሀሳብ የሚጥል ቢሆን እንጂ:: ወዲያዉም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ማጥመሚያ ቃል ያስወግዳል:: ከዚያም አላህ አናቅጽን ያጠነክራል (ያጸናል):: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":53,"translation":"53. ሰይጣን የሚጥለውን ነገር ለእነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ላለባቸውና ልቦቻቸው ደረቆች ለሆኑት ፈተና ሊያደርግ ይጥላል:: በዳዮችም ከእውነት በራቀ ጭቅጭቅ (ውዝግብ) ውስጥ ናቸው::"},{"id":54,"translation":"54. እነዚያም እውቀትን የተሰጡት እርሱ (ቁርኣን) ከጌታህ የሆነ እውነት መሆኑን እንዲያውቁና በእርሱ እንዲያምኑ ልቦቻቸዉም በእርሱ እንዲረኩ (ያጠነክራል):: አላህም እነዚያን በትክክል ያመኑትን ሁሉ ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ መሪ ነው::"},{"id":55,"translation":"55. እነዚያ የካዱት ሰዎች ሰዓቲቱ በድንገት እስከምትመጣባቸው ወይም ከደግ ነገር መካን የሆነው ቀን ቅጣት እስከሚመጣባቸው ድረስ በቁርኣን ጉዳይ ከመጠራጠር አያቆሙም::"},{"id":56,"translation":"56. በዚያ ቀን ንግስናው የአላህ ብቻ ነው:: በመካከላቸውም ይፈርዳል:: እነዚያም ያመኑትና መልካም ስራዎችን የሰሩት በመደሰቻ ገነቶች ውስጥ ናቸው።"},{"id":57,"translation":"57. እነዚያም የካዱትና በአናቅጻችንም ያስተባበሉት ሁሉ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":58,"translation":"58. እነዚያም ለአላህ ሀይማኖት ሲሉ የተሰደዱና ከዚያም ሲታገሉ የተገደሉ ወይም የሞቱ አላህ መልካምን ሲሳይ በእርግጥ ይሰጣቸዋል:: አላህም እርሱ ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው::"},{"id":59,"translation":"59. የሚወዱትን መግቢያ ገነትን በእርግጥ ያስገባቸዋል:: አላህም በእርግጥ አዋቂና ታጋሽ ነውና::"},{"id":60,"translation":"60. (ነገሩ) ይህ ነው:: ያ በተበደለበት ብጤ (መጠን) የተበቀለና ከዚያ በእርሱ ላይ ግፍ የተዋለበት ሰው አላህ በእርግጥ ይረዳዋል:: አላህ ይቅር ባይና መሓሪ ነውና::"},{"id":61,"translation":"61. ይህ የሆነው አላህ ሌሊትን በቀን ውስጥ የሚያስገባ፤ ቀንንም በሌሊት ውስጥ የሚያስገባ (ቻይ) ፤ ሁሉንም ሰሚ፤ ሁሉንም ተመልካች በመሆኑ ነው።"},{"id":62,"translation":"62. ይህ የሆነው አላህም ፍፁም እውነት በመሆኑ፤ ከርሱም ሌላ የሚገዙት ነገር ፍጹም ውሸት በመሆኑና አላህም የሁሉ በላይ ታላቅ በመሆኑ ነው::"},{"id":63,"translation":"63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ከሰማይ ውሃን ማውረዱንና ከዚያ ምድር የምትለመልም መሆኗን አላየህምን? አላህ ፍጹም ሩህሩህና ውስጠ አዋቂ ነውና::"},{"id":64,"translation":"64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: አላህ እርሱ ተብቃቂዉና ምስጉኑ ነውና::"},{"id":65,"translation":"65. አላህ በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ ለእናንተ የገራላችሁ መርከቦችንም በባህር ውስጥ በፈቃዱ የሚንሻለሉ ሲሆኑ የገራላችሁ መሆኑን፤ ሰማይንም በፈቃዱ ካልሆነ በምድር ላይ እንዳትወድቅ የሚይዛት መሆኑን አላየህምን? አላህ ለሰዎች በእርግጥ ሩህሩህና አዛኝ ነውና::"},{"id":66,"translation":"66. እርሱም ያ ህያው ያደረጋችሁ ነው:: ከዚያም ይገድላችኋል:: ከዚያም ህያው ያደርጋችኋል:: ሰው በእርግጥ በጣም ከሓዲ ነው::"},{"id":67,"translation":"67. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለየህዝቡ ሁሉ እነርሱ የሚሰሩበት የሆነን ስርዓተ ሃይማኖት አድርገናል:: ስለዚህ በነገሩ አይከራከሩህ:: ወደ ጌታህ መንገድም ጥራ:: አንተ በእርግጥ በቅኑ መመርያ ላይ ነህና።"},{"id":68,"translation":"68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢከራከሩህም (እንዲህ) በላቸው: «አላህ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነው።"},{"id":69,"translation":"69. «አላህ በትንሳኤ ቀን በዚያ በእርሱ ትለያዩበት (ትወዛገቡበት) በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል።» (በላቸው)"},{"id":70,"translation":"70. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ በእርግጥ የሚያውቅ መሆኑን አታውቅምን? ይህ በመጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ እውነት ነው:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነው::"},{"id":71,"translation":"71. ከአላህ ሌላም ምንም ማስረጃን ያላወረደበትንና ለእነርሱም በእርሱ እውቀት የሌላቸውን ነገር ያመልካሉ፤ ለበዳዮች ምንም ረዳት የላቸዉም::"},{"id":72,"translation":"72. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አናቅጻችን የተብራሩ ሆነው በእነርሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ በእነዚያ በአላህ በካዱት ሰዎች ፊት ላይ ጥላቻን ታውቃለህ:: በእነዚያ አናቅጻችንን በሚያነቡት ላይም በኃይል ሊተናኮሏቸው ይቃረባሉ:: ይልቅ ከዚህ የከፋን ነገር ልንገራችሁን? እርሷም እሳት ናት:: አላህ ለእነዚያ በርሱ ለካዱት ሰዎች ሁሉ ቀጥሯታል:: መመለሻነቷ ምን ይከፋ በላቸው::"},{"id":73,"translation":"73. ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለጸላችሁ:: ለእርሱም አድምጡት፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣዖታት ሁሉ ዝንብን ለመፍጠር ቢሰበሰቡ ፈጽሞ መፍጠር እንኳ አይችሉም:: አንዳችንም ነገር ዝንብ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም:: ፈላጊዉም (አምላኪው) ተፈላጊዉም (ተመላኪው) ደከሙ::"},{"id":74,"translation":"74. አላህን ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም:: አላህ በጣም ሀያልና ሁሉን አሸናፊ ነውና::"},{"id":75,"translation":"75. አላህ ከመላእክት ውስጥ መልዕክተኞችን ይመርጣል:: ከሰዎችም መካከል እንደዚሁ መልዕክተኞችን ይመርጣል:: አላህ ሁሉን ሰሚ ሁሉን ተመልካች ነው::"},{"id":76,"translation":"76. በስተፊታቸዉም ሆነ በስተኋላቸው ያለን ሁሉ ያውቃል:: ወደ አላህም ነገሮች ሁሉ ይመለሳሉ::"},{"id":77,"translation":"77. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአላህ ቁጣ ትድኑ ዘንድ በስግደታችሁ አጎንብሱ:: በግንባራችሁም ላይ ተደፉ:: (ሩኩዕና ሱጁድ አድርጉ) ጌታችሁንም በትክክል ተገዙት:: በጎንም ነገር ስሩ:: ልትድኑ ይከጀልላችኋልና:: {1}","footnotes":"{1} እዚህ የንባብ ሱጁድ (ሱጁድ ትላዋ) ይደረጋል።"},{"id":78,"translation":"78. በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ:: እርሱ መርጧችኋል:: በናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም:: የአባታችሁን የኢብራሂምን ሃይማኖት ተከተሉ:: እርሱ (አላህ) ከዚህ በፊት በነበሩት መጽሐፍትም ሆነ በዚህ ቁርኣን ሙስሊሞች ብሎ ሰይሟችኋል። (ይሄዉም) መልዕክተኛው በእናንተ ላይ መስካሪ እንዲሆን እና እናንተም በሰዎች ላይ መስካሪዎች እንድትሆኑ ነው:: ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ:: ዘካንም በአግባቡ ለተገቢው ስጡ:: በአላህም ተጠበቁ:: እርሱ ረዳታችሁ ነውና:: እርሱ ምን ያማረ ጠባቂ፤ ምን ያማረም ረዳት ነው።"}]},{"id":23,"verses":[{"id":1,"translation":"1.ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ተሳካላቸው)::"},{"id":2,"translation":"2. እነዚያም በስግደታቸው ውስጥ አላህን ፈሪዎች የሆኑት፤"},{"id":3,"translation":"3. እነዚያም ከመጥፎ ነገር ሁሉ የራቁ::"},{"id":4,"translation":"4. እነዚያም ዘካን በአግባቡ ሰጪዎች፤"},{"id":5,"translation":"5. እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት፤"},{"id":6,"translation":"6. በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው ሴት ባሪያዎች ላይ ካልሆነ በቀር (ብልቶቻቸውን ጠባቂ የሆኑት)፤ እነርሱ በነዚህ የማይወቀሱ ናቸውና።"},{"id":7,"translation":"7. ከዚህ ሌላ በሆነ መንገድ (ስሜታቸዉን ሊያረኩ) የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ የአላህን ወሰን አላፊዎች ናቸው::"},{"id":8,"translation":"8. እነዚያም ለአደራዎቻቸውና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች፤"},{"id":9,"translation":"9. እነዚያም በስግደቶቻቸው ላይ (ሁለንተናዋን) የሚጠባበቁ የሆኑት"},{"id":10,"translation":"10. እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው::"},{"id":11,"translation":"11. እነዚያ ፊርደውስን (ላዕላይ ገነትን) የሚወርሱ ናቸው:: እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች እነርሱ ብቻ ናቸው::"},{"id":12,"translation":"12. በእርግጥ ሰውን (አደምን) ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው::"},{"id":13,"translation":"13. ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው::"},{"id":14,"translation":"14. ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውንም ደም ቁራጭ ስጋ አድርገን ፈጠርን፤ ቁራጭዋንም ስጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን:: አጥንቶችንም ስጋን አለበስናቸው። ከዚያም (በዉስጡ ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረት አድርገን አስገኘነው:: ከቅርፅ ሰጪዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ከሁሉ ላቀ።"},{"id":15,"translation":"15. (ሰዎች ሆይ!) ከዚያም እናንተ ከዚህ በኋላ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ::"},{"id":16,"translation":"16. ከዚያም እናንተ በትንሳኤ ዕለት ትቀሰቀሳላችሁ::"},{"id":17,"translation":"17. በእርግጥም ከበላያችሁ ሰባትን ሰማያት ፈጠርን:: ከፍጥረቶቹም ዘንጊዎች አይደለንም::"},{"id":18,"translation":"18. ከሰማይም ውሃን በልክ አወረድን:: በምድርም ውስጥ አስቀመጥነው:: እኛም እርሱን በማስወገድ ላይ በእርግጥ ቻዮች ነን::"},{"id":19,"translation":"19. በእርሱም ከዘምባባዎችና ከወይኖች አትክልቶችን ለእናንተ አስገኘንላችሁ:: በውስጧ ለእናንተ ብዙ ፍራፍሬዎች አሏችሁ:: ከእርሷም ትበላላችሁ::"},{"id":20,"translation":"20. ከሲና ተራራም የምትወጣ ዛፍ በቅባትና ለበይዎች መባያ በሚሆን ዘይት ተቀላቅላ የምትበቅልን አስገኘንላችሁ::"},{"id":21,"translation":"21. (ሰዎች ሆይ!) እናንተም በግመል፤ በከብት በፍየልና በበግ መገምገሚያ አላችሁ:: በሆዶችዋ ውስጥ ካለው ወተት እናጠጣችኋለን:: ለእናንተም በእርሷ ብዙ ጥቅሞች አሏችሁ:: ከእርሷም ትበላላችሁ::"},{"id":22,"translation":"22. በእርሷም ላይና በመርከብም ላይ ትጫናላችሁ::"},{"id":23,"translation":"23. ኑሕን ወደ ህዝቦቹ በእርግጥ ላክነው። ወዲያዉም «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: አትጠነቀቁምን?» አላቸው።"},{"id":24,"translation":"24. ከህዝቦቹም እነዚያ ታላላቆቹ ሰዎች አሉ: «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም። በእናንተ ላይ መብለጥን ይፈልጋል። አላህም ቢፈልግ ኖሮ መላእክትን ባወረደ ነበር። ይህንንም የሚለውን በመጀመሪያዎቹ አባቶቻችን አልሰማንም።"},{"id":25,"translation":"25. «እርሱ እብደት ያለበት ሰው እንጂ ሌላ አይደለም:: በእርሱም እስከ ጊዜው ድረስ ተጠባበቁ።» አሉ።"},{"id":26,"translation":"26. ኑሕም «ጌታዬ ሆይ! ስለ አስተባበሉኝ እርዳኝ።» አለ።"},{"id":27,"translation":"27. ወደ እርሱ እንዲህ ስንል ላክን: «በተመልካችነታችንና በትእዛዛችን ታንኳን ስራ። ከዚያ ትእዛዛችን በመጣና ምድጃው (እቶኑ) በፈለቀ ጊዜ በውስጧ ከሁሉም ነገር ሁለት ሁለት ዓይነቶችንና ቤተሰቦችህን ከእነርሱ መካከል ጠፊ በመሆኑ ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር አስገባ። በእነዚያ ራሳቸውን በአላህ በመካድ በበደሉት ሰዎች ጉዳይ አታነጋግረኝ። እነርሱ በውኃ ተሰማጪዎች ናቸውና።"},{"id":28,"translation":"28. አንተም አብረውህ ካሉት ፍጡሮች ጋር በታንኳይቱ ላይ በተደላደልክ ጊዜ በል: «ምስጋና ሁሉ ለዚያ ከበደለኛ ህዝቦች ላዳነን አላህ ይገባው።"},{"id":29,"translation":"29. «ጌታዬ ሆይ! ብሩክ የሆነን ማውረድ አውርደኝ:: አንተም ከአደላዳዮች ሁሉ በላጭ ነህና።» በል።"},{"id":30,"translation":"30. በዚህ ውስጥ ለሃያልነታችን አያሌ ተዓምራት አሉበት:: እነሆ እኛ (የኑሕን ሰዎች) ፈታኞች ነበርን::"},{"id":31,"translation":"31. ከዚያ ከኋላቸው ሌሎችን የክፍለ ዘመናት ህዝቦች አስገኘን::"},{"id":32,"translation":"32. በውስጣቸዉም ከእነርሱ የሆኑን መልዕክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የላችሁም:: አትጠነቀቁምን? በማለት ላክን።"},{"id":33,"translation":"33. ከህዝቦቹም እነዚያ የካዱት ሰዎች በመጨረሻይቱም ቀን መገናኘት ያስተባበሉት በቅርቢቱም ህይወት ያቀማጠልናቸው ታላላቅ ሰዎች አሉ: «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም። ከምትበሉት ምግብ ይበላል፤ ከምትጠጡትም ውሃ ይጠጣል።"},{"id":34,"translation":"34. «የናንተው ብጤያችሁ የሆነን ሰው ብትታዘዙ በእርግጥ የተሞኛችሁ ናችሁ።"},{"id":35,"translation":"35. «‹እናንተ ሞታችሁ አፈርና አጥንቶችም በሆናችሁ ጊዜ እናንተ ከመቃብር ትወጣላችሁ› በማለት ያስፈራራችኋልን?"},{"id":36,"translation":"36. «ያ የምትስፈራሩበት ነገር ከእውነት ራቀ፤ በጣም ራቀ"},{"id":37,"translation":"37. «እርሷ (ህይወት) ማለት ቅርቢቱ ህይወታችን ብቻ እንጂ ሌላ አይደለችም:: እንሞታለን። ህያዉም እንሆናለን። እኛም ፈጽሞ ተቀስቃሾች አይደለንም\" (አሉ)።"},{"id":38,"translation":"38. «እርሱ በአላህ ላይ ውሸትን የቀጠፈ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም:: እኛም በእርሱ አማኞች አይደለንም።» አሉ።"},{"id":39,"translation":"39. መልዕክተኛዉም «ጌታዬ ሆይ! ስላስተባበሉኝ በእነርሱ ላይ እርዳኝ።» አለ።"},{"id":40,"translation":"40. አላህም «ከጥቂት ጊዜ በኋላ በጥፋታቸው በእርግጥ ተጸጻቾች ይሆናሉ።» አለው።"},{"id":41,"translation":"41. ወዲያዉም (የጥፋት) ጩኸቲቱ በእውነት ያዘቻቸው፤ እንደ ጎርፍ ግብስባሽም አደረግናቸው:: ለበደለኞች ህዝቦችም ከእዝነት መራቅ ተገባቸው::"},{"id":42,"translation":"42. ከዚያም ከእነርሱ በኋላ ሌሎችን የክፍለ ዘመናት ህዝቦች አስገኘን::"},{"id":43,"translation":"43. ማንኛይቱም ህዝብ ጊዜዋን አትቀድምም:: ከጊዜያቸዉም አይቆዩምም::"},{"id":44,"translation":"44. ከዚያም መልዕክተኞቻችንን በተከታታይ ላክን፤ ማንኛይቱንም ህዝብ መልእክተኛዋ በመጣላት ቁጥር አስተባበሉት። ከፊላቸውንም በከፊሉ በጥፋት አስከታተልን፤ ወሬዎችም አደረግናቸው፤ ለማያምኑም ህዝቦች ከእዝነታችን መራቅ ተገባቸው።"},{"id":45,"translation":"45. ከዚያ ሙሳንና ወንድሙን ሃሩንን በተአምራታችንና በግልጽ ማስረጃ ላክናቸው::"},{"id":46,"translation":"46. ወደ ፈርዖንና ወደ ጭፍሮቹ ላክናቸው። ድሮውም የኮሩና የተንበጣረሩ ህዝቦችም ነበሩ።"},{"id":47,"translation":"47. «ህዝቦቻቸው ለኛ ተገዢዎች ሆነው ሳሉ ብጤያችን ለሆኑ ሰዎች እናምናለን?» አሉ።"},{"id":48,"translation":"48. አስተባበሏቸዉም፤ ከጠፊዎችም ሆኑ::"},{"id":49,"translation":"49. ሙሳንም ነገዶቹ ይመሩ ዘንድ መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው::"},{"id":50,"translation":"50. የመርየምን ልጅ ዒሳንና እናቱንም ተዓምር አደረግናቸው:: የመደላደልና የምንጭ ባለቤት ወደ ሆነች ከፍተኛ ስፍራም አስጠጋናቸው::"},{"id":51,"translation":"51. እናንተ መልእክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ሁሉ ብሉ:: በጎ ስራንም ስሩ:: እኔ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነኝና::"},{"id":52,"translation":"52. ይህችም በአንድ አምላክ የማመን ህግጋት አንድ መንገድ ስትሆን ሃይማኖታችሁ ናት:: እኔም ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ::"},{"id":53,"translation":"53. ከዚያም ተከታዮቻቸው ሃይማኖታቸውን በመካከላቸው ክፍልፍሎች አድርገው ቆራረጡ፤ ህዝቦች ሁሉ እነርሱ ዘንድ ባለው ሃይማኖት ተደሳቾች ናቸው::"},{"id":54,"translation":"54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እስከ ጊዜያቸዉም ድረስ በጥመታቸው ውስጥ ተዋቸው::"},{"id":55,"translation":"55. ከገንዘብና ከልጆች በእርሱ የምንጨምርላቸውን ያስባሉን?"},{"id":56,"translation":"56. በበጎ ነገሮች የምንቻኮልላቸው እንደሆነ ያስባሉን? አይደለም፤ ይህ ሁሉ እነርሱን ለማዘናጋት መሆኑን አያውቁም።"},{"id":57,"translation":"57. እነዚያ እነርሱ ጌታቸውን ከመፍራት የተነሳ ተጨናቂዎች የሆኑት፤"},{"id":58,"translation":"58. እነዚያም እነርሱ በጌታቸው ተዓምራት የሚያምኑት፤"},{"id":59,"translation":"59. እነዚያም በጌታቸው የማያጋሩት፤"},{"id":60,"translation":"60. እነዚያም የሚሰጡትን ነገር ሁሉ እነርሱ ወደ ጌታቸው ተመላሾች መሆናቸውን ልቦቻቸው የሚፈሩ ሆነው የሚሰጡ ናቸው::"},{"id":61,"translation":"61. እነዚያ በመልካም ስራዎች ይጣደፋሉ:: እነርሱም ለርሷ ቀዳሚዎች ናቸው::"},{"id":62,"translation":"62. ማንኛይቱንም ነፍስ የችሎታዋን ያህል እንጂ አናስገድዳትም:: እኛም ዘንድ በእውነት የሚናገር መጽሐፍ አለ:: እነርሱም አይበደሉም::"},{"id":63,"translation":"63. በእውነቱ ከሓዲያን ልቦቻቸው ከዚህ መጽሐፍ በዝንጋታ ውስጥ ናቸው:: ለእነርሱም ከዚህ ሌላ እነርሱ ለእርሷ ሰሪዎችዋ የሆኑ መጥፎ ስራዎች አሏቸው::"},{"id":64,"translation":"64. ቅምጥሎቻቸውንም በቅጣት በያዝናቸው ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ይወተውታሉ::"},{"id":65,"translation":"65. (ይባላሉም) «ዛሬ አትወትውቱ፤ እናንተ ከእኛ ዘንድ አትረዱምና።"},{"id":66,"translation":"66. «አንቀፆቼ በእናንተ ላይ በእርግጥ ይነበቡላችሁ ነበር። እናንተ ግን በተረከዞቻችሁ ላይ ወደ ኋላችሁ ትመለሱ ነበር።"},{"id":67,"translation":"67. «በእርሱ (በክልሉ ቤት) ኩሩዎች ሌሊት ተጫዋቾች (ቁርኣንንም) የምትተው ሆናችሁ (ትመለሱ ነበር)።» ይባላሉ።"},{"id":68,"translation":"68. የቁርኣንን ንግግርን አያስተነትኑምን? ወይስ ለመጀመሪያዎቹ አባቶቻቸው ያልመጣ ነገር መጣባቸውን?"},{"id":69,"translation":"69. ወይስ መልዕክተኛቸውን አላወቁምን? ስለዚህ እነርሱ በእርሱ ከሓዲያን ናቸውን?"},{"id":70,"translation":"70. ወይስ «በእርሱ ዕብደት አለበት» ይላሉን? እብድ አይደለም። እውነትን ይዞ መጣላቸው:: አብዛኞቻቸዉም ግን እውነትን ጠይዎች ናቸው።"},{"id":71,"translation":"71. እውነታው (አላህ) ዝንባሌዎቻቸውን በተከተለ ኖሮ ሰማያትና ምድር በውስጣቸዉም ያለው ሁሉ በእርግጥ በተበላሸ ነበር:: ይልቁንም ክብራቸው ያለበትን ቁርኣን አመጣንላቸው:: እነርሱም ክብራቸውን ዘንጊዎች ናቸው::"},{"id":72,"translation":"72. ወይስ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ግብርን ትጠይቃቸዋለህን? የጌታህም ችሮታ ከሁሉም በላጭ ነው:: እርሱም ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው::"},{"id":73,"translation":"73.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትጠራቸዋለህ::"},{"id":74,"translation":"74. እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ግን ከትክክለኛው መንገድ ተዘንባዮች ናቸው።"},{"id":75,"translation":"75. ባዘንላቸውና በእነርሱ ያለውን ጉዳትም ባነሳንላቸው ኖሮ በጥመታቸው ውስጥ የሚዋዥቁ ሆነው ይዘወትሩ ነበር::"},{"id":76,"translation":"76. በእርግጥም በቅጣት ያዝናቸው:: ታዲያ ለጌታቸው አልተናነሱም:: የሚዋደቁም አይደሉም።"},{"id":77,"translation":"77. በእነርሱም ላይ የብርቱ ቅጣት ባለቤት የሆነ ደጃፍን በከፈትንባቸው ጊዜ እነርሱ ያን ጊዜ በእርሱ ተስፋ ቆራጮች ናቸው::"},{"id":78,"translation":"78. እርሱም ያ መስሚያዎችን፤ ማያዎችንና ልቦችን ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው:: ጥቂትን እንጂ አታመሰግኑም::"},{"id":79,"translation":"79. እርሱም ያ በምድር ውስጥ የበተናችሁ ነው:: በመጨረሻም ጊዜ ወደ እርሱም ትሰበሰባላችሁ::"},{"id":80,"translation":"80. እርሱም ያ ህያው የሚያደርግ የሚገድልም ነው:: የሌሊትና የቀን መተካካትም የእርሱ ነው :: አታውቁምን?"},{"id":81,"translation":"81. ይልቁንም የመካ ከሓዲያን ልክ የፊተኞቹ ህዝቦች እንዳሉት ብጤ አሉ::"},{"id":82,"translation":"82. አሉም: «በሞትንና አፈርና አጥንቶች በሆንን ጊዜ እኛ እንደገና ተቀስቃሾች ነን?"},{"id":83,"translation":"83. «ይህንን ሁኔታ እኛም ሆነ ከእኛ በፊት የነበሩት አባቶቻችን በእርግጥ ተቀጥረናል፤ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ።"},{"id":84,"translation":"84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የማን ነው? የምታውቁ ከሆናችሁ እስቲ ንገሩኝ።» በላቸው።"},{"id":85,"translation":"85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርግጥ የአላህ ነው።» ይሉሃል። «ታዲያ አትገሠጹምን?» በላቸው።"},{"id":86,"translation":"86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የሰባቱ ሰማያት ጌታ የታላቁም ዐርሽ ጌታ ማን ነው?» በላቸው።"},{"id":87,"translation":"87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል፤ «እንግዲያ አትፈሩትምን?» በላቸው።"},{"id":88,"translation":"88. «የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የሆነ፤ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው? የምታውቁ ከሆናችሁ (እስቲ መልሱልኝ)» በላቸው።"},{"id":89,"translation":"89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል፤ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ?» በላቸው።"},{"id":90,"translation":"90. ይልቁንም እውነትን አመጣንላቸው እነርሱም በመካዳቸው ውሸታሞች ናቸው::"},{"id":91,"translation":"91. አላህ ምንም ልጅን አልያዘም አልወለደም:: ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም:: ሌላ አምላክ በነበረማ አምላኩ ሁሉ የፈጠረውን ነገር በማስተዳደር ከሌላው በተለየ ነበር:: ከፊላቸዉም በከፊሉ ላይ በነገሰ ነበር:: አላህ ከሓዲያን እሱን ከሚመጥኑበት መግለጫ ሁሉ ጠራ::"},{"id":92,"translation":"92. ሩቁንና ቅርቡን ሁሉ አዋቂ ነው:: በእርሱ ከሚያጋሩትም ሁሉ ከፍ አለ::"},{"id":93,"translation":"93. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «ጌታዬ ሆይ! የሚስፈራሩበትን ቅጣት ብታሳየኝ፤"},{"id":94,"translation":"94. «ጌታዬ ሆይ! በበደለኞች ህዝቦች ውስጥ አታድርገኝ።» በል።"},{"id":95,"translation":"95. እኛ የምናስፈራራቸውን ነገር ልናሳይህ በእርግጥ ቻዮች ነን::"},{"id":96,"translation":"96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ጠባይ መጥፎይቱን ነገር መልስ:: እኛ ከሓዲያን የሚሉትን ሁሉ አዋቂዎች ነንና::"},{"id":97,"translation":"97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በል: «ጌታዬ ሆይ ከሰይጣናት ጉትጎታዎች ባንተ እጠበቃለሁ።"},{"id":98,"translation":"98. «ጌታዬ ሆይ! ወደ እኔ ከመጣዳቸው ከመቅረባቸውም ባንተው እጠበቃለሁ።» በል።"},{"id":99,"translation":"99. አንዳቸውን ሞት በመጣበት ጊዜ ይላል: «ጌታዬ ሆይ! ወደ ምድረ ዓለም መልሱኝ።"},{"id":100,"translation":"100. «ችላ ብዬ የተውኩትን በጎ ስራ ልሰራ እከጅላለሁና።» (ይላል)። (ይህን ከማለት ይከልከል):: እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የሆነች ቃል (ብቻ) ናት:: ከበስተፊታቸዉም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶ አለ::"},{"id":101,"translation":"101. በቀንዱም በተነፋ ጊዜ በዚያ ቀን በመካከላቸው ዝምድና የለም። አይጠያየቁምም::"},{"id":102,"translation":"102.ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸው ሰዎች እነዚያ እነርሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው::"},{"id":103,"translation":"103. እነዚያ ሚዛኖቻቸዉም የቀለሉባቸው ሰዎች እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፤ በገሀነም ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::"},{"id":104,"translation":"104. ፊቶቻቸውን እሳት ትገርፋቸዋለች:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ከንፈሮቻቸው የተኮማተሩ ናቸው::"},{"id":105,"translation":"105. «አንቀፆቼ በእናንተ ላይ የሚነበቡላችሁና በእነርሱ የምታስተባብሉ አልነበራችሁምን?» ይባላሉ።"},{"id":106,"translation":"106. (እነርሱም) ይላሉ: «ታላቁ ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መናጢነታችን አሸነፈችንና ጠማማ ህዝቦች ነበርን።"},{"id":107,"translation":"107. «ጌታችን ሆይ! ከእርሷ አውጣንና ወደ ዱንያ መልሰን:: ከዚህ በኋላ ወደ ክህደት ብንመለስ እኛ በዳዮች ነን።» ይላሉ።"},{"id":108,"translation":"108. አላህም ይላቸዋል: «ወራዶች ሆናችሁ በውስጧ አርፋችሁ ኑሩ እንጂ ፍጹም አታናግሩኝ።"},{"id":109,"translation":"109. «እነሆ ከባሮቼ መካከል ‹ጌታችን ሆይ! አምነናልና ማረን:: እዘንልንም:: አንተ ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ› የሚሉ ክፍሎች ነበሩ።"},{"id":110,"translation":"110. «እኔንም ማውሳትን እስካስረሷችሁ ድረስም ማላገጫ አድርጋችሁ ያዛችኋቸው:: በእነርሱም ላይ ትስቁባቸው ነበር።"},{"id":111,"translation":"111. «እኔ ዛሬ በትዕግስታቸው ምክንያት ፍላጎታቸውን የሚያገኙት እነርሱን ብቻ በማድረግ መነዳኋቸው።» ይላቸዋል።"},{"id":112,"translation":"112. «በምድር ውስጥ ስንትን አመታትን ቆያችሁ?» ይላቸዋል።"},{"id":113,"translation":"113. «አንድ ቀንን ወይም ከፊል ቀንን ቆየን:: ቆጣሪዎችንም ጠይቅ» ይላሉ።"},{"id":114,"translation":"114. ይላቸዋልም: «እናንተ የቆያችሁትን መጠን የምታውቁ ብትሆኑ ኖሮ (በእሳት ውስጥ ከምትቆዩት ጊዜ አንጻር) ጥቂትን ጊዜ እንጂ አልቆያችሁም።"},{"id":115,"translation":"115. «የፈጠርናችሁ ለከንቱ መሆኑን እናንተም ወደ እኛ የማትመለሱ መሆናችሁን ጠረጠራችሁን? (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን?)።» (ይባላሉ።)"},{"id":116,"translation":"116. የእውነቱ ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው:: ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: የዚያ የሚያምረው ዐርሽ ጌታም እሱ ብቻ ነው::"},{"id":117,"translation":"117. ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ በእርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚገዛ ሁሉ ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው:: እነሆ ከሓዲያን አይድኑም።"},{"id":118,"translation":"118. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ ሆይ! ማር:: እዘንም:: አንተም ከአዛኞች ሁሉ በላጭ ነህና።» በል፡:"}]},{"id":24,"verses":[{"id":1,"translation":"1.(ሙስሊሞች ሆይ!) (ይህ) ያወረድነውና በእናንተ ላይ (እንድትሰሩበት) የደነገግነው ምዕራፍ ነው:: እርሱ በርሷም ውስጥ ትገሰጹ ዘንድ ግልጽ አናቅጽን አውርደናል::"},{"id":2,"translation":"2. ዝሙተኛይቱ ሴትና ዝሙተኛው ወንድ ከሁለቱ እያንዳንዳቸው (ያላገቡ እንደሆኑ) መቶ ግርፋትን ግረፏቸው:: በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደሆናችሁ በእነርሱ ላይ በደነገገው በአላህ ፍርድ ርህራሄ አትያዛችሁ። ሙስሊሞች ሆይ! ቅጣታቸውንም በምትፈጽሙበት ጊዜ ከአማኞች የተወሰኑ ቡድኖች ይገኙበት::"},{"id":3,"translation":"3. ዝሙተኛ ወንድ ዝሙተኛን ሴት ወይም በአላህ አጋሪን ሴት እንጂ ሌላን አያገባም (አይፈልግም) :: ዝሙተኛይቱም ሴት ዝሙተኛ ወይም በአላህ አጋሪ ወንድ እንጂ ሌላ አያገባትም (አይፈልጋትም):: ይህም በአማኞች ላይ ተከልክሏል::"},{"id":4,"translation":"4. እነዚያ ጥብቆችን ሴቶች በዝሙት የሚሰድቡ ከዚያ በሰደቡበት አራት ምስክሮች ያላመጡ ሰማንያ ግርፋት ግረፏቸው:: ከእነርሱም ምስክርነትን ለሁልጊዜ አትቀበሉ:: እነዚያም እነርሱ አመጸኞች ናቸው::"},{"id":5,"translation":"5. እነዚያ ከዚህ በኋላ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩ ሲቀሩ:: አላህ በጣም መሓሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":6,"translation":"6. እነዚያ ሚስቶቻቻውን (በዝሙት) የሚሰድቡ ለነሱም ከነፍሶቻቸው በስተቀር ምስክሮች የሌሏቸው የሆኑ የአንዳቸው ምስክርነት ከእውነተኞች ለመሆናቸው በአላህ ስም አራት ጊዜ ምሎ መመስከር ነው::"},{"id":7,"translation":"7. አምስተኛይቱም ከውሸታሞች ቢሆን በእርሱ ላይ የአላህ እርግማን እንዲሰፍንበት (ምሎ መመስከር ነው)።"},{"id":8,"translation":"8. «እርሱም ከውሸታሞች ነው።» ብላ አራት ጊዜ በአላህ ስም መመስከሯ ከእርሷ ላይ ቅጣትን ይከላከልላታል::"},{"id":9,"translation":"9. አምስተኛይቱም እርሱ ከእውነተኞች ቢሆን በርሷ ላይ የአላህ ቁጣ ይኑርባት ብላ መመስከሯ ነው::"},{"id":10,"translation":"10. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረና አላህ ጸጸትን ተቀባይና ጥበበኛ ባልሆነ ኖሮ (ውሸታሙን ሁሉ በዚሁ አለም ላይ ይገልጸው ነበር)::"},{"id":11,"translation":"11. እነዚያ መጥፎን ውሸት ያመጡ ከናንተው የሆኑ ቡድኖች ናቸው:: ለእናንተ ክፉ ነገር እንደሆነ አታስቡት፤ በእውነቱ እርሱ ለእናንተ መልካም ነገር ነው:: ከጭፍሮቹ ለእያንዳንዱ ሰው ከኃጢአት የሠራው ሥራ ዋጋ አለው:: ያም ከእነርሱ ትልቁን ኃጢአት የተሸከመው ለእርሱ ከባድ ቅጣት አለው::"},{"id":12,"translation":"12. (ውሸቱን) በሰማችሁት ጊዜ አማኞችና ምዕመናት በነፍሶቻቸው ለምን ደግን ነገር አልጠረጠሩም? ለምንስ «ይህ ግልጽ ቅጥፈት ነው።» አላሉም?"},{"id":13,"translation":"13. በእርሱ ላይ ለምን አራትን ምስክሮች አላመጡም? ምስክሮቹንም ካላመጡ እነዚያ አላህ ዘንድ ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው::"},{"id":14,"translation":"14. በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም በእናንተ ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ በውስጡ በገባችሁበት ወሬ ምክንያት ታላቅ ቅጣት በእርግጥ በደረሰባችሁ ነበር::"},{"id":15,"translation":"15. በምላሶቻችሁም በምትቀባበሉት ጊዜ ለእናንተም በእርሱ እውቀት በሌላችሁ ነገር በአፎቻችሁ በተናገራችሁና አላህ ዘንድ ከባድ ኃጢአት ሆኖ ሳለ ቀላል አድርጋችሁ ባሰባችሁት ጊዜ ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር::"},{"id":16,"translation":"16. በሰማችሁትም ጊዜ: «በዚህ ጉዳይ ልንናገር ለእኛ አይገባንም:: አላህ ጥራት ይገባህ:: ይህ ከባድ ቅጥፈት ነው።» አትሉም ነበርን?"},{"id":17,"translation":"17. አማኞች እንደሆናችሁ ወደ ዚህ መሰል ተግባር ብጤው በፍጹም እንዳትመለሱ አላህ ይገስጻችኋል::"},{"id":18,"translation":"18. ለእናንተም አላህ አናቅጽን ይገልጽላችኋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::"},{"id":19,"translation":"19. እነዚያ በነዚያ በትክክል በአላህ ባመኑት ሰዎች መካከል መጥፎ ወሬ እንድትስፋፋ የሚወዱ ለእነርሱ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም አሳማሚ ቅጣት አላቸው:: አላህ ሁሉን ነገር ያውቃል እናንተ ግን አታውቁም::"},{"id":20,"translation":"20. በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታውና እዝነቱ ባልነበረ አላህም ሩህሩህና አዛኝ ባልሆነ ኖሮ (ቶሎ ባጠፋችሁ ነበር)::"},{"id":21,"translation":"21. እናንተ ያመናችሁሆይ! የሰይጣንን እርምጃዎች አትከተሉ:: የሰይጣንን እርምጃዎች የሚከተል ሰው ሁሉ ኃጢአትን ተሸከመ:: እርሱ በመጥፎና በሚጠላ ነገር ያዛልና፤ በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከናንተ አንድም ፈጽሞ (ከወንጀል) ባልጠራ ነበር:: ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያጠራል:: አላህ ሁሉንም ሰሚ ሁሉንም አዋቂ ነው።"},{"id":22,"translation":"22. ከናንተም መካከል የችሮታና የክብረት ባለቤቶች የሆኑት ክፍሎች ለቅርብ ዘመዶችና ለድሆችና በአላህም መንገድ ለተሰደዱ ሰዎች ምንንም ነገር ላይሰጡ አይማሉ:: ይቅርታም ያድርጉ:: ጥፋተኞቹንም ይለፉ። አላህ ለእናንተ ሊምር አትወዱምን ? አላህ መሓሪና አዛኝ ነው::"},{"id":23,"translation":"23. እነዚያ ጥብቆቹንና ከዝሙት ዘንጊዎቹን ምዕምናት የሚሰድቡ ሰዎች ሁሉ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ተረገሙ:: ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":24,"translation":"24. በእነርሱ ላይ ምላሶቻቸው እጆቻቸውና እግሮቻቸው ይሰሩት በነበሩት ነገር ሁሉ በሚመሰክሩባቸው ቀን ከባድ ቅጣት አለላቸው::"},{"id":25,"translation":"25. በዚያም ቀን አላህ ተገቢ ዋጋቸውን ይሞላላቸዋል:: አላህም ፍፁም ግልፅ እውነት መሆኑን ያውቃሉ።"},{"id":26,"translation":"26. መጥፎዎቹ ሴቶች ለመጥፎዎቹ ወንዶች፤መጥፎዎቹ ወንዶችም ለመጥፎዎቹ ሴቶች ብቻ የተገቡ ናቸው:: ጥሩዎቹ ሴቶችም ለጥሩዎቹ ወንዶች፤ ጥሩዎቹ ወንዶችም ለጥሩዎቹ ሴቶች ብቻ የሚገቡ ናቸው:: እነዚህ ጥሩዎቹም መጥፎዎቹ ከሚሉት ነገር ንጹህ የተደረጉ ናቸው:: ለእነርሱ በገነት ምህረትና መልካም ሲሳይ አለላቸው::"},{"id":27,"translation":"27. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከምታስፈቅዱና በባለቤቶቹ ላይ ሰላምታን እስከምታቀርቡ ድረስ በሌላ ሰዎች ቤቶች አትግቡ:: ይህ ጉዳይ ለእናንተም መልካም ነው:: እናንተ ትገነዘቡ ዘንድ በዚህ ታዘዛችሁ::"},{"id":28,"translation":"28. በውስጧም አንድንም ሰው ባታገኙ ለእናንተ እስከሚፈቀድላችሁ ድረስ አትግቧት። «ተመለሱ» ከተባላችሁም ተመለሱ:: እርሱ ለእናንተ የተሻለ ነው:: አላህ የምትሠሩትን ሁሉ አዋቂ ነው::"},{"id":29,"translation":"29. መኖሪያ ያልሆኑን ቤቶች ግን በውስጣቸው ለእናንተ ጥቅም ካላችሁ ሳታስፈቅዱ ብትገቡ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህም የምትገልጹትንም ሆነ የምትደብቁትን ሁሉ ያውቃል::"},{"id":30,"translation":"30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለአማኞች ንገራቸው አይኖቻቸውን (ያልተፈቀደላቸዉን) ከማየት ይከልክሉ:: ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ:: ይህ ለእነርሱ የተሻለ ነው:: አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::"},{"id":31,"translation":"31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለምዕመናት (ሴቶችም) ንገራቸው አይኖቻቸውን ይከልክሉ። ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ:: ጌጣቸውንም ግልጽ ከሆነው በስተቀር ሆን ብለው አይግለጡ:: ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ያጣፉ:: (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው (ሙስሊም ሴቶች) ወይም በእጆቻቸው ለያዙት (ባሪያ) ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለሆኑ ተከታዮች ወይም ለእነዚያ በሴቶች ሀፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ህጻኖች ካልሆነ በስተቀር አይግለጹ:: ከጌጣቸዉም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ:: ምዕመናኖች ሆይ! ከጀሀነም ቅጣት ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ ተጸጸቱ::"},{"id":32,"translation":"32. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከናንተ መካከል ትዳር የሌላቸውን ሰዎች አጋቡ:: ከወንዶች ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻችሁም ለጋብቻ ብቁ የሆኑትን ክፍሎች አጋቡ:: ድሆች ከሆኑም አላህ ከችሮታው ያከብራቸዋል:: አላህ ስጦታው ሰፊና ሁሉን አዋቂ ነውና::"},{"id":33,"translation":"33. እነዚያም የማግቢያን ጣጣ የማያገኙ ሰዎች አላህ ከችሮታው እስከሚያከብራቸው ድረስ ይጠብቁ። እነዚያንም እጆቻችሁ ከጨበጧቸው አገልጋዮች መካከል ገንዘብ ሰጥተው ነጻ ለመውጣት መጻጻፍን የሚፈልጉትን ከእነርሱ መልካም ነገርን ብታውቁ (ብታዩ) ተጻጻፏቸው:: አላህ ከሰጣችሁ ገንዘብም ስጧቸው:: ሴቶች ባሮቻችሁንም መጠበቅን ከፈለጉ የቅርቢቱን ህይወት ጥቅም ለመፈለግ ብላችሁ በዝሙት ተግባር ላይ አታስገድዷቸው:: የሚያስገድዳቸዉም ሰው አላህ ከመገደዳቸው በኋላ ለተገደዱት መሓሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":34,"translation":"34. (ሰዎች ሆይ!) ወደ እናንተ አብራሪ የሆኑን አናቅጽ ከእነዚያ ከበፊታችሁ ካለፉትም ምሳሌዎች ዓይነት ምሳሌን ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ አወረድን::"},{"id":35,"translation":"35. አላህ የሰማያትና የምድር ብርሃን (አብሪ) ነው፤ የብርሃኑ ምሳሌ በውስጡ መብራት እንዳለባት ዝግ መስኮት፤ መብራቱ በብርጭቆ ውስጥ የሆነ፤ ብርጭቆው ደግሞ ፍጹም ሉላዊ ክብ የምትመስል ምስራቃዊም ምዕራባዊም ካልሆነች፤ ከተባረከች የወይራ ዛፍ ዘይቷ እሳት ባይነካዉም እንኳ ሊያበራ የሚቀርብ ከሆነች ዘይት የሚቃጠል እንደሆነ መብራት ነው:: ይህ በብርሃን ላይ የሆነ ብርሃን ነው:: አላህ ወደ ብርሃኑ የሚሻውን ሰው ይመራል:: አላህም ለሰዎች ምሳሌዎችን ያቀርባል። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ ነውና።"},{"id":36,"translation":"36. አላህ እንዲከበሩና ስሙ በውስጣቸው እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ አወድሱት:: በውስጧ በጧትና በማታ ለርሱ ያጠሩታል።"},{"id":37,"translation":"37. አላህን ከማውሳትና ሶላትን ከመስገድ ዘካንም ከመስጠት ንግድም ሽያጭም የማያታልላቸው ልቦችና ዓይኖች በእርሱ የሚገላበጡበትን ቀን የሚፈሩ የሆኑ ሰዎች ያጠሩታል::"},{"id":38,"translation":"38. አላህም የሰሩትን ስራ መልካሙን ሊመነዳቸው ከችሮታዉም ሊጨምርላቸው ያጠሩታል:: አላህም ለሚሻው ሁሉ ያለ ግምት ይሰጣል::"},{"id":39,"translation":"39. እነዚያም በአላህ የካዱት ሰዎች መልካም ስራዎቻቸው በበረሃ ሜዳ እንዳለ ሲሪብዱ ነው:: ሲሪብዱ ውሃ የጠማው ሰው እንደውሃ አስቦት በቀረቡት ጊዜ ምንም ነገር ሆኖ እንደማያገኘው ነው፤ አላህንም እስፍራው ዘንድ ያገኘዋል:: ምርመራውንም ይሞላለታል፤ አላህም ምርመራው ፈጣን ነው።"},{"id":40,"translation":"40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወይም መጥፎ ስራዎቻቸው ከበላዩ ማዕበል ከበላዩ ደመና ያለበት ማዕበል በሚሸፍነው ጥልቅ ባህር ውስጥ እንዳሉ ጨለማዎች ነው:: እነዚያ ከፊላቸው ከከፊሉ በላይ ድርብርብ የሆኑ ጨለማዎች ናቸው:: በዚህች የተሞከረ ሰው እጁን ባወጣ ጊዜ ሊያያት አይደርስም:: አላህ ለእርሱ ብርሃንን ያላደረገለት ሰው ሁሉ ለእርሱ ምንጊዜም ምንም ብርሃን የለዉም::"},{"id":41,"translation":"41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማያትና በምድር ላይ ያለ ሁሉ በራሪዎችም ክንፎቻቸውን በአየር ላይ ያንሳፈፉ ሆነው ለእርሱ የሚያጠሩ መሆናቸውን አላወቅህምን? ሁሉም ስግደቱንና ማጥራቱን በእርግጥ አወቀ:: አላህ የሚሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነውና::"},{"id":42,"translation":"42. የሰማያትም ሆነ የምድር ግዛት የአላህ ነው:: መመለሻም ወደ አላህ ነው::"},{"id":43,"translation":"43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ደመናን የሚነዳ መሆኑን አላየህምን? ከዚያም ከፊሉን ከከፊሉ ያገናኛል፤ ከዚያም የተደራረበ ያደርገዋል፤ ዝናቡንም ከመካከሉ የሚወጣ ሆኖ ታየዋለህ፤ ከሰማይም ከደመናም በውስጡ ካሉት ጋራዎችም በረዶን ያወርዳል:: በእርሱም የሚሻውን ሰው በጉዳት ይነካል:: ከሻዉም ሰው ላይ ይመልሰዋል:: የብልጭታው ብርሃን ዓይኖችን ሊወስድ ይቀርባል::"},{"id":44,"translation":"44. አላህ ሌሊትንና ቀንን ያገላብጣል፤ በዚህም ለአስተዋዮች በእርግጥ ማስረጃ አለበት።"},{"id":45,"translation":"45. አላህም ተንቀሳቃሽን ሁሉ ከውሃ ፈጠረ:: ከእነርሱም መካከል በሆዱ ላይ የሚሄድ አለ፤ ከእነርሱም መካከል በሁለት እግሮቹ ላይ የሚሄድ አለ፤ ከእነርሱም መካከል በአራት እግሩ የሚሄድ አለ:: አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::"},{"id":46,"translation":"46. አብራሪን አናቅጽ በእርግጥ አወረድን፤ አላህ የሚሻውን ወደ ቀጥተኛ መንገድ ይመራዋል::"},{"id":47,"translation":"47. (አስመሳዮች) «በአላህና በመልዕክተኛው አምነናል ታዘናልም» ይላሉ። ከዚያም ከዚህ በኋላ ከእነርሱ ከፊሉ ይሸሻል:: እነዚያም ትክክለኛ አማኞች አይደሉም::"},{"id":48,"translation":"48. ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛዉም በመካከላቸው ለሚከሰቱ ጉዳዮች ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ ከእነርሱ መካከል ከፊሉ ወዲያውኑ ይሸሻሉ::"},{"id":49,"translation":"49. እውነቱም (ሐቁ) ለእነርሱ ቢሆን ወደ እርሱ ታዛዣች ሆነው ይመጣሉ።"},{"id":50,"translation":"50. በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ አለን? ወይስ በነብይነቱ ተጠራጠሩን? ወይስ አላህና መልዕክተኛው በእነርሱ ላይ የሚበድሉ መሆንን ይፈራሉን? ይልቁንም እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው::"},{"id":51,"translation":"51. የምዕምናን ቃል ግን የነበረው ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ «ሰማን ታዘዝንም» ማለት ብቻ ነው:: እነዚህ ማለት እነዚያ የፈለጉትን የሚያገኙቱ ናቸው::"},{"id":52,"translation":"52. አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ፤ አላህንም የሚፈራና ቁጣውን የሚጠነቀቀው፤ ፍላጎታቸውን የሚያገኙ እነዚያ እነርሱ ናቸው።"},{"id":53,"translation":"53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለዘመቻ ብታዛቸው በእርግጥ እንደሚወጡ የጠነከሩ መሓላዎቻቸውን በአላህ ስም ይምላሉ፤ «አትማሉ:: የታወቀ የንፍቅና መታዘዝ ነውና:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።» በላቸው።"},{"id":54,"translation":"54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ሙስሊሞች ሆይ!) «አላህንና መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: ብትሸሹም አትጎዱትም:: በእርሱ ላይ ያለበት የተገደደውን ማድረስ ብቻ ነው:: በእናንተም ላይ ያለባችሁ የተገደዳችሁትን መታዘዝ ብቻ ነው:: ብትታዘዙትም ወደ ቀናው መንገድ ትመራላችሁ በመልዕክተኛው ላይ ግልጽ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትምና።» በላቸው።"},{"id":55,"translation":"55. አላህ እነዚያን ከናንተ መካከል በትክክል ያመኑትንና መልካም ስራዎችን የሰሩትን እነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን እንደተካቸው ሁሉ በምድር ላይ በእርግጥ ሊተካቸው፤ ለእነርሱም ያንን የወደደላቸውን ሃይማኖታቸውን ሊያደላድልላቸው፤ ከፍርሃታቸዉም በኋላ ደህናነትን ሊለውጥላቸው የተስፋን ቃል ሰጥቷቸዋል:: በእኔ ምንንም የማያጋሩ ሆነው ሊገዙኝ ነው፤ ከዚያም በኋላ በሱ የካዱ ሰዎች እነዚያ አመጸኞች ማለት እነርሱ ብቻ ናቸው::"},{"id":56,"translation":"56. (ሙስሊሞች ሆይ!) ይታዘንላችሁ ዘንድ ሶላትን አስተካክላችሁ ስገዱ፣ ምጽዋትንም ስጡ፣ መልዕክተኛውንም ታዘዙ።"},{"id":57,"translation":"57. እነዚያን በአላህ የካዱትን በምድር ውስጥ የሚያቅቱ አድርገህ አታስብ፤ መኖሪያቸውም እሳት ናት:: ገሀነም በእርግጥም ምንኛ ትከፋ።"},{"id":58,"translation":"58. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው ባሮች እነዚያም ከናንተ መካከል ለአካለ መጠን ያልደረሱት (ህፃናት) በሶስት ጊዜ: ከጎህ ስግደት በፊት፤ በቀትር ልብሶቻችሁን በምታወልቁበት ጊዜና ከምሽት ስግደትም በኋላ ወደ እናንተ ለመግባት ሲፈልጉ ያስፈቅዷችሁ:: እነዚህ የእናንተ ሶስት የሐፍረተ ገላ መግለጫ ጊዜያቶች ናቸውና:: ከእነዚህ በኋላ ግን በእናንተም ሆነ በነሱ ላይ (ያለፈቃድ በመግባት) ኃጢአት የለም:: እናንተን ለማገልገል በዙሪያችሁ ዟሪዎች ናቸውና:: ከፊላችሁ በከፊሉ ላይ ዟሪ ነውና፤ ልክ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ ህግጋቱን ይገልጽላችኋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":59,"translation":"59. ከናንተም መካከል ለአቅመ አዳም በደረሱ ጊዜ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት ታላላቆች እንዳስፈቀዷችሁ ያስፈቅዱ:: ልክ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ አንቀፆቹን ያብራራል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::"},{"id":60,"translation":"60. (ሙስሊሞች ሆይ!) እነዚያ ጋብቻን የማይፈልጉት ባልቴቶች በጌጥ የተገለጹ ሳይሆኑ የላይ ልብሶቻቸውን ቢጥሉ በእርሱ ኃጢአት የለባቸዉም:: ግን መጠበቃቸው ለእነርሱ የተሻለ ነው:: አላህም ለሚባለው ሁሉ ሰሚ ለሁሉም አዋቂ ነው::"},{"id":61,"translation":"61. (ከሰዎች ጋር በመብላት) በዕውር (አይነስውር) ላይ ኃጢአት የለበትም:: በአንካሳም ላይ ኃጢአት የለበትም:: በበሽተኛም ላይ ኃጢአት የለበትም:: በነፍሶቻችሁም ላይ ከቤቶቻችሁ ወይም ከአባቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከእናቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከውድሞቻችሁ ቤቶች ወይም ከእህቶቻችሁ ቤቶች፤ ወይም ከአባት ወንድሞች አጎቶቻችሁ ቤቶች፤ ወይም ከአባት እህቶች አክስቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከእናት ወንድሞች የሹሞቻችሁ ቤቶች፤ ወይም ከእናት እህቶች የሜዎቻችሁ ቤቶች ወይም መክፈቻዎችን ከያዛችሁት ቤት ወይም ከወዳጃችሁ ቤት ብትበሉ ኃጢአት የለባችሁም:: ተሰብስባችሁ ወይም ተለያይታችሁ ብትበሉ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: ቤቶችንም በገባችሁ ጊዜ ከአላህ ዘንድ የሆነችን የተባረከች መልካም ሰላምታ በነፍሶቻችሁ ላይ ሰላም በሉ:: ልክ እንደዚህ አላህ አናቅጽን ለእናንተ ያብራራል፤ ልታውቁ ይከጅላልና::"},{"id":62,"translation":"62. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ትክክለኛ አማኞች ማለት እነዚያ በአላህና በመልዕክተኛው ያመኑት:: ከመልዕክተኛው ጋር በሚሰበሰብ ጉዳይ ላይ በሆኑ ጊዜ እስከሚያስፈቅዱት ድረስ የማይሄዱት ብቻ ናቸው:: እነዚያ የሚያስፈቅዱህ እርሱ እነዚያ በትክክል በአላህና በመልዕክተኛው የሚያምኑት ናቸው:: ለግል ጉዳያቸዉም ፈቃድ በጠየቁህ ጊዜ ከእነርሱ ላሻኸው ሰው ፍቀድለት:: ለእነርሱም ከአላህ ምህረትን ለምንላቸው:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":63,"translation":"63. አማኞች ሆይ በመካከላችሁ የመልዕክተኛውን ጥሪ ከፊላችሁ ከፊሉን እንደመጥራት አታድርጉት:: ከናንተ ውስጥ እነዚያን እየተከለሉ በመሽሎክሎክ የሚወጡትን አላህ በእርግጥ ያውቃቸዋል:: እነዚያም ትእዛዙን የሚጥሱ ሁሉ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ::"},{"id":64,"translation":"64. (ሙስሊሞች ሆይ! አስተዉሉ) በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: እናንተ በእርሱ ላይ ያላችሁበትን ሁኔታ በእርግጥ ያውቃል:: ወደ እርሱ የሚመለሱበትን ቀንም ያውቃል:: ከዚያ የሰሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል:: አላህም ነገሩን ሁሉ አዋቂ ነውና::"}]},{"id":25,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ያ ፉርቃንን (እውነትን ከውሸት የሚለየውን) ቁርኣን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስፈራሪ ይሆን ዘንድ ያወረደው (አምላክ) ክብሩ ላቀ (ጥራት ተገባው)።"},{"id":2,"translation":"2. አላህ ያ የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ የሆነ፤ ልጅንም ያልያዘ (ልጅም የሌለው)፤ በንግስናዉም ተጋሪ የሌለው፤ ሁሉንም ነገር የፈጠረና በትክክልም (በስርአት) የመጠነው አምላክ ነው።"},{"id":3,"translation":"3. ከሓዲያን ከእርሱ ከአላህ ሌላ ምንንም የማይፈጥሩንና እነርሱ ራሳቸው የሚፈጠሩ፤ ለነፍሶቻቸዉም (ከራሳቸው ላይ) ጉዳትን መከላከልም ሆነ ለራሳቸው ጥቅምን ማምጣት (ማስከበር) የማይችሉ፤ ለሞት ማብቃትም ሆነ ህይወትን መለገስና ከሞት መቀስቀስንም የማይችሉን አማልክትን አምላክ አድርገው ያዙ።"},{"id":4,"translation":"4. እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች «ይህ ቁርኣን እርሱ (ሙሐመድ) በራሱ የቀጠፈውና በእርሱም ላይ ሌሎች ህዝቦች ያገዙት ውሸት እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ። በእርግጥም በደልንና እብለትን ፈጸሙ።"},{"id":5,"translation":"5. «እነዚህ የመጀመሪያ ሰዎች ተረቶች (አፈታሪክ) ናቸው። አስጽፎታል፤ እናም በእርሱ ላይ ጧትና ማታ ትነበብለታለች።» አሉ።"},{"id":6,"translation":"6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው:: እርሱ መሓሪና አዛኝ ነውና።» በላቸው።"},{"id":7,"translation":"7. አሉም: «ይህ መልዕክተኛ ምን አይነት መልዕክተኛ ነው? ምግብ የሚመገብ ወደ ገበያ የሚመላለስ፤ ከእርሱ ጋር አስፈራሪ ይሆን ዘንድ ወደ እርሱ መልአክ (በገሃድ) አይወረድም ኖሯልን?"},{"id":8,"translation":"8. «ወይም ወደ እርሱ ድልብ አይሰጠዉምን? ወይም ከእርሷ የሚበላባት አትክልት ለእርሱ አትኖረዉምን?» አሉ። «በዳዮችም ላመኑት የተደገመበትን ሰው እንጂ ሌላን አትከተሉም።» አሉ።"},{"id":9,"translation":"9.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ላንተ ምሳሌዎችን እንዴት እንዳደረጉልህና ከዚያም እንዴት እንደ ተሳሳቱ ተመልከት:: ወደ እውነት ለመድረስ መንገድንም አይችሉም::"},{"id":10,"translation":"10. ያ ቢሻ ከዚህ ካሉት የተሻለን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው አትክልት ስፍራዎችን ላንተ የሚያደርግልህ ህንጻ ቤቶችንም የሚያደርግልህ የሆነው ጌታ ችሮታው በዛ:: (ክብሩ ላቀ)"},{"id":11,"translation":"11. ይልቁንም እነርሱ በትንሳኤ አስተባበሉ:: በትንሳኤ ላስተባበለም ሁሉ አቃጣይ እሳት አዘጋጅተናል::"},{"id":12,"translation":"12. ከሩቅ ስፍራ ባየቻቸው ጊዜ የእርሷን የቁጭት መገንፈልንና ማናፋትን ይሰማሉ::"},{"id":13,"translation":"13. ከጓደኞቻቸው ጋር (ከሰይጣኖቻቸው ጋር) በአንድ የታሰሩ ሆነዉም ከእርሷ በጠባብ ስፍራ በተጣሉ ጊዜ በዚያ ስፍራ ጥፋትን ይጠራሉ:: (ዋ ጥፋታችን! ይላሉ)።"},{"id":14,"translation":"14. ዛሬማ አንድን ጥፋት ብቻ አትጥሩ:: ይልቁንም ብዙን ጥፋት ጥሩ ይባላሉ::"},{"id":15,"translation":"15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በላቸው: «ይህ የተሻለ ነውን? ወይስ ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጡት የዘልዓለሟ ገነት?» ገነት ለእነርሱ ምንዳና መመለሻ ሆነች።"},{"id":16,"translation":"16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ሆነው የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው:: ይህ ተስፋ ከጌታህ ሊለመን የሚገባው ተስፋ ነው::"},{"id":17,"translation":"17. እነርሱንና ከአላህ ሌላ የሚገዟቸውን የሚሰበስብበትንና «እናንተ እነዚህን ባሮቼን አሳሳታችሁን? ወይስ እነርሱው እራሳቸው መንገድን ሳቱ?» የሚልበትን ቀን አስታውስ።"},{"id":18,"translation":"18. (ተመላኪዎቹም): «አላህ ሆይ! ጥራት ይገባህ:: ከአንተ ሌላ ረዳቶችን ልንይዝ አይገባንም:: ግን እነርሱንም ሆነ አባቶቻቸውን መገንዘብን እስከ ተውና ጠፊ ህዝቦችም እስከሚሆኑ ድረስ አጣቀምካቸው።» ይላሉ።"},{"id":19,"translation":"19. በምትሉትም አማልክቶቻችሁ አስዋሹዋችሁ:: ቅጣቴን መገፍተርንም ሆነ እራሳችሁን መርዳት አትችሉም:: ከናንተም የሚበድልን ሰው ታላቅን ቅጣት እናቀምሰዋለን:: (ይባላሉ።)"},{"id":20,"translation":"20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም ከመልዕክተኞች እነርሱ በእርግጥ ምግብን የሚበሉ በገበያዎችም የሚሄዱ ሆነው እንጂ አላክንም:: ከፊላችሁንም ለከፊሉ ፈተና አድርገናል:: ትታገሳላችሁን? ጌታህም ተመልካች ነው::"},{"id":21,"translation":"21. እነዚያ መገናኘታችንን የማይጠብቁ ሰዎች «በእኛ ላይ ለምን መላእክት አልወረደም ወይም ጌታችንን ለምን አናይም?» አሉ። በነፍሶቻቸው ውስጥ በእርግጥ ኮሩ። ታላቅንም አመጽ አመጹ።"},{"id":22,"translation":"22. መላዕክትን በሚያዩበት ቀን በዚያ ጊዜ ለአመጸኞች የምስራች የላቸዉም። (መላዕክቱም) «የተከለከለ ክልክል» ይላሉ።"},{"id":23,"translation":"23. ወደ ሰሩት ስራም እናስባለን:: ከዚያም እንደ ተበተነ ትቢያ እናደርገዋለን::"},{"id":24,"translation":"24. የገነት ሰዎች በዚያ ቀን በመርጊያ የተሻሉ በማረፊያም በጣም ያማሩ ናቸው::"},{"id":25,"translation":"25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰማይ በደመና የምትቀደድበትንና መላእክትም መውረድን የሚወርዱበትን ቀን አስታውስ።"},{"id":26,"translation":"26. እውነተኛው ንግስና በዚያ ቀን ለአር-ረህማን ብቻ ነው:: በከሓዲያን ላይ አስቸጋሪ ቀን ነው::"},{"id":27,"translation":"27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዳይም «ዋ ምኞቴ! ከመልዕክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ምነው ይዤ በሆነ፤ እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆችን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)::"},{"id":28,"translation":"28. «ዋ ጥፋቴ! እገሌን በወዳጅነት ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ።"},{"id":29,"translation":"29. (የእምነት ቃል የሆነው) «ቁርኣን ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ።» ይላል:: ሰይጣንም ለሰው አጋላጭ ነውና።"},{"id":30,"translation":"30. መልዕክተኛዉም (ሙሐመድ) «ጌታዬ ሆይ! ህዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ ነገር አደረጉት።» አለ።"},{"id":31,"translation":"31. ልክ እንደዚሁም ለነብያቱ ሁሉ ከአመጸኞች የሆነ ጠላትን አድርገናል:: መሪነትና ረዳትነት በጌታህ በቃ።"},{"id":32,"translation":"32. እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎችም «ቁርኣንን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ በአንድ ጊዜ አልተወረደለትም።» አሉ። ልክ እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ (ከፋፍለን በተለያየ አወረድነው):: ቀስ በቀስ መለያየትንም ለየነው::"},{"id":33,"translation":"33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በየትኛዉም ጥያቄ አይመጡብህም እውነተኛውን መልስና መልካም ፍቹንም የምናመጣልህ ብንሆን እንጅ::"},{"id":34,"translation":"34. እነዚያ በፊቶቻቻው ላይ እየተጎተቱ ወደ ገሀነም የሚሰበሰቡት እነዚያ ስፍራቸው የከፋ መንገዳቸዉም የጠመመ ናቸው።"},{"id":35,"translation":"35. በእርግጥም ለሙሳ መጽሐፍን ሰጠነው:: ከእርሱም ጋር ወንድሙን ሃሩንን ረዳት አደረግንለት::"},{"id":36,"translation":"36. «ወደ እነዚያም በተዓምራታችን ወደ አስተባበሉት ህዝቦች ሂዱ።» አልናቸው። (አስዋሿቸዉም) ማጥፋትንም አጠፋናቸው።"},{"id":37,"translation":"37. የኑህን ሰዎችም መልዕክተኞችን ባስተባበሉ ጊዜ አሰመጥናቸው:: ለሰዎችም መገሰጫ አደረግናቸው፤ ለበደለኞችም አሳማሚን ቅጣት አዘጋጅተናል::"},{"id":38,"translation":"38. ዓድንም፤ሰሙድንም፤ የረስ ሰዎችንና በዚህ መካከል የነበሩትንም ብዙ የክፍለ ዘመናት ህዝቦችንም አጠፋን።"},{"id":39,"translation":"39. ሁሉንም (ገሠጽን):: ለእነርሱ ምሳሌዎችን ገለጽን:: ሁሉንም ማጥፋትን አጠፋናቸዉም::"},{"id":40,"translation":"40. በዚያችም ክፉ ዝናብን በተዘነበችው ከተማ ላይ (የመካ ከሓዲያን) በእርግጥ መጥተዋል:: የሚያዩዋት አልነበሩምን? በእውነቱ መቀስቀስን የማይፈሩ ነበሩ::"},{"id":41,"translation":"41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባዩህም ጊዜ (እንዲህ) እያሉ መሳለቂያ እንጅ ሌላ አያደርጉህም: «ያ አላህ መልዕክተኛ እድርጎ የላከው ይህ ነውን?"},{"id":42,"translation":"42. «እነሆ በእርሷ ላይ መታገሳችን (ጽናታችን) ባልነበረ ኖሮ ከአማልክቶቻችን ሊያሳስተን ቀርቦ ነበር።» ሲሉም ይሳለቃሉ:: ወደ ፊትም ቅጣትን በሚያዩ ጊዜ መንገድን በጣም የተሳሳተው ማን እንደ ሆነ በእርግጥ ያኔ ያውቃሉ::"},{"id":43,"translation":"43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘን ሰው አየህን? አንተም በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን?"},{"id":44,"translation":"44. ይልቁንም አብዛኛዎቻቸው የሚሰሙ ወይም የሚያውቁ መሆናቸውን ታስባለህን? እነርሱ እንደ እንስሳዎች እንጂ ሌላ አይደሉም:: ከቶውንም እነርሱ ከእንስሳዎች በባሰ መንገድን የተሳሳቱ ናቸው::"},{"id":45,"translation":"45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ጥላን እንዴት እንደ ዘረጋ አላየህምን? በሻም ኖሮ የረጋ ባደረገው ነበር:: ከዚያ ጸሐይን በእርሱ ላይ ምልክት አደረግን።"},{"id":46,"translation":"46. ከዚያም ቀስ በቀስ ወደ እኛ ሰበሰብነው::"},{"id":47,"translation":"47. እርሱም ያ ለእናንተ ሌሊትን ልብስ እንቅልፍንም ማረፊያ ያደረገ:: ቀንንም መተኛ ያደረገላችሁ አምላክ ነው።"},{"id":48,"translation":"48. እርሱ (አላህ) ያ ንፋሶችን አብሳሪዎች ሲሆኑ ከዝናቡ በስተፊት የላከ ነው:: ከሰማይም አጥሪ ውሃን አወረድን::"},{"id":49,"translation":"49. በእርሱ የሞተችን ሀገር ህያው ልናደርግበት፤ ከፈጠርነዉም ፍጡር እንስሳዎችንና ብዙ ሰዎችንም ልናጠጣበት አወረድነው።"},{"id":50,"translation":"50. ጸጋችንን ይገነዘቡም ዘንድ በመካከላቸው ከፋፈልነው አበላለጥነዉም:: ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች ክህደትን እንጂ እንቢ አሉ::"},{"id":51,"translation":"51. በሻንም ኖሮ በየከተማይቱ አስፈራሪን በላክን ነበር::"},{"id":52,"translation":"52. ከሓዲያንን አትታዘዛቸው:: በእርሱም (በቁርኣን) ታላቅን ትግል ታገላቸው::"},{"id":53,"translation":"53. እርሱ ያ ሁለትን ባህሮች አጎራብቶ የለቀቀ ነው:: አንዱ ጥም የሚቆርጥና ጣፋጭ ነው:: ሌላኛው ደግሞ የሚመረግግ ጨው ነው:: በመካከላቸዉም ከመቀላቀል መለያንና የተከለለን ክልል ያደረገ ነው::"},{"id":54,"translation":"54. እርሱም ያ ከውሃ ሰውን የፈጠረ የዝምድናና የአማችም ባለቤት ያደረገው ነው:: ጌታህም ሁሉን ነገር ቻይ ነው::"},{"id":55,"translation":"55. ከአላህ ሌላ የማይጠቅማቸውንና የማይጎዳቸውን አካል ይገዛሉ:: ከሓዲ በጌታው ላይ (በማመጽ ለሰይጣን) ረዳት ነው::"},{"id":56,"translation":"56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን እንጂ አላክንህም::"},{"id":57,"translation":"57. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርሱ ላይ ዋጋን በፍጹም አልጠይቃችሁም። ወደ ጌታው መልካም መንገድን ለመያዝ የሻ ሰው ይስራ።» በላቸው።"},{"id":58,"translation":"58. በዚያም በማይሞተው ህያው አምላክ ላይ ተመካ፤ ከማመስገንም ጋር አጥራው:: የባሮቹን ኃጢአቶች ውስጥ በማወቅ በእርሱ በቃ::"},{"id":59,"translation":"59. ያ ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ ብቻ የፈጠረ ነው። ከዚያም በዐርሹ ላይ ከፍ አለ:: አር-ረህማን ነው:: ከእርሱም አዋቂን ጠይቅ።"},{"id":60,"translation":"60. ለእነርሱም «ለአር-ረህማን ስገዱ።» በተባሉ ጊዜ «አር-ረህማን ማን ነው? ለምታዘንና ለማናውቀው እንሰግዳለን እንዴ?» ይላሉ። ይህም መራቅን ጨመራቸው። {1}","footnotes":"{1} እዚህ የንባብ ሱጁድ (ሱጁዱ ትላወህ) ይደረጋል።"},{"id":61,"translation":"61. ያ በሰማይ ቡሩጆችን ያደረገና በእርሷም አንጸባራቂን ጸሐይ አብሪ ጨረቃንም የፈጠረ ጌታ ክብሩ በጣም ላቀ።"},{"id":62,"translation":"62. እርሱም ያ ያመለጠውን ስራ ማስታወስን ለሚፈልግ ወይም ማመስገንን ለሚፈልግ ሌሊትንና ቀንን ተተካኪ ያደረገ ነው::"},{"id":63,"translation":"63. የአር-ረህማን ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚሄዱት፤ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሯቸው ጊዜ ሰላም የሚሉት ናቸው::"},{"id":64,"translation":"64. እነዚያም ለጌታቸው በግንባራቸው ተደፊዎችና ቋሚዎች (ሰጋጆች) ሆነው የሚያድሩት ናቸው።"},{"id":65,"translation":"65. እነዚያም (እንዲህ) የሚሉት ናቸው: «ጌታችን ሆይ! የገሀነምን ቅጣት ከእኛ ላይ መልስልን ቅጣቷ የማይለይለቅ ነውና።"},{"id":66,"translation":"66. «እርሷ መርጊያና መቀመጫ ለመሆን ከፋች!» የሚሉት ናቸው።"},{"id":67,"translation":"67. እነዚያም በለገሱ ጊዜ የማያባክኑት የማይቆጥቡትም ናቸው:: በዚህም መካከል ልግስናቸው ትክክለኛ የሆነ ነው::"},{"id":68,"translation":"68. እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፤ ያችንም አላህ እርም ያደርጋትን ነፍስ ያለ ህግ የማይገድሉ እና የማያመነዝሩት ናቸው:: ይህንን የሚፈጽም ሰው ወንጀለኛ ይሆናል::"},{"id":69,"translation":"69. በትንሳኤ ቀን ቅጣት ይደራረብበታል:: በእርሱም ውስጥ የተዋረደ ሆኖ ዘልአለሙን ይኖራል::"},{"id":70,"translation":"70. ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም የሰራ ሰው ብቻ ሲቀር እነዚያም አላህ መጥፎ ስራዎቻቸውን በመልካም ስራዎች ይለውጣል:: አላህም እጅግ መሓሪና አዛኝ ነው::"},{"id":71,"translation":"71. ተጸጽቶ የተመለሰና መልካምን ተግባር የሰራ እርሱ በአላህ ዘንድ የተወደደን መመለስ ወደ አላህ ይመለሳል::"},{"id":72,"translation":"72. እነዚያ በሐሰት የማይጣዱ፤ በውድቅ ቃል (ተናጋሪ) አጠገብም ባለፉ ጊዜ የተከበሩ ሆነው የሚያልፉ ናቸው::"},{"id":73,"translation":"73. እነዚያም በጌታቸው አናቅጽ በተገሠጹ ጊዜ (የተረዱ ተቀባዮች ሆነው እንጂ) ደንቆሮዎችና እውሮች ሆነው በእርሷ ላይ የማይደፉት ናቸው::"},{"id":74,"translation":"74. እነዚያ «ጌታችን ሆይ! ከሚስቶቻችንና ከዘሮቻችን ለዓይኖች መርጊያን ለእኛ ስጠን፤ አላህን ለሚፈሩትም መሪ አድርገን።» የሚሉ ናቸው::"},{"id":75,"translation":"75. እነዚያ በመታገሳቸው የገነትን ሰገነቶች ይመነዳሉ:: በእርሷም ውስጥ ውዳሴንና ሰላምታን ይሰጣሉ::"},{"id":76,"translation":"76. በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ሆነው (ይሰጣሉ):: መርጊያና መኖሪያይቱ ገነት አማረች::"},{"id":77,"translation":"77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ) «ጸሎታችሁ ባልነበረ ኖሮ ጌታዬ እናንተን ከምንም አይቆጥራችሁም ነበር:: አስተባበላችሁ:: እናም ወደ ፊት ቅጣት ያዣችሁ ይሆናል።» በላቸው።"}]},{"id":26,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ጣ፤ሲን፤ሚይም::"},{"id":2,"translation":"2. እነዚህ ግልጽ የሆነው መጽሀፍ አናቅጽ ናቸው::"},{"id":3,"translation":"3.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን አማኞች ባለ መሆናቸው በቁጭት ነፍስህን እንዳታጠፋ ይፈራልሃል (ያሰጋል)::"},{"id":4,"translation":"4. ብንሻ ኖሮ በእነርሱ ላይ ከሰማይ ተዓምርን እናወርድና አንገቶቻቸው (መሪዎቻቸው) ለእርሷ ተዋራጆች እናደርጋለን::"},{"id":5,"translation":"5. ከአር-ረህማን ዘንድ አዲስ የተወረደ ተግሳፅ አይመጣላቸዉም:: ከእርሱ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጂ::"},{"id":6,"translation":"6. በእርግጥም አስተባበሉ:: የዚያም በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ወሬዎች ፍጻሜ ይመጣባቸዋል::"},{"id":7,"translation":"7.ወደ ምድርም በውስጧ ከመልካም በቃይ ጎሳ ብዙን እንዳበቀልን አላዩምን።"},{"id":8,"translation":"8. በዚህ አስደናቂ ምልክት አለበት፤ አብዛኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም።"},{"id":9,"translation":"9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በትክክል ሁሉን አሸናፊና አዛኝ ነው::"},{"id":10,"translation":"10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ሙሳን «ወደ እነዚያ በደለኛ ህዝቦች ሂድ።» በማለት በጠራው ጊዜ የሆነውን አስታውስ።"},{"id":11,"translation":"11. «ወደ ፈርዖን ህዝቦች አላህን አይፈሩምን?»"},{"id":12,"translation":"12. ሙሳም «ጌታዬ ሆይ! እኔ ያስተባብሉኛል ብዬ እፈራለሁ።"},{"id":13,"translation":"13. «ልቤም ይጠባል፤ ምላሴም ይንተባተባል። ስለዚህ ወደ ሃሩንም ላክ።"},{"id":14,"translation":"14. «በተጨማሪም ለእነርሱም በእኔ ላይ (የደም) ወንጀል አላቸው:: ስለዚህ እንዳይገድሉኝም እፈራለሁ።» አለ።"},{"id":15,"translation":"15. አላህ አለ: «ተው! አይነኩህም ሁለታችሁም በተአምሮታችን ታጅባችሁ ሂዱ። እኛ ከናንተ ጋር ሁነን ሰሚዎች ነንና።"},{"id":16,"translation":"16. «ወደ ፈርዖንም ሂዱና። በሉትም: ‹እኛ የዓለማት ጌታ መልዕክተኞች ነን።"},{"id":17,"translation":"17. «‹የኢስራኢልን ልጆችም ከእኛ ጋር ልቀቅልን።›» (በሉት)"},{"id":18,"translation":"18. ፈርዖንም አለ፡ «ልጅ ሆንህ በእኛ ውስጥ አላሳደግንህምን? በእኛ ውስጥም ከዕድሜህ ብዙ ዓመታትን አልተቀመጥክምን?"},{"id":19,"translation":"19. «ያችን የሰራሃትን ስራስ አልሰራህምን? አንተ ከውለታ ቢሶች ነህ።» (አለ)።"},{"id":20,"translation":"20. ሙሳም አለ፡ «ያን ጊዜ እኔም ከተሳሳቱት ሆኜ ሰራኋት።"},{"id":21,"translation":"21. «በፈራኋችሁም ጊዜ ከናንተ ሸሸሁ። ጌታዬም ለእኔ ጥበብን ሰጠኝ:: ከመልዕክተኞችም አደረገኝ:።"},{"id":22,"translation":"22. «ይህችም የኢስራኢልን ልጆች ባሪያ በማድረግህ በእኔ ላይ የምትመጻድቅባት ጸጋ ናት።»"},{"id":23,"translation":"23. ፈርዖን: «ሙሳ ሆይ! ላከኝ የምትለው የዓለማት ጌታ ምንድን ነው?» አለ።"},{"id":24,"translation":"24. ሙሳ፡- «የሰማያት የምድርና በመካከላቸዉም ያለው ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው። የምታረጋግጡ ብትሆኑ ነገሩ ይህ ነው።» አለው።"},{"id":25,"translation":"25. ፈርዖንም ዙሪያውን ላሉት ሰዎች: «አትሰሙምን?» አለ።"},{"id":26,"translation":"26. ሙሳ፡- «ጌታችሁና የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው።» አለ።"},{"id":27,"translation":"27. ፈርዖን፡- «ያ ወደ እናንተ የተላከው መልዕክተኛችሁ በእርግጥ ዕብድ ነው።» አለ።"},{"id":28,"translation":"28. ሙሳ፡- «(አላህ) የምስራቅና የምዕራብ በመካከላቸዉም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ነው:: ታውቁ እንደሆናችሁ (እመኑበት)።» አለ።"},{"id":29,"translation":"29. ፈርዖን: «ከእኔ ሌላ አምላክን ብትይዝ በእውነቱ ከእስረኞቹ አደርግሃለሁ።» አለ።"},{"id":30,"translation":"30. ሙሳ፡- «ግልጽ የሆነ አስረጅ ባመጣም እንኳን?» አለው።"},{"id":31,"translation":"31. ፊርዓውን «እንግዲያውስ ከእውነተኞች እንደሆንክ አስረጁን አምጣው።» አለ።"},{"id":32,"translation":"32. በትሩንም ጣለ:: እርሷም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ሆነች::"},{"id":33,"translation":"33 እጁንም አወጣ እርሷም ወዲያውኑ ለተመልካቾች ነጭ (የምታበራ) ሆነች::"},{"id":34,"translation":"34. ፈርዖንም በዙሪያው ላሉት መማክርት አለ: «ይህ በእርግጥ አዋቂ ድግምተኛ ነው።"},{"id":35,"translation":"35. «ከምድራችሁ በድግምት ሊያወጣችሁ ይፈልጋልና ምንን ታዛላችሁ?» አላቸው።"},{"id":36,"translation":"36. እነርሱም አሉ: «እርሱንና ወንድሙን አቆያቸው:: ወደየከተሞቹ ሁሉ ሰብሳቢዎችን ላክ።"},{"id":37,"translation":"37. «በጣም አዋቂ ድግምተኞችን ሁሉ ያመጡልሃልና።» አሉ።"},{"id":38,"translation":"38. ድግምተኞችም በታወቀ ቀን ቀጠሮ ተሰበሰቡ::"},{"id":39,"translation":"39. ለሰዎቹም ተባለ: «እናንተ ተሰብስባችኋልን?"},{"id":40,"translation":"40. «ድግምተኞቹን እነርሱ አሸናፊዎች ቢሆኑ እንከተል ዘንድ» ተባለ።"},{"id":41,"translation":"41. ድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ለፈርዖን: «እኛ አሸናፊዎች ብንሆን ለእኛ ዋጋ አለን?» አሉት።"},{"id":42,"translation":"42. እርሱም( ፈርዖን) «አዎን። እናንተ ያን ጊዜ እኔ ዘንድ ከባለሟሎቹ ትሆናላችሁ።» አላቸው።"},{"id":43,"translation":"43. ሙሳ ለእነርሱ: «የምትጥሉትን ጣሉ።» አላቸው።"},{"id":44,"translation":"44. ገመዶቻቸውንና በትሮቻቸውንም ጣሉ:: «በፈርዖንም ክብር ይሁንብን። እኛ በእርግጥ አሸናፊዎች ነን።» አሉ።"},{"id":45,"translation":"45. ሙሳም ብትሩን ጣለ:: ወዲያዉም እርሷ የሚያስመስሉትን ሁሉ ትውጣለች::"},{"id":46,"translation":"46. ከዚያም ድግምተኞቹ ሰጋጆች ሆነው ሱጁድ አደረጉ(ወረዱ)።"},{"id":47,"translation":"47. እነርሱም አሉ፡- «በዓለማት ጌታ አመንን።"},{"id":48,"translation":"48. «በሙሳና በሃሩን ጌታ (አመንን)።» (አሉ)"},{"id":49,"translation":"49. ፈርዖንም «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁን? እርሱ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ታላቃችሁ ነው። ወደፊትም በእርግጥ የሚያገኛችሁን ታውቃላችሁ:: እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን ቀኝና ግራን (በማናጋት) በማፈራረቅ እቆራርጣችኋለሁ:: ሁላችሁንም እሰቅላችኃለሁ።» አለ።"},{"id":50,"translation":"50. እነርሱም አሉ፡- «ጉዳት የለብንም እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን።"},{"id":51,"translation":"51. «እኛ የምዕምናን መጀመሪያ በመሆናችን ጌታችን ኃጢአቶቻችንን ለኛ ሊምር እንከጅላለን።»"},{"id":52,"translation":"52. ወደ ሙሳም «ባሮቼን ይዘህ ሌሊት ሂድ እናንተ የሚከተሏችሁ ናችሁና።» ስንል ላክን።"},{"id":53,"translation":"53. ፈርዖንም በየከተሞቹ ሰብሳቢዎችን (እንዲህ ሲል) ላከ::"},{"id":54,"translation":"54. «እነዚህ ጥቂቶቹ ቡድኖች ናቸው።"},{"id":55,"translation":"55. «እነርሱም ለእኛ አስቆጪዎች ናቸው።"},{"id":56,"translation":"56. «እኛም ብዙዎች ጥንቁቆች ነን።» አለ።"},{"id":57,"translation":"57. አወጣናቸዉም፤ ከአትክልቶችና ከምንጮች::"},{"id":58,"translation":"58. ከድልቦችም ከመልካም መቀመጫዎችም፤"},{"id":59,"translation":"59. ልክ እንደዚሁ ለኢስራኢል ልጆች አወረስናትም::"},{"id":60,"translation":"60. ጸሐይዋ ስትወጣም ተከተሏቸው::"},{"id":61,"translation":"61. ሁለቱ ቡድኖችም በተያዩ ጊዜ የሙሳ ጓዶች «እኛ (የፈርዖን ሰዎች) የሚደርሱብን ነን።» አሉ።"},{"id":62,"translation":"62. ሙሳ «በፍፁም! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው። በእርግጥ ይመራኛል።» አለ።"},{"id":63,"translation":"63. ወደ ሙሳም «ባህሩን በበትርህ ምታው።» ስንል ላክንበት:: ከዚያ መታውና ተከፈለ፤ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ሆነ::"},{"id":64,"translation":"64. እዚያም ዘንድ ሌሎችን አቀረብን::"},{"id":65,"translation":"65. ሙሳንና ከእርሱ ጋር ያሉትንም ሰዎች ሁሉንም አዳን::"},{"id":66,"translation":"66. ከዚያም ሌሎቹን አሰመጥን::"},{"id":67,"translation":"67. በዚህ ውስጥ ታላቅ ተዐምር አለበት፤ አብዛሀኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም።"},{"id":68,"translation":"68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ አላህ እርሱ አሸናፊና አዛኝ ነው::"},{"id":69,"translation":"69. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱም (በህዝቦችህ) ላይ የኢብራሂምን ወሬ አንብብላቸው::"},{"id":70,"translation":"70. ለአባቱና ለህዝቦቹ «ምንን ትገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ።"},{"id":71,"translation":"71. «ጣኦታትን እንገዛለን:: እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን።» አሉ።"},{"id":72,"translation":"72. ኢብራሂም አለ፡- «በጠራችኋቸው ጊዜ ይሰሟችኋልን?"},{"id":73,"translation":"73. «ወይስ ይጠቅሟችኋልን? ወይስ ይጎዷችኋልን?»"},{"id":74,"translation":"74. «የለም! ነገር ግን አባቶቻችን ልክ እንደዚሁ ሲሰሩ አገኘን(ና እኛም እነርሱን እንከተላለን።») አሉት።"},{"id":75,"translation":"75. እርሱም አለ: «ትገዙት የነበራችሁትን አስተዋላችሁን?"},{"id":76,"translation":"76. «እናንተም የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁም እየተገዛችሁት ያለውን።"},{"id":77,"translation":"77. «እነርሱም ጣኦቶቹ ለእኔ ጠላቶች ናቸው:: የዓለማት ጌታ ብቻ ሲቀር:: እርሱማ ወዳጄ ነው።"},{"id":78,"translation":"78. «እርሱ ያ የፈጠረኝ ነው:: እርሱም ይመራኛል።"},{"id":79,"translation":"79. «ያም እርሱ የሚያበላኝና የሚያጠጣኝም ነው።"},{"id":80,"translation":"80. «በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል።"},{"id":81,"translation":"81. «ያም የሚገድለኝ ከዚያም ህያው የሚያደርገኝ ነው።"},{"id":82,"translation":"82. «ያም በፍርዱ ቀን ኃጢአቴን ሊምርልኝ የምከጅለው ነው።» (አለ)"},{"id":83,"translation":"83. (ኢብራሂምም) «ጌታዬ ሆይ! እውቀትን ስጠኝ በደጋጎቹም ሰዎች አስጠጋኝ።"},{"id":84,"translation":"84. «በኋለኞቹም ህዝቦች ውስጥ ለእኔ መልካም ዝናን አድርግልኝ።"},{"id":85,"translation":"85. «የጸጋይቱን ገነት ከሚወርሱትም ሰዎች አድርገኝ።"},{"id":86,"translation":"86. «ለአባቴም ኃጢያቱን ማር። እርሱ ከተሳሳቱት ነበርና።"},{"id":87,"translation":"87. «በሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ።"},{"id":88,"translation":"88. «ገንዘብም ሆነ ልጆች በማይጠቅሙበት ቀን፤"},{"id":89,"translation":"89. «ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ቢሆን አንጂ።»"},{"id":90,"translation":"90. ገነትም ለጥንቁቆቹ በምትቀረብበት ቀን፤"},{"id":91,"translation":"91. ገሀነምም ለጠማሞቹ በምትገለጽበት ቀን::"},{"id":92,"translation":"92. ለእነርሱም «እነዚያ ትገዟቸው የነበራችሁት የት ናቸው?"},{"id":93,"translation":"93. « ከአላህ ሌላ ሲሆኑ (ትገዟቸው የነበራችሁ) ይረዱዋችኋልን? ወይስ ለራሳቸው ይረዳሉን?» በሚባል ቀን።"},{"id":94,"translation":"94. በውስጧም እነርሱና ጠማሞች በፊቶቻቸው ተጥለው ይንከባለላሉ::"},{"id":95,"translation":"95 የሰይጣንም ሰራዊቶች መላዉም ይጣላሉ::"},{"id":96,"translation":"96. እነርሱም በርሷ ውስጥ የሚከራከሩ ሆነው ይላሉ:"},{"id":97,"translation":"97. «በአላህ እንምላለን፤ እኛ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነብርን።"},{"id":98,"translation":"98. «በዓለማት ጌታ ባስተካከልናችሁ ጊዜ።"},{"id":99,"translation":"99. «አመጸኞቹም እንጅ ሌላ አላሳሳተንም።"},{"id":100,"translation":"100. «ከአማላጆችም ለኛ ምንም የለንም።"},{"id":101,"translation":"101. «አዛኝ ወዳጅም የለንም።"},{"id":102,"translation":"102 «ለእኛም አንዲት ጊዜ እንኳን የመመለስ እድል በኖረንና ከትክክለኛ አማኞች በሆን እንመኛለን።» ይላሉ።"},{"id":103,"translation":"103. በዚህ ውስጥ አስደናቂ ግሣጼ አለበት:: አብዛሀኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም::"},{"id":104,"translation":"104. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እርሱ በእርግጥ ሁሉን አሸናፊዉና አዛኙ ነው::"},{"id":105,"translation":"105. የኑህ ህዝቦች መልዕክተኞችን አስተባበሉ::"},{"id":106,"translation":"106. ወንድማቸው ኑህ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ፡ «አትጠነቀቁምን?"},{"id":107,"translation":"107. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።"},{"id":108,"translation":"108. «አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም።"},{"id":109,"translation":"109. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም:: ዋጋዬ ከዓለማት ጌታ ብቻ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም።"},{"id":110,"translation":"110. «አላህንም ፍሩ። ታዘዙኝም።»"},{"id":111,"translation":"111. እነርሱም «ወራዶቹ ብቻ የተከተሉህ ሆነህ ላንተ እናምናለን?» አሉት።"},{"id":112,"translation":"112. እርሱም አላቸው፡- «ይሰሩት በነበሩት ነገር ምን ዕውቀት አለኝና?"},{"id":113,"translation":"113. «ምርመራቸው በጌታዬ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም:: ብታውቁ ኖሮ ይህንን ትረዱት ነበር።"},{"id":114,"translation":"114. «እኔ አማኞችን አባራሪ አይደለሁም።"},{"id":115,"translation":"115. «እኔም እኮ ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» (አለ)"},{"id":116,"translation":"116. «ኑህ ሆይ! ከምትለው ባትከለከል በእርግጥ ከሚወገሩት ትሆናለህ።» አሉት።"},{"id":117,"translation":"117. እርሱም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! ህዝቦቼ አስተባበሉኝ።"},{"id":118,"translation":"118. «በእኔና በእነርሱም መካከል ተገቢ ፍርድን ፍረድ:: ከእነርሱ አድነኝም:: ከእኔ ጋር ያሉትን አማኞችም አድን።»"},{"id":119,"translation":"119. እርሱንም ሆነ ከእርሱ ጋር ያሉትን ሁሉ በተሞላው መርከብ ውስጥ አዳንን::"},{"id":120,"translation":"120. ከዚያም በኋላ ቀሪዎቹን አሰመጥን።"},{"id":121,"translation":"121. በዚህ ውስጥ ታላቅ ግሣጼ አለበት፤ አብዛሀኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም::"},{"id":122,"translation":"122. ጌታህም እርሱ በእርግጥ ሁሉን አሸናፊዉና አዛኙ ነው::"},{"id":123,"translation":"123. ዓድ መልዕክተኞችን አስተባበለች፤"},{"id":124,"translation":"124. ወንድማቸው ሁድ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ: «አትጠነቀቁምን?"},{"id":125,"translation":"125. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።"},{"id":126,"translation":"126. «አላህን ብቻ ፍሩ ታዘዙኝም።"},{"id":127,"translation":"127. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አለምናችሁም:: ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ ብቻ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም።"},{"id":128,"translation":"128. «የምትጫወቱ ሆናችሁ በከፍተኛ ስፍራ ሁሉ ላይ ምልክት ትገነባላችሁን?"},{"id":129,"translation":"129. «የውሃ ማጠራቀሚያዎችንና ህንፃዎችንም ለዘላለም መኖርን የምትከጅሉ ሆናችሁ ትሰራላችሁን?"},{"id":130,"translation":"130. «በቀጣችሁም ጊዜ ጨካኞች ሆናችሁ ትቀጣላችሁን?"},{"id":131,"translation":"131. «አላህንም ፍሩ። ታዘዙኝም።"},{"id":132,"translation":"132. «ያንንም በምታውቁት ጸጋ ያጣቀማችሁን ጌታን (አላህን) ፍሩ።"},{"id":133,"translation":"133. «በእንስሳዎችና በልጆችም ያጣቀማችሁ።"},{"id":134,"translation":"134. «በአትክልቶችና በምንጮችም ያጣቀማችሁን ጌታን (አላህን) ፍሩ።"},{"id":135,"translation":"135. «እኔ በእናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራለሁና።»"},{"id":136,"translation":"136. እነርሱም አሉ: «ብትገስጽም ወይም ከገሳጮች ባትሆንም በእኛ ላይ እኩል ነው።"},{"id":137,"translation":"137. «(ያለንበትን አንለቅም)። ይህ የፊተኞቹ ሰዎች መንገድ እንጂ ሌላ አይደለም።"},{"id":138,"translation":"138. «እኛም የምንቀጣ አይደለንም።» አሉ።"},{"id":139,"translation":"139. አስተባበሉትም፤ አጠፋናቸዉም፤ በዚህም ውስጥ እርግጠኛ ግሣጼም አለበት:: አብዛኞቻቸዉም ምዕምናን አልነበሩም::"},{"id":140,"translation":"140. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊውና አዛኙ ነው::"},{"id":141,"translation":"141. የሰሙድ ህዝቦች መልዕክተኞችን አስተባበሉ::"},{"id":142,"translation":"142. ወንድማቸው ሷሊህ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ: «አትጠነቀቁምን?"},{"id":143,"translation":"143. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።"},{"id":144,"translation":"144. «አላህን ፍሩ ታዘዙኝም።"},{"id":145,"translation":"145. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም:: ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ ብቻ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም።"},{"id":146,"translation":"146. «በዚያ እዚህ ባለው ጸጋ ውስጥ የረካችሁ ሆናችሁ ትቀራላችሁን?"},{"id":147,"translation":"147. «በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ"},{"id":148,"translation":"148. «በአዝመራዎችም ፍሬዋ የበሰለ በሆነች ዘንባባም ውስጥ ትቀራላችሁን?"},{"id":149,"translation":"149. «ብልሆች ሆናችሁ ከጋራዎች ቤቶችንም ትጠርባላችሁ።"},{"id":150,"translation":"150. «አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም።"},{"id":151,"translation":"151. «የወሰን አላፊዎችንም ትዕዛዝ አትከተሉ።"},{"id":152,"translation":"152. «የእነዚያን በምድር ላይ የሚያጠፉትንና የማያበጁትን (ትዕዛዝ አትከተሉ)።» (አለ)"},{"id":153,"translation":"153. እነርሱም አሉ: «አንተ በብዙ ከተደገመባቸው ሰዎች ብቻ ነህ።"},{"id":154,"translation":"154. «አንተ ብጤያችን ሰው እንጂ ሌላ አይደለህም። ከእውነተኞችም ከሆንክ ተዐምርን አምጣ።» (አሉ)"},{"id":155,"translation":"155. እርሱም አለ: «ይህች ግመል ናት:: ለእርሷ የመጠጥ ፋንታ አላት:: ለእናንተም የታወቀ ቀን ፋንታ አላችሁ፤"},{"id":156,"translation":"156. «በክፉም አትንኳት የታላቅ ቀን ቅጣት ይይዛችኋልና።»"},{"id":157,"translation":"157. ወጓትም:: ወዲያው ተጸፃቾች ሆነው አነጉ::"},{"id":158,"translation":"158. ቅጣትም ያዛቸው በዚህም ውስጥ አያሌ ግሣጼ አለበት:: አብዛኞቻቸዉም አማኞች አልነበሩም::"},{"id":159,"translation":"159. ጌታህም እርሱ በእርግጥ ሁሉን አሸናፊውና አዛኙ ነው።"},{"id":160,"translation":"160. የሉጥ ህዝቦች መልዕክተኞችን አስተባበሉ::"},{"id":161,"translation":"161. ወንድማቸው ሉጥ ለእነርሱ ባለ ጊዜ: «አትጠነቀቁምን?"},{"id":162,"translation":"162. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።"},{"id":163,"translation":"163. «አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም።"},{"id":164,"translation":"164. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አለምናችሁም:: ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም::"},{"id":165,"translation":"165. «ከዓለማት ሰዎች መካከል የተለየ ወንዶችን ትገናኛላችሁን?"},{"id":166,"translation":"166. «ከሚስቶቻችሁም ጌታችሁ ለእናንተ የፈጠረላችሁን ትተዋላችሁን? በእውነት እናንተ ወሰን አላፊዎች ህዝቦች ናችሁ።» (አለ)"},{"id":167,"translation":"167. እነርሱም አሉ: «ሉጥ ሆይ! ከዚህ ነገርህ ባትከለከል በእርግጥ በሀይል ከአገር ከሚወጡት ትሆናለህ።»"},{"id":168,"translation":"168. እርሱም አለ: «እኔ ስራችሁን ከሚጠሉት ሰዎች አንዱ ነኝ።"},{"id":169,"translation":"169. «ጌታዬ ሆይ! እኔንም ሆነ ቤተሰቦቼን እኒህ ህዝቦች ከሚሰሩት ስራ ቅጣት አድነን።»"},{"id":170,"translation":"170. እርሱንም ሆነ ቤተሰቦቹንም በጠቅላላ አዳንናቸው።"},{"id":171,"translation":"171. በቀሪዎቹ ውስጥ የሆነች አሮጊት ስተቀር (እርሷ ግን ጠፋች)::"},{"id":172,"translation":"172. ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን።"},{"id":173,"translation":"173. በእነርሱም ላይ የድንጋይን ዝናብን አዘነብንባቸው:: የተስፋራሪዎችም ዝናብ ከፋ::"},{"id":174,"translation":"174. በዚህ ውስጥ አስደናቂ ተዐምር አለበት:: አብዛኞቻቸዉም ምዕምናን አልነበሩም::"},{"id":175,"translation":"175. ጌታህ እርሱ አሸናፊውና አዛኙ ነው።"},{"id":176,"translation":"176. የአይካ ሰዎች መልዕክተኞችን አስተባበሉ::"},{"id":177,"translation":"177. ወንድማቸው ሹዐይብ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ: «አትጠነቀቁምን?"},{"id":178,"translation":"178. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።"},{"id":179,"translation":"179. «አላህን ፍሩ፤ ታዘዙኝም።"},{"id":180,"translation":"180. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፤ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም።"},{"id":181,"translation":"181. «ስፍርንም ሙሉ:: ከአጎዳዮችም አትሁኑ።"},{"id":182,"translation":"182. «በትክክለኛ ሚዛንም መዝኑ።"},{"id":183,"translation":"183. «ሰዎችንም ነገሮቻቸውን አታጉድሉባቸው:: በምድርም ላይ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ።"},{"id":184,"translation":"184. «ያንንም የፈጠራችሁን የቀድሞዎቹንም ፍጡሮች የፈጠረውን ፍሩ።» (ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ)"},{"id":185,"translation":"185. እነርሱም አሉ: «ሹዓይብ ሆይ! አንተ በብዛት ከተደገመባቸው ሰዎች አንዱ ነህ።"},{"id":186,"translation":"186. «አንተም ብጤያችን ሰው እንጂ ሌላ አይደለህም:: እነሆ ከውሸታሞች ነህ ብለን እንጠረጥርሃለን፤"},{"id":187,"translation":"187. «ከእውነተኞችም እንደሆንክ በእኛ ላይ ከሰማይ ቁራጭን ጣልብን።» (አሉ)"},{"id":188,"translation":"188. «ጌታዬ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነው።» አላቸው።"},{"id":189,"translation":"189. አስተባበሉትም የጥላይቱ ቀን ቅጣትም ያዛቸው፤ እርሱ የከባድ ቀን ቅጣት ነበርና::"},{"id":190,"translation":"190. በዚህ ውስጥ አስደናቂ ተዐምር አለበት:: አብዛዛቻቸዉም አማኞች አልነበሩም::"},{"id":191,"translation":"191. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊዉንና አዛኙ ነው::"},{"id":192,"translation":"192. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱም (ቁርኣን) በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው::"},{"id":193,"translation":"193. እርሱን ታማኙ መንፈስ ጂብሪል አወረደው::"},{"id":194,"translation":"194. ከአስፈራሪዎች ነብያት ትሆን ዘንድ በልብህ ላይ አወረደው፤"},{"id":195,"translation":"195. ግልጽ በሆነ ዐረብኛ ቋንቋ፤ (አወረደው)"},{"id":196,"translation":"196. እርሱም (ቁርኣን) በቀድሞዎቹ መጽሐፍት ውስጥ የተወሳ ነው::"},{"id":197,"translation":"197. የኢስራኢል ልጆች ሊቃውንት የሚያውቁት መሆኑ ለእነርሱ (ለመካ ከሓዲያን) ምልክት አይሆናቸዉም?"},{"id":198,"translation":"198. ከአዕጀሞች ባንዱ ላይ ባወረድነዉም ኖሮ"},{"id":199,"translation":"199. በእነርሱ ላይ ቢያነበዉም በእርሱ አማኞች አይሆኑም ነበር::"},{"id":200,"translation":"200. እንድዚሁ ማስተባበልን በተንኮለኞች ልቦች ውስጥ አስገባነው::"},{"id":201,"translation":"201. አሳማሚ ቅጣትን እስከሚያዩ ድረስ በእርሱ አያምኑም::"},{"id":202,"translation":"202. እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ ቅጣቱ ድንገት እስከሚመጣባቸዉም ድረስ (አያምኑም)::"},{"id":203,"translation":"203. በመጣባቸው ጊዜ: «እኛ የምንቆይ ነን?» እስከሚሉም (አያምኑም)።"},{"id":204,"translation":"204. በቅጣታችን ያቻኩላሉን?"},{"id":205,"translation":"205. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) አየህን? ብዙ ዓመታትን ብናጣቅማቸው::"},{"id":206,"translation":"206. ከዚያም ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ቢመጣባቸው"},{"id":207,"translation":"207. ይጣቀሙበት የነበሩት ሁሉ ከእነርሱ ምንም አያብቃቃቸዉም::"},{"id":208,"translation":"208. አንዲትንም ከተማ ለእርሷ አስፈራሪዎች ያሏት (እና ያስተባበለች) ሆና እንጂ አላጠፋንም::"},{"id":209,"translation":"209. ይህች ግሣጼ ናት:: በዳዮችም አልነበርንም::"},{"id":210,"translation":"210. ሰይጣናትም እርሱን ቁርኣንን አላወረዱትም::"},{"id":211,"translation":"211. ለእነርሱም አይገባቸዉም፤ አይችሉምም::"},{"id":212,"translation":"212. እነርሱ የመላዕክትን ንግግር ከመስማት የተከለከሉ ናቸው።"},{"id":213,"translation":"213. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትገዛ:: ከሚቀጡት ትሆናለህና::"},{"id":214,"translation":"214. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቅርቦች ዘመዶችህንም አስጠንቅቅ::"},{"id":215,"translation":"215. (ሙሐመድ ሆይ!) ከምዕምናንም ለተከተሉህ ሰዎች ክንፍህን ዝቅ አድርግ ልዝብ ሁን::"},{"id":216,"translation":"216. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንቢ ካሉህ «እኔ ከምትሰሩት ወንጀል ሁሉ ንጹህ ነኝ።» በላቸው።"},{"id":217,"translation":"217. (ሙሐመድ ሆይ!) አሸናፊና አዛኝ በሆነው ጌታህ ላይም ተጠጋ::"},{"id":218,"translation":"218. በዚያ ለሶላት በምትቆም ጊዜ በሚያይህ::"},{"id":219,"translation":"219. በሰጋጆች ውስጥ መዘዋወርህንም (በሚያየው ጌታህ ላይ ተጠጋ::)"},{"id":220,"translation":"220. እነሆ እርሱ (አላህ) ሁሉ ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና።"},{"id":221,"translation":"221. ሰይጣናት በማን ላይ እንደሚወርዱ ልንገራችሁን?"},{"id":222,"translation":"222. በውሸታም ኃጢአተኛ ሁሉ ላይ ይወርዳሉ::"},{"id":223,"translation":"223. የሰሙትን ወደ ጠንቋዮች ይጥላሉ:: አብዛኞቻቸዉም ውሸታሞች ናቸው::"},{"id":224,"translation":"224. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባለ ቅኔዎችንም ጠማማዎች ይከተሏቸዋል::"},{"id":225,"translation":"225. እነርሱ (በንግግር) ሸለቆ ሁሉ የሚዋልሉ መሆናቸውን አታይምን?"},{"id":226,"translation":"226. እነርሱም የማይሰሩትን ነገር የሚናገሩ መሆናቸውን አታይምን::"},{"id":227,"translation":"227. እነዚያ ያመኑና መልካም ስራዎችን የሰሩ አላህን በብዛት ያወሱ ከተበደሉም በኋላ (በቅኔ) የተከላከሉ ሲቀሩ፤ (እነርሱ አይወቀሱም)። እነዚያም የበደሉ ከሞቱ በኋላ እንዴት ያለን መመለስ እንደሚመለሱ በእርግጥ ያውቃሉ::"}]},{"id":27,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ጣ፤ ሲን፤ ይህ ከቁርኣኑና ከገላጩ መጽሐፍ አናቅጽ ነው።"},{"id":2,"translation":"2. ለምዕምናን መሪና ብስራት ነው::"},{"id":3,"translation":"3. ለእነዚያ ሶላትን ለሚሰግዱት፤ ዘካንም ለሚሰጡ፤ እነርሱም በመጨረሻይቱ ሕይወት እነርሱ የሚያረጋግጡ ለሆኑት::"},{"id":4,"translation":"4. እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ለእነርሱ ክፉ ሥራዎቻቸውን ሸለምንላቸው:: ስለዚህ እነርሱ ይዋልላሉ::"},{"id":5,"translation":"5. እነርሱ እነዚያ ክፉ ቅጣት ያላባቸው ናቸው:: እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ በጣም ከከሳሪዎቹ ናቸው::"},{"id":6,"translation":"6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ቁርኣንን ጥበበኛና አዋቂ ከሆነው ጌታህ ዘንድ በእርግጥ ትስሰጣለህ::"},{"id":7,"translation":"7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳ ለቤተሰቦቹ «እኔ እሳትን አየሁ ከእርሷ ወሬን አመጣላችኋለሁ፤ ወይም ትሞቁ ዘንድ የተለኮሰ ችቦን አመጣላችኋለሁ» ባለ ጊዜ የሆነውን አውሳላቸው።"},{"id":8,"translation":"8. በመጣትም ጊዜ እንዲህ በማለት ተጠራ፡- «በእሳቲቱ ያለው ሰውና በዙሪያዋ ያሉም ሰዎች ሁሉ ተባረኩ:: የዓለማትም ጌታ አላህ ጥራት ይገባው።"},{"id":9,"translation":"9. «ሙሳ ሆይ! እነሆ እኔ አሸናፊዉና ጥበበኛው (አምላክህ) አላህ ነኝ።"},{"id":10,"translation":"10. «በትርህንም ጣል» (ተባለና ጣለም):: እርሷ እንደ ትንሽ እባብ በፍጥነት ስትስለከለክ ባያትም ጊዜ ፊቱን አዙሮ ሸሸ:: አልተመለሰምም:: «ሙሳ ሆይ! አትፍራ:: መልዕክተኞች እኔ ዘንድ ፈጽሞ አይፈሩምና።"},{"id":11,"translation":"11. «ግን የበደለ ሰው ከዚያም ከመጥፎ ሥራው በኋላ መልካምን የለወጠ እኔ መሓሪ፤ አዛኝ ነኝ።"},{"id":12,"translation":"12. «እጅህንም በአንገትየህ ውስጥ አስገባ ያለ ነውር (ወይም ያለ ለምጽ) ነጭ ሆና ትወጣለችና በዘጠኝ ታዐምራት ወደ ፈርዖንና ወደ ሕዝቦቹ ሂድ እነርሱ አመጸኞች ህዝቦች ናቸውና።»"},{"id":13,"translation":"13. ተዓምራታችንም ግልጽ ሆና በመጣቻቸው ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው።» አሉ።"},{"id":14,"translation":"14. ነፍሶቻቸዉም ያረጋገጧት ሲሆኑ ለበደልና ለኩራት በእርሷ ካዱ:: የአበላሾችም ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ ተመልከት::"},{"id":15,"translation":"15. ለዳውድና ለሱለይማንም እውቀትን በእርግጥ ሰጠናቸው:: «ምስጋና ሁሉ ለአላህ ለዚያ ከአማኞች ባሮቹ በብዙዎቹ ላይ ላበለጠን ይገባው።» አሉም።"},{"id":16,"translation":"16. ሱለይማንም ዳውድን ወረሰ:: አለም «ሰዎች ሆይ የበራሪን ንግግር (የወፍን ቋንቋ) ተስተማርን ከነገሩም ሁሉ ተሰጠን ይህ እርሱ በእርግጥ ግልጽ የሆነ ችሮታ ነው።»"},{"id":17,"translation":"17. ለሱለይማንም ከአጋንንት ከሰዉም ከበራሪም የሆኑት ሰራዊቶቹ ተሰበሰቡ:: እነርሱም ይከመከማሉ::"},{"id":18,"translation":"18. በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን፡- «እናንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ:: ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ እንዳይሰባብሯችሁ።» አለች።"},{"id":19,"translation":"19. ከንግግርዋም እየሳቀ ጥርሱን ፈገግ አደረገ። «ጌታዬ ሆይ! ያቺን በእኔና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን የምትወደውንም በጎ ሥራ እንድሠራ ምራኝ፤ በችሮታህም በመልካሞቹ ባሮችህ ውስጥ አስገባኝ።» አለ።"},{"id":20,"translation":"20. በራሪዎቹንም ተመለከተ:: ከዚያ «ሁድሁድን ለምን አላየሁትም! በእውነት ከራቁት ነበርን?"},{"id":21,"translation":"21. «ብርቱን ቅጣት በእርግጥ እቀጣዋለሁ:: ወይም በእርግጥ አርደዋለሁ:: ወይም ግልጽ የሆነ አስረጅን ያቀርብልኛል።» አለ።"},{"id":22,"translation":"22. (ሁድሁድ የተባለው ወፍ) እሩቅ ያልሆነንም ጊዜ ቆየ:: ከዚያም አለ «ያላወቅከውን ነገር አወቅኩ ከሰበእም እርግጠኛን ወሬ አመጣሁልህ።"},{"id":23,"translation":"23. «እኔ የምትገዛቸው የሆነችን ሴት ከነገሩም ሁሉ የተሰጠችን አገኘሁ:: ለእርሷም ታላቅ ዙፋን አላት።"},{"id":24,"translation":"24. «እርስዋንም ሕዝቦችዋንም ከአላህ ሌላ ለጸሐይ ሲሰግዱ አገኘኋቸው። ሰይጣንም ለእነርሱ ሥራዎቻቸውን ሸልሞላቸዋል። ከእውነተኛዉም መንገድ አግዷቸዋል:: ስለዚህ እነርሱ ወደ እውነት አይመሩም።"},{"id":25,"translation":"25. «ለዚያም በሰማያትና በምድር ዉስጥ የተደበቀውን ለሚያወጣው የምትሸሽጉትንና የምትገልጹትንም ሁሉ ለሚያውቀው አላህ እንዳይሰግዱ ሰይጣን አግዷቸዋል።"},{"id":26,"translation":"26. «አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው።» (አለ) {1}","footnotes":"{1} እዚህ የንባብ ሱጁድ (ሱጁዱ ትላወህ) ይደረጋል።"},{"id":27,"translation":"27. ሱለይማንም አለ፡- «እውነት እንደ ተናገርክ ወይም ከውሸታሞቹ እንደሆንክ ወደ ፊት እናያለን።"},{"id":28,"translation":"28. «ይህንን ደብዳቤዬን ይዘህ ሂድ:: ወደ እነርሱም ጣለው ከዚያ ከእነርሱ ዘወር በልና ምን እንደሚመልሱም ተመልከት።»"},{"id":29,"translation":"29. እርሷም በደረሳት ጊዜ አለች፡- «እናንተ መማክርቶች ሆይ! እኔ ክብር ያለው ጽሑፍ ወደ እኔ ተጣለ።"},{"id":30,"translation":"30. «እርሱ ከሱለይማን ነው። እርሱም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።"},{"id":31,"translation":"31. «‹በእኔ ላይ አትኩሩ:: ታዛዦችም ሆናችሁ ወደ እኔ ኑ› የሚል ነው።»"},{"id":32,"translation":"32. «እናንተ መማክርቶች ሆይ! በነገሬ የሚበጀውን ንገሩኝ እስከምትነግሩኝ ድረስ አንድንም ነገር ቆራጭ አይደለሁምና» አለች።"},{"id":33,"translation":"33. «እኛ የሃይል ባለቤቶች የብርቱ ጦርም ባለቤቶች ነን:: ግን ትዕዛዙ ከወደ አንቺ ብቻ ነው። ምን እንደምታዝዢንም አስተውይ» አሏት::"},{"id":34,"translation":"34. እርሷም አለች፡- «ንጉሶች ከተማን በሃይል በገቡባት ጊዜ ያበላሿታል የተከበሩ ሰዎቿንም ወራዶች ያደርጋሉ:: ልክ እንደዚሁ ነው የሚያደርጉት።"},{"id":35,"translation":"35. «እኔም ወደ እነርሱ ገጸበረከትን የምልክና መልዕክተኞቹ በምን እንደሚመልሱ የምጠባበቅ ነኝ።»"},{"id":36,"translation":"36. መልዕክተኛው ሱለይማንን በመጣውም ጊዜ አለ፡- «በገንዘብ ትረዱኛላችሁን? አላህም የሰጠን ከሰጣችሁ የበለጠ ነው:: ይልቁንም እናንተ በገጸበረከታችሁ ትደሰታላችሁ።"},{"id":37,"translation":"37. «ወደ እነርሱ ተመለስ:: ለእነርሱም በእርሷ ችሎታ በሌላቸው ሰራዊት እንመጣባቸዋለን:: ከእርሷም እነርሱ የተዋረዱ ሆነው በእርግጥ እናወጣቸዋለን።» አለ።"},{"id":38,"translation":"38. «እናንተ መኳንንቶች ሆይ! ሙስሊሞች ሆነው ወደ እኔ ሳይመጡ በፊት ዙፋኗን የሚያመጣልኝ ማንኛችሁ ነው?» አለ::"},{"id":39,"translation":"39. ከጋኔን ሃይለኛው «ከችሎትህ ከመነሳትህ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ:: እኔም በእርሱ ላይ ብርቱ ታማኝ ነኝ።» አለ።"},{"id":40,"translation":"40. ያ እርሱ ዘንድ ከመጽሐፉ ጥልቅ ዕውቀት ያለው ሰው «የተገለጸው ዓይንህ ወደ አንተ ከመመለሱ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ።» አለ:: እንደዚሁም አደረገ:: እርሱ ዘንድ ረግቶ ባየዉም ጊዜ «ይህ ከጌታዬ ችሮታ ነው። የማመሰግን ወይም የምክድ መሆኔን ሊሞክረኝ ቸረልኝ:: አላህን ያመሰገነ ሁሉ የሚያመሰግነው ለራሱ ነው:: አላህን የካደም ሰው ሁሉ ጌታዬ ከእርሱ ተብቃቂ፤ ቸር ነው።» አለ::"},{"id":41,"translation":"41. «ዙፋኗን ለእርሷ አሳስቱ ታውቀው እንደሆነ ወይም ከእነዚያ ከማያውቁት ትሆን እንደሆነ እናያለን።» አላቸው።"},{"id":42,"translation":"42. በመጣችም ጊዜ፡- «ዙፋንሽ እንደዚህ ነውን?» ተባለች «እርሱ ልክ እርሱን ነው የመሰለኝ።» አለች። ሱለይማንም አለ: «ከእርሷ በፊትም እውቀትን ተሰጠን:: ሙስሊሞችም ነበርን።"},{"id":43,"translation":"43. «ከአላህ ሌላ ትገዛው የነበረችውንም ከለከላት:: እርሷ ከከሓዲያን ሕዝቦች ነበረችና።»"},{"id":44,"translation":"44. «ሕንጻውን ግቢ።» ተባለች:: ባየችዉም ጊዜ ባህር ነው ብላ ጠረጠረችው:: ከባቶቿም ገለጠች:: «እርሱ ከመስተዋት የተለሰለሰ ህንጻ ነው።» አሏት:: «ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ ከሱለይማንም ጋር ሆኜ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ታዘዝኩኝ።» አለች።"},{"id":45,"translation":"45. ወደ ሰሙድም ወንድማቸውን ሷሊህን አላህን ተገዙ በማለት በእርግጥ ላክነው:: ወዲያዉም እነርሱ የሚነታረኩ ሁለት ቡድኖች ሆኑ::"},{"id":46,"translation":"46. «ሕዝቦቼ ሆይ! ከመልካሙ በፊት በክፉው ቅጣትን አምጣብን በማለት ለምን ታስቸኩላላችሁ ይታዘንላችሁ ዘንድ አላህን ምህረትን አትለምኑምን?» አላቸው።"},{"id":47,"translation":"47. «ባንተና ካንተም ጋር ባሉት ሰዎች ምክንያት ገደ ቢሶች ሆንን።» አሉት:: «ገደ ቢስነታችሁ አላህ ዘንድ ነው:: ይልቁንም እናንተ የምትፈተኑ ህዝቦች ናችሁ።» አላቸው።"},{"id":48,"translation":"48. በከተማይቱም ውስጥ ምድርን የሚያበላሹና የማያሳምሩ ዘጠኝ ሰዎች ነበሩ::"},{"id":49,"translation":"49. ዘጠኞቹም «እርሱንና ቤተሰቦቹን ሌሊት እንግደልና ከዚያም ለዘመዱ የቤተሰቦቹን መገደል አላየንም:: እኛም እውነተኞች ነን ልንል በአላህ እንማማል።» አሉ።"},{"id":50,"translation":"50. ተንኮልንም መከሩ:: እነርሱም የማያውቁ ሲሆኑ በተንኮላቸው ምክኒያት አጠፋናቸው::"},{"id":51,"translation":"51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተንኮላቸዉም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ እኛ እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም በሙሉ እንዴት እንዳጠፋናቸው ተመልከት::"},{"id":52,"translation":"52. እንዚህም በበደላቸው ምክንያት ባዶዎች ሲሆኑ እነዚህም ቤቶቻቸው ናቸው:: በዚህም ውስጥ ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ አስደናቂ ተዐምር አለበት::"},{"id":53,"translation":"53. እነዚያንም ያመኑትንና ከክህደት ይጠነቀቁ የነበሩትን አዳንን::"},{"id":54,"translation":"54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሉጥንም ለህዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ):: «እናንተ የምታዩ ስትሆኑ መጥፎን ነገር ትሠራላችሁን?"},{"id":55,"translation":"55. «እናንተ ከሴቶች አልፋችሁ ወንዶችን ለመከጀል ትመጣላችሁን? በእውነቱ እናንተ የምትሳሳቱ ህዝቦች ናችሁ።»"},{"id":56,"translation":"56. የህዝቦቹም መልስ «የሉጥን ቤተሰቦች ከከተማችሁ አውጡ:: እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና።» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም።"},{"id":57,"translation":"57. እርሱንና ቤተሰቦቹንም አዳንን:: ሚስቱ ብቻ ስትቀር:: እርሷማ በጥፋቱ ውስጥ ከቀሪዎቹ አደረግናት::"},{"id":58,"translation":"58. በእነርሱም ላይ የድንጋይ ዝናብን አዘነብንባቸው:: የተስፈራሪዎቹም የቅጣት ዝናብ ከፋ።"},{"id":59,"translation":"59. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)፡- «ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይገባው:: በእነዚያም በመረጣቸው ባሮቹ ላይ ሁልጊዜም ሰላም ይውረድ:: አላህ በላጭ ነውን? ወይስ ያ በእርሱ የሚያጋሩት ጣዖት?» በል።"},{"id":60,"translation":"60. ወይስ ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረና ከሰማይም ለእናንተ ውሃን ያወረደው ማን ሆነና? በእርሱም ባለ ውበት የሆኑትን የታጠሩ አትክልቶችን ዛፍዋን ልታበቅሉ ለእናንተ ችሎታ ሳይኖራችሁ እኛ ብቻችንን አበቀልን:: ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? (የለም) ግን እነርሱ ከእውነት የሚያዘነብሉ ህዝቦች ናቸው።"},{"id":61,"translation":"61. ወይስ ምድርን መርጊያ ያደረገና በመካከሏም ወንዞችን ያደረገ ለእርሷም ጋራዎችን ያደረገ በጣፋጩና በጨዋማው በሁለቱ ባህሮችም መካከል ግርዶን ያደረገ ማን ሆነና? ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም።"},{"id":62,"translation":"62. ወይስ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል መከራንም የሚያስወግድ በምድርም ላይ ምትኮች የሚደርጋችሁ ማን ሆነና? ከአላህ ጋር ሌላ ትክክለኛ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሰጹም።"},{"id":63,"translation":"63. ወይስ በየብስና በባህር ጨለማዎች ውስጥ የሚመራችሁ ንፋሶችንም ከዝናቡ በፊት አብሳሪ ሆነው የሚልክ ማን ሆነና? ከአላህ ጋር ሌላ ትክክለኛ አምላክ አለን? አላህ በእርሱ ከሚያጋሯቸው ነገሮች ሁሉ ላቀ።"},{"id":64,"translation":"64. ወይስ መፍጠርን የሚጀምር ከዚያም የሚመልሰው፤ ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣቸሁ አምላክ ማን ሆነና? ከአላህ ጋር ሌላ ትክክለኛ አምላክ አለን? እውነተኞች እንደሆናችሁ አስረጃችሁን አምጡ በላቸው::"},{"id":65,"translation":"65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ምስጢር አያውቅም:: አላህ ግን ያውቀዋል:: መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም።» በላቸው።"},{"id":66,"translation":"66. በእውነት የመጨረሻይቱን ዓለም ሁኔታ ማወቃቸው ተሟላን? አይደለም። እነርሱ ከእርሷ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: በእውነትም እነርሱ ከእርሷ እውሮች ናቸው::"},{"id":67,"translation":"67. እነዚያም በአላህ የካዱት አሉ፡- «እኛም አባቶቻችንም ዐፈር በሆንን ጊዜ እንደ ገና ከመቃብር የምንወጣ ነን?"},{"id":68,"translation":"68. «ይህንን እኛም ሆነ ከእኛ በፊትም የነበሩት አባቶቻችን በእርግጥ ተቀጥረንበታል:: ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ።"},{"id":69,"translation":"69. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በምድር ላይ ሂዱ የአመጸኞችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልክቱ።» በላቸው።"},{"id":70,"translation":"70. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱም ላይ አትዘን:: ከሚመክሩብህም ነገር በጭንቀት ውስጥ አትሁን::"},{"id":71,"translation":"71. «እውነተኞችም እንደሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ።"},{"id":72,"translation":"72. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የዚያ የምትቻኮሉበት ከፊሉ ለእናንተ የቀረበ መሆኑ ተረጋግጧል።» በላቸው።"},{"id":73,"translation":"73. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነው:: ግን አብዛኛዎቻቸው አያመሰግኑም::"},{"id":74,"translation":"74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ልቦቻቸው የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ያውቃል::"},{"id":75,"translation":"75. በሰማይም ሆነ በምድር ውስጥ ምንም የተደበቀ ነገር የለም:: ገላጭ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ያለ ቢሆን እንጂ::"},{"id":76,"translation":"76. ይህ ቁርኣን እነዚያ የኢስራኢል ልጆች እነርሱ በእርሱ ላይ የሚለያዩበትን ጉዳይ አብዛኛውን ይነግራል::"},{"id":77,"translation":"77. እርሱም ለአማኞች ብቸኛ መምሪያና እዝነት ነው::"},{"id":78,"translation":"78. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በመካከላቸው በትክክል ፍርዱ ይፈርዳል፤ እርሱም ሁሉን አሸናፊዉና አዋቂው ነው።"},{"id":79,"translation":"79. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህም ላይ ተጠጋ:: አንተ ግልጽ በሆነው እውነት ላይ ነህና።"},{"id":80,"translation":"80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ሙታንን አታሰማም። ደንቆሮዎችንም የሚተው ሆነው በዞሩ ጊዜ ጥሪን አታሰማም።"},{"id":81,"translation":"81.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ልበ ዕውሮችን ከጥመታቸው አቅኚ አይደለህም:: እነዚያን በአናቅጻችን በትክክል የሚያምኑትን እንጂ አታሰማም:: እነርሱ ፍጹም ታዛዦች (ሙስሊሞች) ናቸውና።"},{"id":82,"translation":"82. በእነርሱም ላይ የቅጣት ቃሉ በተረጋገጠ ጊዜ ሰዎቹ በአናቅጻችን የማያረጋግጡ እንደነበሩ የምትነግራቸውን እንስሳ ለእነርሱ ከምድር እናወጣላቸዋለን::"},{"id":83,"translation":"83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሕዝቦቹም ሁሉ በአናቅጽ የሚያስተባብሉትን ቡድኖች የምንሰበስብበትን ቀን አስታውስ:: እነርሱም ይከመከማሉ::"},{"id":84,"translation":"84. በመጡም ጊዜ (አላህ) ይላቸዋል፡ «በአንቀጾቼ እርሷን በማወቅ ያላዳረሳችሁ ስትሆኑ አስተባበላችሁን? ወይስ ምንን ትሰሩ ነበራችሁ?»"},{"id":85,"translation":"85. በመበደላቸዉም ምክኒያት በእነርሱ ላይ ቃሉ ይፈጸምባቸዋል:: እነርሱም አይናገሩም::"},{"id":86,"translation":"86. እኛ ሌሊትን በእርሱ ውስጥ እንደሚያርፉበት ቀንንም የሚያሳይ እንዳደረግን አያዩምን? ለሚያምኑ ሕዝቦች በዚህ ውስጥ አያሌ ተዓምራት አሉበት::"},{"id":87,"translation":"87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በቀንዱም በሚነፋ ቀን በሰማያት ውስጥ ያሉትና በምድርም ውስጥ ያሉት ሁሉ አላህ የሻው ነገር ብቻ ሲቀር በሚደነግጡ ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ። ሁሉም የተናነሱ ሆነዉም ወደ እርሱ ይመጣሉ::"},{"id":88,"translation":"88. ጋራዎችንም እርሷ እንደ ደመና አስተላለፍ የምታልፍ ስትሆን የቆመች ናት ብለህ የምታስባት ሆና ታያለህ፤ የዚያን ነገሩን ሁሉ ያጠነከረውን የአላህን ጥበብ ተመልከት:: እርሱ በምትሠሩት ሁሉ ውስጥ አዋቂ ነው::"},{"id":89,"translation":"89. መልካም ሥራን የሰራ ለእርሱ ከእርሷ የበለጠ ምንዳ አለው:: እነርሱም በዚያ ቀን ከድንጋጤ ነፃ ናቸው::"},{"id":90,"translation":"90. መጥፎንም የሰሩ ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ ይደፋሉ። «ትሠሩት የነበራችሁትን እንጂ አትመነዱም» ይበላሉ።"},{"id":91,"translation":"91. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! በላቸው:) «የታዘዝኩት የዚህችን አገር የመካን ጌታ ያንን ክልክል ያደረጋትንም አላህን እንድገዛ ብቻ ነው:: ነገሩም ሁሉ የእርሱ ነው:: ከሙስሊሞችም እንድሆን ታዝዣለሁ።"},{"id":92,"translation":"92. «ቁርኣንንም እንዳነብ ታዝዣለሁ:: በቀጥተኛው መንገድ የተመራ ሁሉ የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው:: የተሳሳተም እኔ ከአስፈራሪዎች ነኝ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» በላቸው።"},{"id":93,"translation":"93. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ብቻ ነው:: ተአምራቱን ወደ ፊት ያሳያችኋል:: ታውቋታላችሁም።» በላቸው:: ጌታህ ከምትሠሩት ነገር ሁሉ ዘንጊ አይደለም።"}]},{"id":28,"verses":[{"id":1,"translation":"1.ጧ፤ ሲን፤ ሚም፤"},{"id":2,"translation":"2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ አናቅጽ ገላጭ ከሆነው መጽሐፍ አናቅጽ ናቸው::"},{"id":3,"translation":"3. ከሙሳና ከፈርዖን ዜና ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ ባንተ ላይ እናነባለን::"},{"id":4,"translation":"4. ፈርዖን በምድር ላይ ተንበጣረረ:: ነዋሪዎቿንም የተከፋፈሉ ጓዶች አደረጋቸው:: ከእነርሱም ቡድኖችን ያዳክማል:: ወንዶች ልጆቻቸውን በብዛት ያርዳል:: ሴቶቻቸውንም ይተዋል፤ እርሱ ከሚያበላሹት ሰዎች ነበርና::"},{"id":5,"translation":"5. በእነዚያ በምድር ውስጥ በተጨቆኑት ህዝቦች ላይ ልንለግስና መሪዎችም ልናደርጋቸው ወራሾችም ልናደርጋቸው እንሻለን::"},{"id":6,"translation":"6. ለእነርሱም በምድር ላይ ልናስመች ፈርዖንን፤ ሃማንንና ሰራዊቶቻቸውንም ከእነርሱ ይፈሩት የነበሩትን ነገር ልናሳያቸው እንሻለን::"},{"id":7,"translation":"7. ወደ ሙሳም እናት “አጥቢው፤ በእርሱም ላይ በፈራሽ ጊዜ በባህሩ ውስጥ ጣይው፤ አትፍሪም:: አትዘኝም:: እኛ ወዳንቺ መላሾቹና ከመልእክተኞቹም አድራጊዎቹ ነንና” ማለትን አመለከትን (አወረድን)::"},{"id":8,"translation":"8. የፈርዖን ቤተሰቦችም መጨረሻው ለእነርሱ ጠላት ሐዘንም ይሆን ዘንድ አነሱት:: ፈርዖንና ሃማንም ሰራዊቶቻቸዉም ኃጢአተኞች ነበሩ::"},{"id":9,"translation":"9. የፈርዖንም ሚስት “ለእኔም ሆነ ላንተ የዓይናችን መርጊያ ነው:: አትግደሉት:: ሊጠቅመን ወይም ልጅ ልናደርገው ይከጀላልና” አለች:: እነርሱም ፍጻሜውን የማያውቁ ሆነው (አነሱት)::"},{"id":10,"translation":"10. የሙሳም እናት ልብ ባዶ ሆነ:: ከምእምናን ትሆን ዘንድ በልቧ ላይ ባላጠነከርን ኖሮ ልትገልጸው ቀርባ ነበር::"},{"id":11,"translation":"11. ለእህቱም “ተከታተይው” አለቻት:: (እርሱንም) እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ በሩቅ ሆና አየችው፤"},{"id":12,"translation":"12. ወደ እናቱ ከመመለሱ በፊትም አጥቢዎችን መጥባትን በእርሱ ላይ እርም አደረግን:: እህቱም “ለእናንተ የሚያሳድግላችሁን እነርሱም ለእርሱ ቅን አገልጋዮች የሆኑን ቤተሰቦች ላመልክታችሁን?” አለችም።"},{"id":13,"translation":"13. ወደ እናቱም ዓይኗ እንድትረጋ እንዳታዝንም የአላህም የተስፋ ቃል እርግጥ መሆኑን እንድታውቅ መለስነው:: ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም::"},{"id":14,"translation":"14. ብርታቱንም በደረሰና በተስተካከለ ጊዜ ጥበብንና እውቀትን ሰጠነው፤ ልክ እንደዚሁም መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን::"},{"id":15,"translation":"15. ሙሳ ከተማይቱንም ሰዎቿ በዝንጋቴ ላይ ሆነው ሳሉ ገባ:: በእርሷም ውስጥ የሚጋደሉን ሁለት ሰዎች አገኘ:: ይህ (አንዱ) ከወገኑ ነው፤ ይህ (ሌላው) ደግሞ ከጠላቱ ነው፤ ያ ከወገኑ የሆነው ሰው በዚያ ከጣላት በሆነው ሰው ላይ እርዳታን ጠየቀው:: ሙሳም በጡጫ መታው:: ገደለዉም:: “ይህ ከሰይጣን ስራ ነው:: እርሱ ግልጽ አሣሣች ጠላት ነውና” አለ::"},{"id":16,"translation":"16. “ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ ለኔም ማር” አለ ለርሱም ምህረት አደረገለት:: እርሱ መሓሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":17,"translation":"17. “ጌታዬ ሆይ! በእኔ ላይ በመለገስህ ይሁንብኝ (ከስህተቴ እጸጸታለሁ):: ለአመጸኞችም ፈጽሞ ረዳት አልሆንም” አለ::"},{"id":18,"translation":"18. በከተማይቱም ውስጥ ፈሪና የሚጠባበቅ ሆኖ አደረ:: በንጋቱም ያ ትላንት እርዳታን የጠየቀው ሰው በጩኸት እርዳታን ይጠይቀዋል:: ሙሳም ለእርሱ፡- “አንተ በእርግጥ ግልጽ ጠማማ ነህ” አለው::"},{"id":19,"translation":"19. ሙሳ ያንን እርሱ ለሁለቱም ጠላት የሆነው ሰው በኃይል ሊይዘው በፈለገም ጊዜ “ሙሳ ሆይ በትላንትናው ቀን ነፍስን እንደ ገደልክ ልትገድለኝ ትፈልጋለህን? በምድር ላይ ጨካኝ መሆንን እንጂ ሌላ አትፈልግም ከመልካም ሰሪዎች መሆንን አትፈልግም” አለው።"},{"id":20,"translation":"20. ከከተማይቱም ዳርቻ አንድ ሰው እየሮጠ መጣ “ሙሳ ሆይ! ሹማምንቶቹ ሊገድሉህ ባንተ ይመካከራሉና ውጣ እኔ ላንተ ከመካሪዎች ነኝና” አለው::"},{"id":21,"translation":"21. የፈራና የሚጠባበቅ ሆኖም ከእርሷ ወጣ:: “ጌታዬ ሆይ! ከበደለኞች ህዝቦች አድነኝ” አለ::"},{"id":22,"translation":"22. ወደ መድየን አቅጣጫ ፊቱን ባዞረ ጊዜም “ጌታዬ ቀጥተኛውን መንገድ ሊመራኝ እከጅላለሁ” አለ::"},{"id":23,"translation":"23. ወደ መድየንም ውሃ በመጣ ጊዜ እርሱ ላይ ከሰዎች ቡድኖችን መንጋዎቻቸውን የሚያጠጡ ሆነው አገኘ:: ከእነርሱ በታችም ከውሃው መንጎቻቸውን የሚከለክሉ ሁለት ሴቶች ልጆችን አገኘ። “ነገራችሁ ምንድን ነው?” አላቸው። “እረኞች ሁሉ መንጋዎቻቸውን እስከሚመልሱ አናጠጣም። አባታችንም ትልቅ ሽማግሌ ነው።” አሉት::"},{"id":24,"translation":"24. ለሁለቱም አጠጣላቸው ከዚያ ወደ ጥላው ዘወር አለና “ጌታዬ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ወደ እኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ” አለ::"},{"id":25,"translation":"25. ከሁለቱ አንደኛይቱም ከሀፍረት ጋር የምትሄድ ሆና ወደ እርሱ መጣች፤ “አባቴ ለእኛ ያጠጣህልንን ዋጋ ሊሰጥህ ይጠራሃል” አለችው፤ ወደ እርሱ በመጣና ወሬውን በእርሱ ላይ በተረከለትም ጊዜ “አትፍራ:: ከበደለኞች ህዝቦች ድነሃል” አለው::"},{"id":26,"translation":"26. ከሁለቱ አንደኛይቱም “አባቴ ሆይ ቅጠረው ከቀጠርከው ሰው ሁሉ በላጩ፤ ብርቱው፤ ታማኙ ነውና” አለችው።"},{"id":27,"translation":"27. “ስምንትን ዓመታት ልታገለግለኝ እኔ ከእነዚህ ሁለት ሴቶች ልጆቼ አንዲቷን ላጋባህ እሻለሁ፤ ዐስርን ብትሞላም ካንተ ነው:: ባንተ ላይ ማስቸገርንም አልሻም:: አላህ የሻ እንደሆነ ከመልካም ሰዎች ሆኜ ታገኘኛለህ” አለው::"},{"id":28,"translation":"28. ሙሳም \"ይህ ውለታ በእኔና ባንተ መካከል ረጊ ነው:: ከሁለት ጊዜያቶች ማንኛውንም ብፈጽም በእኔ ላይ ወሰን ማለፍ የለም:: አላህ በምንለው ላይ ሁሉ ምስክር ነው\" አለ።"},{"id":29,"translation":"29. ሙሳም ጊዜውን በጨረሰና ከቤተሰቦቹ ጋር በሄደ ጊዜ ከጡር ተራራ ጎን እሳትን አየ:: ለቤተሰቡም “እዚህ ቆዩ:: እኔ እሳትን አየሁ:: ከእርሷ አጠገብ ወሬ ወይም ትሞቁ ዘንድ ከእሳት ትንታግን (ችቦን) አመጣላችኋለሁ” አለ::"},{"id":30,"translation":"30. ወደ እርሷ በመጣም ጊዜ ከሸለቆው ቀኝ ዳርቻ ከዛፊቱ በኩል በተባረከችው ስፍራ ውስጥ “ሙሳ ሆይ! እኔ የዓለማት ጌታ አላህ ነኝ” በማለት ተጠራ።"},{"id":31,"translation":"31. “ብትርህንም ጣል” ተባለ:: እንደ ትንሽ እባብ ስትስለከለክ ባያትም ጊዜ ወደ ኋላ ዞሮ ሸሸ:: አልተመለሰምም፤ ተባለም: “ሙሳ ሆይ! ተመለስ አትፍራም፤ አንተ ከጥብቆቹ ነህና"},{"id":32,"translation":"32. \"እጅህን በአንገትጌህ ውስጥ አስግባ:: ያለ ነውር ነጭ ሆና ትወጣለችና፤ ክንፍህንም ከፍርሃት ለመዳን ወደ አንተ አጣብቅ:: እነዚህም ከጌታህ የሆኑ ወደ ፈርዖንና ወደ መኳንቶች የሚደርሱ ሁለት አስረጅዎች ናቸው:: እነርሱ አመጠኞች ህዝቦች ነበሩና።“"},{"id":33,"translation":"33. ሙሳ አለ: \"ጌታዬ ሆይ! እኔ ከእነርሱ ነፍስን ገድያለሁ ስለዚህ እንዳይገሉኝ እፈራለሁ::"},{"id":34,"translation":"34. \"ወንድሜንም ሃሩን እርሱ ምላሱ ከእኔ የተባ (የተሻለ) ነው:: እውነተኛነቴንም የሚያረጋግጥልኝ ረዳት ሆኖ ከእኔ ጋር ላከው እኔ ሊያስተባብሉኝ እፈራለሁና።”"},{"id":35,"translation":"35. (አላህም)፡- “ጡንቻህን በወንድምህ በእርግጥ እናበረታለን:: ለሁለታችሁም ስልጣንን እናደርጋለን:: ወደ እናንተም በመጥፎ አይደርሱም:: በታዓምራታችን ሂዱ:: እናንተና የተከተላችሁ ሁሉ አሸናፊዎች ናችሁ” አላቸው።"},{"id":36,"translation":"36. ሙሳም ተዓምራቶቻችንም ግልጽ ሆነው በመጣባቸው ጊዜ “ይህ የተቀጠፈ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም:: ይህንንም በመጀመሪያዎች አባቶቻችን ውስጥ አልሰማንም” አሉ::"},{"id":37,"translation":"37. ሙሳም “ጌታዬ ከእርሱ ዘንድ በቀጥታው መንገድ የመጣውን ምስጉኒትም አገር ለእርሱ የምትሆንለትን ሰው አዋቂ ነው:: እነሆ በደለኞች አይድኑም” አለ።"},{"id":38,"translation":"38. ፈርዖንም “እናንተ ቡድኖች ሆይ! ከእኔ ሌላ ለእናንተ አምላክን ምንም አላውቅም:: ሃማን ሆይ! ጭቃ ለእኔ አቃጥልልኝ:: ጡብ ስራልኝ:: ለእኔም ከፍተኛ ህንጻን ስራልኝ:: ወደ ሙሳ አምላክ ልወጣ እከጅላለሁና:: እኔም ከውሸታሞች መሆኑን እጠረጥረዋለሁ” አለ።"},{"id":39,"translation":"39. እርሱም ሰራዊቶቹም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ:: እነርሱም ወደእኛ የማይመለሱ መሆናቸውን ጠረጠሩ::"},{"id":40,"translation":"40. እርሱንም ሰራዊቱንም በጥብቅ ያዝናቸው:: በባህርም ውስጥ ጣልናቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የበደለኞች መጨረሻም እንዴት እንደነበረ ተመልከት::"},{"id":41,"translation":"41. ወደ እሳት የሚጠሩ መሪዎችም አደረግናቸው:: በትንሳኤም ቀን አይረዱም::"},{"id":42,"translation":"42. በዚችም በቅርቢቱ ዓለም ውስጥ እርግማንን አስከተልናቸው:: በትንሳኤም ቀን እነርሱ ከሚባረሩት ናቸው::"},{"id":43,"translation":"43. የፊተኞቹን የክፍለ ዘመናት ህዝቦችንም ከአጠፋን በኋላ ለሰዎች የልብ ብርሃን መሪም እዝነትም ሲሆን ይገሠጹ ዘንድ ለሙሳ መጽሐፉን በእርግጥ ሰጠነው::"},{"id":44,"translation":"44. ወደ ሙሳም ትዕዛዝን ባወረድንለት ጊዜ ከተራራው በምዕራባዊው ጎን አልነበርክም:: ከተጣዱትም አልነበርክም::"},{"id":45,"translation":"45. እኛ ግን ከእርሱ ኋላ አያሌ የክፍለ ዘመናትን ሰዎች አስገኘን:: በእነርሱም ላይ ዕድሜዎች ተራዘሙ:: በመድየንም ሰዎች ውስጥ ተቀማጭና በእነርሱ ላይ አናቅጻችንን የምታነብ አልነበርክም:: እኛ ግን ላኪዎችህ ሆንን::"},{"id":46,"translation":"46. በጠራነዉም ጊዜ በጡሩ (ጋራ) ጎን አልነበርክም፤ ግን ካንተ በፊት ምንም አስፈራሪ ያልመጣባቸውን ህዝቦች ታስፈራራ ዘንድ ከጌታህ በሆነ ችሮታ ላክንህ ሊገሠጹ ይከጅላልና።"},{"id":47,"translation":"47. እጆቻቸዉም ባሳለፉት ምክንያት መከራ የምትነካቸውና “ጌታችን ሆይ! አናቅጽህን እንድንከተል ከትክክለኛ አማኞችም እንድንሆን ወደ እኛ መልዕክተኛን አትልክም ኖሯልን? ይህ ሁሉ የሚሉ ባልሆኑ ኖሮ” አንልክም ነበር።"},{"id":48,"translation":"48. እውነቱም ከኛ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ “ለሙሳ የተሰጠው ብጤ አይሰጠዉም ኖሯልን?” አሉ፤ ከዚህ በፊት ሙሳ በተሰጠው አልካዱምን? “ሁለት የተረዳዱ ድግምቶች ናቸው። እኛ በሁሉም ከሓዲያን ነን” አሉ።"},{"id":49,"translation":"49. “ከአላህ ዘንድ የሆነን መጽሐፍ እርሱ ከሁለቱም ይበልጥ ቅን የሆነን አምጡ፤ እውነተኞች እንደ ሆናችሁ ብታመጡት እከተለዋለሁ” በላቸው።"},{"id":50,"translation":"50. እሺ ባይሉህም የሚከተሉት ዝንባሌዎቻቸውን ብቻ መሆኑን ዕወቅ፤ ከአላህም የሆነ መምሪያ ሳይኖረው ዝንባሌውን ብቻ ከተከተለ ይበልጥ የጠመመ አንድም የለም፤ አላህ በደለኞች ህዝቦችን አይመራምና::"},{"id":51,"translation":"51. ይገሠጹም ዘንድ ቃልን (ቁርኣንን በያይነቱ) ለእነርሱ በእርግጥ አስከታተልን::"},{"id":52,"translation":"52. እነዚያም ከእርሱ በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ በእርሱ ያምናሉ::"},{"id":53,"translation":"53. በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸዉም ጊዜ «በእርሱ አምነናል:: እርሱ ከጌታችን የሆነ እውነት ነው እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን።» ይላሉ።"},{"id":54,"translation":"54. እነዚያ በመታገሳቸው ምክኒያት ዋጋቸውን ሁለት ጊዜ ይሰጣሉ:: ክፉውንም ነገር በበጎ ምግባር ይገፈትራሉ፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ ይለግሳሉ::"},{"id":55,"translation":"55. ውድቅንም ቃል በሰሙ ጊዜ ከእርሱ ይርቃሉ። «ለእኛ ስራዎቻችን አሉን:: ለእናንተም ስራዎቻችሁ አሉላችሁ:: ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን ባለጌዎችን አንፈልግም።» ይላሉ።"},{"id":56,"translation":"56. አንተ የወደድከውን ሰው ፈጽሞ አታቀናም:: ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል:: እርሱም ቅኖቹን አዋቂ ነው።"},{"id":57,"translation":"57. «ካንተ ጋር ቅንን መንገድ ብንከተል ከምድራችን እንባረራለን።» አሉም:: ከእኛ ዘንድ የተሰጠ ሲሳይ ሲሆን የነገሩ ሁሉ ፍሬዎች ወደ እርሱ የሚሄዱበትን ጸጥተኛ ክልል (መካን) እነርሱ አላስመቸናቸዉምን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም::"},{"id":58,"translation":"58. ከከተማም ኑሮዋን ምቾትዋን የካደችን ከተማ ያጠፋናት ብዙ ናት፤ እነዚህም ከእነርሱ በኋላ ጥቂት ጊዜ እንጂ ያልተኖረባቸው ሲሆኑ መኖሪያዎቻቸው ናቸው:: እኛም ከእነርሱ ወራሾች ነበርን።"},{"id":59,"translation":"59. ጌታህም ከተሞችን በዋናዋ ከተማ ውስጥ አናቅጻችንን በእነርሱ ላይ የሚያነብ መልዕክተኛን እስከሚልክ ድረስ አጥፊ አልነበረም:: ከተሞችንም ባለቤቶችዋ በዳዮች ሆነው እንጂ አጥፊዎች አልነበርንም::"},{"id":60,"translation":"60. ሰዎች ሆይ! በማንኛዉም ነገር የተሰጣችሁት የቅርቢቱ ሂይወት ጥቅምና ጌጣ ጌጥ ነው:: አላህ ዘንድ ያለዉም ምንዳ በጣም በላጭና ዘውታሪ ነው:: አታውቁምን?"},{"id":61,"translation":"61. መልካምን ተስፋ ቃል የገባንለትና እርሱም አግኚው የሆነ ሰው የቅርቢቱን ህይወት ጥቅም እንዳስመቸነውና ከዚያ እርሱ በትንሳኤ ቀን ለእሳት ከሚቀረቡት እንደ ሆነው ሰው ነውን?"},{"id":62,"translation":"62. (አላህ) የሚጠራባቸውንና «እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሏቸው የነበራችሁት የት ናቸው?» የሚልበትን ቀን (አስታውስ)::"},{"id":63,"translation":"63. እነዚያ በእነርሱ ላይ ቅጣቱ የተረጋገጠባቸው ይላሉ «ጌታችን ሆይ እነዚህ እነዚያ ያጠመምናቸው ናቸው፤ እንደጠመምን አጠመምናቸው (ከእነርሱ) ወደ አንተ ተጥራራን:: እኛን ይገዙ አልነበሩም።»"},{"id":64,"translation":"64. «ለአላህ የምታጋሯቸውንም ጥሩ» ይባላሉ:: ይጠሩዋቸዋልም ግን ለእነርሱ አይመልሱላቸዉም:: ቅጣትንም ያያሉ፤ እነርሱ ይመሩ በነበሩ ኖሮ (አያዩትም ነበር)::"},{"id":65,"translation":"65. የሚጠራባቸውንና «ለመልዕክተኞች ምንን መለሳችሁ?» የሚልበትን ቀን አስታውስ።"},{"id":66,"translation":"66. በዚያም ቀን ወሬዎች ሁሉ በእነርሱ ላይ ይሰወሩባቸዋል፤ እነርሱም አይጠያየቁም::"},{"id":67,"translation":"67. የተጸጸተና ያመነማ መልካምንም የሰራ ከሚድኑት ሊሆን ይከጀላል::"},{"id":68,"translation":"68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም የሚፈልገውን ይፈጥራል:: ይመርጣልም:: ለእነርሱ ምርጫ የላቸዉም:: አላህ ከማይገባው ሁሉ ጠራ ከሚያጋሯቸዉም ላቀ::"},{"id":69,"translation":"69. ጌታህም ልቦቻቸው የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ ያውቃል።"},{"id":70,"translation":"70. እርሱም አላህ ነው። ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ምስጋና ሁሉ በመጀመሪያም በመጨረሻይቱም ዓለም ለእርሱ ብቻ ነው:: ፍርዱም የእርሱ ብቻ ነው፤ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::"},{"id":71,"translation":"71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አያችሁን? (እስቲ ንገሩኝ) አላህ በእናንተ ላይ ሌሊትን እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ዘውታሪ ቢያደርገው ከአላህ ሌላ ብርሃንን የሚያመጣላችሁ አምላክ ማነው? አትሰሙምን?» በላቸው።"},{"id":72,"translation":"72. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አያችሁን? አላህ በእናንተ ላይ ቀንን እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ዘውታሪ ቢያደርገው ከአላህ ሌላ በውስጡ የምታርፉበትን ሌሊት የሚያመጣላችሁ አምላክ ማን ነው? አታስተውሉምን?» በላቸው።"},{"id":73,"translation":"73. ከችሮታዉም ለእናንተ ሌሊትንና ቀንን በውስጡ ልታርፉበት ከትሩፋቱም ልትፈልጉበት አመስጋኞችም ልትሆኑ አደረገላችሁ::"},{"id":74,"translation":"74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሚጠራባቸውንም ቀንና «እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሉዋቸው የነበራችሁት የት ናቸው?» የሚልበትን ቀን አስታውስ::"},{"id":75,"translation":"75. ከህዝቦችም ሁሉ መስካሪን እናወጣና «ማስረጃችሁን አምጡ» እንላለን። ያን ጊዜ እውነተኛዉም አምላክነት ለአላህ ብቻ መሆኑን ያውቃሉ:: ይቀጣጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ይጠፋባቸዋል::"},{"id":76,"translation":"76. ቃሩን ከሙሳ ነገዶች አንዱ ነበር:: በእነርሱም ላይ አመጸ:: ከድልቦችም ያንን መክፈቻዎቹ ብቻ የኃይል ባለቤቶች የሆኑ ቡድኖችን ሸክሙ የሚከብድን ሰጠነው:: ወገኖቹ ለእርሱ ባሉትም ጊዜ አስታውስ: «አትኩራ አላህ ኩራተኞችን አይወድምና።"},{"id":77,"translation":"77. «አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ:: ሆኖም ከቅርቢቱ አለምም ፈንታህን አትርሳ:: አላህ ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ መልካምን አድርግ:: በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ:: አላህ አጥፊዎችን አይወድምና።» አሉት።"},{"id":78,"translation":"78. «(ሀብትን) የተሰጠሁት እኔ ዘንድ ባለው እውቀት ነው።» አለ። አላህ ከእርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሰዎች በኃይል ከእርሱ ይበልጥ የበረቱትን ሀብትን በመሰብሰብም ይበልጥ የበዙትን በእርግጥ ያጠፋ መሆኑን አያውቅምን? አመጸኞችም ከኃጢአቶቻቸው ጥያቄ አይጠየቁም።"},{"id":79,"translation":"79. በህዝቦቹም ላይ በጌጡ ውስጥ ሆኖ ወጣ:: እነዚያ ቅርቢቱን ህይወት የሚፈልጉት «ወይ ምኞታችን! ቃሩን የተሰጠው ቢጤ ምነው ለእኛ በኖረን፤ እርሱ የታላቅ ዕድል ባለቤት ነውና።» አሉ።"},{"id":80,"translation":"80. እነዚያም ዕውቀትን የተሰጡት «ወዮላችሁ! የአላህ ምንዳ ላመነ ሰው መልካምንም ለሰራ በላጭ ነው:: ታጋሾችም እንጂ ሌላው አያገኛትም።» አሉ።"},{"id":81,"translation":"81. በእርሱም በቤትም ምድርን ደረባን (አሰጠምን):: ለእርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዱት ቡድኖች ምንም አልነበሩትም:: ከሚረዱትም አልነበረም::"},{"id":82,"translation":"82. እነዚያም በትላንትናው ቀን ስፍራውን ይመኙ የነበሩት «ወይ ጉድ! ለካ አላህ ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ሲሳይን ያሰፋል:: ያጠባልም:: አላህ በእኛ ላይ በእምነት ባልለገሰልን ኖሮ ምድርን በእኛ ላይ በገለበጠብን ነበር:: ወይ ጉድ! ከሓዲያን አይድኑም።» የሚሉ ሆነው አነጉ።"},{"id":83,"translation":"83. ይህች የመጨረሻይቱ አገር ናት:: ለእነዚያ በምድር ውስጥ ኩራትንና ማመጽን ለማይፈልጉት ሁሉ እናደርጋታለን:: ምስጉኒቱም መጨረሻ ለጥንቁቆቹ ብቻ ናት::"},{"id":84,"translation":"84. በደግ ስራ የመጣ ለእርሱ ከእርሷ በላጭ ምንዳ አለው:: በክፉም ስራ የመጡ እነዚህ መጥፎዎችን የሰሩ ይሰሩት የነበሩትን እንጂ አይመነዱም::"},{"id":85,"translation":"85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ ቁርኣንን የተከፋፈለ ሆኖ ባንተ ላይ ያወረደውና ህግጋቱን እንድትትገበር ግድ ያደረግብህ አምላክ ወደ መመለሻ (ወደ መካ) በእርግጥ መላሽህ ነው። «ጌታዬ በቅን መንገድ የመጣውንና እርሱም በግልጽ ስህተት ውስጥ የሆነውን አዋቂ ነው» በላቸው።"},{"id":86,"translation":"86.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መጽሐፉ ወደ አንተ መወረዱን ተስፋ የምታደርግ አልነበርክም :: ግን ከጌታህ ችሮታ ተወረደልህ:: ለከሓዲያን በፍጹም ረዳት አትሁን::"},{"id":87,"translation":"87.(መልዕክተኛችንሙሐመድ ሆይ!) ከአላህም አናቅጽ ወደ አንተ ከተወረዱ በኋላ አያግዱህ:: ወደ ጌታህም ሰዎችን ጥራ:: ከአጋሪዎችም አትሁን::"},{"id":88,"translation":"88. ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትገዛ:: ከእርሱም በቀር አምላክ የለም። ከእርሱ በስተቀር ሁሉም ጠፊ ነው:: ፍርዱ የእርሱ ብቻ ነው:: ሁላችሁም ወደ እርሱ ትመለሳላችሁ::"}]},{"id":29,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚይም፤"},{"id":2,"translation":"2. ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ (ከአላህ በልዩ ልዩ ነገሮች) ሳይፈተኑ የሚተው መሰላቸውን?"},{"id":3,"translation":"3. እነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትንም ህዝቦች በርግጥ ፈትነናል። እነዚያን እውነት የተናገሩትን አላህ በእርግጥ ያውቃል። ውሸታሞችንም ያውቃል።"},{"id":4,"translation":"4.ይልቁንም እነዚያ መጥፎዎችን ሥራዎች የሚሠሩት ሰዎች የሚያመልጡን መሰላቸውን? ያ የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ::"},{"id":5,"translation":"5. የአላህን መገናኘት ተስፋ የሚያደርግ ሰው ሁሉ የአላህ ቀጠሮ በእርግጥ መጪ ነው:: እርሱም ሰሚም ሁሉን አዋቂ ነው።"},{"id":6,"translation":"6. በአላህ መንገድ ላይ የታገለ ሰው የሚታገለው ለነፍሱ ብቻ ነው:: አላህ ከዓለማት ሁሉ በእርግጥ የተብቃቃ ነውና::"},{"id":7,"translation":"7. እነዚያም በአላህና በመልዕክተኛው ያመኑና መልካም ተግባራትንም የሠሩ መጥፎ ሥራዎቻቸውን ከእነርሱ ላይ እናብስላቸዋለን። በዚያም ይሠሩት በነበሩት መልካም ሥራ በእርግጥ እንመነዳቸዋለን።"},{"id":8,"translation":"8. የሰውን ልጅ ለወላጆቹ መልካም ተግባርን ሁሉ እንዲፈጽም አዘዝነው:: ወላጆችም ላንተም በእርሱ እውቀት የሌለህን ጣኦት በእኔ እንድታጋራው ቢያስገድዱህ አትታዘዛቸው:: መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው:: ከዚያም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ እነግራችኋለሁ::"},{"id":9,"translation":"9. እነዚያንም በአላህ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ሁሉ ከደጋጎቹ ውስጥ በእርግጥ እናስገባቸዋለን::"},{"id":10,"translation":"10. ከሰዎች መካከል «በአላህ አመንን።» የሚል ሰው አለ:: ከዚያ በአላህ በማመኑ ምክኒያት በተሰቃየ ጊዜ የሰዎችን ማሰቃየት እንደ አላህ ቅጣት ያደርጋል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህም እርዳታ ቢመጣ እኛ በእርግጥ ከናንተ ጋር ነበርን ይላሉ:: አላህ በዓለማት ሕዝብ ልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ አይደለምን?"},{"id":11,"translation":"11. አላህ እነዚያንም በትክክል ያመኑትን በእርግጥ ያውቃል:: መናፍቆቹንም ያውቃል::"},{"id":12,"translation":"12. እነዚያንም የካዱት ሰዎች ለእነዚያ ላመኑት «መንገዳችንን ተከተሉ:: ኃጢአቶቻችሁንም እንሸከማለን» አሉ:: እነርሱም ከኃጢአቶቻቸው ምንንም ተሸካሚዎች አይደሉም:: እነርሱ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው።"},{"id":13,"translation":"13. ሸክሞቻቸውንና ከሸክሞቻቸው ጋር ሌሎች ሸክሞችንም በእርግጥ ይሸከማሉ:: በትንሳኤም ቀን ይቀጥፉት ከነበሩት ሁሉ በእርግጥ ይጠየቃሉ::"},{"id":14,"translation":"14. ኑሕንም ወደ ህዝቦቹ በእርግጥ ላክነው:: በውስጣቸዉም ሺህ ዓመትን ሀምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ:: እነርሱ በዳዮች ሆነዉም የውሃው ማዕበል አጥለቀለቃቸው::"},{"id":15,"translation":"15. ኑህንና የመርከቢቱን ጓዶች አዳንናቸው:: እርሷንም ለዓለማት ተዓምር አደረግናት::"},{"id":16,"translation":"16. መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ኢብራሒም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ የሆነውን (አስታውስ)። «አላህን ተገዙ ፍሩትም ይህን ማድረጋችሁ የምታውቁት ብትሆኑ ለናንተ በላጭ ነው።"},{"id":17,"translation":"17. (ሰዎች ሆይ!) ከአላህ ሌላ የምትገዙት ጣኦታትን ብቻ ነው:: ውሸትንም ትቀጥፋላችሁ:: እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣዖታት ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም:: ስለዚህ ሲሳይን ከአላህ ዘንድ ብቻ ፈልጉ:: ተገዙትም:: ለርሱም አመስግኑ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::"},{"id":18,"translation":"18. ብታስተባብሉም ከፊታችሁ የነበሩት ህዝቦች በእርግጥ አስተባብለዋል:: በመልዕክተኛዉም ላይ ግልጽ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትም::"},{"id":19,"translation":"19. አላህ መፍጠርን እንዴት እንደሚጀምርና ከዚያ እንዴት እንደሚመልሰው አይመለከቱምን? ይህ በአላህ ላይ ቀላል ነው::"},{"id":20,"translation":"20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በምድር ላይ ሂዱ:: እናም መፍጠርን እንዴት እንደጀመረ ተመልከቱ:: ከዚያም አላህ የመጨረሻይቱን መነሳት ያስነሳል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።» በላቸው::"},{"id":21,"translation":"21. የሚሻውን ሰው ይቀጣል:: የሚሻውንም ሰው ያዝንለታል ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::"},{"id":22,"translation":"22. እናንተ በምድርም ሆነ በሰማይ የምታቅቱ አይደላችሁም። ከአላህም ሌላ ወዳጅም ተከላካይም ምንም የላችሁም።"},{"id":23,"translation":"23. እነዚያም በአላህ አናቅጽና በመገናኘቱ የካዱ እነዚያ ከእዝነቴ ተስፋን ቆረጡ:: እነዚያም ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":24,"translation":"24. የህዝቦቹም መልስ፡- «ግደሉት ወይም አቃጥሉት።» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም። ከዚያም ከእሳቲቱ አላህ አዳነው። በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ብዙ ተዐምራት አሉበት።"},{"id":25,"translation":"25. (ኢብራሂም) አለ፡- «ከአላህ ሌላ ጣኦታትን አማልክት የያዛችሁት በቅርቢቱ ህይወት በመካከላችሁ ለመዋደድ ብቻ ነው። ከዚያም በትንሳኤ ቀን ከፊላችሁ በከፊሉ ይክዳል:: ከፊላችሁም ከፊሉን ይረግማል:: መኖሪያችሁም እሳት ናት:: ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም።»"},{"id":26,"translation":"26. ከዚያም ሉጥ ለእርሱ አመነ:: (ኢብራሂምም) «እኔ ወደ ጌታዬ ተሰዳጅ ነኝ:: እነሆ እርሱ አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና።» አለ።"},{"id":27,"translation":"27. ለእርሱም ኢስሐቅንና ያዕቆብን ሰጠነው በዘሩም ውስጥ ነብይነትንና መጽሐፍን አደረግን:: ምንዳውንም በቅርቢቱ ዓለም ሰጠነው:: እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከደጋጎቹ ነው::"},{"id":28,"translation":"28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ: «እናንተ ጠያፍን ሥራ ትሰራላችሁን? በእርሷ ከዓለማት አንድም ሰው አልቀደማችሁም።"},{"id":29,"translation":"29. «እናንተ በእርግጥ ወንዶችን ትመጣላችሁን? መንገድንም ትቆርጣላችሁን? በሸንጓችሁም የሚነወርን ነገር ትሠራላችሁን?» አላቸው:: የሕዝቦቹም መልስ «ከእውነተኞቹ እንደሆንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን።» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም።"},{"id":30,"translation":"30. «ጌታዬ ሆይ! በአመጸኞች ሕዝቦች ላይ እርዳኝ።» አለ::"},{"id":31,"translation":"31. መልዕክተኞቻችንም ወደ ኢብራሂም በብስራት በመጡ ጊዜ «እኛ የዚችን ከተማ ሰዎች አጥፊዎች ነን ሰዎችዋ በዳዮች ነበሩና።» አሉት።"},{"id":32,"translation":"32. «በእርሷ ውስጥ ሉጥ አለ እኮ?» አላቸው:: «እኛ በውስጧ ያለውን ካንተ ይበልጥ አዋቂ ነን:: እርሱንማ በእርግጥ እናድነዋለን:: ቤተሰቦቹንም ጭምር ሚስቱ ብቻ ስትቀር እርሷ በጥፋቱ ውስጥ ከሚቀሩት ናት።» አሉት::"},{"id":33,"translation":"33. መልዕክተኞቻችንም ወደ ሉጥ በመጡት ጊዜ በነሱ ምክንያት አዘነ:: በእነርሱም ልቡ ተጨነቀ። አሉትም: «አትፍራ። አትዘንም። እኛ አዳኞችህ ነን:: ቤተሰቦችህንም ሚስትህ ብቻ ስትቀር:: እርሷ ግን በጥፋቱ ውስጥ ከቀሪዎቹ ናት።"},{"id":34,"translation":"34. «እኛ በዚህ ከተማ ሰዎች ላይ ያምጹ በነበሩበት ምክንያት ከሰማይ ቅጣትን አውራጆች ነን።» (አሉት)"},{"id":35,"translation":"35. በእርግጥም ለሚያስቡ ሰዎች ሁሉ ከእርሷ ግልጽ ምልክትን ተውን (አስቀረን)::"},{"id":36,"translation":"36. ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን። «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ:: የመጨረሻውንም ቀን ፍሩ:: በምድርም ውስጥ የምታጠፉ ሆናችሁ አታበላሹ።» አላቸው።"},{"id":37,"translation":"37. እናም አስተባበሉትና የምድር መንቀጥቀጥ ያዘቻቸው፡፡ ባገራቸዉም ውስጥ ተንከፍረው አደሩ (አነጉ)።"},{"id":38,"translation":"38. ዓድንና ሠሙድንም አጠፋን:: የመኖሪያዎቻቸውን ፍርስራሾች በማየት መጥፋታቸው ለእናንተ በእውነት ተገለጠላችሁ:: ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ሸለመላቸው:: ከመንገድም አገዳቸው:: የማስተዋልም ባለቤቶች ነበሩ:: ግን አላስተዋሉም::"},{"id":39,"translation":"39. ቃሩንንም ፈርዖንንም ሃማንንም አጠፋን:: ሙሳም በተዐምራት በእርግጥ መጣባቸው:: በምድርም ላይ ኮሩ:: አምላጮችም አልነበሩም::"},{"id":40,"translation":"40. ሁሉንም በኃጢአቱ ያዝነው:: ከእነርሱም ውስጥ ጠጠርን ያዘለ ነፍስን የላክንበት አለ:: ከእነርሱም ውስጥ ጩኸት የያዘችው አለ:: ከእነርሱም ውስጥ በእርሱ ምድርን የደረባንበት አለ:: ከእነርሱም ውስጥ ያሰመጥነው አለ:: አላህ የሚበድላቸው አልነበረም:: ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ::"},{"id":41,"translation":"41. የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣኦታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደሠራች ሸረሪት ብጤ ነው:: ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው:: ቢያውቁ ኖሮ አማልክት አድርገው አይገዟቸዉም ነበር::"},{"id":42,"translation":"42. አላህ ያንን ከእርሱ ሌላ የሚገዙትን ማንኛውንም ያውቃል:: እርሱም ሁሉን አሸናፊዉና ጥበበኛው ነው::"},{"id":43,"translation":"43. እነዚህንም ምሳሌዎች ለሰዎች እንገልጻቸዋለን:: ከሊቃውንቶቹም በስተቀር ሌሎችአያውቋትም፡፡"},{"id":44,"translation":"44. አላህም ሰማያትንና ምድርን እውነተኛ ሆኖ ፈጠረ፤ በዚህ ውስጥ ለአማኞች ተዐምር አለበት።"},{"id":45,"translation":"45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመጽሐፉ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ:: ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ:: ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና:: አላህን ማውሳት ከመልካም ነገር ሁሉ በላጭ ነው:: አላህም የምትሠሩትን ስራ ሁሉ ያውቃል::"},{"id":46,"translation":"46. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር የመጽሐፉ ባለቤቶችን በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ:። በሉም፡- «በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን:: አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው:: እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን።»"},{"id":47,"translation":"47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንደዚሁም ወደ አንተ መጽሐፍን አወረድን:: እነዚያም መጽሐፍን የሰጠናቸው በእርሱ ያምናሉ:: ከእነዚህም (ከመካ) ሰዎች በእርሱ የሚያምኑ አሉ:: በተዓምራታችንም ከሓዲያን እንጂ ማንም አይክድም::"},{"id":48,"translation":"48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእርሱ በፊትም መጽሐፍን የምታነብ በቀኝህም የምትጽፈው አልነበርክም:: ያን ጊዜ አጥፊዎቹ በእርግጥ በተጠራጠሩ ነበር::"},{"id":49,"translation":"49. አይደለም:: እርሱ (ቁርኣን) በእነዚያ እውቀትን በተሰጡት ሰዎች ልቦች ውስጥ የጠለቀ ግልፆች አናቅጽ ነው:: በአናቅጻችንም በዳዮቹ እንጂ ሌላው አይክድም::"},{"id":50,"translation":"50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን «በእርሱ ላይ ከጌታው ዘንድ ተዐምራት ለምን አልተወረዱም?» አሉ:: »ተዐምራት ከአላህ ዘንድ ብቻ ናቸው:: እኔም ግልጽ አስፈራሪ ብቻ ነኝ።» በላቸው::"},{"id":51,"translation":"51. እኛ መጽሐፉን በእነርሱ ላይ የሚነበብ ሆኖ ባንተ ላይ ማውረዳችን አይበቃቸዉምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ሁሉ ችሮታና ግሳጼ አለበት::"},{"id":52,"translation":"52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአላህ በቃ:: በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ ያውቃል።» በላቸው:: እነዚያም በብላሽ ነገር ያመኑና በአላህ የካዱ እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው።"},{"id":53,"translation":"53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በቅጣትም ያስቸኩሉሃል! የተወሰነም ጊዜ ባልነበረ ኖሮ ቅጣቱ በመጣባቸው ነበር:: እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑም በድንገት በእርግጥ ይመጣባቸዋል::"},{"id":54,"translation":"54. በቅጣት ያስቸኩሉሃል! ገሀነምም ከሓዲያንን በእርግጥ ከባቢ ናት::"},{"id":55,"translation":"55. ቅጣቱ ከበላያቸው ከእግሮቻቸዉም ሥር በሚሸፍናቸው ቀን «ትሰሩት የነበራችሁትን ቅመሱ።» በሚላቸዉም ቀን ትከባቸዋለች።"},{"id":56,"translation":"56. እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት:: ብትቸገሩ ተሰደዱ እኔንም ብቻ ተገዙኝ::"},{"id":57,"translation":"57. ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት:: ከዚያም ወደ እኛ ትመለሳላችሁ::"},{"id":58,"translation":"58. እነዚያም በአላህ ያመኑና መልካም ስራዎችን የሠሩ ከገነት በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ሰገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በእርግጥ እናሰፍራቸዋለን:: የሠራተኞችም ምንዳ ምንኛ አማረ!"},{"id":59,"translation":"59. እነርሱ እነዚያ የታገሱ በጌታቸዉም ላይ የሚመኩ ናቸው፡"},{"id":60,"translation":"60. ከተንቀሳቃሽ ፍጡራን ምግባቸውን የማይሸከሙ ብዙ ናቸው:: አላህ ይመግባቸዋል:: እናንተንም ይመግባል:: እርሱ ሰሚና አዋቂ ነውና::"},{"id":61,"translation":"61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ጸሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ ”አላህ ነው“ ይሉሃል:: ታዲያ እንዴት ይመለሳሉ።"},{"id":62,"translation":"62. አላህ ከባሮቹ ለሚሻው ሲሳይን ያሰፋል:: ለእርሱም ያጠባል:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነውና::"},{"id":63,"translation":"63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሰማይ ውሃን ያወረደና በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ያደረጋት ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው \"አላህ ነው\" ይሉሃል:: \"ስለዚህ ምስጋና ሁሉ ለአላህ ነው።“ በላቸው:: ግን አብዛኞቻቸው ይህን አያውቁም።"},{"id":64,"translation":"64. ይህም የቅርቢቱ ሕይወት መታለያና ጨዋታ እንጂ ሌላ አይደለም:: የመጨረሻይቱም አገር እርሷ በእርግጥ የዘላለም ህይወት አገር ናት:: የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ ጠፊይቱን ሕይወት አይመርጡም ነበር::"},{"id":65,"translation":"65. በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይጠሩታል:: ወደ የብስ በማውጣት ባዳናቸው ጊዜ ግን ወዲያውኑ እነርሱ ጣዖትን ያጋራሉ::"},{"id":66,"translation":"66. በሰጠናቸው ጸጋ ሊክዱና ሊጠቃቀሙ ያጋራሉ፤ ወደ ፊትም የሚጠብቃቸውን ያውቃሉ።"},{"id":67,"translation":"67. ሰዎቹ ከየዙሪያቸው ሲነጠቁ እኛ አገራቸውን ጸጥተኛ ክልል ማድረጋችንን አያዩምን? በውድቅ ነገር ያምናሉን? በአላህም ጸጋ ይክዳሉን?"},{"id":68,"translation":"68. በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰው ወይም እውነት በመጣለት ጊዜ ከአስዋሸ ሰው ይበልጥ ራሱን በዳይ ማነው? በገሀነም ውስጥ ለከሓዲያን መኖሪያ የለምን?(አለ)"},{"id":69,"translation":"69. እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ ህዝቦችን መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን:: አላህ በእርግጥ ከበጎ ሰሪዎች ጋር ነውና፡:"}]},{"id":30,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚይም::"},{"id":2,"translation":"2. ሩም (በፋርሶች) ተሸነፈች፡፡"},{"id":3,"translation":"3. በጣም (ለዐረቡ ዓለም) ቅርብ በሆነችው ምድር ላይ እነርሱም (ከሶስት አመት ያላነሰ ከዘጠኝ ባልበለጠ በጥቂት አመታት ውስጥ) ከመሸነፋቸው በኋላ ያሸንፋሉ::"},{"id":4,"translation":"4. (ከሶስት አመት ያላነሰ ከዘጠኝ ባልበለጠ) በጥቂት አመታት ውስጥ (ያሸንፋሉ)። ጉዳዩ በፊትም ሆነ በኋላ የአላህ ነውና:: በዚያ ቀንም ምዕምናን ይደሰታሉ::"},{"id":5,"translation":"5. በአላህ እርዳታ (ይደሰታሉ)፡፡ አላህ የሚሻውን ሰው ይረዳል:: እርሱም ሁሉን አሸናፊና አዛኝ ነው::"},{"id":6,"translation":"6. አላህ እርዳታን በቁርጥ ቀጠረ:: አላህ ቀጠሮውን አያፈርስም:: ግን አብዛሀኞቹ ሰዎች አያውቁም::"},{"id":7,"translation":"7. ከቅርቢቱ ህይወት ግልጹን ብቻ ያውቃሉ:: እነርሱም ከኋለኛይቱ ዓለም ፍጹም ዘንጊዎች ናቸው::"},{"id":8,"translation":"8. በነፍሶቻቸው ሁኔታ አያስተውሉምን ? ሰማያትን፤ ምድርንና በመካከላቸው ያለውን ሁሉ በእውነትና በተወሰነ ጊዜ እንጂ አልፈጠራቸዉም:: ከሰዎች መካከል ብዙዎቹ ከጌታቸው ጋር በመገናኘት ከሓዲያን ናቸው::"},{"id":9,"translation":"9. በምድር ላይ አይሄዱምና የእነዚያን ከበፊታቸው የነበሩትን ሰዎች ፍፃሜ እንዴት እንደነበር አይመለከቱምን? በኃይል ከእነርሱ ይበልጡ ነበሩ:: ምድርንም አረሱ:: እነዚህ ከአለሟትም የበለጠ አለሟት:: መልዕክተኞቻቸዉም በተአምራቶች መጡባቸው:: ግና አስተባበሉና ጠፉ:: አላህም የሚበድላቸው አልነበረም:: ግና ነፍሶቻቸውን በራሳቸው ይበድሉ ነበር::"},{"id":10,"translation":"10. ከዚያም የእነዚያ ያጠፉት ሰዎች መጨረሻ በአላህ አናቅጽ ማስተባበላቸውና በእርሷ የሚሳሳቁ የሚያፌዙ መሆናቸው (ምክንያት መጥፎ ቅጣት) ሆነ።"},{"id":11,"translation":"11. አላህ መፍጠርን ይጀምራል:: ከዚያም ይመልሰዋል:: ከዚያም ወደ እርሱ ትመለሳለችሁ::"},{"id":12,"translation":"12. ሰዓቲቱም በምትከሰትበት ቀን አመጸኞች ጭጭ ይላሉ (ተስፋ ይቆርጣሉ)።"},{"id":13,"translation":"13. ለእነርሱም ከሚያጋሯቸው ጣዖታት መካከል አማላጆች አይኖሩዋቸዉም:: በሚያጋሯቸዉም ጣዖታት ከሓዲያን ይሆናሉ::"},{"id":14,"translation":"14. ሰዓቲቱም በምትከሰትበት ቀን በዚያ ቀን ይለያያሉ::"},{"id":15,"translation":"15. እነዚያ በአላህ ያመኑትና መልካሞችን ስራዎች የሰሩትማ እነርሱ በገነት ጨፌ ውስጥ ይደሰታሉ::"},{"id":16,"translation":"16. እነዚያም በአላህ የካዱትማ በአናቅጻችንና በኋለኛይቱም ዓለም መገናኘት ያስተባበሉት እነዚያ በቅጣት ውስጥ የሚጣዱ ናቸው::"},{"id":17,"translation":"17. አላህንም በምታመሹና በምታነጉም ጊዜ አጥሩት::"},{"id":18,"translation":"18. ምስጋናም በሰማያትና በምድር ውስጥ ለእርሱ ብቻ የተገባው ነው:: በሰርክም በቀትር ውስጥ በምትገቡም ጊዜ አጥሩት::"},{"id":19,"translation":"19. ህያውን ከሙት ያወጣል:: ሙትንም ከህያው ያወጣል:: ምድርንም ከሞተች በኋላ ህያው ያደርጋታል:: ልክ እንደዚሁም (ከመቃብር) ትወጣላችሁ::"},{"id":20,"translation":"20. እናንተንም ከአፈር መፍጠሩ ከዚያም እናንተ ወዲያውኑ የምትበታተኑ ሰዎች መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው::"},{"id":21,"translation":"21. ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ ሚስቶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተዐምራት አሉበት::"},{"id":22,"translation":"22. ሰማያትንና ምድርን መፍጠሩ የቋንቋዎቻችሁና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለአዋቂዎች አያሌ ታዐምራት አሉበት::"},{"id":23,"translation":"23. በሌሊትም ሆነ በቀን መተኛታችሁ ከችሮታዉም መፈለጋችሁም ከምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ህዝቦች ሁሉ ብዙ ታዐምራት አሉበት::"},{"id":24,"translation":"24. ብልጭታንም ፈሪዎችና ከጃዮች ስትሆኑ ለእናንተ ማሳየቱ ከሰማይም ውሃን ማውረዱ በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚያስቡ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ታዐምራት አሉበት::"},{"id":25,"translation":"25. ሰማይና ምድርም ያለ ምሰሶ በትእዛዙ መቆማቸው ከዚያም መልአክ ለትንሳኤ ከምድር ጥሪን በጠራችሁ ጊዜ እናንተ ወዲያውኑ የምትወጡ መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው::"},{"id":26,"translation":"26. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው::"},{"id":27,"translation":"27. እርሱ ያ ፍጡራንን ከምንም የሚጀምር (የሚያስገኝ) ከዚያም የሚመልሳቸው ብቸኛ አምላክ ነው:: መመለሱም በእርሱ ላይ በጣም ቀላል ነው:: ለእርሱም በሰማያትና በምድር ከፍተኛው ምሳሌ (ባህሪ) አለው:: እርሱም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው።"},{"id":28,"translation":"28. (ጣዖት አምላኪዎች ሆይ!) ለእናንተ ከነፍሶቻችሁ የሆነን ምሳሌ አደረገላችሁ:: እርሱም እጆቻችሁ ከያዟቸው ባሮች ውስጥ በሰጠናችሁ ጸጋ ለእናንተ ተጋሪዎች አሏችሁን? ታዲያ እናንተና እነርሱ በእርሱ እኩል ለኩል (ትክክል) ናችሁን? ነፍሶቻችሁን (ብጤዎቻችሁን) እንደምትፈሩ ትፈሯቸዋላችሁን ? ልክ እንደዚሁ ለሚያስተውሉ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን እንገልጻለን::"},{"id":29,"translation":"29. ይልቁንም እነዚህ የበደሉ ሰዎች ያለ ዕውቀት ዝንባሌዎቻቸውን ተከተሉ:: አላህም ያጠመመውን ሰው የሚያቀናው ማነው? ለእነርሱም ከረዳቶች ምንም የላቸዉም::"},{"id":30,"translation":"30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እውነት ተዘንባይ ሆነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ:: የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በርሷ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት (ያዟት):: የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም:: ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::"},{"id":31,"translation":"31. ወደ እርሱ ተመላሾች ሆናችሁ የአላህን ሃይማኖት ያዙ:: ፍሩትም:: ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ:: ከአጋሪዎችም አትሁኑ::"},{"id":32,"translation":"32. ከእነዚያ ሃይማኖታቸውን ከለያዩትና ክፍልፍልም ከሆኑት አትሁኑ:: ህዝብ ሁሉ እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር ብቻ ተደሳቾች ናቸው::"},{"id":33,"translation":"33. ሰዎችንም ችግር ባገኛቸው ጊዜ ጌታቸውን ወደ እርሱ ተመላሾች ሆነው ይጠሩታል:: ከዚያም ከእርሱ ችሮታንም ባቀመሳቸው ጊዜ ከእነርሱ ከፊሎቹ ወዲያውኑ በጌታቸው ጣዖትን ያጋራሉ::"},{"id":34,"translation":"34. በሰጠናቸው ጸጋ ሊክዱ (ያጋራሉ):: ተጣቀሙም:: በእርግጥም መጨረሻችሁን ወደፊት ታውቃላችሁ::"},{"id":35,"translation":"35. በእነርሱ ላይ አላህ አስረጅን አወረደን? ታድያ እርሱ በነዚያ በእርሱ ያጋሩ በነበሩት ነገር ይናገራልን? የለም::"},{"id":36,"translation":"36. ሰዎችንም ችሮታን ባቀመስናቸው ጊዜ በእርሷ ይደሰታሉ:: እጆቻቸዉም ባሳለፉት ምክንያት መከራ ብታገኛቸው ወዲያውኑ እነርሱ ተስፋ ይቆርጣሉ::"},{"id":37,"translation":"37. አላህ ለሚሻው ሰው ሲሳይን የሚያሰፋ የሚያጠብም መሆኑን አያዩምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ህዝቦች አስደናቂ ምልክቶች አሉበት::"},{"id":38,"translation":"38.ስለዚህ (አማኝ ሆይ!) የዝምድናን ባለቤት ተገቢውን ስጠው:: ለድሃም ለመንገደኛም እርዳ:: ይህ ለእነዚያ የአላህን ፊት ለሚሹ ሁሉ መልካም ነው:: እነዚያ እነርሱም በሁለተኛው ዓለም የፈለጉትን የሚያገኙ ምርጥ ክፍሎች ናቸው::"},{"id":39,"translation":"39. (ሰዎች ሆይ!) በሰዎች ውስጥም ይጨመር ዘንድ በማቀድ የምትሰጡት ገንዘብ በአላህ ዘንድ ቅንጣት አይጨምርም:: የአላህን ፊት ብቻ የምትሹ ሆናችሁ የምትሰጡት ምጽዋት ግን እነዚያ እውነተኛ ሰጪዎች (አበርካቾች) እነርሱ ናቸው::"},{"id":40,"translation":"40. አላህ ያ የፈጠራችሁ ከዚያም ሲሳይን የሰጣችሁ ከዚያም የሚገድላችሁ ከዚያም ህያው የሚያደርጋችሁ ነው:: ከምታጋሯቸው ጣዖታት ውስጥ ከዚሃችሁ አንዳችን የሚሰራ አለን? ለአላህ ጥራት ይገባው በእርሱ ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ::"},{"id":41,"translation":"41. የሰዎች እጆች በሰሩት ኃጢአት ምክንያት የዚያን የሰሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባህር ተገለጠ (ተሰራጨ)። እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና::"},{"id":42,"translation":"42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በምድር ላይ ሂዱ የእነዚያንም በፊት የነበሩት ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ።» በላቸው:: አብዛኞቻቸው አጋሪዎች ነበሩ።"},{"id":43,"translation":"43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእርሱ መመለስ የሌለው ቀን የትንሳኤ ቀን ከአላህ ሳይመጣ በፊት ፊትህን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት ቀጥ አድርግ :: በዚያ ቀን ወደ ገነትና ወደ እሳት ይለያያሉ::"},{"id":44,"translation":"44. በአላህ የካደ ሰው የክህደቱ ጠንቁ በእርሱው ላይ ብቻ ነው:: መልካምም የሰሩ ሁሉ ለነፍሶቻቸው ማረፊያዎችን ያዘጋጃሉ::"},{"id":45,"translation":"45. እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሰሩትን ከችሮታው ይመነዳ ዘንድ (ይለያያሉ):: እርሱ ከሓዲያንን አይወድምና::"},{"id":46,"translation":"46. (ሰዎች ሆይ!) ንፋሶችንም (በዝናብ) ልታበስራችሁ ከችሮታዉም (በእርሷ) ሊያቀምሳችሁ መርከቦችም በትእዛዙ እንዲንሻለሉ ከችሮታዉም እንድትፈልጉ ታመሰግኑትም ዘንድ መላኩ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው::"},{"id":47,"translation":"47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም መልዕክተኞችን ወደ የህዝቦቻቸው በእርግጥ ላክን:: በግልጽ ማስረጃዎችም መጡባቸው:: ከእነዚያ ካመጹትም ተበቀልን:: ምዕመናኖችንም መርዳት በእኛ ላይ ተገቢ ሆነ::"},{"id":48,"translation":"48. አላህ ያ ! ንፋሶችን የሚልክ ነው:: ደመናንም ይቀሰቅሳል:: በሰማይ ላይም እንደሚሻ ይዘረጋዋል :: ቁርጥራጮችም ያደርገዋል:: ዝናቡንም ከደመናው መካከል ሲወጣ ታያለህ:: በእርሱም ከባሮቹ የሚሻውን በለየ ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ይደሰታሉ::"},{"id":49,"translation":"49. በእነርሱም ላይ ከመውረዱ በፊት ከእርሱ በፊት በእርግጥ ተስፋ ቆራጮች ነበሩ::"},{"id":50,"translation":"50. ምድርንም ከሞተች በኋላ እንዴት ህያው እንደሚያደርጋት ወደ አላህ ችሮታ ፈለጎች ተመልከት:: ይህን አድራጊ ጌታ ሙታንንም በእርግጥ ህያው አድራጊ ነው :: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::"},{"id":51,"translation":"51. ንፋስንም በአዝመራዎች ላይ ብንልክና ገርጥቶ ቢያዩት ከእርሱ በኋላ በእርግጥ ችሮታውን የሚክዱ ይሆናሉ::"},{"id":52,"translation":"52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ሙታንን አታሰማም:: ደንቆሮዎችንም ዟሪዎች ሆነው በሸሹ ጊዜ ጥሪን አታሰማም::"},{"id":53,"translation":"53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ እውሮችንም ከጥመታቸው የምታቀና አይደለህም:: በአናቅጻችን የሚያምኑትን ሰዎች እንጂ ሌላን አታሰማም:: እነርሱም ታዛዦች ናቸው::"},{"id":54,"translation":"54. (ሰዎች ሆይ!) አላህ ያ ከደካማ ፍትወት ጠብታ የፈጠራችሁ ነው:: ከዚያ ከደካማነት በኋላም ኃይልን አደረገ:: ከዚያም ከብርቱነት በኋላ ደካማነትና ሽበትንም አደረገ:: የሚሻውን ይፈጥራል:: እርሱም ሁሉን አዋቂውና ቻዩ ነው::"},{"id":55,"translation":"55. ሰዓቲቱ በምትከሰትበት ቀን ከሓዲያን «ከአንዲት ሰዓት በስተቀር በመቃብር (በዱንያ) አልቆየንም።» ብለው ይምላሉ:: ልክ እንደዚሁ በዚህኛው ዐለምም እያሉ ከእውነት ይመለሱ ነበር::"},{"id":56,"translation":"56. እነዚያም እውቀትንና እምነትን የተሰጡት «በአላህ መጽሐፍ ፍርድ እስከ ትንሳኤ ቀን በእርግጥ ቆያችሁ ይህም የካዳችሁት የትንሳኤ ቀን ነው:: ግን እናንተ የማታውቁ ነበራችሁ።» ይሏቸዋል::"},{"id":57,"translation":"57. በዚያም ቀን እነዚያን የበደሉትን ማመካኘታቸው አይጠቅማቸዉም:: እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም::"},{"id":58,"translation":"58. በዚህም ቁርኣን ውስጥ ለሰዎች የምሳሌ አይነቶችን ሁሉ በእርግጥ ገለጽን:: በተዓምርን ብታመጣላቸው እንኳን እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች «እናንተ አበላሺዎች የጥፋት ተጣሪ ዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።» ይላሉ::"},{"id":59,"translation":"59 ልክ እንደዚሁ አላህ በነዚያ በማያውቁት ሰዎች ልቦች ላይ ያትማል::"},{"id":60,"translation":"60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለዚህ ታገሥ:: የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና:: እነዚያም በትንሳኤ የማያረጋግጡት ሰዎች አያቅልሉህ::"}]},{"id":31,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚይም፤"},{"id":2,"translation":"2. እነዚህ አናቅጽ ጥበብ ከተሞላው መጽሐፍ ናቸው።"},{"id":3,"translation":"3. ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ መሪ፣ እዝነት ሲሆን፤"},{"id":4,"translation":"4. ለእነዚያ ሶላትን አስተካክለው ለሚሰግዱ፤ ዘካንም ለሚሰጡት፤ በመጨረሻይቱም ዓለም የሚያረጋግጡ ለሆኑት፤"},{"id":5,"translation":"5. እነዚያ (የተጠቀሱትን ባህሪያት የሚላበሱ ሰዎች ሁሉ) በጌታቸው መመሪያ ላይ የሚጓዙ ናቸው። እነዚያ ፍላጎታቸውንም ያገኙትም እነርሱ ብቻ ናቸው::"},{"id":6,"translation":"6. ከሰዎች መካከል ያለ ምንም እውቀት ሰዎችን ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና የአላህን መንገድ ማላገጫ ሊያደርግ አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ:: እነዚያ ይህን የሚያደርጉ ሁሉ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":7,"translation":"7. አናቅጻችን በእርሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ እንዳልሰማትና በጆሮቹ ድንቁርና እንዳለበት የኮራ ሆኖ ይዞራል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህን ሰው በአሳማሚ ቅጣት አብስረው::"},{"id":8,"translation":"8. እነዚያ ያመኑና መልካሞችን ተግባራት የሰሩ ሁሉ ለእነርሱ የጸጋ ገነቶች አሏቸው::"},{"id":9,"translation":"9. በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ሲሆኑ አላህ እውነተኛን የተስፋ ቃል ገባላቸው:: እርሱም ሁሉንም አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":10,"translation":"10. ሰማያትን የምታዮዋት ምሰሶ ሳያደርግላት ፈጠረ:: በምድርም ውስጥ በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለ:: በእርሷም ላይ ከተንቀሳቃሽ ነገሮች ሁሉ በተነ:: ከሰማይም ውሃን አወረድን:: በእርሷ ውስጥ ከመልካም ዓይነት ሁሉ አበቀልን::"},{"id":11,"translation":"11. ይህ ሁሉ የአላህ ፍጡር ነው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደ ፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ:: በዳዮች በእውነት በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው::"},{"id":12,"translation":"12. ለሉቅማንም ጥበብን በእርግጥ ሰጠነው:: አላህን አመስግን አልነዉም:: ያመሰገነም ሁሉ የሚያመሰግነው ለራሱ ብቻ ነው:: የካደም ሰውም (በራሱ ላይ ነው::) አላህ ተብቃቂና ምስጉን ነውና::"},{"id":13,"translation":"13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገስጸው ሲሆን «ልጄ ሆይ! በአላህ አታጋራ። ማጋራት ታላቅ በደል ነውና።» ያለውን አስታውስ።"},{"id":14,"translation":"14. ሰውንም በወላጆቹ በጎ እንዲያደርግ በጥብቅ አዘዝነው:: እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው:: ጡት መጣያዉም በሁለት ዓመት ውስጥ ነው:: «ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን\" በማለትም አዘዝነው። መመለሻው ወደ እኔ ብቻ ነው።"},{"id":15,"translation":"15. ላንተ በእርሱ እውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢያስገድዱህ አትታዘዛቸው:: በቅርቢቱም ዓለም በመልካም ስራ ተወዳጃቸው:: ወደ እኔም የተመለሰን ሰው መንገድ ተከተል:: ከዚያ መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው:: ትሰሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ (አልነው)።"},{"id":16,"translation":"16. (ሉቅማንም አለ:) «ልጄ ሆይ! የእርሷ (መጥፎም ይሁን በጎ) የሰናፍጭ ቅንጣት ክብደት ያህል እንኳን ብትሆንና በቋጥኝ ውስጥ ወይም በሰማያት ውስጥ ወይም በምድር ውስጥ ብትሆን አላህ ያመጣታል:: አላህ ሩህሩህና ውስጠ አዋቂ ነውና።"},{"id":17,"translation":"17. «ልጄ ሆይ! ሶላትን አስተካክለህ ስገድ፤ በበጎ ነገርም እዘዝ ከሚጠላም ሁሉ ከልክል፤ በሚያገኝህም መከራ ላይ ታገስ ይህ በምር ከሚያዙ ወሳኝ ነገሮች ነው።"},{"id":18,"translation":"18. «ጉንጭህንም በኩራት ከሰዎች አታዙር:: በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ:: አላህ ተንበጥራሪን (ኮራተኛ) ጉረኛን ሁሉ አይወድምና::"},{"id":19,"translation":"19. «በአካሄድህም መካከለኛ ሁን:: ከድምጽህም ዝቅ አድርግ:: ከድምፆች ሁሉ አስከፊው የአህዮች ድምጽ ነውና።»"},{"id":20,"translation":"20. (ሰዎች ሆይ!) አላህ በሰማያት እና በምድር ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ ለእናንተ ያገራላችሁ፤ ጸጋዎችንም ግልጽም ይሁኑ ድብቅ የሞላላችሁ መሆኑን አታዩምን? ከስሞች መካከል ያለ በቂ እውቀትና ያለ መሪ፤ ያለ ግልጽ መጽሀፍም፤ ስለ አላህ የሚከራከር አለ::"},{"id":21,"translation":"21. ለእነርሱም «አላህ ያወረደውን ተከተሉ።» በተባሉ ጊዜ «አይደለም በእርሱ ላይ አባቶቻችንን ያገኘንበትን እንከተላለን።» ይላሉ:: ሰይጣን (ይህን ተግባር በማስዋብ) ወደ እሳት ቅጣት የሚጠራቸው ቢሆንም ይከተሏቸዋልን?"},{"id":22,"translation":"22. መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥ ሁሉ ጠንካራ ገመድን በእርግጥ ጨበጠ:: የነገሩ ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ብቻ ነው::"},{"id":23,"translation":"23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ የካደም ሁሉ ክህደቱ አያሳዝንህ። መመለሻቸው ወደ እኛ ብቻ ነውና:: ከዚያም የሰሩትንም ሁሉ እንነግራቸዋለን:: አላህ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃልና፡፡"},{"id":24,"translation":"24. ጥቂትን ጊዜ እናጣቅማቸዋለን:: ከዚያም ወደ ብርቱ ቅጣት እናስገድዳቸዋለን::"},{"id":25,"translation":"25. ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው።» ይላሉ። «ምስጋና ሁሉ ለአላህ ብቻ ይገባው።» በላቸው:: ይልቁንም አብዛኞቹ አያውቁም።"},{"id":26,"translation":"26. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: አላህ በራሱ ተብቃቂዉና ምስጉኑ ነው::"},{"id":27,"translation":"27. በምድር ያሉ ሁሉ ዛፎች ብዕሮች ቢሆኑ ኖሮ ባህሩም ከእርሱ ማለቅ በኋላ ሰባት ባህሮች የሚጨመሩለት ሆኖ ቀለም ቢሆንና ቢጻፍባቸው የአላህ ቃላት ባላለቀች ነበር:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":28,"translation":"28. (ሰዎች ሆይ!) እናንተን መፍጠርና እናንተን መቀስቀስ እንደ አንዲት ነፍስ እንጂ ሌላ አይደለም:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነውና::"},{"id":29,"translation":"29. (የሰው ልጅ ሆይ) አላህ ሌሊትን በቀን ውስጥ የሚያስገባ ቀንንም በሌሊት ውስጥ የሚያስገባ ጸሀይንና ጨረቃንም የገራ መሆኑን አታይምን? ሁሉም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ይሮጣሉ:: አላህም በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::"},{"id":30,"translation":"30. ይህም የእርሱ (የአላህ) ብቸኛ አምላክነት እውነት በመሆኑ፤ ከእርሱ ሌላ የሚገዙት ጣዖት ሁሉ ውሸት በመሆኑና አላህ የበላይ ታላቅ በመሆኑ ነው።"},{"id":31,"translation":"31. (የሰው ልጅ ሆይ!) ከአስደናቂ ምልክቶቹ ሊያሳያችሁ መርከቦች በአላህ ችሮታ በባህር ውስጥ የሚንሻለሉ መሆናቸውን አታይምን? በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽ አመስጋኝ ለሆኑ ሁሉ አያሌ ተዓምራት አሉበት::"},{"id":32,"translation":"32. እንደ ጥላዎች የሆነ ማዕበል በሸፈናቸው ጊዜ ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው አላህን ይጠሩታል:: ወደ የብስ ባዳናቸው ጊዜ ግን ከእነርሱ መካከል ትክክለኛም አለ:: (ከእነርሱም መካከል የሚክድ አለ):: በአናቅጻችንም አታላይና ከዳተኛ የሆነ ሁሉ እንጂ ሌላው አይክድም::"},{"id":33,"translation":"33. እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ:: ወላጅ ከልጁ በምንም የማይጠቅምበት ልጅም ወላጅን በምንም ጠቃሚ የማይሆንበትን ቀን ፍሩ:: የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና:: ቅርቢቱም ህይወት አትሸንግላችሁ:: በአላህ (መታገስም) አታላዩ (ሰይጣን) አያታልላችሁ።"},{"id":34,"translation":"34. አላህ የሰዓቲቱ እውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው:: ዝናብንም ያወርዳል:: በማህጸኖችም ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃል። ማንኛይቱም ነፍስ ነገ የምትሰራውን አታውቅም:: ማንኛይቱም ነፍስ በየትኛው ምድር እንደምትሞትም አታውቅም:: አላህ አዋቂና ውስጠ አዋቂ ነው::"}]},{"id":32,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚይም፤"},{"id":2,"translation":"2. የመጽሐፉ መወረድ ጥርጥር የለበትም:: የወረደዉም ከዓለማቱ ጌታ ነው::"},{"id":3,"translation":"3. ይልቁንም «ቀጠፈው» ይላሉን? አይደለም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱ ከጌታህ የሆነ እውነት ነው:: በእርሱ ካንተ በፊት ከአስፈራሪ ነቢይ ያልመጣባቸውን ሕዝቦች በእርሱ ልታስፈራራበት ያወረደልህ ነው:: እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና::"},{"id":4,"translation":"4. አላህ ያ! ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ ከዚያም ለክብሩ በሚስማማ መልኩ በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ ነው:: ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ወዳጅም አማላጅም ምንም የላችሁም:: አትገሰጹምን?"},{"id":5,"translation":"5. ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያዘጋጃል፤ ከዚያም ከምትቆጥሩት (ዘመን) ልኩ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ ይወጣል::"},{"id":6,"translation":"6. ይህንን ያደረገው ሩቁንም ቅርቡንም ሁሉ አዋቂው፤ ሁሉን አሸናፊና አዛኙ ጌታ ነው::"},{"id":7,"translation":"7. ያ የፈጠረውን ነገር ሁሉ ያሳመረው:: የሰውንም ፍጥረት ከጭቃ የጀመረው ነው::"},{"id":8,"translation":"8. ከዚያም ዘሮቹን ከተንጣለለ ከደካማ ውሃ የፈጠረ ነው::"},{"id":9,"translation":"9. ከዚያም ቅርጹን አስተካከለው:: በእርሱ ውስጥም ከመንፈሱ ነፍስ ዘራበት:: ለናንተም ጆሮዎችን ዓይኖችንና ልቦችንም አደረገላችሁ። በጣም ጥቂትን ብቻ ታመሰግናላችሁ።"},{"id":10,"translation":"10. «በምድርም ውስጥ በስብሰን በጠፋን ጊዜ እኛ በአዲስ መፈጠር ውስጥ እንሆናለን?» አሉ:: በእውነቱ እነርሱ በጌታቸው መገናኘት ከሓዲያን ናቸው::"},{"id":11,"translation":"11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእናንተ ላይ የተወከለው መልአከ ሞት ይገድላችኋል:: ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ።» በላቸው።"},{"id":12,"translation":"12. አመጸኞችም በጌታቸው ዘንድ ራሶቻቸውን ያቀረቀሩ ሆነው፡‐ «ጌታችን ሆይ! አየን። ሰማንም። መልካምን እንሠራለንና (ወደ ምድረ ዓለም) መልሰን እኛ አረጋጋጮች ነን» የሚሉ ሲሆኑ ብታይ ኖሮ( አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር)።"},{"id":13,"translation":"13 በሻንም ኖሮ ነፍስን ሁሉ ቅንነቷን(እምነቷን) በሰጠናት ነበር:: ግን ገሀነምን ከአጋንንትና ከሰዎች የተሰበሰቡ ሆነው በእርግጥ እሞላለሁ ማለት ቃሉ ከእኔ ተረጋግጧል::"},{"id":14,"translation":"14. ይህንንም ቀናችሁን መገናኘትን በመርሳታችሁ ምክንያት ቅጣትን ቅመሱ! እኛ ተውናችሁ። ትሰሩት በነበራችሁትም ጥፋት ዘውታሪን ቅጣት ቅመሱ ይባላሉ::"},{"id":15,"translation":"15. በአናቅጻችን የሚያምኑት እነዚያ በእርሷ በተገሰጹ ጊዜ ሰጋጆች ሆነው የሚወድቁትና እነርሱም የማይኮሩ ሆነው በጌታቸው ምስጋና (ተጎናጽፈው) የሚያወድሱት ሰዎች ብቻ ናቸው። {1}","footnotes":"{1} እዚህጋ ሱጁዱትላዋ (የንባብ ሱጁድ) መድረግ ያስፈልጋል። በሶላት ውስጥም ከሶላት ውጪም መድረጉ ይወደዳል።"},{"id":16,"translation":"16. ጌታቸውን ለመፍራትና ለመከጀል የሚጠሩት ሆነው ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ቦታዎቻቸው ይርቃሉ:: ከሰጠናቸዉም ጸጋ ይለግሳሉ::"},{"id":17,"translation":"17. ይሰሩት በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም::"},{"id":18,"translation":"18. አማኝ የሆነ ሰው አመጸኛ እንደሆነ ሰው ነውን? አይስተካከሉም::"},{"id":19,"translation":"19. እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሰሩማ ለነሱ ይሰሩት በነበሩት ምክንያት መስተንግዶ ሲሆኑ መኖሪያ ገነቶች አሏቸው::"},{"id":20,"translation":"20. እነዚያ ያመጹትማ መኖሪያቸው እሳት ናት:: ከእርሷ መውጣትን በፈለጉ ቁጥር በእርሷ ውስጥ ይመለሳሉ ለእነርሱም «ያንን በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁትን የእሳት ቅጣት ቅመሱ» ይባላሉ።"},{"id":21,"translation":"21. ይመለሱ ዘንድ ከትልቁ ቅጣት በፊት (በዚህ ዓለም) ትንሹን ቅጣት በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን::"},{"id":22,"translation":"22. በጌታዉም አናቅጽ ከተገሰጸና ከዚያም ከተዋት ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው? (የለም) እኛ ከተንኮለኞቹ ሁሉ ተበቃዮች ነን::"},{"id":23,"translation":"23.ሙሳን መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱን ከመገናኘትህም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን:: ለኢስራኢል ልጆችም መሪ አደረግነው::"},{"id":24,"translation":"24. በታገሱና በተዓምራታችን የሚያረጋግጡ በሆኑም ጊዜ ከእነርሱ በትዕዛዛችን የሚመሩ መሪዎችን አደረግን::"},{"id":25,"translation":"25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በዚያ ይለያዩበት በነበሩት ነገር ሁሉ በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል::"},{"id":26,"translation":"26. ከክፍለ ዘመናት ሰዎች ብዙዎችን ያጠፋን መሆናችን በመኖሪያዎቻቸው የሚሄዱ ሲሆኑ እነርሱ አልተገለጸላቸዉምን? በዚህ ውስጥ አያሌ ምልክቶች አሉበት:: አይሰሙምን?"},{"id":27,"translation":"27. እኛ ውሃን ወደ ደረቅ ምድር የምንነዳ እንስሶቻቸውና ነፍሶቻቸው ከእርሱ የሚበሉለትንም አዝመራ በእርሱ የምናወጣ መሆናችንን አያዩምን? አይመለከቱምን?"},{"id":28,"translation":"28. «ከእውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ፍርድ መቼ ነው።» ይላሉ።"},{"id":29,"translation":"29. «በፍርዱ ቀን እነዚያን የካዱትን ሰዎች እምነታቸው አይጠቅማቸዉም:: እነርሱም ጊዜን አይሰጡም።» በላቸው።"},{"id":30,"translation":"30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ተዋቸው:: ተጠባበቅም:: እነርሱም ተጠባባቂዎች ናቸውና::"}]},{"id":33,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አንተ ነብይ ሆይ! አላህን ፍራ:: ከሓዲያንንና አስመሳዮችንም አትታዘዝ:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":2,"translation":"2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህም ወደ አንተ የሚወረደውን ብቻ ተከተል:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::"},{"id":3,"translation":"3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ ላይ ተመካ:: መመኪያነትም በአላህ ብቻ በቃ።"},{"id":4,"translation":"4. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ለአንድ ሰው በሆዱ ውስጥ ሁለትን ልቦች አላደረገም:: እነዚያን «እንደናቶቻችን ጀርባዎች ይሁኑብን» የምትሏቸውን ሚስቶቻችሁንም እናቶቻችሁ አላደረገም:: ልጅ በማድረግ የምታስጠጓቸውንም ልጆቻችሁ አላደረገም:: ይህ በአፎቻችሁ የምትሉት ቃላችሁ ብቻ ነው:: አላህ እውነትን ይናገራል:: ትክክለኛውን መንገድም ይመራል::"},{"id":5,"translation":"5. (ሙስሊሞች ሆይ!) (ልጅ በማድረግ የምታስጠጓቸውን) በአባቶቻቸው ስም በማስጠጋት ጥሯቸው:: እርሱ አላህ ዘንድ ትክክለኛው መንገድ ነውና:: አባቶቻቸውን ባታውቁም በሃይማኖት ወንድሞቻችሁና ዘመዶቻችሁ ናቸው:: በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: ልቦቻችሁ አውቀው በሰራችሁት ስህተት ግን ኃጢአት አለባችሁ:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":6,"translation":"6. ነብዩ (ሙሐመድ) ለአማኞች ከነፍሶቻቸው ይበልጥ ቀራቢ ነው:: ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው:: የዝምድና ባለቤቶችም ከፊላቸው በከፊሉ ላይ (ለውርስ) በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ከአማኞችና ከስደተኞች ይልቅ የተገባቸው ናቸው:: ለወዳጆቻችሁ በኑዛዜ መልካም ስራን ብትሰሩ ግን ይፈቀዳል:: ይህ በአላህ መጽሐፉ ውስጥ ቀድሞውኑ የተመዘገበ ነው::"},{"id":7,"translation":"7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከነብዮችም ካንተም፤ ከኑህም፤ ከኢብራሂምም፤ ከሙሳም፤ ከመርየም ልጅ ዒሳም የጠበቀ ቃልኪዳናቸውን በያዝን ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን::"},{"id":8,"translation":"8. አላህ እውነተኞችን ከእውነታቸው ሊጠይቃቸው (ይህንን ሰራ):: ለከሓዲያንም አሳማሚን ቅጣት አዘጋጀ::"},{"id":9,"translation":"9. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ብዙ ሰራዊት በመጣባችሁና በእነርሱ ላይ ንፋስንና በአይናችሁ ያላያችሁትን ሰራዊት በላክን ጊዜ ያደረገላችሁን ጸጋ አስታውሱ:: አላህም የምትሰሩትን ተመልካች ነው።"},{"id":10,"translation":"10. ከበላያችሁም ከናንተ በታችም በመጡባችሁ፤ ዓይኖችም በቃበዙ፤ ልቦችም ወደ ላንቃዎች በደረሱና በአላህም መጥፎ ጥርጣሬዎችን በጠረጠራችሁ ጊዜ ያደረገላችሁን ጸጋ (አስታውሱ)::"},{"id":11,"translation":"11. እዚያ ዘንድ አማኞች ተሞከሩ:: ብርቱን መንቀጥቀጥም ተንቀጠቀጡ::"},{"id":12,"translation":"12. መናፍቆችና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ሁሉ «አላህና መልዕክተኛው ማታለልን እንጂ ሌላን አልቀጠሩንም።» በሚሉም ጊዜ ያደረገላችሁን ውለታ አስታውሱ::"},{"id":13,"translation":"13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም የሆነ ቡድን «የየስሪብ ሰዎች ሆይ! ለእናንተ ስፍራ የላችሁምና ተመለሱ።» ባሉ ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ):: ከእነርሱም መካከል ከፊሎቹ ነውረኛ ሳይሆኑ «ቤቶቻችን ነውረኛ ናቸው።» በማለት ነብዩን ከጦሩ ለመመለስ ፈቃድን ይጠይቃሉ:: መሸሽን እንጂ ሌላን አይፈልጉም::"},{"id":14,"translation":"14. በእርሱም ላይ በቤቶቻቸው ከየቀበሌዋ ከጠላት በተገባባትና ከዚያም ከኢስላም መመለስን በተጠየቁ ኖሮ በፍጥነት በሰሯት ነበር ፡፡ በእሷ ጥቂትን ጊዜ እንጂ አይቆዩም ነበር ፡፡"},{"id":15,"translation":"15. ጀርባዎችንም ላያዞሩ ከዚያም በፊት በእርግጥ አላህን ቃል ኪዳን የገቡ ነበሩ:: የአላህም ቃል ኪዳን የሚጠየቁበት ትልቅ ሀላፊነት ነው::"},{"id":16,"translation":"16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከሞት ወይም ከመገደል ብትሸሹ መሸሻችሁ ፈጽሞ አይጠቅማችሁም:: ያን ጊዜም ጥቂትን እንጂ የምትጣቀሙ አትደረጉም።» በላቸው።"},{"id":17,"translation":"17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ሙስሊምቸ ሆይ!) «አላህ በእናንተ ላይ ክፉን ነገር ቢሻ ያ ከአላህ የሚጠብቃችሁ ማን ነው? ወይም ለእናንተ እዝነትን ቢፈልግ ክፉ የሚያመጣባችሁ ማን ነው?» በላቸው። ከአላህም ሌላ ለእነርሱ ወዳጅም ሆነ ረዳት አያገኙም።"},{"id":18,"translation":"18. ከናንተ ውስጥ የሚያደናቅፉትን ለወንድሞቻቸዉም «ወደ እኛ ኑ» የሚሉትን፤ ውጊያንም ጥቂትን እንጂ የማይመጡትን በእርግጥ አላህ ያውቃቸዋል::"},{"id":19,"translation":"19. (አማኞች ሆይ!) በእናንተ ላይ እርዳታን የነፈጉ ሆነው እንጂ የማይመጡትን፤ ሽብሩም በመጣ ጊዜ እንደዚያ ከሞት መከራ በእርሱ ላይ የሚሸፍን አደጋ እንደ ወደቀበት ዓይኖቻቸው ወዲያና ወዲህ የምትንከራተት ሆና ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ:: ሽብሩም በሄደ ጊዜ በገንዘብ ላይ የሚሳሱ ሆነው በተቡ ምላሶች ይነድፏችኋል:: እነዚያ አላመኑም:: ስለዚህ አላህ ስራዎቻቸውን አበላሸ:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነው።"},{"id":20,"translation":"20. (መናፍቆች) አህዛብን አልሄዱም ብለው ያስባሉ አህዛቦችም ቢመጡ እነርሱ በዘላኖች ውስጥ በገጠር የራቁ ሊሆኑ ይመኛሉ:: (ከዚያም) ከወሬዎቻችሁ ይጠይቃሉ:: በእናንተ ውስጥ በነበሩም ኖሮ ጥቂትን እንጂ አይዋጉም ነበር::"},{"id":21,"translation":"21. (አማኞች ሆይ!) ከናንተ መካከል አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነና አላህንም በብዙ ለሚያወሳ ሰው ሁሉ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ::"},{"id":22,"translation":"22. አማኞችም አህዛብን ባዩ ጊዜ «ይህ አላህና መልዕክተኛው የቀጠሩን ነው:: አላህና መልዕክተኛዉም እውነትን ተናገሩ።» አሉ:: ይህ እምነትንና መታዘዝንም እንጂ ሌላን አልጨመረላቸዉም::"},{"id":23,"translation":"23. ከአማኞች መካከል በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አሉ። ከእነርሱም ስለቱን የፈጸመ ለሃይማኖቱ የተገደለም አለ:: ከእነርሱም መካከል ገና የሚጠባበቅ አለ:: የገቡትን ቃል መለወጥንም አለወጡም::"},{"id":24,"translation":"24. አላህ እውነተኞችን በእውነተኛነታቸው ሊመነዳ፤ አስመሳዮችንም ቢፈልግ ሊቀጣ ወይም ቢመለሱ በእነርሱ ላይ ጸጸታቸቸውን ሊቀበል ይህን አደረገ:: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":25,"translation":"25. እነዚያንም በአላህ የካዱትን በቁጭታቸው የተሞሉ መልካምን ነገር ያላገኙ ሆነው አላህ መለሳቸው:: አማኞቹንም አላህ መጋደልን በቃቸው:: አላህም ብርቱና ሁሉን አሸናፊ ነውና::"},{"id":26,"translation":"26. እነዚያንም ከመጽሐፉ ባለቤቶች አህዛቦችን የረዷቸውን (ቁረይዟን) ከምሽጎቻቸው አወረዳቸው:: በልቦቻቸዉም ውስጥ መባባትን ጣለባቸው። ከፊሉን ትገድላላችሁ፤ ከፊሉንም ትማርካላችሁ::"},{"id":27,"translation":"27. ምድራቸውንም ቤቶቻቸውንም ገንዘቦቻቸውንም ገና ያልረገጣችኋትንም ምድር አወረሳችሁ:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::"},{"id":28,"translation":"28. አንተ ነብይ ሆይ! ለሚስቶችህ (እንዲህ) በላቸው: «ቅርቢቱን ህይወትና ጌጧን የምትፈልጉ እንደ ሆናችሁ ኑ:: አጣቅማችኋለሁና መልካምንም መፍታት እፈታችኋለሁና::"},{"id":29,"translation":"29. «አላህንና መልዕክተኛውን የመጨረሻይቱን አገርም የምትፈልጉ ከሆናችሁ እነሆ አላህ ከናንተ ለመልካም ሰሪዎቹ ትልቅን ምንዳ አዘጋጅቷል።»"},{"id":30,"translation":"30. እናንተ የነብዩ ሚስቶች ሆይ! ከናንተ ውስጥ ግልጽ የሆነን መጥፎ ስራ የምትሰራ ሴት ቅጣቷ ሁለት እጥፍ ሆኖ ይነባበርባታል:: ይህም በአላህ ዘንድ ገር ነው::"},{"id":31,"translation":"31. ከናንተም መካከል ለአላህና ለመልዕክተኛው የምትታዘዝ መልካም ስራንም የምትሰራ ሴት ምንዳዋን ሁለት ጊዜ እንሰጣታለን:: ለእርሷም የከበረን ሲሳይ አዘጋጅተንላታል።"},{"id":32,"translation":"32. እናንተ የነቢዩ ሚስቶች ሆይ! እንደ ማናቸዉም ሴቶች አይደላችሁም:: አላህን ብትፈሩ ትበልጣላችሁ። በልቡ ውስጥ በሽታ ያለበት እንዳይከጅል በንግግር እንኳን አትለስልሱም:: መልካምንም ንግግር ተናገሩ።"},{"id":33,"translation":"33. በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ:: እንደ ፊተኛይቱ መሃይምነት ጊዜ መገላለጥም (በመጌጥ) አትገለጡ:: ሶላትንም በደንቡ ስገዱ:: ዘካንም ስጡ:: አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ:: የነብዩ ቤተሰቦች ሆይ! አላህ የሚሻው ከናንተ ላይ ርክሰትን ሊያስወግድና ማጥራትንም ሊያጠራችሁ ብቻ ነው::"},{"id":34,"translation":"34. ከአላህ አናቅጽና ከጥበቡም በቤቶቻችሁ የሚነበበውን አስታውሱ:: አላህ እዝነቱ ረቂቅና ውስጠ አዋቂ ነውና::"},{"id":35,"translation":"35. ሙስሊም ወንዶችና ሙስሊም ሴቶች፤ ምእምናንና ምዕመናትም፤ ታዛዦች ወንዶችና ታዛዦች ሴቶችም፤ እውነተኞች ወንዶችና እውነተኞች ሴቶችም፤ ታጋሽ ወንዶችና ታጋሽ ሴቶችም፤ አላህን ፈሪ ወንዶችና አላህን ፈሪ ሴቶችም፤ መጽዋች ወንዶችና መጽዋች ሴቶችም፤ ጿሚ ወንዶችና ጿሚ ሴቶችም፤ ካልተፈቀደ ስራ ብልቶቻቸውን ጠባቂ ወንዶችና ጠባቂ ሴቶችም፤ አላህን በብዙ አውሺ ወንዶችና አውሺ ሴቶችም አላህ ለእነርሱ ምህረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል::"},{"id":36,"translation":"36. አላህና መልዕክተኛው በአንድ ነገር ላይ በወሰኑ ጊዜ ለምዕምናንና ለምዕመናት ከተነገራቸው ከመቀበል ዉጭ ምንም ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም:: የአላህንና የመልክተኛውን ትእዛዝ የጣሰ ሰው ሁሉ ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ::"},{"id":37,"translation":"37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለዚያም አላህ በእርሱ ላይ ለለገሰለትና አንተም (ነጻ በማውጣት) በእርሱ ላይ ለለገስክለት ሰው አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና አላህን ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ ሆነህ «ሚስትህን ያዝ:: አላህንም ፍራ» በምትል ጊዜ (የሆነዉን አስታውስ):: ዘይድም ከእርሷ ጉዳዩን በፈጸመ ጊዜ በምዕመኖች ላይ ልጅ አድርገው ባስጠጓቸው ሰዎች ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን በፈጸሙ ጊዜ በማግባት ችግር እንዳይደርስባቸው እርሷን አጋባንህ (ዳርንህ):: የአላህም ትእዛዝ ተፈጻሚ ነው::"},{"id":38,"translation":"38. በነብዩ ላይ አላህ ለእርሱ በፈረደው ነገር ምንም ችግር ሊኖርበት አይገባም:: በእነዚያ ከዚያ በፊት ባለፉት ነብያት አላህ ደነገገው። የአላህም ትእዛዝ የተፈረደ ፍርድ ነው::"},{"id":39,"translation":"39. ለእነዚያ የአላህን መልዕክቶች ለሚያደርሱና ለሚፈሩት ከአላህ በስተቀርም አንድንም ለማይፈሩት ተደነገገ። ተቆጣጣሪነትም በአላህ በቃ::"},{"id":40,"translation":"40. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንዱም ሰው አባት አይደለም:: ግን የአላህ መልዕክተኛና የነብያት መደምደሚያ ነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነው::"},{"id":41,"translation":"41. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብዙ ማውሳትን አውሱት::"},{"id":42,"translation":"42. በቀኑ መጀመሪያና መጨረሻም አጥሩት::"},{"id":43,"translation":"43. እርሱ ያ በእናንተ ላይ እዝነትን የሚያወርድ ነው:: መላእክቶችም እንደዚሁ ምህረትን የሚለምኑላችሁ ናቸው:: ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣችሁ ዘንድ (ያዝንላችኋል):: ለትክክለኛ አማኞችም በጣም አዛኝ ነው::"},{"id":44,"translation":"44. በሚገናኙበት ቀን መከባበሪያቸው ሰላም መባባል ነው:: ለእነርሱም የከበረን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል::"},{"id":45,"translation":"45. አንተ ነብይ ሆይ! እኛ መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ላክንህ::"},{"id":46,"translation":"46. ወደ አላህም በፈቃዱ ጠሪ፣ አብሪና ብርሃን አድርገን ላክንህ::"},{"id":47,"translation":"47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማኞችንም ከአላህ ዘንድ ለእነርሱ ታላቅ ችሮታ ያላቸው መሆኑን አብስራቸው::"},{"id":48,"translation":"48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያንና አስመሳዮችንም አትታዘዛቸው ማሰቃየታቸውንም (ለአላህ) ተው:: በአላህም ላይ ተጠጋ:: በመጠጊያነትም አላህ በቃ::"},{"id":49,"translation":"49. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ምዕመናትን ባገባችሁና ከዚያም ሳትነኳቸው በፊት በፈታችኋቸው ጊዜ ለናንተ በእነርሱ ላይ የምትቆጥሩዋት ዒዳ ምንም የላችሁም:: ሆኖም አጣቅሟቸው (ጉርሻ ስጧቸው):: መልካም ማሰናበትንም አሰናብቷቸው::"},{"id":50,"translation":"50. አንተ ነብይ ሆይ! እነዚያን መህሮቻቸውን የሰጠሃቸውን ሚስቶችህን፤ አላህ ባንተ ላይ ከመለሰልህም ሴቶች መካከል እነዚያን እጅህ የጨበጠቻቸውን ምርኮኞች ሴቶች፤ እነዚያን ካንተ ጋር የተሰደዱትን የአጎቶችህንና፤ የአክስቶችህን ሴት ልጆች (እንደዚሁም) የእናትህ ወንድም ሴት ልጆችና የእናትህ እህት ሴት ልጆች ማግባትን ላንተ ፈቅደንልሃል:: ማንኛዋም በአላህ ያመነች ሴት ራሷን ለነብዩ ብትሰጥ ነብዩ ሊያገባት የፈለገ እንደ ሆነ ከአማኞች ሌላ ላንተ ብቻ የተሰጠ መብት ሲሆን ፈቀድንልህ:: በአማኞች ላይ በሚስቶቻቸውና እጆቻቸው በጨበጧቸው ባሮች ነገር ግዴታ ያደረግንባቸውን በእርግጥ አውቀናል:: ባንተ ላይ ችግር እንዳይኖር ያለፉትን ፈቀድንልህ:: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":51,"translation":"51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል የምትፈልጋትን ታቆያለህ :: የምትፈልጋትንም ወደ አንተ ታስጠጋለህ:: በመፍታት ከአራቅሃትም የፈለግሃትን በመመለስ ብታስጠጋ ባንተ ላይ ኃጢአት የለብህም:: ይህ ዓይኖቻቸው ወደ መርጋት ወደ አለማዘናቸዉም ለሁሉም በሰጠሃቸው ነገር ወደ መውደዳቸዉም በጣም የቀረበ ነው:: አላህም በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ታጋሽ ነው::"},{"id":52,"translation":"52. ከእነዚህ በኋላ እጅህ ከጨበጠቻቸው ባሮች በስተቀር ሴቶች ላንተ አይፈቅዱልህም ከሚስቶችም መልካቸው ቢደንቅህም እንኳን በእነርሱ ልትለውጥ አይፈቀድልህም። አላህ በነገሩ ሁሉ ተጠባባቂ ነው::"},{"id":53,"translation":"53. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! መድረሱን የማትጠባበቁ ስትሆኑ ወደ ምግብ ካልተፈቀደላችሁ በስተቀር የነብዩን ቤቶች በምንም ጊዜ አትግቡ ግን በተጠራችሁ ጊዜ ግቡ በተመገባችሁም ጊዜ ወዲያውኑ ተበተኑ:: ለወግ የምትጫወቱ ሆናችሁም አትቆዩ:: ይሃችሁ ነብዩን በእርግጥ ያስቸግራል:: ከናንተም ያፍራል። ግን አላህ ከእውነት አያፍርም:: እቃንም ለመዋስ በጠየቃችኋቸው ጊዜ ከመጋረጃ ኋላ ሆናችሁ ጠይቋቸው። ይሃችሁ ለልቦቻችሁም ለልቦቻቸዉም የበለጠ ንጽህና ነው:: የአላህንም መልክተኛ ልታስቸግሩ ሚስቶቹንም ከእርሱ በኋላ ምንጊዜም ልታገቡ ለእናንተ አይገባችሁም። ይሃችሁ አላህ ዘንድ ከባድ ኃጢአት ነው::"},{"id":54,"translation":"54. ማንኛውንም ነገር ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት በእርሱ ይመነዳችኋል:: አላህ ነገሩን ሁሉ አዋቂ ነውና::"},{"id":55,"translation":"55. (የነብዩ ሚስቶች) በአባቶቻቸው፣ በወንዶች ልጆቻቸዉም፣ በወንድሞቻቸውም፣ በወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆችም፣ በእኅቶቻቸው ወንዶች ልጆችም፣ ምዕመናት በሆኑት በሴቶቻቸዉም በጨበጧቸዉም ባሮች (አጠገብ ቢገለጡ) በእነርሱ ላይ ምንም ኃጢአት የለባቸዉም:: (ሴቶች ሆይ!) (ታዘዙ):: አላህን ፍሩ:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነውና፡"},{"id":56,"translation":"56. አላህና መላዕክቱ በነብዩ (ሙሐመድ) ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ:: እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ:: የማክበርን ሰላምታንም ሰላም በሉ::"},{"id":57,"translation":"57. እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚያስከፉ በቅርቢቱ ዓለምም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም አላህ ረግሟቸዋል:: ለእነርሱም አዋራጅን ቅጣት ደግሶላቸዋል::"},{"id":58,"translation":"58. እነዚያም አማኞችና ምዕመናትን ባልሰሩት ነገር በመዝለፍ የሚያሰቃዩ ዕብለትንና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ::"},{"id":59,"translation":"59. አንተ ነብይ ሆይ ! ለሚስቶችህ ለሴቶች ልጆችህም ለትክክለኛ አማኞች ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው። ይህ እንዳይታወቁና በባለጌዎች እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው:: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":60,"translation":"60. አስመሳዮችና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ (የአመንዝራነት) በሽታ ያለባቸው በመዲናም ውስጥ (በወሬ) አሸባሪዎቹ ከዚህ ስራቸው ባይከለከሉ በእነርሱ ላይ በእርግጥ እንቀሰቅስሃለን ከዚያ በእርሷ ውስጥ ጥቂትን እንጂ አይጎራበቱህም::"},{"id":61,"translation":"61. የተረገሙ ሆነው እንጂ አይጎራበቱህም:: በየትም ስፍራ ቢገኙ ይያዛሉ:: መገደልንም ይገደላሉ::"},{"id":62,"translation":"62. እነዚህ ህጎች በእነዚያ ከዚህ በፊት ባለፉት ህዝቦች ላይ የደነገጋቸው የአላህ ድንጋጌ ናቸው:: ለአላህም ድንጋጌዎች ደግሞ ፈጽሞ መለወጥን አታገኝም::"},{"id":63,"translation":"63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰዎች ከሰዓቲቱ ይጠይቁሃል:: «እውቀቷ አላህ ዘንድ ብቻ ነው።» በላቸው:: የሚያሳውቅህም ምንድን ነው! ሰዓቲቱ በቅርብ ጊዜ ልትሆን ይከጀላል::"},{"id":64,"translation":"64. አላህ ከሓዲያንን በእርግጥ ረግሟቸዋል። ለነርሱም የተጋገመችን እሳት አዘጋጅቷል::"},{"id":65,"translation":"65. በእርሷ ውስጥ ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ወዳጅም ረዳትም አያገኙም::"},{"id":66,"translation":"66. ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ በሚገለባበጡ ቀን «ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ» እያሉ ይጸጸታሉ::"},{"id":67,"translation":"67. ይላሉም «ጌታችን ሆይ! እኛ ጌቶቻችንንና ታላላቆቻችንን ታዘዝን መንገዱንም አሳሳቱን።"},{"id":68,"translation":"68. «ጌታችን ሆይ! ከቅጣቱ እጥፍን ስጣቸው ታላቅን እርግማንም እርገማቸው::»"},{"id":69,"translation":"69. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደ እነዚያ ሙሳን እንዳሰቃዩት ሰዎች አትሁኑ ካሉትም ነገር ሁሉ አላህ አጠራው:: አላህም ዘንድ ባለሞገስ ነበር::"},{"id":70,"translation":"70. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ:: ትክክለኛን ንግግርም ተናገሩ::"},{"id":71,"translation":"71. ስራዎቻችሁን ለእናንተ ያበጅላችኋልና ኃጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምርላችኋል:: አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ በእርግጥ ታላቅን እድል አገኘ::"},{"id":72,"translation":"72. እኛ አደራን በሰማያት በምድር እና በተራራዎች ላይ አቀረብናት:: መሸከሟንም እንቢ አሉ ከእርሷም ፈሩ። ሰው ግን ተሸከማት እርሱ በጣም በደለኛና ተሳሳች ነውና::"},{"id":73,"translation":"73. ወንዶች አስመሳዮችንና ሴቶች አስመሳዮችን ወንዶች አጋሪዎችንና ሴቶች አጋሪዎችንም አላህ ሊቀጣ በምዕምናንና በምዕመናትም ላይ አላህ ንስሃን ሊቀበል (አደራዋን ሰው ተሸከማት):: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::"}]},{"id":34,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ምስጋና ሁሉ ለዚያ በሰማያትም ያለው በምድርም ያለው ሁሉ የእርሱ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው:: በመጨረሻይቱም ዓለም ምስጋና ሁሉ ለእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም ጥበበኛና ውስጠ አዋቂው ነው::"},{"id":2,"translation":"2. አላህ በምድር ውስጥ የሚገባውን ሁሉ ከእርሷ የሚወጣውንም ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷ ውስጥ የሚያርገውንም ሁሉ ያውቃል:: እርሱም አዛኝና መሃሪ ነው::"},{"id":3,"translation":"3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ የካዱትም ሰዎች «ሰዓቲቱ አትመጣብንም» አሉ፡ «ጉዳዩ እንዳሰባችሁት አይደለም። ሩቁን ሁሉ አዋቂ በሆነው ጌታዬ እምላለሁ:: በእርግጥ ትመጣባችኋለች:: የብናኝ ክብደት ያክል እንኳ በሰማያትና በምድር ውስጥ ከእሱ አይሰወርም አይርቅም:: ከዚህ ያነሰም ሆነ የበለጠ የለም በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢሆን እንጂ::» በላቸው"},{"id":4,"translation":"4. እነዚያን ያመኑትንና መልካም የሰሩትን ሊመነዳ ሰዓቲቱ ትመጣባችኋለች:: እነዚያ ለእነርሱ ምህረትና የከበረ ሲሳይ አለላቸው::"},{"id":5,"translation":"5. እነዚያም የሚያመልጡ መስሏቸው አናቅጻችንን ለማፍረስ የጣሩ እነዚያ ለእነርሱ ከመጥፎ ቅጣት የሆነ አሳማሚ ስቃይ አለባቸው::"},{"id":6,"translation":"6. እነዚያም እውቀትን የተሰጡት ያንን ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን እውነትና አሸናፊ ምስጉን ወደ ሆነው የአላህ መንገድ የሚመራ መሆኑን ያውቃሉ::"},{"id":7,"translation":"7. እነዚያም በአላህ የካዱት አሉ: «(ሙታችሁ) ሙሉ መበጣጠስን በተበጣጠሳችሁ ጊዜ በአዲስ መፈጠር ውስጥ ትሆናላችሁ ብሎ የሚነግራችሁን ሰው እናሳያችሁን?"},{"id":8,"translation":"8. «በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈን? ወይስ በእርሱ እብደት አለበት?» አሉ:: እንዳሉት አይደለም። እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት በእርሷ በቅጣት ውስጥ የሚሆኑና አሁንም በራቀ ስህተት ውስጥ ናቸው::"},{"id":9,"translation":"9. ከሰማይና ከምድር በፊታቸውና በኋላቸው ወደ አለው ሁሉ አይመለከቱምን? ብንሻ እኮ በእነርሱ ምድርን እንደረምስባቸዋለን :: ወይም በእነርሱ ላይ ከሰማይ ቁራጭን እንጥልባቸዋለን:: በዚህ ውስጥ ወደ ጌታው ተመላሽ ለሆነ ባሪያ ሁሉ ታላቅ ምልክት አለበት፡"},{"id":10,"translation":"10. ለዳውድም ከእኛ የሆነን ችሮታ በእርግጥ ሰጠነው:: (አልንም) ተራራዎች ሆይ! ከእሱ ጋር ውዳሴን መላልሱ:: በራሪዎችንም (ገራንለት)። ብረትንም ለእሱ አለዘብንለት::"},{"id":11,"translation":"11. ሰፋፊዎችን ጥሩሮዎች ስራ:: በአሰራርዋም መጥን:: መልካምንም ስራ ስሩ:: እኔ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና (አልነው)::"},{"id":12,"translation":"12. ለሱለይማንም ንፋስን የቀትር በፊት ጉዞዋ የወር መንገድ፤ የቀትር በኋላ ጉዞዋም የወር መንገድ ሲሆን ገራንለት:: የነሀስንም ምንጭ ለእርሱ አፈሰስንለት:: ከአጋንንቶችም በጌታው ፈቃድ በፊቱ የሚሰሩትን (አደረግንለት):: ከእነርሱም ውስጥ ከትእዛዛችን ዝንፍ የሚል ከነዳጅ እሳት ቅጣት እናቀምሰዋለን::"},{"id":13,"translation":"13. ከምኩራቦች፤ ከምስሎችም እንደ ገንዳ ከሆነ ገበታዎችም፤ ከተደላደለ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሰሩለታል፣ (አልናቸዉም:) «የዳውድ ቤተሰቦች ሆይ! በጣም አመስጋኞች ሆናችሁ ለጌታችሁ ስሩ::» ከባሮቼ ውስጥ አመስጋኞቹ ጥቂቶች ናቸው::"},{"id":14,"translation":"14. በእርሱም ላይ ሞትን በፈጸምንበት ጊዜ መሞቱን ብትሩን የምትበላ ተንቀሳቃሽ ምስጥ እንጂ ሌላ አላመለከታቸዉም:: በወደቀ ጊዜም አጋንንቶች ሩቅን ሚስጥር የሚያውቁ በሆነ ኖሮ በአዋራጅ ስቃይ ውስጥ የማይቆዩ እንደነበሩ ተረዱ::"},{"id":15,"translation":"15. ለሰበእ ነገዶች በመኖሪያቸው በእውነት አስደናቂ ምልክት ነበራቸው:: ከግራና ከቀኝ ሁለት አትክልቶች ነበሯቸው:: «ከጌታችሁ ሲሳይ ብሉ ለእሱም አመስግኑ:: አገራችሁ ውብ አገር ናት:: ጌታችሁም መሃሪ ጌታ ነው» ተባሉ::"},{"id":16,"translation":"16. አላህን ከማመስገን ዞሩም:: በእነርሱም ላይ የግድቡን ጎርፍ ለቀቅንባቸው:: በሁለቱ አትክልቶቻቸዉም ሌሎች ሁለትን አትክልቶች ባለ መርጋጋ ፍሬዎችን ባለ ጠደቻና ከቁርቁራም ባለ ጥቂት ዛፎችን ለወጥናቸው::"},{"id":17,"translation":"17. በመካዳቸው ምክንያት ይህንን መነዳናቸው:: (እንደዚህ ያለውን ቅጣት) በጣም ከሓዲ ለሆነ ሰው ብቻ እንጂ ለሌላው እንሰጣለን?"},{"id":18,"translation":"18. በእነርሱና በዚያች በውስጧ በረከትን ባደረግንባት አገር (በሻም) መካከልም ተከታታይ መንደሮችን (ቅጥልጥል ከተሞች) አደረግን:: በእርሷም ጉዞን ወሰንን። «በሌሊቶችም ሆነ በቀኖች ዉስጥ ጸጥተኞች ሆናችሁ ተጓዙ» (አልን)::"},{"id":19,"translation":"19. «ጌታችን ሆይ! በጉዞዎቻችን መካከል አራርቅልን» አሉም:: ነፍሶቻቸውንም በደሉ:: መገረሚያ ወሬዎችም አደረግናቸው:: መበታተንንም ሁሉ በታተንናቸው:: በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለሆነ ሁሉ ብዙ መገለጫዎች አሉበት::"},{"id":20,"translation":"20. ዲያብሎስም በእነርሱ ላይ ምኞቱን በእርግጥ ፈጸመ:: እናም ከአመኑት የሆኑት ቡድኖች በስተቀር ተከተሉት::"},{"id":21,"translation":"21. በመጨረሻይቱም ዓለም የሚያምነውን ከዚያ እርሱ ከእርሷ በመጠራጠር ውስጥ ከሆነው ሰው ለይተን እንድናውቅ እንጂ በእነርሱ ላይ ለእርሱ ምንም ስልጣን አልነበረዉም:: ጌታህም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው::"},{"id":22,"translation":"22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ከአላህ ሌላ አማልክት ብላችሁ የምታስቧቸውን ጥሩ:: በሰማያትም ሆነ በምድር ውስጥ የብናኝ ክብደት ያህል እንኳ ምንም አይችሉም:: ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸዉም:: ከእነርሱም ለእርሱ ምንም አጋዥ የለዉም።» በላቸው::"},{"id":23,"translation":"23. ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም:: ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጠ ጊዜ ተማላጆቹ «ጌታችሁ ምን አለ?» ይላሉ:: አማላጆቹም: «እውነትን አለ። እርሱም ከፍተኛውና ታላቁ ጌታ ነው።» ይላሉ::"},{"id":24,"translation":"24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ)፤ «ከሰማያትና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው?» በላቸው። «አላህ ነው እኛ ወይም እናንተ በትክክለኛው መንገድ ላይ ወይም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነን።» በላቸው።"},{"id":25,"translation":"25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ !)«ካጠፋነው ጥፋት አትጠየቁም:: ከምትሰሩትም ስራ አንጠየቅም።» በላቸው::"},{"id":26,"translation":"26.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል። ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል:: እርሱም በትክክል ፈራጁና አዋቂው ነው።» በላቸው።"},{"id":27,"translation":"27.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ተጋሪዎች አድርጋችሁ በእሱ ያስጠጋችኋቸውን ጣዖታት እስቲ አሳዩኝ:: ተው አታጋሩ:: በእውነት እርሱ አሸናፊዉና ጥበበኛው አላህ ነው።» በላቸው::"},{"id":28,"translation":"28. አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጂ አልላክንህም:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::"},{"id":29,"translation":"29. «እውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ::"},{"id":30,"translation":"30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለእናንተ ከእርሱ አንዳችንም ሰዓት የማትዘገዩበት የማትቀድሙበትም የቀጠሮ ቀን አላችሁ።» በላቸው::"},{"id":31,"translation":"31. እነዚያም የካዱት «በዚህ ቁርኣንና በዚያ ከበፊቱ ባለዉም መጽሐፍ በጭራሽ አናምንም።» አሉ:: በዳዮችም ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ንግግርን የሚመላላሱ ሆነው በጌታቸው ዘንድ በሚቆሙ ጊዜ ብታይ ኖሮ አስደናቂን ነገር ታይ ነበር:: እነዚያ የተዋረዱት ለእነዚያ ለኮሩት «እናንተ ባልነበራችሁ ኖሮ ትክክለኛ አማኞች በሆንን ነበር።» ይላሉ::"},{"id":32,"translation":"32. እነዚያ የኮሩት ለእነዚያ ለተዋረዱት «ትክክለኛው እምነት ከመጣላችሁ በኋላ እኛ ከለከልናችሁን? አይደለም:: እናንተው ከሓዲያን ነበራችሁ።» ይሏቸዋል።"},{"id":33,"translation":"33. እነዚያም የተዋረዱት ለእነዚያ ለኮሩት «አይደለም። በአላህ እንድንክድና ለእርሱ ባላንጣዎችን እንድናደርግ ስታዙን (የከለከለን) የሌሊትና የቀን ዱለታችሁ ነው።» ይላሉ:: ቅጣትንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይደብቃሉ:: በእነዚያም በካዱት አንገቶች ላይ እንዛዝሎችን እናደርጋለን:: ይሰሩት የነበሩትን እንጂ ሌላን ይመነዳሉን?"},{"id":34,"translation":"34. በየትኛዋም ከተማ አስፈራሪን አላክንም ነዋሪዎችዋ «እኛ በተላካችሁት ከሓዲያን ነን።» ያሉ ቢሆኑ እንጂ::"},{"id":35,"translation":"35. «እኛም በገንዘቦችና በልጆች ይበልጥ የበዛን ነን:: እኛም የምንቀጣ አይደለንም» አሉ::"},{"id":36,"translation":"36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ሁሉ ያሰፋል:: ለሚሻው ሰዉም ሁሉ ያጠባል:: ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች ይህን አያውቁም።» በላቸው።"},{"id":37,"translation":"37. ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁም ያች እኛ ዘንድ መቅረብን የምታቀርባችሁ አይደለችም:: ያ በትክክል ያመነና መልካምን የሰራ ብቻ ሲቀር:: እነዚያ ለእነርሱ በሰሩት መልካም ስራ እጥፍ ምንዳ አለላቸው:: እነርሱም በገነት ሰገነቶች ውስጥ ጸጥተኞች ናቸው።"},{"id":38,"translation":"38. እነዚያም የሚያቅቱ መስሏቸው አናቅጻችንን ለማበላሸት የሚጥሩ ሁሉ እነዚያ በቅጣት ውስጥ የሚጣዱ ናቸው::"},{"id":39,"translation":"39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ ሲሳይን ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ያሰፋል:: ለእርሱም ያጠባል:: ከማንኛዉም ነገር የምትለግሱትን እርሱ ይተካዋል:: እርሱም ከሲሳይ ሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው።» በላቸው።"},{"id":40,"translation":"40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሁሉንም በሚሰበስባቸውና ከዚያም ለመላእክቶቹ «እነዚህ እናንተን ይገዙ ነበሩን?» በሚላቸው ቀን የሚሆነውን አስታውስ::"},{"id":41,"translation":"41. መላእክቶቹም «ጥራት ይገባህ ረዳታችን ከእነርሱ ሌላ የሆንከው አንተው ብቻ ነህ:: እንደሚሉት አይደለም:: ይልቁንም አጋንንትን ይገዙ ነበሩ:: አብዛኞቻቸው በእነርሱ አማኞች ናቸው።» ይላሉ።"},{"id":42,"translation":"42. ዛሬም ከፊላችሁ ለከፊሉ መጥቀምንም ሆነ መጉዳትን አይችሉም:: ለእነዚያም ለበደሉት ሰዎች «ያችን በእርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁትን የእሳት ቅጣት ቅመሱ» እንላቸዋለን::"},{"id":43,"translation":"43. በእነርሱም ላይ አናቅጻችን ግልጽ ሆነው በተነበቡላቸው ጊዜ «ይህ አባቶቻችሁ ይገዙት ከነበሩት ነገር ሊከለክላችሁ የሚፈልግ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ:: «ይህም ቁርዓን የተቀጣጠፈ ውሸት ነው እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉም። እነዚያም በአላህ የካዱት እውነትን በመጣላቸው ጊዜ «ግልጥ ድግምት ነው እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ።"},{"id":44,"translation":"44. የሚያጠኗቸው የሆኑ መጽሐፎችንም ምንም አልሰጠናቸዉም:: ካንተ በፊትም አስፈራሪ ነብይን ወደ እነርሱ አልላክንም::"},{"id":45,"translation":"45. እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል:: የሰጠናቸውንም ከአስር አንዱን እንኳን እነዚህ አልደረሱም:: እናም መልዕክተኞቼን አስተባበሉ:: ነቀፍኳቸዉም:: መንቀፌም እንዴት ነበር::"},{"id":46,"translation":"46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የምገስጻችሁ በአንዲት ነገር ብቻ ነው:: እርሷም ሁለት ሁለት፤ አንድ አንድም ሆናችሁ ለአላህ እንድትነሱና ከዚያም በጓደኛችሁ (በሙሐመድ) ምንም እብደት የሌለበት መሆኑን መርምራችሁ እንድትረዱ ነው:: እርሱ ለእናንተ ከብርቱ ቅጣት በስተፊት አስጠንቃቂ ነው እንጂ ሌላ አይደለም።» በላቸው።"},{"id":47,"translation":"47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከዋጋ ማንኛውንም የጠየቅኋችሁ ቢኖር እርሱ ለእናንተው ነው:: ዋጋዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ ነው።» በላቸው።"},{"id":48,"translation":"48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ እውነትን ብቻ ያወርዳል:: ሩቅ የሆኑትን ምስጢሮች ሁሉ አዋቂ ነው።» በላቸው።"},{"id":49,"translation":"49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እውነቱ መጣ ውሸት መነሻም መድረሻም የለዉምና ተወገደ።» በላቸው።"},{"id":50,"translation":"50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ብሳሳትም የምሳሳተው በራሴ ላይ ብቻ ነው:: ብመራም ጌታዬ ወደ እኔ በሚያወርደው መመሪያ መሰረት ነው:: እርሱ ሁሉ ሰሚና ለሁሉም ቅርብ ነውና።» በላቸው::"},{"id":51,"translation":"51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በደነገጡና ማምለጫ በሌላቸው ጊዜ ከቅርብ ስፍራም በተያዙ ጊዜ ሁኔታቸውን ብታይ ኖሮ (አስደናቂን ነገር ባየህ ነበር)::"},{"id":52,"translation":"52. «በእርሱም አሁን አመንን።» ይላሉ:: ለእነርሱም ከሩቅ ስፍራ እምነትን በቀላሉ ማግኘት ከየታቸው ይታደሉና?"},{"id":53,"translation":"53. በፊትም በእርሱ በእርግጥ ክደዋል:: ከሩቅ ስፍራም በግምት ንግግርን ይጥላሉ::"},{"id":54,"translation":"54. ከዚህ ቀደም በመሰሎቻቸው እንደተሰራዉም ብጤ በእነርሱና በሚፈልጉት መካከል ተጋረደ:: እነርሱ በእርግጥ በአወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ነበሩና::"}]},{"id":35,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ምስጋና ሁሉ ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ፤ መላእክትንም ባለ ሁለት ሁለት፤ ባለ ሶስት ሶስትና ባለ አራት አራት ክንፎች የሆኑ መላዕክተኞች አድራጊ ለሆነው አላህ ይገባው:: በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና።"},{"id":2,"translation":"2. አላህ ለሰዎች ከችሮታ የሚከፍታትን ለእርሷ ምንም አጋጅ የላትም:: የሚያግደዉም ከእርሱ በኋላ ለእርሱ ምንም ለቃቂ የለዉም:: እርሱ ብቸኛ አሸናፊና ጥበበኛ ው ነውና።"},{"id":3,"translation":"3. እናንተ ሰዎች ሆይ! በእናንተ ላይ (ያለውን) የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ ከአላህ ሌላ ፈጣሪ አለን? ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣችሁ አለን? ከእርሱ በስተቀር አምላክ (ሰጪም) የለም፡፡ ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ፡፡"},{"id":4,"translation":"4. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ካንተ በፊት የነበሩ ነብያትም ህዝቦቻቸው አስተባብለዋቸዋል:: የሁሉ ነገር መመለሻ ወደ አላህ ብቻ ነው::"},{"id":5,"translation":"5. (እናንተ ሰዎች ሆይ!) የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው:: እናም የቅርቢቱም ህይወት አታታላችሁ:: አታላዩም (ሰይጣን) በአላህ ላይ አያታላችሁ::"},{"id":6,"translation":"6. ሰይጣን ለእናንተ የለየለት ጠላት ነውና ስለዚህ እሱን ጠላት አድርጋችሁ ያዙት:: ሰይጣን ተከታዮቹን የሚጠራው ከእሳት ጓዶች እንዲሆኑ ብቻ ነው::"},{"id":7,"translation":"7. እነዚያ በአላህ የካዱት ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው:: እነዚያም በአላህ ያመኑትና በጎ ስራዎችንም የሰሩት ሁሉ ለእነርሱ በአላህ ዘንድ ምህረትና ታላቅ ምንዳ አለላቸው።"},{"id":8,"translation":"8. መጥፎ ሥራው የተሸለመለትና መልካም አድርጎ ያየው ሰው (አላህ እንዳቀናው ሰው ነውን?) አላህም የሚሻውን ሰው ያጠምማል፡፡ የሚሻውንም ያቀናል፡፡ ስለዚህ በእነርሱ ላይ (ባለመቅናታቸው) ስለመቆላጨት ነፍስህ አትጥፋ፡፡ አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡"},{"id":9,"translation":"9. አላህም ያ ንፋሶችን የላከ ነው:: ከዚያም ዳመናዎችን ትቀሰቅሳለች። ወደ ሙት (ድርቅ) አገርም እንነዳዋለን:: በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው እናደርጋታለን:: ሙታንንም መቀስቀስ ልክ እነደዚሁ ነው::"},{"id":10,"translation":"10. ማሸነፍን የሚፈልግ ሰው አሸናፊነት ለአላህ ብቻ ነው። (እርሱን በመገዛት ይፈልገው):: መልካም ንግግር ወደ እርሱ (ወደ አላህ) ይወጣል:: በጎ ስራም ከፍ ያደርገዋል:: እነዚያ መጥፎ ስራዎችን የሚዶልቱ ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው :: የእነዚያም ተንኮል እርሱ ይጠፋል::"},{"id":11,"translation":"11. አላህም ከአፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ፈጠራችሁ:: ከዚያም ዓይነቶች አደረጋችሁ:: የትኛዋም ሴት አታረግዝም አትወልድምም በእውቀቱ ቢሆን አንጂ:: እድሜው ከሚረዝምለትም አንድም አይረዘምለትም ከእድሜዉም አይጎድልበትም በመጽሀፉ ውስጥ ያለ ቢሆን እንጂ:: ይህ በአላህ ላይ ገር ነው::"},{"id":12,"translation":"12. ሁለቱ ባህሮች አይስተካከሉም ይህ ጣፋጭ፤ ጥምን ቆራጭ መጠጡ በገር ተዋጭ ነው:: ይህኛው ደግሞ ጨው መርጋጋ ነው:: ከሁሉም እርጥብ ስጋን ትበላላችሁ:: የምትለብሷትንም ጌጥ ታወጣላችሁ። ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑትም መርከቦችን በእርሱ ውስጥ ውሃውን ቀዳጆች ሆነው ሲንሻለሉ ታያለህ::"},{"id":13,"translation":"13. ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል:: ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል:: ጸሀይንና ጨረቃንም ገራ:: ሁሉም እስከ ተወሰነለት ጊዜ ድረስ ይሮጣል :: ይህን የሚያደርገው ጌታችሁ አላህ ብቻ ነው :: ንግስናው የእሱ ብቻ ነው:: እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን ያህል እንኳን አይኖራቸዉም::"},{"id":14,"translation":"14. ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም:: ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም:: በትንሳኤም ቀን እነርሱን በአላህ ማጋራታችሁን ይክዳሉ። እንደ ውስጠ አዋቂው አላህ ማንም አይነግርህም::"},{"id":15,"translation":"15. እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ ሁል ጊዜ ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ:: አላህም እርሱ ተብቃቂውና ምስጉኑ ነው::"},{"id":16,"translation":"16. (አላህ) ቢሻ ያስወግዳችሁና አዲስን ፍጡር ያመጣል (ይፈጥራል)::"},{"id":17,"translation":"17. ይህም በአላህ ላይ ምንም አስቸጋሪ አይደለም::"},{"id":18,"translation":"18. ኃጢአትን ተሸካሚም ነፍስ የሌላውን ሸክም አትሸከምም:: የራሷ ወንጀል የከበዳትም ነፍስ እርዳታ እንዲደረግላት ብትጠራ ተጠሪው የቅርብ ዝምድና ባለቤት ቢሆንም እንኳን ከእርሷ አንድን ነገር የሚሸከምላት አታገኝም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምታስጠነቅቀው እነዚያን ጌታቸውን፤ በሩቅ የሚፈሩትን ሶላትንም አስተካክለው የሚሰገዱትን ብቻ ነው:: ከወንጀልም የተጥራራ ሁሉ የሚጥራራው ለራሱ ብቻ ነው:: መመለሻዉም ወደ አላህ ብቻ ነው::"},{"id":19,"translation":"19. እውርና የሚያይ አይሰተካከሉም፤"},{"id":20,"translation":"20. ጨለማዎችና ብርሃንም፤"},{"id":21,"translation":"21. ጥላና ሐሩርም።"},{"id":22,"translation":"22. ህያውና ሙታንም አይስተካከሉም:: አላህ የሚሻውን ሰው ያሰማል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ግን በመቃብር ውስጥ ያሉትን አሰሚ አይደለህም::"},{"id":23,"translation":"23. አንተ አስጠንቃቂ እንጂ ሌላ አይደለህም::"},{"id":24,"translation":"24. እኛ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን በእውነቱ መምሪያ ላክንህ:: ማንኛይቱም ህዝብ በውስጧ አስፈራሪ ያላለፈባት የለችም::"},{"id":25,"translation":"25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ከእነዚህ ከበፊታቸው የነበሩትም ህዝቦች በእርግጥ ነብያትን አስተባብለዋል:: መልዕክተኞቻቸው በግልጽ ማስረጃዎች፣ በጹሁፎችም አብራሪ በሆነ መጽሐፍም መጥተዋቸዋል::"},{"id":26,"translation":"26. ከዚያም እነዚያን የካዱትን ቀጣኋቸው:: ቅጣቴም እንዴት ነበር! (በስፍራው ነው ተገቢ ነው)።"},{"id":27,"translation":"27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ከሰማይ ውሃን ማውረዱን አላየህምን? በእርሱም ዓይነቶቻቸው የተለያዩ ፍሬዎችን አወጣን:: ከጋራዎችም መልካቸው የተለያዩ ነጮችም፤ ቀዮችም፤ በጣም ጥቁሮችም የሆኑ መንገዶች አሉ።"},{"id":28,"translation":"28. ከሰዎችም፤ ከተንቀሳቃሾችም፤ ከቤት እንስሳዎችም እንደዚሁ መልኮቻቸው የተለያዩ አሉ:: አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት አዋቂዎቹ ብቻ ናቸው:: አላህ አሸናፊና መሃሪ ነው::"},{"id":29,"translation":"29. እነዚያ የአላህን መጽሐፍ የሚያነቡ፣ ሶላትን አስተካክለው የሰገዱ፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ በምስጢርም ሆነ በግልጽ የለገሱ የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ::"},{"id":30,"translation":"30. ምንዳዎቻቸውን ሊሞላላቸው ከችሮታዉም ሊጨምርላቸው ተስፋ ያደርጋሉ:: እርሱ በጣም መሃሪና አመስጋኝ ነውና::"},{"id":31,"translation":"31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ ከመጽሐፉ ወደ አንተ ያወረድነው ከበፊቱ ላለው አረጋጋጭ ሲሆን እርሱ እውነት ነው:: አላህ በእርግጥ በባሮቹ ውስጥ አዋቂና ተመልካች ነው::"},{"id":32,"translation":"32. ከዚያ እነዚያ ከባሮቻችን የመረጥናቸውን መጽሐፉን አወረስናቸው :: ከእነርሱም ነፍሱን በዳይ አለ:: ከእነርሱም መካከለኛ አለ:: ከእነርሱም በአላህ ፈቃድ በበጎ ስራዎች ቀዳሚ አለ:: ያንኑ ማውረስ እርሱ ታላቅ ችሮታ ነው::"},{"id":33,"translation":"33. የመኖሪያ ገነቶችን በውስጧ የወርቅ አንባሮችን ሉልንም የሚሸለሙ ሆነው ይገቡበታል:: በእርሷ ውስጥ አልባሳታቸዉም ሀር ነው::"},{"id":34,"translation":"34. ይላሉም «ምስጋና ሁሉ ለዚያ ከእኛ ላይ ሐዘንን ላስወገደልን ይገባው። ጌታችን በጣም መሃሪና አመስጋኝ ነውና።"},{"id":35,"translation":"35. እርሱም ያ ከችሮታው የዘላለም መኖሪያን አገር ያሰፈረን ነው:: በእርሷም ውስጥ መከራ አይነካንም:: በእርሷም ውስጥ ድካም አይነካንም::"},{"id":36,"translation":"36. እነዚያ በአላህ የካዱት ለእነርሱ የገሀነም እሳት አለላቸው:: ይሞቱ ዘንድም በእነርሱ ላይ ሞት አይፈረድም:: ከቅጣቷም ከእነርሱ አይቀለልላቸዉም:: ልክ እንደዚሁ ከሓዲያንን ሁሉ እንመነዳለን::"},{"id":37,"translation":"37. እነርሱም በእርሷ ውስጥ እርዳታን በመፈለግ በኃይል ይጮሃሉ:: «ጌታችን ሆይ! ከእዚያ እንሠራው ከነበርነው ሌላ በጎ ሥራን እንሠራ ዘንድ አውጣን» (ይላሉ)፡፡ «በእርሱ ውስጥ ያስታወሰ ሰው የሚገሰጽበትን እድሜ አላቆየናችሁምን? አስጠንቃቂዉም መጥቶላችኋል:: አስተባብላችኋልም:: ስለዚህ ቅመሱ:: ለበደለኞችም ምንም ረዳት የላቸዉም» ይባላሉ::"},{"id":38,"translation":"38. አላህ የሰማያትንና የምድርን ምስጢር በእርግጥ አዋቂ ነው:: እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ እንኳ አዋቂ ነውና::"},{"id":39,"translation":"39. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ በምድር ውስጥ ምትኮች ያደረጋችሁ ነው:: የካደም ክህደቱ በእርሱው ላይ ብቻ ነው:: ከሓዲያንም ክህደታቸው ከጌታቸው ዘንድ መጠላትን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸዉም:: ከሓዲያንም ክህደታቸው ክስረትን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸዉም::"},{"id":40,"translation":"40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን ተጋሪዎቻችሁ አያችሁን? ከምድር ምንን እንደ ፈጠሩ አሳዩኝ? ወይስ ለእነርሱ በሰማያት ውስጥ ሽርክና አላቸውን? ወይስ ለእነርሱ መፅሀፍ ሰጠናቸውና ከእርሱ በግልፅ አስረጂ ላይ ናቸውን? አይደለም በደለኞች ከፊላቸው ከፊሉን ማታለልን እንጂ አይቀጥሩም» በላቸው::"},{"id":41,"translation":"41. አላህ ሰማያትንና ምድርን እንዳይወገዱ ይይዛቸዋል:: ቢወገዱም ከእርሱ ሌላ አንድም የሚይዛቸው የለም:: እነሆ እርሱ ታጋሽና መሃሪ ነውና::"},{"id":42,"translation":"42. አስፈራሪም ቢመጣላቸው ከህዝቦች ሁሉ ከአንደኛዋ ይበልጥ የተመሩ ሊሆኑ የመሃላቸውን ዲካ አድርሰው በአላህ ማሉ:: አስፈራሪም በመጣላቸው ጊዜ መበርገግን እንጂ ሌላ አልጨመረላቸዉም::"},{"id":43,"translation":"43. በምድር ላይ ኩራትንና በክፉ ተንኮል መዶለትንም እንጂ አልጨመረላቸዉም:: ክፉ ተንኮልም በባለቤቱ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይሰፍርም:: የቀድሞዎቹን ደንብ እንጂ ይጠብቃሉን? በመሆኑም ለአላህ ደንብ መለወጥን አታገኝም፤ ለአላህ ደንብም መዛወርን (መቀየር) አታገኝም።"},{"id":44,"translation":"44. በምድር ላይ አይሄዱምና የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ አይመለከቱምን? ከእነርሱም በኃይል የበረቱ ነበሩ:: አላህም በሰማያትም ሆነ በምድር ውስጥ ምንም ነገር የሚያቅተው አይደለም:: እርሱ ሁሉን አዋቂና በሁሉ ላይ ቻይ ነውና::"},{"id":45,"translation":"45. አላህ ሰዎችን በሰሩት ኃጢአት ሁሉ ቢቀጣ ኖሮ በምድር ወለል ላይ ምንንም ተንቀሳቃሽ ባልተወ ነበር:: ግን እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ያቆያቸዋል:: ጊዜያቸዉም በመጣ ወቅት በኃጢአታቸው ይቀጣቸዋል:: አላህ በባሮቹ ሁኔታ ሁሉ ተመልካች ነውና::"}]},{"id":36,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ያሲን::"},{"id":2,"translation":"2-ጥበብ በተሞላበት ቁርኣን እምላለሁ::"},{"id":3,"translation":"3.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞቹ መካከል አንዱ ነህ።"},{"id":4,"translation":"4. አንተ በእርግጥ በቀጥታው መንገድ ላይ ነህ ::"},{"id":5,"translation":"5.ቁርኣን አሸናፊውና አዛኙ ከሆነው አምላክ ከአላህ ተወረደ::"},{"id":6,"translation":"6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አባቶቻቸው ያልተስፈራሩትን ህዝቦች ልታስጠነቅቅበት ቁርኣን ተወረደ። እነርሱ ዘንጊዎች ናቸውና።"},{"id":7,"translation":"7. በአብዛኞቻቸቸው ላይ ቃሉ በእውነት ተረጋገጠ:: ስለዚህ እነርሱ አያምኑም::"},{"id":8,"translation":"8. እኛ በአንገቶቻቸው ላይ እንዛዝላዎችን አደረግን። (እንዛዝላይቱም) ወደ አገጮቻቸው ደራሽ ናት። እናም ከዚያም እነርሱ ራሶቻቸውን ያንጋጠጡ ናቸው።"},{"id":9,"translation":"9. ከበስተፊታቸዉም ግርዶን ከበስተኋላቸዉም ግርዶን አደረግንና ሸፈንናቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያዩም::"},{"id":10,"translation":"10. ብታስጠነቅቃቸዉም ባታስጠነቅቃቸዉም ለእነርሱ ሁሉም እኩል ነው:: (ምንም ለውጥ አያመጣም) አያምኑምና::"},{"id":11,"translation":"11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምታስጠነቅቀው ግሳጼን የተከተለንና አር-ረህማንን በሩቅ የፈራን ሰው ብቻ ነው:: እናም በምህረትና በመልካም ምንዳ አብስረው::"},{"id":12,"translation":"12. እኛ ሙታንን በእርግጥ ህያው እናደርጋለን:: ያስቀደሙትንም ስራ ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን:: ሁሉን ነገርም ገላጭና መሪ በሆነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው::"},{"id":13,"translation":"13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱም የከተማይቱን (የአንጾኪያን) ሰዎች ምሳሌ መልዕክተኞች በመጧት ጊዜ የሆነውን ግለጽላቸው።"},{"id":14,"translation":"14. ወደ እነርሱ ሁለትን ሰዎች በላክንና ባስተባበሉዋቸውም ጊዜ፤ በሶስተኛም ባበረታናቸውና «እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን» ባሏቸው ጊዜ የሆነውን ምሳሌ ግለጽላቸው።"},{"id":15,"translation":"15. «እናንተ መሰላችን ሰዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም:: አር-ረህማንም ምንንም ነገር አላወረደም:: እናንተ የምትዋሹ እንጂ ሌላ አይደላችሁም» አሏቸው።"},{"id":16,"translation":"16. መልዕክተኞቹም አሉ: «ጌታችን ያውቃል። እኛ ወደ እናንተ በእርግጥ መልክተኞች ነን።"},{"id":17,"translation":"17. «በእኛ ላይም ግልጽ የሆነ ማድረስ እንጂ ሌላ የለብንም።» አሉ።"},{"id":18,"translation":"18. ህዝቦቹም «እኛ በእናንተ ገደ ቢሶች ሆንን። ከዚህ ጥሪያችሁ ባትከለክሉም በእርግጥ እንወግራችኋለን:: ከእኛም አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ያገኛችኋል» አሉ።"},{"id":19,"translation":"19. «ገደ ቢስነታችሁ ከናንተው ጋር ነው:: ብትገሰጹ (ትዝታላችሁን?) በእውነቱ እናንተ ወሰን አላፊ ህዝቦች ናችሁ» አሏቸው።"},{"id":20,"translation":"20. ከከተማይቱም ሩቅ ዳርቻ የሚሮጥ ሰው መጣና (እንዲህ) አለ: «ወገኖቼ ሆይ! መልዕክተኞቹን ተከተሉ።"},{"id":21,"translation":"21. «እነርሱም ቅኑን መንገድ የተመሩ ሲሆኑ ክፍያን የማይጠይቋችሁን ሰዎች ተከተሉ።"},{"id":22,"translation":"22. «ያንንም የፈጠረኝንና ወደ እርሱም የምትመለሱበትን ጌታ የማልገዛበት ምን ምክንያት አለኝ?"},{"id":23,"translation":"23. «ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልራህማን ሊጎዳኝ ቢፈልግ ምልጃቸው ከእኔ (ለመመለስ) ምንም አትጠቅመኝም አያድኑኝምም።"},{"id":24,"translation":"24. «እኔ ያን ጊዜ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነኝ።"},{"id":25,"translation":"25. «እኔ በጌታችሁ አመንኩ። ስሙኝም።» አለ።"},{"id":26,"translation":"26. {1} «ገነትን ግባ» ተባለም። እርሱም አለ: «ወገኖቼ ቢያውቁ እመኛለሁ።","footnotes":"{1} ደብድበው ገደሉት ከሞተ በኋላ ጀነት ግባ ተባለ"},{"id":27,"translation":"27. «ጌታዬ ለእኔ ምህረት ያደረገልኝና ከተከበሩትም ያደረገኝ መሆኑን።» (ቢያውቁ ተመኘሁ)"},{"id":28,"translation":"28. ከእርሱም በኋላ በህዝቦቹ ላይ ልናጠፋቸው ሰራዊትን ከሰማይ አላወረድንም (በማንም) ላይ አውራጆችም አልነበርንም::"},{"id":29,"translation":"29. ቅጣታቸው አንዲት ጩኸት እንጂ ሌላ አልነበረችም:: ወዲያውኑም እነርሱ ጠፊዎች ሆኑ::"},{"id":30,"translation":"30. በባሮች ላይ ዋ ቁጭት! ከመልዕክተኛ አንድም አልመጣላቸዉም በእርሱ ያፌዙበት ቢሆን እንጂ፤"},{"id":31,"translation":"31. ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙዎችን ማጥፋታችንንና እነርሱ የማይመለሱ መሆናቸውን አላወቁምን?"},{"id":32,"translation":"32. ሁሉም እኛ ዘንድ (የሚሰበሰቡ) የሚቀረቡ እንጂ ሌላ አይደሉም::"},{"id":33,"translation":"33. የሞተችዉም ምድር ለእነርሱ ምልክት ናት:: ህያው አደረግናት:: ከእርሷ ፍሬን አወጣን፤ ከእሱም ይበላሉ::"},{"id":34,"translation":"34. በእርሷ ውስጥ ከዘምባባዎችና ከወይኖች የሆነ አትክልቶችን አደረግን:: በእርሷም ውስጥ ምንጮችን አፈለቅን::"},{"id":35,"translation":"35. ከፍሬዉና እጆቻቸው ከሰሩትም ይበሉ ዘንድ ይህን አደረግን:: አያመሰግኑምን?"},{"id":36,"translation":"36. ያ! ምድር ከምታበቅለው፤ ወንዴንና ሴቴን ከነፍሶቻቸዉም ከማያውቁትም ነገር (ዓይነቶችን) ሁሏንም የፈጠረ (አምላክ) ጥራት ይገባው::"},{"id":37,"translation":"37. ሌሊቱም ለእነርሱ ምልክት ነው:: ከእርሱ ላይ ቀንን አንገፋለን:: ወዲያውኑም እነርሱ በጨለማ ውስጥ ይገባሉ::"},{"id":38,"translation":"38. ጸሐይም ለእርሷ ወደ ሆነው መርጊያ ትሮጣለች:: ይህ የአሸናፊውና የአዋቂው አምላክ የአላህ ውሳኔ ነው::"},{"id":39,"translation":"39. ጨረቃንም የመስፈሪያዎች ባለቤት ሲሆን እንደ አሮጌ ዘንባባ ቀንዘል እስኪሆን ድረስ መሄዱን ለካነው::"},{"id":40,"translation":"40. ጸሐይ ጨረቃን ልትደርስበት አይገባትም:: ሌሊትም ቀንን ያለ ጊዜው ቀዳሚ አይሆንም:: ሁሉም በየመዞሪያቸው (በፈለክ) ውስጥ ይዋኛሉ::"},{"id":41,"translation":"41. እኛም የቀድሞ ትውልዳቸውን (አባቶቻቸውን) በተሞላች መርከብ ውስጥ የጫን መሆናችን ለእነርሱ ምልክት ነው::"},{"id":42,"translation":"42. ከመሰሉም በእርሱ የሚሳፈሩበትን ለእነርሱ ፈጠርንላቸው::"},{"id":43,"translation":"43. ስንፈልግ እናሰምጣቸዋለን:: ለእነርሱም ነፃ የሚያደርጋቸው ረዳት የላቸዉም:: እንዲድኑ የሚደረጉም አይደሉም።"},{"id":44,"translation":"44. እኛ ግን በችሮታችንና እስከ ጊዜ ሞታቸው ለማጣቀም አዳንናቸው::"},{"id":45,"translation":"45. ለእነርሱም «በስተፊታችሁና በኋላችሁ ያለውን ነገር ተጠንቀቁ፤ ይታዘንላችኋልና» በተባለ ጊዜ ፊታቸውን ያዞራሉ።"},{"id":46,"translation":"46. ከጌታቸውም ተዓምራት አንዲትም ተዓምር አትመጣላቸዉም ከእርሷ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጅ።"},{"id":47,"translation":"47. ለእነርሱም «አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ለግሱ» በተባሉ ጊዜ እነዚያ በአላህ የካዱት ለእነዚያ በአላህ ላመኑት «አላህ ቢሻ ኖሮ የሚያበላውን እናበላለን? እናንተ በግልጽ ስህተት ውስጥ እንጂ በሌላ ላይ አይደላችሁም።» ይላሉ።"},{"id":48,"translation":"48. «እውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ።"},{"id":49,"translation":"49. እነርሱ የሚከራከሩ ሲሆኑ በድንገት የምትይዛቸው የሆነችን አንዲትን ጩኸት እንጂ ሌላን አይጠባበቁም::"},{"id":50,"translation":"50. ያን ጊዜ መናዘዝን እንኳን አይችሉም:: ወደ ቤተሰቦቻቸዉም አይመለሱም::"},{"id":51,"translation":"51. በቀንዱም ይነፋል:: ወዲያውኑም እነርሱ ከየመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ::"},{"id":52,"translation":"52. «ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን መልዕክተኞቹም እውነቱን የነገሩን ነው።» ይላሉ።"},{"id":53,"translation":"53. እርሷ አንዲት ጩኸት እንጂ ሌላ አይደለችም:: ወዲያውኑም እነርሱ እኛ ዘንድ የሚሰበሰቡ የሚቀርቡ ናቸው::"},{"id":54,"translation":"54. ዛሬም ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም:: ትሰሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም (ይባላሉ።)"},{"id":55,"translation":"55. የገነት ሰዎች ዛሬ በእርግጥ በስራዎች ውስጥ ተደሳቾች ናቸው::"},{"id":56,"translation":"56. እነርሱም ሆኑ ሚስቶቻቸው በጥላዎች ውስጥ ናቸው:: ባለ አጎበር አልጋዎች ላይም ተደጋፊዎች ናቸው::"},{"id":57,"translation":"57. በውስጧ ለእነርሱ ፍራፍሬዎች አሏቸው:: ለእነርሱም የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው::"},{"id":58,"translation":"58. ለእነርሱም አዛኝ ከሆነው ጌታ በቃል ሰላምታ አለላቸው።"},{"id":59,"translation":"59. (አላህም ይላል): «እናንተ አመጸኞች ሆይ! ዛሬ ከትክክለኛ አማኞች ተለዩ።"},{"id":60,"translation":"60. «የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አትገዙ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደ እናንተ አላዘዝኩምን?"},{"id":61,"translation":"61. «ተገዙኝም ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው በማለትም::"},{"id":62,"translation":"62. «ከናንተም ብዙን ፍጡር በእርግጥ አሳስቷል:: የምታውቁም አልነበራችሁምን?"},{"id":63,"translation":"63. «ይህቺ ያቺ ትቀጠሯት የነበረችው ገሀነም ናት።"},{"id":64,"translation":"64. «ትክዱ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬዉኑ ግቧት።» (ይባላሉ።)"},{"id":65,"translation":"65. ዛሬ በአፎቻቸው ላይ እናትምና እጆቻቸው ያነጋግሩናል:: እግሮቻቸዉም ይሰሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ::"},{"id":66,"translation":"66. ብንፈልግ ኖሮ በዓይኖቻቸው ላይ በአበስን ነበር:: መንገድንም እንደ ልማዳቸው በተሸቀዳደሙ ነበር:: እንዴትስ ያያሉ?"},{"id":67,"translation":"67. ብንፈልግ ኖሮ በስፍራቸው ላይ እንዳሉ ወደ ሌላ ፍጥረት በለወጥናቸው ነበር:: ከዚያም መሄድንም ሆነ መመለስን ባልቻሉም ነበር::"},{"id":68,"translation":"68. እድሜውንም የምናረዝመውን በፍጥረቱ ወደ ደካማነት እንመልሰዋለን:: አያውቁምን?"},{"id":69,"translation":"69. (ሙሐመድን) ቅኔንም አላስተማርነዉም:: ለእርሱም አይገባዉም:: እርሱ (መጽሐፉ) መገሰጫና ገላጭ ቁርኣን አንጅ (ቅኔ አይደለም)::"},{"id":70,"translation":"70. ግሳጼነቱም ልቡ ህያው የሆነን ሰው ሊያስፈራራበትና ቃሉም በከሓዲያን ላይ ይፈጸም ዘንድ ነው::"},{"id":71,"translation":"71. እኛ እጆቻችን ከሰሩት ለእነርሱ እንሰሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ ባለ መብቶች ናቸው::"},{"id":72,"translation":"72. ለእነርሱም ገራናት:: ስለዚህ ከእርሷ ውስጥ የሚጋልቡት አለ:: ከእርሷም ይመገባሉ::"},{"id":73,"translation":"73. ለእነርሱም በእርሷ ውስጥ ሌሎች ጥቅሞችና መጠጦችም አሏቸው። ታዲያ አያመሰግኑምን?"},{"id":74,"translation":"74. መረዳትንም በመከጀል ከአላህ ሌላ አመለኩ።"},{"id":75,"translation":"75. ሊረዷቸውም አይችሉም። እነርሱም ለእርሳቸው ወደ እሳት የተቀረቡ ሰራዊት ናቸው::"},{"id":76,"translation":"76. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ንግግራቸዉም አያሳዝንህ:: እኛ የሚደብቁትንም የሚገልፁትንም እናውቃለንና::"},{"id":77,"translation":"77. ሰው እኛ ከፍትወት ጠብታ የፈጠርነው መሆናችንን አላወቀምን? ወዲያዉም እርሱ ትንሳኤን በመካድ ግልጽ ተከራካሪ ይሆናልን?"},{"id":78,"translation":"78. ለእኛም ምሳሌን አደረገልን:: መፈጠሩንም ረሳ:: «አጥንቶችን እነርሱ የበሰበሱ ሲሆኑ ህያው የሚያደርጋቸው ማነው?» አለ::"},{"id":79,"translation":"79. «ያ! በመጀመሪያ ጊዜ (ከኢምንት) ያስገኛት ጌታ እንደገና ህያው ያደረጋታል:: እርሱም በፍጡሩ ሁሉ ሁኔታ አዋቂ ነው።» በለው።"},{"id":80,"translation":"80. ያ! ለእናንተ ከእርጥብ ዛፍ እሳትን የፈጠረላችሁ ነው:: ወዲያውኑም እናንተ ከእርሱ ታቀጣጥላላችሁ::"},{"id":81,"translation":"81. ያ! ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ አይደለምን? እንዴታ ቻይ ነው እንጂ:: እርሱም በብዙ ፈጣሪውና እጅግ አዋቂው ነው።"},{"id":82,"translation":"82. ነገሩ አንድን ነገር በሻ ጊዜ ሁን ማለት ብቻ ነው:: ከዚያ ወዲያው ይሆናልም::"},{"id":83,"translation":"83. እናም ያ የነገሩ ሁሉ ስልጣን በእጁ የሆነው ጌታ ጥራት ይገባው:: ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::"}]},{"id":37,"verses":[{"id":1,"translation":"1. መሰለፍን በሚሰለፉት፤"},{"id":2,"translation":"2. (ደመና) መንዳትን በሚነዱት፤"},{"id":3,"translation":"3. ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ::"},{"id":4,"translation":"4. አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ብቻ ነው::"},{"id":5,"translation":"5. እርሱ ያ በሰማያትና በምድር በመካካለቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው:: የምስራቆችም ጌታ ነው::"},{"id":6,"translation":"6. እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት (አስዋብናት)::"},{"id":7,"translation":"7. አመጸኛ ከሆነ ሰይጣንም ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት::"},{"id":8,"translation":"8. ወደ ላይኛው ሰራዊት አያደምጡም፤ ከየአቅጣጫውም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፤ (ይቀጠቀጣሉ)።"},{"id":9,"translation":"9. የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፤ ለእነርሱም ዘውታሪ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":10,"translation":"10. ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውኑም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር (እርሱ ይሰማዋል)::"},{"id":11,"translation":"11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ ከእነርሱ በፊት የፈጠረነው ፍጡር? እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው::"},{"id":12,"translation":"12. ይልቁንም ማስተባበላቸው አስደነቀህ፤ በመደነቅህም ይሳለቃሉ::"},{"id":13,"translation":"13. በተገሰጹም ጊዜ አይገሰጹም::"},{"id":14,"translation":"14. ተዓምርንም ባዩ ጊዜ ለመሳለቅ ይጣጣራሉ።"},{"id":15,"translation":"15. አሉም: «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።"},{"id":16,"translation":"16. «በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በሆን ጊዜ የምንቀስቀስ ነን?"},{"id":17,"translation":"17. «የቀድሞዎቹ አባቶቻችንም እንደዚሁ ይቀሰቀሳሉን?» (ይላሉ።)"},{"id":18,"translation":"18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አዎን! እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)።» በላቸው።"},{"id":19,"translation":"19. እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት:: እነርሱም ወዲያውኑ ምን እንደሚፈጸምባቸው ያያሉ::"},{"id":20,"translation":"20. «ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው።» (ይላሉም)"},{"id":21,"translation":"21. «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉት የነበራችት መለያው ቀን ነው።» ይባላሉ።"},{"id":22,"translation":"22. (ለመላዕክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ከአላህ ሌላ ይገዟቸው የነበሩትንም ጣዖታት በአንድ ሰብስቡ።"},{"id":23,"translation":"23. ከአላህ ውጭ (ይገዟቸው የነበሩትን ሰብስቡ)። ከዚያም ወደ ገሀነም መንገድ ምሯቸው።"},{"id":24,"translation":"24. «እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና አቁሟቸዉም።» (ይባላል።)"},{"id":25,"translation":"25. ለነርሱም «ምን ሆናችሁ ነው የማትረዳዱት?» ይባላሉ።"},{"id":26,"translation":"26. በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ማምለጫ የሌላቸው ወራዳዎች ናቸው::"},{"id":27,"translation":"27. እርስ በራሳቸውም የሚወቃቀሱም ሆነው ይመጣሉ።"},{"id":28,"translation":"28. (ተከታዮቹ ለአስከታዮቻቸው) «እናንተ በጉልበት ትመጡብን ነበር» ይላሉ።"},{"id":29,"translation":"29. (አስከታዮቹም) ይላሉ፡- «አይደለም ፈጽሞ አማኞች አልነበራችሁም።"},{"id":30,"translation":"30. «ለእኛም በናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም። በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ህዝቦች ነበራችሁና ነው እንጂ።"},{"id":31,"translation":"31. «በእኛም ላይ የጌታችን ቃል የተረጋገጠብንና ሁላችንም ቅጣቱን ቀማሽ ነን።"},{"id":32,"translation":"32. «እኛ ጠማሞች ስለ ነበርን ወደ ጥመት ጠራናችሁም።» ይላሉ።"},{"id":33,"translation":"33. ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ተጋሪዎች ናቸው::"},{"id":34,"translation":"34. እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሰራለን።"},{"id":35,"translation":"35. እነርሱ «ከአላህ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም» በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ።"},{"id":36,"translation":"36. «እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን እንዴ?» ይሉ ነበር።"},{"id":37,"translation":"37. አይደለም እውነቱን ሃይማኖት አመጣ፤ መልዕክተኞቹንም እውነተኝነታቸውን አረጋገጠ።"},{"id":38,"translation":"38. እናንተ አሳማሚውን ቅጣት እርግጥ ቀማሾች ናችሁ::"},{"id":39,"translation":"39. ትሰሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም::"},{"id":40,"translation":"40. ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ቅጣትን አይቀምሱም::"},{"id":41,"translation":"41. እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አለላቸው::"},{"id":42,"translation":"42. ፍራፋሬዎች (አሉላቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው::"},{"id":43,"translation":"43. በድሎት ገነቶች ውስጥ::"},{"id":44,"translation":"44. ፊት ለፊት የሚተያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ ይንፈላሰሳሉ::"},{"id":45,"translation":"45. ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዙ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል::"},{"id":46,"translation":"46. ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከሆነች፤"},{"id":47,"translation":"47. በእርሷ ውስጥም የራስ ምታት የለባትም:: እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም::"},{"id":48,"translation":"48. እነርሱ ዘንድ ዓይናቸውን በባሎቻቸው ላይ ብቻ አሳጣሪዎች የሆኑ ዓይናማ ሴቶች አሉ::"},{"id":49,"translation":"49. እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) እንቁላል ይመስላሉ::"},{"id":50,"translation":"50. የሚጠያያቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ::"},{"id":51,"translation":"51. ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ (እንዲህ) ይላል: «እኔ ጓደኛ ነበረኝ።"},{"id":52,"translation":"52. (እንዲህ) የሚል: ‹በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን?"},{"id":53,"translation":"53. ‹በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆነ ጊዜ እኛ በእርግጥ እኛ እንመረመራለን?› የሚልም።"},{"id":54,"translation":"54. እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል::"},{"id":55,"translation":"55. ይመለከታልም በገሀነም መካከልም ጓደኛውን ያየዋል::"},{"id":56,"translation":"56. ይላል «በአላህ እምላለሁ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር።"},{"id":57,"translation":"57. «የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር።» (ይላል)"},{"id":58,"translation":"58. (የገነት ሰዎች ይላሉ)፡ «እኛ የምንሞት ሰዎች አይደለንምን?»"},{"id":59,"translation":"59. «የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር እኛም የምንቀጣ አይደለንም» ይላሉ።"},{"id":60,"translation":"60.ይህ ለገነት ሰዎች የተወሳው እርሱ በእርግጥ ታላቅ እድል ነው::"},{"id":61,"translation":"61. ለዚህ ብጤ ሰሪዎች ሁሉ ይስሩ::"},{"id":62,"translation":"62. በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ?"},{"id":63,"translation":"63. እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል።"},{"id":64,"translation":"64. እርሷ ከገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፤"},{"id":65,"translation":"65. እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል::"},{"id":66,"translation":"66. እነርሱ ከእርሷ በይዎች ናቸው:: ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው::"},{"id":67,"translation":"67. ከዚያ ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅልን መጠጥ አላቸው።"},{"id":68,"translation":"68. ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው::"},{"id":69,"translation":"69. እነርሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋል።"},{"id":70,"translation":"70. እነርሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና።"},{"id":71,"translation":"71. ከእነርሱም በፊት የነበሩት የቀድሞዎቹ ህዝቦች አብዛሀኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል::"},{"id":72,"translation":"72. በውስጣቸዉም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል::"},{"id":73,"translation":"73. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት!"},{"id":74,"translation":"74. ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ::"},{"id":75,"translation":"75. ኑህም በእርግጥ ጠራን:: ምንኛ ያማርን ምላሽ ሰጪ ነን?"},{"id":76,"translation":"76. እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን::"},{"id":77,"translation":"77. ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን::"},{"id":78,"translation":"78. በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካምን ዝና ተውን::"},{"id":79,"translation":"79. «በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑህ ላይ ይሁን።»"},{"id":80,"translation":"80. እኛ ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን::"},{"id":81,"translation":"81. እርሱ ከአማኞች ባሮቻችን ነውና::"},{"id":82,"translation":"82. ከዚያም ሌሎችን አሰመጥን::"},{"id":83,"translation":"83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) ኢብራሂምም በእርግጥ ከወገኖቹ አንዱ ነው።"},{"id":84,"translation":"84. ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ የሆነውን (አስታውስ)::"},{"id":85,"translation":"85. ለአባቱና ለህዝቦቹ ባለ ጊዜ: «ምንን ትገዛላችሁ?"},{"id":86,"translation":"86. «ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን?"},{"id":87,"translation":"87. «በዓለማቱ ጌታስ ሀሳባችሁ ምንድ ነው?።»"},{"id":88,"translation":"88. በከዋክብት መመልከትን ተመለከተ::"},{"id":89,"translation":"89. እኔ «በሽተኛ ነኝ» አለ።"},{"id":90,"translation":"90. እነርሱም ከእርሱ የሸሹ ሆነው ሄዱ።"},{"id":91,"translation":"91. ከዚያ እሱ ወደ አማልዕክቶቻቸው ተዘነበለ፤ (እንዲህ) አለም፡- «አትበሉም እንዴ?"},{"id":92,"translation":"92. «ምንም የማትናገሩበትስ ምን ምክኒያት አላችሁ?»"},{"id":93,"translation":"93. በቀኝ (እጁ) የሚመታቸዉም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ::"},{"id":94,"translation":"94. ወደ እርሱም ሰዎቹ እየሮጡ መጡ።"},{"id":95,"translation":"95. አለ: «የምትጠርቡትን ትገዛላችሁን?"},{"id":96,"translation":"96. «አላህ እናንተንም ሆነ የምትሰሩትን ሁሉ የፈጠረ ሲሆን» አላቸው።"},{"id":97,"translation":"97. «ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም።» አሉ።"},{"id":98,"translation":"98. ለእርሱ ተንኮልን አስቡ ወራዶችም አደረግናቸው።"},{"id":99,"translation":"99. አለም፡- «እኔ ወደ ጌታየ ሂያጅ ነኝ፤ በእርግጥ ይመራኛልና።"},{"id":100,"translation":"100. «ጌታየ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ።»"},{"id":101,"translation":"101. ታጋሽም በሆነ ልጅም አበሰርነው።"},{"id":102,"translation":"102. ከእርሱ ጋርም (ለስራ) በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በህልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፤ ተመልከትም፤ ምን ትላለህ?» አለው። «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ስራ፤ አላህ ቢሻ ከታጋሾች ሆኜ ታገኘኛለህ።» አለ።"},{"id":103,"translation":"103. ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)::"},{"id":104,"translation":"104. ጠራነዉም: «ኢብራሂም ሆይ!"},{"id":105,"translation":"105. «ራዕዩን በርግጥ እውን አደረግክ።» እኛ ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን።"},{"id":106,"translation":"106. ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው::"},{"id":107,"translation":"107. በታላቅ እርድም መስዕዋት ቤዛ አደረግንለት።"},{"id":108,"translation":"108. በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት::"},{"id":109,"translation":"109. ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን::"},{"id":110,"translation":"110. ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን::"},{"id":111,"translation":"111. እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው::"},{"id":112,"translation":"112. በኢስሐቅም አበሰርነው። ከመልካሞች የሆነ ነብይ ሲሆን::"},{"id":113,"translation":"113. በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን። ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሰሪ አለ:: ነፍሱን በግልጽ በዳይም አለ::"},{"id":114,"translation":"114. በሙሳና በሀሩን ላይ በእርግጥ ለገስን::"},{"id":115,"translation":"115. እነርሱንም ሆነ ህዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን::"},{"id":116,"translation":"116. ረዳናቸውናም እነርሱ አሸናፊዎቹ ሆኑ::"},{"id":117,"translation":"117. በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው::"},{"id":118,"translation":"118. ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው::"},{"id":119,"translation":"119. በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካምን ዝናን ተውንላቸው::"},{"id":120,"translation":"120. ሰላም በሙሳና በሀሩን ላይ ይሁን::"},{"id":121,"translation":"121. እኛ ልክ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን::"},{"id":122,"translation":"122. ሁለቱም በትክክል በአላህ ካመኑት ባሮቻችን ናቸው::"},{"id":123,"translation":"123. ኢልያስም በእርግጥ ከመልዕክተኞቹ ነው።"},{"id":124,"translation":"124. ለህዝቦቹም ባለ ጊዜ (አስታውስ) «አላህን አትፈሩምን?"},{"id":125,"translation":"125. «ስዕልን ትገዛላችሁ? ከስዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነዉም አምላክ ትተዋላችሁን?"},{"id":126,"translation":"126. «አላህ ጌታችሁና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁንም ጌታ ትተዋላችሁን?»"},{"id":127,"translation":"127. አስተባበሉትም ስለዚህ እነርሱ ለቅጣት የሚጣዱ ናቸው::"},{"id":128,"translation":"128. ንጹህ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ::"},{"id":129,"translation":"129. በእነርሱ ላይም በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት::"},{"id":130,"translation":"130. ሰላም በኢልያስ ላይ ይሁን፤"},{"id":131,"translation":"131. እኛ ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን::"},{"id":132,"translation":"132. እርሱ በእርግጥ ከምዕመናን ባሮቻችን ነው::"},{"id":133,"translation":"133. ሉጥም በእርግጥ ከመልዕክተኞቹ ነው::"},{"id":134,"translation":"134. እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳናቸው ጊዜ (የሆነዉን አስታውስ)::"},{"id":135,"translation":"135. በቅጣቱ ውስጥ ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር::"},{"id":136,"translation":"136. ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን::"},{"id":137,"translation":"137. (መኮች ሆይ)፤ እናንተም በእነርሱ መኖሪያዎች ላይ ያነጋችሁ ስትሆኑ ታልፋላችሁ።"},{"id":138,"translation":"138. በሌሊትም ታልፋላችሁ:: ልብ አታደርጉምን?"},{"id":139,"translation":"139. ዩኑስም በእርግጥ ከመልዕክተኞቹ ነው።"},{"id":140,"translation":"140. ወደ ተሞላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ አስታውስ::"},{"id":141,"translation":"141. እጣም ተጣጣለ፤ ከተሸነፉትም ሆነ::"},{"id":142,"translation":"142. እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳ ነባሪው ዋጠው::"},{"id":143,"translation":"143. እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነ ኖሮ"},{"id":144,"translation":"144. እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር::"},{"id":145,"translation":"145. እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው ባህር ዳርቻ ላይ ጣልነዉም::"},{"id":146,"translation":"146. በእርሱም ላይ በአጠገቡ ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን::"},{"id":147,"translation":"147. ወደ መቶ ሺህ ሰዎችም ላክነው፤ ከቶውንም ይጨምራሉ::"},{"id":148,"translation":"148. አመኑም። እስከ ጊዜው ድረስም አጣቀምናቸው::"},{"id":149,"translation":"149. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመካን ሰዎች ጠይቃቸዉም: «ለጌታህ ሴት ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራሉን?"},{"id":150,"translation":"150. «ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላዕክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን?»"},{"id":151,"translation":"151. አስተውሉ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው የተነሳ ይላሉ:"},{"id":152,"translation":"152.፡- «አላህ መላዕክትን ወለደ።» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው።"},{"id":153,"translation":"153. በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጠን?"},{"id":154,"translation":"154. ለእናንተ ምን አስረጂ አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ!"},{"id":155,"translation":"155. አትገነዘቡምን?"},{"id":156,"translation":"156. ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጂ አላችሁን?"},{"id":157,"translation":"157. «እውነተኞች እንደሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» በላቸው።"},{"id":158,"translation":"158. በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ:: አጋንንትም ሆኑ ይህን ባዩች በእሳት የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ አውቀዋል::"},{"id":159,"translation":"159. አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ::"},{"id":160,"translation":"160. ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች በአላህ ላይ አይዋሹም::"},{"id":161,"translation":"161. (ካሐዲያን ሆይ!) እናንተም የምትገዟቸዉም ሁሉ፤"},{"id":162,"translation":"162. በእርሱ በአላህ ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም"},{"id":163,"translation":"163. ያንን እርሱ ገሀነም ገቢ የሆነውን ቢሆን እንጂ (አጥማሚዎች አይደላችሁም)።"},{"id":164,"translation":"164. (መላእክቶችም አሉ)? «ከእኛ አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ።"},{"id":165,"translation":"165. «እኛም ጌታን ለመገዛት ተሰላፊዎቹ እኛ ነን።"},{"id":166,"translation":"166. «እኛም አላህን አጥሪዎቹ እኛው ነን።»"},{"id":167,"translation":"167. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ (ከሓዲያን) በእርግጥ ይሉ ነበር:"},{"id":168,"translation":"168. «ከቀድሞዎቹ መጽሐፍ ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረ ኖሮ"},{"id":169,"translation":"169. «የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር።»"},{"id":170,"translation":"170. ግን ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ በእርሱ ላይ ካዱ። ወደ ፊትም በእርግጥ ያውቃሉ::"},{"id":171,"translation":"171. የእርዳታ ቃላችንም መልዕክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች::"},{"id":172,"translation":"172. እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ብቻ ናቸው::"},{"id":173,"translation":"173. ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው::"},{"id":174,"translation":"174. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ከመካ ከሓዲያን እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር ተዋቸው::"},{"id":175,"translation":"175. ተመልከታቸዉም ወደፊትም የሚደርስባቸውን ያያሉ::"},{"id":176,"translation":"176. በቅጣታችንም ያቻኩሉናልን?"},{"id":177,"translation":"177. በቀያቸዉም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ!"},{"id":178,"translation":"178. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ተዋቸው::"},{"id":179,"translation":"179. ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ::"},{"id":180,"translation":"180. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ::"},{"id":181,"translation":"181. በመልዕክተኞቹም ላይ ሰላም ይሁን::"},{"id":182,"translation":"182. ምስጋና ሁሉም ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው::"}]},{"id":38,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ሷድ፤ የግሳፄ ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ።"},{"id":2,"translation":"2. ይልቁንም እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች በከባድ ትዕቢትና በአጓጉል ክርክር ውስጥ ናቸው።"},{"id":3,"translation":"3. ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙን አጥፍተናል:: ጊዜው የመሸሻና የማምለጫ ጊዜ ሳይሆንም (ለእርዳታ) ተጣሩ::"},{"id":4,"translation":"4. ከእነርሱ መካከል የሆነ አስፈራሪ ስለመጣላቸውም ተደነቁ:: ከሓዲያንም አሉ: «ይህ ድግምተኛ ጠንቋይ ውሸታም ነው።"},{"id":5,"translation":"5. «አማልዕክቶችን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው።» አሉ።"},{"id":6,"translation":"6. ከእነርሱም መካከል ባላባቶቹ (እንዲህ) እያሉ አዘገሙ: «ሂዱ በአማልክቶቻችሁም መገዛት ላይ ጽኑ:: ይህ ከእኛ የሚፈለግ ነገር ነውና"},{"id":7,"translation":"7. «ይህንንም አስተምህሮት ከኋለኛይቱ (ከመጨረሻይቱ) ሃይማኖት አልሰማንም:: ይህ ውሸትን መፍጠር እንጂ ሌላ አይደለም።"},{"id":8,"translation":"8. «ከመካከላችን በእርሱ ላይ ብቻ ቁርኣን ተወረደን?» (እያሉ አዘገሙ።) ይልቁን እነርሱ ከግሳጼየ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: በእርግጥም ቅጣትን ገና አልቀመሱም::"},{"id":9,"translation":"9. ወይስ የአሸናፊውና የለጋሹ ጌታህ የአላህ የችሮታው መካዚኖች እነርሱ ዘንድ ናቸውን?"},{"id":10,"translation":"10. ወይስ የሰማይ የምድር እና የመካከላቸዉም ንግስና የእነርሱ ነውን? (ነው ካሉ) እስቲ በመሰላሎች ወደ ላይ ይውጡ::"},{"id":11,"translation":"11. እነርሱም እዚያ ዘንድ ከአህዛብ ሁሉ ተሸናፊ የሆነ ሰራዊት ናቸው::"},{"id":12,"translation":"12. ከእነርሱም በፊት የኑህ ህዝቦች፤ ዓድ እና የችካሎች ባለቤት የሆነው ፈርዖንም አስተባብለዋል።"},{"id":13,"translation":"13. ሰሙድም፤ የሉጥ ሰዎችም፤ የአይካ ሰዎችም፤ አስተባበሉ:: እነዚህ አህዛቦቹ ናቸው::"},{"id":14,"translation":"14. ሁሉም መልዕክተኞችን ያስዋሹ እንጂ ሌላ አይደሉም:: ከዚያ ቅጣቴ ተረጋገጠባቸው::"},{"id":15,"translation":"15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ ያችን ለእርሷ መመለስ የሌላትን አንዲት ጩኸት ብቻ እንጂ ሌላን አይጠባበቁም::"},{"id":16,"translation":"16. (በመሳለቅም) «ጌታችን ሆይ! ከምርመራው ቀን በፊት ቅጣታችንን አጣድፍልን» አሉ።"},{"id":17,"translation":"17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሚሉት ነገር ላይ ታገስ:: የሃኃይል ባለቤት የሆነውን ባሪያችንንም ዳውድን አውሳው:: እርሱ በጣም መላሳ ነው::"},{"id":18,"translation":"18. እኛ ተራራዎችን ከቀትር በኋላና በረፋዱም ከእርሱ ጋር የሚያወድሱ ሲሆን እንዲታዘዙት አገራንለት::"},{"id":19,"translation":"19. በራሪዎችንም (አእዋፍን) የሚሰበሰቡ ሆነው አገራንለት:: ሁሉም ለእርሱ ማወደስ የሚመላለስ ነው::"},{"id":20,"translation":"20. ንግስናውንም አበረታንለት ጥበብንና ንግግርን መለየትንም ሰጠነው።"},{"id":21,"translation":"21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተከራካሪዎቹ ወሬ መጥቶልሃልን? እልፍኙን (ምኩራቡን) በተንጠላጠሉ ጊዜ።"},{"id":22,"translation":"22. በዳውድ ላይም በገቡ ጊዜ ከእነርሱም ሁኔታ በደነገጠ ጊዜ (እንዲህ) አሉት: «አትፍራ። እኛ ከፊላችን በከፊሉ ላይ ወሰን ያለፈ ሁለት ተከራካሪዎች ነን። በመካከላችንም በእውነት ፍረድ። አታዳላም። ወደ ትክክለኛው መንገድም ምራን።"},{"id":23,"translation":"23. «ይህ ወንድሜ ነው:: ለእርሱ ዘጠና ዘጠኝ ሴት በጎች አሉት ለእኔም አንዲት ሴት በግ አለችኝ ‹እርሷንም ለእኔ አድርጋት› አለኝ:: በንግግርም አሸነፈኝ።» አለው::"},{"id":24,"translation":"24. «ሴት በግህን ወደ በጎቹ ለመቀላቀል በመጠየቁ በእርግጥ በደለህ። ከተጋሪዎች ብዙዎቹ ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ወሰን ያልፋሉ:: እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩት ብቻ ሲቀሩ፤ እነርሱም በጣም ጥቂቶች ናቸው።» አለ:: ዳውድም የፈተንነው መሆኑን ወዲያዉኑ አወቀ:: ከጌታዉም ምህረትን ለመነና ሰጋጅ ሆኖም ወደቀ። በመጸጸትም ተመለሰ:: {1}","footnotes":"{1} እዚህ አንድ ሱጁድ ይደረጋል"},{"id":25,"translation":"25. ያንንም ማርነው። ለእርሱም እኛ ዘንድ የመቅረብ ክብር መልካም መመለሻም አለው።"},{"id":26,"translation":"26. (እኛም አልነው) «ዳውድ ሆይ! እኛ በምድር ላይ ምትክ አድርገንሀልና በሰዎች መካከል በእውነት ፍረድ:: የግል ዝንባሌህንም አትከተል:: ከአላህ መንገድ ያሳስተሃልና።» እነዚያ ከአላህ መንገድ የሚሳሳቱ ሁሉ የምርመራውን ቀን በመርሳታቸው ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":27,"translation":"27. ሰማይን ምድርና በመካከላቸዉም ያለውን ሁሉ ለከንቱ አልፈጠርንም:: ይህ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ጥርጣሬ ነው:: ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ሁሉ ከእሳት ወዮላቸው።"},{"id":28,"translation":"28. በእውነቱ እነዚያ ያመኑትና መልካም ተግባሮችን የሰሩትን ልክ በምድር ውስጥ እንደሚያጠፉት እናደርጋለንን? ወይስ አላህን ፈሪዎችን ልክ እንደ ከሓዲያን እናደርጋለን?"},{"id":29,"translation":"29. ይህ መጽሀፍ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሀፍ ነው:: አናቅጽን እንዲያስተነትኑና የአእምሮ ባላቤቶችም እንዲገሰጹበት አወረድነው::"},{"id":30,"translation":"30. ለዳውድም ሱለይማንን ሰጠነው:: ሱለይማን ምን ያምር ባሪያ ነው:: እርሱ ወደ ጌታው መላሳ ነውና::"},{"id":31,"translation":"31. በእርሱ ላይ ከቀትር በኋላ በሶስት እግሮችና በአራተኛው እግር ኮቴ ጫፍ የሚቆሙ ጮሌ ፈረሶች በተቀረቡለት ጊዜ (የሆነዉን አስታውስ)::"},{"id":32,"translation":"32. (እንዲህም) አለ: «ጸሀይ በግርዶ እስከተደበቀች ድረስ ጌታየን ከማስታወስ ፈንታ ፈረስን መውደድን መረጥኩ!"},{"id":33,"translation":"33. «በሉ ፈረሶችን ወደ እኔ መልሷቸው።» (አለ)። ከዚያም እግሮቻቸዉንና አንገቶቻቸዉን መቁረጥ ያዘ::"},{"id":34,"translation":"34. ሱለይማንንም በእርግጥ ፈተንነው። በመንበሩም ላይ የሆነ አካልን ጣልን:: ከዚያም በመጸጸት ተመለሰ።"},{"id":35,"translation":"35. «ጌታዬ ሆይ! ማረኝ ከእኔ በኋላ ለአንድም የማይገባን ንግስናንም ስጠኝ:: ለጋሹ አንተ ብቻ ነህና» አለ።"},{"id":36,"translation":"36. ንፋስንም በትዕዛዙ ወደ ፈለገበት ስፍራ ልዝብ ሆና የምትነፍስ ስትሆን ገራንለት::"},{"id":37,"translation":"37. ሰይጣናትንም ገንቢዎችንና ሰማጮችን ሁሉ ገራንለት::"},{"id":38,"translation":"38. ሌሎችንም በሰንሰለቶች ተቆራኞችን ገራንለት::"},{"id":39,"translation":"39. ይህ ስጦታችን ነው ያለ ግምት ለግስ:: ወይም ጨብጥ (አልነው)።"},{"id":40,"translation":"40. ለእርሱም እኛ ዘንድ መቅረብ መልካም መመለሻም በእርግጥ አለው::"},{"id":41,"translation":"41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባሪያችን አዩብንም: «እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝ» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ።የሆነውን አስታውስ"},{"id":42,"translation":"42. በእግርህ ምድርን ምታ:: ይህ ቀዝቃዛ መታጠቢያ መጠጥም ነው (ተባለ)::"},{"id":43,"translation":"43. ለእርሱ ከእኛ ዘንድ በሆነ ችሮታ ባለ አእምሮዎችንም ለመገሰጽ ቤተሰቦቹንም ከእነርሱ ጋር መሰላቸውን ሰጠነው።"},{"id":44,"translation":"44. «በእጅህ ጭብጥ አርጩሜን ያዝ በእርሱም (ሚስትህን) ምታ። ማላህንም አታፍርስ።» (አልነው) እነሆ ታጋሽ ሆኖ አገኘነው:: ምን ያምር ባሪያ ነው:: እርሱም በጣም መላሳ ነው።"},{"id":45,"translation":"45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዚያን የኅይልና የማስተዋል ባለቤቶች የሆኑትን ባሮቻችንም ኢብራሂምን ኢስሐቅንና ያዕቆብንም ለህዝቦችህ አውሳላቸው።"},{"id":46,"translation":"46. እኛ ጥሩ በሆነች ጠባይ መረጥናቸው፤ እርሷም የመጨረሻይቱን አገር ማስታወስ ናት::"},{"id":47,"translation":"47. እነርሱም እኛ ዘንድ ከመልካሞቹ ምርጦች ናቸው::"},{"id":48,"translation":"48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢስማኢልንም፤ ኢልያስንም፤ ዙልኪፍልንም አውሳ፤ ሁሉም ከበላጮቹ ናቸው::"},{"id":49,"translation":"49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ መልካም ዝና ነው:: አላህን ለሚፈሩም በእርግጥ ውብ የሆነ መመለሻ አላቸው።"},{"id":50,"translation":"50. በሮቻቸው ለእነርሱ የተከፈቱ ሲሆኑ የመኖሪያ ገነቶች አሏቸው::"},{"id":51,"translation":"51. በእርሷ ውስጥ የተደገፉ ሆነው በውስጧ በብዙ እሸቶችና በመጠጥም ያዝዛሉ::"},{"id":52,"translation":"52. እነርሱ ዘንድም ዓይኖቻቸውን በባሎቻቸው ላይ አሳጣሪዎች እኩያዎች ሴቶች አሉ::"},{"id":53,"translation":"53. ይህ ለምርመራው ቀን የምትቀጠሩት ተስፋ ነው::"},{"id":54,"translation":"54. ይህ ሲሳያችን ነው:: ለእርሱ ምንም ማለቅ የለዉም::"},{"id":55,"translation":"55. ይህ (ለትክክለኛ አማኞች ሲሆን።) ለጠማሞችም በጣም የከፋ መመለሻ አላቸው::"},{"id":56,"translation":"56. የሚገቧት ስትሆን ገሀነም አለቻቸው:: ምንጣፊቱም ምንኛ ከፋች::"},{"id":57,"translation":"57. ይህ ለከሓዲያን ነው:: ይቅመሱትም የፈላ ውሃና እዥ ነው::"},{"id":58,"translation":"58. ሌላም እነርሱን ከመሰሉ ብዙ አይነቶች አሉ::"},{"id":59,"translation":"59. ይህ ከናንተ ጋር በመጋፈጥ ገቢ ቡድን ነው (ይባላሉ):: ለእነርሱ አይስፋቸዉም:: እነርሱ እሳትን ገቢዎች ናቸውና (ይላሉ)::"},{"id":60,"translation":"60. ተከታዮቹም ይላሉ፡- «ይልቁን እናንተ አይስፋችሁ። እናንተ ክህደቱን ለእኛ አቀረባችሁት መርጊያይቱም ገሀነም ከፋች።»"},{"id":61,"translation":"61. «ጌታችን ሆይ! ይህንን ያቀረበልንን ሰው በእሳት ውስጥ ድርብ ቅጣትን ጨምርለት» ይላሉ።"},{"id":62,"translation":"62. ይላሉም «ለእኛ ምን አለን? ከመጥፎዎች እንቆጥራቸው የነበሩትን ሰዎች እዚህ አናይምሳ።"},{"id":63,"translation":"63. «(ሳይገባቸው) መቀለጃ አድርገን ይዘናቸው ነውን? ወይስ ዓይኖቻችን ከእነርሱ ዋለሉ?»"},{"id":64,"translation":"64. ይህ በእርግጥ እውነት ነው:: እርሱም የእሳት ሰዎች የእርስ በርስ የመካሰስ ወሬ ነው::"},{"id":65,"translation":"65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «እኔ አስፈራሪ ብቻ ነኝ። ኃያልና አንድ ከሆነ አላህ በስተቀር ምንም አምላክ የለም።"},{"id":66,"translation":"66. «የሰማያትና የምድር በመካከላቸዉም ያለው ሁሉ ጌታ አሸናፊና መሐሪ ነው።»"},{"id":67,"translation":"67. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «እርሱ (ቁርኣን) ታላቅ ዜና ነው።"},{"id":68,"translation":"68. «እናንተ ከእርሱ ዘንጊዎች ናችሁ።"},{"id":69,"translation":"69. «በሚከራከሩ ጊዜ በላይኛዋ ሰራዊት ለእኔ ምንም እውቀት አልነበረኝም።"},{"id":70,"translation":"70. «ወደ እኔም አስፈራሪ ገላጭ በመሆኔ እንጂ በሌላ አይወርድልኝም።» በል::"},{"id":71,"translation":"71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታህ ለመላዕክት እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ ባለ ጊዜ (የነበረዉን አስታውስ)::"},{"id":72,"translation":"72. «ፍጥረቱንም ባስተካከልኩና ከመንፈሴ በነፋሁበትም ጊዜ ሁላችሁም ለእርሱ ሰጋጆች ሆናችሁ ውደቁ።» (አልኩ።)"},{"id":73,"translation":"73. መላው መላዕክትም በአንድነት ሰገዱ።"},{"id":74,"translation":"74. ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር። ኮራም። ከከሓዲያንም ሆነ።"},{"id":75,"translation":"75. አላህ «ዲያብሎስ ሆይ! በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት ለአደም ከመስገድ ምን ከለከለህ? ኮርተህ ነው? ወይስ ፊቱኑ ከትዕቢተኞች ነበርክ?» አለው።"},{"id":76,"translation":"76. ዲያብሎስም «እኔ ከእርሱ የተሻልኩ ነኝ። እኔን ከእሳት የፈጠርከኝ ስትሆን እሱን ግን ከጭቃ ነው የፈጠርከው።» አለ።"},{"id":77,"translation":"77. (አላህም) አለ፡- «ከእርሷ ውጣ። አንተ የተባረርክ ነህና።"},{"id":78,"translation":"78. «እርግማኔም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ባንተ ላይ ይሁን።» አለው።"},{"id":79,"translation":"79. (ዲያብሎስም) «ጌታየ ሆይ! እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ እባክህ አቆየኝ።» አለ"},{"id":80,"translation":"80. (አላህም) አለ፡- «አንተ ከሚቆዩት ነህ።"},{"id":81,"translation":"81. «እስከ ታወቀው ወቅት ቀን ድረስ።»"},{"id":82,"translation":"82. (እርሱም) አለ: «በአሸናፊነትህ ይሁንብኝ ሁላቸዉንም አሳስታቸዋለሁ።"},{"id":83,"translation":"83. «ከእነርሱ መካከል ምርጥ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ።»"},{"id":84,"translation":"84. (አላህም) አለ: «እውነቱም ከእኔ ነው:: እውነትንም እላለሁ(እናገራለሁ)።"},{"id":85,"translation":"85. «በአንተና ከእነርሱ መካከል በተከተሉህም ባንድ ላይ ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ» አለው።"},{"id":86,"translation":"86.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «በእርሱ ላይ ምንም ዋጋ አል ጠይቃችሁም:: እኔም ከተግደርዳሪዎቹ አይደለሁም።"},{"id":87,"translation":"87. «እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም።"},{"id":88,"translation":"88. «የትንቢቱን እውነትነት ከጊዜ በኋላም ቢሆን በእርግጥ ታውቁታላችሁ።» በላቸው።"}]},{"id":39,"verses":[{"id":1,"translation":"1. የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ነው::"},{"id":2,"translation":"2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት የተሞላ ሲሆን አወረድነው:: አላህንም ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠራህ ሆነህ ተገዛው::"},{"id":3,"translation":"3. (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ ፍጹም ጥሩ የሆነው ሃይማኖት ለአላህ ብቻ ነው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች አድረገው የያዙት ሁሉ «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቃርቡን በማሰብ እንጂ ለሌላ አንገዛቸዉም።» ይላሉ:: አላህ በዚያ እነርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል:: አላህም ውሸታምንና ከሓዲ የሆነን ሰው አያቀናም::"},{"id":4,"translation":"4. አላህ ልጅን መያዝ በፈለገ ኖሮ ከሚፈጥረው ውስጥ የሚሻውን ይመርጥ ነበር:: ጥራት ተገባው:: እርሱ አሸናፊውና ብቸኛው አንዱ አላህ ነው::"},{"id":5,"translation":"5. አላህ ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ:: ሌሊቱንም በቀን ላይ ይጠቀልላል:: ቀኑንም በሌሊት ላይ እንዲሁ ይጠቀልላል:: ጸሐይንና ጨረቃንም ገራ:: ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ! እርሱ አሸናፊዉና መሀሪው ነውና::"},{"id":6,"translation":"6. (ሰዎች ሆይ!) ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ:: ከዚያም ከእርሷ መቀናጆዋን ፈጠረ:: ለእናንተም ከግመልና ከዳልጋ ከብት፤ ከፍየልና ከበግ ስምንት አይነቶችን (ጥንዶችን) አወረደ:: በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ በሶስት ጨለማዎች ውስጥ ከመፍጠር በኋላ ሙሉ መፍጠርን ይፈጥራችኋል፤ ይህን ያደረገው ጌታችሁ አላህ ነው:: ስልጣኑም የእርሱ ብቻ ነው:: ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ::"},{"id":7,"translation":"7. በአላህ ብትክዱ አላህ ከናንተ የተብቃቃ ነው:: ለባሪያዎቹም ክህደትን አይወድም፤ ብታመሰግኑም እርሱን ይወድላችኋል:: ማንኛይቱም ኃጢአትን ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም:: ከዚያም የሁላችሁም መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ብቻ ነው:: ትሰሩት የነበራችሁትንም ሁሉ ይነግራችኋል:: እርሱ በልቦች ውስጥ ያሉትን ሁሉ አዋቂ ነውና::"},{"id":8,"translation":"8. የሰውን ልጅ ጉዳት ባገኘው ጊዜ ወደ እርሱ ተመላሽ ሆኖ ጌታወን ይጠራል:: ከዚያም ከእርሱ ዘንድ ጸጋን በሰጠው ጊዜ ያንን ከዚያ በፊት ወደ እርሱ ይጸልይበት የነበረውን መከራ ይረሳል:: ከመንገዱ ለማሳሳትም ለአላህ ባላንጣዎችን ያደርጋል:: ለእንዲህ አይነቱ ሰው «በክህደት ጥቂትን ተጣቀም፤ አንተ በእርግጥ ከእሳት ጓዶች ነህ።» በለው።"},{"id":9,"translation":"9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ የመጨረሻይቱን ዓለም ቅጣት የሚፈራ የጌታውንም ችሮታ የሚከጅል ሲሆን በሌሊት ሰዓቶችም ሰጋጅና ቋሚ ሆኖ ለጌታው የሚገዛ ሰው (እንደ ተስፋ ቢሱ ከሓዲ ነውን? በለው።) «እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?» በላቸው:: የሚገሰፁት ባለ አእምሮዎች ብቻ ናቸው።"},{"id":10,"translation":"10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ጌታችሁ) «እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ለነዚያ በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ለሠሩት መልካም ምንዳ አላቸው፡፡ የአላህ ምድርም ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ ተሰደዱ)፡፡ ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው» (ይላል) በላቸው፡፡"},{"id":11,"translation":"11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በል: «እኔ አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ያጠራሁ ሆኜ እንድገዛው ታዘዝኩ።"},{"id":12,"translation":"12. «የሙስሊሞች መጀመሪያ እንድሆን ታዘዝኩ» በል።"},{"id":13,"translation":"13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ከጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ» በል::"},{"id":14,"translation":"14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በል: «አላህን ሃይማኖቴን ለእርሱ ያጠራሁ ሆኜ እገዛዋለሁ።"},{"id":15,"translation":"15. «ከእርሱ ሌላ የሻችሁትን ተገዙ:: ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በትንሳኤ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ሰዎች ሆይ! አስተዉሉ:: ግልጽ ከሳራ ማለት ይህ ነው።» በላቸው።"},{"id":16,"translation":"16. ለእነርሱ ከበላያቸው ከእሳት የሆኑ ድርብርብ ጥላዎች አሏቸው:: ከስራቸዉም እንዲሁ:: ይህ አላህ ባሮቹን እንዲጠነቀቁ በእርሱ ያስፈራራበታል:: ባሮቼ ሆይ! ስለዚህ ፍሩኝ::"},{"id":17,"translation":"17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም ጣዖታትን ከመገዛት የራቁ እና ወደ አላህ የዞሩ ሁሉ ለእነርሱ ታላቅ ብስራት አላቸው። ስለዚህ ባሮቼን አብስር፡፡"},{"id":18,"translation":"18. እነዚያን ንግግርን የሚያዳምጡትንና መልካምን የሚከተሉትን (ባሮቼን አብስር)፤ እነዚያ አላህ ወደ ቀናው መንገድ የመራቸው ናቸው። እነዚያም እነርሱ ባለ አእምሮዎቹ ናቸው።"},{"id":19,"translation":"19. በእርሱ ላይ የቅጣት ቃል የተረጋገጠችበትን (ትመራዋለህን?) አንተ በእሳት ውስጥ ያለን ታድናለህን?"},{"id":20,"translation":"20. ግን እነዚያ ጌታቸውን የፈሩ፤ ለእነርሱም ከበላያቸው የታነጹ ሰገነቶች ያሏቸው ሰገነቶች ከስሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸው የሆኑ አሏቸው:: (ይህንን) አላህ ቃል ገባላቸው፤ አላህም ቃሉን አያፈርስም::"},{"id":21,"translation":"21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ከሰማይ ውሃን እንዳወረደና በምድር ውስጥ ምንጮች አድርጎ እንዳስገባው አላየህምን? ከዚያም በእርሱ ብዙ አይነቶች የሆኑ የተለያዩ አዝመራዎችን ያወጣበታል:: ከዚያም ይደርቃል:: ገርጥቶም ታየዋለህ:: ከዚያ ስብርብር ያደርገዋል፤ በዚህ ውስጥ ለባለ አእምሮዎች ግሳፄ አለበት::"},{"id":22,"translation":"22. አላህ ደረቱን ለእስልምና ያሰፋለትና እርሱም ከጌታው ዘንድ በብርሃን ላይ የሆነ ሰው (ልቡ እንደ ደረቀ ሰው ነውን?) ልቦቻቸዉም ከአላህ መወሳት ለደረቁ ሰዎች ወየውላቸው፤ እነዚያ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ናቸው::"},{"id":23,"translation":"23. አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን ተመሳሳይ ተደጋጋሚ የሆነን መጽሐፍ (ቁርኣንን) አወረደ:: ከእርሱ ግሳፄ የእነዚያ ጌታቸውን የሚፈሩት ሰዎች ቆዳዎች ይኮማተራሉ:: ከዚያም ቆዳዎቻቸውና ልቦቻቸው ወደ አላህ ተስፋ ማስታወስ ይለዝባሉ:: ይህ የአላህ መምሪያ ነው፤ በእርሱ የሚሻዉን ሰው ይመራበታል። አላህም የሚያጠመውን ሰው ለእርሱ ምንም አቅኝ የለዉም::"},{"id":24,"translation":"24. በትንሳኤ ቀን ክፉን ቅጣት በፊቱ የሚመክት ሰው (ከቅጣቱ እንደዳነው ነውን?) ለበዳዮችም «ትሰሩት የነበራችሁን ቅጣትን ቅመሱ» ይባላሉ።"},{"id":25,"translation":"25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ በፊት የነበሩት አስተባበሉ:: ቅጣቱም ከማያውቁት በኩል መጣባቸው::"},{"id":26,"translation":"26. አላህም በቅርቢቱ ሕይወት ውርደትን አቀመሳቸው:: የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት በጣም ትልቅ ነው:: የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ አያስተባብሉም ነበር::"},{"id":27,"translation":"27. በዚህም ቁርኣን ውስጥ ለሰዎች ይገሰጹ ዘንድ ከየምሳሌው ሁሉ በእርግጥ አብራራን::"},{"id":28,"translation":"28. መዛባት የሌለበት ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን (አብራራነው):: ሊጠነቀቁ ይከጀላልና::"},{"id":29,"translation":"29. አላህ በእርሱ ተጨቃጫቂዎች የሆኑ ተጋሪዎች ያሉትን ባሪያና ለአንድ ሰው ብቻ ንጹህ የሆነን ባሪያ ለሚያጋራና በአንድነት ለሚያምን ሰው ምሳሌ አደረገ። በምሳሌ ይስተካካላሉን? ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይገባው:: በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም::"},{"id":30,"translation":"30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው::"},{"id":31,"translation":"31 ከዚያም እናንተ በትንሳኤ ቀን እጌታችሁ ዘንድ ትከራከራላችሁ::"},{"id":32,"translation":"32. በአላህ ላይም ከዋሸ እውነቱንም በመጣለት ጊዜ ካስተባበለ ሰው ይበልጥ በዳይ ማን ነው? በገሀነም ውስጥ ለከሓዲያን መኖሪያ የለምን? (አለ እንጂ)::"},{"id":33,"translation":"33. ያም በእውነት የመጣውና በእርሱ ያመነዉም እነዚያ እነርሱ አላህን ፈሪዎቹ ናቸው::"},{"id":34,"translation":"34. ለእነርሱም በጌታቸው ዘንድ የሚሹት (የሚፈልጉት) ሁሉ አላቸው:: ይህ የበጎ አድራጊዎች ምንዳ ነው::"},{"id":35,"translation":"35. አላህ ያንን በስህተት የሰሩትን መጥፎ ስራ ከእነርሱ ሊሰርዝላቸውና በዚያም ይሰሩት በነበሩት መልካም ስራ ምንዳቸውን ሊመነዳቸው ይህንን አደረገ::"},{"id":36,"translation":"36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነዚያ ከእርሱ ሌላ በሆኑትም ጣኦታት ያስፈራሩሀል፤ አላህ ለባሪያው በቂ አይደለምን? አላህ የሚያጠመውን ለእርሱ ምንም አቅኝ የለዉም::"},{"id":37,"translation":"37. አላህ የሚያቀናውንም ለእርሱ ምንም አጥማሚ የለዉም:: አላህ አሸናፊውና የመበቀል ባለቤት አይደለምን?"},{"id":38,"translation":"38. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው «አላህ ነው» ይሉሃል:: «ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን ጣዖታት አያችሁን? እስቲ ንገሩኝ:: አላህ በጉዳት ቢፈልገኝ እነርሱ ጉዳቱን ገላጮች ናቸውን? ወይስ በችሮታው ቢፈልገኝ እነርሱም ችሮታውን አጋጆች ናቸውን?» በላቸው:: «አላህ በቂዬ ነው:: በእርሱ ላይ ተመኪዎች ይመካሉ» በል::"},{"id":39,"translation":"39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸውም: «ህዝቦቼ ሆይ! ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ሁናችሁ ስሩ:: እኔም ባለሁበት ሁኔታ ላይ ሁኜ ሰሪ ነኝና:: ወደ ፊትም ትክክለኛው የቱ እንደነበር ታውቃላችሁ።"},{"id":40,"translation":"40. «ያንን የሚያሳፍረው ቅጣት የሚመጣበትንና በእርሱ ላይ ዘውታሪ ቅጣት የሚሰፍርበትን ማንነት ታውቃላቸሁ።»"},{"id":41,"translation":"41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ መጽሐፉን ባንተ ላይ ለሰዎች ጥቅም በእውነት አወረድነው:: እናም በሱ የተመራ ሰው ሁሉ ፋይዳው ለነፍሱ ነው:: የጠመመም ሰው ጉዳቱ ለራሱ ነው የሚጠመው:: አንተም ታስገድዳቸው ዘንድ በእነርሱ ላይ ጠባቂ አይደለህም::"},{"id":42,"translation":"42. አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል:: ያችንም ያልሞተችውን ነፍስ በእንቅልፈ ጊዜ ይወስዳታል:: ከዚያም ያችን ሞትን የፈረደባትን ነፍስ ይይዛታል:: ሌላይቱን ደግሞ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ይለቃታል:: በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተአምራት አሉበት::"},{"id":43,"translation":"43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም ቁረይሾች ከአላህ ሌላ አማላጆችን ያዙ። «እነርሱ ምንም የማይችሉና ምንም የማያውቁ ቢሆኑም ታመልኳቸዋላችሁን?» በላቸው።"},{"id":44,"translation":"44. «ምልጃ ሁሉም የአላህ ብቻ ነው:: የሰማያትና የምድር ስልጣንም የእርሱ ብቻ ነው:: ከዚያም ወደ እርሱ ትመለሳላችሁ» በላቸው::"},{"id":45,"translation":"45. አላህ ብቻዉን በተወሳ ጊዜ የእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ልቦች ይሸማቀቃሉ (ይደነብራሉ) እነዚያ ከእርሱ ሌላ የሆኑት ጣዖታት በተወሱ ጊዜ ደግሞ እነርሱ ወዲያውኑ ይደሰታሉ።"},{"id":46,"translation":"46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰማያትንና ምድርን የፈጠርክ ሩቁንም ቅርቡንም አዋቂ የሆንከው አላህ ሆይ! አንተ በባሮችህ መካከል በዚያም ይለያዩበት በነበሩት ነገር ትፈርዳለህ» በል::"},{"id":47,"translation":"47. ለነዚያም ለበደሉት በምድር ያለው ሁሉ መላዉም ከእርሱ ጋር መሰሉም ቢኖራቸው ኖሮ በትንሳኤ ቀን ከቅጣቱ ክፋት የተነሳ በእርሱ ነፍሶቻቸውን በተበዡበት ነበር:: ለእነርሱም ከአላህ ዘንድ ያስቡት ያልነበሩት ሁሉ ይገለጽላቸዋል::"},{"id":48,"translation":"48. ለእነርሱም የሰሯቸው መጥፎዎቹ ይገልጹላቸዋል:: በእነርሱም ላይ በእርሱ ያላግጡበት የነበሩት ቅጣት ይሰፍርባቸዋል::"},{"id":49,"translation":"49. ሰውም ጉዳት ባገኘው ጊዜ ይጠራናል:: ከዚያም ከእኛ የሆነውን ጸጋ በሰጠነው ጊዜ «እርሱን የተሰጠሁት በእውቀቴ ብቻ ነው።» ይላል:: ይልቁንም እርሷ (ጸጋይቱ) መፈተኛ ናት:: ግን አብዛሀኞቻቸው አያውቁም::"},{"id":50,"translation":"50. እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት ህዝቦች ይችኑ ቃል በእርግጥ ብለዋታል:: ይሰሩት የነበሩትም ነገር ከእነርሱ አልጠቀማቸዉም::"},{"id":51,"translation":"51. የሰሯቸዉም መጥፎዎች ቅጣት አገኛቸው:: ከእነዚህም እነዚያ የበደሉት የሰሯቸውን መጥፎዎች ፍዳ በእርግጥ ይነካቸዋል:: እነርሱም አምላጮች አይደሉም::"},{"id":52,"translation":"52. አላህ ሲሳዩን ለሚሻው ሰው የሚያሰፋ፤ ለሚሻው ሰው የሚያጠብም መሆኑን አያውቁምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑት ህዝቦች ሁሉ አያሌ ግሳጼዎች አሉበት::"},{"id":53,"translation":"53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ:: አላህ ኃጢአቶችን ሁሉ ይምራልና:: እነሆ እርሱ መሀሪዉና አዛኙ ነውና።»"},{"id":54,"translation":"54. (ሰዎች ሆይ!) ቅጣቱ ወደ እናንተ ከመምጣቱና ከዚያም የማትረዱ ከመሆናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ (በመጸጸት) ተመለሱ:: ለእርሱም ታዘዙ::"},{"id":55,"translation":"55. እናንተ የማታውቁ ስትሆኑ ቅጣቱ በድንገት ሳይመጣባችሁ በፊት ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን መልካሙን መጽሐፍ ተከተሉ::"},{"id":56,"translation":"56. የካደች ነፍስ ሁሉ «እኔ ከሚሳለቁት የነበርኩ ስሆን በአላህ በኩል ባጓደልኩት ዋ! ጸጸቴ!» የምትል እንዳትሆን"},{"id":57,"translation":"57. ወይም «አላህ በመራኝ ኖሮ ከሚጠነቀቁት ሰዎች እሆን ነበር።» የምትል እንዳትሆን"},{"id":58,"translation":"58. ወይም ቅጣቱን በምታይ ጊዜ «ለእኔ ወደ ምድረ አለም አንድ ጊዜ የመመለስ ዕድል በኖረኝና ከበጎ አድራጊዎች በሆንኩ።» የምትል ከመሆኗ በፊት መልካሙን ተከተሉ::"},{"id":59,"translation":"59. የለም ተመርተሃል:: አንቀፆቼ በእርግጥ መጥተውሃል:: በእነርሱም አስተባብለሃል፤ ኮርተሃልም:: ከከሓዲያንም ሆነሃል (ይባላል)::"},{"id":60,"translation":"60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በትንሳኤ ቀንም እነዚያን በአላህ ላይ የዋሹትን ፊቶቻቸው የጠቆሩ ሆነው ታያቸዋለህ:: በገሀነም ውስጥ ለትዕቢተኞች መኖሪያ የለምን?"},{"id":61,"translation":"61. እነዚያም የተጠነቀቁትን በማግኛቸው ስፍራ ሆነው አላህ ያድናቸዋል፤ ክፉ ነገር አይነካቸዉም:: እነርሱም አያዝኑም::"},{"id":62,"translation":"62. አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው::"},{"id":63,"translation":"63. የሰማያትና የምድር (ድልብ) መከፈቻዎች የእርሱ ብቻ ናቸው:: እነዚያም በአላህ አናቅጽ የካዱት እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው::"},{"id":64,"translation":"64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ መሃይማን ሆይ! ከአላህ ሌላን እንድንገዛ ታዙኛላቸሁን?» በላቸው::"},{"id":65,"translation":"65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብታጋራ ስራህ በእርግጥ ይታበሳል:: በእርግጥም ከከሓዲያን ትሆናለህ በማለት ወደ አንተና እነዚያ ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ሰዎች በእርግጥ ተወርዷል::"},{"id":66,"translation":"66. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቅ አላህን ብቻ ተገዛም:: ከአመስጋኞችም ሁን::"},{"id":67,"translation":"67. አላህንም በትንሳኤው ቀን ምድርን በመላ ጭብጡ ስትሆንና ሰማያትም በቀኝ እጁ የሚጠቀለሉ ሲሆኑ ከእርሱ ጋር ሌላን በማጋራታቸው ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም:: ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ። ላቀም::"},{"id":68,"translation":"68. በቀንዱም ይነፋል:: በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡርና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ አላህ የሻው ሲቀር በድንጋጤ ይሞታል:: ከዚያም በእርሱ ሌላ መነፋት ይነፋል:: ወዲያውኑም እነርሱ የሚሰራባቸውን የሚጠባበቁ ሆነው ቋሚዎች ይሆናሉ::"},{"id":69,"translation":"69. ምድርም በጌታዋ ብርሃን ታበራለች፤ መጽሐፉም ይቀርባል:: ነብያትና ምስክሮችም ይመጣሉ:: በመካከላቸዉም በእውነት ይፈረዳል:: እነርሱም አይበደሉም::"},{"id":70,"translation":"70. ነፍስም ሁሉ የሰራቸውን ስራ ትሞላለች (ትሰፍራለች):: እርሱም የሚሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነው::"},{"id":71,"translation":"71. እነዚያ በአላህ የካዱትም የተከፋፈሉ ቡድኖች ሆነው ወደ ገሀነም ይነዳሉ፤ በመጧትም ጊዜ በሮቿ ይከፈታሉ:: ወደሷ በመጡም ጊዜ ዘበኞቿ «ከእናንተ የሆኑ የጌታችሁን አናቅጽ በእናንተ ላይ የሚያነቡላችሁ የዚህንም ቀን መገናኘት የሚያስጠነቅቋችሁ መልዕክተኞች አልመጧችሁምን ነበርን?» ይሏቸዋል፤ «የለም መጥተውልናል። ግን የቅጣቲቱ ቃል በከሓዲያን ላይ ተረጋገጠች።» (ይላሉ።)"},{"id":72,"translation":"72. «የገሀነምን በሮች በውስጧ ዘወታሪዎች ስትሆኑ ግቡ የትዕቢተኞችም መኖሪያ ምን ትከፋ!» ይባላል።"},{"id":73,"translation":"73. እነዚያም ጌታቸውን የፈሩት የተከፋፈሉ ቡድኖች ሆነው ወደ ገነት ይነዳሉ:: በመጧትም ጊዜ ደጃፎቿ የተከፈቱ ሲሆኑ ዘበኞቿም ለእነርሱ «ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን ተዋባችሁ፤ ዘወታሪዎች ሆናችሁ ግቧት።» ይሏቸዋል።"},{"id":74,"translation":"74. «ምስጋና ሁሉ ለአላህ ለዚያ የተስፋ ቃሉን ለሞላልን፤ የገነትንም ምድር በምንሻው ስፍራ የምንሰፍር ስንሆን ላወረሰን ይገባው።» ይላሉ። የሰሪዎችም ምንዳ ምን ያምር!"},{"id":75,"translation":"75. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላዕክትንም በጌታቸው ምስጋና ቀላቅለው የሚያጠሩ ሲሆኑ በአርሹ ዙሪያ ከባቢዎች ሆነው ታያለህ፡፡ በመካከላቸውም እውነት ይፈረዳል። ይባላልም፤ «ምስጋና ሁሉ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው።»"}]},{"id":40,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ሓ፤ ሚይም፤"},{"id":2,"translation":"2. የመጽሐፉን መውረድ አሸናፊው አዋቂው ከሆነው ከአላህ ብቻ ነው::"},{"id":3,"translation":"3. ኃጢአት መሀሪና ጸጸትን ተቀባይ፤ ቅጣተ ብርቱ፤ የልግስና ባለቤት ከሆነው አላህ ብቻ የተወረደ ነው:: ከእርሱ በስተቀር (እውነተኛ) አምላክ የለም:: መመለሻዉም ወደ እርሱ ብቻ ነው::"},{"id":4,"translation":"4. በአላህ አንቀጾች እነዚያ የካዱት ቢኾኑ እንጅ ማንም (በመዝለፍ) አይከራከርም፡፡ በያገሮችም ውስጥ መዘዋወራቸው አይሸንግልህ፡፡"},{"id":5,"translation":"5. ከእነርሱ በፊት የኑህ ህዝቦች ከኋላቸዉም አህዛቦች አስተባበሉ:: ህዝቦችም ሁሉ መልዕክተኛቸውን ሊይዙ አሰቡ፤ በውሸትም በእርሱ እውነትን ሊያጠፉበት ተከራከሩ:: ያዝኳቸዉም። ታዲያ ቅጣቴ እንዴት ነበር?"},{"id":6,"translation":"6. ልክ እንደዚሁም የጌታህ ቃል በእነዚያ በአላህ በካዱት ላይ እነርሱ የእሳት ጓዶች ናቸው ማለት ተረጋገጠች::"},{"id":7,"translation":"7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፤ በእርሱም ያምናሉ። ለነዚያ ላመኑትም (እንዲህ እያሉ) ምህረትን ይለምኑላቸዋል: «ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነትና በእውቀት ከበሃል፤ ስለዚህ ለእነዚያ ለተጸጸቱት መንገድህንም ለተከተሉት ምህረት አድርግላቸው፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው፤"},{"id":8,"translation":"8. «ጌታችን ሆይ! እነርሱም ከአባቶቻቸውና ከሚስቶቻቸዉም ከዝርዮቻቸዉም የበጀውን ሁሉ እነዚያንም ቃል የገባህላቸውን የመኖሪያ ገነቶች አስገባቸው፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው ነህና::"},{"id":9,"translation":"9. «ከቅጣቶችም ጠብቃቸው፤ በዚያ ቀንም የምትጠብቀውን በእርግጥ አዘንክለት:: ይህም እርሱ ታላቅ ማግኘት ነው::»"},{"id":10,"translation":"10. እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች «ወደ እምነት በምትጠሩና በምትክዱ ጊዜ አላህ (እናንተን) መጥላቱ ነፍሶቻችሁን (ዛሬ) ከመጥላታችሁ የበለጠ ነው።» በማለት ይጠራሉ::"},{"id":11,"translation":"11. «ጌታችን ሆይ! ሁለትን ሞት አሞትከን:: ሁለትንም ሕይወት ህያው አደረግከን:: በኃጢአቶቻችንም መሰከርን። ታዲያ (ከእሳት) ወደ መውጣት መንገድ አለን?» ይላሉ።"},{"id":12,"translation":"12. (ከሀዲያን ሆይ!) «ይሃችሁ እነሆ አላህ ብቻውን በተጠራ ጊዜ ስለ ካዳችሁ በእርሱም ተጋሪ ቢደረግ የምታምኑ ስለሆናችሁ ነው:: ስለዚህ ፍርዱ ከፍተኛ ታላቅ ለሆነው አላህ ብቻ ነው::» (ይባላሉ)"},{"id":13,"translation":"13. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ለአምላክነቱ ምልክቶችን የሚያሳያችሁ፤ ለእናንተም ከሰማይ ሲሳይን የሚያወርድላችሁ ነው:: ወደርሱም የሚመለስ ሰው ቢሆን እንጂ ሌላው አይገሰጽም::"},{"id":14,"translation":"14. አላህንም ከሓዲያን ቢጠሉም (እንኳ) ሃይማኖትን ለእርሱ አጥሪዎች ሆናችሁ ተገዙ::"},{"id":15,"translation":"15. እርሱ ደረጃዎችን ከፍ አድራጊ የዐርሹ ባለቤት ነው:: የመገናኛውን ቀን ያስፈራራ ዘንድ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከትዕዛዙ ራዕይን ያወርዳል::"},{"id":16,"translation":"16. እነርሱ ከመቃብር በሚወጡበት ቀን ከእነርሱ ምንም ነገር በአላህ ላይ አይደበቅም:: «ንግስናው ዛሬ ለማን ነው?» ይባላል:: «ለአሸናፊው ለአንዱ አላህ ብቻ ነው» ይባላል::"},{"id":17,"translation":"17. «ዛሬ ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ ትመነዳለች፤ ዛሬ በደል የለም:: አላህ በእርግጥ ምርመራው ፈጣን ነው።» ይባላል::"},{"id":18,"translation":"18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቅርቢቱንም የትንሳኤ ቀን ልቦች ጭንቀትን የተሞሉ ሆነው ላንቃዎች ዘንድ የሚደርሱበትን ጊዜ አስጠንቅቃቸው:: ለበዳዮች ምንም ወዳጅና ተሰሚ አማላጅ የላቸዉም::"},{"id":19,"translation":"19. አላህ የዓይኖችን ክዳት ልቦችም የሚደብቁትን ሁሉ ያውቃል::"},{"id":20,"translation":"20. አላህም በእውነት ይፈርዳል:: እነዚያም ከእርሱ ሌላ የሚገዟቸው በምንም አይፈርዱም:: አላህ እርሱ ሰሚው ተመልካቹ ነው::"},{"id":21,"translation":"21. የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ፍፃሜ እንዴት እንደነበረ ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን? በሀይልና በምድር ላይ በተዋቸው ምልክቶች ከእነርሱም ይበልጥ የበረቱ ነበሩ:: አላህም በኃጢአቶቻቸው ያዛቸው። ለእነርሱም ከአላህ ቅጣት ምንም ጠባቂ አልነበራቸዉም::"},{"id":22,"translation":"22. ይህ (መያዝ) እነርሱ መልዕክተኞቻቸው በተዓምራት ይመጡባቸው ስለ ነበሩና ስለካዱ ነው:: አላህም ያዛቸው። እርሱ ኃያል፤ ቅጣተ ብርቱ ነውና::"},{"id":23,"translation":"23. ሙሳንም በተዓምራቶቻችንና በግልጽ ማስረጃ በእርግጥ ላክነው::"},{"id":24,"translation":"24. ወደ ፈርዖን ወደ ሃማን እና ወደ ቃሩንም ላክነው:: «ድግምተኛ እና ውሸታም ነው» አሉ::"},{"id":25,"translation":"25. ከእኛ ዘንድ እውነትን ይዞ በመጣላቸውም ጊዜ: «የእነዚያን ከእርሱ ጋር ያመኑት ሰዎች ወንድ ልጆች ግደሉ፤ ሴቶቻቸውንም አስቀሩ።» አሉ፤ የከሓዲያንም ተንኮል በጥፋት ውስጥ እንጂ ሌላ አይደለም::"},{"id":26,"translation":"26. ፈርዖንም «ተዉኝ፤ ሙሳን ልግደል:: (ያድነው እንደሆነም) ጌታውን ይጥራ:: እኔ ሃይማኖታችሁን ሊለውጥ ወይም በምድር ውስጥ ጥፋትን ሊያሰራጭ እፈራለሁና።» አለ::"},{"id":27,"translation":"27. ሙሳም «እኔ በምርመራው ቀን ከማያምን ትዕቢተኛ ሁሉ በጌታየና በጌታችሁ ተጠበቅሁ።» አለ::"},{"id":28,"translation":"28. ከፈርዖን ቤተሰቦች አንድ እምነቱን የሚደብቅ ምዕመን ሰውም አለ: «ሰውዬው ከጌታችሁ በታዐምራቶች በእርግጥ የመጣላችሁ ሲሆን 'ጌታየ አላህ ነው' ስለሚል ትገድሉታላችሁን? ውሸታምም ቢሆን ውሸቱ በእርሱ ላይ ነው:: እውነተኛ ቢሆን ግን የእዚያ የሚያስፈራራችሁ ከፊሉ ያገኛችኋል:: አላህ እርሱ ያንን ድንበር አላፊና ውሸታም የሆነውን አይመራምና።"},{"id":29,"translation":"29. «ወገኖቼ ሆይ! በምድር ላይ አሸናፊዎች ስትሆኑ ዛሬ መንግስትነት የእናንተ ነው:: ታዲያ ከአላህ ቅጣት ቢመጣብን የሚያድነን ማን ነው?» አለ:: ፈርዖንም «የማየውን እንጂ አላመላክታችሁም፤ ቅኑን መንገድ እንጂ አልመራችሁም።» አላቸው።"},{"id":30,"translation":"30. ያ ያመነው ሰውም አለ፡- «እኔ በእናንተ ላይ የአህዛብን ቀን ብጤ እፈራላችኋለሁ።"},{"id":31,"translation":"31. «የ(ነብዩ) ኑህን ህዝቦች የዓድንና የሰሙድም የእነዚያን ከኋላቸው የነበሩትንም ህዝቦች ልማድ ብጤ እፈራላችኋለሁ:: አላህም ለባሮቹ መበደል የሚሻ ጌታ (ሆኖ) አይደለም::"},{"id":32,"translation":"32. «ወገኖቼ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ የመጠራሪያን ቀን እፈራለሁ::»"},{"id":33,"translation":"33. ወደ ኋላ ዞራችሁ በምትሸሹበት ቀን፤ ለእናንተ ከአላህ ቅጣት ምንም ጠባቂ የላችሁም፤ አላህም የሚያጠመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኚ የለዉም::"},{"id":34,"translation":"34. ዩሱፍም ከዚህ በፊት ግልጽ ማስረጃዎችን በእርግጥ አመጣላችሁ:: ከዚያ እርሱ ካመጣላችሁ ነገር ከመጠራጠር አልተወገዳችሁም:: በጠፋም ጊዜ «አላህ ከእርሱ በኋላ መልዕክተኛን በጭራሽ አይልክም» አላችሁ፤ አላህ እንደዚሁ ድንበር አላፊ ተጠራጣሪ የሆነን ሰው ያሳስታል።"},{"id":35,"translation":"35. እነዚያ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር በአላህ ታዓምራቶች የሚከራከሩ (ክርክራቸው) አላህ ዘንድና እነዚያም ያመኑት ዘንድ መጠላቱ በጣም ተለቀ:: እንደዚሁ አላህ በኩሩ ጨካኝ ልብ ሁሉ ላይ ያትማል::"},{"id":36,"translation":"36. ፈርዖንም አለ፡- «ሃማን ሆይ! መንገዶችን እደርስ ዘንድ ረዥም ህንፃን ካብልኝ። የሰማያትን መንገዶች እደርስ ዘንድ።"},{"id":37,"translation":"37. «የሰማያትን መንገዶች እደርስ ዘንድ። ከዚያ ወደ ሙሳ አምላክ እመለከት ዘንድ። እኔም ውሸታም ነው ብዬ እጠረጥረዋለሁ።» አለ:: ልክ እንደዚሁ ለፈርዖን መጥፎ ስራው ተሸለመለት:: ከቅኑ መንገድም ታገደ:: የፈርዖንም ተንኮል በከሳራ ውስጥ እንጂ አይደለም::"},{"id":38,"translation":"38. ያ ያመነውም አለ፡- «ወገኖቼ ሆይ! ተከተሉኝ ቀጥታውን መንገድ እመራችኋለሁና::"},{"id":39,"translation":"39. «ወገኖቼ ሆይ! ይህች ቅርቢቱ ሕይወት የጥቂት ቀናት መጣቀሚያ ብቻ ናት፤ መጨረሻይቱ ዓለም ግን እርሷ ትክክለኛ መርጊያ አገር ናት::"},{"id":40,"translation":"40. «መጥፎን የሰራ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም:: እርሱ ምዕመን ሆኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎ የሰራም እነዚያ ገነትን ይገባሉ:: በእርሷ ውስጥም ያለ ቁጥር ይለገሳሉ።"},{"id":41,"translation":"41. «ወገኖቼ ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስሆን ወደ እሳትም የምትጠሩኝ ስትሆኑ ለእኔ ምን አለኝ!"},{"id":42,"translation":"42. « (እናንተ) በአላህ ልክድና በእርሱም ለእኔ እውቀቱ የሌለኝ ነገር በእርሱ እንዳጋራ ትጠሩኛላችሁ! እኔ አሸናፊና መሀሪ ወደ ሆነው አላህ እጠራችኋለሁ።"},{"id":43,"translation":"43. «በእርግጥ ወደ እርሱ የምትጠሩኝ ጣዖት ለእርሱ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ተሰሚ ጥሪ የለዉም። መመለሻችንም እርግጥ ወደ አላህ ብቻ ነው:: ወሰን አላፊዎችም እነርሱ የእሳት ጓዶች ናቸው።"},{"id":44,"translation":"44. «ወደ ፊትም ለእናንተ የምላችሁን ምክር (ቅጣትን በምታዩ ጊዜ) ታስታውሱታላችሁ:: ነገሬንም ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋለሁ:: አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና።»"},{"id":45,"translation":"45. ካሴሯቸዉም መጥፎዎች አላህ ጠበቀው፡፡ በፈርዖን ቤተሰቦችም ላይ ክፉ ቅጣት ሰፈረባቸው::"},{"id":46,"translation":"46. እሳት በጧትና በማታ በእርሷ ላይ ይቀርባሉ፡፡ ሰዓቲቱም በምትሆንበት ቀን «የፈርዖንን ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት ገሀነምን አስገቧቸው» ይባላል።"},{"id":47,"translation":"47. በእሳት ውስጥ የሚከራከሩበትን ጊዜ አስታውስ: ደካማዎቹም ለነዚያ ለኮሩት «እኛ ለእናንተ ተከታዮች ነበርንና እናንተ አሁን ከእሳት ከፊሉን ከእኛ ላይ ገፍታሪዎች ናችሁን?» ይላሉ::"},{"id":48,"translation":"48. እነዚያም የኮሩት «እኛ ሁላችንም በውስጧ ነን አላህ በባሮቹ መካከል በእርግጥ ፈርዷል» ይላሉ::"},{"id":49,"translation":"49. እነዚያም በእሳት ውስጥ ያሉት ለገሀነም ዘበኞች «ጌታችሁን ለምኑልን፤ ከእኛ ላይ ከቅጣቱ ለአንድም ቀን ያቃልልን።» ይላሉ።"},{"id":50,"translation":"50. ዘበኞቹም «መልዕክተኞቻችሁ በታዐምራቶች ይመጡላችሁ አልነበሩምን?» ይላሉ ከሓዲያንም «እንዴታ መጥተውልናል እንጅ፤ ግን አሰተባበልናቸው።» ይላሉ። «እንግዲያውስ ጸልዩ የከሓዲያንም ጸሎት በከንቱ እንጂ አይደለም።» ይሏቸዋል፡:"},{"id":51,"translation":"51. እኛ መልክተኞቻችንን እነዚያንም ያመኑትን በቅርቢቱ ሕይወትም ምስክሮች በሚቆሙበት ቀንም በእርግጥ እንረዳለን።"},{"id":52,"translation":"52. በደለኞችን ምክንያታቸው በማይጠቅማቸው ቀን እንረዳለን። ለነርሱም ርግማን አላቸው:: ለነርሱም መጥፎ አገር አላቸው::"},{"id":53,"translation":"53. ሙሳንም መምሪያ በእርግጥ ሰጠነው:: የኢስራኢልንም ልጆች መጽሐፍን አወረስናቸው::"},{"id":54,"translation":"54. ለባለ አእምሮዎች መሪና ገሳጭ ሲሆን፤"},{"id":55,"translation":"55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ታገስም የአላህ ተስፋ እውነት ነውና፤ ለስህተትህም ምህረትን ለምን፤ ከቀትር በኋላም በማለዳም ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው::"},{"id":56,"translation":"56. እነዚያ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር በአላህ አናቅጽ የሚከራከሩ በልቦቻቸው ውስጥ እነርሱ ደራሾች ያልሆኑት ኩራት ብቻ እንጂ ምንም የለም:: በአላህም ብቻ ተጠበቅ፤ እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነውና::"},{"id":57,"translation":"57. ሰማያትንና ምድርን መፍጠር ሰዎችን ከመፍጠር ይልቅ ታላቅ ነው:: ግን አብዛሀኞቹ ሰዎች አያውቁም::"},{"id":58,"translation":"58. ዐይነ ስዉርና የሚያይ እነዚያም አምነው መልካሞችን የሰሩትና መጥፎ ሰሪው አይስተካከሉም። በጣም ጥቂትን ብቻ ትገስፃላችሁ::"},{"id":59,"translation":"59. ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት:: በእርሷ ጥርጥር የለም:: ግን አብዛሀኞቹ ሰዎች አያምኑም::"},{"id":60,"translation":"60. (ባሮቼ ሆይ!) ጌታችሁም አለ: «ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና። እነዚያ እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነም በእርግጥ ይገባሉ።»"},{"id":61,"translation":"61. አላህ ያ ለእናንተ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት ጨለማ፤ ቀንኑ ደግሞ ልትሰሩበት የሚያሳይ ብርሃን ያደረገላችሁ ነው:: አላህ በሰዎች ላይ በእርግጥ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና:: ግን አብዛሀኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም::"},{"id":62,"translation":"62. ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው:: የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ::"},{"id":63,"translation":"63. ልክ እንደዚሁ እነዚያ በአላህ አናቅጽ ይክዱ የነበሩት ከእምነት ይመለሳሉ::"},{"id":64,"translation":"64. (ሰዎች ሆይ)! አላህ ያ ምድርን መርጊያ ሰማይንም ጣሪያ ያደረገላችሁ ነው፡፡ የቀረፃችሁም ቅርፃችሁንም ያሳመረ፤ ከጣፋጭ ሲሳዮችም የሰጣችሁ ነው:: ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው። የዓለማትም ጌታ አላህ ላቀ::"},{"id":65,"translation":"65. እርሱ ብቻ ሁል ጊዜ ህያው ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ሃይማኖትንም ለርሱ ያጠራችሁ ስትሆኑ «ምስጋና ሁሉ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው›› የምትሉ ሆናችሁ ተገዙት::"},{"id":66,"translation":"66. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ከጌታዬ አስረጂዎች በመጡልኝ ጊዜ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዙዋቸውን እንዳልገዛ ተከልክያለሁ፤ ለዓለማትም ጌታ ብቻም እንድገዛ ታዝዣለሁ።» በላቸው::"},{"id":67,"translation":"67. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ (አላህ) ያ ከዐፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ከዚያም ከረጋ ደም የፈጠራችሁ ነው:: ከዚያም ህፃን አድርጎ ያወጣችኋል:: ከዚያም ጥንካሬያችሁን ትደርሱ ዘንድ፤ ከዚያም ሽማግሌዎች ትሆኑ ዘንድ ያቆያችኋል:: ከናንተም ውስጥ ከዚህ በፊት የሚሞት አለ:: ይህንንም ያደረገው ኑራችሁ የተወሰነ ጊዜም ልትደርሱ ታውቁም ዘንድ ነው::"},{"id":68,"translation":"68. እርሱ (አላህ) ያ ህያው የሚያደርግና የሚያሞትም ነው:: አንዳችን ነገር በሻም ጊዜ ለእርሱ የሚለው ሁን ነው ወዲያዉም ይሆናል::"},{"id":69,"translation":"69.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ በአላህ አናቅጽ ወደሚከራከሩት ከእምነት እንዴት እንደሚመለሱ አታይምን?"},{"id":70,"translation":"70. ወደ እነዚያ በመጽሐፉ በዚያም መልዕክተኞቻችንን በእርሱ በላክንበት ወዳስተባበሉበት አታይምን? ወደፊትም ያውቃሉ::"},{"id":71,"translation":"71. እንዘዝላዎቹና ሰንሰለቶቹ በአንገቶቻቸው ላይ በተደረጉ ጊዜ (በእርሷ) ይጎተታሉ።"},{"id":72,"translation":"72. በገሀነም ውስጥ ይጎተታሉ፤ ከዚያም በእሳት ውስጥ ይማገዳሉ::"},{"id":73,"translation":"73. ከዚያም ለእነርሱ ይባላሉ፡- «(በአላህ) ታጋሯቸው የነበራችሁት የታሉ?"},{"id":74,"translation":"74. ከአላህ ሌላ የምታጋሩዋቸው (የት አሉ)?» «ከእኛ ተሰወሩብን፤ ከቶ ከዚህ በፊት ምንም የምንገዛ አልነበርንም» ይላሉ:: ልክ እንደዚሁ አላህ ካሐዲያንን ያሳስታል::"},{"id":75,"translation":"75. «ይህ (ቅጣታችሁ) ያላአግባብ በምድር ውስጥ ትደሰቱ በነበራችሁትና ትንበጣረሩ በነበራችሁት ነው።"},{"id":76,"translation":"76. የገሀነምን በሮች ውስጧ ዘወታሪዎች ስትሆኑ ግቡ።» (ይባላሉ)። የትዕቢተኞችም መኖሪያ (ገሀነም) ምን ትከፋ!"},{"id":77,"translation":"77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ታገስም:: የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፤ የዚያንም የምናስፈራራቸውን ከፊሉን በህይወትህ ብናሳይህ መልካም ነው:: ወይም ሳናሳይህ ብንገድልህ ወደ እኛ ይመለሳሉ::"},{"id":78,"translation":"78. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም መልዕክተኞችን በእርግጥ ልከናል። ከእነርሱ ባንተ ላይ የተረክንልህ አለ:: ከእነርሱም ባንተ ላይ ያልተረክነውም አለ:: ለማንኛዉም መልዕክተኛ በአላህ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር ተዓምርን ሊያመጣ አይገባዉም:: የአላህም ትዕዛዝ በመጣ ጊዜ በእውነት ይፈረዳል:: እዚያ ዘንድም አጥፊዎች ይከስራሉ::"},{"id":79,"translation":"79. አላህ ያ ለእናንተ ግመልን ከብትንና ፍየልን ከእርሷ ከፊሏን ልትጋልቡ የፈጠረላችሁ ነውና:: ከእርሷም ትበላላችሁ::"},{"id":80,"translation":"80. ለእናተም በርሷ ውስጥ ጥቅሞች አሏችሁ:: በእርሷም ላይ ዕቃን በመጫን በልቦቻችሁ ያሰባችሁትን ጉዳይ ትደርሱ ዘንድ ፈጠረላችሁ። በእርሷም ላይ በመርከቦችም ላይ ትሳፈራላችሁ::"},{"id":81,"translation":"81. ተዓምራትንም ያሳያችኋል:: ታዲያ ከአላህ ተዓምራት መካከል የትኛውን ትክዳላችሁ?"},{"id":82,"translation":"82. የእነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ፍፃሜ እንዴት እንደነበር ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን ? ከእነርሱ ይበልጥ ብዙዎች በኃይልና በምድር ላይ በተዋቸው ምልክቶችም በጣም ብርቱዎች ነበሩ:: ያም ይሰሩት የነበሩት ለእነርሱ ምንም አልጠቀማቸዉም::"},{"id":83,"translation":"83. መልዕክተኞቻቸዉም ተዓምራትን ባመጡላችሁ ጊዜ እነርሱ ዘንድ ባለው ዕውቀት ተደሰቱ:: በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣትም በእነርሱ ላይ ሰፈረባቸው::"},{"id":84,"translation":"84. ብርቱ ቅጣታችንንም ባዩ ጊዜ «በአላህ አንድነት አምነናል በእርሱም እናጋራ በነበርነው ጣዖታት ክደናል» አሉ::"},{"id":85,"translation":"85. ብርቱ ቅጣታችንን ባዩ ጊዜ ማመናቸዉም የሚጠቅማቸው አልነበረም:: የአላህን ደንብ ያችን በባሮቹ ውስጥ ያለፈችውን ተጠንቀቁ:: በዚያ ጊዜም ከሓዲያን ከሰሩ::"}]},{"id":41,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ሓ፤ ሚይም፤"},{"id":2,"translation":"2. ይህ ቁርኣን እጅግ በጣም ሩህሩህና በጣም አዛኝ ከሆነው ጌታ ከአላህ የተወረደ ነው::"},{"id":3,"translation":"3. አናቅጾቹ የተብራሩ የሆነ መጽሐፍ ነው:: ዐረበኛ ቁርኣን ሲሆን ለሚያውቁ ሕዝቦች የተብራራ ነው::"},{"id":4,"translation":"4. አብሳሪና አስፈራሪ ሲሆን ተወረደ። አብዛኞቻቸዉም ተውት:: እነርሱም አይሰሙም::"},{"id":5,"translation":"5. አሉም፡- «ልቦቻችን ከዚያ ወደርሱ ከምትጠራን እምነት በመሸፈኛዎች ውስጥ ናቸው:: በጆሮቻችንም ላይ ድንቁርና አለ:: በእኛና በአንተ መካከል ግርዶሽ አለ:: በሃይማኖትህ ስራ እኛም ሰሪዎች ነንና::»"},{"id":6,"translation":"6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዲህ በላቸው «እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: ወደ እርሱም ቀጥ በሉ:: ምህረትንም ለምኑት በማለት ወደ እኔ ይወርድልኛል እንጂ መሰላችሁ ሰው ብቻ ነኝ።» ለአጋሪዎችም ወዮላቸው።"},{"id":7,"translation":"7. ለእነዚያ ዘካን ለማይሰጡ እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ ከሓዲያን ለሆኑት (ወዮላቸው)::"},{"id":8,"translation":"8. እነዚያ ያመኑትና በጎ ስራዎችንም የሰሩት ሁሉ ለእነርሱ የማይቋረጥ ምንዳ አላቸው::"},{"id":9,"translation":"9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ !) «እናንተ በዚያ ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን? ለእርሱም ባላንጣዎች ታደርጋላችሁን? ያ (ይህንን የሰራው) የዓለማቱ ጌታ ነው።» በላቸው::"},{"id":10,"translation":"10. በእርሷም ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ:: በእርሷም በረከትን አደረገ:: በውስጧም ምግቦችዋን (ካለፉት ሁለት ቀኖች ጋር) በአራት ቀናት ውስጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲሆን ወሰነ::"},{"id":11,"translation":"11. ከዚያም እርሷ ጭስ ሆና ሳለች ወደ ሰማይ አሰበ:: ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ሆነ ጠልታችሁ ኑ» አላቸው:: «ታዛዦች ሆነን መጣን» አሉ::"},{"id":12,"translation":"12. በሁለት ቀናትም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው:: በሰማያትም ሁሉ ነገሯን አዘጋጀ:: ቅርቢቱንም ሰማይ በመብራቶች አጌጥን:: ከሰይጣናት መጠበቅንም ጠበቅናት:: ይህ የአሸናፊውና የአዋቂው ጌታ ውሳኔ ነው::"},{"id":13,"translation":"13. ከእምነት እምቢ ቢሉም (እንዲህ) በላቸው: «እንደ ዓድና ሰሙድ መቅሰፍት ብጤ የሆነን መቅሰፍት አስጠነቅቄያችኋለሁ።»"},{"id":14,"translation":"14. መልዕክተኞቹ «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ» በማለት ከስተፊታቸዉም ከበስተኋላቸዉም በመጡባቸው ጊዜ «ጌታችን በሻ ኖሮ መላዕክትን ባወረደ ነበር:: ስለዚህ እኛ በዚህ በእርሱ በተላካችሁት ከሓዲያን ነን።» አሉ።"},{"id":15,"translation":"15. የዓድም ነገዶችም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ፤ ከእኛ ይበልጥ በኃይል ብርቱ ማን ነው ? አሉም ያ የፈጠራቸው አላህ እርሱ በኃይል ከእነርሱ ይበልጥ የበረታ መሆኑን አያምኑምን? በታዐምራታችንም ይክዱ ነበሩ::"},{"id":16,"translation":"16. በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ልናቀምሳቸዉም በእነርሱ ላይ የሚንሻሻ ብርቱ ነፋስ መናጢዎች በሆኑ ቀናት ውስጥ ላክንባቸው:: የመጨረሻይቱም ዓለም ስቃይ በጣም አዋራጅ ነው:: እነርሱም አይረዱም::"},{"id":17,"translation":"17. ሰሙዶችማ ወደ ቀናው መንገድ መራናቸው:: እነርሱ ግን እውርነትን ከቅንነት ይልቅ መረጡ:: ይሰሩትም በነበሩት ኃጢአት አዋራጅ የሆነችው የመብረቅ ቅጣት ያዘቻቸው::"},{"id":18,"translation":"18. እነዚያንም ያመኑትንና ይጠነቀቁ የነበሩትንም አዳንናቸው::"},{"id":19,"translation":"19. የአላህም ጠላቶች ወደ እሳት የሚሰበሰቡበትን ቀን አስታውሱ:: የሚከመከሙ ሆነውም ይነዳሉ።"},{"id":20,"translation":"20. በመጧትም ጊዜ ጀሮዎቻቸው፤ ዓይኖቻቸውና ቆዳዎቻቸዉም ይሰሩት በነበረ ነገር በእነርሱ ላይ ይመሰክሩባቸዋል::"},{"id":21,"translation":"21. ለቆዳዎቻቸዉም «በእኛ ላይ ለምን መሰከራችሁብን?» ይላሉ። «ያ ሁሉን ነገር ያናገረው አላህ አናገረን:: እርሱም (ነው) በመጀመሪያ ጊዜ የፈጠራችሁ። ወደ እርሱም ብቻ ትመለሳላችሁ» ይሏቸዋል::"},{"id":22,"translation":"22. ጆሮዎቻችሁ ዓይኖቻችሁና ቆዳዎቻችሁ በእናንተ ላይ እንዳይመሰክሩባችሁ የምትደበቁባቸው አልነበራችሁም:: ግን አላህ ከምትሰሩት ብዙውን አያውቅም ብላችሁ ጠረጠራችሁ::"},{"id":23,"translation":"23. ይህም ለጌታችሁ የጠረጣችሁት ጥርጣሬያችሁ አጠፋችሁ:: ከከሳሪዎችም ሆናችሁ ይባላሉ::"},{"id":24,"translation":"24. ቢታገሱም እሳት ለእነርሱ መኖሪያቸው ናት:: ወደ ሚወዱት መመለስንም ቢጠይቁ እነርሱ ተቀባይ የሚያገኙ አይደሉም::"},{"id":25,"translation":"25. ለእነርሱም ቁራኛዎችን አዘጋጀንላቸው:: በፊታቸውን ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ለእነርሱ ሸለሙላቸው:: ከአጋንንትና ከሰዉም ከእነርሱ በፊት በእርግጥ ካለፉት ህዝቦች ጋር ሆነው ቃሉ በእነርሱ ላይ ተረጋገጠባቸው:: እነርሱ በእርግጥ ከሳሪዎች ነበሩና::"},{"id":26,"translation":"26. እነዚያም «በአላህ የካዱት ሰዎች ይህንን ቁርኣን አታዳምጡ ታሸንፉም ዘንድ ሲነበብም ተንጫጩበት።» አሉ።"},{"id":27,"translation":"27. እነዚያንም በአላህ የካዱትን ብርቱ ቅጣት እናቀምሳቸዋለን:: የእነዚያንም ይሰሩት የነበሩትን መጥፎውን ፍዳ እንመነዳቸዋለን::"},{"id":28,"translation":"28. ይህ የአላህ ጠላቶች ፍዳ እሳት ነው:: በውስጧም ለእነርሱ የዘላለም መኖሪያ አገር አላቸው:: በአንቀፆቻቸን ይክዱ በነበሩት ምንዳ ይመነዳሉ::"},{"id":29,"translation":"29. እነዚያም በአላህ የካዱት በእሳት ውስጥ ሆነው «ጌታችን ሆይ! እነዚያ ከአጋንንትና ከሰው ያሳሳቱንን አሳየን። ከታችኞች ይሆኑ ዘንድ ከጫማዎቻችን ስር እናደርጋቸዋለንና» ይላሉ::"},{"id":30,"translation":"30. እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉና ከዚያም ቀጥ ያሉ። እንዲህ እያሉ መላዕክቱ በነርሱ ላይ ይወርዳሉ: «አትፍሩ አትዘኑ:: በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላቸሁ:: በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ።"},{"id":31,"translation":"31. «እኛ በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም ረዳቶቻችሁ ነን! ለእናተም በእርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አላችሁ:: ለእናንተም በእርሷ ውስጥ የምታዙት ሁሉ አለላችሁ::"},{"id":32,"translation":"32. «መሀሪና አዛኝ ከሆነው አላህ መስተንግዶ ሲሆን» ይባላሉ።"},{"id":33,"translation":"33. ወደ አላህ ከጠራንና መልካምንም ከሰራ፤ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለው ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?"},{"id":34,"translation":"34. መልካሚቱና ክፉይቱም ጸባይ አይስተካሉም በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ጸባይ መጥፎይቱን ገፍትር፤ ያን ጊዜ ባንተና በእርሱ መካከል ጠብ ያለው ሰው እርሱ ልክ እንደ ወዳጅ ዘመድ ይሆናል::"},{"id":35,"translation":"35. ይህችንም ጸባይ እነዚያን የታገሱት እንጂ ሌላው አያገኛትም:: የትልቅም እድል ባለቤት እንጂ ማንም አያገኛትም::"},{"id":36,"translation":"36. ከሰይጣን ጉትጎታ ቢያገኝህ (ከመልካም ጸባይ ቢመልስህ) በአላህ ተጠበቅ እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና::"},{"id":37,"translation":"37. ሌሊትና ቀንም ጸሀይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው። ለጸሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፤ ለዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ:: እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደሆናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)::"},{"id":38,"translation":"38. ቢኮሩም እነዚያ በጌታህ ዘንድ ያሉት መላዕክት በቀንም በሌሊትም ለእርሱ ያወድሳሉ:: እነርሱም አይሰለቹም:: {1}","footnotes":"{1} እዚህ የቲላዋ ሱጁድ ይደረጋል።"},{"id":39,"translation":"39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ምድርን ደረቅ ሆና ማየትህም ከምልክቶቹ ነው:: በእርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ በቡቃያዎችዋ ትላወሳለች፤ ትነፋለችም። ያ ህያው ያደረጋት ጌታ በእርግጥ ሙታንንም ህያው አድራጊ ነው:: እርሱ በነገሩ ሁሉ ቻይ ነውና።"},{"id":40,"translation":"40. እነዚያ አናቅጻችንን የሚያጣምሙ በእኛ ላይ አይደበቁም:: (የሚያጣምም) በእሳት ውስጥ የሚጣለው ይበልጣልን? ወይስ በትንሳኤ ቀን ደህነኛ ሆኖ የሚመጣው? የሻችሁትን ስሩ:: ዋጋችሁን ታገላችሁ:: እርሱም (አላህ) የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::"},{"id":41,"translation":"41. እነዚያ በቁርኣን እርሱ አሸናፊው መጽሐፍ ሲሆን በመጣላቸው ጊዜ የካዱ ሁሉ ጠፊዎች ናቸው::"},{"id":42,"translation":"42. ከኋላዉም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም:: ጥበበኛ ምስጉን ከሆነው ጌታ የተወረደ ነው::"},{"id":43,"translation":"43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለነበሩት መልዕክተኞች የተባለው ቢጤ እንጂ ላንተ ሌላ አይባልም:: ጌታህ የምህረት ባለቤትና የአሳማሚ ቅጣትም ባለቤት ነው::"},{"id":44,"translation":"44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአዕጀምኛ የሆነ ቁርኣን ባረግነው ኖሮ «አናቅጹ በምናውቀው ቋንቋ አይብራሩም ኖሯልን? (ቁርኣኑ) አዕጀምኛና (መልዕክተኛው) አረባዊ ይሆናልን?» ባሉ ነበር:: እርሱ ለእነዚያ በአላህ ላመኑት ሰዎች መመሪያና መፈወሻ ነው:: እነዚያም የማያምኑት በጆሮዎቻቸው ውስጥ ድንቁርና ነው (አይሰሙትም):: እርሱ በእነርሱ ላይ እውርነት ነው:: እነዚያ ከሩቅ ስፍራ እንደሚጠሩ ናቸው::"},{"id":45,"translation":"45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው። በእርሱም ተለያዩበት። ከጌታህም ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በመካከላቸው በተፈረደ ነበር፤ እነርሱም በእርሱ አወላዋይ በሆነ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው::"},{"id":46,"translation":"46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መልካምን የሰራ ለነፍሱ ነው:: ያጠፋም በእርሷው ላይ ነው:: ጌታህም ለባሮቹ በዳይ አይደለም::"},{"id":47,"translation":"47. የትንሳኤ መከሰቻ ሰዐቱን ማወቅ ወደ እርሱ ብቻ ይመለሳል:: ከፍሬዎችም ከሽፋኖቻቸው አይወጡም ከሴትም አንዲትም አታረግዝም፤ አትወልድምም በእውቀቱ ቢሆን እንጂ:: «ተጋሪዎቼ የት ናቸው?» በማለት በሚጠራቸው ቀንም ከእኛ ውስጥ («ተጋሪ አለህ» ብሎ) ምንም መስካሪ አለመኖሩን አምነናል» ይላሉ::"},{"id":48,"translation":"48. ያም በፊት ይገዙት የነበሩት ጣዖት ከእነርሱ ይጠፋቸዋል:: ለእነርሱም ምንም መሸሻ የሌላቸው መሆኑን ያረጋግጣሉ::"},{"id":49,"translation":"49. ሰው በጎ ነገርን ከመለመን አይሰለችም:: ክፋት ቢያገኘው (ግን) ወዲያውኑ በጣም ተስፋ ቆራጭ ተበሳጭ ይሆናል::"},{"id":50,"translation":"50. ካገኘችዉም መከራ በኋላ ከእኛ የሆነን እዝነት ብናቀምሰው «ይህ ለእኔ በስራየ የተገባኝ ነው፤ ሰዓቲቱም መጪ ናት ብየ አላስብም። ወደ ጌታየ ብመለስ (እንኳ) ለእኔ እርሱ ዘንድ መልካሚቱ ገነት በእርግጥ አለችኝ» ይላል:: እነዚህም የካዱትን ስራዎቻቸውን በእርግጥ እንነግራቸዋለን:: ከበረታዉም ስቃይም በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን::"},{"id":51,"translation":"51. በሰዉም ላይ ጸጋችንን በለገስን ጊዜ ከማመስገን ይዞራል በጎኑም ይርቃል:: መከራም ባገኘው ጊዜ የብዙ ልመና ባለቤት ይሆናል::"},{"id":52,"translation":"52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው: «እስቲ ንገሩኝ ቁርኣን ከአላህ ዘንድ ቢሆንና ከዚያም በእርሱ ብትክዱ፤ ከእውነት በራቀ ጭቅጭቅ ላይ ከሆነ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማን ነው?»"},{"id":53,"translation":"53. እርሱም (ቁርኣን) እውነት መሆኑ ለእነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ በአጽናፎችና በነፍሶቻቸዉም ውስጥ ያሉትን ታዐምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን:: ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ አዋቂ መሆኑ አይበቃቸዉምን?"},{"id":54,"translation":"54. (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ! እነርሱ ከጌታቸው ጋር መገናኘትን በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ! እርሱ በነገሩ ሁሉ በእውቀቱ ከባቢ ነው::"}]},{"id":42,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ሓ፤ሚይም፤"},{"id":2,"translation":"2. ዐይን፤ ሲን፤ ቃፍ::"},{"id":3,"translation":"3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እንዳለው አሸናፊውና ጥበበኛው አላህ ወደ አንተ ያወርዳል:: ወደ እነዚያም ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ህዝቦችም አውርዷል::"},{"id":4,"translation":"4. በሰማያትና በምድር ዉስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም የበላዩ ታላቁ ነው::"},{"id":5,"translation":"5. ከአላህ ፍራቻ የተነሳ ሰማያት ከበላያቸው ሊቀደዱ ይቀርባሉ፤ መላእክትም ጌታቸውን እያመሰገኑ ያጠራሉ:: በምድር ላለው ፍጡርም ምህረትን ይለምናሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተዉሉ:: መሀሪውና አዛኙ አላህ ነው::"},{"id":6,"translation":"6. እነዚያም ከእርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች አድርገው የያዙ ሁሉ አላህ በእነርሱ ላይ ተጠባባቂ ነው:: አንተም በእነርሱ ላይ ሀላፊ አይደለህም::"},{"id":7,"translation":"7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁም የከተሞች እናት የሆነችውን የመካን ሰዎችና በአካባቢዋ ያሉትን ህዝቦች ልታስፈራራ የመሰብሰቢያውንም ቀን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ልታስጠነቅቅ በዐረበኛ ቋንቋ የሆነን ቁርኣንን ወደ አንተ አወረድን:: ከእነርሱም ከፊሉ በገነት ውስጥ ከፊሉም ደግሞ በእሳት ውስጥ ነው::"},{"id":8,"translation":"8. አላህ በፈለገ ኖሮ ሰዎችን በአንድ ሃይማኖት ላይ የሆኑ አንድ ህዝብ ባደረጋቸው ነበር:: ግን የሚፈልገውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባዋል:: በዳዮች ሁሉ ምንም ወዳጅና ረዳት የላቸዉም::"},{"id":9,"translation":"9. ከእርሱ ሌላ ረዳቶች ያዙን? (እነርሱ ረዳቶች አይደሉም) ትክክለኛ ረዳት አላህ ብቻ ነው:: እርሱ ሙታንን ህያው ያደርጋል:: እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና::"},{"id":10,"translation":"10. (ሰዎች ሆይ!) «ያ የተለያያችሁበት ነገር ሁሉ ፍርዱ ወደ አላህ ብቻ ነው:: እርሱ (አላህ) ጌታዬ ነው:: በእርሱ ላይ ተመካሁ:: ወደ እርሱም ብቻ እመለሳለሁ» በላቸው::"},{"id":11,"translation":"11. ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው አላህ ከነፍሶቻችሁ ሴቶችን ከቤት እንሰሳዎችም አይነቶችን (ወንዶችና ሴቶችን) ለእናንተ ፈጠረላችሁ:: በዚህ ድርጊቱም ያባዛችኋል:: የሚመስለው ምንም ነገር የለም:: እርሱ ሁሉን ነገር ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነው::"},{"id":12,"translation":"12. የሰማያትና የምድር (ድልቦች) መክፈቻዎች የእርሱ ብቻ ናቸው:: ሲሳይን ለሚፈልገው ሰው ያሰፋል:: ለሚፈልገዉም ያጠባል:: እርሱ ሁሉን ነገር አዋቂ ነውና::"},{"id":13,"translation":"13. (ሰዎች ሆይ!) ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑህን ያዘዘበትን ያንንም ወደ አንተ ያወረድነውን ያንንም ኢብራሂምን፤ ሙሳንና ዒሳንም በእርሱ ያዘዝንበት የሆነውን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም ላይ አትለያዩ በማለት ደነገገላችሁ::(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ አጋሪዎች ያ ወደ እርሱ የምትጠራቸው ነገር (ኢስላም) ከበዳቸው:: አላህ የሚፈልገውን ሰው ወደ እርሱ እምነት ይመርጣል:: የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል::"},{"id":14,"translation":"14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሃይማኖት ሰዎች እውቀት ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ባለ ወሰን አላፊነት እንጂ በሌላ አልተለያዩም:: እስከተወሰነ ጊዜ በማቆየት ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በእነርሱ መካከል አሁኑኑ በተፈረደ ነበር:: እነዚያም ከኋላቸው መጽሐፍን እንዲወርሱ የተደረጉት ከእርሱ በእርግጥ ባወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው::"},{"id":15,"translation":"15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እዚህ መንገድም ጋኔንንና ሰዎችን ጥራ:: ልክ እንደታዘዝከዉም ቀጥ በል:: ዝንባሌያቸውን አትከተል:: «ከመጽሐፍም አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ:: በመካከላችሁ በፍርድ ላስተካክልም ታዘዝኩ:: አላህ ጌታችን ጌታችሁም ነው:: ለእኛ ስራዎቻችን አሉን:: ለእናንተም እንዲሁ ስራዎቻችሁ አሏችሁ:: በእኛና በእናንተ መካከል ክርክር የለም:: አላህ በመካከላችን ይሰበስባል:: መመለሻው ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው::"},{"id":16,"translation":"16. እነዚያም በአላህ ሃይማኖት ተቀባይነት ካገኘ በኋላ የሚከራከሩት ሰዎች ማስረጃዎቻቸው በጌታቸው ዘንድ ብልሹ (ዉድቅ) ናቸው:: በእነርሱም ላይ የአላህ ቁጣ አለባቸው (ወደቀባቸው):: ለእነርሱም ብርቱ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":17,"translation":"17. አላህ ያ መጽሐፉን በእውነት ያወረደ ነው:: ሚዛንንም ልክ እንደዚሁ ያወረደ ነው:: ሰዓቲቱ ምን አልባት ቅርብ ብትሆንስ ምን አሳወቀህ?"},{"id":18,"translation":"18. እነዚያ በእርሷ የማያምኑት በእርሷ ያቻኩላሉ:: እነዚያ በአላህ ያመኑት ግን ከእርሷ ፈሪዎች ናቸው:: እርሷ እውነት መሆኗንም በትክክል ያውቃሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ:: እነዚያ በሰዓቲቱ የሚከራከሩ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ ከእውነት በራቀ ስህተት ውስጥ ናቸው::"},{"id":19,"translation":"19. አላህ ለባሮቹ በጣም ሩህሩህ ነው:: ለሚፈልገው ሰውም ሁሉ በሰፊው ሲሳይን ይሰጣል:: እርሱም ብርቱዉ እና አሸናፊው ነው::"},{"id":20,"translation":"20. በስራው የኋለኛይቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ ሰው ሁሉ ለእርሱ በአዝመራው ላይ ሌላን እንጨምርለታለን:: የቅርቢቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ ሰው ግን በእርሷ የተወሰነለትን ብቻ እንሰጠዋለን:: ለእርሱም በኋለኛይቱ ዓለም ምንም ድርሻ የለዉም::"},{"id":21,"translation":"21. ከሓዲያን ከአላህ ያልተፈቀደውን ሃይማኖት የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን? የፍርዱ ቃል ባልነበረ ኖሮ በመካከላቸው ወዲያውኑ በተፈረደ ነበር:: በደለኞችም አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ አለባቸው::"},{"id":22,"translation":"22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በደለኞችን በሰሩት ስራ ዋጋ በትንሳኤ ቀን ፈሪዎች ሆነው ታያቸዋለህ:: እርሱም በእነርሱ ላይ የማይቀር ወዳቂ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ ያመኑና መልካም ስራን የሰሩ ሁሉ በገነት ጨፌዎች ዉስጥ ናቸው:: ለእነርሱም በጌታቸው ዘንድ የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው:: ይህ ታላቅ ችሮታ ነው::"},{"id":23,"translation":"23. (ይህ ታላቅ ችሮታ) ያ አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትንና መልካሞችን የሰሩት ባሮቹን የሚያበስርበት ነው::(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መልዕክቴን በማድረሴ ላይ የዝምድና ውዴታየን እንጂ ሌላ ዋጋ አልጠይቃችሁም በላቸው:: መልካም ስራ የሚሰራ ሰው ሁሉ ለእርሱ በእርሷ ላይ መልካምን ነገርን እንጨምርለታለን:: አላህ መሀሪ እና አመስጋኝ ነውና::"},{"id":24,"translation":"24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም «በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈ» ይላሉን? አላህም ቢፈልግ በልብህ ላይ ያትማል:: አላህ ውሸትን ያብሳል:: እውነትንም በቃላቱ ያረጋግጣል:: እርሱ በይፋ የተነገሩት ቀርቶ በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነውና::"},{"id":25,"translation":"25. እርሱም አላህ ያ ሁልጊዜም ከባሮቹ ንስሀን የሚቀበል ኃጢአቶችንም ይቅር የሚል የምትሰሩትንም ሁሉ የሚያውቅ ጌታ ነው::"},{"id":26,"translation":"26. እነዚያም በአላህ ያመኑትና መልካም ተግባሮችን የሰሩትን ልመናቸውን ይቀበላል:: ከችሮታዉም ይጨምርላቸዋል:: ከሓዲያንም ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":27,"translation":"27. አላህም ለባሮቹ ሁሉ ሲሳይን በዘረጋ ኖሮ በምድር ውስጥ ሁሉም ወሰን ባለፉ ነበር:: ግን የሚፈልገውን በልክ ያወርዳል:: እርሱ በባሮቹ ውስጠ አዋቂ፤ ተመልካች ነውና::"},{"id":28,"translation":"28. አላህ ያ ተስፋ ከቆረጡ በኋላ ዝናብን የሚያወርድ ችሮታውንም የሚዘረጋ ነው:: እርሱም ረዳቱና ምስጉኑ ነውና::"},{"id":29,"translation":"29. ሰማያትንና ምድርን መፍጠሩ ከተንቀሳቃሽም በሁለቱ ውስጥ የበተነውን ፍጡር መፍጠሩ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ከፊሎቹ ናቸው:: እርሱም በሚፈልግ ጊዜ እነርሱን በመሰብሰብ ላይ ቻይ ነው::"},{"id":30,"translation":"30. (ሰዎች ሆይ!) ማንኛዉም መከራ (ያገኛችሁ ነገር) እጆቻችሁ በሰሩት ኃጢአት ምክንያት ብቻ ነው:: ብዙውንም ይቅር ይላል::"},{"id":31,"translation":"31. (ሰዎች ሆይ!) እናንተ በምድር ውስጥ የምትሳኑን (አምላጮች) አይደላችሁም:: ለእናንተም ከአላህ ሌላ ወዳጅም ሆነ ረዳት ምንም የላችሁም::"},{"id":32,"translation":"32. በባህር ላይ እንደ ጋራዎች ሆነው ተንሻላዮቹ መርከቦችም ከአስደናቂ ምልክቶቹ ናቸው::"},{"id":33,"translation":"33. ቢፈልግ ንፋሱን የረጋ ያደርገዋል:: ከዚያም መርከቦች በባህሩ ጀርባ ላይ የረጉ ይሆናሉ:: በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽ፤ አመስጋኝ ለሆኑ ሁሉ በእርግጥም ብዙ ተዓምራት አሉ::"},{"id":34,"translation":"34. ወይም ተሳፋሪዎች በሰሩት ኃጢአት ምክንያት እነርሱን በባህሩ በማስመጥ ያጠፋቸዋል:: ከብዙ ጥፋቶችም ይቅርታ ያደርጋል።"},{"id":35,"translation":"35. ከእነርሱ መካከል እነዚያን በአናቅጻችን የሚከራከሩትን ሰዎች ለማወቅ (ያጠፋቸዋል):: ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም መሸሻ የላቸዉም::"},{"id":36,"translation":"36. (ሰዎች ሆይ!) የተሰጣችሁት ነገር ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጠቃቀሚያ ብቻ ነው:: በአላህ ዘንድ ያለው ምንዳ ግን ለእነዚያ በትክክል በእሱ ላመኑትና በጌታቸው ላይ ብቻ ለሚመኩት ሁሉ በላጭና ሁልጊዜ ነዋሪ ነው::"},{"id":37,"translation":"37. ለእነዚያም ታላላቅ ሃጢያቶችንና ዝሙትን የሚርቁ፤ በተቆጡም ጊዜ የሚምሩ ለሆኑት፤"},{"id":38,"translation":"38. ለእነዚያም የጌታቸውን ጥሪ ለተቀበሉት፤ ሶላትንም ላዘወተሩት፤ በነገራቸው ላይም በመካከላቸው መመካከር ልምዳቸው ለሆነው፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ ለሚለግሱት፤"},{"id":39,"translation":"39. ለእነዚያም በደል በደረሰባቸው ጊዜ በመሰሉ የሚመልሱ ለሆኑት (በላጭና ነዋሪ ነው)::"},{"id":40,"translation":"40. የመጥፎ ነገሮች ሁሉ ዋጋው ተመሳሳዩ መጥፎ ነው:: ይቅር ያለና ያሳመረ ሰው ደግሞ ምንዳው በአላህ ላይ ብቻ ነው:: እርሱ በደለኞችን አይወድምና::"},{"id":41,"translation":"41. እነዚያ ከተበደሉ በኋላ በመሰሉ የተበቀሉ በእነርሱ ላይ ምንም የወቀሳ መንገድ የለባቸዉም::"},{"id":42,"translation":"42. የወቀሳ መንገዱ በእነዚያ ሰዎችን በሚበድሉት እና በምድር ውስጥም ያለ ህግ ወሰንን በሚያልፉት ሰዎች ላይ ብቻ ነው:: እነዚያ ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":43,"translation":"43. የታገሰና ምህረት ያደረገ፤ ይህ ተግባር በእጅጉን ተፈላጊ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ነው::"},{"id":44,"translation":"44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የሚያጠመውን ሰው ከእርሱ ማጥመም በኋላ ለእርሱ ምንም ወዳጅ የለዉም:: በደለኞችም ቅጣትን ባዩ ጊዜ «ለመመለስ መንገድ አለን?» የሚሉ ሲሆኑ ታያቸዋለህ::"},{"id":45,"translation":"45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከውርደት የተነሳ ፈሪዎች ሆነው በዓይን ስርቆት ወደ እሳት እያስተዋሉ በእርሷ ላይ የሚቀርቡ ሁነው ታያቸዋለህ:: እነዚያም በአላህ ያመኑት፡- «በእርግጥ ከሳሪዎች ማለት እነዚያ ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በትንሳኤ ቀን የከሰሩት ናቸው» ይላሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተዉሉ:: በደለኞች በእርግጥ ዘወታሪ ስቃይ ውስጥ ናቸው::"},{"id":46,"translation":"46. ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዷቸው ረዳቶች ምንም አልነበሯቸዉም:: አላህ የሚያጠመው ሰው ሁሉ ለእርሱ ወደ እውነት የሚመለስበት ምንም መንገድ የለዉም::"},{"id":47,"translation":"47. ያ ከአላህ ከመጣ መላሽ የሌለለው ቀን ከመምጣቱ በፊት ለጌታችሁ ታዘዙ:: በዚያ ቀን ለእናንተ ምንም መጠጊያም ሆነ መቃወም የላችሁም።"},{"id":48,"translation":"48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢዞሩም (ወቀሳ የለብህም::) በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድረገን አላክንህምና:: ባንተ ላይ ማድረስ እንጂ ሌላ የለብህም:: እኛም ሰውን ከእኛ የሆነን ጸጋ ባቀመስነው ጊዜ በእርሷ ይደሰታል:: እጆቻቸው ባስቀደሙት ኃጢአት ምክንያት መከራ ብትደርስባቸው ደግሞ ተስፋ ይቆርጣሉ:: ሰው በጣም ውለታን ከሓዲ ነውና::"},{"id":49,"translation":"49. የሰማያትና የምድር ንግስና የአላህ ብቻ ነው:: የሚፈልገውን ይፈጥራል:: ለሚፈልገው ሴቶችን ልጆች ይሰጣል:: ለሚፈልገዉም ወንዶችን ይሰጣል::"},{"id":50,"translation":"50. ወይም ወንዶችንና ሴቶችን አድርጎ ያጠናዳቸዋል:: የሚፈልገውንም መካን ያደርገዋል:: እርሱ ሁሉን አዋቂና ሁሉን ቻይ ነውና::"},{"id":51,"translation":"51. ሰውን አላህ በራዕይ ወይም ከግርዶሹ ወዲያ ወይም መልዕከተኛን በመላክና በፈቃዱ የሚፈልገውን ነገር የሚያወርድለት ቢሆን እንጂ በገሀድ ሊያናግረው ተገቢው አይደለም:: እርሱ የበላይና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":52,"translation":"52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ ወደ አንተ ከትዕዛዛችን ሲሆን ሂወት የሆነውን (ቁርአን) አወረድነው:: መጽሐፉም ሆነ እምነቱ ምን እንደሆነ የምታውቅ አልነበርክም:: ግን ቁርኣንን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው:: አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ::"},{"id":53,"translation":"53. ወደዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ወደ ሆነው ወደ አላህ መንገድ (ትመራለህ):: ሙስሊሞች ሆይ! አስተውሉ:: ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ::"}]},{"id":43,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ሓ፤ሚም፤"},{"id":2,"translation":"2. ገላጭ በሆነው መጽሐፍ እምላለሁ::"},{"id":3,"translation":"3. እኛ ታውቁ ዘንድ ቁርኣንን በዐረብኛ ቋንቋ አደረግነው::"},{"id":4,"translation":"4. እርሱም እኛ ዘንድ በመጽሐፎቹ እናት (መሰረት) ውስጥ ያለ፤ እርግጥ ከፍተኛ ማዕረግ ያለውና በጥበብ የተሞላ ነው።"},{"id":5,"translation":"5. ድንበር አላፊዎች ህዝቦች በመሆናችሁ ምክኒያት ቁርኣኑን ከማውረድ ከናንተ ማገድን እናግዳለንን? (አናግድም)::"},{"id":6,"translation":"6. በፊተኞቹም ህዝቦች ውስጥ ከነብያት መካከል ብዙን ልከናል::"},{"id":7,"translation":"7. ከነብይም አንድንም የሚመጣላቸው አልነበረም በእርሱ ይቀልዱበት (ያፌዙበት) የነበሩ ቢሆን እንጂ::"},{"id":8,"translation":"8. ከእነርሱም በሀይል ይበልጥ የበረቱትን አጥፍተናል:: የፊተኞቹም አጠፋፍ ምሳሌ አልፏል።"},{"id":9,"translation":"9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰማያትንና ምድርን ማን ፈጠራቸው?» ብለህ ብትጠይቃቸው «ያ ሁሉን አሸናፊዉና ሁሉን አዋቂው ጌታ ነው የፈጠራቸው» ይላሉ::"},{"id":10,"translation":"10. አላህ ያ ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ ያደረገላችሁ በእርሷም ውስጥ ትመሩ ዘንድ ለእናንተ መንገዶችን ያደረገላችሁ ነው::"},{"id":11,"translation":"11. ያም ከሰማይ ውሃን በልክ ያወረደላችሁ ነው። በእርሱም (በውሀው) የሞተችውን አገር ህያው አደረግን:: (ሰዎች ሆይ!) ልክ እንደዚሁ ከየመቃብሮቻችሁ ትወጣለችሁ::"},{"id":12,"translation":"12. ያም የፍጡር ዓይነቶችን ሁሉ (ጥንድ) አድርጎ የፈጠረ ለእናንተም ከመርከቦችና ከቤት እንሰሳዎች መካከል የምትጋልቧቸውን ያደረገላችሁ ነው::"},{"id":13,"translation":"13. በጀርባዎቻቸው ላይ እንድትደላደሉ ከዚያም በእርሱ ላይ በተደላደላችሁ ጊዜ የጌታችሁን ጸጋ እንድታስታውሱ፤ እንድትሉም «ይህንን የማንችለው ስንሆን ለእኛ ያገራልን ጌታ ጥራት ተገባው::"},{"id":14,"translation":"14. እኛም በእርግጥ ወደ ጌታችን አላህ ተመላሾች ነን» እንድትሉ ነው::"},{"id":15,"translation":"15. ከባሮቹም መካከል ለእርሱ ክፋይን (የተወሰነን) ብቻ አደረጉለት:: ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነውና::"},{"id":16,"translation":"16. አላህ ከሚፈጥረው ፍጡር መካከል ሴቶች ልጆችን ብቻ ለይቶ የራሱ ልጅ አድርጎ ያዘን? (ከዚያም) እናንተን በወንዶች ልጆች መረጣችሁን? (አይደለም)።"},{"id":17,"translation":"17. አንዳቸዉም ለአር-ረህማን ምሳሌ ባደረገው ነገር (በሴት ልጅ) በተበሰረ ጊዜ በቁጭት የተሞላ ሆኖ ፊቱ ጥቁር ይሆናል::"},{"id":18,"translation":"18. በጌጣጌጥ ተከልሶ እንዲያድግ የሚደረገውን ክፍል እርሱም ከደካማነቱ የተነሳ በክርክር የማያብራራውን ፍጡር ለይተው ለአላህ ያደርጋሉን?"},{"id":19,"translation":"19. እነዚያን የአር-ረሕማን ቅን ባሮች የሆኑትን መላእክትንም ሴቶች አደረጓቸው። ለመሆኑ እነርሱ መላእክት ሲፈጠሩ አብረው ነበሩን? መመስከራቸው በእርግጥ ትፃፋለች:: ስለ እርሷም ይጠየቃሉ::"},{"id":20,"translation":"20. «አር-ረሕማንም በፈለገ ኖሮ ባልተገዛናቸው ነበር» አሉ። ለእነርሱም በዚህ ምንም እውቀት የላቸዉም፤ እነርሱ የሚዋሹ ህዝቦች እንጂ ሌላ አይደሉም።"},{"id":21,"translation":"21. ከእርሱ (ቁርኣን) በፊት መጽሐፍን ሰጠናቸውና እሱን አጥብቀው የያዙ ናቸውን?"},{"id":22,"translation":"22. ከቶውንም «እኛ አባቶቻችንን (በዚሁ) ሃይማኖት ላይ አገኘናቸው:: እኛም በፈለጎቻቸው ላይ ተመሪዎች ነን» አሉ እንጂ።"},{"id":23,"translation":"23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነገሩ ልክ እንደዚህ ነው:: ከበፊትም በማንኛይቱም ከተማ ውስጥ አስፈራሪን አላክንም ቅምጥሎቿ «እኛ አባቶቻችንን (በዚሁ) ሃይማኖት ላይ አገኘን:: እኛም ፈለጎቻቸውን ተከታዩች ነን» ያሉ ቢሆኑ እንጂ::"},{"id":24,"translation":"24. አስፈራሪው «አባቶቻችሁን በእርሱ ላይ ካገኛችሁበት ይበልጥ ቀጥተኛው ሃይማኖት ባመጣላችሁም?» ቢላቸው «እኛ በተላካችሁበት ነገር (ሀይማኖት) ከሓዲያን ነን» አሉ።"},{"id":25,"translation":"25. ከእነርሱም ተበቀልን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያስተባባዮች መጨረሻ እንዴት እንደነበር ተመልከት::"},{"id":26,"translation":"26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂምም ለአባቱና ለህዝቦቹ «እኔ ከምትገዙት ጣኦታት ሁሉ ንጹህ ነኝ::"},{"id":27,"translation":"27. «ከዚያ ከፈጠረኝ በስተቀር ማንንም አልገዛም:: አላህንማ በእርግጥ ይመራኛልና ብቻውን አመልከዋለሁ» ባለ ጊዜ የነበረውን አስታውስ::"},{"id":28,"translation":"28. በዝርዮቹም ውስጥ ወደ አላህ ይመለሱ ዘንድ (በአንድ አምላክ) ማመንን ቀሪ ቃል አደረጋት::"},{"id":29,"translation":"29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁን እነዚህን ቁረይሾችንም አባቶቻቸውንም ቁርኣንንና ገላጭ መልዕክተኛ እስካመጣላቸው ድረስ አጣቀምኳቸው::"},{"id":30,"translation":"30. እውነት በመጣላቸው ጊዜም «ይህ ያመጣሀው ድግምት ነው። እኛም በእርሱ ከሓዲያን ነን።» አሉ::"},{"id":31,"translation":"31. ይህም «ቁርኣን በሁለቱ ከተሞች በአንዱ በሚኖር ታላቅ ሰው ላይ አይወርድም ኖሯልን?» አሉ።"},{"id":32,"translation":"32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ የጌታህን ስጦታ ያከፋፍላሉን? እኛ በቅርቢቱ ሕይወት እንኳን ኑሯቸውን በመካከላቸው አከፋፍለናል:: ከፊላቸዉም ከፊሉን አገልጋይ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ (በሀብት) አበለጥን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህም ጸጋ ገነት ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው::"},{"id":33,"translation":"33. ሰዎችም (በክህደት) ላይ አንድ ህዝብ የሚሆኑ ባልነበሩ ኖሮ በአል-ረህማን ለሚክዱ ሰዎች ሁሉ (በዚህች ዓለም) ለቤቶቻቸው የብር ጣራዎች፤ የሚወጣጡባቸውም የብር መሰላሎች፤ ባደረግንላቸው ነበር።"},{"id":34,"translation":"34. ለቤቶቻቸው የብር በሮች፤ ለሚደገፉባቸዉም የብር አልጋዎች፤(ባደረግንላቸው ነበር)።"},{"id":35,"translation":"35. የወርቅ ጌጥንም ባደረግንላቸው ነበር። ይህም ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጣቀሚያ እንጂ ሌላ አይደለም:: ጠፊ ነው:: መጨረሻይቱም አገር በጌታህ ዘንድ ለጥንቁቆች ብቻ ናት::"},{"id":36,"translation":"36. (በቁርኣን ከተወሳው) ከአል-ረሕማን ግሳጼ የሚደናበርም ሰው ለእርሱ ሰይጣንን እናስጠጋለን። ስለዚህ እርሱ ለእርሱ የሁልግዜ ቁራኛው ነው::"},{"id":37,"translation":"37. እነርሱም (ተደናባሪዎቹ) ሁሉ ወደ ትክክለኛው መንገድ ተመሪዎች መሆናቸውን የሚያስቡ ሲሆኑ እነርሱ (ሰይጣናት) ከቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ያግዷቸዋል::"},{"id":38,"translation":"38. (በትንሳኤ) ወደ እኛ በመጣ ጊዜ «(ቁራኛዬ ሆይ) በእኔና ባንተ መካከል የምስራቅና የምዕራብ ርቀት በኖረ ዋ ምኞቴ! ምን የከፋ ቁራኛ ነህ።» ይላል::"},{"id":39,"translation":"39. (ከሓዲያን ሆይ!) ስለ በደላችሁም ዛሬ እናንተ በቅጣት ተጋሪዎች መሆናችሁ አይጠቅማችሁም (ይባላሉ)።"},{"id":40,"translation":"40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ደንቆሮዎችን ታሰማለህን? ወይስ እውሮችንና በግልጽ ጥመት ውስጥ የሆኑ ሰዎችን ትመራለህን?"},{"id":41,"translation":"41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ቅጣታቸውን ሳታይ ብንወስድህ እኛ ከእነርሱ ተበቃዮች ነን።"},{"id":42,"translation":"42. ወይም ያንን የቀጠርናቸውን ብናሳይህ እኛ በእነርሱ ቅጣት ላይ ቻይዎች ነን::"},{"id":43,"translation":"43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ:: አንተ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና::"},{"id":44,"translation":"44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱ (ቁርኣን) ላንተም ሆነ ለህዝቦችህ ታላቅ ክብር ነው:: ወደፊተም ከርሱ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ::"},{"id":45,"translation":"45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞችም ካንተ በፊት የላክናቸው ከአር-ረሕማን ሌላ የሚገዙዋቸው የሆነን አማልክት አድርገን እንደሆነ (ተከታዮቻቸውን) ጠይቃቸው።"},{"id":46,"translation":"46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳንም በተዓምራታችን ወደ ፈርዖንና ወደ ሹማምንቶቹ በእርግጥ ላክን:: «እኔ የዓለማቱ ጌታ መልዕክተኛ ነኝ» አላቸዉም::"},{"id":47,"translation":"47. በተዓምራታችን በመጣላቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ በእርሷ ይስቃሉ::"},{"id":48,"translation":"48. ከተዓምራት አንዲትንም እናሳያቸዉም እርሷ ከብጤዋ በጣም የበለጠች ብትሆን እንጅ። ከክህደታቸው ይመለሱም ዘንድ በቅጣት ያዝናቸው::"},{"id":49,"translation":"49. አንተ ድግምተኛ ሆይ! «ጌታህን አንተ ዘንድ ቃል በገባልህ ለእኛ ለምንልን እኛ (ቅጣቱን ቢያነሳልን) ተመሪዎች ነን» አሉም::"},{"id":50,"translation":"50. ስቃዩን ከእነርሱ ላይ በገለጥንም ጊዜ ወዲያውኑ ቃልኪዳናቸውን ያፈርሳሉ::"},{"id":51,"translation":"51. ፈርዖንም በህዝቦቹ ውስጥ ተጣራ። (እንዲህ) አለም: «ህዝቦቼ ሆይ! የሚስር (ግብጽ) ግዛት የእኔ አይደለምን? እነዚህም ጅረቶች ከስሬ የሚፈሱ ሲሆኑ የእኔ አይደሉምን? አትመለከቱምን?"},{"id":52,"translation":"52. «በእውነት እኔ ከዚያ ያ እርሱ ወራዳ ጉዳዩንም በደንብ ሊገልጽ የማይችል ከሆነው ሰው በላጭ ነኝ።"},{"id":53,"translation":"53. «እርሱ ላይ የወርቅ አንባሮች ለምን አልተጣሉበትም? ወይም መላዕክት ከእርሱ ጋር ተቆራኝተው ለምን አልመጡም?» አለ።"},{"id":54,"translation":"54. ህዝቦቹንም አቄላቸው:: ታዘዙትም:: እነርሱ አመጸኞች ህዝቦች ነበሩና::"},{"id":55,"translation":"55. ባስቆጡንም ጊዜ ከእነርሱ ተበቀልን:: ሁሉንም አሰመጥናቸውም::"},{"id":56,"translation":"56. በጥፋት ቀዳሚዎችና ለኋለኞች መቀጣጫ ምሳሌም አደረግናቸው::"},{"id":57,"translation":"57. የመርየም ልጅ ዒሳ ምሳሌ በተደረገ ጊዜ ህዝቦችህ (ከሀዲያኑ) ወዲያውኑ ከእርሱ ሌሎችን ያግዳሉ።"},{"id":58,"translation":"58. «አማልክቶቻችን ይበልጣሉን? ወይስ እርሱ ይበልጣል?» አሉም:: ለክርክር እንጅ ላንተ (እርሱን) ምሳሌ አላደረጉትም:: በእውነት እነርሱ ክርክረ ብርቱ ህዝቦች ናቸው::"},{"id":59,"translation":"59. እርሱ (ዒሳ) በእርሱ ላይ የለገስንለት ለኢስራኢል ልጆችም ተዐምር ያደረግነው አገልጋይ ባሪያችን እንጂ ሌላ አይደለም::"},{"id":60,"translation":"60. ብንፈልግም ኖሮ በምድር ላይ በእናንተ ምትክ መላዕክትን ባደረግን ነበር::"},{"id":61,"translation":"61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እርሱም (ዒሳ) ለስዓቲቱ ማወቂያ በእርግጥ ምልክት ነው:: በእርሷም አትጠራጠሩ:: ተከተሉኝም:: ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» በላቸው::"},{"id":62,"translation":"62. ሰይጣንም አያግዳችሁ:: እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና::"},{"id":63,"translation":"63. ዒሳ ግልፅ ተዓምራታችንን ይዞ በመጣ ጊዜ «በእርግጥ በጥበብ መጣሁላችሁ:: የዚያንም የምትለያዩበትን ጉዳይ ከፊሉን ለእናንተ ላብራራላችሁ መጣሁ:: እናም አላህን ፍሩ:: ታዘዙኝም::"},{"id":64,"translation":"64. «አላህ ጌታዬ ጌታችሁም ነውና በብቸኝነት ተገዙት:: ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው::» አለ።"},{"id":65,"translation":"65. ከመካከላቸዉም አህዛቦቹ ተለያዩ:: ለእነዚያም ለበደሉት ህዝቦች ከአሳማሚ ቀን ቅጣት ወዮላቸው::"},{"id":66,"translation":"66. ሰዓቲቱን እነርሱ የማያውቁ ሆነው በድንገት ልትመጣባቸው እንጂ (ሌላ) ይጠባበቃሉን?::"},{"id":67,"translation":"67. አላህን የሚፈሩ ሰዎች ብቻ ሲቀሩ ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ናቸው።"},{"id":68,"translation":"68. (አላህም ለነርሱ) «ባሮቼ ሆይ! ዛሬ ቀን በእናንተ ላይ ምንም ፍርሀት የለባችሁም:: እናንተም የምታዝኑ አይደላችሁም።"},{"id":69,"translation":"69. «እነዚያ በአናቅጻችን ያመኑና ፍጹም ታዛዦች የነበሩ::"},{"id":70,"translation":"70. (ባሮቼ ሆይ!) « እናንተም ሚስቶቻችሁም ገነትን ግቡ ትደሰታላችሁ (ትከበራላችሁ)።» ይባላሉ::"},{"id":71,"translation":"71. ከወርቅ የሆኑ ሰፋፊ ዝርግ ሳህኖችና ኩባያዎች በእነርሱ ላይ እንዲዞሩ ይደረጋሉ። በእርሷም ውስጥ ነፍሶች የሚከጅሉት ዓይኖችም የሚደስቱበት ሁሉ አለ:: እናንተም በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናችሁ::"},{"id":72,"translation":"72. ይህም ያ ስትሰሩት በነበራችሁት ዋጋ የተሰጣችኋት ገነት ነው::"},{"id":73,"translation":"73. ለእናንተ በውስጧ ብዙ ፍራፍሬዎች አሏችሁና ከእርሷም እንደልባችሁ ትበላላችሁ ይባላሉ::"},{"id":74,"translation":"74. አመጸኞች በገሀነም ስቃይ ውስጥ በእርግጥ ዘወታሪዎች ናቸው::"},{"id":75,"translation":"75. ከእነርሱም ቅጣት በፍጹም አይቀለልላቸዉም:: እነርሱም በእርሱ ውስጥ ተስፋ ቆራጮች ናቸው::"},{"id":76,"translation":"76. አልበደልናቸዉም:: በዳዮቹ ግን እነርሱው ብቻ ነበሩ::"},{"id":77,"translation":"77. «ማሊክ ሆይ! ጌታህ በእኛ ላይ (በሞት) ይፍረድ።» እያሉ ይጣራሉም:: ይላቸዋልም: «እናንተ (በቅጣት ውስጥ) ለዘላለም ነዋሪዎች ናችሁ።"},{"id":78,"translation":"78. «እውነተኛውን መንገድ በእርግጥ አመጣንላችሁ:: ግን አብዛኞቻችሁ እውነትን ጠይዎች ነበራችሁ» ይባላሉ::"},{"id":79,"translation":"79. ይልቁንም (በነብዩ ላይ) በማደም ነገርን አጠነከሩን? እኛም ተንኮላቸውን ወደ እነርሱ በመመለስ አጠንካሪዎች ነን::"},{"id":80,"translation":"80. ወይም እኛ ሚስጥራቸውንና ውይይታቸውን የማንሰማ መሆናችንን ያስባሉን? ነገሩ እነርሱ እንደሚሉት አይደለም:: መልዕክተኞቻችን እነርሱ ዘንድ ናቸው:: የሚሉትን ሁሉ ይጽፋሉ::"},{"id":81,"translation":"81. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለአር-ረሕማን ልጅ (የለዉም እንጂ) ቢኖረው እኔ ለልጁ የተገዢዎች መጀመሪያ ነኝ» በላቸው::"},{"id":82,"translation":"82. የሰማያት፤ የምድርና የዙፋኑ ጌታ ከሓዲያን ስለ እሱ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ::"},{"id":83,"translation":"83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን ይስፈራሩበት የነበሩትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ በስህተታቸው ውስጥ ይዋኙ ተዋቸው :: ይጫዎቱም::"},{"id":84,"translation":"84. እርሱም ያ በሰማይ ውስጥ ሊገዙት የሚገባው በምድርም ውስጥ ሊገዙት የሚገባው ብቸኛ አምላክ ነው:: እርሱም ጥበበኛውና ሁሉን አዋቂው ነው::"},{"id":85,"translation":"85. ያም የሰማያት፤ የምድርና በመካከላቸው ያለው ሁሉ ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነው አምላክ ላቀ:: የሰዓቲቱም የመምጫዋ ዘመን ዕውቀት በእርሱ ዘንድ ብቻ ነው:: ወደ እርሱም ብቻ ትመለሳላችሁ::"},{"id":86,"translation":"86. እነዚያም ከአላህ ሌላ የሚገዟቸው አማልክት ሁሉ እነርሱ ትክክለኛውን የሚያውቁ ሆነው በእውነት ከመሰከሩት ክፍሎች በስተቀር ምልጃ አይችሉም::"},{"id":87,"translation":"87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ማን እንደ ፈጠራቸው ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይላሉ:: ታዲያ (ከትክክለኛው እምነት) ወዴት ይዞራሉ::"},{"id":88,"translation":"88. (ነብዩ) ጌታዬ ሆይ! እነዚህ የማያምኑ ህዝቦች ናቸው የማለቱም እውቀቱ አላህ ዘንድ ብቻ ነው።"},{"id":89,"translation":"89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ተዋቸው:: «ነገሬ ስላም ነው» በልም:: ወደፊትም የሚመጣባቸውን ሲደርስ ያውቃሉ::"}]},{"id":44,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ሓ፤ ሚይም፤"},{"id":2,"translation":"2. ሁሉን ነገር አብራሪ በሆነው መጽሐፍ እንምላለን::"},{"id":3,"translation":"3. እኛ ቁርኣኑን በዚያች በተባረከችው ሌሊት ውስጥ አወረድነው:: እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና::"},{"id":4,"translation":"4. በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይለያል::"},{"id":5,"translation":"5. ከእኛ ዘንድ የሆነ ትዕዛዝ ሲሆን አወረድነው:: እኛ መልዕክተኞችን ላኪዎች ነበርንና::"},{"id":6,"translation":"6. (መልዕክተኞች) ከጌታህ በሆነው ችሮታ (ተላኩ)። እነሆ እርሱ(አላህ) የሚባለዉን ሁሉ ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና::"},{"id":7,"translation":"7. የሰማያት፤ የምድር እና በመካከላቸው ያሉ ነገሮች ሁሉ ጌታ ከሆነው (ተላኩ)። የምታረጋግጡ እንደሆናችሁ (ነገሩ እንዳልነው መሆኑን እወቁ)::"},{"id":8,"translation":"8. ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም። ህያው ያደርጋል። ህይወትም ይነሳል። ጌታችሁ የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው::"},{"id":9,"translation":"9. በእውነቱ እነርሱ የሚጫወቱ ሲሆኑ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው::"},{"id":10,"translation":"10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ( ሰዎችን) የሚሸፍን በሆነ ግልጽ ጭስ ሰማይ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ::"},{"id":11,"translation":"11.ሰዎችን ይሸፍናል ይህ አሳማሚ ቅጣት ነው::"},{"id":12,"translation":"12. ጌታችን ሆይ! ክእኛ ላይ ቅጣቱን ግለጥልን:: እኛ ትክክለኛ አማኞች ነንና (ይላሉ::)"},{"id":13,"translation":"13. አስረጂ መልዕክተኛ የመጣላቸው እና በአላህ የካዱ ሲሆኑ (ቅጣቱ በወረደ ጊዜ) ለእነርሱ መገሰጽ እንዴት ይኖራቸዋል?"},{"id":14,"translation":"14. ከዚያም «ከሰው የተስተማረ እብድ ነው» ያሉ ሲሆኑ ከእርሱ ዞሩ።"},{"id":15,"translation":"15. እኛ ቅጣትን ለጥቂት ጊዜ ገላጮች ነን። እናንተ ግን ወደ ክህደታችሁ በእርግጥ አንደገና ተመላሾች ናችሁ::"},{"id":16,"translation":"16. ታላቂቱን ብርቱ አያያዝ በምንይዝበት ቀን እኛ ተበቃዮች ነን።"},{"id":17,"translation":"17. ከእነርሱ በፊት የፈርዖንን ህዝቦች በእርግጥ ሞከርን:: ክቡር መልዕክተኛም መጣላቸው::"},{"id":18,"translation":"18. «የአላህን ባሮች ወደ እኔ አድርሱ (ለኔ ስጡኝ):: እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝና።"},{"id":19,"translation":"19. «በአላህም ላይ ላትኮሩ። እኔ ግልጽ የሆነን አስረጂ ያመጣሁላችሁ ነኝና በማለት መጣላቸው።"},{"id":20,"translation":"20. «እኔ እንዳትወግሩኝ በጌታዬና በጌታችሁ ተጠብቂያለሁ።"},{"id":21,"translation":"21. «በእኔም ባታምኑ ራቁኝ። ተውኝ።» አለ::"},{"id":22,"translation":"22. «ቀጥሎም እነዚህ አመጸኞች ህዝቦች ናቸው (አጥፋቸው)።» ሲል ጌታውን ለመነ።"},{"id":23,"translation":"23. (ጌታዉም አለ) «ባሮቼንም ይዘህ በሌሊት ሂድ። እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና።"},{"id":24,"translation":"24. «ባህሩንም የተከፈተ ሆኖ ተወው፤ እነርሱ የሚሰምጡ ሰራዊት ናቸውና» አለው።"},{"id":25,"translation":"25. ከአትክልቶችና ከምንጮች ብዙ ነገሮችን ትተው ሄዱ።"},{"id":26,"translation":"26. ከአዝመራዎችም ከመልካም መቀመጫም"},{"id":27,"translation":"27. በእርሷ ተደሳቾች ከነበሩባትም ድሎት (ብዙን ነገር ትተው ሞቱ)።"},{"id":28,"translation":"28. ነገሩ ልክ እንደዚህ ሆነ፤ ለሌሎች ህዝቦች አወረስናትም።"},{"id":29,"translation":"29. ሰማይና ምድር በእነርሱ ላይ አላለቀሱም:: የሚቆዩም አልነበሩም::"},{"id":30,"translation":"30. የኢስራኢል ልጆችን ከዚያ አዋራጅ ከሆነው ስቃይ በእርግጥ አዳንናቸው::"},{"id":31,"translation":"31. ከፈርዖን እርሱ (ፈርዖውን) የኮራ ከወሰን አላፊዎችም አንዱ ነበርና::"},{"id":32,"translation":"32. ከማወቅም ጋር ከዓለም ህዝቦች መካከል በእርግጥ መረጥናቸው::"},{"id":33,"translation":"33. ከተአምራቶችም በውስጡ ግልጽ የሆነ ፈተና ያለበትን ሰጠናቸው::"},{"id":34,"translation":"34. እነዚህ (የመካ ካሓዲያን) በእርግጥ ይላሉ:"},{"id":35,"translation":"35. «እርሷ የፊተኛይቱ ሞታችን እንጅ (ሌላ) አይደለችም። እኛም የምንቀሰቀስ አይደለንም።"},{"id":36,"translation":"36. «እውነተኞችም እንደሆናችሁ አባቶቻችንን እስቲ አምጡልን።» (ይላሉ)"},{"id":37,"translation":"37. እነርሱ በላጮች ናቸውን? ወይስ የቱበዕ ህዝቦችና እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት? እነርሱን አጠፋናቸው። እነርሱ አመጸኞች ነበሩ።"},{"id":38,"translation":"38. ሰማያትና ምድርን በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ሆነን አልፈጠርንም::"},{"id":39,"translation":"39. ሁለቱንም በቁምነገር እንጂ አልፈጠርናቸዉም:: ግን አብዛሀኞቻቸው አያውቀዉም::"},{"id":40,"translation":"40. የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው::"},{"id":41,"translation":"41. ዘመድ ከዘመዱ ምንንም የማይጠቅምበት እነርሱም የማይረዱበት ቀን ነው::"},{"id":42,"translation":"42. አላህ ያዘነለትና ያመነ ብቻ ሲቀር:: (እርሱ ይረዳል) እርሱ (አላህ) ሁሉን አሸናፊና አዛኝ ነውና::"},{"id":43,"translation":"43. የዘቁም ዛፍ"},{"id":44,"translation":"44. የኃጢአተኞች ምግብ ናት::"},{"id":45,"translation":"45. እሱም ልክ እንደ ዘይት አተላ በሆዶች ውስጥ ይፈላል።"},{"id":46,"translation":"46. እንደገነፈለ ውሃ አፈላል የሚፈላ ነው::"},{"id":47,"translation":"47. ያዙትና ወደ ገሀነም መካከል (ውስጥ) በሀይል ጎትቱት (ገፍትሩት)::"},{"id":48,"translation":"48. ከዚያም በራሱ ላይ ከፈላ ውሃ ስቃይ አንቧቡበት::"},{"id":49,"translation":"49. (ይባላልም) «ቅመስ አንተ አሸናፊው፤ ክቡር የነበርክ ነህና።"},{"id":50,"translation":"50. «ይህ ያ በእርሱ ትጠራጠሩበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)::"},{"id":51,"translation":"51. ጥንቁቆች በእርግጥ በደህናማ መኖሪያ ውስጥ ናቸው::"},{"id":52,"translation":"52. በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው::"},{"id":53,"translation":"53. ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሆነው ከስስ ሐርና ከወፍራም ሐር ይለብሳሉ::"},{"id":54,"translation":"54. ነገሩ ልክ እንደዚህ ነው። ዓይናማዎች የሆኑን ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን::"},{"id":55,"translation":"55. በእርሷ ውስጥም የተማመኑ ሆነው ከፍራፍሬ ሁሉ ያዛሉ::"},{"id":56,"translation":"56. የፊተኛይቱን ሞት እንጂ ዳግመኛ በእርሷ ውስጥ ሞትን አይቀምሱም:: የገሀነምንም ቅጣት አላህ ጠብቋቸዋል።"},{"id":57,"translation":"57. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ይህም ) ከጌታህ (አላህ) የሆነ ትሩፋት ሲሆን ይህም እርሱ ታላቁ እድል ነው::"},{"id":58,"translation":"58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣኑንም በቋንቋህ ያገራነው ህዝቦች ይገነዘቡት ዘንድ ብቻ ነው::"},{"id":59,"translation":"59. ተጠባበቅ:: እነርሱም ተጠባባቂዎች ናቸውና::"}]},{"id":45,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ሓ፤ሚይም፤"},{"id":2,"translation":"2. የመጽሐፉ መወረድ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ነው::"},{"id":3,"translation":"3. በሰማያትና በምድር ውስጥ ለአማኞች ሁሉ እርግጠኛ ምልክቶች አሉ::"},{"id":4,"translation":"4. (ሰዎች ሆይ!) እናንተን በመፍጠር እና ከተንቀሳቃሽ ነገሮች በምድር ላይ የሚበተነውን ሁሉ በመፍጠሩ ለሚያረጋግጡ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተአምራት አሉ::"},{"id":5,"translation":"5. በሌሊትና በቀን መተካካትም፤ አላህ ከሰማይ ባወረደው ሲሳይ (ዝናብ) በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው በማድረጉ፤ ንፋሶችንም (በየ አቅጣጫው) በማዘዋወሩ ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ በቂ ማስረጃዎች አሉ።"},{"id":6,"translation":"6. እነዚህ ባንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው የሆኑ የአላህ ማስረጃዎች ናቸው:: ከአላህና ከማስረጃዎቹ በኋላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?"},{"id":7,"translation":"7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ውሸታም፤ ኃጢአተኛ ለሆነ ሁሉ ወዮለት (ጥፋት ተገባው)።"},{"id":8,"translation":"8. የአላህን አናቅጽ በእርሱ ላይ የሚነበቡለት ሲሆኑ ይሰማል:: ከዚያም የኮራ ሲሆን እንዳልሰማ ሆኖ በክህደቱ ላይ ይዘወትራል:: እናም እርሱን በአሳማሚ ቅጣት አብስረው::"},{"id":9,"translation":"9. ከአናቅጻችንም አንዲትን ነገር ባወቀ ጊዜ መሳለቂያ ያደርጋታል:: እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":10,"translation":"10. ከፊታቸዉም ገሀነም አለች:: የሰበሰቡት ሀብትም ከእነርሱ ላይ ምንንም አይመልስላቸዉም:: ከአላህ ሌላም ረዳቶች ያደረጓቸው ሁሉ ምንንም አይጠቅሟቸዉም:: ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":11,"translation":"11. ይህ ቁርኣን መሪ ነው:: እነዚያም በጌታቸው አናቅጽ የካዱት ሁሉ ለእነርሱ ከብርቱ ቅጣት ድርሻቸው አለባቸው።"},{"id":12,"translation":"12. አላህ ያ ባህርን በውስጡ ታንኳዎች በፈቃዱ እንዲንሻለሉበት ከችሮታዉም እንድትፈልጉበት እንድታመሰግኑትም ለእናንተ የገራላችሁ ነው።"},{"id":13,"translation":"13. ለእናንተ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ በመላ ከእርሱ ሲሆን ያገራላችሁ ነው። በዚህ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተዐምራት አሉበት።"},{"id":14,"translation":"14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያ በአላህ ላመኑት «ለእነዚያ የአላህን ቀናት ለማይፈሩት ሰዎች ምህረት (ይቅርታ) አድርጉ» በላቸው:: (አላህ) ህዝቦችን ይሰሩት በነበሩት ነገር ይመነዳልና።"},{"id":15,"translation":"15. መልካምን የሰራ ሁሉ ጥቅሙ ለነፍሱ ነው:: ክፉንም ተግባር የሰራ ሁሉ ክፋቱ በእርሱው ላይ ነው:: ከዚያም ሁላችሁም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ::"},{"id":16,"translation":"16. ለኢስራኢል ልጆችም መጽሐፍን፤ ሕግን እና ነብይነትን በእርግጥ ሰጠናቸው:: ከመልካም ሲሳዮችም ለገስንላቸው:: (በዘመናቸው ከነበሩት) የዓለማት ህዝብ ላይም አበለጥናቸው::"},{"id":17,"translation":"17. ከትዕዛዝም ግልጽ ነገሮችን ሰጠናቸው:: እውቀቱም ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ለምቀኝነት እንጅ ለሌላ አልተለያዩም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በትንሳኤ ቀን በዚያ በእርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር ሁሉ በመካከላቸው በትክክል ይፈርዳል::"},{"id":18,"translation":"18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያም ከሃይማኖት በትክክለኛው ሕግ ላይ አደረግንህ:: ስለዚህ ተከተለው:: የነዚያን የማያውቁትን ህዝቦች ዝንባሌዎች አትከተል::"},{"id":19,"translation":"19. እነርሱ ከአላህ ቅጣት ምንንም ካንተ አይገፈትሩልህምና። በደለኞችም ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው:: አላህ የጥንቁቆቹ ወዳጅ ነውና::"},{"id":20,"translation":"20. ይህ (ቁርኣን) ለሰዎች የልብ ብርሃኖች ነው:: ለሚያረጋግጡትም ህዝቦች ሁሉ መሪና እዝነት ነው::"},{"id":21,"translation":"21. እነዚያ ኃጢአቶችን የሰሩ ሕይወታቸዉንም ሞታቸዉንም ልክ እንደነዚያ እንዳመኑት መልካሞችንም እንደሰሩት ልናደርጋቸው ያስባሉን? (አይስቡ):: ይህ ከሆነ ፍርዱ ምንኛ ከፋ፤"},{"id":22,"translation":"22. አላህም ሰማያትንና ምድርን በትክክል ፈጠረ:: እነርሱ የማይበደሉ ሲሆኑ ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ ትመነዳ ዘንድ።"},{"id":23,"translation":"23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ዝንባሌውን አምላኩ ያደረገውን አላህም ከእውቀት ጋር ያጠመመውን በጆሮውና በልቡም ላይ ያተመበትን በዓይኑም ላይ ሺፋን ያደረገበትን ሰው አየህን? ታዲያ ከአላህ በኋላ የሚያቀናው ማነው? አትገሰጹምን?"},{"id":24,"translation":"24. (ከሓዲያን) «እርሷም(ሕይወት) የቅርቢቱ ሕይወታችን ብቻ እንጂ ሌላ አይደለችም:: እንሞታለን:: ህያዉም እንሆናለን:: ከጊዜም (ማለፍ) በሰተቀር ሌላ አያጠፋንም» አሉ:: ለእነርሱም በዚህ በሚሉት ምንም እውቀት የላቸዉም:: እነርሱ የሚጠራጠሩ እንጂ ሌላ አይደሉም::"},{"id":25,"translation":"25. አናቅጻችንም ግልፆች ሆነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ የክርክራቸው ማስረጃ «እውነተኞች እንደሆናችሁ እስቲ የቀድሞ አባቶቻችንን አምጡ» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም።"},{"id":26,"translation":"26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ህያው ያደርጋችኋል ከዚያም ያሞታችኋልም:: ከዚያም በትንሳኤ ቀን ይሰበስባችኋል:: ይህም ጥርጥር የለበትም:: ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም።» በላቸው::"},{"id":27,"translation":"27. የሰማያትና የምድር ግዛት የአላህ ብቻ ነው:: ሰዓቲቱም በምትከሰትበት ቀን ያን ጊዜ አጥፊዎች ሁሉ ይከስራሉ::"},{"id":28,"translation":"28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ህዝቦችን ሁሉ ተንበርካኪ ሆነው ታያቸዋለህ:: ህዝብም ሁሉ ወደ ግል መጽሐፋቸው ይጠራሉ:: ይባላሉም: «ዛሬ ቀደም ሲል ትሰሩት የነበራችሁትን ነገር ትመነዳላችሁ"},{"id":29,"translation":"29. «ይህ መጽሐፋችን ነው:: በእናንተ ላይ በእውነት ይናገራል:: እኛ ያንን ትሰሩት የነበራችሁትን ሁሉ እናስገለብጥ ነበርንና» (ይባላሉ)::"},{"id":30,"translation":"30. እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩትማ ጌታቸው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባቸዋል:: ይህ እርሱ ግልጽ የሆነ እድልን ማግኘት ነው::"},{"id":31,"translation":"31. እነዚያም የካዱትማ ለእነርሱ ይባላሉ: «አናቅጾቼ በእናንተ ላይ ይነበቡ አልነበሩምን? ኮራችሁም :: ከሓዲያን ህዝቦችም ነበራችሁ::"},{"id":32,"translation":"32. «የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው:: በእርሷ መምጣት (ጥርጥር) የለም:: በተባለ ጊዜም 'ሰዓቲቱ ምን እንደሆነች አናውቅም መጠራጠርን የምንጠራጠር እንጂ ሌላ አይደለንም:: እኛም አረጋጋጮች አይደለንም' አላችሁ::» (ይባላሉ)"},{"id":33,"translation":"33. የሰሩዋቸው ኃጢአቶችም ለእነርሱ ይገለጹላቸዋል:: ያም በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት በእነርሱ ላይ ይወርድባቸዋል::"},{"id":34,"translation":"34. «በዱንያ የዚህንም ቀናችሁን መገናኘት እንደረሳችሁ ሁሉ ዛሬ እኛም እንተዋችኋለን:: መኖሪያችሁም እሳት ናት:: ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም» ይባላል።"},{"id":35,"translation":"35. «ይህ እናንተ የአላህን አናቅጽ መቀላጃ በማድረጋችሁና ቅርቢቱ ሕይወት ስለ አታለለቻችሁ ነው» ይባላሉ:: ዛሬ ከእርሷ አይወጡም:: እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም::"},{"id":36,"translation":"36. ምስጋና ሁሉ ለሰማያት፤ ለምድርና ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ የተገባው ነው::"},{"id":37,"translation":"37. ኩራትም በሰማያትም ሆነ በምድር ለእርሱ ብቻ ነው:: እርሱ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::"}]},{"id":46,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ሓ፤ ሚይም፤"},{"id":2,"translation":"2. የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ፤ ጥበበኛ ከሆነው አላህ ነው::"},{"id":3,"translation":"3. ሰማያትን፤ ምድርን እና በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በምር እና በተወሰነ ጊዜንም በመለካት እንጂ ለቀልድ አልፈጠርናቸዉም። እነዚያ በአላህ የካዱት የተስፈራሩትን ነገር ደንታ አይሰጡትም።"},{"id":4,"translation":"4. (መልዕክተኛችንሙሐመድ ሆይ!) «ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አላያችሁምን? ከምድር ምንን እንደፈጠሩ እስቲ አሳዩኝ:: ወይስ በሰማያት መፍጠር ለእነርሱ ከአላህ ጋር መጋራት አላቸውን? (ያማልዱናል በማለታችሁ) እውነተኞች እንደሆናችሁ ይህንን ጉዳይ ከዚህ በፊት የሆነን መጽሐፍ ወይም ከእውቀት ቅሪት እስቲ አምጡልኝ» በላቸው::"},{"id":5,"translation":"5. እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልሱለትን ጣዖታት ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማንነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው::"},{"id":6,"translation":"6. ሰዎችም በተሰበሰቡ ጊዜ ጣኦቶቹ ለእነርሱ ጠላቶች ይሆናሉ:: እነርሱን መገዛታቸውንም ይክዳሉ::"},{"id":7,"translation":"7. በእነርሱም ላይ አንቀፆቻችን ግልፆች ሆነው በተነበቡ ጊዜ እነዚያ እውነቱ በመጣላቸው ጊዜ የካዱት ክፍሎች «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ።"},{"id":8,"translation":"8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም «(ሙሐመድ ራሱ) ቀጠፈው» ይላሉን? «ብቀጥፈው ኖሮ እኔን ከአላህ ቅጣት ለማዳን በምንም አትችሉም:: እርሱ ያንን የምትቀባዥሩበትን ነገር ሁሉ አዋቂ ነው:: በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪነት እሱው በቃ:: እርሱ መሀሪ እና አዛኝ ነውና» በላቸው።"},{"id":9,"translation":"9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞች የተለየሁ ብጤ የሌለኝ አይደለሁም:: በእኔም በእናንተም ላይ ምን እንደሚሰራብንም አላውቅም:: ወደ እኔ የሚወረደውን እንጂ ሌላን መመሪያ አልከተልም:: እኔም ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም» በላቸው::"},{"id":10,"translation":"10. «(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እስቲ ንገሩኝ ቁርኣኑ ከአላህ ዘንድ ቢሆንና በእርሱ ብትክዱ ከኢስራኢል ልጆች የሆነ መስካሪ ደግሞ በቢጤው ቢያምንና በእርሱ ላይ ቢመሰክር እናንተ (ግን) ብትኮሩ (በዳይ አትሆኑምን)? አላህ በእርግጥ በደለኛ ህዝቦችን ሁሉ አያቀናም» በላቸው።"},{"id":11,"translation":"11. እነዚያም የካዱት ሰዎች ስላመኑት ሰዎች «እምነቱ መልካም ነገር በሆነ ኖሮ ወደ እርሱ ባልቀደሙን ነበር» አሉ:: በእርሱም ባልተቀኑ ጊዜ «ይህ ቁርኣን ጥንታዊ ቅጥፈት ነው» ይላሉ::"},{"id":12,"translation":"12. ከፊቱም የሙሳን መጽሐፍ ለሰዎች መሪና የአላህ ጸጋ ሲሆን እንዳወረድን አላየህምን? ይህ ቁርኣን እነዚያን የበደሉትን ሊያስፈራራ በዐረብኛ ቋንቋ የወረደ ሲሆን የፊቶቹንም መጽሐፍት አረጋጋጭ እና ለበጎ አድራጊዎችም ሁሉ የብስራት መጽሐፍ ነው::"},{"id":13,"translation":"13. «እነዚያ ጌታችን አላህ ነው» ያሉና ከዚያም በዚሁ ቃላቸው ላይ ቀጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በእነርሱ ላይ ምንም (ይደርስብናል ብለው) ፍርሀት የለባቸዉም:: ምንም (ነገር ያመልጠናል ብለው) አያዝኑምም::"},{"id":14,"translation":"14. እነዚያ የገነት ጓዶች ናቸው:: በእርሷ ውስጥ ዘወታሪዎች ሲሆኑ በዚያ በዱንያ ይሰሩት በነበሩት መልካም ተግባር ምክንያት ያገኙት ምንዳ ነው።"},{"id":15,"translation":"15. የሰውን ልጅ ለወላጆቹ በጎ መዋል እንዳለበት በጥብቅ አዘዝነው:: እናቱ በችግር ላይ ሆና አረገዘችው:: በችግርም ላይ ሆና ወለደችው:: እርግዝናውና (ከጡት) መለያው ሙሉ ሰላሳ ወር ነው:: ከዚያም የጥንካሬውን ወቅት በደረሰ ጊዜ አርባ ዓመት በደረሰ ጊዜ «ጌታዬ ሆይ! ያን በእኔ ላይና በወላጆቼ ላይ የለገስከዉን ጸጋህን እንዳመሰግንህና የምትወደውን መልካም ስራም እንድሰራ ወደ ቀናው መንገድ ምራኝ:: ዘሮቼንም ለእኔ አብጅልኝ:: እኔ ወደ አንተ ብቻ ተመለስኩ:: እኔ ከሙስሊሞች አንዱ ነኝ» አለ::"},{"id":16,"translation":"16. እነዚያ (ይህንን ባዩች ሁሉ) ከገነት ጓዶች መካከል ሲሆኑ እነዚያ ከሰሩት ስራ መልካሙን የምንቀበላቸውና ከኃጢአቶቻቸዉም የምናልፋቸው ሰዎች ናቸው:: ያንን ተስፋ ይሰጡት የነበሩትን እውነተኛ ቀጠሮ እንሞላላቸዋለን::"},{"id":17,"translation":"17. ያንንም ለሁለቱ ወላጆቹ አላህን የሚለምኑ ሲሆኑ «በአላህ እመን፤ የአላህ ቀጠሮ እርግጠኛ ነው፤» ሲሉት «ኡፍ! ከእኔ በፊት የብዙ ክፈለ ዘመናት ሰዎች ሳይወጡ በእርግጥ ያለፉ ሲሆኑ ከመቃብር እንደምወጣ ታስፈራሩኛላችሁን?» ይላልም: \"ይህ የቀደምቶች ተረት እንጅ ሌላ አይደለም\" ይላል።"},{"id":18,"translation":"18. እነዚህ እነዚያ ከአጋንንትም ከሰዉም ከእነርሱ በፊት ካለፉት ህዝቦች ጋር የአላህ ቃሉ በእነርሱ ላይ የተረጋገጠባቸው ናቸው:: እነርሱ ከሳሪዎች ነበሩና::"},{"id":19,"translation":"19. ለሁሉም በሰሩት ስራ ልክ ተገቢ የሆኑ ደረጃዎች አሏቸው:: ስራዎቻቸውንም ይሞላላቸው ዘንድ ይህንን መነዳቸው:: እነርሱም አይበደሉም::"},{"id":20,"translation":"20. እነዚያም የካዱት በእሳት ላይ በሚጋፈጡበት ቀን ጣፋጮቻችሁን በአነስተኛይቱ ሕይወታችሁ አሳለፋችሁ:: በእርሷም ተጣቀማችሁ። ስለዚህ በምድር ላይ ያለ አግባብ ትኮሩ በነበራችሁትና ታምጹ በነበራችሁት ምክኒያት ዛሬ የውርደትን ቅጣት ትመነዳላችሁ ይባላሉ፡"},{"id":21,"translation":"21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአል አሕቃፍ የነበረው የዓድ ወንድም የሆነው ሁድ ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ በኋላም አስፈራሪዎች ባለፉት መልኩ «ከአላህ ውጪ ሌሎች አማልክትን አታምልኩ:: የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ።» በሚል ሲያስጠነቅቃቸው (የነበረውን አስታውስ)"},{"id":22,"translation":"22. «ከአማልክቶቻችን ልታሸሸን መጣህን? እውነተኛ ከሆንክ ያንን የምታስፈራራን ቅጣት አሁን እንዲከሰት አድርግ» አሉት።"},{"id":23,"translation":"23. «የቅጣቱ መከሰቻ ትክከለኛ ወቅት እውቀት ያለው ከአላህ ዘንድ ብቻ ነው:: የተላኩበትን መልዕክት ብቻ አደርስላችኋለሁ:: ግና እንደማያችሁ መሀይማን ህዝቦች ናችሁ።» አላቸው::"},{"id":24,"translation":"24. ለቅጣት የተላከባቸውን (ዳመና) ወደ ሸለቆዎቻቸው አቅጣጫ ሲጓዝ ባዩ ጊዜ «ይህ ዝናብ የሚያወርድልን ዳመና ነው» አሉ:: አይደለም። ይልቁንም ያ በፍጥነት ይከሰት ዘንድ የጠየቃችሁት ቅጣት ነው:: አሳማሚ ቅጣት ያዘለ ንፋስ ነው።"},{"id":25,"translation":"25. በጌታዋ ትዕዛዝ ሁሉን ነገር ታጠፋለች» (አላቸው)፡፡ ባዶ ቤቶቻቸው እንጂ ሌላ ነገር የማይታይ ሆነው አነጉ:: አመጸኞች ህዝቦችን በዚህ መልኩ እንቀጣለን::"},{"id":26,"translation":"26. ለእናንተ ያልሰጠነውን ኃይልና ምቾት ለእነርሱ ሰጥተናል:: መሰሚያ ጆሮዎችን፤ መመልከቻ ዓይኖችን እና ማሰቢያ አእምሮንም ለግሰናቸዋል:: ግና ጆሮዎቻቸዉም፤ ዓይኖቻቸዉም፤ አእምሮዎቻቸዉም የፈየዷቸው ነገር አልነበረም:: የአላህን አናቅጽ ያስተባብሉ ነበርና:: በመሆኑም በእነርሱ ላይ ያ ያፌዙበት በነበረው ቅጣት ወረደባቸው::"},{"id":27,"translation":"27. በዙሪያችሁ የነበሩ ከተሞችንም አጠፋን:: ይመለሱ ዘንድም ተደጋጋሚ ታዐምራትን አሳይተናቸው ነበር::"},{"id":28,"translation":"28. እነዚያ መቃረቢያ ይሆናቸው ዘንድ ከአላህ ሌላ በረዳትነት የያዟቸው አማልክት በመከራቸው ወቅት ለምን አልረዷቸዉም? ይልቁንም ከእነርሱ ራቁ:: ይህ ሀሰታቸውና ይቀጥፉት የነበረው ነውና::"},{"id":29,"translation":"29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአጋንንት የሆኑ ቡድኖች ቁርኣንን የሚያደምጡ ሁነው በላክንልህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ሲነበብ በደረሱ ጊዜ «ዝም በሉ» ተባባሉ:: ንባቡ ሲጠናቀቅም ወገኖቻቸውን ለማስጠንቀቅ ወደ ህዝቦቻቸው ተመለሱ::"},{"id":30,"translation":"30. አሉም ለወገኖቻቸው: «ወገኖቻችን ሆይ! ከሙሳ ተውራት በኋላ የተወረደንና ከእርሱ በፊት የወረዱትን መጽሐፍት አጽዳቂ ወደ እውነትና ወደ ቀጥተኛው ጎዳና መሪም የሆነን መጽሐፍ አደመጥን::"},{"id":31,"translation":"31. «ወገኖቻችን ሆይ! ለዚህ ወደ አላህ ለሚጠራችሁ ሰው በጎ ምላሽ ስጡ:: በእርሱ እመኑም:: ይህን ካረጋችሁ (አላህ) ከኀጢአቶቻችሁ ለእናንተ ይምራልና፡፡ ከአሳማሚ ቅጣትም ይጠብቃችኋል::"},{"id":32,"translation":"32. ወደ አላህ ለሚጠራ ሰው ሁሉ በጎ ምላሽ ያልሰጠ በምድር ላይ ከአላህ ቅጣት አያመልጥም:: ከእርሱ ሌላም ረዳት አይኖረዉም:: እንዲህ አይነት ሰዎች ግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው::» (አሉ)"},{"id":33,"translation":"33. ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው እርሱም በመፍጠሩም ድካም ያልተሰማው አላህ ሙታንን ህያው ማድረግ እንደሚችል አላዩምን ? በእርግጥም ይህን ማድረግ የሚሳነው አይደለም :: እርሱ ሁሉንም ነገር ቻይ ነውና::"},{"id":34,"translation":"34. እነዚያም የካዱት ሰዎች ሁሉ ወደ እሳት እንዲቀርቡ በሚደረጉ ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ። «ይህ እውነት አይደለምን ?» ይባላሉ :: «አዎ እውነት መሆኑን በጌታችን በመማል እናረጋግጣለን» ይላሉ:: እርሱም «ታስተባብሉት በነበራችሁት ሰበብ ቅጣትን ቅመሱ» ይላቸዋል::"},{"id":35,"translation":"35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞች መካከል የጽናት ባለቤቶች እንደታገሱት ሁሉ አንተም ታገስ::(በህዝቦችህ ላይ) ቅጣቱ ይፋጠንባቸው ዘንድም አትጠይቅ:: ያን ቃል የተገባላቸውን ቅጣት በሚያዩ ጊዜ ምድር ላይ ከቀን ውስጥ የተወሰነ ወቅት ብቻ እንጂ እንዳልቆዩ ይሰማቸዋል:: ይህ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ነው:: ከአመጸኞች ህዝቦች ውጪ ሌሎች እንዲጠፉ ይደረጋልን?"}]},{"id":47,"verses":[{"id":1,"translation":"1. እነዚያ የካዱ እና ከአላህ መንገድ ሌሎችን የከለከሉ አላህ ስራዎቻቸውን አጠፋባቸው::"},{"id":2,"translation":"2. እነዚያም ያመኑ በጎዎችንም ተግባራት የሰሩ በሙሐመድ ላይም የተወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲሆን እውነት ስለሆነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያብሳል:: ሁኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል::"},{"id":3,"translation":"3.ይህ እነዚያ የካዱት ውሸትን የተከተሉ በመሆናቸውና እነዚያም ያመኑት ከጌታቸው የሆነን እውነት ስለተከተሉ ነው:: ልክ እንደዚሁ አላህ ለሰዎች ምሳሌዎቻቸውን ያብራራል።"},{"id":4,"translation":"4. አማኞች ሆይ! እነዚያንም የካዱትን ሰዎች በጦር ላይ ባገኛችኋቸው ጊዜ ጫንቃዎችን በሀይል ምቱ:: ባደከማችኋቸው ጊዜም አትግደሏቸው፤ ማርኳቸው:: መሳሪያውንም አጥብቁ:: በኋላም በነጻ ትለቋቸዋላችሁ:: ወይም ፊዳ ታስከፍሏቸዋላችሁ:: ይህም ጦሩ መሳሪያዉን እስከሚጥል ድረስ ነው:: ነገሩ ይህ ነው:: አላህም ቢፈልግ ከእነርሱ ያለ ጦር በተበቀለ ነበር ግን ከፊላችሁን በከፊሉ ሊሞክር (በዚህ አዘዛችሁ)። እነዚያንም በአላህ መንገድ ላይ የተገደሉት ሰዎች ስራዎቻቸውን ፈጽሞ አያጠፋባቸዉም::"},{"id":5,"translation":"5. በእርግጥ ይመራቸዋል:: ሁኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል::"},{"id":6,"translation":"6. ገነትንም ያገባቸዋል፡፡ ለእነርሱ አስታውቋታል፡፡"},{"id":7,"translation":"7. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የአላህን ሃይማኖት ብትረዱ ይረዳችኋል:: ጫማዎቻችሁንም ያደላድላል።ያጸናላችኋል።"},{"id":8,"translation":"8. እነዚያም የካዱት ለእነርሱ ጥፋት ተገባቸው:: ስራዎቻቸውንም አጠፋባቸው።"},{"id":9,"translation":"9. ይህ እነርሱ አላህ ያወረደውን ስለጠሉ ነው:: ስለዚህ ስራዎቻቸውን አበላሸባቸው::"},{"id":10,"translation":"10. የእነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩ ከሓዲያን ሁሉ መጨረሻ እንዴት እንደነበር ያዩ ዘንድ በምድር ላይ አልሄዱምን? አላህ ያላቸውን ሁሉ አጠፋባቸው። ለካሓዲያንም ሁሉ የዚሁ ተመሳሳይ አለባቸው።"},{"id":11,"translation":"11. ይህ አላህ የእነዚያ ያመኑት ረዳት ስለሆነና ከሓዲያንም ለእነርሱ ረዳት ስሌላቸው ነው::"},{"id":12,"translation":"12. አላህ እነዚያን በእሱ ያመኑትንና መልካሞችን ተግባራት የሰሩትን ሁሉ ከስሮቻቸው ወንዞች ወደ ሚፈሱባቸው ገነቶች ያስገባቸዋል:: እነዚያም በአላህ የካዱት በቅርቢቱ ዓለም ብቻ ይጣቀማሉ። እንሰሳዎች እንደሚበሉም ይበላሉ:: የገሀነም እሳትም ለእነርሱ (የሁል ጊዜ) መኖሪያቸው ናት::"},{"id":13,"translation":"13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያች አንተን ካወጣችህ ከተማህ ይበልጥ በሀይል ጠንካራ የሆኑ ባለቤቶቻቸዉን ያጠፋናቸው ብዙ ናቸው:: ለእነርሱም ረዳት አልነበራቸዉም::"},{"id":14,"translation":"14. ከጌታው በሆነች አስረጅ ላይ የሆነ ምዕመን ክፉ ስራቸው ለእነርሱ እንደተሸለመላቸውና ዝንባሌዎቻቸውን እንደ ተከተሉ ክፍሎች ነውን?"},{"id":15,"translation":"15. ያች አላህን ለሚፈሩ ሰዎች ቃል የተገባችው ገነት (ይህን ትመስላለች)፤ በውስጧ ሽታው ከማይለወጥ የውሃ ወንዞች፤ ጣዕሙ የማይለወጥ የወተት ወንዞች፤ ለጠጪዎች ሁሉ እጅግ ጣፋጭ የሆኑ የወይን ጠጅ ወንዞችና የንጹህ(የተነጠረ) ማር ወንዞች አሉባት:: በውስጧ ሁሉም የፍራፍሬ አይነቶች ከጌታቸዉም ምህረት ተዘጋጅተውላቸዋል:: በእነዚህ ገነቶች የሆነ እንደነዚያ እሳት ውስጥ ዘወትር እንደሚኖሩ የፈላ ውሃም እንዲጠጡ እንደሚደረጉትና ውሃዉም የሆድ ዕቃቸውን እንደሚበጣጥስባቸው ነውን? አይደለም።"},{"id":16,"translation":"16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም መካከል ወደ አንተ የሚያዳምጡ አሉ:: ካንተ ዘንድ በወጡ ጊዜ ለእነዚያ እውቀት ለተሰጡት «አሁን ምን አለ?» ይላሉ:: እነዚያ እነዚህ በልቦቻቸው ላይ አላህ ያተማቸው ዝንባሌዎቻቸውን የተከተሉ ናቸው::"},{"id":17,"translation":"17. እነዚያም ወደ ቀናው መንገድ የተመሩት አላህ መመራትን ጨመረላቸው:: (ከእሳት) መጠበቂያቸውንም ሰጣቸው::"},{"id":18,"translation":"18. የሰዓቲቱንም በድንገት መምጣት እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? ምልክቶቿም በእርግጥ መጥተዋል:: በመጣችባቸዉም ጊዜ ማስታወሳቸው ለእነርሱ እንዴት ይጠቅማቸዋል::"},{"id":19,"translation":"19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነሆ ከአላህ ሌላ ትክክለኛ አምላክ አለመኖሩንም እወቅ:: ስለ ስህተትህም ሆነ ለወንድም ለሴትም አማኞች ስህተት ምህረትን ለምን:: አላህም መዘዋወሪያችሁንም ሆነ መርጊያችሁን ያውቃል::"},{"id":20,"translation":"20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ያመኑት ሰዎች (ለዲን ለመታገል ግፊት ያለበት)« የቁርኣን ምዕራፍ አይወረድም ኖሯልን?» ይላሉ:: የጠነከረም ምዕራፍ በወረደና በውስጡም መጋደል በተወሳ ጊዜ እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ የንፍቅና በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ከሞት የሆነ መከራ በእርሱ ላይ እንደወደቀበት ሰው አስተያያት ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ:: ለእነርሱው ተገባቸው።"},{"id":21,"translation":"21. ታዛዥነትና መልካም ንግግር ይሻላቸዋል:: ትዕዛዙም ቁርጥ በሆነ ጊዜ ለአላህ ትእዛዝ እውነተኞች በሆኑ ኖሮ ለእነርሱ የተሻለ በሆነ ነበር::"},{"id":22,"translation":"22. ብትሾሙም በምድር ላይ ማበላሸትን ዝምድናችሁንም መቁረጥን ከጀላችሁን?"},{"id":23,"translation":"23. እነዚህ እነዚያ አላህ የረገማቸው ያደነቆራቸዉም ዓይኖቻቸውንም ያወራቸው ናቸው።"},{"id":24,"translation":"24. ቁርኣንንም አያስተነትኑምን? በእውነቱ በልቦቻቸው ላይ ቁልፎቿ አሉባቸውን?"},{"id":25,"translation":"25. እነዚያ ለእነርሱ ቅኑው መንገድ ከተብራራላቸው በኋላ ወደ ኋላቸው የተመለሱት ሰይጣን መቀልበሳቸውን ለእነርሱ ሸለመላቸው:: ለእነርሱም አዘናጋቸው።"},{"id":26,"translation":"26. ይህ እነርሱ ለእነዚያ አላህ ያወረደውን ለጠሉት «በነገሩ ከፊሉን እንታዘዛችኃለን» ያሉ በመሆናቸው ነው:: አላህም መደበቂያቸውንም ያውቃል::"},{"id":27,"translation":"27. መላዕክት ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን የሚመቱ ሲሆኑ በገደሏቸው ጊዜ (ሁኔታቸው እንዴት ይሆናል?)"},{"id":28,"translation":"28. ይህ እነርሱ አላህን ያስቆጣውን ነገር ሁሉ ስለተከተሉ ውዴታውንም ስለጠሉ ነው:: ስለዚህ ስራዎቻቸውን አበላሸባቸው::"},{"id":29,"translation":"29. እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ሰዎች በሙስሊሞች ላይ የነበራቸዉን ቂሞቻቸውን አላህ አለማውጣቱን ጠረጠሩን?"},{"id":30,"translation":"30. (ሙሐመድ ሆይ!) ብንፈልግ ኖሮ እነርሱን ባሳየንህና በምልክታቸዉም በእርግጥ ባወቅካቸው ነበር:: ንግግርንም በማሸሞራቸው በእርግጥ ታውቃቸዋለህ:: አላህም ስራዎቻችሁን ሁሉ ያውቃልና::"},{"id":31,"translation":"31. (አማኞች ሆይ!) ከናንተ መካከል ተዋጊዎችንና ታጋሾቹን እስከምንገልጽ ድረስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን:: ወሬዎቻችሁንም (እስከምንገልጽ ድረስ) እንሞክራችኋለን::"},{"id":32,"translation":"32. እነዚያ የካዱና ከአላህም መንገድ ሰዎችን ያገዱ ለእነርሱም ቅኑ መንገድ ከተገለጸላቸው በኋላ መልዕክተኛውን የተከራከሩ ሁሉ አላህን በምንም አይጎዱትም:: ስራዎቻቸውንም በእርግጥ ያበላሻል::"},{"id":33,"translation":"33. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ:: መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: ስራዎቻችሁንም አታበላሹ::"},{"id":34,"translation":"34. እነዚያ የካዱ ከአላህ መንገድ ሌሎችን ያገዱና ከዚያም እነርሱ ከሓዲያን ሆነው የሞቱ አላህ ለእነርሱ በፍጹም አይምርም::"},{"id":35,"translation":"35. እናንተ አሸናፊዎች ስትሆኑና አላህም ከናንተ ጋር ሲሆን አትድከሙ:: ወደ እርቅም አትጥሩ:: ስራዎቻችሁን ፈጽሞ አያጎድልባችሁም::"},{"id":36,"translation":"36. ቅርቢቱ ሕይወት ጫወታና ዛዛታ ብቻ ናት:: ብታምኑና ቅጣቱንም ብትጠነቀቁ ምንዳዎቻችሁን ይሰጣችኋል:: ገንዘቦቻችሁንም ሁሉ አይጠይቃችሁም::"},{"id":37,"translation":"37. እርሷን ቢጠይቃችሁና ችክ ቢልባችሁ ትሰስታላችሁ:: ቂሞቻችሁንም ያወጣል::"},{"id":38,"translation":"38. (አማኞች ሆይ!) አስተውሉ:: እናንተ እነዚያ በአላህ መንገድ ትለግሱ ዘንድ የምትጠሩ ናችሁ:: ከናንተም መካከልም የሚሰስት ሰው አለ:: የሚሰስት ሰው ሁሉ የሚሰስተው በራሱ ላይ ብቻ ነው:: አላህ በራሱ ተብቃቂ ነውና:: እናንተ ግን ድሆች ናችሁ:: ብትሸሹም ሌሎችን ሀዝቦች በቦታችሁ ይለውጣል:: ከዚያም ባለመታዘዝ እንደናንተ ብጤዎቻችሁ አይሆኑም::"}]},{"id":48,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ላንተ (መካን) በመክፈት ግልጽ የሆነን ድል ለገስንህ።"},{"id":2,"translation":"2. አላህ ያለፈውንና የሚመጣውን ኃጢአትክን ሊምርህ፤ ፀጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላና ቀጥተኛዉን መንገድ ሊመራህ፤"},{"id":3,"translation":"3. አላህም ብርቱን እርዳታ ሊረዳህ መካን ከፈተልህ::"},{"id":4,"translation":"4. አላህ ያ በአማኞች ልቦች ውስጥ ከእምነታቸው ጋር እምነትን ይጨምሩ ዘንድ እርጋታን ያወረደ ነው:: አላህ የሰማይና የምድር ስራዊት ሁሉ የሱ ብቻ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::"},{"id":5,"translation":"5. ወንድ አማኞችና ሴት ምዕመናትን በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ ሊያስገባቸው፤ ከነርሱም ሐጢያቶቻቸዉን ሊያብስላቸው (መካን ከፈተልህ):: ይህም ከአላህ ዘንድ የሆነ ታላቅ መታደል ነው::"},{"id":6,"translation":"6. በአላህም ክፉ ጥርጣሬን ወንድ ተጣራጣሪ አስመሳዮችንና ሴት አስመሳዮችን ወንድ አጋሪዎችና ሴት አጋሪዎችን ያሰቃይም ዘንድ (በትግል አዘዘ):: በእነርሱ ላይ ክፉ ከባቢ አለባቸው:: በእነርሱ ላይ አላህ ተቆጣባቸው ረገማቸዉም:: ለእነርሱ ገሀነምን አዘጋጀላቸው:: ገሀነም መመለሻነቷም ከፋች::"},{"id":7,"translation":"7. ለአላህ የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አሉት:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::"},{"id":8,"translation":"8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ መስካሪ፤ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን በእርግጥ ላክንህ::"},{"id":9,"translation":"9. በአላህ ልታምኑ። በመልዕክተኛዉም ልታምኑ፤ ልትረዱትና ልታከብሩት፤ አላህንም በጠዋትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱት (ላክንህ)።"},{"id":10,"translation":"10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ቃል ኪዳን የሚጋቡህ ቃል ኪዳን የሚጋቡት አላህን ብቻ ነው:: የአላህ እጅ ከእጆቻቸው በላይ ነው:: ያፈረሰም ሰው የሚያፈርሰው በነፍሱ ላይ ብቻ ነው:: በእርሱ ላይ አላህን ቃል ኪዳን የተጋባበትን የሞላ ሰው ታላቅ ምንዳ በእርግጥ ይሰጠዋል::"},{"id":11,"translation":"11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዐረብ ዘላኖች መካከል እነዚያ ከዘመቻ ወደ ኋላ የቀሩት «ገንዘቦቻችንና ቤተሰቦቻችን አስቸግረዉን ስለነበር ነውና (የቀረነው) ምህረትን ለምንልን» ይሉሃል:: በልቦቻቸው ውስጥ የሌለውን ነገር በምላሶቻቸው ይናገራሉ:: «አላህ እናንተን መጉዳትም ሆነ መጥቀም ቢፈልግ ከአላህ ለእናተ አንዳችን ለመከላከል የሚችል ማን ነው? በእውነቱ አላህ ለምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።» በላቸው።"},{"id":12,"translation":"12. ይልቁንም መልዕክተኛውና ምዕመናኖቹ ወደየቤተሰቦቻቸው ፈጽሞ አለመመለሳቸውን እርግጠኞች (ተጠራጣሪዎች) ስለነበራችሁ ነው። ይህም በልቦቻችሁ ውስጥ ተሸለመላችሁ:: መጥፎንም መጠርጠር ጠረጠራችሁ ጠፊዎች ህዝቦችም ሆናችሁ::"},{"id":13,"translation":"13. በአላህና በመልዕክተኛው ላለመነ ሰው እኛ ለከሓዲያን እሳትን አዘጋጅተናል::"},{"id":14,"translation":"14. የሰማያትና የምድር ንግስና የአላህ ብቻ ነው:: የሚፈልገውን ወደ ቀናው ይመራል:: የሚፈልገውንም ሰው ይቀጣል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":15,"translation":"15. ከጠላት የተማረኩትን ገንዘቦች ልትይዙ በሄዳችሁ ጊዜ እነዚያ ወደ ኋላ የቀሩት ሰዎች «ተውን እንከተላችሁ» ይሏችኋል:: በዚህም የአላህን ቃል ሊለውጡ ይፈልጋሉ:: «ፈጽሞ አትከተሉንም:: ልክ እንደዚሃችሁ ቃል የመሰለ ከዚህ በፊት አላህም ብሏል» በሏቸው:: «ይልቁንም ትመቀኙናላችሁ» ይላሉም:: በእውነት እነርሱም ጥቂትን እንጂ የማያውቁ ነበሩ::"},{"id":16,"translation":"16. ዘላኖች (ከአዕራቦች) ወደ ኋላ ለቀሩት (እንዲህ) በላቸው: «የብርቱ ጭካኔ ባለቤት ወደ ሆኑ ህዝቦች ውጊያ ወደ ፊት ትጠራላችሁ፤ ትጋደሏቸዋላችሁ:: ወይም ይሰልማሉ ብትታዘዙም አላህ መልካም ምንዳን ይሰጣችኋል:: ከአሁን በፊት እንደ ሸሻችሁ ብትሸሹ ደግሞ አሳማሚ ቅጣት ይቀጣችኋል::»"},{"id":17,"translation":"17. (ሰዎች ሆይ!) በአይነስውር ላይ (ከዘመቻ በመቅረቱ) ኃጢአት የለበትም:: በአንካሳ ላይም ኃጢአት የለበትም:: በበሽተኛም ላይ ኃጢአት የለበትም:: አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያስገባዋል:: የሚያፈገፍገዉንም ሁሉ አሳማሚ ቅጣት ይቀጣዋል::"},{"id":18,"translation":"18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከምዕመናኖቹ በዛፊቱ ስር ቃል ኪዳን በሚጋቡህ ጊዜ አላህ በእርግጥ ስራቸዉን ወደደላቸው:: በልቦቻቸዉም ውስጥ ያለውን ዐወቀ:: በነሱም ላይ እርጋታን አወረደ:: ቅርብ የሆነንም መክፈት መነዳቸው::"},{"id":19,"translation":"19. ብዙዎች የተማረኩትን ገንዘቦች የሚወስዷቸው የሆኑን መነዳቸው:: አላህም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::"},{"id":20,"translation":"20. (አማኞች ሆይ!) አላህ ብዙዎቹን ምርኮዎች የምትወስዷቸው የሆኑን አላህ ቃል ገባላችሁ። ይህንንም ለእናንተ አስቸኮለላቻችሁ:: ከናንተም የሰዎችን እጆች ሠበሰበላችሁ። ብታመሰግኑና ለአማኞችም መልዕክት እንድትሆን ቀጥተኛውን መንገድ ይመራችሁም ዘንድ ይህን አደረግንላችሁ::"},{"id":21,"translation":"21. ሌላይቱንም በእርሷ ላይ ገና ያልቻላችኋትን አላህ ያወቃትን ለእናንተ አዘጋጅቷል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::"},{"id":22,"translation":"22. እነዚያም የካዱት (የመካ ሰዎች) በተዋጓችሁ ኖሮ ለሽሽት ጀርባዎችን ባዞሩ ነበር:: ከዚያ ዘመድም ረዳትም አያገኙም::"},{"id":23,"translation":"23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያችን ከዚህ በፊት በእርግጥ ያለችፈውን ልማድ ደነገገ:: ለአላህ ልማድ መቸም ለውጥን አታገኝም::"},{"id":24,"translation":"24. እርሱ(አላህ) ያ በመካ ውስጥ በእነርሱ ላይ ካስቻላችሁ በኋላ እጆቻቸዉን ከእናንተ ላይ እጆቻችሁንም ከእነርሱ ላይ የከለከለ ነው:: አላህም የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነው::"},{"id":25,"translation":"25. እነርሱ ማለት እነዚያ በአላህ የካዱ፤ ከተከበረው መስጊድም የከለከሏችሁ መስዋዕትንም የታሰረ ሲሆን ወደ ስፍራው እንዳይደርስ የከለከሉ ናቸው:: የማታውቋቸው ወንድ አማኞችና ሴት ምዕመናት ከከሓዲያኑ ጋር ባልነበሩ ኖሮና እናንተም ያለ እውቀት እነርሱን ረግጣችሁ ከእነርሱ (በኩል) መከፋት የሚነካችሁ ባይሆን ኖሮ እጆቻችሁን ባላገድን ነበር:: አላህም የሚፈልገውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባ ዘንድ (እጆቻችሁን አገደ):: በተለዩ ኖሮ እነዚያን ከእርሱ ውስጥ በአላህ የካዱትን አሳማሚን ቅጣት በቀጣናቸው ነበር::"},{"id":26,"translation":"26. እነዚያን በአላህ የካዱት ደራይቱን (እልህን) የመሀይምነቲቱን ደራ (እልህ) በልቦቻቸው ውስጥ ባደረጉ ጊዜ በቀጣናቸው ነበር:: አላህም በመልዕክተኛው ላይ እና በምዕመናኖቹ ላይ እርጋታውን አወረደ:: መጠበቂያይቱንም ቃል አስያዛቸው:: በእርሷም ተገቢዎች ባለቤቶቿም ነበሩ:: አላህም በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነው።"},{"id":27,"translation":"27. ህልሙ እውነተኛ ሲሆን አላህ የፈለገ አንደሆነ ጸጥተኞች ሆናችሁ ራሳችሁን ላጭታችሁ አሳጥራችሁ የማትፈሩ ስትሆኑ የተከበረውን መስጊድ በእርግጥ ትገባላችሁ ያለውን ህልም አሏህ ለመልዕክተኛው(ለሙሀመድ) እውነት አደረገለት:: አላህ (ከእርቁ) ከመመለሳችሁ ሂደት ያላወቃችሁትንም ነገር አወቀ:: እናም ከዚህ በፊት ቅርብን የመክፈት እርቅ አደረገ::"},{"id":28,"translation":"28. እርሱ (አላህ) ያ መልዕክተኛውን (ነብዩ ሙሐመድን) በመሪ መጽሐፍና በእውነተኛ ሀይማኖት በሁሉ ላይ ሊያልቀው (የበላይ ሊያደርገው) የላከ ነው:: መስካሪነትም አላህ በቃ።"},{"id":29,"translation":"29. የአላህ መልዕክተኛ (ነብዩ) ሙሐመድ እና እነዚያም የእርሱ ጓደኞች በከሓዲያን ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው ተዛዛኞች ናቸው:: አጎንባሾች፤ ሰጋጆች፤ ሆነው ታያቸዋልህ:: ችሮታንና ውዴታን ሁልጊዜም ከአላህ ይፈልጋሉ:: ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትሆን በፊታቸው ላይ ናት:: ይህ በተውራት (የተነገረላቸው) ጸባያቸው ነው:: በኢንጅል ውስጥ የተጠቀሰው ምሳሌያቸው ደግሞ ቀንዘሉን እንደ አወጣ አዝመራና (ቀንዘሉን) እንዳበረታው እንደ ወፍራምና ገበሬዎቹን የሚያስደነቅ ሆኖ አገዳዎቹ ላይ ተስተካክሎ እንደቆመ (አዝመራ) ነው:: ያበረታቸውና ከሓዲያን በእርሱ ሊያሰቆጭ ነው:: አላህ እነዚያን በእሱ ያመኑትንና ከእነርሱ በጎዎችን ተግባራት የሰሩትን ሁሉ ምህረትንና ታላቅ ምንዳን ቃል ገበቶላቸዋል::"}]},{"id":49,"verses":[{"id":1,"translation":"1. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልዕክተኛው ፊት ነፍሶቻችሁን አታስቀድሙ:: አላህንም ፍሩ:: አላህ ለሚባለው ሁሉ ሰሚ ለሚፈጸመው ነገር ሁሉ አዋቂ ነውና::"},{"id":2,"translation":"2. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ድምፆቻችሁን ከነብዩ ድምጽ በላይ ከፍ አታድርጉ:: ከፊላችሁ ለከፊሉ እንደሚጮህም ሁሉ በንግግር ለርሱ ስትናገሩ አትጩሁ:: እናንተ የማታውቁ ስትሆኑ ስራዎቻችሁ እንዳይበላሹ (ከዚህ ተከልከሉ)::"},{"id":3,"translation":"3. እነዚያ በአላህ መልዕክተኛ ዘንድ ድምፆቻቸውን ዝቅ የሚያደርጉ እነዚህ እነዚያ አላህ ልቦቻቸውን ለፍርሃት የፈተናቸው ናቸው:: ለእነርሱም ምህረትና ታላቅ ምንዳ አለላቸው::"},{"id":4,"translation":"4. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ከመኖሪያ ክፍሎቹ ውጭ ሆነው የሚጠሩህ አብዛሀኞቻቸው አያውቁም::"},{"id":5,"translation":"5. ወደ እነርሱም እስክትወጣ ድረስ ዝምብለው በታገሱ ኖሮ ለእነርሱ በላጭ በሆነ ነበር:: አላህም እጅግ መሀሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":6,"translation":"6. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬ ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ሆናችሁ ህዝባችሁን እንዳትጎዱና ከዚያም በሰራችሁት ነገር ላይ ተጸፃቾች እንዳትሆኑ አረጋግጡ::"},{"id":7,"translation":"7. በውስጣችሁም የአላህ መልዕክተኛ መኖሩን እወቁ:: ከነገሩ በብዙው ነገሮች ቢከተላችሁ ኖሮ በእርግጥ በተቸገራችሁ ነበር:: ግን አላህ እምነትን ወደ እናንተ አስወደደ :: በልቦቻችሁም ውስጥ አስዋበው። ክህደትን፣ አመፅንና እምቢተኝነትንም ለናንተ የተጠላ አደረገ። እነዚያ እምነትን የወደዱና ክሕደትን የጠሉ ሰዎች እነርሱ ትክክለኛ ቅኖቹ ናቸው።"},{"id":8,"translation":"8. ከአላህ በሆነው ችሮታና ጸጋ ሲሆን ቅኖች ናቸው። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው።"},{"id":9,"translation":"9. ሁለት የምዕምናን ቡድኖች እርስ በእርስ ቢጋደሉ በመካከላቸው አስታርቁ:: ከሁለት አንደኛይቱ በሌላኛይቱ ላይ ወሰን ብታልፍ ያችን ወሰን የምታልፈውን ወደ አላህ ትዕዛዝ እስከምትመጣ ድረስ ተጋደሏት፤ ብትመለስ ግን በመካከላቸው በትክክል አስታርቁ:: በነገሩ ሁሉ አስተካክሉ:: አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና።"},{"id":10,"translation":"10.(አማኞች ሆይ!) ምዕመናኖች ወንድማማቾች ናቸውና በሁለት ወንድሞቻችሁ መካከል አስታርቁ:: ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ::"},{"id":11,"translation":"11.እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች በወንዶች አይሳለቁ:: ከእነርሱ የበለጡ ሊሆኑ ይከጀላልና:: ሴቶችም በሴቶች አይሳለቁ:: ከእነርሱ የበለጡ ሊሆኑ ይከጀላልና:: ነፍሶቻችሁንም አታነዉሩ በመጥፎ ሰሞችም አትጠራሩ:: ከእምነት በኋላ መጥፎ ስም ከፋ:: ያልተጸጸተ ሰው በእውነት እነርሱ በዳዮቹ ናቸው።"},{"id":12,"translation":"12. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙን ራቁ:: ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና:: ነውርንም አትከታተሉ። ከፊላችሁም ከፊሉን አይማው። አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ሆኖ ሊበላ ይወዳልን? (መብላቱን) ጠላችሁት (ሀሜቱንም ጥሉት):: አላህንም ፍሩ:: አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና::"},{"id":13,"translation":"13. እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ:: እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ:: አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ብቻ ነው:: አላህ ግልጽን አዋቂ ውስጥንም አዋቂ ነው::"},{"id":14,"translation":"14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዐረብ ዘላኖች አምነናል አሉ:: «አላመናችሁም ግን ሰልመናል በሉ እምነቱም በልቦቻችሁ ውስጥ ገና ጠልቆ አልገባም:: አላህንና መልዕክተኛውን ብትታዘዙ ከስራዎቻችሁ ምንም አይጎድልባችሁም:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና» በላቸው::"},{"id":15,"translation":"15. አማኞች እነዚያ በአላህና በመልዕክተኛው ያመኑትና ከዚያም ያልተጠራጠሩት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸዉም በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት ሰዎች ብቻ ናቸው:: እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው::"},{"id":16,"translation":"16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ በሰማያት ውስጥ ያለውንና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ ሲሆን አላህን በሃይማኖታችሁ ታስታውቁታላችሁን?» በላቸው:: አላህም በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነው::"},{"id":17,"translation":"17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመስለማቸው ባንተ ላይ ይመፃደቃሉ። «በእስልምናችሁ በእኔ ላይ አትመጻደቁ:: ይልቁንም አላህ ወደ ትክክለኛው እምነት ስለመራችሁ ፀጋውን ውሎላችኋል:: እውነተኞች ብትሆኑ (መመፃደቅ የሚገባው ለአላህ) ብቻ ነው» በላቸው።"},{"id":18,"translation":"18. አላህ የሰማያትንና የምድርን ሩቅ ሚስጥር ሁሉ ያውቃል:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካችም ነው::"}]},{"id":50,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ቃፍ ፤ በተከበረው ቁርኣን እምላለሁ::"},{"id":2,"translation":"2. ይልቁንም ከእነርሱ መካከል የሆነ አስፈራሪ ስለ መጣላቸው ተደነቁ:: ከሓዲያንም አሉ: «ይህ አስደናቂ ነገር ነው።"},{"id":3,"translation":"3. «በሞትንና አፈር በሆንን ጊዜ እንመለሳለንን? ይህ ሩቅ የሆነ መመለስ ነው።» አሉ።"},{"id":4,"translation":"4. ከእነርሱ አካል ምድር የምታጎድለውን በእርግጥ አውቀናል:: እኛም ዘንድ ጠባቂ መጽሐፍ አለ::"},{"id":5,"translation":"5. ይልቁንም ቁርኣን በመጣላቸው ጊዜ አስተባበሉ። እነርሱም በተምታታ ነገር ውስጥ ናቸው።"},{"id":6,"translation":"6. ወደ ሰማይም ከበላያቸው ስትሆን ለእርሷ ምንም ቀዳዳዎች የሌሏቸው ሆነው እንዴት እንደገነባናትና በከዋክብት እንዳጌጥናት አልተመለከቱምን?"},{"id":7,"translation":"7. ምድርም ዘረጋናት በእርሷም ውስጥ ጋራዎችን ጣልንባት :: በውስጧም ከሚያስደስት አይነት ሁሉ አበቀልን::"},{"id":8,"translation":"8. ይህንን ያደረግነው ተመላሽ ለሆነ ባሪያ ሁሉ ለማሳየትና ለማስገንዘብ ነው::"},{"id":9,"translation":"9. ከሰማይም ብሩክን ውሃ አወረድን በእርሱም አትክልቶችንና የሚታጨድን አዝመራ ፍሬ አበቀልን::"},{"id":10,"translation":"10. ዘንባባንም ረዣዥም ለእርሷ የተደራረበ እንቡጥ ያላት ስትሆን አበቀልን::"},{"id":11,"translation":"11. ለባሮቹ ሲሳይ ትሆን ዘንድ (አዘጋጀናት):: በእርሱም የሞተችን ሀገር ሕያው አደረግንበት:: ከመቃብር መውጣትም ልክ እንደዚሁ ነው::"},{"id":12,"translation":"12. ከእነርሱ በፊት የኑህ ህዝቦችና የረስስ ሰዎችም ሰሙድም አስተባበሉ::"},{"id":13,"translation":"13. ዓድም ፈርዖንም የሉጥ ወንድሞችም፤"},{"id":14,"translation":"14. የጫካው ባለቤቶችም የቱብበዕ ህዝቦችም ሁሉ መልዕክተኞችን አስተባበሉ:: ዛቻየም ተረጋገጠባቸው።"},{"id":15,"translation":"15. በመጀመሪያው መፍጠር ደከምን? በእውነቱ እነርሱ ከአዲስ መፍጠር በመጠራጠር ውስጥ ናቸው::"},{"id":16,"translation":"16. ሰውንም ነፍሱ በሀሳቡ የምታጫውተውን የምናውቅ ስንሆን ፈጠርነው:: እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደ እርሱ ቅርብ ነን::"},{"id":17,"translation":"17-ሁለት ቃል ተቀባዮች መላዕክት ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ሆነው በሚቀበሉ ጊዜ አስታውስ::"},{"id":18,"translation":"18. ከቃል ምንም አይናገርም ከአጠገቡ ተጠባባቂ እና ዝግጁ የሆኑ መላዕክት ያሉበት ቢሆን እንጂ::"},{"id":19,"translation":"19. የሞትም መከራ እውነቱን ነገር ታመጣለች። «(ሰው ሆይ!) ይህ ያ ከእርሱ ትሸሸው የነበርከው ነው» ይባላል።"},{"id":20,"translation":"20. በቀንዱም ውስጥ ይነፋል። ያ ቀን የዛቻው መፈጸሚያ ቀን ነው::"},{"id":21,"translation":"21. ነፍስም ሁሉ ከእርሷ ጋር ነጅና መስካሪ ያለባት ሆና ትመጣለች::"},{"id":22,"translation":"22. «ከዚህ ነገር በእርግጥ የዘነጋህ ነበርክ። ሽፋንህንም ካንተ ላይ ገለጥንልህ:: ስለዚህ ዛሬ ዓይንህ ስለታም ነው» (ይባላል)::"},{"id":23,"translation":"23. ቁራኛዉም (መልዓክ) «ይህ ያ እኔ ዘንድ ያለው ቀራቢ ነው።» ይላል።"},{"id":24,"translation":"24. (አላህም ይላል): «ሞገደኛ ከሓዲን ሁሉ በገሀነም ውስጥ ጣሉ።"},{"id":25,"translation":"25. «ለበጎ ስራ ከልካይ በዳይ ተጠራጣሪ የሆነን ሁሉ ጣሉ።"},{"id":26,"translation":"26. «ያንን ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ ያደረገውን በብርቱ ቅጣት ውስጥ ጣሉት» ይባላል።"},{"id":27,"translation":"27. «ቁራኛው (ሰይጣን) ጌታችን ሆይ! እኔ አላሳሳትኩትም ግን ራሱ በሩቅ ስህተት ውስጥ ነበር» ይላል።"},{"id":28,"translation":"28. (አላህም) ይላል: «ወደ እናተ ዛቻን በእርግጥ ያስቀደምኩ ስሆን እኔ ዘንድ አትጨቃጨቁ።"},{"id":29,"translation":"29. «ቃሉ እኔ ዘንድ አይለወጥም እኔም ለባሮቼ ፈጽሞ በዳይ አይደለሁም» (ይላቸዋል)።"},{"id":30,"translation":"30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለገሀነም «ሞላሽን?» የምንልበትንና (ገሀነምም) «ጭማሪ አለን?» የምትልበትን ቀን አስጠንቅቃቸው::"},{"id":31,"translation":"31. ገነትም አላህን ለፈሩት ሁሉ ሩቅ ባልሆነ ስፍራ ትቀረባለች::"},{"id":32,"translation":"32. (ይባላሉም) «ይህ ወደ አላህ ተመላሽና ህግጋቱን ጠባቂ ለሆነ ሁሉ የተቀጠራችሁት ነው።"},{"id":33,"translation":"33. «አር-ረህማንን በሩቅ ሆኖ ለፈራና በተመላሽ ልብ ለመጣ ትቅቀረባለች::"},{"id":34,"translation":"34. «በሰላም ግቧታ ይህ የመዘውተሪያ ቀን ነው» (ይባላሉ)።"},{"id":35,"translation":"35. ለእነርሱ በውስጧ ሲሆኑ የሚሹት ሁሉ አላቸው እኛም ዘንድ ጭማሪ አለ::"},{"id":36,"translation":"36. ከእነርሱም (ከቁረይሾች) በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች በሀያልነት ከእነርሱ ይበልጥ የበረቱ ሆነው ማምለጫ ፍለጋ በየሀገሮቹ የመረመሩ ብዙዎችንም አጥፍተናል። ማምለጫ አለን?"},{"id":37,"translation":"37. በዚሁ ውስጥ ልብ ላለው ወይም እርሱ በህሊናው ጆሮውን የሰጠ ሆኖ ወደ ሚነበብለት ጆሮውን ለጣለ ሰው ሁሉ ግሳጼ አለበት::"},{"id":38,"translation":"38. ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን። ድካምም ምንም አልነካንም::"},{"id":39,"translation":"39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሚሉትም ላይ ታገስ ጌታህንም ከማመስገን ጋር ጸሐይ ከመውጣቷ በፊትና ከመገባቷም በፊት አጥራው።"},{"id":40,"translation":"40. ከሌሊትም አጥራው፤ ከስግደቶችም በኋላዎች አጥራው።"},{"id":41,"translation":"41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (የሚነገርህን) አዳምጥም፤ ጠሪው ከቅርብ ስፍራ በሚጠራበት ቀን ከመቃብራቸው ይወጣሉ።"},{"id":42,"translation":"42. ጩኸቲቱን በእውነቱ የሚሰሙበት ቀን፤ ያ ከመቃብር የመውጫው ቀን ነው።"},{"id":43,"translation":"43. እኛው ሕያው እናደርጋለን:: እንገድላለንም:: በመጨረሻም ጊዜ መመለሻው ወደ እኛ ብቻ ነው::"},{"id":44,"translation":"44. የሚፈጥኑ ሆነው ምድር ከእነርሱ ላይ የምትሰነጣጠቅበት ቀን (የመውጫ ቀን ነው):: ይህ በእኛ ላይ ገር የሆነ መሰብሰብ ነው::"},{"id":45,"translation":"45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ የሚሉትን ሁሉ አዋቂ ነን:: አንተም በእነርሱ ላይ አሰገዳጅ አይደለህም:: ስለዚህ ዛቻየን የሚፈራን ሰው ሁሉ በቁርኣን አስታውስ::"}]},{"id":51,"verses":[{"id":1,"translation":"1. መበተንን በታኝ በሆኑት (ንፋሶች) እምላለሁ"},{"id":2,"translation":"2. ከባድ ዝናብን ተሸካሚዎች በሆኑትም (ዳመናዎች)፤"},{"id":3,"translation":"3. ገር መንሻለልን ተንሻላዩች በሆኑትም (መርከቦች) እምላለሁ::"},{"id":4,"translation":"4. ጉዳይን ሁሉ አከፋፋዮች በሆኑትም (መላዕክት) እምላለሁ::"},{"id":5,"translation":"5. የምተቀጠሩት ትንሳኤ እውነት ነው::"},{"id":6,"translation":"6. (እንደየስራው) ዋጋን ማግኘትም የማይቀር ነው።"},{"id":7,"translation":"7.የ(ከዋክብት) መንገዶች ባለቤት በሆነችው ሰማይ እምላለሁ::"},{"id":8,"translation":"8. እናንተ በተለያየ ቃል ውስጥ ናችሁ።"},{"id":9,"translation":"9. ከእርሱ የሚዝዞር ሰው ይዝዞራል::"},{"id":10,"translation":"10. በግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ::"},{"id":11,"translation":"11. እነዚያ እነርሱ በሚሸፍን ስህተት ውስጥ ዘንጊዎች የሆኑት::"},{"id":12,"translation":"12. የዋጋ መስጫው ቀን መቼ እንደሆነ ይጠይቃሉ::"},{"id":13,"translation":"13. (እነርሱ) በእሳት ላይ በሚፈተኑበት ቀን ነው::"},{"id":14,"translation":"14. «መከራችሁን ቅመሱ ይህ ያ በእርሱ ትቻኮሉበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)::"},{"id":15,"translation":"15. አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው::"},{"id":16,"translation":"16. ያንን ጌታቸው የሰጣቸውን ተቀባዮች ሆነው በገነት ውስጥ ይሆናሉ:: እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሰሪዎች ነበሩና::"},{"id":17,"translation":"17. ከሌሊቱ ጥቂቱን ብቻ ይተኙ ነበር::"},{"id":18,"translation":"18. በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምህረትን ይለምናሉ::"},{"id":19,"translation":"19. በገንዘቦቻቸዉም ውስጥ ለለማኝና ከልመና ለተከለከለም (በችሮታቸው) መብት አለ።"},{"id":20,"translation":"20. በምድርም ውስጥ ለሚያረጋግጡ ሰዎች አያሌ ምልክቶች አሉ::"},{"id":21,"translation":"21. (ሰዎች ሆይ!) በነፍሶቻችሁም ውስጥ አያሌ ምልክቶች አሉ:: ታዲያ አትመለከቱምን?"},{"id":22,"translation":"22. ሲሳያችሁም የምትቀጠሩት (ፍዳና ምንዳ) በሰማይ ነው።"},{"id":23,"translation":"23. በሰማይና በምድር ጌታም እምላለሁ። እርሱ እናንተ እንደምትናገሩት ብጤ እርግጠኛ (እውነት) ነው።"},{"id":24,"translation":"24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን?"},{"id":25,"translation":"25. በእርሱም ላይ በገቡና «ሰላም» ባሉት ጊዜ ምን እንደሆነ አስታውስ። ሰላም ግና ያልታወቃችሁ ህዝቦች ናችሁ አላቸው።"},{"id":26,"translation":"26. ወደ ቤተሰቡም ተዘነበለና ወዲያውም የሰባ ወይፈን አመጣ::"},{"id":27,"translation":"27. ከዚያ ወደ እነርሱ (አዘጋጅቶ) አቀረበውና «አትበሉም ወይ? አላቸው።"},{"id":28,"translation":"28. ከእነርሱ መፍራትን በልቡ አሳደረ። «አትፍራ» አሉትም በአዋቂ ልጅም አበስሩት::"},{"id":29,"translation":"29. ሚስቱም (በደስታ) እየጮኸች መጣች፤ ፊቷንም መታች «መካን አሮጊት (ነኝ)» አለችም።"},{"id":30,"translation":"30. እነርሱም «ጌታሽ 'እንዲሁ (ይሁን)' ብሏል። እነሆ እርሱ ጥበበኛና ሁሉን አዋቂ ነው» አሏት::"},{"id":31,"translation":"31. «እናንተ መልዕክተኞች ሆይ! ታዲያ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው::"},{"id":32,"translation":"32. እነርሱም አሉ: «እኛ ወደ አመጸኖች ህዝቦች ተልከናል።"},{"id":33,"translation":"33. «በእነርሱ ላይ ከጭቃ የሆኑ ድንጋዮችን ልንለቅባቸው ተላክን።"},{"id":34,"translation":"34. «በጌታህ ዘንድ ለድንበር አላፊዎቹ በየስማቸው ምልክት የተደረገባት ስትሆን።» አሉ"},{"id":35,"translation":"35. ከምዕመናም በእርሷ በከተማቸው ውስጥ የነበሩትን አወጣን::"},{"id":36,"translation":"36. በውስጧም ከአንድ ቤት ቤተሰቦች በስተቀር ሙስሊሞችን አላገኘንም::"},{"id":37,"translation":"37. በውስጧም ለእነዚያ አሳማሚውን ቅጣት ለሚፈሩት ምልክትን አስቀረን::"},{"id":38,"translation":"38. በሙሳ ወሬ ውስጥም ወደ ፈርዖን በግልጽ ማስረጃ በላክነው ጊዜ (ምልክትን አደረግን)::"},{"id":39,"translation":"39. ከድጋፉ (ከሰራዊቱ) ጋርም ከእምነት ዞረ:: «እርሱ ድግምተኛ ወይም እብድ ነው» አለ::"},{"id":40,"translation":"40. እርሱንም ሰራዊቱንም ያዝናቸው እርሱ ተወቃሽ ሲሆን በባህር ውስጥ ጣልናቸውም።"},{"id":41,"translation":"41. በዓድም በእነርሱ ላይ መካን (የሆነች) ንፋስን በላክን ጊዜ ምልክት አለ::"},{"id":42,"translation":"42. በላዩ ላይ የመጣችበትን ማንኛዉንም ነገር እንደበሰበሰ አጥነት ያደረገችው ብትሆን እንጂ አትተወዉም።"},{"id":43,"translation":"43. በሰሙድም ለእነርሱ «እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ ተጣቀሙ።» በተባሉ ጊዜ (ምልክት አለ)።"},{"id":44,"translation":"44. ከጌታቸው ትዕዘዝም ኮሩ:: እነርሱም እያዩ ጩኸቷ ያዘቻቸው::"},{"id":45,"translation":"45. መቆምንም አልቻሉም:: እርዳታ የሚደረግላቸውም አልነበሩም::"},{"id":46,"translation":"46. የኑህንም ህዝቦች (ከዚህ በፊት አጠፋን) እነርሱ አመጸኞች ህዝቦች ነበሩና::"},{"id":47,"translation":"47. ሰማይንም በሀይል ገነባናት:: እኛም በእርግጥ የምናስፋት ነን::"},{"id":48,"translation":"48. ምድርንም ዘረጋናት ምን ያማርንም ዘርጊዎች ነን::"},{"id":49,"translation":"49. ትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት ተቃራኒ አይነትን ፈጠርን::"},{"id":50,"translation":"50. ወደ አላህም ሽሹ እኔ ለእናንተ ከእርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝ።"},{"id":51,"translation":"51. ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አታድርጉ:: እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላኩ:: ግልጽ አስፈራሪ ነኝና::"},{"id":52,"translation":"52. ልክ እንደዚሁ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ከመልዕክተኛ ማንም አልመጣቸዉም:: «እርሱ ድግምተኛ ወይም እብድ ነው» ያሉ ቢሆን እንጂ::"},{"id":53,"translation":"53. በእርሱ (በዚህ ቃል) አደራ ተባብለዋልን? ይልቁን እነርሱ ጥጋበኞች ህዝቦች ናቸው::"},{"id":54,"translation":"54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ዘወር በል (ተዋቸው)፤ አንተ ምንም ተወቃሽ አይደለህምና::"},{"id":55,"translation":"55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ገስጽም ግሳጼ አማኞችን ትጠቅማለችና::"},{"id":56,"translation":"56. ጋኔንና ሰዉን ሊገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸዉም::"},{"id":57,"translation":"57. ከእነርሱም ምንም ሲሳይን አልፈልግም:: እንዲመግቡኝም አልፈልግም::"},{"id":58,"translation":"58. አላህ ሰጪና የብርቱ ሀይል ባለቤት ነውና::"},{"id":59,"translation":"59. ለእነዚያም ለበደሉት እንደ ጓደኞቻቸው ፋንታ ብጤ የቅጣት ፋንታ አለላቸው:: ስለዚህ አያስቸኩሉኝ::"},{"id":60,"translation":"60. ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከዚያ ከሚቀጠሩት ቀናቸው ወዩላቸው::"}]},{"id":52,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በጡር (ጋራ)፤ እምላለሁ።"},{"id":2,"translation":"2. በተጻፈው መጽሓፍም፤"},{"id":3,"translation":"3. በተዘረጋው ብራና ላይ፤"},{"id":4,"translation":"4. በደመቀው ቤትም፤"},{"id":5,"translation":"5. ከፍ በተደረገው ጣራም፤"},{"id":6,"translation":"6. በእሳት በተሞላው ባህርም እምላለሁ::"},{"id":7,"translation":"7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ ቅጣት በእርግጥ ወዳቂ ነው (የማይቀር ነው)::"},{"id":8,"translation":"8. ለእርሱ ምንም ገፍታሪ የለዉም::"},{"id":9,"translation":"9. ሰማይ ብርቱ መዞርን በምትዞርበት ቀን (ይሆናል)::"},{"id":10,"translation":"10. ተራራዎችም መሄድን በሚሄዱበት ቀን::"},{"id":11,"translation":"11. ላስተባባዮችም ሁሉ ያን ጊዜ ወዮላቸው።"},{"id":12,"translation":"12. ለነዚያ ለእነርሱ በውሸት ውስጥ የሚጫወቱ ለሆኑት ሰዎች::"},{"id":13,"translation":"13. ወደ ገሀነም እሳት በሀይል መገፍተርን በሚገፈተሩበት ቀን"},{"id":14,"translation":"14. «ይህች ያቺ በእርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁት እሳት ናት ይባላሉ»።"},{"id":15,"translation":"15. «ይህ (ፊት ትሉን እንደነበራችሁት) ድግምት ነውን? ወይስ እናንተ አታዩምን?"},{"id":16,"translation":"16. «ግቧት ታገሱም ወይም አትታገሱ በእናንተ ላይ እኩል ነው:: የምትመነዱት ትሰሩት የነበራችሁትን ፍዳ ብቻ ነው» ይባላሉ::"},{"id":17,"translation":"17. አላህን ፈሪዎቹ በእርግጥ በገነቶችና በጸጋ ውስጥ ናቸው::"},{"id":18,"translation":"18. ጌታቸው በሰጣቸው ጸጋ ተደሳቾች ሆነው በገነት ውስጥ ናቸው:: የገሀነምንም ስቃይ ጌታቸው ጠበቃቸው::"},{"id":19,"translation":"19. «ትሰሩት በነበራችሁት ምክንያት ተደሳቾች ሆናችሁ ብሉ ጠጡም» (ይባላሉ።)"},{"id":20,"translation":"20. በተደረደሩ አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ሆነው በገነት ይኖራሉ:: አይናማዎች በሆኑ ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን::"},{"id":21,"translation":"21. እነዚያም በአላህ ያመኑና ዝርያቸዉም በእውነት የተከተለቻቸው ዝርያቸውን ከእነርሱ ጋር እናስጠጋቸዋለን:: ከስራዎቻቸዉም ምንንም አናጎድልባቸዉም:: ሰው ሁሉ በሰራው ስራ ተጠያቂ ነው::"},{"id":22,"translation":"22. ከሚሹትም ሁሉ እሸትንና ስጋን እንጨምርላቸዋለን::"},{"id":23,"translation":"23. በውስጧ መጠጥን ይሰጣጣሉ:: በውስጧ ውድቅ ንግግርና መወንጀልም የለም::"},{"id":24,"translation":"24. ለእነርሱም የሆኑ ወጣቶች ልክ የተሸፈነ ሉል መስለው በእነርሱ ላይ ለማሰላፍ ይዘዋወራሉ::"},{"id":25,"translation":"25. የሚጠያየቁ ሆነዉም ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይዞራል::"},{"id":26,"translation":"26. ይላሉም: «እኛ ፊት በቤተሰቦቻችን ውስጥ ከቅጣት ፈሪዎች ነበርን።"},{"id":27,"translation":"27. «አላህ በእኛ ላይ ለገሰ:: የመርዛም እሳት ቅጣትንም ጠበቀን::"},{"id":28,"translation":"28. «እኛ ከዚህ በፊት እንለምነው ነበርን:: እነሆ እርሱ በጎ ዋይ አዛኝ ነውና» ይላሉ::"},{"id":29,"translation":"29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ሰዎችን) አስታውስ አንተም በጌታህ ጸጋ ምክንያት ጠንቋይም እብድም አይደለህም::"},{"id":30,"translation":"30. «ይልቁንም የሞትን አደጋ በእርሱ የምንጠባበቅበት የሆነ ባለ ቅኔ ነው» ይላሉን?"},{"id":31,"translation":"31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ተጠባበቁ እኔም ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ» በላቸው::"},{"id":32,"translation":"32. አእምሮዎቻቸው በዚህ ተግባር ያዟቸዋልን? ወይስ በእውነቱ እነርሱ ወሰን አላፊ ህዝቦች ናቸው::"},{"id":33,"translation":"33. ወይም «ቀጠፈው» ይላሉን? አይደለም። ይልቁንም አያምኑም::"},{"id":34,"translation":"34. እውነተኞችም ከሆኑ መሰሉ የሆነን ንግግር ያምጡ::"},{"id":35,"translation":"35. ወይስ ያለ አንዳች ፈጣሪ ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን?"},{"id":36,"translation":"36. ወይስ ሰማያትንና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም፤ አያረጋግጡም::"},{"id":37,"translation":"37. ወይስ የጌታህ ግምጃ ቤቶች እነርሱ ዘንድ ናቸውን? ወይስ እነርሱ አሸናፊዎች ናቸው?"},{"id":38,"translation":"38. ወይስ ለእነርሱ በእርሱ ላይ ከሰማይ የሚያዳምጡበት መሰላል አላቸውን? (እንግዲያውስ) አድማጫቸዉ ሰማሁ የሚለውን ግልጽ አስረጂ ያምጣ::"},{"id":39,"translation":"39. ወይስ ለእናንተ ወንዶች ልጆች እያሏችሁ ለእርሱ ሴቶች ልጆች አሉትን?"},{"id":40,"translation":"40. ወይስ ዋጋን ትጠይቃቸዋለህን? በዚህም እነርሱ በእዳው የተከበዱ ናቸውን?"},{"id":41,"translation":"41. ወይስ ሩቁ ሚስጢር እነርሱ ዘንድ በመሆኑ እነርሱ ይጽፋሉን?"},{"id":42,"translation":"42. ወይስ ተንኮልን (ባንተ) ይሻሉን? እነዚያም የካዱት የተተነኮለባቸው ናቸው::"},{"id":43,"translation":"43. ወይስ ለእነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ አላቸውን? አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ::"},{"id":44,"translation":"44. ከሰማይም ቁራጭን በእነርሱ ላይ ወዳቂ ሆኖ ቢያዩ ኖሮ «ይህ የተደራረበ ደመና ነው» ይሉ ነበር::"},{"id":45,"translation":"45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)ያንንም በእርሱ የሚገደሉበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው::"},{"id":46,"translation":"46. ተንኮላቸው ከእነርሱ ምንም የማይጠቅማቸውንና እነርሱም የማይረዱበትን ቀን እስከሚያገኙ ተዋቸው::"},{"id":47,"translation":"47. ለእነዚያም ለበደሉትም ከዚህ ሌላ ቅርብ ቅጣት አለባቸው:: ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም::"},{"id":48,"translation":"48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለጌታህ ፍርድም ታገስ:: አንተ በጥበቃችን ስር ነህና:: ጌታህንም በምትቆም ጊዜ ከማመስገን ጋር አጥራው::"},{"id":49,"translation":"49. ከሌሊቱና በከዋክብት መደበቂያም ጊዜ (ንጋት ላይም) አጥራው::"}]},{"id":53,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በኮከብ እምላለሁ በገባ ጊዜ፤"},{"id":2,"translation":"2. (እናንተ የመካ ሰዎች ሆይ)፤ ባልደረባችሁ ሙሐመድ ከሐቅ አልተሳሳተም። አላፈነገጠም።"},{"id":3,"translation":"3. ከልብ ወለድ ስሜቱም አይናገርም::"},{"id":4,"translation":"4. እርሱ (ንግግሩ) ከአላህ የተወረደ እንጂ ሌላ አይደለም።"},{"id":5,"translation":"5. ሀይለ ብርቱ የሆነው አስተማረው::"},{"id":6,"translation":"6. የእውቀት ባለቤት የሆነው:: ከዚያም ላይ ሆኖ ተመቻቸ።"},{"id":7,"translation":"7. በላይኛው አድማስ ላይ ሆኖ፤"},{"id":8,"translation":"8. ከዚያም (ነቢዩን) ቀረበው፤ በጣም ተጠጋውም።"},{"id":9,"translation":"9. ከዚያም የሁለት ደጋን ጫፎች ያህል ወይም ከዚያም ባነሰ ርቀት ላይ ሆነም::"},{"id":10,"translation":"10. እናም (አላህ) ለአገልጋዩ (ለሙሐመድ) ማውረድ የሻውን አወረደ::"},{"id":11,"translation":"11. ያየውን ነገር ሁሉ ልቦናው አላስተባበለዉም::"},{"id":12,"translation":"12. ታዲያ (ከሓዲያን ሆይ!) በሚያየው ጉዳይ ላይ ትከራከሩታላችሁን?"},{"id":13,"translation":"13. እርግጥ በሌላይቱም መውረድ (ነቢዩ ሙሐመድ መልዐኩ ጂብሪልን) አይቶታል::"},{"id":14,"translation":"14. ይኸዉም ሲድረቱ አል-ሙንተሃ (የመጨረሻቱ ቁርቁራ) በተባለው ዓለም ላይ ነው::"},{"id":15,"translation":"15. እርሷ ዘንድ መኖርያ የሆነችው ገነት አለች::"},{"id":16,"translation":"16. (ቁርቁራይቱን) ሸፋኝ ነገር በሸፈናት ጊዜ (አየው)።"},{"id":17,"translation":"17. አይኑ አልተዘነበለም:: ወሰንም አላለፈም።"},{"id":18,"translation":"18. ከጌታው ታላላቅ ተዐምራት በእርግጥ ተመለከተ።"},{"id":19,"translation":"19. (ቁርይሾች ሆይ!) ላትንና ዑዛን አያችሁን?"},{"id":20,"translation":"20. ስለ ሶስተኛዋ መናትም የምታውቁትን እስቲ ንገሩኝ::"},{"id":21,"translation":"21. ለእናንተ ወንድ ወንድ ለእሱ ግን ሴት ሴት ታደርጋላችሁን::"},{"id":22,"translation":"22. ይህ ተግባር አድሏዊ ክፍፍል ነው::"},{"id":23,"translation":"23. እነዚያ ጣዖታት እናንተና አባቶቻችሁ የሰየማችኋቸው ስሞች ብቻ እንጂ ሌላ አይደሉም::አላህ በእርሷ (መገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም፡፡ ጣኡት አምላኪዎች ሁሉ ከጌታቸው የተላከላቸው ቅኑ መመሪያ እያለ የሚከተሉት ግን ጥርጣሬንና ስሜትን ብቻ ነው::"},{"id":24,"translation":"24. የሰው ልጅ የፈለገውን ሁሉ ያገኛልን?"},{"id":25,"translation":"25. መጪውን ዓለምም ሆነ የመጀመሪያው ዓለም የአላህ ብቻ ነው::"},{"id":26,"translation":"26. በሰማያት ውስጥ ካሉ መላዕክት አላህ የሚሻውንና የሚወደውን ለሰው ያማልዱ ዘንድ ከፈቀደላቸው በኋላ እንጂ ምልጃቸው የማይፈይድ አያሌዎች ናቸው::"},{"id":27,"translation":"27. እነዚያ በመጪው ዓለም የማያምኑት መላዕክትን በእንስት ስም ይሰይማሉ::"},{"id":28,"translation":"28. ለእነርሱም በእርሱ እውቀት የላቸውም። እነርሱ የሚከተሉት ጥርጣሬን ብቻ ነው:: ጥርጣሬ ደግሞ ሀቅን አይተካም::"},{"id":29,"translation":"29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከቁርኣን አፈንግጦና የዚችን ዓለም ኑሮ እንጂ ሌላ ከማይመኝ ሰው እራስህን አሽሽ::"},{"id":30,"translation":"30. ይህ የእውቀታቸው ጣሪያ (መጨረሻ) ነው:: ጌታህ ግን መንገዱን የሳተውን ሁሉ አዋቂ ነው:: የተቀናውንም እንዲሁ አዋቂ ነው።"},{"id":31,"translation":"31. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የአላህ ነው:: እነዚያን ያጠፉትን በተግባራቸው ለመመንዳትና እነዚያን መልካም የሰሩትንም በመልካሟ (በገነት) ሊመነዳ ነው::"},{"id":32,"translation":"32. እነርሱም ከጥቃቅን ጥፋቶች በቀር ከባባድ ወንጀሎችንና አጸያፊ ተግባሮችን የራቁ ናቸው:: ጌታህ ምህረተ ሰፊ ነው:: እርሱ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜም ሆነ በእናቶቻችሁ ማሕጸን ውስጥ ጽንሶች በሁናችሁበት ጊዜ ያውቃችኋል:: ስለዚህ እራሳችሁን አታሞግሱ:: እርሱ በትክክል የሚፈራውን ሰው ከሁሉም ይበልጥ አዋቂ ነው::"},{"id":33,"translation":"33. ያን ከእምነት የሸሸውን አየህን (እስቲ ንገረኝ)?"},{"id":34,"translation":"34. ጥቂትን ብቻ ሰጥቶ ያቋረጠውን፤"},{"id":35,"translation":"35, ለመሆኑ የሚያውቀው የሩቅ ሚስጢር አለውና እርሱንም ያያልን?"},{"id":36,"translation":"36. ወይስ በሙሳ ፅሁፍ ያለው አልተነገረውም?"},{"id":37,"translation":"37. በኢብራሂም (ትእዛዛቱን) በፈፀመው ያለውስ አልተነገረዉምን?"},{"id":38,"translation":"38. ይኸዉም ወንጀለኛ ነፍስ የሌላውን ነፍስ ወንጀል በፍጹም አትሸከምም::"},{"id":39,"translation":"39. የሰው ልጅም የለፋበትን ብቻ እንጂ ሌላ የለዉም::"},{"id":40,"translation":"40. የሰራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል::"},{"id":41,"translation":"41. ከዚያም ጌታው ሙሉ ምንዳውን ይመነዳዋል::"},{"id":42,"translation":"42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሁሉም መጨረሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው::"},{"id":43,"translation":"43. እርሱ ያ ያሳቀና ያስለቀሰ ነው::"},{"id":44,"translation":"44. እርሱ ያ የገደለና ሕያው ያደረገም ነው::"},{"id":45,"translation":"45. እርሱ ያ ጥንድን፤ ወንድንና ሴትን የፈጠረ ነው::"},{"id":46,"translation":"46. ይኸዉም ከፍትወት ጠብታ በማሕጸን ውስጥ በምትፈሰስ ጊዜ ነው::"},{"id":47,"translation":"47. ሌላውን ማስገኘትም በእርሱ ላይ ነው::"},{"id":48,"translation":"48. እርሱ ያ ሀብትን የሰጠና ያብቃቃ ነው::"},{"id":49,"translation":"49. እርሱ የሺዕራ ጌታ ነው::"},{"id":50,"translation":"50. እርሱ የቀድሞ ሰዎችን የአድ ሕዝቦችንም አጠፋ።"},{"id":51,"translation":"51. ሰሙድንም አጠፋ:: አንድንም አላስቀረም::"},{"id":52,"translation":"52. በፊትም የኑህን ህዝቦች አጥፍቷል:: እነርሱ እጅግ በዳዮችና በጣም አመጸኞች ነበሩና ነው::"},{"id":53,"translation":"53.የተገለበጡትንም ደፋ።"},{"id":54,"translation":"54. ባሸፈናት ሸፈናት::"},{"id":55,"translation":"55. (የሰው ልጅ ሆይ)፤ ከጌታህ ጸጋዎች በየትኛው ነው የምትጠራጠረው::"},{"id":56,"translation":"56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ከቀድሞዎቹ አስጠንቃቂዎች አንዱ ነው::"},{"id":57,"translation":"57. ቀራቢቱም ቀረበች::"},{"id":58,"translation":"58. ከአላህ በስተቀር ገላጭ የላትም::"},{"id":59,"translation":"59. በዚህ ዘገባ ትደነቃላችሁን?"},{"id":60,"translation":"60 ትስቃላችሁን? አታለቅሱምን?"},{"id":61,"translation":"61. እናንተ ዘወትር ዘንጊዎች ናችሁን?"},{"id":62,"translation":"62. ለአላህ ስገዱ በብቸኝነትም አምልኩትም::"}]},{"id":54,"verses":[{"id":1,"translation":"1. የትንሳኤ ቀን ተቃረበ:: ጨረቃም ተገመሰ::"},{"id":2,"translation":"2. ከሓዲያን ተዐምርን ቢያዩም እንቢ ብለው ይዞራሉ:: «ይህ ዘውታሪ ድግምት ነው» ይላሉ::"},{"id":3,"translation":"3.አስተባበሉም :: ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ:: ነገርም ሁሉ (ወሰን አለው) ረጊ ነው።"},{"id":4,"translation":"4. ከዜናዎቹ በእርሱ ውስጥ መገሰጫ የሚሆን ነገር ያለበት በእርግጥ መጣላቸው::"},{"id":5,"translation":"5. ሙሉ ከሆነ ጥበብ (መጣላቸው):: ግን አስፈራሪዎች (ለማያምኑት) አይፈይዱም።"},{"id":6,"translation":"6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ተውና ዙር። (ይልቁንስ) ጠሪው መልዓክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ።"},{"id":7,"translation":"7. ዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ሆነውና ፍጹም የተበተኑ አንበጣ መስለው ከየመቃብሮቻቸው ይወጣሉ::"},{"id":8,"translation":"8. ወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎችና ቸኳዩች ሆነው ይወጣሉ:: ከሓዲያን ያን ጊዜ «ይህ ብርቱ ቀን ነው» ይላሉ።"},{"id":9,"translation":"9. ከእነርሱ በፊት የ(ነብዩ) ኑህ ህዝቦች አስተባበሉ:: ባሪያችንንም ኑህን አስተባበሉ:: «ዕብድ ነዉም» አሉት:: ተገላመጠም::"},{"id":10,"translation":"10. «ጌታውንም እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ» ሲል ተጣራ::"},{"id":11,"translation":"11. ወዲያውም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን::"},{"id":12,"translation":"12. የምድርንም ምንጮች በሃይል አፈነዳን:: የሰማዩና የምድሩ ውሃዉም ቀድሞ በተወሰነ ሁኔታ ላይ ተገናኘ::"},{"id":13,"translation":"13. ባለ ብዙ ሳንቃዎችና ባለ ብዙ ሚስማሮች በሆነቸው ታንኳ ላይም ጫንነው::"},{"id":14,"translation":"14. በጥበቃችን ስር ሆና ትንሻለላለች፡፡ ተክዶ ለነበረ ሰው ምንዳ ይህን ሰራን።"},{"id":15,"translation":"15. ተዓምር አድርገንም በእርግጥ ተውናት:: ተገሳጭ አለን?"},{"id":16,"translation":"16. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?"},{"id":17,"translation":"17. ቁርኣንን ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው:: ተገንዛቢ አለን?"},{"id":18,"translation":"18. የዓድ ህዝቦች አስተባበሉ:: ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ፤"},{"id":19,"translation":"19. እኛ በእነርሱ ላይ ዘወትር መናጢ በሆነ ቀን በኃይል የምንትሻሻ ነፋስን ላክንባቸው::"},{"id":20,"translation":"20. ሰዎችንም ልክ ከስሮቻቸው እንደተጎለሰሱ የዘንባባ ግንዶች መስለው ከየተደበቁበት ትነቅላቸዋለች::"},{"id":21,"translation":"21. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?"},{"id":22,"translation":"22. ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው:: ተገሳጭ አለን?"},{"id":23,"translation":"23. የሰሙድ ህዝቦች በአስፈራሪዎቹ አስተባበሉ::"},{"id":24,"translation":"24. (እንዲህም) አሉ: «ከእኛ የሆነን አንድን ሰው እንከተለዋለን? እኛ ያ! ጊዜ በስህተትና በእብደት ውስጥ ነን አሉ።"},{"id":25,"translation":"25. «ከእኛ መካከል በእርሱ ላይ ብቻ ማስገንዘቢያ ራዕይ ተጣለለትን? አይደለም እርሱ ውሸታም ኩሩ ነው» አሉ::"},{"id":26,"translation":"26. ውሸታሙ ኩሩው ማን እንደሆነ ነገ በእርግጥ ያውቃሉ::"},{"id":27,"translation":"27. እኛ ሴት ግመልን ለእነርሱ መፈተኛ ትሆን ዘንድ ላኪዎች ነን:: ተጠባበቃቸዉም ታገስም::"},{"id":28,"translation":"28. ውሃዉም በመካከላቸው የተከፈለ መሆኑን ንገራቸው:: ከውሃ የሆነ ፈንታ ሁሉ በየተራ የሚጣዱት ነው።"},{"id":29,"translation":"29. ጓደኛቸውንም ጠሩት:: ወዲያዉም (ሰይፉን) ተቀበለ:: ወጋትም::"},{"id":30,"translation":"30. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?"},{"id":31,"translation":"31. እኛ በእነርሱ ላይ አንዲትን ጩኸት ላክንባቸው። ወዲያዉም ከበረት አጣሪ (አጥር) እንደ ተሰባበረ እርጋፊ ሆኑ።"},{"id":32,"translation":"32. ቁርኣንን ለመገንዘብ አገራነው:: ተገሳጭ አለን?"},{"id":33,"translation":"33. የ(ነብዩ) ሉጥ ህዝብ በአስፈራሪዎቹ አስተባበሉ::"},{"id":34,"translation":"34. እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስ ላክን:: የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱንስ በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው::"},{"id":35,"translation":"35. ከእኛ በሆነ ጸጋ አዳናቸው:: ልክ እንደዚሁ ያመሰገነን ሰው እንመነዳለን::"},{"id":36,"translation":"36. ብርቱ አያያዛችንን በእርግጥ አስጠነቀቅናቸው:: በማስጠንቀቂያዎቹም ተከራከሩ።"},{"id":37,"translation":"37. ከእንግዶቹም እንዲያስመቻቸው ደጋግመው ፈለጉት። ወዲያዉም ዓይኖቻቸውን አበስን። ቅጣቱንና ማስጠንቀቂያዎቹን ቅመሱ አልናቸው።"},{"id":38,"translation":"38. በማለዳም ዘወታሪ የሆነ ቅጣት በእርግጥ ማለደባቸው::"},{"id":39,"translation":"39. ቅጣቱንና ማስጠንቀቂያዎችም ቅመሱ ተባሉ::"},{"id":40,"translation":"40 ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው:: ተገሳጭ አለን?"},{"id":41,"translation":"41.የፈርዖንን ቤተሰቦችም ማስጠንቀቂያዎች በእርግጥ መጧቸው።"},{"id":42,"translation":"42. በተዓምራታችንም በሁሏም አስተባበሉ:: የብርቱ ቻይንም አቀጣጥ ቀጣናቸው::"},{"id":43,"translation":"43. የእናንተ ከሓዲያኖቻችሁ ከእነዚያችሁ በላጮች ናቸውን? ወይስ ለእናንተ በመጽሐፎች ውስጥ በተለየ የተነገረ ነፃነት አላችሁ?"},{"id":44,"translation":"44. ወይስ «እኛ የተረዳን ክምቹዎች ነን» ይላሉ?"},{"id":45,"translation":"45. ክምቹዎቹ በእርግጥ ድል ይመታሉ:: ጀርባዎቻቸውንም ያዞራሉ::"},{"id":46,"translation":"46. ይልቁንም ሰዓቲቱ ትንሳኤ ቀጠሯቸው ናት:: ሰዓቲቱም በጣም የከበደችና የመረረች ናት::"},{"id":47,"translation":"47. አመጸኞች በስህተትና በእሳቶች ውስጥ ናቸው::"},{"id":48,"translation":"48. በእሳት ውስጥ በፊታቸው በሚጎተቱበት ቀን የሰቀርን (የገሀነምን) ቅጣት መንካትን ቅመሱ ይባላሉ::"},{"id":49,"translation":"49. እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው::"},{"id":50,"translation":"50. ትዕዛዛችንም እንደ ዓይን ቅጽበት የሆነች አንዲት ቃል እንጂ ሌላ አይደለችም::"},{"id":51,"translation":"51. ብጤዎቻችሁንም በእርግጥ አጠፋን፤ ተገሳጭ አለን?"},{"id":52,"translation":"52. የሰሩትም ነገር ሁሉ በመጽሐፎች ውስጥ ነው::"},{"id":53,"translation":"53. ትንሹም ትልቁም ሁሉ የተፃፈ ነው::"},{"id":54,"translation":"54. አላህን ፈሪ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በአትክልቶችና በወንዞች ውስጥ ናቸው::"},{"id":55,"translation":"55. እነርሱም (ውድቅ ቃልና መውወንጀል በሌለበት) በእውነት መቀመጫ ውስጥ ላይ ከሆነው ንጉስ አላህ ዘንድ ናቸው::"}]},{"id":55,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አር-ረህማን"},{"id":2,"translation":"2. ቁርኣንን አስተማረ::"},{"id":3,"translation":"3. ሰውን ፈጠረ::"},{"id":4,"translation":"4. መግለፅንም አስተማረው::"},{"id":5,"translation":"5. ጸሐይና ጨረቃ በተወሰነ (በየሂሳባቸው) ልክ ይሄዳሉ::"},{"id":6,"translation":"6. የሰማይ ከዋክብትና የምድር ዛፎችም ለእርሱ ይሰግዳሉ::"},{"id":7,"translation":"7. ሰማይንም ከፍ አደረጋት:: የትክክለኛነትን ሚዛንንም አስቀመጠ::"},{"id":8,"translation":"8. በሚዛን ስትመዝኑም እንዳትበድሉ::"},{"id":9,"translation":"9. መመዘንንም በትክክል መዝኑ:: ስትመዝኑም አታጉድሉ::"},{"id":10,"translation":"10. ምድርንም ለፍጡር አደላደላት::"},{"id":11,"translation":"11. በውስጧ እሸትም ባለ ሽፍን የሆኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትሆን፤"},{"id":12,"translation":"12. ባለቅርፊት ቅንጣትና ባለ መልካም መዓዛ ቅጠሎችም ያሉባት ስትሆን፤"},{"id":13,"translation":"13. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች መካከል በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":14,"translation":"14. ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው::"},{"id":15,"translation":"15. ጂንንም ከጭስ አልባ የእሳት ነበልባል ፈጠረው::"},{"id":16,"translation":"16. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ ?"},{"id":17,"translation":"17. የሁለቱ ምስራቆችና የሁለቱ ምዕራቦች ጌታ ነው::"},{"id":18,"translation":"18. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":19,"translation":"19. ሁለቱም ባህሮች የሚገናኙ ሲሆኑ ለቀቃቸው::"},{"id":20,"translation":"20. እንዳይዋሀዱ በመካከላቸው የማይታይ መጋረጃ አለ:: አንዱ በሌላው ላይ ወሰን አያልፉም::"},{"id":21,"translation":"21. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":22,"translation":"22. ሉልና መርጃን የተባሉት ማዕድናት ከሁለቱ (ባህሮች) ይወጣሉ::"},{"id":23,"translation":"23. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":24,"translation":"24. እንደ ጋራዎች ሆነው በባህር ውስጥ የተሰሩት ተንሻላዮችም (ታንኳዎች) የእርሱ ናቸው::"},{"id":25,"translation":"25. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":26,"translation":"26. በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው::"},{"id":27,"translation":"27. የልቅና እና የልግስና ባለቤት የሆነው የጌታህ ፊት ብቻ ይቀራል (አይጠፋም)::"},{"id":28,"translation":"28. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":29,"translation":"29.በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል። በየቀኑ ሁሉ እርሱ በስራ ላይ ነው።"},{"id":30,"translation":"30. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":31,"translation":"31. እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ መቆጣጠር በእርግጥ እንገኛለን::"},{"id":32,"translation":"32. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":33,"translation":"33. የአጋንንትና የሰው ስብስቦች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ከቻላችሁ ውጡ:: በአላህ ስልጣን እንጂ አትወጡም::"},{"id":34,"translation":"34. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":35,"translation":"35. በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበላባልና ጭስን ይላክባችኋል:: ሁለታችሁም ድል አታደርጉም::"},{"id":36,"translation":"36. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ !) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":37,"translation":"37. ሰማይ በተሰነጠቀችና እንደጽጌረዳ እንደታረበ ቆዳ በሆነች ጊዜ (ጭንቁን ምን አበረታው)::"},{"id":38,"translation":"38. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":39,"translation":"39. በዚያ ቀን ሰዉም ጂንም ከሐጢአት አይጠየቅም::"},{"id":40,"translation":"40. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":41,"translation":"41. ከሓዲያን በምልክታቸው ይታወቃሉ:: ከዚያ አናቶቻቸውንና እግሮቻቸውን ይያዛሉ::"},{"id":42,"translation":"42. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":43,"translation":"43. \"ይህች ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት\" (ይባላሉ)::"},{"id":44,"translation":"44. በእርሷና በጣም ሞቃት በሆነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ::"},{"id":45,"translation":"45. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":46,"translation":"46. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታዉም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁሉ ሁለት ገነቶች አሉት፡"},{"id":47,"translation":"47. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":48,"translation":"48. የቀንዘሎች ባለቤቶች የሆኑ ገነቶች፤"},{"id":49,"translation":"49. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":50,"translation":"50. በሁለቱ ውስጥ የሚፈሱ ሁለት ምንጮች አሉ፤"},{"id":51,"translation":"51. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":52,"translation":"52. በሁለቱ ውስጥ ከየፍራፍሬው ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አሉ፤"},{"id":53,"translation":"53. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":54,"translation":"54. የውስጥ ጉዝጉዛቸው ከወፍራም ሀር በሆኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቸ ሲሆን ይንፈላሰሳሉ፤ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ ለለቃሚ ቅርብ ነው።"},{"id":55,"translation":"55. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":56,"translation":"56. በውስጣቸው ከባሎቻቸው በፊት ሰዉም ጂንም ያልዳሰሳቸው (ያልገሰሳቸው) ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ ብቻ) አሳጣሪዎች ሴቶች አሉ::"},{"id":57,"translation":"57. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":58,"translation":"58. ልክ የያቁትንና የመርጃንን ማዕድናት ይመስላሉ::"},{"id":59,"translation":"59. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":60,"translation":"60. የበጎ ስራ ዋጋ በጎ እንጂ ሌላ ነውን?"},{"id":61,"translation":"61. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":62,"translation":"62. ከሁለት ገነቶች ሌላም ሁለት ገነቶች አሉ::"},{"id":63,"translation":"63. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":64,"translation":"64. ከልምላሜዎቻቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው::"},{"id":65,"translation":"65. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":66,"translation":"66. በውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አሉ::"},{"id":67,"translation":"67. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":68,"translation":"68. በውስጣቸው ፍራፍሬ ዘንባባና ሩማን አለ::"},{"id":69,"translation":"69. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":70,"translation":"70. በውስጣቸው ጸባየ መልካሞችና መልከ ውብ ሴቶች አሉ::"},{"id":71,"translation":"71. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":72,"translation":"72. በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቸቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የሆኑ ናቸው::"},{"id":73,"translation":"73. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":74,"translation":"74. ከእነርሱ በፊት ሰዉም ሆነ ጃን አልዳሰሳቸዉም (አልገሰሳቸዉም) ::"},{"id":75,"translation":"75. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":76,"translation":"76. በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲሆኑ ይቀመጣሉ::"},{"id":77,"translation":"77. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?"},{"id":78,"translation":"78. የግርማ የመከበር ባለቤት የሆነው ጌታህ ስም ላቀ።"}]},{"id":56,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ተጨባጪቱ (ቂያማ) እውን በሆነች ጊዜ፤"},{"id":2,"translation":"2. (ቂያማ) እውን ለመሆኗ አንዲትም አስተባባይ ነፍስ የለችም።"},{"id":3,"translation":"3. እርሷ (ገሚሱን) ዝቅ አድራጊና (ገሚሱን) ደግሞ ከፍ አድራጊ ናት::"},{"id":4,"translation":"4. ምድር መናወጥን በተናወጠች ጊዜ::"},{"id":5,"translation":"5. ተራራዎች (እንደተፈጨ ዱቄት) መፈርፈርን በተፈረፈሩ ጊዜ።"},{"id":6,"translation":"6. የተበተነ ብናኝ በሆኑም ጊዜ::"},{"id":7,"translation":"7. እናንተ (ሰዎች) ሶስት ዓይነቶችም በሆናችሁ ጊዜ (ገሚሱን ዝቅ እና ገሚሱን ከፍ ታደርጋለች)::"},{"id":8,"translation":"8. እናም በዚያ ቀን የቀኝ ጓዶች ለመሆን የበቁ ሁሉ ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው::"},{"id":9,"translation":"9. የግራ ጓዶች ምን (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች ናቸው::"},{"id":10,"translation":"10. እነዚያ (ለበጎ ስራ) ቀዳሚዎች የሆኑ ሁሉ (ለገነትም) ቀዳሚዎች ናቸው::"},{"id":11,"translation":"11. እነዚያ (በአላህ ዘንድም) ባለሟሎች ናቸው"},{"id":12,"translation":"12. በመደሰቻ ገነቶች ውስጥ ሲሆኑ"},{"id":13,"translation":"13. (የዚህ እድል ባለ ቤቶች) ከፊተኞቹ ብዙ ቡድኖች ናቸው::"},{"id":14,"translation":"14. ከኋለኞቹ ግን ጥቂቶች ናቸው::"},{"id":15,"translation":"15. በተሸሞኑ አልጋዎች ላይ ይሆናሉ::"},{"id":16,"translation":"16. በእርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲሆኑ።"},{"id":17,"translation":"17. እነርሱን (ለማገለገል) በእነርሱ ዙሪያ ሁልጊዜ የማያረጁ ወጣት ልጆች ይዘዋወራሉ።"},{"id":18,"translation":"18. ከ(ጠጅ) ምንጭ በብርጨቆዎች፣ በኩስኩስቶችና (እብሪቆች) በጽዋም በእነርሱ ዙሪያ እንዲዞሩ ይደረጋሉ።"},{"id":19,"translation":"19. ከእርሷ የራስ ምታት እንኳን አያገኛቸዉም:: አይሰክሩምም::"},{"id":20,"translation":"20. ከእሸቶች ከሚመርጡት ዓይነት"},{"id":21,"translation":"21. ከሚፈልጉት የበራሪ ስጋ ይዘው ይዞሩላቸዋል::"},{"id":22,"translation":"22. ዓይናማዎች የሆኑ ነጫጭ ቆንጆ ሴቶችም አሏቸው::"},{"id":23,"translation":"23. ልክ እንደተሸፈነ ሉል የሚመስሉ::"},{"id":24,"translation":"24. ለዚያ ይሰሩት በነበሩት መልካም ተግባር ምክንያት ዋጋ ይሆን ዘንድ ይህንን አደረግንላቸው።"},{"id":25,"translation":"25. በውስጧ ውድቅ ንግግርንና መወንጀልንም አይሰሙም።"},{"id":26,"translation":"26. ሰላም ሰላም መባባልን ግን ይሰማሉ::"},{"id":27,"translation":"27. የቀኝ ጓዶች ምንኛ የከበሩ የቀኝ ጓዶች ናቸው::"},{"id":28,"translation":"28. በተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው::"},{"id":29,"translation":"29. ፍሬው በተነባበረ ሙዝ ዛፍም ውስጥ ናቸው።"},{"id":30,"translation":"30. በተዘረጋ ጥላ ስርም ናቸው::"},{"id":31,"translation":"31. በሚንቧቡ ውሃ አጠገብም ናቸው::"},{"id":32,"translation":"32. በብዙ ዓይነት ፍራፍሬዎችም ውስጥ ናቸው።"},{"id":33,"translation":"33. ምንጊዜም የማትቋረጥ የማትከለከልም የሆነች፤"},{"id":34,"translation":"34. ከፍ በተደረጉ ምንጣፎች ላይም ናቸው።"},{"id":35,"translation":"35. እኛ (የገነት ሴቶችን) አዲስ ፍጥረት አድርገን ፈጠርናቸው::"},{"id":36,"translation":"36. እናም ደናግሎችም አደረግናቸው::"},{"id":37,"translation":"37. ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎችና እኩያዎች አደረግናቸው::"},{"id":38,"translation":"38. ለቀኝ ጓዶች አዘጋጀናቸው::"},{"id":39,"translation":"39. ከፊተኞቹ ብዙ ቡድኖች ናቸው::"},{"id":40,"translation":"40. ከኋለኞቹም ብዙ ቡድኖች ናቸው::"},{"id":41,"translation":"41. የግራ ጓዶችም ምንኛ የተዋረዱ የግራ ጓዶች ናቸው::"},{"id":42,"translation":"42. በመርዛም ንፋስና በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው::"},{"id":43,"translation":"43. ከጥቁር ጭስም በሆነ ጥላ ውስጥ"},{"id":44,"translation":"44. ቀዝቃዛም መልካምም ያልሆነ"},{"id":45,"translation":"45. እነርሱ ከዚህ በፊት የነብያትን አስተምህሮት ወደ ጎን የተው የዱንያ ቅምጥሎች ነበሩና::"},{"id":46,"translation":"46. በከባድ ኃጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና::"},{"id":47,"translation":"47. (እንዲህ) ይሉ ነበርም፡ \"ሞተን አፈር፣ አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን?"},{"id":48,"translation":"48. \"የፊተኞቹ አባቶቻችንንም (ይቀሰቀሳሉን)?\" (ይሉ ነበር)"},{"id":49,"translation":"49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) \"ፊተኞቹም ሆኑ ኋለኞቹ"},{"id":50,"translation":"50. \"በተወሰነ ቀን ቀጠሮ በእርግጥ ተሰብሳቢዎች ናቸው\" በላቸው::"},{"id":51,"translation":"51. ከዚያም እናንተ ጠማሞችና አስተባባዩች ሆይ!"},{"id":52,"translation":"52. ከዘቁም ዛፍ በእርግጥ በይዎች ናችሁ::"},{"id":53,"translation":"53. ከእርሷም ሆዶቻችሁን ሞይዎች ናችሁ::"},{"id":54,"translation":"54. በእርሱ ላይም ከፈላ ውሃ ጠጪዎች ናችው::"},{"id":55,"translation":"55. የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ብጤ ጠጪዎች ናቸው::"},{"id":56,"translation":"56. ይህ የፍርዱ ቀን መስተንግዷቸው ነው::"},{"id":57,"translation":"57. (ሰዎች ሆይ!) እኛ ፈጠርናችሁ አታምኑምን?"},{"id":58,"translation":"58. በሴቶች ማህጸኖች የምታፈሱትን (የምትረጩትን ፍትወት) አያችሁን?"},{"id":59,"translation":"59. እናንተ ትፈጥሩታላችሁን! ወይስ እኛ ነን ፈጣሪዎቹ?"},{"id":60,"translation":"60. እኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም::"},{"id":61,"translation":"61. ብጤዎቻችሁን በመለወጥና በዚያ በማታውቁትም ቅርጽ እናንተኑ በመፍጠር ላይ (አንሸነፍም)።"},{"id":62,"translation":"62. የፊተኛይቱን አፈጣጠር በእርግጥ አውቃችኋል አትገነዘቡምን?"},{"id":63,"translation":"63. የምትዘሩትን (አዝርአት) አያችሁን"},{"id":64,"translation":"64. እናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን?"},{"id":65,"translation":"65. ብንሻ ኖሮ ደረቅ ስብርብር ባረደግነው እና የምትደነቁም በሆናችሁ ነበር::"},{"id":66,"translation":"66. \"እኛ በእዳ ተያዥዎች ነን::"},{"id":67,"translation":"67. \"በእርግጥም እኛ (ከመጠቀም) የተከለክልን ነን\" ትሉ ነበር።"},{"id":68,"translation":"68. ያንን ምትጠጡትን ውሃ አያችሁን?"},{"id":69,"translation":"69. እናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን?"},{"id":70,"translation":"70. ብንፈልግ ኖሮ መርጋጋ ባደረግነው ነበር:: አታመሰግኑምን?"},{"id":71,"translation":"71. ያችንም የምትሰብቋትን እሳት አያችሁን?"},{"id":72,"translation":"72. እናንተ ዛፏን ፈጠራችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹ ነን?"},{"id":73,"translation":"73. እኛ ለገሀነም ማስታወሻ ለመንገደኞችም መጠቀሚያ አደረግናት::"},{"id":74,"translation":"74. የታላቁን ጌታህንም ስም አጥራው::"},{"id":75,"translation":"75. በከዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ::"},{"id":76,"translation":"76. እርሱም ብታውቁ ታላቅ መሀላ ነው::"},{"id":77,"translation":"77. እርሱ የተከበረ ቁርኣን ነው::"},{"id":78,"translation":"78. በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥም ነው::"},{"id":79,"translation":"79. የተጥራሩት እንጂ ሌላ አይነካዉም::"},{"id":80,"translation":"80. ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው::"},{"id":81,"translation":"81. በዚህ ንግግር እናንተ ቸልተኞች ናችሁን?"},{"id":82,"translation":"82. ሲሳያችሁንም (ዝናብን) እናንተ የምታስተባበሉት ታደርጋላችሁን?"},{"id":83,"translation":"83. ነፍስ ጉሮሮንም በደረሰች ጊዜ::"},{"id":84,"translation":"84. እናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትሆኑ፤"},{"id":85,"translation":"85. እኛም ግን እናንተ አታዩም እንጂ ከናንተ ይልቅ ወደ እርሱ የቀረብን ነን::"},{"id":86,"translation":"86. የማትዳኙም ከሆናችሁ"},{"id":87,"translation":"87. እውነተኞች እንደሆናችሁ ነፍሲቱን ወደ አካል ለምን አትመልሷትም?"},{"id":88,"translation":"88. እናም ሟቹ ከባለሟሎቹ ከሆነም፤"},{"id":89,"translation":"89. ለእርሱ እረፍት መልካም ሲሳይና የመጠቀሚያ ገነት አለው::"},{"id":90,"translation":"90. ሟቹ ከቀኝ ጓዶችም ከሆነ"},{"id":91,"translation":"91.\"ከቀኝ ጓዶች ስለሆንክ ላንተ ሰላም ነው የሚገባህ\" ይባላል።"},{"id":92,"translation":"92. ሟች ከእነዚያ ከሚያስተባብሉት ጠማማዎች ከሆነ ደግሞ"},{"id":93,"translation":"93. ከፈላ ውሃ የሆነ መስተንግዶ አለለት::"},{"id":94,"translation":"94. በገሀነም መቃጠልም አለለት::"},{"id":95,"translation":"95. ይህ እርሱ እርግጠኛው እውነት ነው::"},{"id":96,"translation":"96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የታላቁ ጌታህን ስም አጥራው::"}]},{"id":57,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉ ሁሉ አላህን አጠሩ። እርሱም ኃያሉና ጥበበኛው ነው።"},{"id":2,"translation":"2. የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱው ብቻ ነው:: ሕይወትን የሚሰጥና ሕይወትን የሚነሳ እሱው ብቻ ነው:: እርሱ ሁሉንም ነገር ቻይ ነውና::"},{"id":3,"translation":"3. እርሱ ( ከበፊቱ ምንም ያልቀደመው) የመጀመሪያ! (ፊት ያለ) (ከኋላው ምንም የሌለ የመጨረሻ) ብቻዉን ቀሪ፤ ከበላዩ ማንም የሌለ (ግልጽና የበላይ) ስውርም (ድብቅ) ነው:: እርሱ (በምድርም ሆነ በሰማይ ያለን) ሁሉ ነገር አዋቂ ነው::"},{"id":4,"translation":"4. እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ብቻ የፈጠረ ነው:: ከዚያ በዐርሹ ላይ ከፍ አለ። ወደ ምድር የሚገባውንና ከእርሷ የሚወጣውን ያውቃል:: ከሰማይ የሚወረደውንና ወደ እርሷ የሚወጣውን ያውቃል:: እርሱ የትም ብትሆኑ (በእውቀቱ) ከናንተው ጋር ነው:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::"},{"id":5,"translation":"5. የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ ነው:: ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ::"},{"id":6,"translation":"6. ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል:: ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል:: እርሱም በልቦች ውስጥ የተደበቁትን ሁሉ አዋቂ ነው::"},{"id":7,"translation":"7. (ሰዎች ሆይ!) በአላህና በመልዕክተኛው እመኑ:: አላህ በእርሱ ላይ ተተካኪዎች ካደረጋችሁ ገንዘብ ዉስጥም ለግሱ:: እነዚያ ከእናንተ መካከል በአላህ ያመኑትና የለገሱት ሁሉ ለእነርሱ ታላቅ ምንዳ አለላቸው::"},{"id":8,"translation":"8. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁም ቃልኪዳናችሁን የያዘባችሁ ሲሆን መልዕክተኛውም በጌታችሁ እንድታምኑ የሚጠራችሁ ሲሆን በአላህ የማታምኑበት ምን ምክኒያት አላችሁ? እናንተ በትክክል የምታምኑ ከሆናችሁ?"},{"id":9,"translation":"9. እርሱ ከጨለማዎች ወደ ብርሀን ሊያወጣችሁ ግልፆች የሆኑን አናቅጽ በባሪያው ላይ የሚያወርድ ነው:: አላህ ለእናንተ በእርግጥ ሩህሩህ አዛኝ ነው::"},{"id":10,"translation":"10. የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ ብቻ ሲሆን በአላህ መንገድ የማትለግሱበት ምን ምክንያት አላችሁ? ከናንተ መካከል ከመካ መከፈት በፊት የለገሰና የተጋደለ ሰው ከተከፈተ በኋላ ከለገሰና ከተጋደለ ሰው ጋር አይስተከከልም:: ከእነዚያ በኋላ ከለገሱትና ከተጋደሉት እነዚህ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸውና:: ሁሉንም አላህ የመልካሚቱን ተስፋ ቃል ገብቶላቸዋል:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::"},{"id":11,"translation":"11. ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና ለእርሱ አላህ ምንዳውን የሚያነባብርለት ሰው ማን ነው? ለእርሱም መልካም ምንዳ አለው::"},{"id":12,"translation":"12. ወንድ ትክክለኛ አማኞችንና ሴት ትክክለኛ አማኞችን በስተፊቶቻቸው በቀኞቻቸዉም ብርሀናቸው የሚሮጥ ሲሆን በምታያቸው ቀን (ታላቅ ምንዳ አለላቸው።) \"ዛሬ ብስራታችሁ በውስጦቻቸው ዘውታሪዎች ስትኾኑ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸው ገነቶች ናቸው (ይባላሉ)፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ እድል ነው::"},{"id":13,"translation":"13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የወንድ አስመሳዮችና የሴት አስመሳዮች ለእነዚያ በአላህ ላመኑት \"ጠብቁን ከብርሀናችሁ እናበራለንና\" የሚሉበትን ቀን አስታውስ:: \"ወደ ኋላችሁ ተመለሱ:: ብርሀንንም እዚያው ፈልጉ\" ይባላሉ:: በመካከላቸዉም ለእርሱ ደጃፍ ባለው አጥር ይከለላል:: ግቢው በውስጡ ገነት ያለበት ከውጪዉም በኩሉ ደግሞ የእሳት (ስቃይ) ያለበት የሆነ (ደጃፍ ባለው አጥር ይከለላል)።"},{"id":14,"translation":"14. \"ከናንተ ጋር አልነበርንምን?\" በማለት ይጠሯቸዋል:: \"እውነት ነው እኛ ጋር ነበራችሁ:: ግን እናንተ ነፍሶቻችሁን አጠፋችሁ:: በነብዩ አደጋዎችን ተጠባበቃችሁ ትጠራጠራላችሁም:: የአላህ ትዕዛዝ እስከ መጣ ድረስ ከንቱ ምኞቶች አታለሏችሁ። አታላዩም ሰይጣን በአላህ መታገስ ሸነገላችሁ ይሏቸዋል::"},{"id":15,"translation":"15. በመሆኑም ዛሬ ከናንተም ሆነ በአላህ ከካዱት ሰዎች የገንዘብ ክፍያ (ቤዛ) አይወሰድም:: መኖሪያችሁ የገሀነም እሳት ብቻ ናት:: እርሷ ተገቢያችሁ ናትና:: የገሀነም እሳት መመለሻነቷ ምን ትከፋም\" (ይሏቸዋል)::"},{"id":16,"translation":"16. ለእነዚያ (በአላህ) ላመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርኣንም ለወረደው እውነታ ልቦቻቸው ሊፈሩ፤ እንደነዚያ በፊት መጽሐፍን እንደ ተሰጡትና በእነርሱ ላይ ጊዜ ስለ ረዘመባቸው ልቦቻቸውም እንደ ደረቁባቸው ህዝቦች የማይሆኑበት ጊዜ አልቀረበምን? ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው።"},{"id":17,"translation":"17. (ሰዎች ሆይ!) አላህ ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው የሚደርጋት መሆኑን እወቁ። ታውቁም ዘንድ አናቅጽን ለእናንተ በእርግጥ አብራራንላችሁ።"},{"id":18,"translation":"18. የመጸወቱ ወንዶችና የመጸወቱ ሴቶች ለአላህ መልካምን ብድር ያበደሩ ሁሉ ለእነርሱም ምንዳ ይደራረብላቸዋል:: ለእነርሱም መልካም የተከበረ ምንዳ አለላቸው::"},{"id":19,"translation":"19. እነዚያ በአላህና በመልዕክተኞቹ ያመኑ ሰዎች እነዚያ እነርሱ በጣም እውነቶኞች በጌታቸዉም ዘንድ መስካሪዎች ናቸው:: ለእነርሱ ምንዳቸውም ብርሀናቸዉም አለላቸው:: እነዚያ (በአላህ) የካዱትና በአናቅጻችን ያስተባበሉ ሰዎች ደግሞ የእሳት ጓዶች ናቸው::"},{"id":20,"translation":"20. (ሰዎች ሆይ!) ቅርቢቱን ሕይወት ጨዋታና ዛዛታ፤ ማጌጫም፤ በመካከችሁም መፎካከሪያ፤ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መሆኗን እወቁ:: እርሷ በቃዩ ገበሬዎችን ቡቃያው እንደሚያስደስት ዝናብና ከዚያ በቃዩ እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደሚታየው ከዚም የተሰባበረ እንደሚሆን ብጤ ነው:: በመጨረሻይቱም ዓለም ለአጥፊዎች ብርቱ ቅጣት፤ ለትክክለኛ አማኞች ከአላህ ምህረትና ውዴታ አለ:: የቅርቢቱ ሕይወት እኮ የመታለያ ጥቅም እንጂ ሌላ አይደለችም::"},{"id":21,"translation":"21. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በአላህና በመልዕክተኞች ላመኑት ወደ ተዘጋጀችውና የወርዷ ስፋት እንደ ሰማይና ምድር ወደ ሆነችም ገነት ተሸቀዳደሙ:: ይህ የአላህ ችሮታ ነው:: ለሚፈልገው ሰው ብቻ ይሰጠዋል:: አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና::"},{"id":22,"translation":"22. በምድርም ሆነ በነፍሶቻችሁ መከራ ማንንም አታጋጥምም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትሆን እንጂ:: ይህ በአላህ ላይ ቀላል ነው::"},{"id":23,"translation":"23. (ይህን ማሳወቃችን) ባመለጣችሁ ጸጋ ላይ እንዳታዝኑና አላህ በሰጣችሁ ነገር (በትዕቢት) እንዳትደሰቱ ነው:: አላህ ኩራተኛንና ጉረኛን ሁሉ አይወድምና::"},{"id":24,"translation":"24. እነርሱም እነዚያ የሚሰስቱና ሰዎችንም በስስት ላይ የሚያዙ ናቸው:: ከእውነት የሚሸሽ (ሰው) ሁሉ ጉዳቱ ለራሱ ብቻ ነው:: አላህ ተብቃቂ ና ምስጉን ነውና::"},{"id":25,"translation":"25. መልዕክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች አጠናክረን በእርግጥ ላክን:: ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን:: ብረትንም ከውስጡ ብርቱ ኃይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ሲሆን አወረድን:: አላህ ሃይማኖትንና መልዕክተኞችን በሩቁ ሆኖ የሚረዳውን (ሰው) ሊያውቅ (ሊገልጽ) አወረደው:: አላህ ብርቱና አሸናፊ ነውና::"},{"id":26,"translation":"26. ኑህንና ኢብራሂምን በእርግጥ ላክን:: በዘሮቻቸዉም ውስጥ ነብይነትንና መጽሐፍትን አደረግን:: ከእነርሱም መካከል ቅን ሰው አለ:: ከእነርሱም መካከል ብዙዎቹ ግን አመጸኞች ናቸው::"},{"id":27,"translation":"27. ከዚያም በእነርሱ ፈለጋቸው ላይ መልዕክተኞችን አከታተልን:: የመርየም ልጅን ዒሳንም አስከተልን:: ኢንጂልንም ሰጠነው:: በእነዚያም በተከተሉት ሰዎች ልቦች ውስጥ መለዘብንና እዝነትን አደረግን፤ አዲስ የፈጠሯትንም ምንኩስና በእነርሱ ላይ አልደነገግንም:: ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ከራሳቸው ፈጠሯት:: ተገቢ አጠባበቅንም አልጠበቋትም:: ከእነርሱም መካከል በአላህ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው:: ከእነርሱ ብዙዎቹ ግን አመጸኞች ናቸው::"},{"id":28,"translation":"28. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ:: በመልክተኛዉም እመኑ:: ከችሮታው ሁለትን ክፍሎች ይሰጣችኋልና:: ለእናተም የምትሄዱበትን ብርሃን ያደርግላችኋል:: ለእናንተም ወንጀላችሁን ይምራል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነው::"},{"id":29,"translation":"29. (ይህም) የመጽሐፍ ሰዎች ከአላህ ችሮታ በምንም ላይ የማይችሉ መሆናቸውንና ችሮታዉም አላህ ለሚሻው ሰው ብቻ የሚሰጠው በእርሱ እጅ ብቻ መሆኑን እንዲያውቁ ነው:: አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው::"}]},{"id":58,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የዚያችን በባሏ ጉዳይ ላይ የምትከራከርህንና ወደ አላህ ስሞታን የምታሰማውን ሴትዮ ቃል ሰማ:: አላህ በንግግር መመላለሳችሁን (መወያየታችሁን) ይሰማል:: አላህ (ለሚባለው) ሁሉ ሰሚ (ለሚፈጸመው ሁሉ ነገር) አዋቂ ነውና።"},{"id":2,"translation":"2. እነዚያ ከናንተ መካከል ሚስቶቻቸውን እንደእናቶቻቸው ጀርባዎች ይሁኑብን በማለት የሚምሉ ሰዎች እነርሱ እናቶቻቸው አይደሉም:: ትክክለኛ እናቶቻቸው እነዚያ የወለዷቸው ሴቶች ብቻ ናቸው:: እነርሱ በዚህ ቃል የተጠላ ንግግርንና ውሸትን በእርግጥ ይናገራሉ:: አላህ ለሚጸጸት ሰው ሁሉ ይቅር ባይና መሀሪ ነው::"},{"id":3,"translation":"3. እነዚያ ሚስቶቻቸውን እንደእናቶቻቸው ጀርባዎች ይሁኑብን በማለት የሚምሉና ከዚያ ወደ ተናገሩት የሚመለሱ ሳይነካኩ በፊት በባርነት የተያዘችዋን ጫንቃ ነፃ ማውጣት ግዴታ አለባቸው:: ይህ ህግ (የተጠቀሰው ህግ) በእርሱ ትገሰጹበታላችሁ:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።"},{"id":4,"translation":"4. ይህን ላላገኘም ሰው ከመነካካታቸው በፊት ሁለት ተከታታይ ወሮችን መፆም አለበት:: ይህን ላልቻለም ሰው ስልሳ ድሆችን ማብላት አለበት:: ይህ በአላህና በመልዕክተኛው እንድታምኑ ነው:: እነኚህ ህግጋት የአላህ ህግጋት ናቸው:: (እናም አትተላለፏቸው::) ለከሓዲያንም ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":5,"translation":"5. ግልጽ ማስረጃዎችን ያወረድን ስንሆን እነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን የሚከራከሩ ሰዎች እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩ ሰዎች እንደተዋረዱት ሁሉ ተዋርደዋል:: ለከሓዲያን አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":6,"translation":"6. አላህ ሁላቸውንም በአንድ አድርጎ (አንድም ሳይቀር በአንድ ዓይነት) በሚቀሰቅሳቸው ቀን (ይቀጣቸዋል):: ከዚያም በዚህ ዓለም የሰሩትን ነገር ሁሉ ይነግራቸዋል:: እነርሱ የረሱት ሲሆን (መዝገባቸው ተመዝግቦ ያገኙታል) አላህ ግን አንድም ሳይቀር አውቆታል:: አላህ ሁሉንም ነገር ተመልካች ነውና::"},{"id":7,"translation":"7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ መሆኑን አታውቅምን? (በእውነቱ ሁሉንም አካቧል::) የሶስት ሰዎች መንሾካሾክ አይከሰትም፤ አላህ አራተኛው ቢሆን እንጂ፤ የአምስትም ሰዎች መንሾካሾክ አይከሰትም እርሱ ስድስተኛ ቢሆን እንጂ፤ ከዚያ ያነሰም ይሁን የበዛ ሰው መሾካሾክ አይከሰትም እርሱ ባሉበት ቦታ አብሯቸው ቢሆን እንጂ:: ከዚያ በትንሳኤ ቀን የሰሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል:: አላህ ሁሉን ነገር አዋቂ ነው።"},{"id":8,"translation":"8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ በመጥፎ ነገር ከመመሳጠር ወደ ተከለከሉት፤ ከዚያ ከእርሱ ወደ ተከለከሉት ነገር የሚመለሱትንና በኃጢአት፣ በጠላትነትና መልዕክተኛውን በመቃወም ወደ ሚመሳጠሩ አላየህምን? (ሰላም ሊሉ) ወደ አንተ በመጡ ጊዜ አላህ ባላናገረህ ቃል ያናግሩሃል:: ውስጣቸው ይህ ሰው ነብይ ከሆነ በምንለው ነገር አላህ አይቀጣንም ኖሯልን? (ነብይ ከሆነስ) የለመነውን ነገር አላህ ተቀብሎት በሞትን ነበር ይላሉ:: ገሀነም የሚገቡባት ሲሆኑ ከአሁኑ ሞት ይልቅ በቂያቸው ናት:: ገሀነምም መመለሻነቷ ከፋች!"},{"id":9,"translation":"9. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተመሳጠራችሁ ጊዜ በኃጢአት ወሰንን በማለፍና መልዕክተኛውንም በመቃወም አትሾካሾኩ ግን በበጎ ስራና አላህን በመፍራት ተወያዩ:: ያንንም ወደ እርሱ የምትሰበሰቡበትን አላህን ፍሩ::"},{"id":10,"translation":"10. በመጥፎ መመሳጠር ከሰይጣን ማስዋብና ማሳመር የሚመጣ ብቻ ነው:: እነዚያ ያመኑ ሙስሊሞች ያዝኑ ዘንድ ይቀሰቅሰዋል:: ከአላህ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር የሰይጣንም መመሳጠር በምንም ነገር አይጎዳቸዉም:: እናም ትክክለኛ አማኞች በአላህ ብቻ ይመኩ::"},{"id":11,"translation":"11. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ በመቀመጫዎች ስፍራ ተስፋፉ በተባላችሁ ጊዜ ስፍራን አስፉ:: አላህ በገነት ያሰፋላችኃልና:: ተነሱ በተባለም ጊዜ ተነሱ:: አላህ ከናንተ መካከል እነዚያን በትክክል ያመኑትንና እነዚያንም እውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች (በዚች ዓለምም ሆነ በአኼራ) ከፍ ያደርጋል:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አወቂ ነውና::"},{"id":12,"translation":"12. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከመልዕክተኛው ጋር በተወያያችሁ ጊዜ ከመወያየታችሁ በፊት ምጽዋትን አስቀድሙ:: (ሰደቃ ስጡ):: ይህ (ምጸዋትን አስቀድሞ መስጠት) ለእናንተ መልካምና አጥሪ ነው:: ባታገኙም ምንንም (ሳትከፈሉ) ሳትሰጡ ብትወያዩ ችግር የለባችሁም:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":13,"translation":"13. ከውይይታችሁ በፊት ምጽዋቶችን በማስቀደም ድህነትን ፈራችሁን? የታዘዛችሁትን ባልሰራችሁ ጊዜ አላህ ከናንተ ጸጸትን የተቀበለ ሲሆን ሶላትን ስገዱ፤ ዘካንም ስጡ፤ አላህንና መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: አላህ በምትሰሩት ነገር ውስጠ አዋቂ ነውና::"},{"id":14,"translation":"14. ወደ እነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ የተቆጣባቸውን ህዝቦች (አይሁዶች) ወደ ተወዳጁት አስመሳዮች አላየህምን? እነርሱ ከናንተ አይደሉም:: ከእነርሱም አይደሉም። እያወቁ በውሸት ይምላሉ።"},{"id":15,"translation":"15. አላህ ለእነርሱ (በዚህ መወዳጃና የሀሰት መሀላ) ብርቱ ቅጣትን አዘጋጀ:: እነርሱ ይሰሩት የነበሩት መጥፎ ስራ ምንኛ ከፋ!"},{"id":16,"translation":"16. መሓሎቻቸውን ጋሻ አድርገው ያዙ:: ሰዎችንም ከአላህ መንገድ አገዱ:: ስለዚህ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":17,"translation":"17. ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸውም ከአላህ (ቅጣት) ምንም አያድኗቸዉም:: እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘወታሪዎች ናቸው::"},{"id":18,"translation":"18. አላህ የተሰበሰቡ ሆነው በሚያስነሳቸውም ቂያማ ቀን ለእናንተ እንደ ሚምሉላችሁ በሚጠቅም ነገር ላይ መሆናቸውን የሚያስቡ ሆነው ለእርሱም (ለአላህም) ይምላሉ:: ሙስሊሞች አስተዉሉ:: ውሸታሞች እነርሱ ብቻ ናቸው::"},{"id":19,"translation":"19. በእነርሱም ላይ ሰይጣን ተሾመባቸው (ተመቻቸባቸው) እናም አላህን ማስታወስን አስረሳቸው( ትዕዛዛቱን ተው):: እነዚያ የሰይጣን ቡድኖች ( ሰራዊቶች) ናቸው:: ሙስሊሞች አስተዉሉ:: የሰይጣን ቡድኖች ከሳሪዎች እነርሱ ብቻ ናቸው::"},{"id":20,"translation":"20. እነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን የሚከራከሩ ሁሉ እነዚያ በዱንያም ሆነ በአኺራ በጣም ከተዋረዱ ወገኖች ውስጥ ናቸው::"},{"id":21,"translation":"21. አላህ እኔ አሸንፋለሁ መልዕክተኞቼም እንዲሁ ያሸንፋሉ ሲል ድሮውኑ ጽፏል:: አላህ ብርቱና አሸናፊ ነውና::"},{"id":22,"translation":"22. በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ህዝቦች አላህንና መልዕክተኛውን የሚከራከሩት ሰዎች አባቶቻቸው ወይም ልጆቻቸው ወይም ወንድሞቻቸው ወይም ዘመዶቻቸው ቢሆኑም እንኳ የሚወዳጁ ሆነው አታገኛቸዉም:: እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል:: ከእርሱም በሆነ መንፈስ ደግፏቸዋል:: ከስሮቻቸዉም ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ ያስገባቸዋል:: አላህ ተግባራቸውን ወዷል:: እነርሱም የእርሱን ችሮታ ወደዋል:: እነዚያ የአላህ ህዝቦች ናቸው:: ንቁ! የአላህ ህዝቦች ምኞታቸውን የሚያገኙ እነርሱ ናቸው::"}]},{"id":59,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ አላህን አጠራ:: እርሱም ሁሉንም አሸናፊና ጥበበኛው ነው::"},{"id":2,"translation":"2. እርሱ ያ! ከመጽሐፍ ሰዎች መካከል እነዚያን በአላህ የካዱትን ወገኖች ከቤቶቻቸው የመጀመሪያውን ማስወጣት ያስወጣቸው ነው:: (ሙስሊሞች ሆይ!) መውጣታቸውንም አላሰባችሁትም ነበር:: እነርሱም ምሽጎቻቸው ከአላህ ኃይል የሚከላከሉላቸው መሆናቸውን አሰቡ:: አላህ ግን ካላሰቡት በኩል መጣባቸው:: እናም በልቦቻቸው ውስጥ መርበድበድን (ፍርሃትን) ጣለባቸው:: ቤቶቻቸውን በገዛ እጆቻቸውና በትክክለኛ አማኞች እጅ ያፈርሳሉ (አፈረሱ):: እናንተ የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! አስተውሉ::"},{"id":3,"translation":"3. በእነርሱም ላይ አላህ ከአገር መውጣትን ባልፈረደ ኖሮ በቅርቢቱ ዓለም በቀጣቸው ነበር:: ለእነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም የእሳት ቅጣት አለባቸው::"},{"id":4,"translation":"4. ይህ እነርሱ አላህንና መልዕክተኛውን በመከራከራቸው ምክንያት ነው:: አላህን የሚከራከር ሰው ሁሉ (ይቀጣዋል።) አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና ይቀጣቸዋል::"},{"id":5,"translation":"5. ከዘንባባ (ከተምር ዛፍ) ማንኛዋም የቆረጣችኋት ወይም በግንዶቿ ላይ የቆመች ሆና የተዋችኋት ሁሉ በአላህ ፈቃድ ነው:: አመጸኞችንም ያዋርድ ዘንድ (መቁረጥን ፈቀደ)::"},{"id":6,"translation":"6. ከእነርሱም ገንዘብ ወደ መልዕክተኛው አላህ የመለሰውን በእርሱ ላይ ፈረሶችንና ግመሎችን አላስጋልባችሁበትም:: ግን አላህ መልዕክተኞቹን በሚሻው ላይ ይሾማል:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና::"},{"id":7,"translation":"7. አላህ ከከተሞች ሰዎች ሀብት መካከል በመልዕክተኛው ላይ የመለሰው ሀብት ከናንተ ውስጥ በሀብታሞች መካከል ብቻ ተዘዋዋሪ እንዳይሆን ለአላህና ለመልዕክተኛው፤ ለዝምድና ባለቤትም፤ አባት ለሌላቸው የቲም ልጆችም፤ ለድሆችና፤ ለመንገደኛ፤ የሚሰጥ ነው:: መልዕክተኛው የሰጣችሁን ሁሉ ማንኛዉም ነገር ያዙት:: የከለከላችሁን ነገር ሁሉም ተከልከሉ:: አላህን ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና::"},{"id":8,"translation":"8. ለእነዚያ የአላህን ችሮታና ውዴታውን የሚፈልጉና አላህንና መልዕክተኛውን የሚረዱ ሆነው ከአገሮቻቸውና ከገንዘቦቻቸው ለተወጡ (ለተባረሩ) ስደተኞች ድሆች ይሰጣል:: እነዚያ እነርሱ እውነተኞች ናቸው::"},{"id":9,"translation":"9..እነዚያ ከበፊታቸው ሀገሪቱን መዲና መኖሪያ ያደረጓትና እምነት በልባቸው የሰረጸባቸው ወደ እነርሱ የተሰደዱትን ሰዎች ይወዳሉ:: ስደተኞችም ከተሰጡት ነገር ላይ በልቦቻቸው ውስጥ እንኳን ምንም ቅሬታን አያሳድሩም:: በእነርሱ ላይ ችግር ቢኖርባቸዉም እንኳ በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ያስቀድማሉ:: ከነፍሶቻቸው ንፉግነት የሚጠበቁ ሰዎች ሁሉ እነዚያ የተሳካለቸውና ምኞታቸውን አግኚዎች ማለት እነርሱ ብቻ ናቸው::"},{"id":10,"translation":"10. እነዚያ ከበኋላቸው የመጡት «ጌታችን ሆይ! ለእኛም ለእነዚያም በእምነት ለቀደሙን ወንድሞቻችንም ምህረት አድርግ:: በልቦቻችንም ውስጥ ለእነዚያ ለአመኑት ሰዎች ሁሉ ጥላቻን አታድርግ:: ጌታችን ሆይ! አንተ ሩህሩህ፤ አዛኝ ነህና» ይላሉ።"},{"id":11,"translation":"11. እነዚያን ወደ ንፍቅና የገቡትን አላወክምን? ከመጽሐፍ ሰዎች መካከል ለእነዚያ ለካዱት ወንድሞቻቸው «ከአገር ብትባርሩ አብረናችሁ እንወጣለን:: በእናንተ ጉዳይ አንድንም ሰው በፍጹም ሁልጊዜም አንታዘዝም:: ጦርነት ቢታወጅባችሁም በእርግጥ እንረዳችኋለን» ይሏቸዋል:: አላህም እነርሱ ውሸታሞች መሆናቸውን ይመሰክራል::"},{"id":12,"translation":"12. ቢባረሩም አብረዋቸው አይባረሩም:: ቢገደሉም (ቢወጉም) ቢዘመትባቸዉም አይረዱዋቸዉም:: ቢረዷቸዉም ለሽሽት ጀርባዎችን ያዞራሉ:: ከዚያም እርዳታን አያገኙም::"},{"id":13,"translation":"13. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እናንተ በልቦቻቸው ውስጥ በማስፈራራት ከአላህ ይልቅ የበረታችሁ (የከበዳችሁ) ናችሁ:: ይህም የሆነው እነርሱ የማይገነዘቡ ህዝቦች በመሆናቸው ነው::"},{"id":14,"translation":"14. በተመሸጉ ከተሞች ውስጥ ወይም ከአጥሮች በስተጀርባ ሆነው እንጂ የተሰበሰቡ ሆነው አይዋጓችሁም:: ኃይላቸው በመካከላቸው ብርቱ ነው:: ልቦቻቸው የተበታተኑ ሲሆን የተሰበሰቡ ናቸው ብለህ ትጠራጠራቸዋለህ (አንድ ይመስሉሃል):: ይህ እነርሱ አእምሮ የሌላቸው ህዝቦች በመሆናቸው ነው::"},{"id":15,"translation":"15. ብጤያቸው ልክ እንደነዚያ ከእነርሱ በፊት በቅርብ ጊዜ የተግባራቸውን ቅጣት እንደቀመሱት ወገኖች ብጤ ነው:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":16,"translation":"16. ምሳሌያቸው ልክ እንደዚያ ሰውን «በአላህ ካድ ብሎ ሰውየው በካደ ጊዜ እኔ ካንተ ንጹህ ነኝ እኔ የዓለማትን ጌታ አላህን እፈራለሁ» እንዳለው ሰይጣን ነው።"},{"id":17,"translation":"17. የሁለቱም መጨረሻቸው እነርሱ በውስጡ ዘወታሪዎች ሲሆኑ በእሳት ውስጥ መሆን ነው:: ይህም ቅጣት የበዳዩች ሁሉ ዋጋ ነው::"},{"id":18,"translation":"18. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን በትክክል ፍሩ:: ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፤ አላህን በትክክል ፍሩ:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::"},{"id":19,"translation":"19. እንደ እነዚያ አላህን እንደረሱትና ነፍሶቻቸውን እንዳስረሳቸው ሰዎች አትሁኑ:: እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው::"},{"id":20,"translation":"20. የእሳት ጓዶችና የገነት ጓዶች እኩል አይሆኑም:: የገነት ጓዶች ምኞታቸውን አግኝዎች ናቸውና::"},{"id":21,"translation":"21. (ሙሐመድ ሆይ)፤ ይህንን ቁርኣን በተራራ ላይ ባወረድነው ኖሮ ከአላህ ፍራቻ የተነሳ ተዋራጅና ተሰንጣቂ ሆኖ ባየኸው ነበር:: እነዚህን ምሳሌዎች ለሰዎች ያስተነትኑ ዘንድ እንገልፃቸዋለን::"},{"id":22,"translation":"22. እርሱ ያ አላህ ነው:: ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ፤ ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ የሆነ ነው:: እርሱ እጅግ በጣም ሩህሩህ፤ በጣም አዛኝ ነው::"},{"id":23,"translation":"23. እርሱ ያ አላህ ነው:: ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ፤ ንጉሱ፤ ከጎደሎ ሁሉ የጠራ፤ የሰላም ባለቤት፤ ጸጥታን ሰጪ፤ ባሮቹን ጠባቂ፤ አሸናፊ፤ ኃያልና ኩሩ ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው::"},{"id":24,"translation":"24. እርሱ አላህ ፈጣሪዉ፤ ከኢምንት አስገኚዉና ቅርጽን አሳማሪው ነው:: ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት:: በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ እርሱን ያሞግሳል:: እርሱም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::"}]},{"id":60,"verses":[{"id":1,"translation":"1. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጠላቶቼንና ጠላቶቻችሁን ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙ:: የመጣላችሁን ትክክለኛ ሃይማኖት የካዱ ሲሆኑ ውዴታን ለእነርሱ ታደርጋላችሁ:: እነርሱ መልዕክተኛውና እናንተን በጌታችሁ በአላህ ስላመናችሁ ብቻ ከሀገራችሁ አስወጧችሁ። በመንገዴ ለመታገልና ውዴታየን ለመፈለግ የወጣችሁ እንደሆናችሁ እነርሱን ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዟቸው:: እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን የማውቅ ስሆን ከእነርሱ ጋር ፍቅር ትመሳጠራላችሁ:: ከናንተ መካከልም ይህንን ሚፈጽም ሰው ቀጥተኛውን መንገድ በእርግጥ ስቷል::"},{"id":2,"translation":"2. ቢያሸንፏችሁ (ቢያገኟችሁ) ለእናንተ ጠላቶች ይሆናሉ:: እጆቻቸውና ምላሶቻቸውንም ወደ እናንተ በክፉ ይዘረጋሉ:: ብትክዱም ተመኙ::"},{"id":3,"translation":"3. ዘመዶቻችሁም ሆኑ ልጆቻችሁ በትንሳኤ ቀን አይጠቅሟችሁም:: አላህ በትንሳኤ ቀን በመካከላችሁ (ብይን በመስጠት) ይለያል:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::"},{"id":4,"translation":"4. ኢብራሂምና እነዚያ ከእርሱ ጋር አብረው የነበሩት አማኞች ለእናንተ መልካም አርአያ ናቸው:: ይኸዉም ለህዝቦቻቸው «እኛ ከናንተና ከዚያ ከአላህ ሌላ ከምትገዙት ጣዖታት ሁሉ ንጹሆች ነን:: በእናንተም ካድን:: በአላህ አንድነት እስከምታምኑ ድረስ በእኛና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ::» ባሉ ጊዜ ኢብራሂም ለአባቱ፡- «ላንተ ከአላህ ቅጣት ምንም የማልጠቅምህ (የማላድንህ) ስሆን ላንተ በእርግጥ ምህረትን እለምንልሃለሁ::» ማለቱ ብቻ ሲቀር «ጌታችን ሆይ ባንተ ላይ ተመካን ወደ አንተም ተመለስን መመለሻም ወደ አንተ ብቻ ነው::» (ባለው ተከተሉ።)"},{"id":5,"translation":"5. ጌታችን ሆይ! ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች መሞከሪያ አታድረገን:: ለእኛ ምህረት አድርግልን:: ጌታችን ሆይ! አንተ አሸናፊና ጥበበኛው ነህ::"},{"id":6,"translation":"6. ከናንተ መካከል አላህንና የመጨረሻውን ቀን ተስፋ ለሚያደርግ ሰው ሁሉ እነርሱ መልካም አርአያዎች አሉላችሁ:: ፊቱን የሚያዞር ሰው (ራሱን ብቻ ይጎዳል።) አላህ ብቸኛ፤ ተብቃቂና ምስጉን ነውና::"},{"id":7,"translation":"7. አላህ በእናንተና በእነዚያ ከእነርሱ ጋር በተጣላችሁት ሰዎች መካከል መፋቀርን ሊያደርግ ይከጀላል:: አላህ ሁሉን ማድረግ ቻይ ነው:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::"},{"id":8,"translation":"8. ለእነዚያ በሃይማኖት ላልተዋጓችሁ ከአገሮቻችሁም ላላስወጧችሁ ከሓዲያን መልካም ብትውሉላቸውና ወደ እነርሱ ፍትህ ልትውሉላቸው አላህ አይከለክላችሁም:: አላህ ትክክለኞችን (ፍትሃዊያን ትክክለኛ አማኞች) ይወዳልና::"},{"id":9,"translation":"9. አላህ የሚከለክላችሁማ ከእነዚያ በሃይማኖት ሰበብ ከተዋጓችሁና ከቤቶቻችሁም ያስወጧችሁ እናንተንም ከሀገር በማስውጣት ላይ የረዱትን እንዳትወዳጇቸው ብቻ ነው:: እነርሱን ወጃጅ የሚያደርጓቸው ሰዎች ሁሉ እነዚያ እነርሱ (ራሳቸዉን) በዳዩች ናቸው::"},{"id":10,"translation":"10. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሴት ምዕመናት ስደተኞች ሆነው ወደ እናንተ በሚመጡበት ጊዜ (ለሀይማኖት ሲሉ መሰደዳቸውን) ፈትኗቸው:: አላህ በእምነታቸው ከናንተ ይልቅ አዋቂ ነው:: ትክክለኛ አማኞችም መሆናቸውን ብታውቁ ወደ ከሓዲያን ባሎቻቸው አትመልሷቸው:: እነርሱ ሙስሊም ሴቶች ለከሓዲ ወንዶች አይፈቀዱምና:: ከሓዲያን ወንዶችም ለአማኝ ሴቶች የተፈቀዱ አይደሉምና:: ያወጡትንም ገንዘብ መህሩን ስጧቸው:: መህራቸውንም ከሰጣችኋቸው ብታገቧቸው ኃጢአት የለባችሁም :: የከሓዲያንንም ሴቶች የጋብቻ ቃል ኪዳኖች አትያዙ:: ሆኖም እናንተ ያወጣችሁትን ገንዘብ ጠይቁ :: እነርሱም ያወጡትን ይጠይቁ:: ይህ የአላህ ፍርድ ነውና:: በመካከላችሁም ይፈርዳል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::"},{"id":11,"translation":"11. ከሚስቶቻችሁም አንዳቸው ወደ ከሓዲያን ቢያመልጧችሁ ቀጥሎም ብትዘምቱባቸው ለእነዚያ ሚስቶቻቸው ለሄዱባቸው ሰዎች ያወጡትን ወጪ ያክል ስጧቸው። ያንንም እናንተ በእርሱ ያመናችሁበትን አላህን ፍሩት::"},{"id":12,"translation":"12. አንተ ነብይ ሆይ! ምዕመናቶቹ በአላህ ምንም ላያጋሩ፤ ላይሰርቁ፤ ላያመነዝሩ፤ ልጆቻቸውን ላይገድሉ፤ በእጆቻቸውና በእግሮቻቸው መካከል ኃጢአትን ላያመጡ (ላይሰሩ)፤ በበጎም ስራም ትዕዛዝን ላይጥሱ ቃል ኪዳን ሊገቡልህ ወደ አንተ በመጡ ጊዜ ቃል ኪዳን ተጋባቸው:: ለእነርሱም አላህን ምህረት ለምንላቸው:: አላህ በጣም መሀሪና እጂግ በጣም አዛኝ ነውና::"},{"id":13,"translation":"13. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ በእነርሱ ላይ የተቆጣባቸውን ህዝቦች አትወዳጁ:: ከሓዲያን ከመቃብር ሰዎች ተስፋ እንደቆረጡ ሁሉ በመጨረሻይቱም ዓለም (ምንዳ መኖር) በእርግጥ ተስፋ ቆርጠዋል::"}]},{"id":61,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉ ሁሉ አላህን አጠሩ:: እርሱ አሸናፊና ጥበበኛው ነው::"},{"id":2,"translation":"2. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሰሩትን ነገር ለምን ታወራላችሁ?"},{"id":3,"translation":"3. የማትሰሩትን ነገር መናገራችሁ በአላህ ዘንድ በመጠላት እጅግ ከበደ::"},{"id":4,"translation":"4. አላህ እነዚያን ልክ እንደተለሰነ ግንብ የተሰለፉ ሆነው በሃይማኖቱ የሚፋለሙትን ይወዳል::"},{"id":5,"translation":"5. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳም ለህዝቦቹ፡- «ህዝቦቼ ሆይ! እኔ ወደ እናንተ የአላህ መልዕክተኛ መሆኔን እያወቃችሁ ለምን ታሰቃዩኛላችሁ?» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ከእውነት በተዘነበሉ ጊዜ አላህም ልቦቻቸውን አዘነበለባቸው:: አላህ አመጸኞችን ህዝቦች አያቀናምና::"},{"id":6,"translation":"6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የኢስራኢል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊት ያለውን የማረጋግጥና ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልዕክተኛ ስሙ አህመድ በሆነውም የማበስር ስሆን ወደ እናንተ የተላኩ የአላህ መልዕክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ግልጽ ታዐምራቶችን ባመጣላቸው ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ::"},{"id":7,"translation":"7. እርሱ ወደ ኢስላም የሚጠራ ሲሆን በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ይበልጥ በደለኛ ማን ነው? አላህ በዳዮችን ህዝቦች አይመራም::"},{"id":8,"translation":"8. የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ:: ከሓዲያን ቢጠሉም እንኳ አላህ ብርሀኑን ገላጭ ነው::"},{"id":9,"translation":"9. አላህ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልዕክተኛውን በመምሪያ መጽሐፍና በእውነተኛ ሃይማኖት (በኢስላም) ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ሊያደርገው የላከ ነው፡፡"},{"id":10,"translation":"10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአሳማሚ ቅጣት የሚያድናችሁን ትርፋማ ንግድ ላመላክታችሁን?» በላቸው።"},{"id":11,"translation":"11. እርሱም በአላህና በመልዕክተኛው ታምናላችሁ:: በአላህ መንገድ በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ ትታገላለችሁ:: ይህ ተግባር የምታውቁ ከሆናችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው::"},{"id":12,"translation":"12. ኃጢአቶቻችሁን ይምራል:: ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸዉም ገነቶች ያስገባችኋል:: በመኖሪያ ገነቶችም በሚያምሩ ቤቶች ውስጥ ያስቀምጣችኋል:: ይህ ታላቅ እድል ነው::"},{"id":13,"translation":"13. ሌላይቱንም የምትወዷትን ጸጋ ይሰጣችኋል:: እርሷም ከአላህ የሆነ እርዳታና ቅርብ የሆነ አገር መክፈት ነው:: አማኞችንም አብስር::"},{"id":14,"translation":"14. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የመርየም ልጅ ዒሳ ለሐዋሪያቱ፡- «ወደ አላህ ረዳቴ ማን ነው» እንዳለና ሐዋርያቶቹም፡- «እኛ የአላህ ረዳት ነን» እንዳሉት ሁሉ እናንተም የአላህ ረዳቶች ሁኑ፤ ከኢስራኢል ልጆችም አንደኛዋ ቡድን አመነች:: ሌላይቱም ቡድን ካደች:: እነዚያን ያመኑትንም በጠላታቸው ላይ አበረታናቸው:: ከዚያ እነርሱም አሸናፊዎች ሆኑ::"}]},{"id":62,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በሰማይና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ ንጉስ፤ ፍፁም (ከጉድለት ንጹህ)፤ አሸናፊና ጥበበኛ የሆነውን አላህን ያሞግሳል::"},{"id":2,"translation":"2. እርሱ ያ ለመሃይማን ዐረቦች የቁርአን አናቅጽን በእነርሱ ላይ የሚያነብላቸው፤ የሚያጠራቸዉም፤ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸዉም የሆነን መልዕክተኛ ሙሐመድን ከእነርሱ መካከል የላከ ነው:: እነርሱም ከእርሱ በፊት በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ::"},{"id":3,"translation":"3.ከነሱም ሌሎችም ገና ያልተከተሏቸው በሆኑት ላይ የላከው ነው:: እርሱም አሸናፊና ጥበበኛ ነው::"},{"id":4,"translation":"4. ይህ የአላህ ችሮታ ነው:: ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል:: አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው::"},{"id":5,"translation":"5. የእነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያ ያልተሸከሟት (ያልሰሩባት) ሰዎች ምሳሌ ልክ መጽሐፎችን እንደሚሸከም አህያ ብጤ ነው:: የእነዚያ በአላህ አናቅጽ ያስተባበሉት ህዝቦች ምሳሌ ከፋ:: አላህም በዳዮችን ህዝቦች አይመራም::"},{"id":6,"translation":"6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ አይሁዳውያን ሆይ! ከሰው ሁሉ በተለየ እናንተ ብቻ ለአላህ ወዳጆች ነን ብትሉና በዚያ አባባላችሁ እውነተኞች እንደሆናችሁ እስቲ ሞትን ተመኙ» በላቸው::"},{"id":7,"translation":"7. እጆቻቸው ባስቀደሙት ኃጢአት ምክንያት በፍጹም አይመኙትም:: አላህ በዳዮችን አዋቂ ነው::"},{"id":8,"translation":"8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት እርሱ በእርግጥ አግኛችሁ ነው:: ከዚያም ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ ወደ ሆነው ጌታ በቂያማ ዕለት ተመላሾች ናችሁ:: ትሰሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል» በላቸው::"},{"id":9,"translation":"9. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአርብ (በጁሙዓ) ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት (ኹጥባ፣ ሶላት) ተጣደፉ:: መሸጥንም ተው:: የምታውቁ ብትሆኑ ይህ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው::"},{"id":10,"translation":"10. ሶላቷ በተፈጸመችም ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑና የአላህን ችሮታ ፈልጉ:: ልትድኑ ይከጀላልና አላህንም በብዙው አውሱ::"},{"id":11,"translation":"11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ንግድን ወይም ዛዛታን ባዩ ጊዜም ቆመህ የተውህ ሲሆኑ ወደ እርሷ ይበተናሉ:: «አላህ ዘንድ ያለው ከዛዛታም ከንግድም በላጭ ነው:: አላህም ከሰጭዎች ሁሉ ይበልጥ ሲሳይን ሰጪ ነው» በላቸው::"}]},{"id":63,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አስመሳዮች በመጡህ (ወደ አንተ በመጡ) ጊዜ «አንተ የአላህ መልዕክተኛ መሆንህን በእርግጥ (ምለን) እንመሰክራለን» ይላሉ:: አላህም አንተ በእርግጥ መልዕክተኛው መሆንህን ያውቃል:: አላህም አስመሳዮችን ውሸታሞች መሆናቸውን ይመሰክራል::"},{"id":2,"translation":"2. መሓላዎቻቸውን ጋሻ አድርገው ያዙ:: ከአላህም መንገድ ከለከሉ:: እነርሱ ይሰሩት የነበሩት ነገር ሁሉ ከፋ::"},{"id":3,"translation":"3. ይህ እነርሱ (በምላስ) አምነው ከዚያም (በልብ) የካዱ በመሆናቸው በልቦቻቸዉም ላይ ታተመባቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያውቁም::"},{"id":4,"translation":"4. ባየሃቸው ጊዜ አካሎቻቸው ያስደንቁሃል:: ቢናገሩም ንግግራቸውን ታዳምጣለህ:: እነርሱ ልክ ወደ ግድግዳ የተጠጉ ግንዶችን ይመስላሉ:: ጩኸትን ሁሉ በእነርሱ ላይ ነው ብለው ያስባሉ:: እነርሱ ጠላቶች ናቸውና ተጠንቀቃቸው:: አላህ ይጋደላቸው:: (ከእምነት) እንዴት ይመለሳሉ (ያፈገፍጋሉ)::"},{"id":5,"translation":"5. ለእነርሱም፡- «ኑ የአላህ መልዕክተኛ ለእናንተ ምህረትን ይለምንላችኋል» በተባሉ ጊዜ በማፌዝ ራሶቻቸውን ያዞራሉ:: እነርሱም ትዕቢተኞች ሆነው ሲሸሹ ታያቸዋለህ::"},{"id":6,"translation":"6. ምህረትን ብትለምንላቸውም ባትለምንላቸዉም በእነርሱ ላይ ሁሉም እኩል ነው:: አላህ ለእነርሱ በፍጹም አይምርም:: አላህ አመጸኛ ህዝቦችን አይመራምና::"},{"id":7,"translation":"7. እነርሱ፡- «እነዚያ ከአላህ መልዕክተኛ ዘንድ ያሉት ሰዎች እስከ ሚበታተኑ ድረስ ምጽዋት አትስጡ» የሚሉ ናቸው:: የሰማያትና የምድር ድልቦች የአላህ ብቻ ናቸው:: ግን አስመሳዮች አይገነዘቡም::"},{"id":8,"translation":"8. «ወደ መዲና ብንመለስ አሸናፊው ወራዳውን በእርግጥ ከእርሷ ያስወጣል» ይላሉ:: አሸናፊነትም ለአላህ ለመልዕክተኛው እና ለምዕምና ብቻ ነው:: ግን አስመሳዮች አያውቁም::"},{"id":9,"translation":"9. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ አላህን ከማስታወስ አያታልሏችሁ (አያዘናጓችሁ):: ይህንንም የሚሰሩ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎች ናቸው::"},{"id":10,"translation":"10. አንዳችሁም ሞት ሳይመጣበትና «ጌታየ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጎችም ሰዎች እንድሆን ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ» ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ።"},{"id":11,"translation":"11. ማንኛይቱም ነፍስ የሞት ጊዜዋ በመጣባት ጊዜ አላህ በፍጹም አያቆያትም:: አላህም በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::"}]},{"id":64,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በሰማያት ውስጥም ሆነ በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ አላህን ያሞግሳል:: ንግስናው የእርሱ ብቻ ነው:: ምስጋናም ለእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው::"},{"id":2,"translation":"2. እርሱ ያ የፈጠራችሁ ነው:: ከእናንተም መካከል ከሓዲ አለ:: ከእናተም መካከል አማኝ አለ:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነው::"},{"id":3,"translation":"3. (እርሱ) ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ:: ቀረጻችሁም ቅርጻችሁንም አሳመረ፡፡ መመለሻችሁም ወደ እርሱ ብቻ ነው::"},{"id":4,"translation":"4. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል:: የምትደብቋትንም ሆነ የምትገልጡትን ያውቃል:: አላህም በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡"},{"id":5,"translation":"5. የእነዚያ ከአሁን በፊት የካዱትና የክህደታቸውን ቅጣት የቀመሱ ህዝቦች ወሬ አልመጣላችሁምን? ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::"},{"id":6,"translation":"6. ይህ (ቅጣት) እነርሱ መልዕክተኞቻቸው አስረጂዎችን ይዘው ሲመጡላቸው «ሰዎች ይመሩናልን?» ስላሉና ስለ ካዱ፤ ከእምነትም ስለ ዞሩ ነው:: አላህ ከእነርሱ እምነት ተብቃቃ:: አላህ ተብቃቂና ምስጉን ነውና::"},{"id":7,"translation":"7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች በፍጹም የማይቀሰቀሱ መሆናቸውን አሰቡ። «(እንዴት አትቀሰቀሱም?) በጌታየ ይሁንብኝ ትቀሰቀሳላችሁ:: ከዚያ ትፈጽሙት የነበረውን ተግባራችሁን ትናገራላችሁ:: ይህ ተግባር ለአላህ ቀላል ነው» በላቸው።"},{"id":8,"translation":"8. በአላህ በመልዕክተኛውና በዚያም ባወረድነው ብርሃን እመኑም:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና።"},{"id":9,"translation":"9. (ይኸዉም) ለመሰብሰቢያው ቀን የሚሰበስባችሁ እለት አስታውሱ:: ይህ ቀን የቁጭት ቀን ነው:: በአላህም የሚያምን ሰው መልካምንም የሚሠራ ከርሱ ኃጢአቶቹን ይሰርይለታል፤ (ይፍቅለታል)፤ ከስሮቿ ወንዞች የሚፈሱባት ገነቶች ለዘላለም ያስገባዋል:: ይህ ታላቅ እደለኝነት ነው::"},{"id":10,"translation":"10. እነዚያም የካዱትና በአንቀፆቻችንም ያስተባበሉት የዝንታለም እሳት ባለቤቶች ማለት እነርሱ ናቸው:: (ጀሀነም) መመለሻነቷ ምን ይከፋ!"},{"id":11,"translation":"11. ከመከራም በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ ማንንም አይነካም:: በአላህ የሚያምን ሰው አላህ ልቡን ለትግስት ይመራዋል:: አላህም በሁሉም ነገር አዋቂ ነው::"},{"id":12,"translation":"12. አላህን ታዘዙ መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: ብትዞሩም (መልዕክተኛውን አትጎዱም::) በመልዕክተኛችንም ላይ ያለበት በግልጽ ማድረስ ብቻ ነው::"},{"id":13,"translation":"13. አላህ ከእርሱ በስተቀር ትክክለኛ አምላክ የለም:: ትክክለኛ አማኞች በአላህ ብቻ ይመኩ::"},{"id":14,"translation":"14. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሚስቶቻችሁና ከልጆቻችሁ (ከአላህ መንገድ በማስተጓጎል) ለእናንተ ጠላቶች የሆኑ አሉ:: ስለዚህ ተጠንቀቋቸው:: ይቅርታ ብታደርጉ፤ ብታልፏቸዉም፤ ብትምሩዋቸዉም፤ አላህ በጣም መሀሪ፤ አዛኝ ነው::"},{"id":15,"translation":"15. ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ለእናንተ መፈተኛ ብቻ ናቸው:: አላህም ከእርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አለ::"},{"id":16,"translation":"16. አላህንም የቻላችሁትን ያህል ፍሩት:: ትዕዛዙን ስሙም፤ ታዘዙም፤ ለግሱም፤ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ይሰጣችኋልና:: የነፍሶቻቸዉን ንፍገት የሚጠበቁ ሰዎች ሁሉ እነዚያ እነርሱ ፍላጎታቸውን የሚያገኙ ናቸው::"},{"id":17,"translation":"17. ለአላህ መልካም ብድርን ብታበድሩት (ምንዳውን) ለእናንተ ይደራርበዋል:: ለእናንተም ይምራል:: አላህ አመስጋኝና ታጋሽ ነውና::"},{"id":18,"translation":"18. (እርሱ) ስውሩንም ይፋዉንም ሁሉን አዋቂ ኃያልና ጥበበኛ ነዉና።"}]},{"id":65,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አንተ ነብይ ሆይ! ሴቶችን መፍታት ባሰባችሁ ጊዜ፤ ለዒዳቸው ፍቷቸው፤ ዒዳንም ቁጠሩ፤ ጌታችሁን አላህን ፍሩ፤ ግልጽ የሆነችን ጠያፍ ካልሰሩ በስተቀር ከቤቶቻቸው አታውጧቸው:: አይውጡም፤ ይህችም የአላህ ህግጋት ናት:: የአላህንም ህግጋት የተላለፈ ሰው በእርግጥ ነፍሱን በደለ፤ ከዚህ (ፍች) በኋላ አላህ (የመማለስ) ነገርን ምናልባት ያመጣ እንደኾነ አታውቅም፡፡"},{"id":2,"translation":"2. ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም ያዟቸው፤ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፤ ከናንተም ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፤ ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ፤ ይሃችሁ በአላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰጽበታል፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል::"},{"id":3,"translation":"3. ከማያስበዉም በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል፤ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው:: አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው:: አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል::"},{"id":4,"translation":"4. እነዚያም ከሴቶቻችሁ ከአደፍ (ከወር አበባ) ያቋረጡት በዒዳቸው ህግ ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሶስት ወር ነው:: እነዚያም ገና አደፍን ያላዩ ሴቶችም ዒዳቸው እንደዚሁ ነው:: የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለእርሱ መግራትን ያደርግለታል::"},{"id":5,"translation":"5. ይህ የአላህ ፍርድ ነው:: ወደ እናንተ አወረደው፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ሁሉ ኃጢአቶችን ከርሱ ይሰርዝለታል:: ምንዳንም ለእርሱ ያተልቅለታል::"},{"id":6,"translation":"6. ከችሎታችሁ ከተቀመጣችሁበት ስፍራ አስቀምጧቸው:: በእነርሱም ላይ ልታጣብቡ አትጉዷቸው:: የእርግዝና ባለቤቶችም ቢሆኑ እርጉዛቸውን እስኪወልዱ ድረስ በእነርሱ ላይ ቀልቡ። ለእናንተም ልጆቻችሁን ቢያጠቡላችሁ የልፋት ዋጋቸውን ስጧቸው:: በመካከላችሁም በመልካም ነገር ተመካከሩ፤ ብትቸጋገሩም ለእርሱ ሌላ (ሴት) ታጠባለታለች::"},{"id":7,"translation":"7. የችሎታ ባለቤት በችሎታው ልክ ይቀልብ፤ በእርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበበት ሰው አላህ ከሰጠው ይስጥ ነፍስን የሰጣትን ያህል እንጂ አያስገድድም:: አላህ ከችግር በኋላ ምቾትን በእርግጥ ያደርጋል::"},{"id":8,"translation":"8. ከከተማም መካከል ከጌታቸው እና ከመልዕክተኞች ትዕዛዝ ያመጹ በመሆናቸው፤ ብርቱን ቁጥጥር የተቆጣጠርናቸዉና መጥፎንም ቅጣት የቀጣናቸው ብዙ ናቸው::"},{"id":9,"translation":"9. የነገራቸዉንም ቅጣት ቀመሱ:: የነገራቸዉም መጨረሻ ኪሳራ ሆነ::"},{"id":10,"translation":"10. አላህ ለእነርሱ ብርቱ ቅጣትን አዘጋጀ:: እናንተም በአላህ ያመናችሁ የአእምሮ ባለ ቤቶች ሆይ! አላህን ፍሩ፤ አላህ ወደ እናንተ ግሳጼን በእርግጥ አወረደ፤"},{"id":11,"translation":"11. እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሰሩትን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣ ዘንድ የአላህን አንቀጾች ገላጮች ሲኾኑ በእናንተ ላይ የሚያነብላችሁን መልዕክተኛን ላከ:: በአላህም አናቅጽ የሚያምን መልካምን ስራ የሚሰራም ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያገባዋል አላህ ለርሱ ሲሳይን በእርግጥ አሳመረ::"},{"id":12,"translation":"12. አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው:: ከምድርም መሰላቸውን (ፈጥሮአል)፤ በመካከላቸዉም ትዕዛዙ ይወርዳል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን አላህም በነገሩ ሁሉ በእውቀት ያካበበ መሆኑን ታውቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ)::"}]},{"id":66,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አንተ ነብይ ሆይ! አላህ ላንተ የፈቀደልህን ነገር ሚሰቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትሆን (ባንተ ላይ) ለምን እርም ታደርጋለህ? አላህ እጅግ መሀሪና አዛኝ ነው::"},{"id":2,"translation":"2. አላህ ለእናንተ የመሐሎቻችሁን መፍቻ ደነገገላችሁ፤ አላህ ረዳታችሁ ነው:: እርሱም ሁሉን አዋቂና እጅግ ጥበበኛ ነው።"},{"id":3,"translation":"3. ነብዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ (አስታውስ):: እርሱንም በነገረችና አላህ እርሱን ማውራቷን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አሳወቀ፤ ከፊሉንም ተወ፤ በእርሱም ባወራት ጊዜ «ይህን ማን ነገረህ?» አለች፤ «ሁሉን አዋቂው እና ውስጠ አዋቂው ነገረኝ» አላት::"},{"id":4,"translation":"4. (ሁለታችሁም) ወደ አላህ ብትመለሱ ልቦቻችሁ በእርግጥ ተዘንብለዋልና (ትስማማላችሁ):: በእርሱ (ጥቃት) ላይ ብትረዳዱ ግን ረዳቱ አላህ ነው። ጂብሪልም ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቶቹ ናቸው፡፡"},{"id":5,"translation":"5. ሁላችሁንም ቢፈታችሁ ከናንተ የበለጡ ሚስቶች ሙስሊሞች፤ ትክክለኛ አማኞች፤ ታዛዦች፤ ተጸፃቾች፤ ለአላህ ተገዢዎች፤ ጿሚዎች፤ ፈቴዎችም ደናግልም የሆኑትን ጌታው ሊለውጠው ይከጅላል::"},{"id":6,"translation":"6. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከሆነች እሳት ነፍሶቻችሁንም ቤተሰቦቻችሁንም ጠብቁ፤ በእርሷ ላይ ጨካኝና ኃይለኛ የሆኑ መላዕክት አሉ:: አላህን ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሰራሉ::"},{"id":7,"translation":"7. እናንተ በአላህ የካዳችሁ ሰዎች ሆይ! ዛሬ አታመካኙ፤ የምትመነዱት ያንን ትሰሩት የነበራችሁትን ብቻ ነው (ይባላሉ)::"},{"id":8,"translation":"8. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ነብዩን እነዚያንም ከእርሱ ጋር ያመኑትን በማያሳፍርበት፤ ብርሃናቸው በፊቶቻቸውና በቀኞቻቸው የሚሮጥ ሲሆን፡- «ጌታችን ሆይ! ብርሃናችንን ሙላልን፤ ለእኛ ምህረትንም አድርግልን፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና» በሚሉበት ቀን ጌታችሁ ከናንተ ኃጢአቶቻችሁን ሊሰርዝላችሁ፤ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶችም ሊያስገባችሁ ይከጅላልና ንጹህ የሆነችን ጸጸት በመጸጸት ወደ አላህ ተመለሱ።"},{"id":9,"translation":"9. አንተ ነብይ ሆይ! ከሓዲያን እና አስመሳዮችን ታገል፤ በእነርሱም ላይ በርታ፤ መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት:: ምን ትከፋም መመለሻ!"},{"id":10,"translation":"10. አላህ ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች የኑህን ሚስት እና የሉጥን ሚስት ምሳሌ አደረገ፤ ባሮቻችን ከሆኑ ሁለት መልካም ባሪያዎች ስር ነበሩ ከዷቸዉም፤ ኑሕም ሉጥም ከሚስቶቻቸው ምንም የአላህን ቅጣት አልገፈተሩላቸዉም፤ «ከገቢዎችም ጋር እሳትን ግቡ» ተባሉ::"},{"id":11,"translation":"11. ለእነዚያ ለአመኑትም አላህ የፈርዖንን ሚስት ምሳሌ አደረገ:: «ጌታየ ሆይ! አንተ ዘንድ በገነት ውስጥ ለእኔ ቤት ገንባልኝ፤ ከፈርዖንና ከስራዉም አድነኝ፤ ከበደለኞች ህዝቦችም አድነኝ» ባለች ጊዜ።"},{"id":12,"translation":"12. የዒምራን ልጅ መርየምንም ያችን ብልቷን የጠበቀችውን ምሳሌ አደረገ:: በእርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፋን:: በጌታዋ ቃላትና በመጽሐፍቱም አረጋገጠች፤ ከታዛዦችም ነበረች::"}]},{"id":67,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ያ ንግስና በእጁ የሆነው አምላክ ችሮታው በዛ:: እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው::"},{"id":2,"translation":"2. ያ የየትኛችሁ ስራ ይበልጥ ያማረ መሆኑን ሊሞክራችሁ ሞትንና ህይወትን የፈጠረ ነው:: እርሱም አሸናፊና መሀሪ ነው::"},{"id":3,"translation":"3. ያ ሰባቱን ሰማያት የተነባበሩ ሆነው የፈጠረ ነው:: በአል ረህማን አፈጣጠርም ውስጥ ምንም ቅንጣት ያህል መዛነፍን (መቃረንና መበላሸት) አይታይም:: ዓይንህንም መልስ:: ከስንጥቆች አንዳችን ታያለህን?"},{"id":4,"translation":"4. ከዚያም ዓይንህን መላልስ:: ዓይንህ ተዋርዶ (ተናንሶ)፤ እርሱም የደከመ ሆኖ ወደ አንተ ይመለሳል::"},{"id":5,"translation":"5. ቅርቢቱን ሰማይም በእርግጥ በመብራቶች (በከዋክብት) አጌጥናት:: ለሰይጣናትም መቀጥቀጫዎች አደረግናት፤ ለእነርሱም ተንቀልቃይ የእሳትን ቅጣት አዘጋጀንላቸው::"},{"id":6,"translation":"6. ለእነዚያም በጌታቸው ለካዱት የገሀነም ቅጣት አላቸው:: መመላሻይቱም ገሀነም ከፋች!"},{"id":7,"translation":"7. በውስጧ በተጣሉ ጊዜ እርሷ የምትፈላ ስትሆን ከእርሷ እንደ (አህያ) ማናፋትን ይሰማሉ::"},{"id":8,"translation":"8. ከቁጭቷ የተነሳ ልትቆራረጥ ትቀርባለች:: በውስጧ ቡድኖች በተጣሉ ቁጥር «ዘበኞቿ (ስለዚህ ቀን) አስፈራሪ (ነብይ) አልመጣላችሁም ነበርን?» በማለት ይጠይቋቸዋል::"},{"id":9,"translation":"9. «አይደለም በእርግጥ አስፈራሪ መጥቶልናል:: አስተባበልንም:: አላህም ምንንም አላወረደም:: እናንተ አውርዷል ስትሉ፤ በትልቅ ስህተት ውስጥ እንጂ አይደላችሁም አልን» ይላሉ::"},{"id":10,"translation":"10. «የምንሰማ ወይም የምናስብ በነበርን ኖሮ የእሳት ጓዶች ባልሆን ነበር» ይላሉ::"},{"id":11,"translation":"11. በኃጢአታቸዉም ያምናሉ:: ለእሳት ጓዶችም (ከእዝነት) መራቅ ተገባቸው::"},{"id":12,"translation":"12. እነዚያ ጌታቸውን በሩቁ የሚፈሩ ለእነርሱ ምህረትንና ታላቅ ምንዳ አለላቸው::"},{"id":13,"translation":"13. (ሰዎች ሆይ!) ቃላችሁንም መስጥሩ:: ወይም በእርሱ ጩሁ:: እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ አዋቂ ነው::"},{"id":14,"translation":"14. የፈጠረን አምላክ እርሱ እውቀተ ረቂቁ ውስጠ አዋቂው ሲሆን (ሚስጢርን) ሁሉ አያውቅምን?"},{"id":15,"translation":"15. እርሱ ያ ምድርን ለእናንተ የተገራች ያደረገላችሁ ነው:: በጋራዎቿና በመንገዶቿም ሂዱ:: ከሲሳዮም ብሉ:: (ኋላ) መመለሻችሁም ወደ እርሱ ብቻ ነው::"},{"id":16,"translation":"16. በሰማይ ያለው ጌታ በእናንተ ምድርን እንደማያሰምጥባችሁ ወዲያዉም እርሷም (እናንተኑ ውጣ) የምታረገርግ እንደማትሆን ትተማመናላችሁን? (አትፈሩምን?)።"},{"id":17,"translation":"17. ወይስ በሰማይ ያለው ጌታ በእናንተ ላይ ጠጠርን ያዘለች ንፋስን እንደማልክባችሁ ትተማመናላችሁ? (አትፈሩም?) ማስጠንቀቄም እንዴት እንደሆነ ወደ ፊት ታውቃላችሁ"},{"id":18,"translation":"18. እነዚያ ከእነርሱ በስተፊት የነበሩትም አስተባበሉ:: ጥላቻየም እንዴት ነበር (አስተዉል)፤"},{"id":19,"translation":"19. ከበላያቸው ሰልፍ ሰርተው ወዳሉ ወፎች አይመለከቱምን? ክንፎቻቸውን ያጥፋሉ:: ከአር-ረህማን ሌላ የሚይዛቸው የለም:: እርሱ ሁሉን ነገር አዋቂ ነው::"},{"id":20,"translation":"20. በእውነት ያ እርሱ ከአር-ረህማን ሌላ የሚረዳችሁ ለእናንተ የሆነ ሰራዊት ማነው? ከሓዲያን በመታለል ውስጥ እንጂ በሌላ ላይ አይደሉም::"},{"id":21,"translation":"21. ወይም ሲሳዮን ቢይዝባችሁ ያ ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው? በእውነት እነርሱ በሞገድና በመደንበር ውስጥ ጸኑ::"},{"id":22,"translation":"22. በፊቱ ላይ ተደፍቶ የሚሄድ ሰው ይበልጥ የተቀና ነውን? ወይስ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ተስተካክሎ የሚሄድ?"},{"id":23,"translation":"23. እርሱ! ያ አላህ የፈጠራችሁ፤ ለእናተም መስሚያና ማያዎች፤ ልቦችንም ያደረገላችሁ ነው:: ጥቂትንም አታመሰግኑምን በላቸው::"},{"id":24,"translation":"24. እርሱ ያ በምድር ላይ የበተናችሁ ነው:: ወደ እርሱም ትሰበሰባላችሁ በላቸው::"},{"id":25,"translation":"25. «እውነተኞችም እንደሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው ተፈፃሚ የሚሆነው?» ይላሉ::"},{"id":26,"translation":"26. እውቀቱ ከአላህ ዘንድ ብቻ ነው:: እኔ ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም በላቸው::"},{"id":27,"translation":"27. (ቅጣቱ) ቅርብ ሆኖ ባዩትም ጊዜ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ፊቶች ይከፋሉ:: ይህ ያ በእርሱ ትከራከሩበት የነበራችሁት ነው ይባላሉም::"},{"id":28,"translation":"28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አያችሁን? እስኪ ንገሩኝ? አላህ ቢገድለኝ ከእኔ ጋር ያሉትንም (እንደዚሁ) ወይም በማቆየት ቢያዝንልን ከሓዲያንን ከአሳማሚ ቅጣት የሚያድን ማን ነው? በላቸው::"},{"id":29,"translation":"29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱ ያ (እመኑበት የምላችሁ) አር-ረህማን ነው:: እኛ በእርሱ አመንን:: በእርሱም ላይ ተጠጋን:: ወደ ፊትም በግልጽ መሳሳት ውስጥ የሆነው እርሱ ማን እንደሆነ በእርግጥ ታውቃላችሁ በላቸው::"},{"id":30,"translation":"30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አያችሁ (እስኪንገሩኝ?) ውሃችሁ ሰራጊ ቢሆን (ወደ መሬት ቢሰርግ) ፈሳሽን (ምንጭን) ውሃ የሚያመጣላችሁ ማን ነው? በላቸው::"}]},{"id":68,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ኑን፤ በብዕር እና በዚያም በሱ በሚጽፉት ሁሉ እምላለሁ::"},{"id":2,"translation":"2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ በጌታህ ጸጋ ምክኒያት ዕብድ አይደለህም::"},{"id":3,"translation":"3. ላንተም ከጌታህ የማይቋረጥ ምንዳ (የልፋት ዋጋ) በእርግጥ አለህ::"},{"id":4,"translation":"4. አንተም በታላቅ ጸባይ ላይ ነህ::"},{"id":5,"translation":"5. ወደ ፊት አንተም ታያለህ፤ እነርሱም ያያሉ፤"},{"id":6,"translation":"6. ዕብደት በማንኛችሁ እንዳለ (እብዱ ማን እንደሆነ)::"},{"id":7,"translation":"7. ጌታህ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው አዋቂ ነው። ወደ ቀናው መንገድ ተመሪዎችንም አዋቂ ነው::"},{"id":8,"translation":"8. ስለዚህ ለአስተባባዩች (ሁሉ) አትታዘዝ::"},{"id":9,"translation":"9. (አስተባባዩች) ብትመሳሰላቸውና እነርሱም ቢመሳሰሉህ ተመኙ::"},{"id":10,"translation":"10. መሓለኛን ወራዳን ሁሉ አትታዘዝ።"},{"id":11,"translation":"11. ሰውን አነዋሪን፤ ነገር አሳባቂን፤"},{"id":12,"translation":"12.ለበጎ ነገር በጣም ከልካይን፤ ወሰን አላፊን፤ ኃጢአተኛንም፤"},{"id":13,"translation":"13. ልበ ደረቅን ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ የዝሙት ልጅ ዲቃላን (አትታዘዝ)::"},{"id":14,"translation":"14. የገንዘብና የልጆች ባለቤት በመሆኑ (ያስተባብላል)።"},{"id":15,"translation":"15. በእርሱ ላይ እንቀፆቻችን በሚነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል::"},{"id":16,"translation":"16. በአፍንጫው ላይ በእርግጥ (የሚነወርበት) ምልክትን እናደርግበታለን::"},{"id":17,"translation":"17. እኛ እነዚያን የአትክልቲቱን ባለቤቶች ማልደው ፍሬዋን ሊለቅሟት (አላህ ቢሻ ሳይሉ) በማሉ ጊዜ እንደሞከርን ሁሉ የመካ ሰዎችንም ሞከርናቸው::"},{"id":18,"translation":"18. (በመሓላቸው) አያስቀሩምም፡፡"},{"id":19,"translation":"19.እነርሱ የተኙ ሆነዉም ሳሉ ከጌታህ የሆነ ዟሪ በእርሷ ላይ ዞረባት::"},{"id":20,"translation":"20. እንደ ሌሊት ጨለማ የከሰለች ሆና አነጋች (አደረች)።"},{"id":21,"translation":"21.ያነጉም ሆነው ተጠራሩ"},{"id":22,"translation":"22. \"ቆራጮች እንደ ሆናችሁ ወደ እርሻችሁ ለመሄድ ማልዱ በማለት\" (ተጠራሩ)::"},{"id":23,"translation":"23. እነርሱ የሚያሾካሾኩ ሆነው ሄዱም::"},{"id":24,"translation":"24. ዛሬ በእናንተ ላይ አንድም ድሃ እንዳይገባት በማለትና"},{"id":25,"translation":"25. ድሆችን በመከልከልም ላይ በሀሳባቸው ቻዮች ሆነው ማለዱ::"},{"id":26,"translation":"26. ከዚያ ተቃጥላ ባዩዋት ጊዜ (እንዲህ) አሉ: «እኛ በእርግጥ ተሳሳቾች ነን፤"},{"id":27,"translation":"27. «ይልቁንም እኛ ከአላህ የተከለከልን እደለ ቢሶች ነን» አሉ።"},{"id":28,"translation":"28. (ከመካከላቸው) ትክክለኛቸው (አስተዋያቸው)፡- «እናንተ አላህን ለምን አታጠሩም (አታወሱም) አላልኳችሁም ነበርን?» አለ።"},{"id":29,"translation":"29. «(ሁላቸዉም) ጌታችን ጥራት ይገባው፤ እኛ በዳዩች ነበርን» አሉ።"},{"id":30,"translation":"30. እርስ በራሳቸው የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊሎቻቸው በከፊሉ ላይ መጡ::"},{"id":31,"translation":"31. «ዋ፤ጥፋታችን፤ እኛ ድንበር አላፊዎች ነበርን» አሉ::"},{"id":32,"translation":"32. «ጌታችን ከእርሷ የተሻለን (አትክልት) ሊለውጠን ይከጀላል:: እኛ ወደ ጌታችን ከጃዩች ነን» አሉ::"},{"id":33,"translation":"33. (የአላህ) ቅጣቱ ልክ እንደዚሁ ነው:: የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት ከዚህ የበለጠ ከባድ ነው:: የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ (ከዚህ ቅጣት በተጠነቀቁ ነበር)::"},{"id":34,"translation":"34. ለጥንቁቆች በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው::"},{"id":35,"translation":"35. ሙስሊሞችን እንደ ከሓዲያን እናደርጋለን? (አናደርግም)::"},{"id":36,"translation":"36. ለእናንተ ምን (አስረጂ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ( ምን ነካችሁ)::"},{"id":37,"translation":"37. በእውነቱ ለእናንተ በእርሱ የምታጠኑበት መጽሐፍ አላችሁን?"},{"id":38,"translation":"38. በውስጡ ለእናንተ የምትመርጡት አላችሁን? (የሚል)::"},{"id":39,"translation":"39. ወይስ «ለእናንተ የምትፈርዱት አላችሁ» በማለት (ቃል ኪዳን የገባንላችሁ) እስከ ትንሳኤ ቀን ደራሽ የሆኑ መሐላዎች ለእናንተ በእኛ ላይ አሏችሁን?"},{"id":40,"translation":"40. በዚህ ማንኛቸው ተያያዥ እንደ ኾነ ጠይቃቸው፡፡"},{"id":41,"translation":"41. ወይስ ለእነርሱ (በፍርዳቸው ተስማሚ) ተጋሪዎች አሏቸውን? እውነተኞችም እንደሆኑ ተጋሪዎቻቸውን ያምጡ::"},{"id":42,"translation":"42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያን ባት የሚገለጥበትን፤ (ከሓዲያን) ወደ መስገድ የሚጠሩበትና የማይችሉበትን ቀን (አስታውስ)::"},{"id":43,"translation":"43. ዓይኖቻቸው የፈሩ፤ ውርደት የምትሸፍናቸው ሲሆኑ (ወደ ስግደት የሚጠሩበትን):: እነርሱ (በምድረ ዓለም) ደህና ሆነው ሳሉ ወደ ስግድት በእርግጥ ይጠሩ ነበሩ::"},{"id":44,"translation":"44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመሆኑም እኔን በዚህ ንግግር ከሚያስተባብሉት ሰዎች ጋር ተወኝ፤ (ለእነርሱ እኔ እበቃሃለሁ):: ከማያውቁት ስፍራ አዘናግተን እንይዛቸዋለን::"},{"id":45,"translation":"45. እነርሱንም አዘገያቸዋለሁ:: (ዘዴዬ) ብቀላየ ብርቱ ነውና::"},{"id":46,"translation":"46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወይንስ በእውነቱ (በማስተማርህ) ዋጋን እንዲከፍሉህ ትጠይቃቸዋለህን? ስለዚህ እነርሱ ከዕዳ የተከበዱ ናቸውን?"},{"id":47,"translation":"47. ወይስ ከእነርሱ ዘንድ የሩቁ ምስጢር እውቀት አለን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን?"},{"id":48,"translation":"48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ)፤ ለጌታህ (ዉሳኔ) ፍርድ ታገስ:: (በመበሳጨትና ባለ መታገስ) እንደ ዓሳው ባለቤት እንደ (ነብዩ ዩኑስ) አትሁን:: እርሱ በጭንቀት የተሞላ ሆኖ (ጌታውን) በተጣራ ጊዜ"},{"id":49,"translation":"49. ከጌታው የሆነ ጸጋ ባላገኘው ኖሮ በምድረ በዳ ተወቃሽ ሆኖ በተጣለ ነበር::"},{"id":50,"translation":"50. ጌታዉም (በነብይነት) መረጠው:: ከደጋጎችም አደረገው::"},{"id":51,"translation":"51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነሆ እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች ቁርኣኑን በሰሙ ጊዜ በዓይኖቻቸው (ሊያጠፉህ) ይቃረባሉ፤ «እርሱም በእርግጥ እብድ ነዉም» ይላሉ::"},{"id":52,"translation":"52.እርሱ ግን ለዓለማት መገሰጫ (ገሳጭ) እንጂ ሌላ አይደለም::"}]},{"id":69,"verses":[{"id":1,"translation":"1. እውነትን አረጋጋጪቱ (ትንሳኤ)::"},{"id":2,"translation":"2. አረጋጋጪቱ (እርሷ) ምንድን ናት!"},{"id":3,"translation":"3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አረጋግጪቱም ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?"},{"id":4,"translation":"4. የሰሙድና የዓድ ህዝቦች በቆርቋሪይቱ (ትንሳኤ) ቀን አስተባበሉ::"},{"id":5,"translation":"5. የሰሙድ ህዝቦችማ ወሰን በሌላት ነፋስ ጩኸት ተጠፉ::"},{"id":6,"translation":"6. የዓድ ህዝቦችማ በኃይል በምትንሻሻ ብርቱ ነፋስ ተጠፉ::"},{"id":7,"translation":"7. ተከታታይ በሆነ ሰባት ሌሊቶችና ስምንት ቀናቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት:: ህዝቦችንም፤ በውስጧ የተጣሉ ሆነው ልክ ክፍት እደሆኑ የበሰበሱ የዘንባባ ግንዶች ታያቸዋለህ::"},{"id":8,"translation":"8. ከእነርሱ መካከል ቀሪን ታያለህን?"},{"id":9,"translation":"9. ፈርዖን፤ ከበፊቱ የነበሩትን ሰዎችም፤ ተገልባጮችም (የሉጥ ሰዎች ከተሞች) ኃጢአት ፈጸሙ።"},{"id":10,"translation":"10. የጌታቸውንም መልዕክተኛ ትዕዛዝ ጣሱ፤ የበረታችንም ቅጣት ቀጣቸው::"},{"id":11,"translation":"11. እኛ ውሃው ባየለ ጊዜ በተንሳፋፊይቱ ታንኳ ውስጥ ጫንናችሁ::"},{"id":12,"translation":"12. ይህንም ያደረግነው ለእናንተ መገሰጫ ልናደርጋትና አጥኚ የሆነችም ጆሮ ታጠናት ዘንድ ነው::"},{"id":13,"translation":"13. በቀንዱ አንዲት መነፋት በተነፋች ጊዜ::"},{"id":14,"translation":"14. ምድርና ጋራዎች (ከየስፍራቸው) በተነሱና አንዲትን መሰባበር በተሰባበሩ ጊዜ፤"},{"id":15,"translation":"15. በዚያ ቀን (ትንሳኤ) ትከሰታለች::"},{"id":16,"translation":"16. ሰማይም ትቀደዳለች:: በመሆኑም እርሷ በዚያ ቀን ደካማ ናት፤"},{"id":17,"translation":"17. መላዕክትም በየጫፎቿ ላይ ይሆናሉ:: የጌታህንም ዓርሽ በዚያ ቀን ስምንት መላዕክት ከበላያቸው ይሸከማሉ::"},{"id":18,"translation":"18. በዚያ ቀን ከናንተ ተደባቂ (ነገሮች) የማይደበቁ ሲሆኑ ትቀረባላችሁ::"},{"id":19,"translation":"19. ያ መጽሀፉን በቀኝ እጁ የተሰጠ ሰውማ (ለጓደኞቹ እንዲህ) ይላል: «እንኩ መጽሐፌን አንብቡ፤"},{"id":20,"translation":"20. «እኔ ምርመራየን የምገናኝ መሆኔን አረጋገጥኩ።» (ይላል)"},{"id":21,"translation":"21. እርሱም በተወደደች ኑሮ ውስጥ ይሆናል::"},{"id":22,"translation":"22. በከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ፤"},{"id":23,"translation":"23. ፍሬዎቿ ቅርቦች የሆኑ::"},{"id":24,"translation":"24. በአለፉት ቀናት ውስጥ (በምድረ ዓለም) ባስቀደማችሁት ምክንያት ብሉ፤ ጠጡም ይባላሉ::"},{"id":25,"translation":"25. ያ መጽሐፉን በግራው የተሰጠ ሰው ደግሞ (እንዲህ) ይላል: «ዋ ጥፋቴ ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ፤"},{"id":26,"translation":"26. «ምርመራዬም ምን እንደሆነ ባላወቅሁ፤"},{"id":27,"translation":"27. «ሞት ምነው የህይወቴ የመጨረሻ ፍፃሜ በሆነች፤"},{"id":28,"translation":"28. «ገንዘቤ ከእኔ ምንንም አልጠቀመኝም፤"},{"id":29,"translation":"29. «ስልጣኔ ከእኔ ላይ ጠፋ» ይላል::"},{"id":30,"translation":"30. ያዙት ከዚያ እጁን ከአንገቱ ጋር እሰሩት፤"},{"id":31,"translation":"31. ከዚያ በእሳት ውስጥ አስገቡት፤"},{"id":32,"translation":"32. ከዚም እርዝመቷ ሰባ ክንድ በሆነች ሰንሰለት ውስጥ አስገቡት።"},{"id":33,"translation":"33. እርሱ ታላቅ በሆነው አላህ አያምንም ነበርና፤"},{"id":34,"translation":"34. ድሆችንም በማብላት ላይ አያነሳሳም ነበርና::"},{"id":35,"translation":"35. ለእርሱ ዛሬ እዚህ ቦታ ዘመድ ማንም የለዉም::"},{"id":36,"translation":"36. ምግብም ከእሳት ሰዎች ቁስል እጣቢ እዥ በስተቀር የለዉም::"},{"id":37,"translation":"37. ይህን ምግብ ኃጢአተኞች እንጂ ሌላ አይበላዉም ይባላል::"},{"id":38,"translation":"38. በምታዩት ነገር ሁሉ እምላለሁ ::"},{"id":39,"translation":"39. በማታዩትም ነገር ሁሉ እምላለሁ ::"},{"id":40,"translation":"40. ቁርኣን የተከበረው መልዕክተኛ ቃል ነው።"},{"id":41,"translation":"41. እርሱም የባለ ቅኔ ገጣሚ ቃል አይደለም:: ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ::"},{"id":42,"translation":"42. የጠንቋይም ቃል አይደለም:: ጥቂትን ብቻ ታስታውሳላችሁ::"},{"id":43,"translation":"43. ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው::"},{"id":44,"translation":"44. በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት እንኳን (ያላልነው) በቀጠፈ ኖሮ፤"},{"id":45,"translation":"45. በኃይል በቀጣነው ነበር::"},{"id":46,"translation":"46. ከዚያ ከእርሱ የልቡን ስር የተንጠላጠለበትን (ጅማት) በቆረጥን ነበር::"},{"id":47,"translation":"47. ከናንተም ውስጥ ከእርሱ ላይ ከልካዮች ምንም አይኖሩም።"},{"id":48,"translation":"48. እርሱ (ቁርኣን) ለጥንቅቆቹ ብቻ መገሰጫ ነው::"},{"id":49,"translation":"49. እኛም ከናንተ ውስጥ አስተባባዩች መኖራቸውን በእርግጥ እናውቃለን::"},{"id":50,"translation":"50. እርሱ (ቁርኣንም) በከሓዲያን ላይ ጸጸት ነው::"},{"id":51,"translation":"51. እርሱም የተረጋገጠ እውነት ነው::"},{"id":52,"translation":"52. እናም የታላቁን ጌታህን ስም (ታላቁን ጌታህን) አጥራው::"}]},{"id":70,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ወዳቂ (ተከሳች) ከሆነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ::"},{"id":2,"translation":"2. ከሓዲያን ላይ (ወዳቂ ከሆነው) ለእርሱ መላሽ የለዉም።"},{"id":3,"translation":"3. የ (ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከሆነው አላህ (መላሽ የለዉም)::"},{"id":4,"translation":"4. መላዕክትና መንፈሱም ልኩ ሀምሳ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ (ይወጣሉ)::"},{"id":5,"translation":"5. መልካምን ትዕግስት ታገስ::"},{"id":6,"translation":"6. እነርሱ ያንን ቀን ሩቅ አድርገው ያዩታል::"},{"id":7,"translation":"7. እኛም ቅርብ ሆኖ እናየዋለን::"},{"id":8,"translation":"8. ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትሆንበት ቀን፤"},{"id":9,"translation":"9. ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ንፋስ) እንደበተነውና እንደሚያበረው በሚሆኑበት ቀን፤"},{"id":10,"translation":"10. ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን መላሽ የለዉም::"},{"id":11,"translation":"11. (ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፤ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ቤዛ ሊያደርግ ይመኛል::"},{"id":12,"translation":"12. በሚስቱም በወንድሙም፤"},{"id":13,"translation":"13. በዚያች በምታስጠጋው ጎሳውም፤"},{"id":14,"translation":"14. በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያ ሊያድነው (ይመኛል)::"},{"id":15,"translation":"15. ይተው፤እርሷ (እሳቲቱ) ነዲድ እሳት ናት።"},{"id":16,"translation":"16. የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትሆን፤"},{"id":17,"translation":"17. (ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደ እርሷ) ትጠራለች::"},{"id":18,"translation":"18. ገንዘብን የሰበሰበንና ዘካውን ሳይሰጥ የቆጠረንም (ትጠራለች)::"},{"id":19,"translation":"19. ሰው ቅጠ ቢስ ሆኖ ተፈጠረ::"},{"id":20,"translation":"20. ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጭተኛ፤"},{"id":21,"translation":"21. መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘው ጊዜ ከልካይ ሆኖ ተፈጠረ::"},{"id":22,"translation":"22. ሰጋጆች ብቻ ሲቀሩ::"},{"id":23,"translation":"23. እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘወታሪዎች የሆኑት::"},{"id":24,"translation":"24. እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የሆኑት፤"},{"id":25,"translation":"25. ለለማኝ እና ከልመና ለሚቆጠብም መብት (ያለባቸው የሆኑ)፤"},{"id":26,"translation":"26. እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት የሚያረጋግጡ::"},{"id":27,"translation":"27. እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የሆኑት::"},{"id":28,"translation":"28. የጌታቸው ቅጣት የማያስተማምን ነውና።"},{"id":29,"translation":"29. እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት፤"},{"id":30,"translation":"30. በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው ባሮች ላይ ሲቀር:: እነርሱ በነዚህ የማይወቀሱ ናቸውና::"},{"id":31,"translation":"31. ከዚያ ወዲያ የፈለገ እነዚያ እነርሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው።"},{"id":32,"translation":"32. እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የሆኑት::"},{"id":33,"translation":"33. እነዚያም እነርሱ በምስክሮቻቸው ላይ ቀጥ ያሉት::"},{"id":34,"translation":"34. እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት::"},{"id":35,"translation":"35. እነዚያ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው::"},{"id":36,"translation":"36. እነዚያ (በአላህ) የካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው?"},{"id":37,"translation":"37. ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ቡድኖች ሲሆኑ፤"},{"id":38,"translation":"38. ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን?"},{"id":39,"translation":"39. ይከልከል፤ በፍጹም እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍተወት ጠብታ) ፈጠርናቸው::"},{"id":40,"translation":"40. (እናም ጉዳዩ ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: በምስራቆችና በምዕራቦች ጌታ እምላለሁ፤ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን::"},{"id":41,"translation":"41. ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም::"},{"id":42,"translation":"42. ያንንም የሚሰፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚያገኙ ድረስ ተዋቸው፤ በአሉባልታዎችም ዉስጥ ይዋኙ፤ ይጫወቱም።"},{"id":43,"translation":"43. ያ ቀን ወደ ጣዖት እንደሚሽቀዳደሙ ሆነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን ነው::"},{"id":44,"translation":"44. ዓይኖቻቸው ያፈሩ ሆነው፤ ውርደት ትሸፍናቸዋለች:: ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ቀን ነው::"}]},{"id":71,"verses":[{"id":1,"translation":"1. እኛ ኑህን ህዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ በማለት ወደ ወገኖቹ ላክነው::"},{"id":2,"translation":"2. እርሱም አለ፡- «ሀዝቦቼ ሆይ! እኔ ለእናንተ (የቸገራችሁን) ገላጭ የሆንኩ አስጠንቃቂ ነኝ::"},{"id":3,"translation":"3. «አላህን ተገዙት፡-ፍሩት፤ እኔንም ታዘዙኝ በማለት አስጠንቃቂ ነኝ።"},{"id":4,"translation":"4. «ለእናንተ ኃጢአታችሁን ይምራል እስከ ተወሰነ ጊዜም ያቆያችኋል:: አላህ የወሰነው ጊዜ በመጣ ወቅት ግን ለአፍታም አይቆይም:: በትክክል የምታውቁት ብትሆኑ ኖሮ በታዘዛችሁ ነበር።»"},{"id":5,"translation":"5. ስለተቃወሙትም «ጌታየ ሆይ! እኔ በሌሊትም ሆነ በቀን ህዝቦቼን ጠራሁ።"},{"id":6,"translation":"6. «ጥሪየም ይበልጥ መሸሽን እንጂ ሌላ አልጨመረላቸዉም።"},{"id":7,"translation":"7. «እኔም ለእነርሱ ትምራቸው ዘንድ ወደ እምነት በጠራኋቸው ቁጥር ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ:: ልብሶቻቸውንም ተከናነቡ:: በመጥፎ ስራቸው ላይ ዘወተሩም:: ያለ ልክ መኩራትንም ኮሩ::"},{"id":8,"translation":"8. «ከዚያ እኔ በግልጽ ጠራኋቸው።"},{"id":9,"translation":"9. «ከዚያ እኔ ለእነርሱ ጥሪየን ይፋ አደረኩ:: ለእነርሱ መመስጠርን መሰጠርኩም» አለ።"},{"id":10,"translation":"10. «እንዲህም አልኩ: ጌታችሁን ምህረትን ለምኑት:: እርሱም በጣም መሀሪ ነውና።"},{"id":11,"translation":"11. «በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል።"},{"id":12,"translation":"12. «ገንዘቦችና ልጆችንም ይለግሳችኋል:: ለእናንተ አትክልቶችን ያደርግላችኋል:: ለእናተም ወንዞችን ያደርግላችኋል አልኳቸው።»"},{"id":13,"translation":"13. ለአላህ ተገቢውን ልቅና የማትሰጡበት ምክንያት ለእናንተ ምን አላችሁ?"},{"id":14,"translation":"14. በልዩ ልዩ (በተለያዩ) እርከኖች (ሁኔታዎች) በእርግጥ የፈጠራችሁ ሲሆን::"},{"id":15,"translation":"15. አላህ ሰባት ሰማያትን አንዱ በአንዱ ላይ የተነባበረ ሲሆን እንዴት እንደፈጠረ አታዩምን?"},{"id":16,"translation":"16. በውስጣቸዉም ጨረቃን አብሪ አደረገ:: ጸሐይንም ብርሃን አደረገ::"},{"id":17,"translation":"17. አላህም ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ::"},{"id":18,"translation":"18. ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል:: ማውጣትንም ያወጣችኋል::"},{"id":19,"translation":"19. አላህም ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ አደረጋት።"},{"id":20,"translation":"20. ከእርሷ ሰፋፊዎችን መንገዶች ትገቡ ዘንድ::"},{"id":21,"translation":"21. ኑሕም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! እነርሱም አመጹብኝ ገንዘቡና ልጁም ከጥፋት በስተቀር ያልጨመረለትን ሰው ተከተሉ።"},{"id":22,"translation":"22. «ከባድንም ተንኮል ያሴሩትን ሰዎች ተከተሉ።"},{"id":23,"translation":"23. መሪዎችም አሉ፡- <አማልክቶቻችሁን፤ ወድንም፤ ሰዋዕንም፤ የጉስንም፤ የዑቅንና ነስርንም አትተው።>"},{"id":24,"translation":"24. «በእርግጥ (እነዚህ መሪዎች ወይም ጣኦቶች) ብዙዎችን ሰዎች አሳሳቱ:: ከሓዲያንንም ጥመትን እንጂ ሌላን አትጨምርላቸው» አለ።"},{"id":25,"translation":"25. በኃጢአቶቻቸው ምክንያት ተሰመጡ:: እሳትንም እንዲገቡ ተደረጉ:: ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የሆኑ ረዳቶችን አላገኙም::"},{"id":26,"translation":"26. ኑህም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! ከከሓዲያን በምድር ላይ (በዓለም ላይ) የሚኖርን አንድንም አትተው።"},{"id":27,"translation":"27. «አንተ ብትተዋቸው ባሮችህን ያሳስታሉና:: ኃጢአተኛ ከሓዲንም እንጂ ሌላን አይወልዱም።"},{"id":28,"translation":"28. «ጌታየ ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ትክክለኛ አማኝ ሆኖ በቤቴ ለገባ ሁሉ ለአማኞችና ለምዕመናትም ምህረት አድርግ:: ከሓዲያንንም ከጥፋት በስተቀር አትጨምርላቸው።» አለ።"}]},{"id":72,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአጋንንት የሆኑ ቡድኖች ቁርኣንን አዳመጠው እንዲህ ማለታቸው ተወረደልኝ በል: «እኛ አስደናቂ የሆነን ቁርአን ሰማን፤"},{"id":2,"translation":"2. «ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራን (ቁርኣን ሰማን) በእርሱም አመንን:: በጌታችን አንድንም አናጋራም::"},{"id":3,"translation":"3. «እነሆ የጌታችን ክብር ላቀ:: ሚስትንም ልጅንም አልያዘም::"},{"id":4,"translation":"4. «እነሆ ቂላችን በአላህ ላይ ወሰን ያለፈን ውሸት ይናገር ነበር::"},{"id":5,"translation":"5. «እኛም ሰዎችና ጋኔኖች በአላህ ላይ ውሸትን ቃል አይናገሩም ማለትን ጠረጠርን» አሉ በማለት ወደእኔ ተወረደ በል።"},{"id":6,"translation":"6. እነሆ ከሰዎች የሆኑ ወንዶች ከአጋንንት በሆኑ ወንዶች ይጠበቁ ነበር። ኩራትንም (ጥመትን) ጨመሯቸው።"},{"id":7,"translation":"7. አላህ አንድንም አይቀሰቅስም ማለትን እንደጠረጠራችሁ እነርሱም ጠረጠሩ::"},{"id":8,"translation":"8. እኛም ሰማይን ለመድረስ ፈለግን ብርቱ ጠባቂዎችንና ችቦዎችንም ተሞልታ አገኘናት::"},{"id":9,"translation":"9. እኛም ከእርሷ ወሬን ለማዳመጥ በመቀመጫዎች እንቀመጥ ነበር:: አሁን (ግን) የሚያዳምጥ (ሁሉ) ተጠባባቂ የእሳት ችቦ ያገኘዋል።"},{"id":10,"translation":"10. እኛም በምድር ውስጥ ባሉት ክፉ ተሽቷል? ወይስ በእነርሱ (በኩል) ጌታቸው ደግን ነገር ሽቷል? ማለትን አናውቅም።"},{"id":11,"translation":"11. ከእኛም ውስጥ ደጋጎች አሉ:: ከእኛም ውስጥ ከዚህ ሌላ የሆኑ አሉ:: የተለያዩ መንገዶች ባለቤቶች ነበርን::"},{"id":12,"translation":"12. እኛም አላህን በምድር ውስጥ ፈጽሞ የማናቅተው ሸሽተንም ፈጽሞ የማናመልጠው መሆናችንን አረጋገጥን::"},{"id":13,"translation":"13. እኛም መሪውን በሰማን ጊዜ በእርሱ አመንን:: ያ! በጌታው የሚያምን ሰው ሁሉ መጎደልንም ሆነ መጨመርን አይፈራም::"},{"id":14,"translation":"14. ከእኛም ውስጥ ሙስሊሞች አሉ:: ከእኛም ውስጥ በዳዩች አሉ:: እነዚያ የሰለሙ ሰዎች ቅንን መንገድ መረጡ::"},{"id":15,"translation":"15. እነዚያ በዳዩችማ ለገሀነም ማገዶ ሆኑ::"},{"id":16,"translation":"16. (ሰዎች ሁሉ በአላህ) በመንገድ ላይ ቀጥ ባሉ ኖሮ ብዙ ዝናብን ባጠጣናቸው ነበር::"},{"id":17,"translation":"17. በእርሱ ልንፈትናቸው (ባጠጣናቸው ነበር)። ያ ጌታውን ከማስታወስ የሚያፈገፍግ ሰው አስቸጋሪ ቅጣት ውስጥ ያስገባዋል::"},{"id":18,"translation":"18. መስጊዶች ሁሉ የአላህ ብቻ ናቸው:: እናም በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ ማለትን ተወረደልኝ::"},{"id":19,"translation":"19. እነሆ የአላህ ባሪያ (ሙሐመድ) አላህን የሚጠራው ሆኖ በተነሳ ጊዜ ጋኒኖቹ በእርሱ ላይ ድርብርቦች ሊሆኑ ቀረቡ::"},{"id":20,"translation":"20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ የማመልከው ጌታየን ብቻ ነው:: በእርሱ አንድንም አላጋራም» በል።"},{"id":21,"translation":"21. «እኔ ለእናንተ ጉዳትንም ሆነ ማቅናትን አልችልም» በል።"},{"id":22,"translation":"22. «እኔን ከአላህ ቅጣት አንድም (አካል) አያድነኝም:: ከእርሱ ሌላ መጠጊያም አላገኝም» በል።"},{"id":23,"translation":"23. ከአላህ የሆኑ መልዕክቶችን ከማድረስ በስተቀር አልችልም:: አላህንና መልዕክተኛውን የሚያምጽ ሁሉ ለእርሱ የገሀነም እሳት አለው:: በውስጧም ዘላለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ።"},{"id":24,"translation":"24. የሚስፈራሩበትንም ባዩ ጊዜ ረዳተ ደካማ ቁጥሩም አነስተኛ የሆነው ማን እንደሆነ በእርግጥ ያውቃሉ::"},{"id":25,"translation":"25. «ያ! የምትስፈራሩበት ነገር ቅርብ ወይም ጌታየ ለእርሱ የተወሰነ ጊዜን የሚያደርግለት እሩቅ መሆኑን አላውቅም።» በላቸው"},{"id":26,"translation":"26. እርሱም እሩቁን ሚስጢር አዋቂ ነው::በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም፡፡»"},{"id":27,"translation":"27. (በሚስጢሩም ላይ) ከመልዕክተኛው ለወደደው ቢሆን እንጂ (ለሌላ አንድንም አያሳውቅም):: አይገልጽም:: ለእርሱም ከበስተፊቱም ከበስተኋላዉም ጠባቂዎቸን ያደርግለታል::"},{"id":28,"translation":"28. ከእነርሱ ዘንድ ባለው ነገር እውቀት የከበበና ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲሆን የጌታቸውን መልዕክቶች ያደረሱ መሆናቸውን ያውቅ (ዘንድ ጠባቂ ያደርጋል)::"}]},{"id":73,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አንተ ተከናናቢው ሆይ::"},{"id":2,"translation":"2. ሌሊቱን (ሁሉ) ጥቂት ሲቀር ቁም (ስገድ)::"},{"id":3,"translation":"3. ግማሹን (ቁም) ወይም ከእርሱ ጥቂትን ቀንስ::"},{"id":4,"translation":"4. ወይም በእርሱ ላይ ጨምር:: ቁርኣንንም በዝግታ አንብብ::"},{"id":5,"translation":"5. እኛ ባንተ ላይ ከባድ ቃልን እናወርዳለንና::"},{"id":6,"translation":"6. ሌሊት መነሳት (ህዋሳትንና ልብን) ለማስማማት በጣም ብርቱ ነው:: ለማንበብም ትክክለኛ ሰዓት ነው::"},{"id":7,"translation":"7. ላንተ በቀን ውስጥ ረዥም የመዘዋወርያ ሰዓት አለህ::"},{"id":8,"translation":"8. የጌታህን ስም አውሳ:: ወደ እርሱም (አምልኮ) መቋረጥን ተቋረጥ::"},{"id":9,"translation":"9. (እርሱም) የምስራቅና የምዕራብ ጌታ ነው:: ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: መጠጊያ አድርገህም ያዘው::"},{"id":10,"translation":"10. (ከሓዲያንም) በሚሉት ላይ ታገስ:: መልካምንም መተው ተዋቸው::"},{"id":11,"translation":"11. የድሎት ባለቤቶችም ከሆኑት አስተባባዮች ጋር ተወኝ:: ጥቂትንም ጊዜ አቆያቸው::"},{"id":12,"translation":"12. ከእኛ ዘንድ ከባድ ማሰሪያዎችና እሳት አሉንና::"},{"id":13,"translation":"13. (ጉሮሮን) የሚያንቅ ምግብና አሳማሚ ቅጣትም አለ።"},{"id":14,"translation":"14. በዚያ ምድርና ጋራዎች በሚርገፈገፉበት፤ ጋራዎችም ፈሳሽ የአሸዋ ክምር በሚሆኑበት ቀን::"},{"id":15,"translation":"15. እኛ ወደ ፊርዖን መልዕክተኛን እንደላክን ሁሉ በእናንተ ላይ መስካሪ መልዕክተኛንም ወደ እናንተ ላክን።"},{"id":16,"translation":"16. ፊርዓውንም መልዕክተኛውን አመጸ:: ብርቱ መያዝንም ያዝነው::"},{"id":17,"translation":"17. (በአላህ) ከካዳችሁ ያን ልጆችን ሸበቶዎች የሚያደርገውን ቀን ቅጣት እንዴት ትጠነቀቃላችሁ?"},{"id":18,"translation":"18. ሰማዩ በቀኑ ተሰንጣቂ ነው:: ቀጠሮዉም ተፈፃሚ ነው::"},{"id":19,"translation":"19. ይህች መገሰጫ ናት። መዳንንም የሻ (የፈለገ) ሰው ወደ ጌታው (የሚያደርሰዉን) መንገድ ይይዛል::"},{"id":20,"translation":"20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ከሌሊቱ ሁለት እጅ ያነሰን፤ ግማሹንም ሲሶውንም የምትቆም መሆንህን ጌታህ ያውቃል:: (ሙስሊሞች) ከእነዚያም አብረውህ ካሉ ከፊሎች የሚቆሙ መሆናቸውንም ያውቃል:: አላህ ሌሊትና ቀንን ይለካል:: ሌሊቱን በሙሉ የማትቆሙት መሆናችሁን አወቀ:: እናም በእናንተ ላይ ህጉን ወደ ማቃለል ተመለሰላችሁ:: ስለዚህ ከቁርኣን (በስግደት) የተቻላችሁን ያህል አንብቡ:: ከናንተ ውስጥ ሌሎችም በሽተኞች ከአላህ ችሮታ ለመፈለግ በምድር ላይ የሚጓዙ ሌሎችም፤ በአላህ መንገድ ሃይማኖት ላይ የሚጋደሉ እንደሚኖሩ አወቀ:: አቃለለላቸዉም ከቁርኣን የቻላችሁትን አንብቡ:: ሶላትንም ስገዱ:: ዘካንም ስጡ:: ለአላህ መልካም ብድርንም አበድሩ:: ከመልካም ስራም ለነፍሶቻችሁ የምታስቀድሙትን ሁሉ የተሻለና በምንዳም ታላቅ ሆኖ በአላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ:: አላህን ምህረት ለምኑት:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::"}]},{"id":74,"verses":[{"id":1,"translation":"1. አንተ (ልብስ) ደራቢው ሆይ!"},{"id":2,"translation":"2. ተነሳና (ህዝቦችህን) አስጠንቅቅ።"},{"id":3,"translation":"3. ጌታህንም አክብር::"},{"id":4,"translation":"4. ልብስህንም አጥራ::"},{"id":5,"translation":"5. ጣዖትንም ራቅ::"},{"id":6,"translation":"6. ማብዛትንም የምትፈልግ ሆነህ አትለግስ::"},{"id":7,"translation":"7. (ብዙ ዒባዳን ከመስራት አትድከም):: ለጌታህም (ትዕዘዛዝ) ታገስ።"},{"id":8,"translation":"8. በቀንዱም በተነፋ ጊዜ፤"},{"id":9,"translation":"9. ይህን ጊዜ ያ ቀን አስቸጋሪ ቀን ነው።"},{"id":10,"translation":"10. (በተለይ) በከሓዲያን ላይ ገር ያልሆነ ቀን ነው።"},{"id":11,"translation":"11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በብቸኝነት ከፈጠርኩት ጋር ተወኝ።"},{"id":12,"translation":"12. ለእርሱም የተዘረጋን ገንዘብ (በዓይነቱ) አደረግኩለት።"},{"id":13,"translation":"13. በየአደባባዩ ተገኝ የሆኑ ወንዶች ልጆችንም ሰጠሁት።"},{"id":14,"translation":"14. ለእርሱም ኑሮውን መዘርጋትን ዘረጋሁለት፤"},{"id":15,"translation":"15. ከዚያ ልጨምርለት ይከጅላል::"},{"id":16,"translation":"16. ሰው ይከልከል! እርሱ ለአናቅጻችን በእርግጥ ተቃዋሚ ነበርና።"},{"id":17,"translation":"17. በእርግጥ (ገሀነም ውስጥ) ችግርን አስገድደዋለሁ።"},{"id":18,"translation":"18. እርሱ (በቁርኣን ጉዳይ) አሰበ፤ ገመተም።"},{"id":19,"translation":"19. እናም ተረገመ:: እንዴት ገመተ!"},{"id":20,"translation":"20. ከዚያ ተረገመ። እንዴትስ ገመተ!"},{"id":21,"translation":"21. ከዚያም እንደገና (በቁርኣን ጉዳይ) ተመለከተ።"},{"id":22,"translation":"22. ከዚያ ፊቱን አጨፈገገ አኮማተረም::"},{"id":23,"translation":"23. ከዚያ (በአላህ ከማመን) ዞረ:: ኮራም::"},{"id":24,"translation":"24. «ይህ ከሌላ (ሰው) የሚቀዳ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።"},{"id":25,"translation":"25. «ይህ የሰው ቃል እንጂ ሌላ አይደለም» አለ::"},{"id":26,"translation":"26. ሰቀር (በተባለ የገሀነም ዋሻ ውስጥ) በእርግጥ አስገባዋለሁ::"},{"id":27,"translation":"27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰቀር ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?"},{"id":28,"translation":"28. (ያገኘችውን ሁሉ) አታስቀርም:: አትተዉምም::"},{"id":29,"translation":"29. የሰዎችን ቆዳ በጣም አክሳይ ናት።"},{"id":30,"translation":"30. በእርሷም ላይ አስራ ዘጠኝ (ዘበኞች) አሉባት::"},{"id":31,"translation":"31. የእሳትን ዘበኞች መላዕክት እንጂ ሌላ አላደረግንም:: ቁጥራቸውንም ለእነዚያ በአላህ ለካዱት ሰዎች መፈተኛ እንጂ ለሌላ አላደረግንም:: እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች እንዲያረጋግጡ፤ እነዚያም በትክክል ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፤ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምዕመናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፤ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው አስመሳዮችና ከሓዲያን «አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል?» እንዲሉ እንጂ (አላደረግንም):: ልክ እንደዚሁ አላህ የሚፈልገውን ያጠማል:: የሚፈልገውንም ያቀናል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህንም ሰራዊት ልክ ከእርሱ በስተቀር ማንም አያውቅም:: የሰቀር እሳት ለሰዎች መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም::"},{"id":32,"translation":"32. (ከክህደት) ይከልከሉ:: በጨረቃ (እምላለሁ)፤"},{"id":33,"translation":"33. በሌሊቱም በሄደ ጊዜ፤"},{"id":34,"translation":"34. በንጋቱም ባበራ ጊዜ እምላለሁ።"},{"id":35,"translation":"35. (ሰቀር) ከታላላቆች አደጋዎች አንዱ፤"},{"id":36,"translation":"36. ለሰዎች አስፈራሪ ናት።"},{"id":37,"translation":"37. ከናንተ መካከል ወደ በጎ ነገር መቅደምን ወይም ወደ ኋላ መቅረትን ለፈለገ (ሰው) ሁሉ፤"},{"id":38,"translation":"38. ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ ተያዥ ናት::"},{"id":39,"translation":"39. እነዚያ መዝገባቸውን በቀኝ እጃቸው የሚሰጡት ብቻ ሲቀሩ::"},{"id":40,"translation":"40. (እነርሱማ) በገነቶች ውስጥ ሁነው እርስ በራሳቸው ይጠያየቃሉ::"},{"id":41,"translation":"41. ከአመጸኞች ሁኔታ (ይጠያየቃሉ)"},{"id":42,"translation":"42. (ከዚያ ለእነርሱ እንዲህ ይሏቸዋል።) «በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?»"},{"id":43,"translation":"43. «ከሰጋጆች አልነበርንም።"},{"id":44,"translation":"44. «ለድሆችም የምናበላም አልነበርንም።"},{"id":45,"translation":"45. «ከዘባራቂዎችም ጋር እንዘባርቅ ነበር።"},{"id":46,"translation":"46. «በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበር፤"},{"id":47,"translation":"47. «እርግጠኛው ነገር ሞት እስከመጣብን ድረስ።» ይላሉ"},{"id":48,"translation":"48. እናም በዚያ ቀን የአማላጆች (ሁሉ) ምልጃ አትጠቅማቸዉም።"},{"id":49,"translation":"49. ከ(ቁርኣን) ከግሳጼም የሚያፈገፍጉበት ምን ምክኒያት አላቸው?"},{"id":50,"translation":"50. እነርሱ ልክ ደንባሪዎች የሜዳ አህዩች ይመስላሉ::"},{"id":51,"translation":"51. ከአንበሳ የሸሹ"},{"id":52,"translation":"52. ይልቁንም ከእነርሱ መካከል ለእያንዳንዱ ሰው የተዘረጉ ጹሑፎችን በእጁ እንዲሰጥ ይፈልጋል::"},{"id":53,"translation":"53. ከዚህ መሰል ተግባራቸው ይከልከሉ:: ይልቁንም የመጨረሻይቱን ዓለም ቅጣት አይፈሩም::"},{"id":54,"translation":"54. ይከልከሉ፤እርሱ(ቁርአን) መገሰጫ ነው።"},{"id":55,"translation":"55. ስለዚህ የፈለገ ሰው ቁርኣንን ይገሰጽበታል::"},{"id":56,"translation":"56. ሆኖም (ሰዎች) አላህ ካልፈለገ በስተቀር አይገሰጹም:: አላህ የመፈራት ባለቤት ነው:: (ለፈሩትም) የምህረት ባለቤት ነው::"}]},{"id":75,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (ሁኔታው ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: በትንሳኤ ቀን እምላለሁ::"},{"id":2,"translation":"2. (ሁኔታው ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: ራሷን ወቃሽ በሆነች ነፍስም እምላለሁ::"},{"id":3,"translation":"3. (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ።) ሰው አጥንቶችን ለመሰብሰባችን ይጠራጠራልን?"},{"id":4,"translation":"4. እንዴታ ጣቶቹንም ፊት እንደነበሩት በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንሆን (እንሰበስባቸዋለን)።"},{"id":5,"translation":"5. ይልቁን ሰው በፊቱ ባለ ነገር በትንሳኤ ቀን ሊያስተባብል ይፈልጋል::"},{"id":6,"translation":"6. «የትንሳኤው ቀን መቼ ነው?» ሲል ይጠይቃል።"},{"id":7,"translation":"7. ዓይንም በዋለለ ጊዜ::"},{"id":8,"translation":"8. ጨረቃም በጨለመ ጊዜ::"},{"id":9,"translation":"9. ጸሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፤"},{"id":10,"translation":"10. ሰው በዚያን ቀን «መሸሻው የት ነው?» ይላል።"},{"id":11,"translation":"11. «ይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም።"},{"id":12,"translation":"12. በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው።» ይባላል።"},{"id":13,"translation":"13. ሰው በዚያን ቀን ያስቀደመውም ያስቆየውም ሁሉ ይነገረዋል።"},{"id":14,"translation":"14. በእርግጥ ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው::"},{"id":15,"translation":"15. ምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣ እንኳን (አይሰማም)።"},{"id":16,"translation":"16. በቁርኣን ንባብ ልትቸኩል ብለህ ምላስህን አታላውስ::"},{"id":17,"translation":"17. በልብህ ውስጥ መሰብሰቡና ማስነበቡ በኛ ላይ ነውና::"},{"id":18,"translation":"18. ባነበብነው ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል።"},{"id":19,"translation":"19. ከዚያም (ላንተ) ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው።"},{"id":20,"translation":"20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመጣደፍ ተከልከል፤ ይልቁንም (ሰዎች ስትባሉ) ፈጣኒቱን ዓለም ትወዳላችሁ::"},{"id":21,"translation":"21. የመጨረሻይቱን ዓለም (ግን) ትተዋላችሁ።"},{"id":22,"translation":"22. (የተወሰኑ) ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው።"},{"id":23,"translation":"23. ወደ ጌታቸው ተመልካቾችም ናቸው::"},{"id":24,"translation":"24. (ሌሎች) ፊቶች ደግሞ በዚያ ቀን አጨፍጋጊዎች ናቸው።"},{"id":25,"translation":"25. በእነርሱም ላይ አደጋ እንደሚሰራባቸው ያረጋገጣሉ::"},{"id":26,"translation":"26. (ሙስሊሞች አስተውሉ።) (ነፍስ) ወደ ጉሮሮ በደረሰች፤"},{"id":27,"translation":"27. «አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፤"},{"id":28,"translation":"28. (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መለየት መሆኑን ባረጋገጠ ጊዜ፤"},{"id":29,"translation":"29. ባትም ከባት በተጣበቀች ጊዜ፤"},{"id":30,"translation":"30. በዚያ ቀን መነዳት ወደ ጌታህ (ፍርድ) ብቻ ነው።"},{"id":31,"translation":"31. እናም (ከሀዲው) አላመነምም፤ አልሰገደምም።"},{"id":32,"translation":"32. ግን በአላህ አስተባበለ፤ ከእምነት ዞረም::"},{"id":33,"translation":"33. ከዚያም እየተንጎማለለ ወደ ቤተሰቡ ሄደ።"},{"id":34,"translation":"34. (የምትጠላውን ነገር) ላንተው ይሁን፤ ላንተ ተገቢህም ነው።"},{"id":35,"translation":"35. ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ላንተ የተገባህም ነው።"},{"id":36,"translation":"36. ሰው እንደፈለገ እንዲኖር ልቅ ሆኖ የሚተው ይመስለዋልን?"},{"id":37,"translation":"37. የሚፈስ ከሆነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን?"},{"id":38,"translation":"38. ከዚያ የረጋ ደም ሆነ:: ከዚያ አላህ ሰው አድርጎ ፈጠረው፤ አስተካከለዉም::"},{"id":39,"translation":"39. ከእርሱም ሁለት ዓይነቶች ወንድና ሴትን አደረገ።"},{"id":40,"translation":"40. (ታዲያ) ይህ ሀያል (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን?"}]},{"id":76,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በሰው ላይ የሚታወስ ነገር (እንኳ) ሳይሆን ከዘመናት የተወሰነ ጊዜ አላለፈም ነበርን? (በእርግጥ አልፏል)።"},{"id":2,"translation":"2. እኛ ሰውን (በሕግጋት ግዳጅ) የምንሞክረው ስንሆን ከወንድና ከሴት ፈሳሽ ቅልቅሎች ከሆነች የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው:: ሰሚና ተመልካችም አደረግነው።"},{"id":3,"translation":"3. እኛ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲሆን መንገዱን መራነው::"},{"id":4,"translation":"4. እኛ ለከሓዲያን ሰንሰሎቶችንና እንዛዝላዎችን፣ እሳትንም (አዘጋጅተናል)::"},{"id":5,"translation":"5. እነዚያ (ትክክለኛ) በጎ አድራጊዎች መበረዣዋ ካፉር ከሆነች ጠጅ ይጠጣሉ::"},{"id":6,"translation":"6. ከእርሷ እነዚያ የአላህ ባሮች የሚጠጡላት ና ወደ ፈለጉበት ማንቧቧትን የሚያንቧቧት ከሆነች የጠጅ ምንጭ (ይጠጣሉ)::"},{"id":7,"translation":"7. (ዛሬ በዚህ ዓለም እያሉ) በስለታቸው ይሞላሉ:: መከራው ተሰራጪ የሆነንም ቀን ይፈራሉ::"},{"id":8,"translation":"8. ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ለድሃ፤ ለየቲምና ለምርኮኛ ያበላሉ::"},{"id":9,"translation":"9. «የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው:: ከናንተ ክፍያንም ሆነ ማመስገንን አንፈልግም::"},{"id":10,"translation":"10. እኛ ያንን (ፊትን) የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና» (ይላሉ)።"},{"id":11,"translation":"11. አላህም የዚያን ቀን ክፋት ጠበቃቸው። (ፊታቸው) ማማርንና መደሰትንም ገጠማቸው::"},{"id":12,"translation":"12. በመታገሳቸዉም (ምክንያት) ገነትንና የሀር ልብስን መነዳቸው::"},{"id":13,"translation":"13. በውስጧ በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች፤ በውስጧ የጸሀይን ሐሩርንም ሆነ ብርድንም የማያዩ ሲሆኑ፤"},{"id":14,"translation":"14. ዛፎቿም ለእነርሱ የቀረበች፤ ፍራፍሬዎችዋም ለለቃሚዎች መገራትን የተገራች ስትሆን ገነትን መነዳቸው::"},{"id":15,"translation":"15. በእነርሱም ላይ ከብር በተሰሩ ዕቃዎች (ሳህኖች)፤ ብርጭቆዎች እና በኩባያዎችም ይዝዞርባቸዋል::"},{"id":16,"translation":"16. መለካትን የለኳቸው በሆኑ የብር ብርጭቆዎች (ይዝዞርባቸዋል)::"},{"id":17,"translation":"17. በእርሷም መበረዣዋ ዝንጂብል የሆነች ወይን ጠጅ ይጥጠጣሉ።"},{"id":18,"translation":"18. በውስጧ ያለችውን ሰልሰቢል ተብላ የምትጠራውን ምንጭ::"},{"id":19,"translation":"19. በእነርሱም ላይ ባሉበት ሁኔታ የሚዘወትሩ ወጣት ልጆች ይዘዋወራሉ:: ባየሃቸው ጊዜ የተበተነ ሉል ናቸው ብለህ ታስባቸዋለህ::"},{"id":20,"translation":"20. እዚያንም በተመለከትክ ጊዜ ጸጋንና ታላቅ ንግስናን ታያለህ::"},{"id":21,"translation":"21. አረንጓዴዎች የሆኑ ቀጭን ሀር ልብሶችና ወፍራም ሀርም በላያቸው ላይ አለ። ከብር የሆኑ አንባሮችንም ይሸለማሉ:: ጌታቸዉም (ከራሱ አልፎ) ሌላን አጥሪ የሆነን መጠጥ ያጠጣቸዋል::"},{"id":22,"translation":"22. «ይህ ለእናንተ ዋጋ ሆነ:: ስራችሁም ምስጉን ሆነ» ይባላሉ::"},{"id":23,"translation":"23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ (ይህንን) ቁርኣን ባንተ ላይ ማውረድን አወረድነው።"},{"id":24,"translation":"24. ለጌታህ ፍርድም ታገስ:: ከእነርሱም መካከል ኃጢአተኛን ወይም ከሓዲን አትታዘዝ::"},{"id":25,"translation":"25. የጌታህን ስም በጠዋትና ከቀትር በኋላ አውሳ::"},{"id":26,"translation":"26 ከሌሊቱም ለእርሱ ብቻ ስገድ፤ በረዢም ሌሊትም አወድሰው።"},{"id":27,"translation":"27. እነዚያ ይህችን ፈጣኒቱን ዓለም ይወዳሉ። ከባድና (አስቸጋሪ) ቀንም በስተፊታቸው ሆኖ ችላ ይላሉ::"},{"id":28,"translation":"28. እኛ ፈጠርናቸው:: የአካሎቻቸዉንም መለያያቸውን አጠነከርን:: በፈለግን ጊዜ መሰሎቻቸውን መለወጥን እንለውጣለን።"},{"id":29,"translation":"29. ይህ መገሰጫ ነው:: የፈለገ ሰውም ወደ ጌታው መንገድ ይይዛል::"},{"id":30,"translation":"30. አላህም ካልሻ በስተቀር አትሹም፤ አላህ አዋቂና ጥበበኛ ነውና::"},{"id":31,"translation":"31. (አላህ) የሚፈልገውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባዋል:: በዳዩችንም (ዝቶባቸዋል) ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅቶላቸዋል::"}]},{"id":77,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ተከታታይ ሆነው በተላኩት ፤ (እምላለሁ)፡፡"},{"id":2,"translation":"2. በኃይል መንፈስን ነፋሾች በሆኑትም (ንፋሶች)፤"},{"id":3,"translation":"3. መበተንን በታኝ በሆኑትም (ንፋሶች)፤"},{"id":4,"translation":"4. መለየትን ለይዎች በሆኑትም (መላዕክት)፤"},{"id":5,"translation":"5. መገሰጫን (ወደ ነብያት ጣይዎች) አምጪዎች በሆኑትም (መላዕክት)፤"},{"id":6,"translation":"6. ማሳበቢያን ለማስወገድ ወይም ለማስጠንቀቅ፤"},{"id":7,"translation":"7. ያ! የምትስፈራሩበት (ትንሳኤ) በእርግጥ ኋኝ ነው ብየ እምላለሁ::"},{"id":8,"translation":"8. ከዋክብትም (ብርሃኗ) በታበሰች ጊዜ፤"},{"id":9,"translation":"9. ሰማይም በተከፈተች ጊዜ፤"},{"id":10,"translation":"10. ጋራዎችም በተንኮታኮቱ ጊዜ::"},{"id":11,"translation":"11. መልዕክተኞቹም ወቅት በተደረገላቸው ጊዜ፤"},{"id":12,"translation":"12. ለየትኛው ቀን ተቀጠሩ የሚባል ሲሆን፤"},{"id":13,"translation":"13. ለዚያ ለመለያው ቀን ተቀጠሩ በተባለ ጊዜ (በፍጡሮች መካከል በትክክል ይፈርዳል)፤"},{"id":14,"translation":"14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመለያው ቀን ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?"},{"id":15,"translation":"15. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያን ቀን ወዮላቸው።"},{"id":16,"translation":"16. የፊተኞቹን (ህዝቦች) አላጠፋንምን?"},{"id":17,"translation":"17. ከዚያ ኋለኞቹን እናስከትላቸዋለን::"},{"id":18,"translation":"18. በአመጸኞች ሁሉ ላይ ልክ እንደዚሁ (ያለ) እንሰራለን።"},{"id":19,"translation":"19. ለአስተባባዩች (ሁሉ) በዚያን ቀን ወዮላቸው።"},{"id":20,"translation":"20. (ሰዎች ሆይ!) ከደካማ ውሃ አልፈጠርናችሁምን?"},{"id":21,"translation":"21. በተጠበቀ መርጊያ ውስጥም (በእናቶች ማህጸን) ውስጥ አደረግነው::"},{"id":22,"translation":"22. እስከታወቀ ጊዜ ድረስ::"},{"id":23,"translation":"23.መጠንነዉም ምን ያማርንም መጣኞች ነን::"},{"id":24,"translation":"24. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያን ቀን ወዮላቸው።"},{"id":25,"translation":"25. (ሰዎች ሆይ!) ምድርን ሰብሳቢ አላደረግናትምን::"},{"id":26,"translation":"26. ህያው ሆናችሁም ሙታን ሆናችሁም።"},{"id":27,"translation":"27. በውስጧም ከፍተኛዎችን (ትላልቅ) ተራራዎች አደረግን፤ ጣፋጭ ውሃንም አጠጣናችሁ::"},{"id":28,"translation":"28. ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላችሁ::"},{"id":29,"translation":"29. «ወደዚያ በእርሱ ታስተባብሉ ወደ ነበራችሁት ቅጣት ሂዱ።"},{"id":30,"translation":"30. ባለ ሶስት ቅርንጫፎች ወደ ሆነው ጥላ ሂዱ።» (ይባላሉም)"},{"id":31,"translation":"31. ጥላም ያልሆነ ከእሳቱም ላንቃ የማያድን ወደ ሆነው (ሂዱ)::"},{"id":32,"translation":"32. እርሷ እንደ ታላላቅ ህንፃ የሆኑን ቃንቄዎች (የእሳት ፍንጣሪዎች) ትወረውራለች::"},{"id":33,"translation":"33. (ቃንቄዉም) ልክ ዳለቻዎች ግመሎችን ይመስላል።"},{"id":34,"translation":"34. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።"},{"id":35,"translation":"35. ይህ የማይናገሩበት ቀን ነው።"},{"id":36,"translation":"36. ይቅርታም ይጠይቁ ዘንድ አይፈቀድላቸዉም::"},{"id":37,"translation":"37. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮውላቸው።"},{"id":38,"translation":"38. ይህ የመለያው ቀን ነው። እናንተንም የፊተኞችንም ሰበሰብናችሁ።"},{"id":39,"translation":"39. ለእናንተም (ለማምለጥ) ብልሃት እንዳላችሁ ተተናኮሉኝ።"},{"id":40,"translation":"40. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።"},{"id":41,"translation":"41. ጥንቅቆች በጥላዎችና በምንጮች፤ውስጥ ናቸው፡፡"},{"id":42,"translation":"42. በሚፈልጉትም የፍራፍሬ (አይነቶች) ውስጥ ናቸው።"},{"id":43,"translation":"43. «ትሰሩትም በነበራችሁት ዋጋ የምትደሰቱ ሆናችሁ ብሉ፤ ጠጡም» ይባላሉ፤"},{"id":44,"translation":"44. እኛ መልካም ሰሪዎችን (ሁሉ) እንደዚሁ እንመነዳለን፤"},{"id":45,"translation":"45. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።"},{"id":46,"translation":"46. አስትባባዮች ሆይ! ብሉ ጥቂትንም ጊዜ ተጠቀሙ እናንተ አመጸኞች ናችሁና::"},{"id":47,"translation":"47. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።"},{"id":48,"translation":"48. ለእነርሱ «ስገዱ» በተባሉም ጊዜ አይሰግዱም።"},{"id":49,"translation":"49. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።"},{"id":50,"translation":"50. ከእርሱም ሌላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?"}]},{"id":78,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ከምን ነገር ይጠያየቃሉ?"},{"id":2,"translation":"2. ከታላቁ ዜና (ቁርኣን) ይጠያየቃሉ።"},{"id":3,"translation":"3. ስለዚያ እነርሱ በእርሱ ላይ ስለተለያዩበት (ስለተወዛገቡበት)::"},{"id":4,"translation":"4. ጉዳዩ እነርሱ እንደሚሉት አይደለም:: (ትክክለኛውን) ወደ ፊት ያውቃሉ::"},{"id":5,"translation":"5. ከዚያም ይከልከሉ፤ (ትክክለኛውን) ወደ ፊት ያውቃሉ።"},{"id":6,"translation":"6. ምድርን ምንጣፍ አላደርግንምን?"},{"id":7,"translation":"7. ጋራዎችንም ችካሎች (አላደረግንምን)?"},{"id":8,"translation":"8. ጥንዶች አድርገንም ፈጠርናችሁ።"},{"id":9,"translation":"9. እንቅልፋችሁንም እረፍት አደረግን።"},{"id":10,"translation":"10. ሌሊቱንም ልባስ አደረግን::"},{"id":11,"translation":"11. ቀኑንም ለኑሮ መስሪያ (ለጉዳይ መከወኛ) አደረግን።"},{"id":12,"translation":"12. ከበላያቸሁም ሰባት ብርቱዎችን (ሰማያት) ገነባን።"},{"id":13,"translation":"13. አንጸባራቂ ብርሃንንም አደርግንላችሁ።"},{"id":14,"translation":"14. ከአረገዙት ደመናዎችም የሚንቧቧ ውሃን አወረድን::"},{"id":15,"translation":"15.በእርሱ እህልንና ቅጠላ ቅጠልን፤ እናወጣ ዘንድ(አወረድን)።"},{"id":16,"translation":"16. የተቆላለፉ አትክልቶችንም ::"},{"id":17,"translation":"17. (በህዝቦች መካከልም) የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው።"},{"id":18,"translation":"18. (ይሀዉም) በቀንዱ በሚነፋበትና በቡድን በቡድን ሆናችሁም በምትመጡበት ቀን ነው።"},{"id":19,"translation":"19. ሰማይም በምትከፈትና ባለ ብዙ ደጃፎችም በምትሆንበት ቀን፤"},{"id":20,"translation":"20. ጋራዎችም በሚናዱበትና እንደ ሲሪብዶም በሚሆንበትም ቀን ነው።"},{"id":21,"translation":"21. ገሀነም (ለከሓዲያን) መጠባበቂያ ኬላ (ስፍራ) ናት::"},{"id":22,"translation":"22. ለህግ ተላላፊዎች መመላለሻ ስትሆን።"},{"id":23,"translation":"23. በውስጧ ብዙ ዘመናትን ነዋሪዎች ሲሆኑ፤"},{"id":24,"translation":"24. በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጠንም አይቀምሱም (አያገኙም)።"},{"id":25,"translation":"25. ሙቅ የፈላ ውሃንና እዥን እንጂ"},{"id":26,"translation":"26. ተመጣጣኝን ምንዳ ይመነዳሉ።"},{"id":27,"translation":"27. ምርመራ (እንዳለባቸው) ቅንጣት አይጠብቁም ነበርና።"},{"id":28,"translation":"28. በአናቅጻችንም ማስተባበልን አስተባበሉ።"},{"id":29,"translation":"29. ነገሩን ሁሉ የተፃፈ ሲሆን አጠቃለልነው።"},{"id":30,"translation":"30. «(የጃችሁን) ቅመሱም፤ ቅጣትን እንጂ ሌላን አንጨምርላችሁም» (ይባላሉም)።"},{"id":31,"translation":"31. ለጥንቅቆቹ (አላህን ለሚፈሩ) ስኬት አላቸው።"},{"id":32,"translation":"32. አትክልቶችና ወይኖችም፤"},{"id":33,"translation":"33. በእድሜ እኩያዎች የሆኑ ጡተ ጉችማዎችም፤"},{"id":34,"translation":"34. የተሞሉ ብርጭቆዎችም፤"},{"id":35,"translation":"35. በውስጧ ትርፍ ቃልንም፤ ማስዋሸትንም አይሰሙም::"},{"id":36,"translation":"36. ከጌታህ የሆነን ምንዳ፤ በቂ ስጦታን ተሰጡ::"},{"id":37,"translation":"37. የሰማያትና የምድር በመካከላቸዉም ላለው ሁሉ ጌታ ከሆነውና በጣም አዛኝ ከሆነው ተመነዱ፤ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም::"},{"id":38,"translation":"38. መልአኩ (ጅብሪል) እና ሌሎች መላዕክትም የተሰለፉ ሆነው በሚቆሙበት ቀን አረህማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ብቻ ቢሆን እንጂ መነጋገርን አይችሉም።"},{"id":39,"translation":"39. ያ! የእውነት ቀን ነው። የፈለገ ሰው ወደ ጌታው በመልካም ተግባር መመለስን ተግባሩ አድርጎ ይይዛል።"},{"id":40,"translation":"40. እኛ ቅርብ የሆነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ። ሰዎች ሁሉ በሁለት እጆቻቸው ያስቀደሙትን በግልጽ የሚያይበትና ከሓዲያን ሁሉ «ዋ ምኞቴ! ምንነው አፈር በሆንኩ ባልተቀሰቀስኩኝ» የሚሉበት ቀን።"}]},{"id":79,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (ነፍስን (ሩህን)) በኃይል መንጫቂዎች በሆኑት፤"},{"id":2,"translation":"2. በቀስታ መምዘዝን መዛዦች በሆኑትም፤"},{"id":3,"translation":"3. መዋኘትንም ዋኚዎች በሆኑት፤"},{"id":4,"translation":"4. መቅደምንም ቀዳሚዎች በሆኑት፤"},{"id":5,"translation":"5. ጉዳይንም አስተናባሪዎች በሆኑት መላዕክት እምላለሁ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)።"},{"id":6,"translation":"6. (ይህም የሚሆነው) ተርገፍጋፊይቱ (ምድር) በምትርገፈገፍበት ቀን፤"},{"id":7,"translation":"7. ተከታይቱም በምትከተላት ቀን (ትቀሰቀሳላችሁ)።"},{"id":8,"translation":"8. በዚያ ቀን ልቦች ተሸባሪዎች ናቸው::"},{"id":9,"translation":"9. ዓይኖቻቸው ተዋራጆች (አቀርቃሪዎች) ናቸው።"},{"id":10,"translation":"10. «እኛ ወደ መጀመሪያይቱ ሁኔታ ተመላሾች ነን እንዴ?» ይላሉ።"},{"id":11,"translation":"11. የበሰበሱ አጥንቶች በሆንን ጊዜ እንደገና እንቀሰቀሳለን?"},{"id":12,"translation":"12. «እንዲያማ ከሆነ ያች የኪሳራ መመለስ ናታ!» ይላሉ።"},{"id":13,"translation":"13. እርሷን (እውን የምታደርጋት) አንዲት ጩኸት ብቻ ናት።"},{"id":14,"translation":"14. ወዲያውኑ በንቃት ላይ ናቸው።"},{"id":15,"translation":"15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሙሳ ወሬ መጣልህን?"},{"id":16,"translation":"16. ጌታው በተቀደሰው ጡዋ ሸለቆ በጠራው ጊዜ፤"},{"id":17,"translation":"17. ወደ ፈርዖን ሂድ፤ ወሰን አልፏልና::"},{"id":18,"translation":"18. (እንዲህም) በለው: «እራስህን ለማጥራት ታስባለህን?"},{"id":19,"translation":"19. ጌታህንም ትፈራ ዘንድ መንገዱን ልመራህ፤ (ታስባለህን?)»"},{"id":20,"translation":"20. (ሙሳ ለፈርዖን) ታላቁንም ተዐምር አሳየው።"},{"id":21,"translation":"21. አስተባበለም፤ አመጸም፤"},{"id":22,"translation":"22. ከዚያ ለመጥፋት የሚተጋ ሆኖ ዞረ::"},{"id":23,"translation":"23. (ህዝቡን) ሰበሰበም ተጣራም።"},{"id":24,"translation":"24. እኔ «ታላቁ ጌታችሁ ነኝ» አለም።"},{"id":25,"translation":"25. አላህም በኋለኛይቱና በፊተኛይቱ ቃል ቅጣት ያዘው::"},{"id":26,"translation":"26. በዚህ ውስጥ አላህን ለሚፈሩ በእርግጥ ማስጠንቀቂያ አለበት።"},{"id":27,"translation":"27. በአፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይስ ሰማይ? (አላህ) ገነባት::"},{"id":28,"translation":"28. ከፍታዋን አጓነ አስተካከላትም።"},{"id":29,"translation":"29. ሌሊቷንም ሸፈነ፤ ቀኗንም ግልጽ አደረገ።"},{"id":30,"translation":"30. ምድርንም ከዚያ በኋላ ዘረጋት።"},{"id":31,"translation":"31. ውሃዋንና ግጦሿን ከእርሷ አወጣ::"},{"id":32,"translation":"32. ጋራዎችንም አደላደላቸው።"},{"id":33,"translation":"33. ለእናንተም ለእንስሶቻችሁም መጣቀሚያ ይሆን ዘንድ (ይሄን አደረገ)።"},{"id":34,"translation":"34. ታላቂቱም መዓት በመጣች ጊዜ፤"},{"id":35,"translation":"35. ሰው ሁሉ የሰራውን የሚያስታውስበት ቀን፤"},{"id":36,"translation":"36. ገሀነምም ለሚያይ ሰው በተገለጠች ጊዜ፤"},{"id":37,"translation":"37. የካደ ሰውማ፤"},{"id":38,"translation":"38. ቅርቢቱንም ሕይወት የመረጠ፤"},{"id":39,"translation":"39. በእርግጥ መኖሪያው ጀሀነም ናት።"},{"id":40,"translation":"40. በጌታው ፊት መቆምን የፈራና ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለማ፤"},{"id":41,"translation":"41. በእርግጥ መኖሪያው ገነት ናት።"},{"id":42,"translation":"42. ስለሰዓቲቱም መነሻዋ መቼ እንደሆነ ይጠይቁሃል።"},{"id":43,"translation":"43. (ለመሆኑ አንተ ስለዚያች እለት) በመወሳቷ ምን ላይ አለህበትና?"},{"id":44,"translation":"44. የእርሷ ጉዳይ የሚመለሰው ወደ ጌታህ ብቻ ነው::"},{"id":45,"translation":"45. አንተ ያለብህ ለሚፈራት ሰው ሁሉ ስለ እርሷ (ከወዲሁ) ማስጠንቀቅ ነው።"},{"id":46,"translation":"46. እነርሱ የሚያይዋት ቀን የአንዲትን ቀን ምሽት ወይም ረፋዷን እንጂ ያልቆዩ ይመስላሉ::"}]},{"id":80,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፤"},{"id":2,"translation":"2. ዓይነስውሩ ወደ እርሱ ስለመጣ።"},{"id":3,"translation":"3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምን ያሳውቅሃል? ምን አልባትም (ይህ አይነስውር ሰው ካንተ በሚሰማው ምክር ከኃጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል::"},{"id":4,"translation":"4. ወይም ሊገሰጽና ግሳጼይቱም ልትጠቅመው ይከጀላል::"},{"id":5,"translation":"5. ያ! ከአላህ የተብቃቃውን ሰውማ፤"},{"id":6,"translation":"6. አንተ ለእርሱ ትዘጋጃለህ።"},{"id":7,"translation":"7. ባይጥራራ (ባያምን)፤ ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትሆን፤"},{"id":8,"translation":"8. ያ! እየገሰገሰ የመጣህ ሰውማ፤"},{"id":9,"translation":"9. እርሱ አላህን የሚፈራ ሲሆን፤"},{"id":10,"translation":"10. አንተ ከእርሱ ትዘናጋለህ::"},{"id":11,"translation":"11. ተከልከል፤ (ቁርኣን) ማስገንዘቢያ ነው::"},{"id":12,"translation":"12. የፈለገ ሰው ሁሉ (ቁርኣኑን) ያስታውሰዋል::"},{"id":13,"translation":"13. በተከበሩት ጹሑፎች ውስጥ ነው::"},{"id":14,"translation":"14. ከፍ በተደረገች፤ ንጹህም በተደረገች (ጹሑፍ ውስጥ ነው)።"},{"id":15,"translation":"15. በጸሐፊዎች መላዕክት እጆች (ንጹህ የተደረገ)::"},{"id":16,"translation":"16. የተከበሩና ታዛዦች በሆኑት ጸሐፊዎች (እጆች)፤"},{"id":17,"translation":"17. ሰው ተረገመ። ምን ከሓዲ አደረገው?"},{"id":18,"translation":"18. (ጌታው) ከምን ነገር ፈጠረው?"},{"id":19,"translation":"19. (አያስብምን?) ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ መጠነዉም::"},{"id":20,"translation":"20. ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራው::"},{"id":21,"translation":"21. ከዚያም ገደለው:: እንዲቀበርም አደረገው፤"},{"id":22,"translation":"22. ከዚያ ማንሳቱን በፈለገ ጊዜ ያስነሳዋል::"},{"id":23,"translation":"23. በእውነት ያንን ጌታው ያዘዘውን ገና አልፈጸመም::"},{"id":24,"translation":"24. ሰው ወደ ምግቡ ይመልከት፤"},{"id":25,"translation":"25. እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መሆናችንን፤"},{"id":26,"translation":"26. ከዚያ ምድርን በደካማ ቡቃያ መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤"},{"id":27,"translation":"27. በውስጧም እህልን ያበቀልን"},{"id":28,"translation":"28. ወይንም እርጥብ ሳርንም፤"},{"id":29,"translation":"29. የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤"},{"id":30,"translation":"30. ጭፍቆች አትክልቶችንም፤"},{"id":31,"translation":"31. ፍራፍሬንና፤ ገለባንም (ያበቀልን መሆናችንን ይመልከት)።"},{"id":32,"translation":"32. ለእናንተም ለእንሰሶቻችሁም መጠቀሚያ ይሆን ዘንድ (ይህን ሰራን)::"},{"id":33,"translation":"33. አደንቋሪይቱ (መከራ) በመጣች ጊዜ፤"},{"id":34,"translation":"34. ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤"},{"id":35,"translation":"35. ከእናቱም፤ ከአባቱም፤ (በሚሸሽበት ቀን)"},{"id":36,"translation":"36. ከሚስቱና ከልጁም፤ (በሚሸሽበት ቀን)"},{"id":37,"translation":"37. ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን ከሌላው የሚያብቃቃው ሁኔታ አለው::"},{"id":38,"translation":"38. ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች፤"},{"id":39,"translation":"39. ሳቂዎችና ተደሳቾች ናቸው::"},{"id":40,"translation":"40. ፊቶች ደግሞ በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትብያ አለባቸው።"},{"id":41,"translation":"41. ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች፤"},{"id":42,"translation":"42. እነዚያ እነርሱ በአላህ ከሓዲያን እና በትዕዛዙ ላይ አመጸኞቹ ናቸው።"}]},{"id":81,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ጸሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤"},{"id":2,"translation":"2. ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤"},{"id":3,"translation":"3. ተራራዎች በተናዱ ጊዜ፤"},{"id":4,"translation":"4. የአስር ወር እርጉዝ ግመሎች ያለጠባቂ በተተው ጊዜ፤"},{"id":5,"translation":"5. አራዊቶችም በተሰበሰቡ ጊዜ፤"},{"id":6,"translation":"6. ባህሮችም በተቀጣጠሉ ጊዜ፤"},{"id":7,"translation":"7. ነፍሶች በተቆራኙ ጊዜ፤"},{"id":8,"translation":"8. ከነሕይወቷ የተቀበረችው ሴት ልጅም በተጠየቀች ጊዜ፤"},{"id":9,"translation":"9. በምን ወንጀል እንደተገደለች፤ በተጠየቀች ጊዜ፤"},{"id":10,"translation":"10. ጹሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤"},{"id":11,"translation":"11. ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤"},{"id":12,"translation":"12. ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤"},{"id":13,"translation":"13 ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤"},{"id":14,"translation":"14. ነፍስ (ሁሉ ከስራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤"},{"id":15,"translation":"15. (ሁኔታው ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: ተመላሾች በሆኑት (ከዋክብት) እምላለሁ::"},{"id":16,"translation":"16. አንዳንድ ጊዜ ሂያጆች በሌላ ጊዜ ገቢዎች በሆኑት"},{"id":17,"translation":"17. በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤"},{"id":18,"translation":"18. በንጋትም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ እምላለሁ::"},{"id":19,"translation":"19. እርሱ (ቁርኣን) የተከበረው መልዕክተኛ ጅብሪል ቃል ነው።"},{"id":20,"translation":"20. የኃይል ባለቤት የሆነ፤ ከዙፋኑ ባለቤት ዘንድም ባለሟል የሆነ፤"},{"id":21,"translation":"21. በዚያ ስፍራ ትዕዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝም የሆነው (መልዕክተኛ ቃል ነው)።"},{"id":22,"translation":"22. ነብያችሁም በፍጹም እብድ አይደለም።"},{"id":23,"translation":"23. በግልጹ አድማስ ላይ ሆኖ (ጅብሪልን) በእርግጥ አይቶታል።"},{"id":24,"translation":"24. እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም::"},{"id":25,"translation":"25. (ቁርኣን) የርጉም ሰይጣን ቃልም አይደለም::"},{"id":26,"translation":"26. ታዲያ (ይህንን በተመለከተ) ወዴት ትሄዳላቸሁ?"},{"id":27,"translation":"27. እርሱ የዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም::"},{"id":28,"translation":"28. ከናንተ መካከል ቀጥተኛ መሆንን ለፈለገ (ሁሉ መገሰጫ) ነው።"},{"id":29,"translation":"29. (ሰዎች ሆይ!) የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ካልሻ በስተቀር እናንተ አንድም ነገር አትሹም።"}]},{"id":82,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤"},{"id":2,"translation":"2. ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤"},{"id":3,"translation":"3. ባህሮችም በተከፈቱና በተደባለቁ ጊዜ፤"},{"id":4,"translation":"4. መቃብሮችም በተገለባበጡና ሙታን በተነሱ ጊዜ፤"},{"id":5,"translation":"5. (ያኔ) ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያዘገየችውን ታውቃለች።"},{"id":6,"translation":"6. አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ?"},{"id":7,"translation":"7. በዚያ በፈጠረህ፤ አካለ ሙሉም ባደረገህ፤ ባስተካከለህም፤"},{"id":8,"translation":"8. በማንኛውም (እርሱ) በፈለገው ቅርጽ በገጣጠመህ ጌታህ ምን አታለለህ?"},{"id":9,"translation":"9 (ሰዎች ሆይ!) ተከልከሉ፤ በእውነት በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ።"},{"id":10,"translation":"10. በእናንተ ላይ ጠባቂዎች ያሉባችሁ ስትሆኑ፤"},{"id":11,"translation":"11. የተከበሩ ጸሐፊዎች የሆኑ (ተጠባባቂዎች)፤"},{"id":12,"translation":"12. የምትሰሩትን (ሁሉ) ያውቃሉ፤"},{"id":13,"translation":"13. (እውነተኞቹ) ደጋጎች በእርግጥም በገነት ውስጥ ናቸው።"},{"id":14,"translation":"14.ከሓዲያንም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው::"},{"id":15,"translation":"15.በፍርዱ ቀን ይገቧታል::"},{"id":16,"translation":"16.እነርሱም (ምን ጊዜም) ከእርሷ ራቂዎች አይደሉም::"},{"id":17,"translation":"17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የፍርዱ ቀን ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?"},{"id":18,"translation":"18. ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደሆነ ምን አሳወቅህ?"},{"id":19,"translation":"19. (እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግ የማትችልበት ቀን ነው:: ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው::"}]},{"id":83,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ለቀሻቢዎች ወዮላቸው፤"},{"id":2,"translation":"2. ለእነዚያ ከሰዎች ለመግዛት ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፤"},{"id":3,"translation":"3. እነርሱም (ለሰዎች) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎሉ (ለሆኑት)::"},{"id":4,"translation":"4. እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መሆናቸውን (በትክክል) አያውቁምን?"},{"id":5,"translation":"5. ለታላቁ ቀን፤"},{"id":6,"translation":"6. ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ) በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መሆናቸውን)::"},{"id":7,"translation":"7. በእውነት የከሓዲያን መዝገብ በእርግጥ በ\"ሲጂን\" ውስጥ ነው።"},{"id":8,"translation":"8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) \"ሲጂን\" ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?"},{"id":9,"translation":"9. የታተመ (የተጠናቀቀ) መጽሐፍ ነው።"},{"id":10,"translation":"10. ለአስተባባዮች (ሁሉ) በዚያ ቀን ወዮላቸው።"},{"id":11,"translation":"11. ለእነዚያ በፍርድ ቀን ለሚያስተባብሉት::"},{"id":12,"translation":"12. በእርሱም ወሰን አላፊ ኃጢአተኛ ሁሉ እንጂ ሌላ አያስተባብልም::"},{"id":13,"translation":"13. አናቅጻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ እኒህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው ይላል::"},{"id":14,"translation":"14. ይከልከሉ፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሰሩት የነበሩት ኃጢአት ደገደገባቸው::"},{"id":15,"translation":"15. ይከልከሉ:: እነርሱ በዚያ ቀን ጌታቸውን ከማየት ተጋራጆች ናቸው::"},{"id":16,"translation":"16. ከዚያ እነርሱ በእርግጥ ገሀነም ገቢዎች ናቸው::"},{"id":17,"translation":"17. ከዚያ ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው ይባላሉ::"},{"id":18,"translation":"18. የ(እውነተኞቹ) ደጋጎች መጽሐፍ በ\"ዒሊዩን\" ውስጥ ነው።"},{"id":19,"translation":"19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) \"ዒሊዩን\"ም ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?"},{"id":20,"translation":"20. የታተመ (የተጠናቀቀ) መጽሐፍ ነው።"},{"id":21,"translation":"21. (የአላህ) ባለሟሎቹ ይጠብቁታል (ይጣዱታል)።"},{"id":22,"translation":"22. (እውነተኞቹ) ደጋጎች በእርግጥም በገነት ውስጥ ናቸው።"},{"id":23,"translation":"23. በተዋቡ ዙፋኖች ላይ የተደገፉ ሆነው ይመለከታሉ።"},{"id":24,"translation":"24. ከፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ትረዳለህ (ታውቃለህ)።"},{"id":25,"translation":"25. ተጣርቶ ከታተመ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ::"},{"id":26,"translation":"26. መደምደሚያው ሚስክ ከሆነ (መጠጥ ይጠጣሉ)። ተሽቀዳዳሚዎች በዚህ ይሽቀዳደሙ።"},{"id":27,"translation":"27. መበረዣዉም ከተስኒም ነው።"},{"id":28,"translation":"28. (የአላህ) ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት።"},{"id":29,"translation":"29. እነዚያ (በአላህ ላይ) ያመጹት በእነዚያ (በአላህ) ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበር።"},{"id":30,"translation":"30. በእነርሱም አጠገብ ባለፉ ጊዜ ይጠቋቆሙባቸው (ይጠቃቀሱባቸው) ነበር::"},{"id":31,"translation":"31. ወደ ቤተሰቦቻቸዉም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ሆነው ይመለሱ ነበር።"},{"id":32,"translation":"32. ባዩዋቸዉም ጊዜ፡- \"እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው።\" ይሉ ነበር።"},{"id":33,"translation":"33. በእነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲሆኑ::"},{"id":34,"translation":"34. ዛሬ (በትንሳኤ ቀን) ግን እነዚያ በትክክል በአላህ ያመኑት ሰዎች በከሓዲያን ላይ ይስቃሉ::"},{"id":35,"translation":"35. በተዋበ ዙፋን ላይ ሆነው የሚመለከቱ ሲሆኑ (ይስቃሉ)።"},{"id":36,"translation":"36. ከሓዲያን ይሰሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)::"}]},{"id":84,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ሰማይ በተቀደደች (በተሰነጠቀች) ጊዜ፤"},{"id":2,"translation":"2. የጌታዋንም ትዕዛዝ በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤"},{"id":3,"translation":"3. ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤"},{"id":4,"translation":"4. በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በሆነች ጊዜ፤"},{"id":5,"translation":"5. ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (ልትስማ) ተገባትም፤"},{"id":6,"translation":"6. አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን በሞት እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ። ተገናኚዉም ነህ።"},{"id":7,"translation":"7. ያ! መጽሐፉን በቀኝ እጅ የተሰጠውማ"},{"id":8,"translation":"8. በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል።"},{"id":9,"translation":"9. ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ሆኖ (በደስታ) ይመለሳል::"},{"id":10,"translation":"10. ያ ! መጽሐፉን በጀርባው በኩል የተሰጠው ግን"},{"id":11,"translation":"11. (ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል::"},{"id":12,"translation":"12. የተጋጋመች እሳትንም ይገባል::"},{"id":13,"translation":"13. እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፤"},{"id":14,"translation":"14. እርሱም ወደ አላህ እንደማይመለስ አሰበ።"},{"id":15,"translation":"15. አይደለም (ይመለሳል)፤ ጌታው በእርሱ (መመለስ) አዋቂ ነው።"},{"id":16,"translation":"16. ስለሆነም በወጋገኑ እምላለሁ።"},{"id":17,"translation":"17. በሌሊቱና በሰበሰበዉም ሁሉ፤"},{"id":18,"translation":"18. በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)።"},{"id":19,"translation":"19. ከአንድ እርከን ወደ ሌላ እርከን ትሸጋገራላችሁ።"},{"id":20,"translation":"20. የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው ( ምን ሆነው ነው)?"},{"id":21,"translation":"21. በእነርሱ ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱትስ ለእነርሱ ምን አላቸውና ነው?"},{"id":22,"translation":"22. በእርግጥ እነዚያ የካዱት ያስተባብላሉ።"},{"id":23,"translation":"23. አላህ በልቦቻቸው የሚቋጥሩትን ሁሉ አዋቂ ነው::"},{"id":24,"translation":"24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው።"},{"id":25,"translation":"25.እነዚያ በአላህ አምነው መልካም ተግባራትን የሰሩት ሲቀሩ፤ ለእነርሱማ የማይቋረጥ ምንዳ አላቸው።"}]},{"id":85,"verses":[{"id":1,"translation":"1. የህብረ ከዋክብት ባለቤት በሆነችው ሰማይ፤"},{"id":2,"translation":"2. በተቀጠረዉም ቀን፤"},{"id":3,"translation":"3. በመስካሪና በሚመሰከርበትም እምላለሁ::"},{"id":4,"translation":"4. የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ::"},{"id":5,"translation":"5. የባለማገዶዋ እሳት ባለቤቶች።"},{"id":6,"translation":"6. እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በሆኑ ጊዜ (ተረገሙ)።"},{"id":7,"translation":"7. እነርሱም በምዕመኖች ላይ ለሚሰሩት (ማሰቃየት) መስካሪዎች ናቸው።"},{"id":8,"translation":"8. ከእነርሱም በአሸናፊውና በምስጉኑ ጌታ ማመናቸውን እንጂ ሌላን ምንንም አልጠሉም::"},{"id":9,"translation":"9. ያ የሰማይና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነውን (ነው ያመኑበት)። አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው (አዋቂ ነው)።"},{"id":10,"translation":"10. እነዚያ አማኞችና ምዕመናትን ያሰቃዩና ከዚያ ያልተጸጸቱ ሁሉ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አለላቸው:: ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው::"},{"id":11,"translation":"11. እነዚያ በአላህ አምነው መልካም ስራዎችን የሰሩ ሁሉ ለእነርሱ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው:: ይህ ታላቅ ስኬት ነው::"},{"id":12,"translation":"12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ በኃይል መያዝ ብርቱ ነው።"},{"id":13,"translation":"13. እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም::"},{"id":14,"translation":"14. እርሱም ምህረቱ የበዛ ወዳድ ነው::"},{"id":15,"translation":"15. የላቀው የዙፋኑ ባለቤት ነው።"},{"id":16,"translation":"16. የሚሻውን ሁሉ ሰሪ (ፈፃሚ) ነው::"},{"id":17,"translation":"17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! የእነዚያ ነብያትን ያስተባበሉ) ሰራዊቶች ወሬ መጣልህን?"},{"id":18,"translation":"18. የፊርዓውንና የሰሙድ (ወሬ ደርሶሃልን)?"},{"id":19,"translation":"19. በእውነት እነዚያ (በአላህ) የካዱት (ሰዎች ሁሉ) እውነትን በማስተባበል ውስጥ ናቸው::"},{"id":20,"translation":"20. አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው::"},{"id":21,"translation":"21. ይልቁንም እርሱ የተከበረ ቁርኣን ነው::"},{"id":22,"translation":"22. የተጠበቀ በሆነ ሰሌዳ (ሎህ) ውስጥ ነው::"}]},{"id":86,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በሰማዩ እና ሌሊት በሚመጣውም እምላለሁ።"},{"id":2,"translation":"2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሌሊት መጪው ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?"},{"id":3,"translation":"3. ጨለማውን ሰንጣቂ ኮከብ ነው::"},{"id":4,"translation":"4. ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጂ ሌላ አይደለችም::"},{"id":5,"translation":"5. የሰው ልጅ ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፤"},{"id":6,"translation":"6. ከተስፈንጣሪ ውሃ (የዘር ፈሳሽ) ተፈጠረ::"},{"id":7,"translation":"7. ከጀርባና ከእርግብግቢቶች መካከል የሚወጣ ከሆነ የዘር ፈሳሽ ውሃ (ተፈጠረ)።"},{"id":8,"translation":"8. አላህ እርሱን በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው::"},{"id":9,"translation":"9. ሚስጥሮች በሚገለጹበት ቀን፤"},{"id":10,"translation":"10. (ለሰው) ምንም ኃይልና ረዳት አይኖረዉም::"},{"id":11,"translation":"11. የመመለስ ባለቤት (ዝናባማ) በሆነችው ሰማይ እምላለሁ::"},{"id":12,"translation":"12. (በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በሆነችው ምድርም እምላለሁ::"},{"id":13,"translation":"13. እርሱ (ቁርኣን)፤ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ (የአላህ) ቃል ነው።"},{"id":14,"translation":"14. እርሱም ቀልድ አይደለም።"},{"id":15,"translation":"15. እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ያሴራሉ (ይሸርባሉ)::"},{"id":16,"translation":"16. እኔ ተንኮልንም እመልሳለሁ (አመክናለሁ)::"},{"id":17,"translation":"17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያንን ቀን ሰጣቸው:: ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው (ታገሳቸው)::"}]},{"id":87,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያን ከሁሉ በላይ የሆነውን ጌታህን ስም አጥራ (አሞግስ)።"},{"id":2,"translation":"2. ያ ሁሉን ነገር የፈጠረውንና ያስተካከለውን፤"},{"id":3,"translation":"3. ያን የወሰነውን ነገርንም ሁሉ ለተፈጠረለት የመራውን፤"},{"id":4,"translation":"4. ያም ግጦሽን ለምለም አርጎ ያወጣውን፤"},{"id":5,"translation":"5.(ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡"},{"id":6,"translation":"6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፤"},{"id":7,"translation":"7. አላህ ከፈለገው ነገር በስተቀር፤ እናም እርሱ ግልጹንም የሚሸሽገውንም ሁሉ ያውቃልና፤"},{"id":8,"translation":"8. ለገሪቱም (ሕይወት እስላምን ትከተል ዘንድ) እናገራሃለን።"},{"id":9,"translation":"9. (ሰዎችንም) ገስፅ፤ ግሳፄይቱ ብትጠቅም።"},{"id":10,"translation":"10. (አላህን) የሚፈራ በእርግጥ ይገሰፃል።"},{"id":11,"translation":"11. መናጢዉም ይርቃታል::"},{"id":12,"translation":"12. ያ! ታላቂቱን እሳት የሚገባው፤"},{"id":13,"translation":"13. ከዚያም በእርሷ ውስጥ የማይሞትና ህያዉም የማይሆነው።"},{"id":14,"translation":"14. (አላህን ከማመፅ) የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፤"},{"id":15,"translation":"15. የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ::"},{"id":16,"translation":"16. ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ታስቀድማላችሁ፤"},{"id":17,"translation":"17. (ሰዎች ሆይ!) መጨረሻይቱ ሕይወት በላጭና፤ ዘወታሪ ሆና ሳለ።"},{"id":18,"translation":"18. ይህ በቀደምቶቹም መጻሕፍት ውስጥ ያለ ነው።"},{"id":19,"translation":"19. በኢብራሂምና በሙሳ መጽሐፍት ውስጥ የሰፈረ እውነታ ነው።"}]},{"id":88,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሸፋኝቱ ትንሳኤ ወሬ መጣልህን?"},{"id":2,"translation":"2. በዚያ ቀን የከሓዲያን ፊቶች ተዋራጆች ናቸው::"},{"id":3,"translation":"3. ሰሪዎች ለፊዎች ናቸው::"},{"id":4,"translation":"4. የምታቃጥልን እሳት ይገባሉ::"},{"id":5,"translation":"5. በጣም ከፈላች ምንጭም ይጋታሉ::"},{"id":6,"translation":"6. ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃማ) ዛፍ እንጂ ሌላ ምግብ የላቸዉም::"},{"id":7,"translation":"7. አካልን አያሰባ፤ ከረኃብም አያብቃቃ፤"},{"id":8,"translation":"8. (የአማንያን) ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው::"},{"id":9,"translation":"9. በስራቸውም ተደሳቾች ናቸው::"},{"id":10,"translation":"10. በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው::"},{"id":11,"translation":"11. በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም::"},{"id":12,"translation":"12. በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አሉ::"},{"id":13,"translation":"13. በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አሉ::"},{"id":14,"translation":"14. በተርታ የተኖሩ ኩባያዎችም፤"},{"id":15,"translation":"15. የተደረደሩ መከዳዎችም፤"},{"id":16,"translation":"16. የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አሉ)::"},{"id":17,"translation":"17. (ከሓዲያን) ግመል እንዴት እንደተፈጠረች አይመለከቱምን?"},{"id":18,"translation":"18. ሰማይም እንዴት ከፍ እንደተደረገች!"},{"id":19,"translation":"19. ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ!"},{"id":20,"translation":"20. ምድርም እንዴት እንደተዘረጋች አይመለከቱምን?!"},{"id":21,"translation":"21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስታውስም:: አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና::"},{"id":22,"translation":"22. በእነርሱ ላይ አስገዳጅ (ተሿሚ) አይደለህም፤"},{"id":23,"translation":"23. ግን ከእውነት የዞረና የካደ፤"},{"id":24,"translation":"24. አላህም ከባዱን ቅጣት ይቀጣዋል።"},{"id":25,"translation":"25. መመለሻቸው ወደ እኛ ብቻ ነው::"},{"id":26,"translation":"26. ምርመራቸዉም በእኛ ላይ ብቻ ነው::"}]},{"id":89,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በጎህ፤ እምላለሁ"},{"id":2,"translation":"2. በአስሩ ሌሊቶችም፤"},{"id":3,"translation":"3. በጥንዱም በነጠላዉም፤"},{"id":4,"translation":"4. በሌሊቱም በሚጓዝበት ጊዜ እምላለሁ።"},{"id":5,"translation":"5. በዚህ መሀላ ለባለ አእምሮ ታላቅ መሀላ የለበትምን?"},{"id":6,"translation":"6. ጌታህ በዓድ ህዝቦች ላይ እንዴት እንደሰራ አላወክምን?"},{"id":7,"translation":"7. በባለ ረዣዥሚቱ አዕማድ ኢረም ላይም፤"},{"id":8,"translation":"8. በዚያች ብጤዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ በሆነችው፤"},{"id":9,"translation":"9. በእነዚያ (በሸለቆዎች) ቋጥኝን የቦረቦሩ በሆኑት ሰሙድም፤"},{"id":10,"translation":"10. ባለ ችካሎች በሆነው ፈርዖንም፤"},{"id":11,"translation":"11. በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሰሩ (በሆኑትም ላይ)፤"},{"id":12,"translation":"12. በእርሷም ውስጥ ጥፋትን ያበዙ በሆኑት (እንዴት እንደሰራ አታውቅምን?)"},{"id":13,"translation":"13. በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸው::"},{"id":14,"translation":"14. ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና::"},{"id":15,"translation":"15. የሰው ልጅ ጌታው በሞከረው ጊዜ ባከበረውና ባጣቀመው ጊዜ ጌታየ አከበረኝ (አበለጠኝ) ይላል::"},{"id":16,"translation":"16. በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበበት (ጊዜ) እንዲሁ ጌታየ አሳነሰኝ ይላል::"},{"id":17,"translation":"17. በፍፁም! ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፤"},{"id":18,"translation":"18. ድሃንም በማብላት ላይ አትበረታቱም፤"},{"id":19,"translation":"19. የውርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል (ያለአግባብ) ትበላላችሁ፤"},{"id":20,"translation":"20. ገንዘብንም አብዝታችሁ (አለቅጥ) ትወዳላችሁ፤"},{"id":21,"translation":"21. (ሰዎች ሆይ! ተዉ):: ታቀቡ:: ምድር ደጋግማ በተንኮታኮተች ጊዜ፤"},{"id":22,"translation":"22. ጌታህ በመጣና መላዕክትም በሰልፍ በሰልፍ ሆነው በመጡ ጊዜ፤"},{"id":23,"translation":"23. ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው ሁሉ ጥፋቱን በትክክል ይገነዘባል። መገንዘቡ በየት በኩል (ይጥቀመው)?"},{"id":24,"translation":"24. \"ወይ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ስራ) ባስቀደምኩ ኖሮ\" ይላል።"},{"id":25,"translation":"25. በዚያ ቀንም የእርሱን አቀጣጥ የመሰለ አንድም አካል አይቀጣም።"},{"id":26,"translation":"26. የእርሱንም፤አሰተሳሰር አንድም አካል አያስርም::"},{"id":27,"translation":"27. (ለአመነች ነፍስም እንዲህ ትባላለች)፡- አንቺ በአላህ የረካሺው ነፍስ ሆይ!"},{"id":28,"translation":"28. (ከእርሱም) የወደድሽ፤ (እርሱ ዘንድም) የተወደደሽ ሆነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ::"},{"id":29,"translation":"29. ከዉድ ባሮቼም ጋር ተቀላቀይ::"},{"id":30,"translation":"30. ወደ ገነቴም ግቢ ትባላለች::"}]},{"id":90,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በዚህ ሀገር (በመካ) እምላለሁ"},{"id":2,"translation":"2.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትሆን።"},{"id":3,"translation":"3.በወላጂና በወለዳቸውም (በአደምና በዘሮቹ) ሁሉ (እምላለሁ)።"},{"id":4,"translation":"4. ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ሆኖ ፈጠርነው::"},{"id":5,"translation":"5. በእርሱ ላይ አንድም አካል የማይችል መሆኑን ይጠረጥራልን?"},{"id":6,"translation":"6. \"ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ\" ይላል፤"},{"id":7,"translation":"7. አንድም ያላየው መሆኑን ያስባልን?"},{"id":8,"translation":"8. ለእርሱ ሁለት አይኖችን አላደረግንለትንምን?"},{"id":9,"translation":"9. አንድ ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፤"},{"id":10,"translation":"10.ሁለትን መንገዶችስ አልመራነዉምን?"},{"id":11,"translation":"11.ዐቀበቱን አልወጣም።"},{"id":12,"translation":"12.ዐቀበቱን መውጣት ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?"},{"id":13,"translation":"13.ያ ጫንቃን መልቀቅ ነው። {1}","footnotes":"{1} ባሪያን ነጻ ማውጣት ማለት ነው"},{"id":14,"translation":"14. ወይም የረሀብ ባለቤት በሆነ ቀን (ረሀብተኛን) ማብላት፤"},{"id":15,"translation":"15. የዝምድና ባለቤት የሆነን የቲም፤"},{"id":16,"translation":"16.ወይም የአፈር ባለቤት የሆነን (ችግረኛ) ማብላት ነው።"},{"id":17,"translation":"17.ከዚያም ከእነዚያ በአላህ ካመኑትና በመታገስ ላይ አደራ ከተባባሉት ሰዎች ጋር መሆን ነው።"},{"id":18,"translation":"18. እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው።"},{"id":19,"translation":"19. እነዚያ በአናቅጻችን የካዱ ሁሉ እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው።"},{"id":20,"translation":"20. ለእነርሱ የምትዘጋባቸው እሳትም አለች።"}]},{"id":91,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በጸሐይና በብርሀኗ፤ (እምላለሁ)"},{"id":2,"translation":"2. በጨረቃም ጸሐይን በተከተላት ጊዜ፤"},{"id":3,"translation":"3. በቀንም ጸሐይን በገለፃት ጊዜ፤"},{"id":4,"translation":"4. በሌሊቱም ጸሐይን በሸፈናት ጊዜ፤"},{"id":5,"translation":"5. በሰማይ እና በገነባትም፤"},{"id":6,"translation":"6. በምድር እና በዘረጋትም፤"},{"id":7,"translation":"7. በነፍስም ባስተካከላትም"},{"id":8,"translation":"8. አመጽዋንና ፍርሃቷንም ባሳወቃት (አምላክም በአላህ እምላለሁ)።"},{"id":9,"translation":"9. (ነፍስን) ከኃጢአት ያጠራ ሰው ሁሉ በእርግጥ ተሳካለት።"},{"id":10,"translation":"10. በኃጢአትም የሸፈናት ሰው ሁሉ በእውነት አፈረ (ከሰረ)::"},{"id":11,"translation":"11. ሰሙድ ወሰን በማለፍዋ ምክንያት አስተባበለች፤"},{"id":12,"translation":"12. ጠማማዋ በተነሳ ጊዜ።"},{"id":13,"translation":"13. ለእነርሱም የአላህ መልዕክተኛ (ሷሊህ)፡-የአላህን ግመልና የመጠጥ ተራዋን (ጠብቁላት) አላቸው::"},{"id":14,"translation":"14. እነርሱ አስተባበሉትም፤ ከዚያ ወጓት፤ በኃጢአታቸዉም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም::"},{"id":15,"translation":"15. (የምታስተካክለውን) ፍፃሜዋንም አይፈራም።"}]},{"id":92,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በሌሊቱ (ጨለማውን) በሚሸፍነው ጊዜ፤ (እምላለሁ)"},{"id":2,"translation":"2. በቀኑም በተገለጸ ጊዜ፤"},{"id":3,"translation":"3. ወንድንና ሴትን በፈጠረዉም (አምላክ) እምላለሁ::"},{"id":4,"translation":"4. ስራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው።"},{"id":5,"translation":"5. ያ! የሰጠና ጌታውንም የፈራማ፤"},{"id":6,"translation":"6. በመልካሚቱ እምነትም ያረጋገጠ ሰው"},{"id":7,"translation":"7. ለገሪቱ እናገራዋለን።"},{"id":8,"translation":"8. ያ! የሰሰተ በራሱም የተብቃቃ፤"},{"id":9,"translation":"9. በመልካሚቱም ያስተባበለውማ"},{"id":10,"translation":"10. ለክፋት እናዘጋጀዋለን።"},{"id":11,"translation":"11. ገሀነም በወደቀ ጊዜ ያ! ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመዉም።"},{"id":12,"translation":"12. ቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን።"},{"id":13,"translation":"13. መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛው ነው።"},{"id":14,"translation":"14. የምትንቀለቀል እሳት አስጠነቀቅኳችሁ።"},{"id":15,"translation":"15. ከጠማማ በስተቀር የማይገባባትን"},{"id":16,"translation":"16. ያ ያስተባበለና ከትዕዛዝም የሸሸ እድለ ቢስ (ነው የሚገባባት)።"},{"id":17,"translation":"17. አላህን በጣም ፈሪ የሆነ በእርግጥ ይርቃታል::"},{"id":18,"translation":"18. ያ (ከወንጀል) የሚጥራራ ሲሆን ገንዘቡን የሚለግስ፤"},{"id":19,"translation":"19. ለአንድም ሰው በእርሱ ዘንድ ተመላሽ የሚሆን ውለታ ሳይኖርበት።"},{"id":20,"translation":"20. የታላቁን ጌታውን የአላህን ውዴታ በመፈለግ ብቻ (ይህንን የሰራ) ሲቀር።"},{"id":21,"translation":"21. እርሱማ ወደ ፊት (በሚሰጠው) በእርግጥ ይደሰታል።"}]},{"id":93,"verses":[{"id":1,"translation":"በረፋዱም፤ (እምላለሁ)"},{"id":2,"translation":"2. በሌሊትም ጸጥ ባለ ጊዜ እምላለሁ::"},{"id":3,"translation":"3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም::"},{"id":4,"translation":"የመጨረሻይቱ ዓለም ከመጀመሪያይቱም ይልቅ ላንተ በላጭ ናት::"},{"id":5,"translation":"ጌታህም ወደ ፊት ብዙ ስጦታ በእርግጥ ይሰጥሃል። ትደሰታለህም።"},{"id":6,"translation":"6. የቲም ሆነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)::"},{"id":7,"translation":"7. የሳትክም ሆነህ አገኘህና መራህ::"},{"id":8,"translation":"8. ደሃም ሆነህ አገኘህና አከበረህ::"},{"id":9,"translation":"9. እናም የቲምን አትጨቁን::"},{"id":10,"translation":"10. ለማኝንም አትገላምጥ::"},{"id":11,"translation":"11. የጌታህንም ጸጋ ግለጽ::"}]},{"id":94,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልብህን ላንተ አላሰፋንልህም?"},{"id":2,"translation":"2. ሸክምህንም አወረድንልህ?"},{"id":3,"translation":"3. ያንን ጀርባህን ያከበደውን (ሸክም)"},{"id":4,"translation":"4. መወሳትህንም ከፍ አላደረግንልህ?"},{"id":5,"translation":"5. እናም ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አለ::"},{"id":6,"translation":"6. ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አለ::"},{"id":7,"translation":"7. (የጀመርከውን ጥሩ ስራ) በጨረስክ ጊዜ ወደ ሌላ ጥሩ ስራ ቀጥል (አስከትል)።"},{"id":8,"translation":"8. ክጃሎትህንም ወደ ጌታህ ብቻ አድርግ።"}]},{"id":95,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በበለስና፤ በወይራ ዛፍ እምላለሁ፣"},{"id":2,"translation":"2. በሲና ተራራም፤"},{"id":3,"translation":"3. በዚህ በጸጥተኛው (ጸጥታ በነገሰበት) አገር መካም እምላለሁ።"},{"id":4,"translation":"4. በርግጥ ሰውን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነው::"},{"id":5,"translation":"5. ከዚያም (ከፊሉን) ከበታቾች ሁሉ በታች አድርገን መለስነው::"},{"id":6,"translation":"6. እነዚያ በአላህ ያመኑትና መልካም ተግባራት የሰሩት ሲቀሩ ለእነርሱማ የማይቋረጥ\nምንዳ አለላቸው::"},{"id":7,"translation":"7. (የሰው ልጅ ሆይ) ታዲያ ከዚህ (እውነታ) በኋላ በፍርዱ ምን አስተባባይ አደረገህ?"},{"id":8,"translation":"8. አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን?"}]},{"id":96,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚያ (ሁሉንም ነገር) በፈጠረ ጌታህ ስም (ጀምርና) አንብብ! {1}","footnotes":"{1} ይህ አንቀጽና ቀጥሎ ያሉት ከቁርአን መጀመሪያ የወረዱ አንቀጾች ናቸው። በኑር ተራራ ላይ በምገኘው የሂራእ ዋሻ ውስጥ ነቢዩ ሰ/ዐ/ወ/ ኸልዋ ወጥተው እያሉ ነው የወረደባቸው። (ቡኻሪና ሙስሊም፤ የወህይ አጀማመር ምእራፍ)"},{"id":2,"translation":"2. ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)::"},{"id":3,"translation":"3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንብብ! ጌታህም በጣም ቸር ነው::"},{"id":4,"translation":"4. ያ በብዕር ያስተማረ (ጌታ)፤"},{"id":5,"translation":"5. የሰውን ልጅ ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ (ጌታ)::"},{"id":6,"translation":"6. በእውነቱ የሰው ልጅ ወሰንን ያልፋል::"},{"id":7,"translation":"7. ራሱን የተብቃቃ ሆኖ በማየቱ ምክንያት"},{"id":8,"translation":"8. መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው::"},{"id":9,"translation":"9. ያንን የሚከለክለውን አየህን?"},{"id":10,"translation":"10. ባሪያን በሰገደ ጊዜ (የሚከለክለውን):"},{"id":11,"translation":"11. እስቲ ንገረኝ (ተከልካዩ ባሪያየ) በትክክል መንገድ ላይ ቢሆን፤"},{"id":12,"translation":"12. ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ ምን እንደሚሆን አየህን?"},{"id":13,"translation":"13. እስቲ ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና ከእምነት ቢሸሽ፤"},{"id":14,"translation":"14. አላህ የሚያይ መሆኑን አያውቅምን?"},{"id":15,"translation":"15. ይታቀብ፤ የማይከለከል ከሆነ አናቱን ይዘን አንጎትተዋለን::"},{"id":16,"translation":"16. ያቺን ውሸታምና ስህተተኛ የሆነችውን አናቱን::"},{"id":17,"translation":"17. ሸንጎውንም ይጥራ፤"},{"id":18,"translation":"18. እኛም ዘበኞቻችንን እንጠራለን::"},{"id":19,"translation":"19. በጭራሽ፤ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህን ለሚል ከሓዲ አትታዘዘው፤ ስገድ፤ ወደ አላህም ተቃረብ። {1}","footnotes":"{1} እዚህ የንባብ ሱጁድ አለ። ይህ የመጨረሻ ሱጁድ ነው።"}]},{"id":97,"verses":[{"id":1,"translation":"1. እኛ (ቁርኣንን) በመወሰኛይቱ ሌሊት ውስጥ አወረድነው።"},{"id":2,"translation":"2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመወሰኛይቱ ሌሊት ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?"},{"id":3,"translation":"3. የመወሰኛይቱ ሌሊት ከሺህ ወር የምትበልጥ ነች።"},{"id":4,"translation":"4. በእርሷ ውስጥ መላዕክትና ሩሕም (ጂብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በሁሉም ጉዳዮች ይዘው ይወርዳሉ።"},{"id":5,"translation":"5. እርሷም ጎህ እስኪወጣ ድረስ ሰላም ነች።"}]},{"id":98,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ከመጽሐፍ ባለቤቶችና ከአጋሪዎች እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች ግልጽ አስረጂ እስኪመጣላቸው ድረስ (ከነበሩበት አቋም) ተወጋጆች አልነበሩም::"},{"id":2,"translation":"2. (አስረጂውም) የተጥራሩ (መጽሐፎችን) የሚያነብ ከአላህ የሆነ መልዕክተኛ ነው።"},{"id":3,"translation":"3. በውስጧም ቀጥተኛ የሆኑ ጹሁፎች ያሉባት የሆነችን (አስረጂ)፤"},{"id":4,"translation":"4. እነዚያ መጽሐፉን የተሰጡ ሰዎችም ግልጽ አስረጂ ከመጣላቸው በኋላ እንጂ አልተለያዩም::"},{"id":5,"translation":"5. ሃይማኖትን ለአላህ ብቻ አጥሪዎችና ቀጥተኞች ሆነው አላህን ሊገዙት፤ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ፤ ዘካንም በትክክል ሊሰጡ እንጂ ያልታዘዙ ሲሆን ተለያዩ:: የቀጥተኛይቱ ሃይማኖት ድንጋጌም ይሀው ነው።"},{"id":6,"translation":"6. ከመጽሐፉ ባለቤቶችና ከአጋሪዎች እነዚያ የካዱት በውስጧ ዘውታሪዎች በሚሆኑባት የገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው:: እነዚያ ከፍጥረቱ ሁሉ መጥፎዎቹ እነርሱ ናቸው::"},{"id":7,"translation":"7. እነዚያ በትክክል አምነው በጎ ተግባራትንም የሰሩት እነዚያ ከፍጥረት ሁሉ በላጭ (ምርጦች) የሆኑት እነርሱ ናቸው።"},{"id":8,"translation":"8. ምንዳቸውም በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ከጌታቸው ዘንድ የሚቸሯቸው የመኖሪያ ገነቶች ናቸው። በውስጣቸው ለዘልዓለም ዘወታሪዎች ሲሆኑ ይገቡባቸዋል:: አላህ ከእነርሱ ስራቸውን ወደደላቸው:: እነርሱም ከእርሱ ምንዳውን ወደዱ:: ይህ እድል ጌታውን ለፈራ ሁሉ ነው::"}]},{"id":99,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምድር በኃይል መንቀጥቀጧን በተንቀጠቀች ጊዜ፤"},{"id":2,"translation":"2. ምድርም ሸክሞቿን ባወጣች ጊዜ፤"},{"id":3,"translation":"3. ሰዉም \"ምን ሆነች?\" ባለ ጊዜ፤"},{"id":4,"translation":"4. በዚያ ቀን ወሬዎቿን ትናገራለች::"},{"id":5,"translation":"5. ጌታህ ለእርሷ አሳውቋታልና፤"},{"id":6,"translation":"6. በዚያ ቀን ሰዎች ሁሉ ስራዎቻቸውን እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ እንደየስራቸው የተበታተኑ ሆነው ከየመቃብራቸው ወደ መቆሚያው ስፍራ ይመለሳሉ::"},{"id":7,"translation":"7. የብናኝን ክብደት ያህል መልካም የሰራ ሰው ያገኘዋል::"},{"id":8,"translation":"8. የብናኝን ክብደት ያህል ክፋት የሰራ ሰውም ያገኘዋል::"}]},{"id":100,"verses":[{"id":1,"translation":"1. እያለከለኩ ሩዋጮች በሆኑ (ፈረሶች)፤"},{"id":2,"translation":"2. ምድርን በሸሆናቸው እያጋጩ የእሳት ብልጭታን አውጪዎች በሆኑትም (ፈረሶች)፤"},{"id":3,"translation":"3. በማለዳ (በጧት) ወራሪዎች በሆኑትም ፈረሶች፤"},{"id":4,"translation":"4. በእርሱም አቧራን በቀሰቀሱት፤"},{"id":5,"translation":"5.በፈረሰኞቻቸው በኩል (የጠላት) ስብስብ መሀልን በተጋፈጡትም (ፈረሶች) እምላለሁ።"},{"id":6,"translation":"6. የሰው ልጅ ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው::"},{"id":7,"translation":"7. እርሱም በዚያ ክህደቱ ላይ መስካሪ ነው::"},{"id":8,"translation":"8. እርሱም ገንዘብን በመውደድ ላይ በጣም ብርቱ ነው::"},{"id":9,"translation":"9. የሰው ልጅ በመቃብሮች ዉስጥ ያሉት ሙታን ሁሉ በተቀሰቀሱ ጊዜ ምን እንደሚከሰት አያውቅምን?"},{"id":10,"translation":"10. በልቦች ውስጥ ያለዉም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ እንዴት እንደሚሆን አያውቅምን?"},{"id":11,"translation":"11. ጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ ነገር በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው::"}]},{"id":101,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤"},{"id":2,"translation":"2. ቆርቋሪይቱ (ጩኸት) ምንድን ናት!"},{"id":3,"translation":"3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቆርቋሪይቱ ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?"},{"id":4,"translation":"4. ሰዎች እንደተበታተነ ቢራቢሮ (ኩብኩባ) የሚሆኑበት ቀን፤"},{"id":5,"translation":"5. ጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ የሚሆኑበት (አስደንጋጭ ቀን) ናት።"},{"id":6,"translation":"6. በዚያ ዕለት ያ ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ"},{"id":7,"translation":"7. እርሱ ኑሮው በአሰደሳቿ ጀነት ውስጥ ይሆናል።"},{"id":8,"translation":"8. ያ ሚዛኖቹ የቀለሉበት ሰው ደግሞ"},{"id":9,"translation":"9. መኖሪያው ሃዊያህ (የምትባል የገሀነም እሳት) ናት።"},{"id":10,"translation":"10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሷ ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?"},{"id":11,"translation":"11. (እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት::"}]},{"id":102,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (በዚህች ዓለም ጸጋዎች) ብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘናጋችሁ::"},{"id":2,"translation":"2. መቃብሮችን እስከጎበኛችሁ ድረስ:: (በዚሁ ላይ ቀጠላችሁ)።"},{"id":3,"translation":"3. ከዚህ ተግባራችሁ ተከልከሉ (ታቀቡ):: ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ፤"},{"id":4,"translation":"4. ከዚያም ከዚህ ተግባራችሁ ተከልከሉ። ወደ ፊትም ታውቃላችሁ፤"},{"id":5,"translation":"5. በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) በእርግጠኝነት ብታውቁ ኖሮ (ይህን ያክል ባልተዘናጋችሁ ነበር)።"},{"id":6,"translation":"6. ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ::"},{"id":7,"translation":"7. ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ፤"},{"id":8,"translation":"8. ከዚያም በድሎታችሁ ጉዳይ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃለችሁ::"}]},{"id":103,"verses":[{"id":1,"translation":"1. በጊዜ እምላለሁ፤"},{"id":2,"translation":"2. ሰው ሁሉ በእርግጥ በኪሳራ ውስጥ ነው::"},{"id":3,"translation":"3. እነዚያ በአላህ በትክክል ያመኑትና መልካሞችን የሰሩ፤ በእውነትም ላይ አደራ የተባባሉ፤ በመታገስም ላይ አደራ የተባባሉ ብቻ ሲቀሩ::"}]},{"id":104,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ለሐሜተኛ፤ ለዘላፊ፤ (ለአሽሟጣጭ ሁሉ) ወዮለት::"},{"id":2,"translation":"2. ለዚያ ገንዘብን የሰበሰበና የቆጣጠረው (ያደለበዉም) ለሆነ ሁሉ፡፡"},{"id":3,"translation":"3. ገንዘቡ በዚህች ዓለም ዘውታሪ እንደሚያደርገው ያስባል።"},{"id":4,"translation":"4. በጭራሽ፤ አውዳሚና የምትፈጭ በሆነችው እሳት ውስጥ በእርግጥ ይጣላል።"},{"id":5,"translation":"5. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምትፈጨዋም ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?"},{"id":6,"translation":"6. የተቀጣጠለችው የአላህ እሳት ናት::"},{"id":7,"translation":"7. ያቺ በልቦች ላይ እንኳን ሳይቀር የምትዘልቅ የሆነች::"},{"id":8,"translation":"8. እርሷ በእርግጥ በእነርሱ ላይ የተዘጋች ናት::"},{"id":9,"translation":"9. በተዘረጋች አዕማድ ውስጥ የተዘጋች ናት::"}]},{"id":105,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ አላህ በዝሆኑ ባለቤቶች ላይ እንዴት እንደሰራ አላወቅክምን?"},{"id":2,"translation":"2. ተንኮላቸውን በጥፋት ውስጥ ከንቱ አላደረገምን?"},{"id":3,"translation":"3. በእነርሱ ላይ መንጎች የሆኑን ወፎችንም ላከ።"},{"id":4,"translation":"4. ከተጠበሰ ጭቃ የሆነን ጠጠር የምትወረውርባቸውን የሆነችን (አእዋፍ)"},{"id":5,"translation":"5. እና ቅጠሉ እንደ ተበላ አዝመራ አደረጋቸው"}]},{"id":106,"verses":[{"id":1,"translation":"1. ቁረይሽን ለማላመድ (ባለ ዝሆኖቹን አጠፋ)::"},{"id":2,"translation":"2. የክረምትንና የበጋን ወራት ጉዞዎች ሊያላምዳቸው ይህንን ሰራ፤"},{"id":3,"translation":"3. ስለዚህም የዚህን ቤት (የካዕባን) ጌታ ብቻ ያምልኩ::"},{"id":4,"translation":"4. ያንን ከርኃብ ያበላቸውን፤ ከፍርሃትም ያዳናቸውን (ጌታ ብቻ ያምልኩ)::"}]},{"id":107,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን በምርመራው ቀን የሚያስተባብለውን ሰው አየህን? (አወከውን?)"},{"id":2,"translation":"2. ይሀውም ያ የቲምን በኃይል የሚገፈትረው፤"},{"id":3,"translation":"3. ድሃን በማብላት ላይም የማያነሳሳው ነው።"},{"id":4,"translation":"4. ወዮላቸው ለሰጋጆች፤"},{"id":5,"translation":"5. ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለሆኑት (ሰጋጆች)፤"},{"id":6,"translation":"6. ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለሆኑት፤"},{"id":7,"translation":"7. የዕቃ ትውስትንም ሰዎችን የሚከለክሉ ለሆኑት ሁሉ ወዮላቸው::"}]},{"id":108,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ በጣም ብዙ በጎ ነገሮችን ሰጠንህ።"},{"id":2,"translation":"2. ስለዚህ ለጌታህ ብቻ ስገድ:: በስሙም ብቻ ሰዋ።"},{"id":3,"translation":"3. የሚጠላህ ሁሉ እርሱ በእርግጥ ዘሩ የተቆረጠው ነው።"}]},{"id":109,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)- (ለካሓዲያን እንዲህ) በላቸው፡- እናንተ ከሓዲያን ሆይ!"},{"id":2,"translation":"2.ያንን የምትገዙትን (ጣዖት አሁን) አልገዛም::"},{"id":3,"translation":"3.እናንተም እኔ የምገዛውን (አምላክ አሁን) ተገዢዎች አይደላችሁም::"},{"id":4,"translation":"4. እኔም ያንን የተገዛችሁትን (ወደ ፊት) ተገዢ አይደለሁም::"},{"id":5,"translation":"5. እናንተም እኔ የምገዛውን (ወደ ፊት) ተገዢዎች አይደላችሁም::"},{"id":6,"translation":"6. እናንተ የራሳችሁ ሃይማኖት አላችሁ:: እኔም የራሴ ሃይማኖት አለኝ -በላቸው::"}]},{"id":110,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የአላህ እርዳታና (የመካ) መከፈት በመጣ ጊዜ፤"},{"id":2,"translation":"2. ሰዎችም ቡድን ቡድን እየሆኑ ወደ አላህ ሃይማኖት ሲገቡ ባየህ ጊዜ፤"},{"id":3,"translation":"3. ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው። ምህረትንም ለምነው፤ እርሱ ጸጸትን በጣም ተቀባይ ነውና።"}]},{"id":111,"verses":[{"id":1,"translation":"1. የአቡ ለሀብ ሁለት እጆች ከሰሩ፤ (ጠፉ)፤ እርሱም ጠፋ።"},{"id":2,"translation":"2.ገንዘቡም ያም ያፈራው ሁሉ ምንም አልጠቀመዉም"},{"id":3,"translation":"3.የመንቀልቀል ባለቤት የሆነችን እሳት በእርግጥ ይገባል::"},{"id":4,"translation":"4.ሚስቱም ትገባለች፤ እንጨት ተሸካሚዋ።"},{"id":5,"translation":"5.በአንገቷ ላይ የጭረት ገመድ ያለባት ስትሆን ትገባለች::"}]},{"id":112,"verses":[{"id":1,"translation":"1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በል፡ -እርሱ አላህ አንድ ብቻ ነው::"},{"id":2,"translation":"2.አላህ የሁሉ ነገር መጠጊያ ነው::"},{"id":3,"translation":"3.አልወለደም፤ አልተወለደምም::"},{"id":4,"translation":"4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለዉም።"}]},{"id":113,"verses":[{"id":1,"translation":"1.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በል፡ -በተፈልቃቂው ጎህ (በአል-ፈለቅ) ጌታ እጠበቃለሁ፤-"},{"id":2,"translation":"2.ከፈጠረው ፍጡር ሁሉ ክፋት::"},{"id":3,"translation":"3.ከሌሊትም ክፋት በጨለመ ጊዜ፤"},{"id":4,"translation":"4. በቋጠሮዎች ላይ ተፊዎች ከሆኑት ደጋሚ ሴቶችም ክፋት፤"},{"id":5,"translation":"5. ከምቀኛም ክፋት፤ በተመቀኘ ጊዜ (በአሏህ) -እጠበቃለሁ- በል::"}]},{"id":114,"verses":[{"id":1,"translation":"1.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በል፡ -የሰዎች ሁሉ ፈጣሪ በሆነው ጌታ እጠበቃለሁ፤"},{"id":2,"translation":"2.የሰዎች ሁሉ ንጉስ በሆነው ጌታ፤"},{"id":3,"translation":"3.የሰዎች ሁሉ አምላክ በሆነው ጌታ፤"},{"id":4,"translation":"4. ከዚያ ብቅ እልም ባይ ከሆነው ጎትጓች ክፋት፤"},{"id":5,"translation":"5. ከዚያ በሰዎች ልቦች ውስጥ የሚጎተጉት ከሆነው፤"},{"id":6,"translation":"6. ከጂንም ይሁን ከሰው ሰይጣን ክፋት (እጠበቃለሁ)።"}]}]
